Telegram Web Link
ቴዲ አፍሮ ዝምታችን በታሪክ ያስጠይቀናል ብሏል።

ሙሉ ፅሁፉ እንደሚከተለው ነው

ለአንፀባራቂውና የጋራ አንድነታችን ውጤት ለሆነው፣ ከሀገር አልፎም ለመላው የአፍሪካ ሕዝብ ኩራት ሆኖ በታሪክ ሲዘከር ለሚኖረው ለ128ኛው የዐድዋ ድል በዓል እንኳን አደረሳችሁ የሚል መልእኬቴን እያስተላለፍኩ፤

የዘንድሮውን 128ኛው የዐድዋ ድል በዓል ስናከብር ሀገራችን ኢትዮጵያ በተለይ ካለፉት አምስት ዓመታት ወዲህ በገጠማት ፖለቲካዊ ቀውስ ሳቢያ በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች እስካሁኗ ሰዓት ድረስ ያለማቋረጥ አለጥፋታቸው በማንነታቸው ብቻ ተለይተው በአሰቃቂ ሁኔታ በግፍ ሕይወታቸው እንደ ቅጠል እየረገፈ ያሉ ንፁሓን ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችንን በሙሉ በሕሊና ጸሎት እያሰብን ሊሆን ይገባል።

ይህንንም ከሰው ልጅ የሞራል ሕግ ያፈነገጠ እጅግ ዘግናኝና ኢሰብዐዊ ተግባር ሲፈፀም አለማውገዝና ከዳር ሆኖ በዝምታ ማየት እንደ አንድ ሀገር ተወላጅ ዜጋ ነገ ማናችንንም ከታሪክ ተወቃሽነት እና ተጠያቂነት እንደማያድነን ከግንዛቤ ውስጥ ልናስገባ ግድ ይለናል።

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር! ፍቅር ያሸንፋል!

ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ)

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
መጠነኛ ጉዳት ደርሷል

በወላይታ ሶዶ መብራት ሀይል ዋናዉ ማስተላለፊያ ጣቢያ (Substation) ላይ የእሳት ቃጠሎ ማጋጠሙ ተሰምቷል። ለጊዜው ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ምሽት 5:00 የተከሰተ መሆኑን ፖሊስ አስረድቷል።

እሳቱን ለማጥፋት የወላይታ ሶዶ ከተማ እሳትና አደጋ መከላከል ቡድን፤የአከባቢው ህብረተሰብና የሚመለከታቸው አካላት በሙሉ ብርቱ ጥረት በማድረጋቸው የተነሳውን እሳት መቆጣጠር ተችሏል።

በወላይታ ሶዶ ከተማ በቀን 21/2016 ዓ.ም ከምሽቱ 5:00 ሰዓት አካባቢ የተከሰተው ድንገተኛ የእሳት አደጋ ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር መቻሉን የከተማው ፖሊስ ገልጿል።(መናኸሪያ ሬዲዬ )

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ተፈረደበት

* 1 ዓመት ና
* 2 ሺህ ብር

ኮሜዲያን ያሬድ ዘላለም (ልጅ ያሬድ) በ 1 ዓመት ቀላል እስራትና በ2 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ ተወሰነ

የቅጣት ውሳኔውን የወሰነው የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ህገመንግስታዊና በህገመንግስት ስርዓቱ ላይ የሚፈጸሙ የወንጀል ጉዳዮችን የሚመለከተው ችሎት ተከሳሹ ያቀረበውን አምስት የቅጣት ማቅለያ አስተያየቶችን ይዟል።

የፍትህ ሚኒስቴር የተደራጁና ድንበር ተሻጋሪ ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ሕግ በኮሜዲያን ያሬድ ዘላለም ላይ ሶስት ክሶችን አቅርቦበት ነበር።

ከቀረቡበት ክሶች መካከል በኮምፒዩተር የሚፈጸም ወንጀል ድንጋጌን መተላለፍ፣ የቤተክርስቲያንና የሰዎችን ክብርና መልካም ስም ማጉደፍ እንዲሁም የጥላቻ ንግግር ማሰራጨት የሚሉ ተደራራቢ ክሶች ይገኙበታል።

ኮሜዲያን ያሬድ ዘላለም የቀረበበት ክስ እንዲሻሻል የክስ መቃወሚያውን በጽሁፍ ያቀረበ ቢሆንም በዐቃቤ ሕግ በኩል ክሱ ሊሻሻል የሚችልበት የህግ አግባብ እንደሌለ ተጠቅሶ መልስ ሰጥቷል።

ፍርድ ቤቱም ግራ ቀኙን መርምሮ ተከሳሹ ያቀረበው የክስ መቃወሚያ ጥያቄ የህግ አግባብነት የለውም በማለት ውድቅ አድርጎታል።

ከዚህም በኋላ ተከሳሹ በክሱ ላይ የተጠቀሰውን የወንጀል ድርጊት አለመፈጸሙን በመጥቀስ የዕምነት ክህደት ቃሉን በመስጠቱ ዐቃቤ ሕግ የሰውና የሰነድ ማምረጃውን አቅርቧል።

የቀረበውን ማስረጃ የመረመረው ችሎቱ ተከሳሹ የቀረቡበት ሶስት ክሶች ተጠቃለው በአዋጅ ቁጥር 1185/2012 አንቀጽ 4 እና 7 መሰረት እንዲከላከል ብይን ሰጥቷል።

ሶስቱም ክስ በአንድ እንዲጠቃለል የታዘዘው የወንጀል ድርጊቱ በሀሳብ፣ በጊዜና በቦታ ተመሳሳይ መሆኑን በምክንያትነት ተጠቅሶ ነበር።

ተከሳሹ የመከላከያ ማስረጃ አለኝ ማለቱን ተከትሎ ፍርድ ቤቱ ተከሳሹ ያቀረባቸውን የሰው መከላከያ ማስረጃዎችን ቃል አዳምጧል።

ተከሳሹ የሰው የመከላከያ ማስረጃ ያቀረበ ቢሆንም የዐቃቤ ሕግ ማስረጃን በተገቢው መከላከል ባለመቻሉ እና በክስ ዝርዝሩ ላይ የተጠቀሰውን የወንጀል ድርጊት መፈጸሙ በፍርድ ቤቱ በመረጋገጡ በዛሬው ቀጠሮ የጥፋተኝነት ፍርድ ተሰጥቶበታል።

ዐቃቤ ሕግ ድርጊቱ ታስቦ የተፈጸመ መሆኑን ጠቅሶ ቅጣቱ ከብዶ እንዲጣል ጠይቋል።

ፍርድ ቤቱ ተከሳሹ ለአካባቢ ጥበቃ ያበረከተውን አስተዋጾኦ፣ የቤተሰብ አስተዳዳሪና የቀደመ የወንጀል ሪከርድ እንደሌለው ገልጾ ያቀረበውን የቅጣት ማቅለያ ይዞለታል።

ፍርድ ቤቱ በድርጊቱ የእርስ በእርስ ግጭት አለመፈጠሩንና ጉዳት አለመድረሱን ከግምት ውስጥ በማስገባት በዕርከን 6 መሰረት በአንድ ዓመት ቀላል እስራትና በሁለት ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ ወስኗል።

የአዲስ አበባ ማረሚያ ቤት ተከሳሹ እጁ ከተያዘበት ከነሃሴ 26 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ያለውን ጊዜ ታሳቢ እንዲያደርግ ታዟል።

Via:- ታሪክ አዱኛ

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ነገ የሚዘጉ መንገዶች ይፋ ሆኑ

128ኛው የዓድዋ ድል መታሰቢያ ክብረ በዓል በአዲስ አበባ ይከበራል፡፡

በዓሉ ፒያሳ አካባቢ በሚገኘው የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም እንደሚከበር ተገልጿል፡፡

ይህ ተከትሎ መንገዶች ይዘጋሉ።

በዚህም መሰረት፡-

ከአፍንጮ በር ወደ ቅ/ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን

ከሰሜን ሆቴል ወደ ቅ/ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን

ከዮሃንስ ቤተ ክርስቲያን ወደ አቡነ ጴጥሮስ ከአራት መንታ ወደ ጅንአድ

ከይርጋ ሃይሌ የገበያ ማዕከል ወደ አቡነ ጴጥሮስ

ከሃብተ ጊዮርጊስ ድልድይ ወደ ሱማሌ ተራ

ከሱማሌ ተራ ወደ ኤሊያና ሆቴል(ባንኮዲሮማ) መስቀለኛ

ከተክለ ሃይማኖት አደባባይ ወደ ቴዎድሮስ አደባባይ

ከአገር አስተዳደር መብራት( ኢሚግሬሽን) ወደ ቴዎድሮስ አደባባይ

ከንግድ ማተሚያ ቤት ወደ ቴዎድሮስ አደባባይ

ከአሮጌው ቄራ ወደ ባንኮ ዲሮማE መብራት

ከራስ መኮንን ድልድይ ወደ ደጎል አደባባይ

ከራስ መኮንን ድልድይ ወደ ቅ/ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን 

ከመቅደላ ሆቴል ወደ ቅ/ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን

ከቅ/ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን ወደ ቴሌ እና ወደ ቅ/ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን ፊት ለፊት ወደሚገኘው አደባባይ የሚወስዱት መንገዶች የካቲት 23 ቀን 2016 ዓ/ም  ከንጋቱ 11 ሰዓት ጀምሮ ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ።

አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ እና የትራፊክ ፖሊሶች የሚጠቁሟቸውን አማራጭ  አቅጣጫዎችን በመጠቀም አስፈላጊውን ትብብር  እንዲያደርጉ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪ አቅርቧል።

ክብረ በዓሉ በሚከበርበት ዙሪያ ከዋዜማው ከየካቲት 22  ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ በዓሉ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ከላይ በተጠቀሱት መንገዶች እና ፕሮግሙ በሚካሄድበት  በአድዋ መታሰቢያ  ሙዚየም ዙሪያ ተሽከርካሪን ማሳደርም ሆነ ለአጭርም ሆነ ለረጀም ሰዓት አቁሞ መሄድ ፈፅሞ የተከለከለ ነው ተብሏል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የሀገሪቱ ዓመታዊ የኢኮኖሚ ዕድገት ወደ ስድስት በመቶ አሽቆልቁሏል-አለም ባንክ‼️

ዓለም ባንክ፣ የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ በኢትዮጵያ ግጭቶችን፣ ድህነትን፣ ማኅበረሰባዊ ውጥረቶችን ሊያባብስ ይችላል በማለት አስጠንቅቋል።

ባንኩ ሰሞኑን ይፋ ባደረገው ሪፖርት፣ የአገሪቱ ዓመታዊ የኢኮኖሚ ዕድገት ወደ ስድስት በመቶ ማሽቆልቆሉንም ገልጿል። የአየር ንብረት ለውጥ፣ በተለይ በግብርናው ዘርፍ ላይ የከፋ ጉዳት እንደሚያስከትልና የሙቀት መጨመርና የዝናብ ሥርጭት መቀያየር፣ በአገሪቱ የወባ በሽታ እንዲስፋፋ፣ ከውሃ የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም እንዲቀንስ፣ ጎርፍ እንዲከሰት እና ምርታማነት እንዲያሽቆለቁል ምክንያት እንደሚሆን ባንኩ ገልጧል። ባንኩ፣ አገሪቱ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም መዋቅራዊ ለውጦች ካላደረገች፣ በቀጣዮቹ 25 ዓመታት የከፋ ርሃብ ይጠብቃታል ብሏል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ተከስቷል በተባለ የኮሌራ በሽታ ከአራት መቶ የማያንሱ ተማሪዎች መያዛቸውን በዩኒቨርሲቲው ትምህርታቸውን እየተከታተሉ የሚገኙ ተማሪዎች ተናገሩ።

ከተከሰተ አንድ ሳምንት ግድም ሆኖታል ስለተባለው ኮሌራም ሆነ በበሽታው ሳቢያ ስለደረሰ ጉዳት ከዩኒቨርሲቲውም ሆነ ከክልሉ ጤና ቢሮ ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ ባለመሳካቱ ሀሳባቸውን ማካተት አልተቻለም።ይሁን እንጂ አስተያየት የሰጡ ተማሪዎች በበሽታው ተይዘው ህክምና ሲደረግላቸው ነበሩ ከተባሉ መካከል አንዳንዶቹ እያገገሙ መሆናቸውን ገልጸዋል።

በዩኒቨርሲቲው ተከሰተ ስለተባለው ወረርሽኝ ለተማሪዎች በይፋ የተገለጸ ነገር የለም ። ይሁንና የበሽታዉ መንስኤ በአንድ በኩል "በውኃ ብክለት" በሌላ በኩል "የግል ንፅህና ባለመጠበቅ" የመጣ ነው የሚል አስተያየቶች ተሰምተዋል።በዚህም ምክንያት ተማሪዎች ወደ መመገቢያ አዳራሾች ሲገቡ ለጥንቃቄ እንዲታጠቡ ሲደረግ ነበር ተብሏል።

ከተከሰተ አንድ ሳምንት ግድም ሆኖታል ስለተባለው ኮሌራም ሆነ በበሽታው ሳቢያ ስለደረሰ ጉዳት ከዩኒቨርሲቲውም ሆነ ከክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት ይህ ዘገባ እስከተጠናከረበት ሰዓት የሞባይል ስልክ ባለመነሳቱ እና ባለመስራቱ ሳቢያ ሀሳባቸውን ማካተት አልተቻለም።በሶማሌ ክልል መቀመጫ ጅግጅጋ ከተማ የሚገኘው ይኸው ዩኒቨርሲቲ ከቀናት በኃላ የተማሪዎች ምረቃ መርሀ ግብር ያከናዉናል ተብሎ ይጠበቃል።

Via DW
@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ተለቀቀ‼️

የተወዳጁ ድምፃዊ ቴዲ አፍሮ "ቤዛ" የተሰኘ አዲስ ነጠላ ዜማ ተለቀቀ

ድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ከደቂቃዎች በፊት በይፋዊ ማህበራዊ ትስስር ገፁ "ቤዛ" የተሰኘ የህብረዝማሬ ሙዚቃ በድምጻዊዉ ይፋዊ የዩቲዩብ ገጽ መለቀቁን ኢትዮ መረጃ ተመልክቷል። ሙዚቃዉን ለማድመጥ ተከታዩን ሊንክ ይጠቀሙ።
https://youtu.be/DwVQSitEjMQ?si=BgodY40B6ovOiwA2

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ባህርዳር‼️

"ሕግ የማስከበር ዘመቻዉ በተሟላ ሁኔታ እየተከናወነ ነዉ"የአማራ ክልል የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ

በባሕርዳር ዙሪያ የመከላከያ ሠራዊትና የክልሉ የፀጥታ ኃይል በጋራ በመሆን ሰርጎ የገባዉን ጽንፈኛ ቡድን በየቤቱ የማሠስና የማፅዳት ሥራ ሲሠራ መቆየቱንና እየተሠራም መኾኑን የአማራ ክልል የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ አስታውቋል

ቢሮው ባወጣው መግለጫ"የጸጥታ ኀይላችን እርምጃ መቋቋም ያቃታቸዉ ጽንፈኞች ራሳቸዉን ለመከላከል የሚያደርጉትን የነፍስ አድን ተኩስ ማጥቃት እያደረጉ እንደሆነ አድርገዉ በሚታወቀዉ የዉጭና የዉስጥ ጽንፈኛ ሚዲያዎች እያስነገሩ ይገኛሉ፤ ሰሞኑን በጎጃም እና በሌሎች አንዳንድ ቦታዎች ላይ እየተወሰደባቸዉ ያለዉን እርምጃም እንዲሁ ማጥቃት እያደረጉ እንደሆነ ከዉጭ ላለዉ ጽንፈኛ አጋሮቻቸዉ የሀሰት ፕሮፓጋንዳቸዉን ሲነዙ ይስተዋላል።ይህ ፍጹም ከእዉነት የራቀ መረጃ ሲሆን የምንጊዜም ማደናገሪያቸዉ ነዉ" ብሏል።

በአሁኑ ሠዓት ሙሉ በሙሉ ባሕርዳር ከተማና አካባቢዉ ከጽንፈኛ ቡድኑ ጸድተዋል።እነዚህ ጽንፈኛ ቡድኖች የጸጥታ ኀይሉን ጥምረት መቋቋም አቅቷቸዉ ሙትና ቁስለኛ ሁነዉ የያዙትን መሳሪያ ሳይቀር እያንጠባጠቡ ሸሽተዋል ነው ያለው።

የመከላከያ ሠራዊት እና የክልሉ የጸጥታ ኀይሎችም ሕግ የማስከበር ሥራዉን በተሟላ ሁኔታ እየተገበሩ እንደሚገኙ አስታውቋል። በቀጣይም እየሸሹ እና እየተደበቁ ያለትን ጽንፈኛ ኀይሎች በያሉበት እያሰሰ ከተደበቁበት ጉሬ እያወጣ የክልላችን ሰላም ሙሉ በሙሉ ወደነበረበት ለመመለስ እየሠራ ነው ብሏል።

የክልሉ ሕዝብም አሁን የተገኘዉን አንጻራዊ ሰላም የተሟላ ለማድረግ ለሚደረገዉ ሕግ የማስከበር ዘመቻ ከመከላከያ ሠራዊት እና ከክልሉ የጸጥታ ኀይሎች ጎን በመቆም ዘላቂ ሰላምን እንዲያረጋግጥ መልእክት አስተላልፏል።

@sheger_press
ቴዲ አፍሮ‼️

ሙሉ ግጥም!!

ቤዛ (ኅብረ ዝማሬ)

ይህቺ ሰንደቅ ዓላማ የክብር ምልክት
ሥፋት እና ምልዓት ርቀት አላት
በዓላማ አንድ ሆና ሦስት ናት በመልክ

ሆ …..
ላላ ….

ቤዛ ለሀገር ቤዛ ሆነው አርበኞቹ
ያቆዩሽ ሀገር ጀግኖቹ
እናት ኢትዮጵያ

ቤዛ ለሀገር ቤዛ ሆነው አርበኞቹ
ያቆዩሽ ሀገር ጀግኖቹ
እናት ኢትዮጵያ

ብለን ተነስተናል ተስፋ አርገን ኹላችን
እኔ ለኔ ሳንል ቅድሚያ ለሀገራችን
እንደ ሐራሴቦን (ወጥተን ከሐራሴቦን) አንድ ዓላማ ይዘን
እንገባለን ከነዓን በፍቅር ተጉዘን

ቤዛ ለሀገር ቤዛ ሆነው አርበኞቹ
ያቆዩሽ ሀገር ጀግኖቹ
እናት ኢትዮጵያ

የጸና ነው በአንድነት ላይ መሠረታችን
አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ነው ባንዲራችን
ማነው ደፍሮ በዘር ቋንቋ የሚነጣጥለን
እኛ እንደሆን እማንለያይ አንድ ነን

የጸና ነው በአንድነት ላይ መሠረታችን
አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ነው ባንዲራችን
ማነው ደፍሮ በዘር ቋንቋ የሚነጣጥለን
እኛ እንደሆን እማንለያይ አንድ ነን

በዘር በሃይማኖት በማሰብ አንሰናል
ይብቃ በኛ ዘመን ታሪክ ይወቅሰናል
እንቁም ተያይዘን በአንድነት
በኢትዮጵያዊነት

ቤዛ ለሀገር ቤዛ ሆነው አርበኞቹ
ያቆዩሽ ሀገር ጀግኖቹ
እናት ኢትዮጵያ

ዓላማ ነው አንድ ያረገን እኛን
አንድ ያረገን እኛን (x2)
ቤታችን ናት አትንኳት ኢትዮጵያን
አትንኳት ኢትዮጵያን (x2)
የአንድነት ኃይል ጨለማን ድል ነሥቶ
ጨለማን ድል ነሥቶ (x2)
እናያለን አዲስ ፀሐይ ወቶ
አዲስ ፀሐይ ወቶ (x2)
በዝምታ ብንመስልም የተኛን
ብንመስልም የተኛን (x2)
ከተነሣን ማን ሊያቆመን እኛን
ማን ሊያቆመን እኛን (x2)
ከሷ በፊት ይፈሳል ደማችን
ይፈሳል ደማችን (x2)
ቀልድ አናውቅም እኛ በሀገራችን
በእናት ሀገራችን (x2)

ዓላማ ነው

ዓላማ ነው አንድ ያረገን እኛን
አንድ ያረገን እኛን (x2)
ቤታችን ናት አትንኳት ኢትዮጵያን
አትንኳት ኢትዮጵያን (x2)
ከሷ በፊት ይፈሳል ደማችን
ይፈሳል ደማችን (x2)
አትምጡብን በቃ በሀገራችን
በእናት ሀገራችን

―———————————————

ዜማ እና ግጥም — ቴዎድሮስ ካሳሁን ( ቴዲ አፍሮ)
ተጨማሪ የመግቢያ ዜማ — ቆየት ካለ ኅብረ ዝማሬ የተወሰደ
ሙዚቃ ቅንብር፣ ሚክሲንግ እና ሊድ ጊታር — በረከት ተስፋዝጊ (ቤኪ)
ቴነር ሣክስ — ዘሪሁን በለጠ
ማስተሪንግ — ማሩ ዓለማየሁ (ማርቨን ስቱዲዮ)
ተቀባዮች ፤
1. ምኞት ኃይሉ (ዲጄ ዊሽ)
2. ልዑል ሲሳይ
3. ግሩም ታምራት

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
አሳዛኝ መረጃ‼️

በሰሜን ጎጃም ሀገረ ስብከት በላይ ጋፊት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን 11 የቅኔ ተማሪዎች መገደላቸውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

በሜጫ ወረዳ ብራቃት ቀበሌ በሚገኘው በላይ ጋፊት  ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን የአብነት ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የነበሩ 11 የቅኔ ተማሪዎች  እንዲሁም 1 በግብርና የሚተዳደር የአካባቢው ነዋሪ ከመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት ተገድለው እንደሞቱ ተነግሯል።

የሟች ቤተሰቦች በሰጡቅ ቃል የካቲት 20 ቀን 2016 ዓ.ም ከሌሊቱ 6:00 ገደማ እንደሆነ ተማሪዎቹ በጎጇቸው ሳሉ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ፦

- " ፋኖን ታስጠልላላችሁ " ፣

- " ለፋኖ አባላት ጥይት የማያስመታ መድኃኒት ትሰጣላችሁ "

- " እናንተም የፋኖ አባላት ናችሁ " በማለት 11 ተማሪዎች እንዲሁም የጩኸት ድምፅ ሰምቶ ወደ ጉባኤ ቤቱ ሲሄድ የነበረን የአካባቢው ነዋሪ መግደላቸውን ገልጸዋል፤

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
አድዋ💚💛❤️

እንኳን ለ128ኛው የዓድዋ ድል በዓል ቀን አደረሳችሁ !

እኛ ኢትዮጵያዊያን ካሉን የጋራ አኩሪ ታሪኮች መካከል አንደኛው አድዋ ሲሆን አያት ቅድመ አያቶቻችን እምቢኝ አሻፈረኝ ሀገሬን ለወራሪ አሳልፌ አልሰጥም ብለው ከሁሉም የሀገሪቷ ክፍሎች ወደ ጦር አውድማ በመትመም በጀግንነት ተዋድቀው ጣሊያንን አሸንፈው ነፃ ሀገር አስረክበውናል ::

አድዋ ከኢትዮጵያም አልፎ የአፍሪካ የነፃነት ፣ የአንድነት፣ የድል ቀን ሆኖ በመላው አፍሪካ ሊከበር የሚገባው የድል ፣ የነፃነት ፣ የከፍታ ፣ የእችላለው ና የአልበገርም ባይነት መታሰቢያ የድል ቀን ነው " አድዋ የኛ የሁላችን የድል ቀን!

እንኳን ለ128ኛው የዓድዋ ድል ቀን አደረሳችሁ 🙏

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
"የትግራይ ክልል ምክር ቤት በመበተኑ የጠቅላይ ፍርድ ቤቱን የ6 ወራት ሪፖርት በሚዲያ ለማቅረብ ተገድጃለሁ" - የትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት

የትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ዶ/ር ፀጋይ ብርሃነና ምክትላቸው በትናንትናው ዕለት በሰጡት መግለጫ የጠቅላይ ፍርድ ቤቱን የስድስት ወራት ሪፖርት ምንም እንኳ ለክልሉ ምክር ቤት መቅረብ የነበረበት ቢሆንም በአሁኑ ሰዓት ምክር ቤቱ አለመኖሩን ተከትሎ ሪፖርቱ በሚዲያ ለማቅረብ መገደዳቸውን ተናግረዋል።

የምክር ቤቱ አለመኖርም የከፍተኛው ፍርድ ቤት የዳኞችን ሹመትና በሥነ ምግባር ጉድለት የሚቀጡ ሰዎችን ለማጽደቅ ከፍተኛ ሥልጣን የነበረው የትግራይ ክልል ምክር ቤት መፍረሱ ክፍተት መፍጠሩንና በዚህ ምክንያትም የህግ የበላይነት ማስከበር ላይ እንዲሁም የሰብአዊ መብት ጥሰቶች እንዲፈፀሙ እድል ፈጥሯል ሲሉም ዳጉ ጆርናል ከመግለጫቸዉ ሰምቷል ።

ከዚህ በተጨማሪ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ዶ/ር ፀጋይ እንደገለፁት ከሆነ የክልሉ ምክር ቤት ባለመኖሩ ምክንያት ለስራ እማይመቹ እንዲሁም መሻሻል ያለባቸው ህጎችነ ለማሻሻል አለመቻሉንና ይህም በዳኞችና ፍርድ ቤቶች ስራ ላይ ጫና እየፈጠረ ነው ብለዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
2024/10/04 11:28:21
Back to Top
HTML Embed Code: