Telegram Web Link
የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት እና የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት አባቶች ከጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ጋር ዛሬ መወያየታቸው ተሰምቷል።

ተሳታፊዎች ሰላም እና ፀጥታን ፣ የኅብረተሰቡን የልማት ፍላጎቶች፣ ቤተክርስቲያኒቷ ውስጥ ስላሉ የአስተዳደር ተግዳሮቶች ብሎም የሃይማኖት አባቶች በሀገራችን ዘላቂ ሰላምን ለማረጋጥ የሚኖራቸውን ሚና አስመልክተው ጉዳዮችን አንስተዋል ተብሏል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ፕሬዚዳንት ፑቲን ሩሲያ ለኒውክሌር ጦርነት ዝግጁ ናት ሲሉ አስጠነቀቁ‼️
የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ሩሲያ ለኒውክሌር ጦርነት ዝግጁ ናት ሲሉ ለምዕራባውያን ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል።

ፑቲን ከቀናት በኋላ ከሚካሄደው የሩሲያ ምርጫ ቀደም ብሎ በሰጡት ቃለ ምልልስ ላይ፥ አሜሪካ ወታደሮቿን ወደ ዩክሬን የምትልክ ከሆነ ሞስኮ ጦርነቱ እንደሚባባስ እና እንደሚካረር ትቆጥረዋለች ብለዋል።

ዋሺንግተን ይህን ካደረገች ሞስኮ ጉዳዩን እንደ ጣልቃ ገብነት ታየዋለችም ነው ያሉት ፑቲን።

የኒውክሌር ጦርነት "አያስቸኩልም" ያሉት ፑቲን፥ በዩክሬን ላይ የኒውክሌር መሳሪያ የመጠቀም አስፈላጊነት እንዳልታያቸውም ነው የተናገሩት።

ይሁን እንጅ ሃገራቸው ለኒውክሌር ጦርነት ቴክኒካሊ ዝግጁ ናት ማለታቸውንም ሬውተርስ አስነብቧል።

ፑቲን ከዚህ ቀደም ምዕራባውያን እና የኔቶ አባል ሀገራት ጦራቸውን ከዩክሬን ጎን አሰልፈው የሚዋጉ ከሆነ የኒውክሌር ጦርነት አይቀሬ ነው ማለታቸው ይታወሳል።

ሩሲያ ከዩክሬን ጋር የገባችበት ጦርነት ከ1962ቱ የኩባ የሚሳዔል ቀውስ ወዲህ በአሜሪካ እና በሩሲያ መካከል ከፍተኛ ፍጥጫ መፍጠሩ ይነገራል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ የአዲስ አበባ ህዝብ እንቅልፍ መተኛት አልቻለም
የተኛ በሽተኛ መዳን ሲገባው እንዳይድን እያደረጉ ነው::

* የአዛኑን ድምፅ
* የቅዳሴውን ድምፅ

በፉክክር ከፍ እያደረጋችሁ ህዝቡን እንዳይተኛ እያደረጋችሁ ነው ይህን ነገር ልታስቡበት ይገባል ሲሉ ተደምጠዋል::

@sheger_press
@sheger_press
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት 205 ሠራተኞቹ ላይ እርምጃ መወሰዱን ገለጸ

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ባለፋት ስድስት ወራት ከውጭ አገር ከደላሎች ጋር በመመሳጠር ህገወጥ ተግባር ሲፈፅሙ የነበሩ 205 ሠራተኞች ላይ እርምጃ መውሰዱን አስታወቀ።

ህገወጥ ተግባር ሲፈፅሙ የነበሩ የተባሉት ሰራተኞች ከስራ እስከማባረር የደረሰ እርምጃ እንደተወሰደባቸው የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት፤ የአገልግሎቱን የ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት የስራ አፈፃፀም አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ ገልጸዋል።

ህጋዊ ሰነድ ሳይኖራቸውና ባልተፈቀደላቸው ስራ ላይ የተሰማሩ ከ10 ሺህ በላይ የውጭ ሀገር ዜጎች ላይ ምርመራ በማድረግ እንደ ጥፋት መጠናቸው ተጠያቂ እንዲሆኑ ተደርጓል ብለዋል። ህጋዊ ሰነድ የሌላቸው የውጭ ዜጎች ሰነድ አሟልተው እንዲመዘገቡ መደረጉም ተገልጿል፡፡

በተጨማሪም በሥድስት ወራት ከ1 ነጥብ 1 ሚሊየን በላይ ፓስፖርት ታትሞ 640 ሺህ የሚሆነው ለደንበኞች መሰራጨቱን ተናግረዋል።

ይሄም የፖስፖርት ህትመት ክፍሉ በትጋት በመስራት ያመጣው ውጤት መሆኑን ጠቅሰው፤ ከመጋቢት 16 ቀን 2016 ዓ.ም በኋላ ዜጎች በተሰጣቸው የቀን ቀጠሮ መሰረት ፓስፖርታቸውን መረከብ ይችላሉ ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ተለቀቁ‼️

ከእስር መለቀቃቸው ተሰማ!!

ላለፉት 42 ቀናት በእስር የቆዩት የፓርላማ አባል ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ዛሬ መለቀቃቸው ተሰምቷል።

ዶ/ር ጫኔ ከወር በፊት በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸው ይታወሳል።

ሌላው የምክር ቤት አባል አቶ ክርስቲያን ታደለ ዛሬ ያለመከሰስ መብታቸው ተነስቷል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
አቶ አብዲ መሐመድ ኡመር (አብዲ ኢሌ) ከእስር ተፈቱ

የቀድሞው የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አብዲ መሐመድ ኡመር (አብዲ ኢሌ) ከእስር መፈታታቸውን ጠበቃቸው ለቢቢሲ ተናገሩ።

ከስድስት ዓመት በፊት ነሐሴ 21/2010 ዓ.ም. አዲስ አበባ ውስጥ በቁጥጥር ስር ውለው አስካሁን በእስር ላይ የቆዩት አቶ አብዲ መሐመድ ኡመር ከእስር የተለቀቁት ዐቃቤ ሕግ ክሱን በማንሳቱ መሆኑን ጠበቃቸው ለቢቢሲ አረጋግጠዋል።

ጠበቃ እና የሕግ አማካሪው እስክንድር ገዛኸኝ እንደተናገሩት የቀድሞው የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ክሳቸው ተነስቶ የተለቀቁት ዛሬ መጋቢት 5/2016 ዓ.ም. መሆኑን አመልክተዋል።

ከአቶ አብዲ በተጨማሪም በተመሳሳይ በእሳቸው የክስ መዝገብ ጉዳያቸው ሲታይ የነበሩ የሌሎችም ተከሳሾች ክስ ተቋርጦ መለቀቃቸውን ጠበቃው ተናግረዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የነዳጅ ዋጋ እንዲስተካከል መደረጉ የነዳጅ ኮንትሮባንድ እንዲቀንስ አስችሏል - አቶ ገብረመስቀል ጫላ

የነዳጅ ዋጋ እንዲስተካከል መደረጉ የነዳጅ ኮንትሮባንድ እንዲቀንስ ማስቻሉን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር አቶ ገብረመስቀል ጫላ ተናገሩ።
የኢትዮጵያን የንግድ ሥርዓት ለማዘመን የተከናወኑ ዐበይት ተግባራትን አስምልክቶ ሚኒስትሩ ለመገናኛ ብዙኃን ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በማብራሪያቸውም ኮንትሮባንድ የገቢና የወጪ ንግድ ሥርዓትን በማቀጨጭ የሀገሪቱ ቁልፍ ችግር መሆኑን ተናግረዋል።

በተለይም ህገ-ወጥ ነጋዴዎች በቁም እንስሳት፣ በጫት፣ በጥራጥሬና ቅባት እህሎች ላይ የሚያካሂዱት የኮንትሮባንድ እንቅስቃሴ በወጪ ንግድ ሥርዓቱ ላይ ጉዳት እያስከተለ መሆኑን ገልጸዋል።

በኮንትሮባንድ የተሰማሩ ህገ-ወጥ ነጋዴዎች ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት ሀገርንና ህዝብን የሚጎዱ ድርጊቶች እየፈጸሙ መሆኑን ተናግረዋል።

ኮንትሮባንድ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ቁልፍ ችግር ነው ያሉት ሚኒስትሩ፤ በኢትዮጵያ ወጪና ገቢ ንግድ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እያሳደረ ነው ብለዋል።

የኮንትሮባንድ እንቅስቃሴን ለመቆጣጠርም በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመራ የጸጥታና ጉምሩክ ተቋማት ግብረ ሃይል ተደራጅቶ እየተሰራ እንደሚገኝም አንስተዋል።

የኢትዮጵያ የነዳጅ ዋጋ ከጎረቤት ሀገራት ጋር ሲነፃጸር ዝቅተኛ በመሆኑ ሙሉ ቦቴ ጭምር ወደ ጎረቤት ሀገራት ሄዶ የሚሸጥበትና ኢትዮጵያም ስትፈተንበት የቆየችው ጉዳይ እንደነበር አስታውሰዋል።

ቀስ በቀስ በተካሄደ የነዳጅ ዋጋ ማሻሻያ ከጎረቤት ሀገራት ተመሳሳይ እንዲሆን በማድረግ ኮንትሮባንድ እንዲቀንስ መደረጉን ገልጸዋል።

አሁንም በነዳጅ ላይ የተወሰነ የኮንትሮባንድ ዝንባሌ ቢስተዋልም በተወሰደው የማሻሻያ እርምጃ ከሀገር የሚወጣበት ሥርዓት እየቀነሰ መምጣቱን ተናግረዋል።

(ኢዜአ)

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
መርጌታ ቃለ ህይወት  የባህል መዳኒት ቀማሚ እና መስተፋቅር እንሰራልን በሁሉም ከተሞች ያላችሁ አናግሩኝ:

መርጌታ ቃለ ህይወት የባህል መድህኒት አስማት እና ጥበብ ይፈልጋሉ:
የምንሰጣቸው የጥበብ አገልግሎቶች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል
1 ለመፍትሔ ስራይ
2 ለህማም
3 ጋኔን ለያዘው ሰው
4 ቡዳ ለበላው
5 ለቁራኛ
6 የዛር ውላጅ ለተዋረሰው
7 ለአይነ ጥላ
8 ነገረ ራዕይ(ራዕይ የሚያሳይ)
9 ለዓቃቤ ርዕስ
10 ለመክስት
11 ለቀለም(ለትምህርት)
14 ለመስተፋቅር
15 ለሁሉ ሠናይ
16 ለገብያ
17 ለአምፅኦ ብእሲት(ፍቅረኛ ላጣ ወይም ላጣች የሚሰራ)
18 ለመድፍነ ፀር
19 ሌባ የማያስነካ
20 ለበረከት

ውድ  ቤተሰቦች  ለማንኛውም ነገር ያማክሩን    ከስላምታ ጋር።
ከምሰጣቸው በትንሹ ይህን ይመስላል 
ለጥያቄወ 09 75-90-23-15
Samsung  Galaxy  note  3
አዲስ  አንደታሸገ 
32  gb
3 gb ram
ዋጋ 4000  ብር በማከፋፈያ ዋጋ
Call me 👇👇👇👇
☎️ 0909255008
☎️ 0912739699
ተጨማሪ ስልኮችን  ለመመልከት
አና ስልክ ለመሽጥ ከፈለጉ 👇 ቤተሰብ ይውኑ
👉https://www.tg-me.com/used_phone_ethiopian
ኢንተርኔት‼️
በርካታ የአፍሪካ ሀገራት የኢንተርኔት መቋረጥ እንዳጋጠማቸው ኔት ብሎክስ አስታወቀ‼️

ኬብሉ በምን ምክንያት እንደተበላሸ እስካሁን ግልጽ አልተደረገም
ከባህር ስር በተዘረጉ የኢንተርኔት ኬብሎች ላይ ባጋጠመው ብልሽት ምክንያት በበርካታ የምዕራብ እና የማዕከላዊ አፍሪካ ሀገራት ኢንተርኔት መቋረጡን ኢንተርኔት ኦብዘርቫቶሪይ ኔት ብሎክስ ገልጿል
በርካታ የአፍሪካ ሀገራት እንተርርኔት መቋረጥ እንዳጋጠማቸው ኔት ብሎክስ አስታውቋል።
ከባህር ስር በተዘረጉ የኢንተርኔት መስመሮች ወይም ኬብሎች ላይ ባጋጠመው ብልሽት ምክንያት በትናትናው እለት በበርካታ የምዕራብ እና የማዕከላዊ አፍሪካ ሀገራት ኢንተርኔት መቋረጡን ኢንተርኔት ኦብዘርቫቶሪይ ኔት ብሎክስ ገልጿል።
ኬብሉ በምን ምክንያት እንደተበላሸ  እስካሁን ግልጽ አልተደረገም።
የአፍሪካ ከባህር ስር ያሉ ኬብሎች ተቆጣጣሪ(ሲኮም) እንዳረጋገጠው የምዕራብ አፍሪካ ኬብል ሲስተም መበላሸቱን እና በዚያ መስመር ላይ የነበሩ ደንበኞች ሲኮም ከሚጠቀምበት ኢኩያኖ ኬብል ጋር እንዲገናኙ መደረጉን አረጋግጧል።
ሲኮም እንደገለጸው አንዱ ኬብል ሲበላሽ ወደ ሌላ የማዛወሩ ስራ አውቶማቲክ ወይም ወዳያውኑ የሚደረግ ነው።
ኮትዲቯር፣ ላይቤሪያ፣ ቤኒን፣ጋና እና ቡርኪናፋሶ ከፍተኛ ችግር እንዳጋጠማቸው የኔትብሎክ መረጃ ያመለክታል።
የኢንተርኔት ኩባንያ የሆነው ክላውድፍሌር በኤክስ ገጹ እንደጻፈው ጋምቢያ፣ ጊኒ፣ ላይቤሪያ፣ ኮትዲቯር፣ ጋና፣ ቤኒን እና ኒጀር ከፍተኛ የኢንተርኔት መቋረጥ አጋጥሟቸዋል።
"ከሰሜን እስከ ደቡብ አፍሪካ ያለው የኢንተርኔት መቆራረጥ የሰአት ተመሳሳይነት ያለው ይመስላል" ብሏል ክላውድ ፍሌር።
የደቡብ አፍሪካው ቴሌኮም ኦፕሬተር ቮዳኮምም በባህር ስር ያሉ ኢንተርኔት ኬብሎች መበላሸት በኢንተርኔት ሰጭ ኩባኔያዎች ላይ ተጽዕኖ አሳድረዋል ብለዋል።
አልአይን
በኢትዮጵያ ከ800 ሺህ በላይ ዲያሌሊስ የሚያስፈልጋቸውን ሰዎች አሉ ተብሎ እንደሚገመት ተገለጸ

👉 የኩላሊት ቀን መጋቢት 5 ቀን ታስቦ ውሏል


ዓለም አቀፍ የኩላሊት ቀን ህብረተሰቡ ስለ ኩላሊት ያለውን ግንዛቤ ለማሳደግ ታስቦ በየዓመቱ በመጋቢት ወር ላይ የሚከበር ሲሆን መጋቢት 5 ቀን 2016 ዓ.ም ታስቦ ዉሏል፡፡በኢትዮጵያ ከ800 ሺህ በላይ ዲያሌሊስ የሚያስፈልጋቸውን ሰዎች አሉ ተብሎ እንደሚገመት የኩላሊት ህመምተኞች በጎ አድራጎት ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ አ/ቶ ሰለሞን አሰፋ ለብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል ።

ደም ማነስ፣ ደም የተቀላቀለበት ሽንት፣ የጠቆረ ሽንት፣ ንቁ  አለመሆን፣ የሽንት መጠን መቀነስ፣ የእግር፣ የእጅ  እና የቁርጭምጭሚት ማበጥ፣ የድካም ስሜት ፣ የደም ግፊት፣ እንቅልፍ እጦት ፣ የሚያሳክክ ቆዳ የኩላሊት ህመም ዋና ዋና ምልክቶች ናቸው ።በተጨማሪም የምግብ ፍላጎት መቀነስ ፣ በሌሊት ቶሎ ቶሎ ለሽንት መመላለስ፣ የትንፋሽ እጥረት፣ ሽንት ላይ ፕሮቲን መገኘት በፍጥነት የሚቀያየር የሰውነት ክብደት እና ራስ ምታት ተጠቃሸ ናቸው ። በሌላ በኩል ሽንት ይዞ አለመቆየት ፣ በቂ ውሃ መጠጣት፣ጨው የበዛበት ምግብ አለመመገብ፣ የአልኮል መጠጥ መጠን መቀነስ፣ ሲጋራ አለማጨስና ሌሎች የኩላሊት ህመምን ለመከላከል የሚረዱ ስለመሆናቸው ተጠቁሟል ።

የኩላሊት ሕመምተኞች እጥበት በጎ አድራጎት ድርጅትን ለመደገፍ በሁለት ክፍለከተሞች የሚገኙ የሶስት ወረዳ ሰራተኞች ወርሃዊ የ 10 ብር መዋጮ እያደረጉ መሆኑን የድርጅቱ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሰለሞን አሰፋ ለብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።የቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 10 እና 11 እንዲሁም የቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 8 ሰራተኞች ከወርሃዊ ደሞዛቸዉ 10 ብር ተቆራጭ በማድረግ ለማህበሩ መዋጮ እና ድጋፍ እያደረጉ ይገኛል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የኢትዮጵያ_ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በአገራዊ ምክክር መድረክ ተሳታፊ እንድትሆን አሳሰበች‼️

ቤተ ክርስቲያኗ በ #አድዋ መታሰቢያ ሙዚየም ውስጥም ተገቢው እውቅና እንዲሰጣትም አሳስባለች።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በአገራዊ ምክክር መድረኩ ተሳታፊ እንድትሆን እና በ #አድዋ መታሰቢያ ሙዚየም ውስጥም ተገቢው እውቅና እንዲሰጣት የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት አስተዳደር ጉባኤ አሳሰበ።

ጉባዔው ከትላንት በስቲያ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባው፤ “ቤተ እምነቷ እየተቃጠለ፣ አገልጋይ ካህናትና ምዕመናን እየሞቱና እየተሰደዱባት የምትገኘው ቤተ ክርስቲያናች ለሚገጥሟት ችግሮች መፍትሔ እንዳታበጅና በሀገራዊ ምክክር መድረኩ ምንም ዓይነት ተሳትፎ እንዳይኖራት መደረጉ ተገቢ አይደለም” ሲል ገልጿል።

በመሆኑም፤ “ቅድስት ቤተክርስቲያን በሀገራዊ ምክክር መድረክ ልትሳተፍ ይገባል” ሲል አሳስቧል።

በተጨማሪም ጉባዔው፤ “የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በአድዋ ዜሮ ዜሮ ፕሮጀክት ውስጥ በጦርነቱ ድል የነበራትን ከፍተኛ ሚና በሚገልጽ መልኩ ታሪኳ አለመቀመጡ አሳዝኖኛል” ብሏል።

ቤተ ክርስቲያኗ፤ ለድሉ መታሰቢያ በተገነባው ሙዚየም ውስጥ "አለመዘከሯ ስህተት ነው" ያለው ጉባዔው፤ በሙዚየም ውስጥ ተገቢው እውቅና እንዲሰጣትና ለአድዋ ድል ያበረከተችውን አስተዋጽኦ የሚያመለክት መታሰቢያ እንዲደረግላት የጠቅላይ ቤተ ክህነት አስተዳደር ጉባኤ አሳስቧል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
አሳዛኝ መረጃ😭

የወንጂ ስኳር ፋብሪካ አምስት ሰራተኞች ከስድስት ቀን በፊት በታጣቂዎች ታፍነው ተወስደው የነበረ ቢሆንም በታጣቃዎቹ ተገድለው መገኘታቸው ተሰምቷል::

ለተጨማሪ መረጃ ይህን
ቻናል ይቀላቀሉ👇👇
@sheger_press
@sheger_press
በኮምቦልቻ ከተማ በታዳጊ ህጻን ላይ የግብረ ሰዶም ተግባር የፈጸመው ግለሰብ በ17 አመት ጽኑ እሰራት ተቀጣ።

ተከሳሽ ሁሴን ይማም የተባለው ግለሰብ ነዋሪነቱ አማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን በኮምቦልቻ ከተማ አሰን አገር ክፍለ ከተማ ሜጃ ቀበሌ ሲሆን አንድ ታዳጊ ህጻንን ስራ ስራልኝ በማለትና በማታለል የግብረ ሰዶም ተግባር እንደፈጸመበት ተገልጿል።

ግለሰቡ ታዳጊው የቀን ስራ በሚጠብቅበት ኮምቦልቻ ከተማ መድን ድርጅት አካባቢ ጥር 9/2016 ከቀኑ 9 አካባቢ ስራ ትፈልጋለህ ብሎ በመጠየቅና 600 ብር እንደሚከፍለው በመስማማት ወደ ስራ ቦታ ሳይሆን በቀኑ ወደጫካ በመውሰድ የግብረ ሰዶም ተግባር እንደፈጸመበት ተገልጿል።

የኮምቦልቻ ከተማ ፍትህ ጽ/ቤት የሰውና የሰነድ ማስረጃ በማዘጋጀት ክስ በአቃቤ ህግ በኩል በማቅረብ ፍርድ ቤት በጉዳዩ ላይ ውሳኔ እንዲሰጥ አድርጓል።

በመሆኑም ጉዳዩ የደረሰው የኮምቦልቻ ከተማ ፍርድ ቤት ተሳሹ 1996 የወጣውን የኢፌዲሪ ወንጀል ህግ 631/1ለን የተመለከተውን መተላለፉን በሰውና በሰነድ ማስረጃ አረጋግጧል።

በመሆኑም ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኙን በመመልከት ተከሳሽን ጥፍተኛ በማድረግ ተከሳሹን ያርማል ሌሎችን ያስተምራል በማለት መጋቢት 2/2016 በዋለው ችሎት ተከሳሹ በ17 አመት ጽኑ እሰራት እንዲቀጣ ውሳኔ አስተላልፏል።
 (Dessie fana FM96.0 //ከድር መሀመድ)

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ከትግራይ ክልል ከተውጣጡ የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ጋር ዛሬ በአዲስ አበባ ተወያይተዋል።

ጠቅላይ ሚንስትሩ፣ ከክልሉ የኅብረተሰብ ክፍሎች ተወካዮች ጋር በተለያዩ ጠቃሚ ጉዳዮች ላይ ዙሪያ መወያየታቸውን በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ገልጠዋል።

መንግሥታቸው  በትግራይ ክልል ሰላም እና ልማትን ለማስገኘት ምንጊዜም ቁርጠኛ መኾኑን የገለጡት ዐቢይ፣ የዛሬው ውይይትም ይህንኑ የጋራ ዓላማ ለማሳካት ነው ብለዋል።

በውይይቱ ላይ፣ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር ጌታቸው ረዳ እና መከላከያ ሚንስትር አብርሃም በላይ ተገኝተዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ATTENTION!!

+1000% coin will be posted in BINANCE WHALE'S LEAK🚀🚀

Link open only for LIMITED TIME🕓

JOIN FAST👀👇

https://www.tg-me.com/+rDT7H_njmis4ODQ0
በአፋር ክልል በኢሳ እና አፋር ጎሳዎች መካከል ግጭት መቀጠሉን ዋዜማ ከምንጮች ሰምታለች።

ትናንት በአፋር ክልል ዞን 6 ወይም ማሂ ረሱ ዞን ውስጥ በሚገኘውና አፋር እና ሶማሌ ክልሎች በሚወዛገቡበት አዳዶ ወረዳ በኹለቱ ጎሳዎች መካከል ግጭት ማገርሸቱን ምንጮች ተናግረዋል።

በኹለቱ ጎሳዎች መካከል ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ተደጋጋሚ ግጭቶች የተከሰቱ ቢኾንም፣ ኹለቱ ክልሎች ግን ስለ ጎሳ ግጭቶች መግለጫ ሲያወጡ አይሰሙም።

የጎሳ ግጭቱ ትናንት በድጋሚ ያገረሸው፣ በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አስተባባሪነት የኸለቱ ክልሎች የጎሳ እና የአገር ሽማግሌዎች ተገናኝተው ከመከሩና ለግጭቶችና አለመግባባቶች ዘላቂ መፍትሄ ለመፍታት ጠቅላይ ምክር ቤቱ የሚመራው መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ ካቋቋሙ ከጥቂት ቀናት በኋላ ነው።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የአሜሪካ ዓለማቀፍ ተረድዖ ድርጅት (ዩ ኤስ አይ ዲ) ከፍተኛ ልዑካን ቡድን ትናንት በድጋሚ በመቀሌ ጉብኝት አድርጓል።

በሰብዓዊ ጉዳዮች ቢሮ የዋና ዳይሬክተሯ ረዳት ሶናሊ ኮርዴ የመሩት ልዑካን ቡድን፣ ከክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ሃላፊዎች ጋር በክልሉ በተከሰተው ሰብዓዊ ቀውስና በወቅታዊ ኹኔታዎች ዙሪያ መክሯል። ልዑካን ቡድኑ ወደ አፋር ክልልም አቅንቶ፣ የዕርዳታ ሥርጭት ሂደቱን ተመልክቷል።

ከጥር ወር ወዲህ፣ ድርጅቱ በትግራይ፣ አፋር፣ አማራ፣ ኦሮሚያና ሶማሌ ክልሎች ለ2 ነጥብ 4 ሚሊዮን ተረጂዎች አስቸኳይ የምግብ ዕርዳታ ማቅረቡን ገልጧል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
2024/10/04 03:16:05
Back to Top
HTML Embed Code: