Telegram Web Link
ዶክተር በሀይሉ ሀይሉ ግድያ ተፈፀመባቸው።

ዶክተር ሀይሉ የሀገራችን ስመጥር የሰርጀሪ ህክምና ባለሙያ ነበሩ።ባሳለፍነው እሁድ ጠዋት አዲስ አበባ ውስጥ የጠዋት ሩጫ በማድረግ ላይ ሳሉ ግድያ እንደተፈፀመባቸው ኤሊያስ መሰረት በገፁ አስፍሯል።

እስካሁን ስለግድያው ፖሊስ የሰጠው ማብራሪያ የለም።

@ethio_mereja_news
ጠ/ሚ ዐቢይ ለእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አመራሮችና ከተለያዩ ክልሎች ከተወጣጡ አባቶች የኢፍጣር ዝግጅት አደረጉ

መጋቢት 10/2016 (አዲስ ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ ማምሻውን ለእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አመራሮች እና ከተለያዩ ክልሎች ከተወጣጡ አባቶች የኢፍጣር ዝግጅት ማድረጋቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ ከሰዓት በኋላ ከአባቶቹ ጋር ውይይት ማድረጋቸው ይታወቃል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ጌታቸው ረዳ‼️

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር ጌታቸው ረዳ፣ የኤርትራ ወታደሮች ትግራይ ውስጥ የፈጸሟቸውን ወንጀሎች ለመዳኘት አገራዊ የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ ማዕቀፍ በቂ አይደለም በማለት ስጋታቸውን ገልጠዋል።

ጌታቸው ይህንኑ ስጋታቸውን የገለጡት፣ ከተመድ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የምሥራቅ አፍሪካ ሃላፊ ማርሴል ክሊመንት ጋር መቀሌ ውስጥ በተወያዩበት ወቅት እንደኾነ የክልሉ ቴሌቪዥን ዘግቧል።

ክሊመንት በበኩላቸው፣ በጦርነቱ ወቅት የተፈጸሙ ወንጀሎችን የማየቱ ሂደት ተጎጂዎችን ማዕከል ያደረገ መኾን እንዳለበት መናገራቸውን ዘገባው አመልክቷል።

በርካታ አገር በቀል ሲቪል ማኅበራትም፣ በረቂቅ ደረጃ ላይ የሚገኘው የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ ማዕቀፍ የኤርትራ ወታደሮች በጦርነቱ ወቅት የፈጸሟቸውን ወንጀሎች ጭምር እንዲያካትትና የኤርትራ ወታደሮችን ወንጀሎች የሚመለከት ልዩ ፍርድ ቤት እንዲቋቋም የሚጠይቅ የምክረ ሃሳብ ሰነድ በቅርቡ ለፍትህ ሚንስቴር ማስገባታቸው ይታወሳል።

@sheger_press
Audio
#ለጥንቃቄ⚠️

እንዲህ ካሉ አጭበርባሪዎች ተጠንቀቁ።

ከላይ የምትሰሙት የድምፅ ቅጂ ከአንድ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል የተላከ ነው።

አጭበርባሪው ደዋይ ግለሰብ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ #ዋናው_ቢሮ እንደደወለ በማስመሰል በኦንላይን ዘረፋ ለመፈፀም ሞክሯል።

የደወለው #የባንክ_ሰራተኛ ጋር መሆኑን አላወቀም ነበር።

ሰራተኛው ግለሰቡ የሚለፈልፈውን ሁሉ እስከ መጨረሻ ድረስ አዳመጠው።

በኃላም የአንድ የባንኩን ቅርንጫፍ ዋና ስራ አስኪያጅ ስምን ይጠይቀዋል።

በዚህ ግዜ ከዋናው መ/ቤት ነኝ ያለው አጭበርባሪ ምን ይዋጠው ? መቀባጠር ይጀምራል።

በመጨረሻ ውርደቱን ተከናንቦ ስልኩን ዘግቷል።

እንዲህ ያሉ የማጭበርበር ስልቶች አንድ ሰሞን እንደጉድ ተበራክተው ነበር። አሁን ደግሞ ሰሞነኛውን የንግድ ባንክን ሁኔታ ተከትሎ እንደ አዲስ ተስፋፍተዋል።

ውድ ቤተሰቦቻችን ፦
* የማታውቋቸው የግል ስልኮችን ባለማንሳት ፣
* #የሚስጥር_ቁጥሮችን ባለመስጠት እራሳችሁን ከአጭበርባሪዎች ጠብቁ። የሚመለከታቸው አካላትም ይህን ነገር እንደ ቀላል ከማየት የማጭበርበር ስራ ላይ የተሰማሩ ሰዎች #በደወሉበት_ስልክ ክትትል በማድረግ ወደ ህግ ማቀረብ አለባቸው።

(የድምፅ ቅጂውን ለላከው የቤተሰባችን አባል ምስጋና እናቀርባለን)

(tikvahethiopia)

@sheger_press
@sheger_press
የጸጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል፣ በአዲስ አበባ እንዲኹም በከተማዋና ኦሮሚያ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች ኹከትና ብጥብጥ ሊፈጥሩ በቡድን ሲንቀሳቀሱ ነበሩ ያላቸውን 50 ግለሰቦችን በቁጥጥር ሥር ማዋሉን ትናንት ምሽት አስታውቋል።

ግብረ ኃይሉ፣ ቡድኑ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያናትን ለመደበቂያነት ሲጠቀም ነበር ብሏል።

ግብረ ኃይሉ፣ ቡድኑ እስክንድር ነጋ ከሚመራው ፋኖ ታጣቂ ኃይል እና በሽብር ወንጀል ተከሰው በእስር ላይ ከሚገኙት ወንደወሰን አሠፋ ጋር ግንኙነት እንደነበረው ገልጧል።

ከአገር ውጭ ደሞ፣ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ፣ ሐብታሙ አያሌው እና መሳይ መኮንን የሥውር ቡድኑ አስተባባሪዎች እንደኾኑ ግብረ ኃይሉ ጠቅሷል። ከቡድኑ ጋር ተተኳሽ መሳሪያዎች፣ ቦምቦችና ተቀጣጣይ ፈንጂዎች ተይዘዋል ተብሏል።

@sheger_press
የትግራይ ክልል ተፈናቃዮች ከክረምቱ በፊት ሙሉ በሙሉ እንደሚመለሱ መንግሥት ገለጸ‼️

በአማራ እና በትግራይ ክልሎች አዋሳኞች የይገባኛል ጥያቄ ለሚነሣባቸው አካባቢዎች፣ በሕገ መንግሥቱ መሠረት ዘላቂ እልባት ለመስጠት በብሔራዊ ደረጃ የተቋቋመው ኮሚቴ፣ ተፈናቃዮችን ወደ ቀዬአቸው ለመመለስ ቅድሚያ ሰጥቶ እንደሚሠራ፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ አስታውቀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ ባለፈው ሳምንት ዐርብ፣ ከትግራይ ክልል የኅብረተሰብ ተወካዮች ጋራ ባደረጉት ውይይት፣ በአከራካሪ ቦታዎች ላይ የፌዴራሉ መንግሥት የጸጥታ ኀይሎች ብቻ እንደሚኖሩ ገልጸዋል።

ከነዚኽ አካባቢዎች ተፈናቅለው በትግራይ ክልል የሚገኙ ተፈናቃዮች፣ በማንኛውም ሰዓት ወደ ቀዬአቸው ለመመለስ ከፈለጉ፣ መንግሥት ለማስፈጸም ዝግጁ እንደኾነም አበክረው ተናግረዋል።

ብሔራዊ ኮሚቴው፣ እስከ አሁን የተፈጸሙና ሊፈጸሙ ሲገባቸው የዘገዩ ጉዳዮችን መገምገሙን የዘገቡ መንግሥታዊ ብዙኀን መገናኛዎችም፣ ተፈናቃዮችን በአጭር ጊዜ ወደ ቀዬቸው ለመመለስ በሚቻልበት አግባብ ላይ ቅድሚያ ተሰጥቶት እንዲሠራ የጋራ መተማመን ላይ እንደተደረሰ አስታውቀዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
አሳዛኝ መረጃ‼️

በአማራ ክልል በኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን በተፈጸመ ጥቃት 27 ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ተናገሩ !!

በአማራ ክልል በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን #ጂሌ_ጥሙጋ ወረዳ፤ ከየካቲት 30፣ 2016 ዓ/ም ጀምሮ በተፈጸመ “የተቀናጀ ጥቃት” 27 ነዋሪዎች መገደላቸውን እና ከ40 በላይ ሰዎች መቁሰላቸውን ነዋሪዎች ተናገሩ።

ጥቃቱ በጂሌ ጥሙጋ ወረዳ በሚገኙ ከ20 በላይ ቀበሌዎች ላይ ግጭቱ እንደተከሰተ ተገልጿል።

“በጥቃቱ ህጻናት፣ እረጋውያን እና ሴቶችን ጨምሮ በርካታ ሰዎች ተገድለዋል። በተጨማሪም መኖሪያ ቤቶችን ጨምሮ በርካታ ንብረቶች ወድመዋል” ሲል ነዋሪዎቹ ተናግረዋል።

እስከ ዛሬ ቀጥሏል በተባለው ግጭት ጉዳት ከደረሰባቸው 40 ሰዎች ውስጥ 20 የሚሆኑት በ #አፋር ክልል አቋርጠው በ #አዳማ ከተማ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው ይገኛሉ ብሏል።

ከዚህ በተጨማሪ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ቀወት ወረዳ የለን፣መዋጮ፣ነገሶ እና ሞላሌ በሚባሉ ቀበሌዎች ሰሞኑን በነበረው ግጭት ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ውድመት ደርሷል።
አጣዬ ዙሪም ዛሬ ተመሳሳይ ግጭት አለ ብለዋል።

@ethio_mereja_news
መርጌታ ቃለ ህይወት  የባህል መዳኒት ቀማሚ እና መስተፋቅር እንሰራልን በሁሉም ከተሞች ያላችሁ አናግሩኝ:

መርጌታ ቃለ ህይወት የባህል መድህኒት አስማት እና ጥበብ ይፈልጋሉ:
የምንሰጣቸው የጥበብ አገልግሎቶች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል
1 ለመፍትሔ ስራይ
2 ለህማም
3 ጋኔን ለያዘው ሰው
4 ቡዳ ለበላው
5 ለቁራኛ
6 የዛር ውላጅ ለተዋረሰው
7 ለአይነ ጥላ
8 ነገረ ራዕይ(ራዕይ የሚያሳይ)
9 ለዓቃቤ ርዕስ
10 ለመክስት
11 ለቀለም(ለትምህርት)
14 ለመስተፋቅር
15 ለሁሉ ሠናይ
16 ለገብያ
17 ለአምፅኦ ብእሲት(ፍቅረኛ ላጣ ወይም ላጣች የሚሰራ)
18 ለመድፍነ ፀር
19 ሌባ የማያስነካ
20 ለበረከት

ውድ  ቤተሰቦች  ለማንኛውም ነገር ያማክሩን    ከስላምታ ጋር።
ከምሰጣቸው በትንሹ ይህን ይመስላል 
ለጥያቄወ 09 75-90-23-15
ኢትዮ መረጃ - NEWS
Photo
ኩላሊት እስከመስጠት የጸናው ፍቅር ፤ ለ11 ዓመታት ዲያሌሲስ እያደረገ የሚገኘውን ወጣት ያገባችው አፍቃሪ

መነሻውን ከቤተ - ክርስቲያን ያደረገ ፍቅር ነው፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ ቂርቆስ ቤተ - ክርስቲያን ውስጥ በተለያየ አገልግሎት ውስጥ ሆነው ተዋወቁ፡፡ አንድ ብሎ መፃፍ የተጀመረው ይህ የትውውቅ ምዕራፋቸውም እስከ ትዳር የቀጠለ የፍቅር መፅሐፍ ሆነ፡፡ መፅሐፉ ግን እንዲሁ የፍቅር ብቻ አልነበረም፡፡ አሳዛኝ ታሪክም አለው፡፡ ፅናትን ይዟል፡፡ እምነት ጎልቶበታል፡፡ ተስፋን ሰንቋል፡፡ በእሷ አፍቃሪነትና በእሱ ብርታት የተመሰረተ ድንቅ የፍቅር ታሪክ ነው፡፡ የሀና እና የቢኒያም ታሪክ።

ቢኒያም አበራ ይባላል፡፡ ተወልዶ ያደገው ከአራዶቹ መንደር ጨርቆስ ነው፡፡ ታዲያ ቢኒያም የተዋጣላት ሼፍ ነበር፡፡ በሚሰራቸው ምግቦች ብዙዎችን ጣት አስቆርጥሟል፡፡ የተራቡትን አጥግቧል፡፡ ከዚህ ባሻገር የሰፈሩ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን ቋሚ አገልጋይ ነበር፡፡ ነገር ግን ቢኒያም ለረጅም ጊዜ ቆሞ የሰራው የምግብ ማብሰል ሙያ የጤና ችግር ፈጠረበት፡፡ ይህን የተገነዘበው ቢኒያምም ሌሎች ኮርሶችን በመማር ሙያ ይቀይራል፡፡ ግን አርፍዷል፡፡ ቢኒያም አርፍዶ ነበር፡፡ በአንድ የቀን ጎዶሎ አይኑ ይጋረድና ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ይገባል፡፡ በኋላም ሁለቱም ኩላሊቶቹ ከአገልግሎት ውጪ እንደሆነ ይነገረዋል፡፡ ዲያሌሲስም ይጀምራል፡፡ ይህ የሆነው እንግዲህ የዛሬ 11 ዓመት ገደማ ነው፡፡

በዚህ ጊዜ ትብብር ባንዲራቸው በሆኑት በሰፈሮቹ ልጆች እገዛ፣ በጓደኞቹ እንዲሁም ሰርቶ ባጠራቀማት ጥቂት ገንዘብ እየታገዘ የኩላሊት እጥበቱን ይቀጥላል፡፡ ቢኒያም ብርቱ ነው፡፡ ጠዋት እጥበት ተደርጎለት ማታ ቤተክርስቲያን ለማገልገል የሚሄድ ጠንካራ ወጣት፡፡ “ነገ መልካም ይሆናል” የሚል ተስፈኛ ወጣት ……….

ታዲያ በዚህ ሁሉ ውጣ ውረድ ውስጥ በሁኔታው የምትደነቅ አንዲት ሴት አለች፡፡ ሀና መስፍን፡፡ እሷም እንደሱ የቂርቆስ ቤተክርስቲያን አገልጋይ ነች፡፡ ከዲያሌሲስ መልስ ወደ ቤተክርስቲያን ሲገባ ስታየው ትገረማለች፡፡ ተስፋው ያስቀናታል፣ እምነቱ ይገርማታል፣ ብርታቱ ይደንቃታል፡፡

በኋላም ተዋወቁ፡፡ ትውውቃቸውም ወደ ፍቅር ከፍ አለ፡፡ ሀናም ለእናቷ የሆነውን ሁሉ ነገረቻቸው፡፡ ይህን የሰማችው እናትም በሁኔታው ግር ተሰኘች፡፡ ብቸኛ ልጇ ሀና ናትና ነገሩ አስፈራት፡፡ ነገር ግን ምንም ከባድ ቢሆን እናት የልጅን ደስታ ነውና የምትሻው “ደስታሽ ደስታዬ” ነው ብላ ፈቀደች፡፡ የወደደችውን ወደደች፡፡ 

በዚህም ከአራት አመት ቆይታ በኋላ መስከረም 4 ቀን 2012 ዓ.ም ትዳር መሰረቱ፡፡ አሁን አራት አመት በትዳር ቆይተዋል፡፡ በሰፈሮቹ ልጆች አጠራር “ከስተም” ዛሬም ዲያሌሲስ እያደረገ ነው፡፡ አሁን ግን ደከመ፡፡ ቢኒያም የድሮው ጥንካሬ ቀንሷል፡፡

በዚሁ ዙሪያ ሀና ከአዲስ ዋልታ ዲጂታል ሚዲያ ጋር ባደረገችው ቆይታ አሁን ቢኒ እየደከመብኝ ነው ትላለች፡፡ “ከዲያሌሲስ ሲመለስ ይደክመዋል፣ ምግብም አይበላም፤ በግድ የሚጎርሳት አንድ ሁለት ጉርሻም መልሳ ትወጣለች” ስትል ነው ያስረዳችን፡፡ 

በመሆኑም ሀና አንድ ኩላሊቷን ልትሰጠው ወስና ሙሉ ዝግጅቷን ጨርሳለች፡፡ በዚህም ለደጋግ ኢትዮጵያውያን ባስተላለፈችው መልዕክት “ያለንበትንና እያሳለፍን ያለውን ችግር በመረዳት የንቅለ ተከላውን ወጪ ሸፍኑልኝ” ስትል ትማፀናለች፡፡

እገዛ ማድረግ ለምትፈልጉ እገዛ ማድረግ የምትፈልጉ ወገኖች በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000608474246 (ቢኒያም አበራ እና ሀና መስፍን) ወይም በስልክ ቁጥር 0913734394 (ቢኒያም አበራ) ደውለው ማግኘት የምትችሉ መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን።

Via ዋልታ

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
#AmharaRegion‼️

° " ህዝቡ በታጠቁ ቡድኖች ነው ለጥቃት የተዳረገው በገዛ ከተማው ነው መአት ያወረደበት ... ጥቃት ፈፃሚዎቹ ከአጎራባች ' ሸኔ ' ናቸው " - የአጣዬ ከተማ ከንቲባ

° " #ሀሰት_ነው የኦሮሞ አርሶ አደሮች እንጂ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት አባላት አይደሉም " " - አባገዳ አህመድ ማህመድ

በአማራ ክልል ፤ የሰሜን ሸዋን እና የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደርን በሚያጎራብቱ አካባቢዎች ላይ ግጭት ከጀመረ ከሳምንት በላይ ሆኖታል።

በተደጋጋሚ ፦
- የሰዎች ደም በሚፈስበት፣
- ንብረት በሚወድምበት ፣
- ሰዎች ቄያቸውን ለቀው በሚፈናቀሉበት በዚህ ቀጠና ባለፈው የካቲት ወር ውስጥም በርካቶች መገደላቸው ይታወሳል።

አሁን ደግሞ #ከ8_ቀናት በፊት የተቀሰቀሰው ግጭት እጅግ መባባሱን ነዋሪዎች ተናግረዋል። በመነሻው ላይ በሁለቱም በኩል እርስ በእርስ መወነጃጀል ያለ ሲሆን በኤፍራታ ግድምና ቀወት ውስጥ ግጭቱ ከፍቶ መዋሉ ነው የተሰማው።

በሁለቱም በኩል ያሉት ነዋሪዎች ፣ የአጣዬ ከንቲባ ፣ የአካባቢው አባገዳ ምን አሉ ?

በኤፍራታ ግድም ወረዳ የአላላ ከተማ ነዋሪ ፤ ጦርነት ከተጀመረ 8 ቀን መያዙን ፣  ብዙ ቤቶች መቃጠላቸውን ገልጸዋል።

ነዋሪው " የአርሶ አደሮች ዱቄት ሳይቀር ፣ በግ ፣ ፍየል ፣ ግመል ፣ አህያ፣ ከብት በሙሉ ሙልጭ አድርገው ወስደውብናል። ኃላሸት የሚባል ሰውም ገድለውብናል እኛው ክልል ላይ ገብተው " ሲሉ ተናግረዋል።

ይህን ካደረጉ በኃላ ህዝቡ ተሬ እና ዘንቦ ወደሚባለው አካባቢ በለበሰው ልብስ ሸሽቶ ተጠልሎ እንደሚገኝ ገልጸዋል። " በተከታታይ 18 ሰዎችን ገድለውብናል "ም ብለዋል።

በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር የሰንበቴ ነዋሪ ፤ " እስከ ጅሌ ጥሙጋ ባርሲሳ ፣ ካራ ሌንጫ ፣ መከና ወይም አጣዬ ከተማ ዙሪያ ባሉ ቀበሌዎች ከትላንትና ጀምሮ ተኩስ ነበር። ትላንት አንዲት ሴት እንዲሁም ግመልና ከብቶችም ተመተው ነበር ግጭቱ የቀጠለው በዚህ ነው፤ አንድ ሰው ሲሞት ሁለት ሰው ቆስለዋል፤ አንዱ ወደ አዳማ ተልኳል። ዛሬ ደግሞ 4 ሰው ሲሞት 3 ሰው ቆስሏል " ብለዋል።

ዋነኛው እቅዳቸው የጅሌ ጥሙጋ ከተማ #ሰንበቴን " እንይዛለን ፣ እናጠፋለን " የሚል ነው ሲሉ ገልጸዋል።

አንድ የአጣዬ ነዋሪ ደግሞ ፤ ሰሞኑን ግጭት ተባብሶ ዛሬ አጣዬን በተኩስ ልውውጥ ሲያናውጥ መዋሉን ፣ 5 ሰው መገደሉም. ጥቃት ፈፃሚዎቹ የታጠቁ አካላት " ሸኔ " ናቸው ብለዋል።

ሌላው የኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ፣ የሰንበቴ ነዋሪ " ግጭቱ የጀመረው #መጋቢት_አንድ ላይ ነው። ይህም በጅሌጥሙጋ ኮላሽ የሚባል ስፍራ 1 ሰው ገድለው 2 ሰው አቁስለው ከብቶችንም ነድተው ከሄዱ በኃላ ነው ግጭቱን የተስፋፋው " ሲሉ ተናግረዋል።

" ከባልች ቀበሌ እስከ ሰንበቴ እና መከና አጣዬ ድረስ ጦርነት ነው። የዛሬውን ለየት ያደረገው ታጣቂዎቹ #ከሰሜን_ሸዋ ተሰባስበው ፤ እራሳቸውን አደራጀትው ሌሊቱን በተሽከርካሪዎች ተጉዘው መጥተው ውጊያ መክፈታቸው ነው " ሲሉ አክለዋል።

ባለፉት 10 ቀናት 29 ሰዎች መገደላቸውን ተናግረው የተወሰዱት ከብቶችና የወደመው ንብረትም ከፍተኛ መሆኑን ጠቁመዋል።

ይህ አስተያየት #አልቀበልም ያሉት የአላላ ነዋሪው ፤ " አማራው ሲያጠፋ በአማራው አጥፊውን መዞ ለህግ ማቅረብ፤ ከኦሮሞውም ሲያጠፋ አጥፊውን መዞ ለህግ ማቅረብ ሰላም የሚያሰፍነው ይሄ ብቻ ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

" በህግ እና በሽምግልና  ነገሩ መክሰም አለበት እነሱ የሚሉት ከጨፋ ጀምሮ እስከ ሸዋሮቢት ድረስ የኦሮሞ ቦታ ነው። አጣዬም #የኛ_ነች ፤ አላላም ፣ ሞላሌም ፣ ማጀቴም ... ሁሉም የኛ ነው የሚሉት። መንግስት ትኩረት ሰጥቶ ችግሩን ሊፈታው ይገባል " ብለዋል።

የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን #አባገዳ አህመድ ማህመድ " መንገድ የለም። ከጅሌ ጥሙጋ እና አርጡማ ፋርሲ ወረዳዎች እንዲሁም ከዞን መገናኘት አልቻልንም " ብለዋል።

" በዚህ ምክንያት የሃይማኖት አባቶች እና አባ ገዳዎች ተሰባስበው መፍትሄው ምንድነው ? ለማለት መንገዱ ተከፍቶ ለህዝቡ ምግብ ለማድረስ ፣ የቆሰሉትንም ወደ ህክምና ቦታ ለመውሰድ ጥረት ላይ ነን። መንገድ ከተዘጋ 1 ወር ሊሆነው ነው። እኛም ሆነ መንግሥታዊ አመራሩ ሄደን ማየት አልቻልንም። የአማራ ክልልም #ታጣቂዎቹን_ስለሚፈሯቸው ቀርበው ለማነጋገር አልተቻለም። እኛ ጋር ያሉትን #ወሰናችሁን አልፋችሁ አትሂዱ እያልን እየመከርናቸው ነው ። " ገልጸዋል።

ነዋሪዎችና የአካባቢው አስተዳደሮች ጥቃቱን የከፈቱት " ሸኔ (የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት) " ናቸው ቢሉም አባገዳ አህመድ " ሀሰት ነው " ብለዋል።

" ሀሰት ነው የኦሮሞ አርሶ አደሮች እንጂ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት አባላት አይደሉም። የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት እዚህ አልገባም። እየተዋጋ ያለው እራሱ ነዋሪው ነው " ብለዋል።

የአጣዬ ከተማ ከንቲባው ተመስገን ተስፋ ፤ ከተማዋና ህዝቡ በታጠቁ ቡድኖች ነው ለጥቃት የተዳረጉት ብለዋል።

አጣዬ ላይ ' #ወረራ ' መፈፀሙን ገልጸው " ሰውም አልቋል፤ ሚሊሻውም የሚችለውን ያህል ሞከረ አለቀ " ብለዋል።

ይህን የሚፈፅሙት ከአጎራባች  " #ሸኔ በሏቸው " ሲሉ የጠሯቸውን የታጠቁ ኃይሎች መሆናቸውን ገልጸዋል።

" ዋናው መፍትሄ መንግሥት ጠንከር ብሎ #እርምጃ መውሰድ ያለበት ላይ እርምጃ መውሰድ ፤ ይሄ ነበረ መፍትሄው  አሁን ባለው መንገድ ፣ #በእሹሩሩ ሰውም አለቀ " ብለዋል።

#የአጣዬ_ህዝብ የገዛ ከተማው ላይ እንዳለ መአት እንደወረደበት የገለጹት ከንቲባው " እጅግ በጣም አስቸጋሪ ነው፤ መንግስት ቢደርስልን ጥሩ ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

ከኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር በኩል ለጥፋቱ ለችገሩ " የፋኖ ሀይሎችን" ተጠያቂ ሲያደርጉ ከሰሜን ሸዋ ዞን በኩል ደግሞ " ሸኔን (የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት) " ተጠያቂ ያደርጋሉ።

NB. ባለፉት አምስት ዓመታት አጣዬ ከ10 ጊዜ በላይ የመቃጠል አደጋ አስተናግዳለች።

እስካሁን የአማራ ክልል መንግሥት ስለ ጉዳዩ ያለው ነገር የለም። (VOA)

@ethio_mereja_news
ደረሰኞችን ብቻ በመሸጥ ሶስት ቢሊዮን የሚጠጋ ብር በመንግስት ላይ ጉዳት ያደረሰ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ዋለ

ቴዎድሮስ ንጉሴ ሀያርያ እና ቴዎድሮስ ንጉሴ ወልድሀዋሪያ በተባሉ ሀሰተኛ ስሞችን በመጠቀም የሀሰት ሰነዶችን እና ደረሰኞችን በመሸጥ በመንግስት ላይ ጉዳት ያደረሰ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ሥር ዋለ።

ተጠርጣሪው ምንም ሽያጭ ሳያካሄድ ደረሰኞችን ብቻ በመሸጥ መጠኑ 2,951,053,749.86 ብር የሚሆን ሽያጭ ማከናወኑን ከፌደራል ፖሊስ የገኘነው መረጃ ያሳያል።

ህጋዊ በመምሰል የዕቃ እና አገልግሎት ግብይት ሳይኖር የተለያዩ ድርጅቶችና ግለሰቦች የመለያ ቁጥር ርLB 0019300 ከሆነው የሽያጭ መመዝገቢያ መሣሪያ በ1 ሺህ 2 መቶ 70 ደረሰኞች መሸጡን ፖሊስ አስታውቋል።

ሀሰተኛ ደረሰኞቹን ከተጠርጣሪው ላይ የገዙ ግብር ከፋዮች ደግሞ በሀሰተኛ ሰነዶች አማካኝነት ወጪያቸውን በማነር ለመንግሥት የሚከፈለውን ግብርና ታክስ እንዲቀንስና ያልተገባ ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመላሽ ከመንግሥት ካዝና አንዲወስዱ ማድረጉንም ፖሊስ ጨምሮ ገልጿል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ትግራይ ክልል ከፍተኛ የወንድ የዘር ፊሳሽ እጥረት ተከስቷል!!

በትግራይ የወንድ የዘር ፈሳሽ (ስፐርም) ለሚለግሱ ሰዎች 10ሺ ብር ስጦታ ይሰጣል ተባለ


'አዶ' በሚል ስም እሚታወቅ አንድ የግል የህክምና ማዕከል በተፈጥሮአዊ መንገድ ፅንስ ለመቋጠር ላልቻሉት ልጅ እእዲኖራቸው ለማድረግ እየሰራሁት ነው ባለው ስራ ሴት እንስቶች 'እንቁላል' ወንዶች ደግሞ 'የዘር ፍሬ (ስፐርም) እንዲለግሱ ጥሪውን አቅርቧል።

በትግራይ ክልል መቀለ ከተማ መቀመጫውን ያደረገው 'አዶ' የእናቶች፣ ሕጻናት እና የነቃ ሕይወት ሕክምና ማዕከል ይህንን ሕክምና ለመስጠት ዝግጅት የጀመረው ከትግራይ ጦርነት በፊት እንደሆነና ህክምናውን ለመጀመር የተደረገው ጥረት በጦርነቱ ምክንያት ቢቋረጥም ጦርነቱ ሲጠናቀቅ ግን ሂደቱ መቀጠሉን ይገለፃል።

ማዕከሉ በአሁኑ ሰዓት ታድያ ለስራው አስፈላጊ የሆኑ ቅድመ ዝግጅቶች በመከወን ስፐርም እና እንቁላል ለመለገስ ፈቃደኛ የሆኑ ሰዎችን እየጠበቀ ነውም መባሉን ዳጉ ጆርናል ታዝቧል። የድርጅቱ ባለቤት የሆኑት ዶ/ር ሳምሶን ሙልጌታ እንዳሉት ከሆነም ለጋሾችን እየጠበቅን ነው ነገር ግን ሁሉም ሰው የወንድ የዘር ፍሬ ወይም እንቁላል መለገስ አይችልም።  ከሁለቱም ፆታዎች ፈቃድ በተጨማሪ የብቃት መስፈርቶች አሉ ብለዋል።

የወንድ ዘር ለጋሾች የዘር ፍሬያቸው መጠን ከ 1.5 ሚ/ሊ በላይ መሆን አለበት፣በአንድ ሚ/ሊ ስፐርም ውስጥ ከ15 ሚሊዮን በላይ የወንድ የዘር ህዋስ (sperm cells) መኖር አለበት በተጨማሪም ለጋሾች ለኤችአይቪ፣ ለሄፐታይተስ ቫይረስ እና ሌሎች ተላላፊ በሽታዎች ምርመራ ማድረግ አለባቸውም ብለዋል።

እንቁላል ለሚለግሱ ሴቶች የእድሜ ገደብ እንዳለና እንቁላል ለመለገስ ብቁ የሆኑ ሴቶች በ 20 እና 30 አመት መካከል ናቸው በተጨማሪም ሴት ለጋሾች ቀደም ብለው የወለዱ መሆን አለባቸው ይላሉ ዶ/ር ሳምሶን። ይህ መስፈርት የተቀመጠው ለምን እንደሆነ ሲገልጹም “[የወለዱ ሴቶች] እንቁላሎቻቸው ተፈትነዋል ብለዋል።

የሕክምና ማዕከሉ ባለቤት እነዚህን መስፈርቶች የሚያሟሉ ለጋሾች ከድርጅቱ ጋር በስምምነት መስራት እንደሚችሉም የገለፁ ሲሆን ከስምምነቱ አንዱ የተበረከተው የወንድ ዘር ወይም እንቁላል ለማን እንደሚሰጥ አለመገለፅ ነው ብለዋል።

በዚህ ልገሳ ለሚሳተፉ ሰዎች ማለትም ስፐርም ለሚለግሱ ወንዶች 10ሺ ብር ስጦታ እንደሚሰጥም ገልፀዋል።

ምንም እንኳ ተቋሙ በአሁኑ ሰዓት ከትግራይ ምግብና መድሓኒት ቁጥጥር ባለስልጣን ፍቃድ ተሰጥቶት እየተንቀሳቀሰ ቢሆንም በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የጤና ኢንስፔክሽን፣የጤና ተቋማት እና ባለሙያዎች ስራ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ እንዳልካቸው ፀዳል ይህ በትግራይ ጤና ቢር በኩል ተሰጠ ስለተባለው ፍቃድ እሚያውቁት ነገር እንደሌለ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

Via ቢቢሲ ትግርኛ

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ባለፍት ሶስት ዓመታት በኦሮሚያና አፋር ክልሎች 1 መቶ ሹፌሮች ተገለዋል ተባለ!!

የጣና የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማህበር ባለፉት ሶስት ዓመታት ወዲህ
1መቶ የሚደርሱ የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች በታጣቂዎች መገደላቸው ተነግሯል።

የማህበሩ ፀሀፊ አቶ ሰጡ ብርሀን እንደተናገሩት  በሹፊሮች ላይ የሚደረገው እንግልት እንደበዛ በማንሳት 1 መቶ የሚደርሱ የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች መገደላቸውን ጠቁመዋል።

የአሽከርካሪዎች እገታ፣   በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ማስከፍል፣ ድብደባ፣ ግድያ እና የንብረት ውድመትም ልላው ጉዳይ እንደሆነ አቶ ሰጡ ተናግረዋል።

በአሁኑ ወቅትም እነዚህ ድርጊቶች በ ኦሮሚያ፣ አፋር እንዲሁም ሌሎች ክልሎች ተባብሰው የቀጠሉ በመሆኑ ሁኔታው አሳሳቢ እንደሆነም ጠቁመዋል።(ኢትዮኤፍ ኤፍ)

@sheger_press
@sheger_press
አስገራሚ መረጃ‼️

ሁለት የሴት መራቢያ አካል እና ሁለት ማህፀን ያላት ሴት

ይች ሴት የ25 ዓመቷ ብሪታናዊት ነች።አኒ ሻርሎት ትባላለች። ከቢልየን ሰዎች መሀል እንኳን የመከሰት እድሉ ጠባብ በሆነው  ዲዴልፊስ ተብሎ በሚጠራው ወጣ ያለ የመራቢያ አካል አቀማመጥ የተጠቃች ሲሆን በዚህም ምክንያት ሁለት የሴት ብልት እና ሁለት ማህፀን ባለቤት መሆኗን The Sun የተሰኘ የመረጃ ምንጭ አስነብቧል።

ሁለት በተለያያ ጊዜ የወር አበባ ሂደት በየወሩ እንደምታስታናግድ የገለፀው ዘገባው ብዙዎችን በጣም  ያስገረመው ግን እራሴን እንደ ሁለት ስለምቆጥር ሁለት የወንድ ጓደኞች አሉኝ ማለቷ ነው። (fidel post)

@sheger_press
@sheger_press
ከንግድ ባንክ በወሰዱት ገንዘብ ላፕቶፕ እና ዘመናዊ ስልኮችን የገዙ ተማሪዎች ገንዘቡ መመለስ አለበት መባሉን ተከትሎ ጭንቅ ላይ ናቸዉ ተባለ!

ቢቢሲ በአንዳንድ ዩኒቨርስቲዎች ያሉ ተማሪዎችን በማናገር ባገኘው መረጃ መሠረት በርካታ ተማሪዎች ከአስር ሺዎች እስከ መቶ ሺዎች የሚቆጠር የራሳቸው ያልሆነ ብር ከባንኩ ለመውሰድ ችለው ነበር።

ችግሩ ከተከሰተ በኋላ ባንኩ ከዩኒቨርስቲዎች እና ከፀጥታ ኃይሎች ጋር በመሆን ገንዘቡን ለማስመለስ እያደረገ ባለው ጥረት፣ ጥቂት የማይባሉ ተማሪዎች በእጃቸው ላይ የቀረውን ብር መመለሳቸው ቢነገርም ለተለያዩ ጥቅም ያዋሉት ግን ግራ በመጋባት በቀጣይ የሚመጣውን በመጠባበቅ ላይ ናቸው።

ቢቢሲ ያነጋገራቸው እና በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ላይ በተፈጠረው ችግር የተለያየ መጠን ያለው ገንዘብ የወሰዱ ተማሪዎች ሂደቱን “ሥራ” በሚል ቃል ነበር የገለጹት። ስሙ እንዳይጠቀስ የጠየቀ ቢቢሲ ያነጋገረው አንድ የጅማ ዩኒቨርሲቲ ተማሪም “እኔ ወደ 150 ሺህ ብር ሠርቻለሁ። 300 ሺህ ብር እና ከዚያ በላይ የሠሩ ተማሪዎች አሉ። . . . ቀድሞ የሰማ [የሲስተም ብልሽቱን] ብዙ ሠርቷል” ብሏል።

ተማሪው አክሎም በዕለቱ “150 ሺህ ብር ‘ሠርቼ’ ነበር። ሁሉንም ብር ተመላሽ አድርጊያለሁ። ወደ ሌላ ባንክ ያዘዋወሩ ጓደኞቼ ግን ጭንቀት ላይ ናቸው” ሲል የተፈጠረውን ሁኔታ መግለጹን ከዘገባው ተመልክተናል። ንግድ ባንክ በገንዘብ ዝውውር ሥርዓቱ ላይ ብልሽት ከማጋጠሙ በፊት በሂሳቡ ውስጥ የነበረው ከ5 ሺህ ብር በታች እንደነበረ የሚገልጸው ይህ ተማሪ፣ የተፈጠረውን ክፍተት እንደ መልካም አጋጣሚ ተጠቅሞ 150 ሺህ ብር መውሰዱን አምኗል። ባንኩ ችግሩ መከሰቱን ተከትሎ ያላግባብ ብር የወሰዱ ደንበኞቹ ተመላሽ እንዲያደርጉ ባሳሰበው መሠረት እና ከዩኒቨርስቲው በኩል በወጣው ማስጠንቀቂያ ምክንያት ተማሪው ገንዘቡን መመለሱን ተናግሯል።

በድንገት እጃቸው ላይ የገባውን ከፍተኛ መጠን ያለውን ገንዘብ የተለያዩ እቃዎች የገዙበት ወይም ከንግድ ባንክ አካውንታቸው ወደ ሌላ ባንክ ገንዘብ ያዘዋወሩ ተማሪዎች ደግሞ ከፍተኛ ጭንቀት ላይ ይገኛሉ።

ተማሪው እንደሚለው የሲሰተም ብልሽት ባጋጠመበት ወቅት ካላቸው ገንዘብ በላይ ወደ ሌላ ባንክ ገንዘብ ያዘዋወሩ ተማሪዎች የባንክ ሂሳባቸው እንዳይንቀሳቀስ በመደረጉ ገንዘቡን ለመመለስ ባለመቻላቸው በግራ መጋባት ጭንቀት ውስጥ ይገኛሉ ብሏል።

የጅማ ዩኒቨርሲቲው ተማሪ እንደሚለው ብዙ ጓደኞቹ በወሰዱት ገንዘብ የተለያዩ ውድ ነገሮችን በመግዛታቸው ገንዘቡን መልሰው ማግኘት በማይችሉበት ሁኔታ ላይ ስላሉ ጭንቀት ላይ ይገኛሉ ይላል።

በተለይ ላፕቶፕ እና ዘመናዊ ስልኮችን የገዙ ተማሪዎች ጥቂት አለመሆናቸውን የሚጠቅሰው ተማሪው “100ሺህ ብር የሠራ አንድ ልጅ በሁለተኛው ቀን ላፕቶፕ እና ስማርት ስልክ ገዝቷል” በመግዛቱ እጁ ላይ የሚመልሰው ገንዘብ እንደሌለ ገልጿል።

Via BBC

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የዓለማቀፉ ገንዘብ ድርጅት (አይ ኤም ኤፍ) ልዑካን ቡድን አዲስ አበባ መግባቱ ታውቋል።

ልዑካን ቡድኑ ላንድ ሳምንት ቆይታ አዲስ አበባ የገባው፣ መንግሥት ለአገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ መርሃ ግብሩ ማስፈጸሚያ በጠየቀው ብድር ዙሪያ ከፋይናንስ ሚንስቴርና ከብሄራዊ ባንክ ባለሥልጣናት ጋር ለመወያየት ነው።

ኢትዮጵያ ከድርጅቱ በጠየቀችው ብድር ዙሪያ ከስምምነት ላይ ካልደረሰች፣ አበዳሪ አገራት እስከ ቀጣዩ የአውሮፓዊያን ዓመት የሰጧትን የብድር መክፈያ እፎይታ እንደሚሰርዙ ቀደም ሲል አስጠንቅቀዋል።

መንግሥት ከድርጅቱ የጠየቀው ብድር 3 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ገደማ ነው።

የድርጅቱ ልዑካን ቡድን ካኹን ቀደም ወደ ኢትዮጵያ ተጉዞ በብድር ጥያቄው ዙሪያ የተወያየው ባለፈው ጥቅምት ወር እንደነበር ይታወሳል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
2024/10/03 23:17:50
Back to Top
HTML Embed Code: