Telegram Web Link
ለውድ የባንካችን ደንበኞች በሙሉ
================================
በሲስተም ችግር ምክንያት በባንኩ አገልግሎቶች ላይ ማለትም በቅርንጫፎች፥ በኢንተርኔት ባንኪንግ፥ በሞባይል ባንኪንግ፥ እንዲሁም በሲቢኢ ብር የአገልግሎት መቋረጥ አጋጥሟል።

አገልግሎቱን መልሶ ለማስጀመር በከፍተኛ እርብርብ እየተሰራ በመሆኑ ደንበኞቻችን በትዕግስት እንድትጠብቁን እየጠየቅን፣ ለተፈጠረው መጉላላት ይቅርታ እንጠይቃለን።


@ethio_mereja_news
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሲስተም ምክንያት ተቋርጦ የነበረው የቅርንጫፎች አገልግሎት መጀመሩን አሳውቋል‼️

የባንኩ ቅርንጫፎች ዛሬ እስከ ምሽቱ 2፡00 ሰዓት አገልግሎት እንደሚሰጡም አሳውቋል።

በተመሳሳይ ዲጂታል የባንክ አገልግሎቶች ፦
- ኢንተርኔት ባንኪንግ፥
- ሞባይል ባንኪንግ፥
- ሲቢኢ ብር ለማስጀመር እየሠራ መሆኑን ገልጾ ለተፈጠረው የአገልግሎት መስተጓጎል በድጋሚ ይቅርታ ጠይቋል።

ባንኩ በምን ምክንያት የሲስተም ችግር እንደተፈጠረ የሰጠው ማብራሪያ የለም።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ሰዎች ከኤቲኤም ማሽኖች ያለገደብ ገንዝብ ማውጣታቸው እና ሲያወጡም ከሂሳበቸው ምንም ቅናሽ እንዳልታየ ባንኩ ገልጿል

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዛሬ ባወጣው መግለጫ በትናንትናው እለት የሳይበር ጥቃት ደርሶበት እንደነበር አስታውቋል።

ባንኩ እንደገለጸው ትናንት ምሽት ላይ በርካታ ሰዎች ከኤቲኤም ማሽኖች ያለገደብ ገንዝብ ማውጣታቸውን እና ሲያወጡም ከሂሳበቸው ምንም ቅናሽ እንዳልታየ ባንኩ ባወጣው መግለጫ ጠቅሷል።

ባንኩ ገንዘብ ሲያወጡ ነበር ያላቸው ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን እና ማጣራት እየተደረገባቸው እንደሚገኝ ገልጿል።
ነገርግን ባንኩ ከጥቂት ሰአታት በፊት ባወጣው መግለጫ የተቋረጠው አገልግሎት በድጋሚ መጀመሩን አስታውቋል።

ባንኩ እንደገለጸው አሁን ላይ አገልግሎት የጀመሩት ቅርጫፎቹ ሲሆኑ የሞባይል፣ የኢንተርኔት ባንኪንግ እና የሲቢኢ ብር አገልግሎቶች ለማስጀመር እየሰራ ነው።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በአዲስ አበባ የሚገኙ አንዳንድ ባለሃብቶች ከማያውቋቸው ሰዎች ስልክ እየተደወለላቸው ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ እንዲከፍሉ እንደሚገደዱ ዋዜማ ተረድታለች።

በአዳማና ባሕርዳር አንዳንድ ባለሃብቶች፣ ታጣቂዎች ጭምር ገንዘብ እንደጠየቋቸው ለዋዜማ ተናግረዋል። ባለሃብቶቹ፣ ገንዘብ የሚጠይቋቸው ግለሰቦች በባንክ ስላላቸው የገንዘብ መጠን መረጃ ያላቸው እንደኾኑ ጠቅሰዋል።

አንድ የአዳማ ነዋሪ ባለሃብት፣ ማንነታቸውን የማያውቋቸው ግለሰቦች ገንዘብ ካልከፈልኩ በደኅንነቴ ላይ አደጋ እንደሚፈጥሩ ስለዛቱብኝ 6 ሚሊዮን ብር ከፍያለኹ ብለዋል።

ፌደራል ፖሊስ፣ ባለሃብቶች ለወንጀለኞች ገንዘብ ከከፈሉ በኋላ የሚደርሱኝ አቤቱታዎች፣ የወንጀል መከላከል ሥራዬን ያከብዱታል በማለት ለዋዜማ ተናግሯል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዲጂታል አግልግሎት ሙሉ በሙሉ ጀመረ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዲጂታል አግልግሎት ሙሉ በሙሉ መጀመሩን አስታወቀ፡፡

በሲስተም ችግር ምክንያት በባንኩ አገልግሎቶች ላይ ማለትም በቅርንጫፎች፣ በኢንተርኔት ባንኪንግ፣ በሞባይል ባንኪንግ፣ እንዲሁም በሲቢኢ ብር የአገልግሎት መቋረጥ አጋጥሞ እንደነበር ባንኩ መግለጹ ይታወቃል፡፡

በቅርንጫፍ እና በኤቲኤም የሚሰጡ አገልግሎቶች ቀደም ብለውም ጀምረዋል፡፡

አሁን ደግሞ በዲጂታል የሚሰጡ የባንክ አገልግሎቶች ሙሉ በሙሉ መጀመራቸውን ባንኩ ለደንበኞች አሳውቋል፡፡

ባንኩ ደንበኞቹን በትእግስት ስለጠበቁ አመስግኖ ፥ ለተፈጠረው የአገልግሎት መስተጓጎል ይቅርታ ጠይቋል፡፡

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ኬና ልዩ የጥርስ ህክምና ክሊኒክ ዘመኑ ባፈራቸው መሳሪያዎች በመታገዝ ሙሉ የጥርስ ህክምናን በመስጠት ላይ ይገኛል::  ከምንሰጣቸው አገልግሎቶች መካከል በከፊል
➢ መጥፎ የአፍ ጠረንን ማከም
➢ የቆሸሹ ጥርሶችን በማሽን እናፀዳለን
➢ በህክምና መዳን የማይችሉትን ጥርሶች መንቀል
➢ ወጣ ገባ ያሉ ጥርሶችን በ ኦርቶዶንቲክ አፕላይንስ እና በብሬስ ማስተካከል(with ceramic bracket and metal brackets
➢ የጥርስ ስር ህክምናን መስጠት
➢ የተቦረቦሩ ጥርሶችን እንሞላለን
➢ የተነቀሉ ጥርሶችን በሰው ሰራሽ አርተፊሻል መተካት (partial dentures, full denture, zirconia , ceramic crown, Implant
➢ የጥርስ ራጅ አገልግሎት መስጠት


አድራሻ: ፒያሳ ከኢትዬ ሴራሚክስ ወረድ ብሎ ከአንበሳ ፉርማሲ አጠገብ ኢመኤ ህንዓ 4ኛ ፋሎር ላይ
  Tel: 0911892011 / 0930202124
ሂውማን ራይትስ ዎች፣ የሶማሌ ክልል የቀድሞ ርዕሰ መስተዳድር አብዲ ሞሃመድ ኡመር (አብዲ ኢሌ) ከእስር መልቀቃቸውን ተችቷል።

ድርጅቱ፣ የአብዲ ከእስር መፈታት በእሳቸው የሥልጣን ዘመን በክልሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ለተፈጸሙባቸው ሰለባዎች ከባድ መርዶ መኾኑን ገልጧል። መንግሥት በዚህ ውሳኔው፣ በአገሪቱ የተጠያቂነት አለመኖር አኹንም ስለመቀጠሉ መልዕክት አስተላልፋል ያለው ድርጅቱ፣ መንግሥት አካሄዱን በመቀየር ለከባድ ጥሰቶች ተጠያቂነትን ለማስፈን ፍቃደኝነቱን ማሳየት መቻል አለበት ብሏል።

@ethio_mereja_news
ቢሾፍቱ ሆራ ሀይቅ ዳርቻ የተከሰተ ድርጊት!

ድርጊቱ የተፈፀመው የዛሬ ሁለት ሳምንት በቢሾፍቱ ሆራ ሀይቅ ዳርቻ ነው። በርካታ በጥቃቅን እና አነስተኛ የእደጥበብ ምርት እና ሽያጭ ላይ የተሰማሩ አብዛኞቹ ሴቶች የሆኑ ዜጎች በአንድ ጃማይካዊት አስተባባሪነት አነስተኛ ባዛር/የንግድ ትርኢት ያዘጋጃሉ።

ከቀኑ 11 ሰአት ሲሆን የታጠቁ ሰዎች ይመጡና እቃዎቻቸውን አይሱዙ መኪና ላይ ይጭናሉ፣ ሰዎቹንም እየመቱ በጫካ ውስጥ ሁለት ሰአት የፈጀ የእግር ጉዞ አድርገው ወስደው ወደ "ካምፓቸው" አደረሷቸው።

በዚህ ካምፓ ለአምስት ቀን ተይዘው ከቆዩ በኋላ ገንዘብ ይጠይቃሉ፣ ገንዘብ የለንም ሲሉ ግን መታወቂያዎቻቸውን በመቀበል በቀጥታ ወደ ባንኮች እየደወሉ ያላቸውን የገንዘብ መጠን አረጋገጡ፣ ከዛም በግድ ገንዘብ ትራንስፈር አስደረጓቸው።

ይህን ከፈፀሙ በኋላ በአምስተኛው ቀን ከለሊቱ 8 ሰአት ለቀዋቸው በድጋሜ 2 ሰአት በእግራቸው ተጉዘው ቢሾፍቱ ተመልሰዋል።(elias meseret)

@sheger_press
የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ መሃመድ ከአንድ ወር በኋላ ተመለስው ወደ ኤርትራ አቅንተዋል!

የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሸህ መሀሙድ ለሁለት ቀናት የስራ ጉብኝት ከሰአት በኋላ አስመራ ገብተዋል። ፕሬዝደንት ኢሳያስ በኤርፖርት ተገኝተው አቀባበል ማድረጋቸውን የሀገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር አሳውቋል።በሁለትዮሽ ጉዳይ ላይ ለመምከር ያለመ ጉብኝት ነው ተብሏል።

@sheger_press
CBE‼️

CBE ከትናንት በስተያ አርብ ለሊት ባጋጠመው የሞባይል ባንኪግ app system 2.4 ቢሊዮን ብር ወጪ እንደተረገበት Addis fortune ጋዜጣ አስነብቧል።

አጠቃላይ 66,000 የሚጠጉ ሰዎች የገንዘብ ዝውውር ፈፅመዋል ተብሏል።

በተለይ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የወሰዱትን ብር እንዲመልሱ ዩኒቨርስቲዎች እያሳሰቡ ቢሆንም በሲስተም ብልሽቱ ምክንያት እስካሁን ምን ያህል ብር እንደተወሰደበት ባንኩ የሰጠው መረጃ የለም።

@sheger_press
@sheger_press
የኢህአፖዉ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር መጋቢ አብርሃም ሃይማኖትን ጨምሮ ሌሎች ፖለቲከኞች ከእስር እንዲፈቱ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሰጠ።

ባለፈዉ ህዳር 30/ 2016 ዓ/ም ”’ ጦርነት ይቁም ሰላም ይስፈን” በሚል መሪ ቃል በአዲሰ አበባ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ታስቦ እንደነበር ይታወቃል።
ይህንን ተከትሎ ሦስት የሠልፉ አስተባባሪዎች የነበሩት መጋቢ ብሉይ አብርሃም ሃይማኖት፣አቶ ናትናኤል መኮንን እና አቶ ጊደና መድህን በቁጥጥር ስር ውለዋል።
ከጣብያችን ኢትዮ ኤፍ ኤም ጋር ቆይታ የነበራቸዉ ጠበቃና የህግ አማካሪ አቶ አበራ ንጉስ ፍርድቤቱ ሐሙስ 05/07/16 ዓ/ም በዋለዉ ችሎት የታሰሩት ከህግ ዉጭ በመሆኑ እንዲፈቱ ሲል ለፌደራል ፖሊሰ ትእዛዝ መስጠቱን ነግረዉናል።
ፓለቲከኞቹ ባለፍት ሁለት ቀናት ከእስር እንዲፈቱ ውሳኔ የተሰጠ ቢሆንም እስካሁን እንዳልተለቀቁና ፍርዱ ተፈፃሚ እንደሚሆን ተስፋቸዉን ገልፀዋል።

በቁጥጥር ከዋሉበት ቀን ጀምሮ ፍርድ ቤት ቀርበዉ የማያዉቁት የሰልፉ አስተባባሪዎች በፌደራል ፖሊስ እጅ መሆናቸዉ የተገለፀ ሲሆን የአካል ነፃነታቸዉ እንዲከበር ሲከራከሩ ቆይተዉ ፍርድ ቤቱ እንዲፈቱ ወስኗል ብለዉናል።
የፌደራል ፖሊስ ከፍተኛዉ ፍርድ ቤት 05/07/16 ዓ.ም በዋለዉ ችሎት ከ1ኛ እስከ 3ኛ ያሉ አመልካቾች የአካል ነፃነታቸዉ እንዲያከብር ትዕዛዝ ሰጥቷል።
የፌዴራል የመጀመሪያዉ ፍርድ ቤት በሰጠዉ ትዕዛዝም ፌደራል ፖሊስ የከፍተኛዉ ፍርደ ቤት ዉሳኔን በማክበር ከእስር በመልቀቅ ምላሽ በፅሁፍ እንዲሰጥ ትዕዛዝ አስተላልፏል።
የአስተባባሪዎቹ ጠበቃና የህግ አማካሪ አቶ አበራ ፌደራል ፖሊስ ይህንን የማይሻር የፍርድ ቤት ትዕዛዝ እንዲያከብር ጠይቀዋል።
በአቤል ደጀኔ

@ኢትዮ ኤፍኤም
@ethio_mereja_news
ወርቅና ብር ይዘው መውጣት አይችሉም ሲሉ የነበሩት አካላት የጉምሩክ ክፍልን የሚመለከት እንደነበርና አሁን በካሜራ እገዛ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታወቀ፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰሞኑን በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ከመንገደኞች አገልግሎት አሠጣጥ ጋር በተያያዘ ቅሬታ መቅረቡን ተከትሎ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈፃሚ መስፍን ጣሰው በመግለጫቸው እንዳሉት እየተሰሙ ያሉ ቅሬታዎችን መርምሮ መፍትሄ ለመስጠት አየር መንገዱ በአዲስ አበባ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ አገልግሎት ከሚሰጡ ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ቅሬታዎችን የማጣራትና የእርምት እርምጃ እየወሰደ ይገኛል፡፡
በዚህም ወርቅና ብር ይዘው መውጣት አይችሉም የተባሉት ደንበኛ ጉዳይ ዋነኛው ቅሬታ እንደነበር ጠቅሰዋል፡፡

ድርጊቱን የፈፀሙት የከስተም ወይም የጉምሩክ ክፍልን የሚመለከት እንደነበር ገልጸው በመሆኑም ግለሰቦቹን በካሜራ እገዛ በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ተደርገዋል ብለዋል። በቀጣይም አየር መንገዱ እንዲህ አይነት ድርጊቶችን የማይታገስ መሆኑንና ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን እርምጃ እንደሚወስድ አሳስቧል፡፡

የደንበኞች አገልግሎት ለተቋማችን የህልውናችን ዋነኛው ጉዳይ ነው የሚሉት ዋና ስራ አስፈፃሚው በመሆኑም የደንበኞቻችንን ፍላጎት ለማሟላትና በታማኝነት ለማገልገል በትጋት መስራታችንን እንቀጥላለን ብለዋል፡፡

ዋና ስራ አስፈፃሚው አክለውም አሁን ያለው ኤርፖት በአመት እስከ 25 ሚሊየን የሚደርሱ ደንበኞችን እያስተናገደ የሚገኝ ሲሆን ነገር ግን የቢሾፍቱ ማስፋፊያ ኤርፖርት ሲጠናቀቅ ይህን አሃዝ ወደ 100 ሚሊየን ከፍ ያደርገዋል፡፡ (አዲስ ዋልታ)

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
“በባንካችን የደንበኞች የግል አካውንት ላይ የደረሰ ምንም አይነት ጉዳት የለም” የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሰሞኑን አጋጥሞት የነበረውን የአገልግሎት መቋረጥ ችግር አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ በባንኩ የደንበኞች የግል አካውንት ላይ የደረሰ ምንም አይነት ጉዳት አለመኖሩን የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ ይፋ አድርገዋል።

ባንኩ የውስጥ አሰራሩን ለማዘመን ሲያደርግ በነበረው እንቅስቃሴ አርብ መጋቢት 6 ለሊቱን በተፈጠረ ስህተት ምክንያት ጤናማ ያልሆነ የገንዘብ እንቅስቃሴ እንደነበረ የጠቆሙት ፕሬዚዳንቱ የተፈጠረው ክስተት ከሳይበር ጥቃት ጋር የተያያዘ አለመሆኑን አስታውቀዋል፡፡

አርብ ለሊት ብቻ ከ490 ሺህ በላይ የገንዘብ ልውውጥ እንደነበር የተገለፀ ሲሆን ይህ የገንዘብ ልውውጥ ጤናማ የሆነውንም እንደሚጨምር ጠቁመዋል፡፡

"ገንዘብ በተለያየ መንገድ ጤናማ ባልሆነ መልኩ ከባንኩ በማውጣት ላይ በዋናነት የተሳተፉት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ናቸው" ያሉት ፕሬዚዳንቱ አብዛኞቹ የድርጊቱ ተሳታፊ ተማሪዎች በባንኩ በተደረገላቸው ጥሪ መሰረት የወሰዱትን ገንዘብ እየመለሱ መሆናቸውን ገልፀዋል። (EBC)

@ethio_mereja_news
የኢትዮ መረጃ NEWS የመወያያ መድረክ የሆነው ኢትዮ መረጃ NEWS ግሩፕን በመቀላቀል ሀሳብ አስታየታቹን በማንሳት መወያየት ትችላላቹ

JOIN US TO ETHIO MEREJA GROUP👇👇

https://www.tg-me.com/joinchat-NW2Bl7tn5Js3M2I0
Update‼️

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባጋጠመዉ የሲስተም ችግር ካጣዉ ገንዘብ ዉስጥ 1.4 ቢሊዮን የሚገመተዉን አስመለሰ

@sheger_press
@sheger_press
መርጌታ ቃለ ህይወት  የባህል መዳኒት ቀማሚ እና መስተፋቅር እንሰራልን በሁሉም ከተሞች ያላችሁ አናግሩኝ:

መርጌታ ቃለ ህይወት የባህል መድህኒት አስማት እና ጥበብ ይፈልጋሉ:
የምንሰጣቸው የጥበብ አገልግሎቶች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል
1 ለመፍትሔ ስራይ
2 ለህማም
3 ጋኔን ለያዘው ሰው
4 ቡዳ ለበላው
5 ለቁራኛ
6 የዛር ውላጅ ለተዋረሰው
7 ለአይነ ጥላ
8 ነገረ ራዕይ(ራዕይ የሚያሳይ)
9 ለዓቃቤ ርዕስ
10 ለመክስት
11 ለቀለም(ለትምህርት)
14 ለመስተፋቅር
15 ለሁሉ ሠናይ
16 ለገብያ
17 ለአምፅኦ ብእሲት(ፍቅረኛ ላጣ ወይም ላጣች የሚሰራ)
18 ለመድፍነ ፀር
19 ሌባ የማያስነካ
20 ለበረከት

ውድ  ቤተሰቦች  ለማንኛውም ነገር ያማክሩን    ከስላምታ ጋር።
ከምሰጣቸው በትንሹ ይህን ይመስላል 
ለጥያቄወ 09 75-90-23-15
“አስመራ የተገኘሁት ለኤርትራው ፕሬዝዳንት ሶማሊያ እያከሄደች ስላለችው ጸረሽብር ትግል የደረሰችበትን አሁናዊ ሁኔታ ለማሳወቅና ምክር ለመጠየቅ ነው” - የሶማሊያው ፕሬዝዳንት

የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሃሳን ሼክ የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ያቀረቡላቸውን ግብዣ ተቀብለው ለሁለት ቀን የሥራ ጉብኝት ከትላንት ወዲያ መጋቢት 8 ቀን 2016 ዓ.ም አስመራ መግባታቸው ይታወሳል።

የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስቴር በድረገጹ ባስነበበው መግለጫ ፕሬዝዳንት ሸክ ሀሰን ጉብኝታቸውን አጠናቀው ተመልሰዋል።

የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሀሰን ሸክ ኤርትራ የተገኘሁት ሶማሊያን ከአሸባሪዎች ነፃ ለማውጣት በሚደረገው ጥረት ሀገራቸው ያለችበትን አሁናዊ ሁኔታ ለፕሬዝዳንት ኢሳያስ ለማስረዳት እና ምክር ለመጠየቅ ነው ሲሉ ከኤርትራ የቴሌቪዥን ጣቢያ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ መናገራቸውን መግለጫው አስታውቋል።

መግለጫው በተጨማሪም ፕሬዝዳንት ሸክ ሀሰን የሀገራቱ ግንኙነት ያለበትን ደረጃ በተመለከተ ከኢሳያስ ጋር ለመወያየት ነው የተገኘሁት ማለታቸውን አካቷል።

ኤርትራ ለሶማሊያ እያደረገች ላለው ሁለንተናዊ ድጋፍ እናመሰግናለን ሲሉ ፕሬዝዳንት ሸክ ሀሰን መናገራቸውንም አመላክቷል።ሁለቱ መሪዎች የሀገራቱን ሁለትዮሽ ግንኙነቶች ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ፣ የጋራ በሆኑ በቀጠናዊ እና አለም አቀፍ ጉዳዮች ዙሪያ መወያየታቸውን የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስቴር በድረገጹ አስነብቧል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ኦነግ፣ መንግሥት አብዲ ኢሌና ሜጀር ጄነራል ክንፈ ዳኘውን ከእስር ፈትቶ ስምንት የኦነግ ከፍተኛ አመራሮችን በእስር ላይ ማቆየቱ ለኦሮሞ ሕዝብ ያለውን ጥላቻ በግልጽ ያሳያል ሲል ትናንት ባወጣው መግለጫ ወቅሷል።

ኦነግ፣ አብዲ ረጋሳን ጨምሮ ስምንት የግንባሩ ከፍተኛ አመራሮች ምንም ወንጀል ባልሰሩበት፣ በፖለቲካ አቋማቸው ብቻ ለሁለት ዓመት ከስድስት ወራት በእስር ቤት እየማቀቁ መቀጠላቸው ግንባሩን የማዳከሚያ አንዱ መንገድ ነው ብሏል።

ኦነግ፣ በሥልጣን ላይ ያለው መንግሥት በተግባር ለኦሮሞ ሕዝብ ያለውን ንቀትና ከፍተኛ ጥላቻ በማሳየት ላይ ይገኛል በማለት ተችቷል።

ዓለማቀፉ ማኅበረሰብ፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶችና የኦሮሞ ሕዝብ በእስር ቤት ውስጥ እየተንገላቱ ለሚገኙት የግንባሩ ከፍተኛ አመራሮች ድምጽ እንዲኾኑም ኦነግ ጠይቋል።

@sheger_press
@sheger_press
ፕሬዝዳንት ፑቲን ሶስተኛው የዓለም ጦርነት ሊነሳ ጫፍ ላይ መድረሱን ተናገሩ

ሩሲያን ለቀጣዮቹ ስድስት ዓመታ በፕሬዝዳንትነት እንዲመሩ የተመረጡት ቭላድሚር ፑቲን ሶስተኛ ዓለም ጦርነት ሊጀመር ጫፍ ደረጃ ለይ መድረሱን ተናግረዋል፡፡ፕሬዝዳንት ፑቲን ምርጫውን ማሸነፋቸውን ተከትሎ ባደረጉት ንግግር ሩሲያ አሜሪካ ከሚመራው ኔቶ ጋር የቀጥታ ጦርነት ለመግጠም የመጨረሻ ደረጃ ላይ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ይህ ጦርነት ከተጀመረ ደግሞ ሶስተኛው የዓለም ጦርነት ይጀመራል ያሉት ፕሬዝዳንት ፑቲን ሩሲያ ይህ እንዳይሆን ፍላጎቷ መሆኑን በንግግራቸው ላይ ጠቅሰዋል ሲል ሮይተርስ ዘግቧል፡፡የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ከሁለት ሳምንት በፊት ወታደሮቿን ወደ ዩክሬን ልትልክ እንደምትችል ከተናገሩ በኋላ ኔቶን ጨምሮ በርካታ ሀገራት ሀሳቡን ውድቅ አድርገውታል፡፡

ሩሲያ ከዩክሬን ጦርነት መጀመሯን ተከትሎ በ1962 ከተከሰተው የኩባ ሚሳኤል ቀውስ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ከምዕራባዊያን ሀገራት ጋር ቅራኔ ውስጥ ትገኛለች፡፡ንግግር በሚደርጉበት ወቅት ከኔቶ ጋር ጦርነት ለመግጠም ዝግጁ ኖት በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄም “ባለንበት ዘመናዊ ዓለም ውስጥ የማይቻል ነገር የለም” ሲሉ ፕሬዝዳንት ፑቲን ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

ፕሬዝዳንቱ አክለውም የኔቶ ወታደሮች በዩክሬን እንዳሉ እናውቃለን፣ ሩሲያ እነዚህን ወታደሮች በዩክሬን እየገደለቻቸው ነው ሲሉም ተናግረዋል፡፤ዩክሬን ሩሲያን ማጥቃቷን ከቀጠለች ለደህንነታችን ስንል ተጨማሪ መሬቶችን ከዩክሬን ሊቀሙ እንደሚችሉም ፕሬዝዳንቱ ገልጸዋል፡፡

ፕሬዝዳንት ማክሮን ጦርነቱን ከሚያባብስ አስተያየት ቢቆጠቡ ጥሩ ነው ያሉት ፕሬዝዳንት ፑቲን አሁንም ያንን ለማድረግ ጊዜው አልረፈደም ብለዋል፡፡ለአንድ ሳምንት በሚል የተጀመረው የሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት ሶስተኛ ዓመቱ ላይ የሚገኝ ሲሆን በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮች ከሁለቱም ወገን እንደሞቱ ሲገለጽ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ደግሞ ለስደት ተዳርገዋል፡፡

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ለአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ለመጎብኘት የተተመነዉ ዋጋ ተመጣጣኝ አይደለም ተባለ

የአድዋ ድል መታሰቢያን መነሻ በማድረግ የተገነባዉ ሙዚየም   አሁን ካለንበት ነባራዊ የኑሮ ሁኔታ እና የጉብኝት ባህላችን ደካማ መሆን አንፃር የመግቢያ ዋጋዉ ተመጣጣኝ አለመሆኑ ነዉ የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች የገለጹት፡፡

እንደዚህ አይነት ታሪካዊ ሰነድን የያዙ ፕሮጀክቶች ማበረታታት እንደሚገባ የማያጠያይቅ ሆኖ ሳለ የተመደበዉ የክፍያ መጠን ግን አሁን ካለንበት  የኑሮ ጫና አንፃር  ተመጣጣኝ አለመሆኑን እና ማስተካከያ ቢደረግበት ሲሉ  የምጣኔ ሀብት ባለሙያዉ ዶ/ር አረጋ ሹመቴ ሃሳብ ሰጥተዋል፡፡   
                  
የግንባታዉ ፕሮጀክት ብዙ በጀት ተመድቦበት እንደተከናወነና ለዚህም የወጣዉ ወጪ ከፍተኛ እንደመሆኑ ገቢ ለማግኘት መሞከሩ ተጠባቂ ቢሆንም  የተጠቀሰዉን የዋጋ ተመን  ከፍለዉ የማየት አቅም የሌላቸዉ፤ መጎብኘት የሚፈልጉ ማህበረሰቦችን በዚህ ምክንያት እንዳናጣ ያሰጋኛል በማለት ሀሳባቸዉን የገለፁት ደግሞ ሌላኛዉ የምጣኔ ሀብት ባለሙያ አቶ ፋሲል ጣሰዉ ናቸዉ፡፡

የአድዋ ድል መታሰቢየ ሙዚየምን ለመጎብኘት ለመደበኛ 150ብር፣ለተማሪ 75 ብር እንዲሁም ለልዩ ልዩ 550 ብር መግቢያ እንደሚከፍል መገለጹ አይዘነጋም፡፡

Via: የመናኸሪያ ሬዲዮ

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
2024/10/04 05:22:25
Back to Top
HTML Embed Code: