Telegram Web Link
ጌታቸው ረዳ‼️

አቶ ጌታቸው ረዳ የህወሓት ምክትል ሊቀመንበር ሆነው መሾማቸዉ በመነገር ላይ ነዉ

ህወሓት ለሁለት ወር ገደማ የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች፣ የጊዝያዊ አስተዳደሩ አመራሮች እንዲሁም የክልሉ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች በተገኙበት ካካሄደው ስብሰባ በኃላ የተለያዩ ምንጮች የስልጣን ሽግሽግ ተደርጓል ሲሉ የቆዩ ቢሆንም ስለዚህ ጉዳይ ህወሓት ይፋዊ መግለጫ አልሰጠም።

ነገር ግን ቪኦኤ ትግርኛ የወ/ሮ ኬርያ ኢብራሂም ከፓርቲው መባረር ላይ አስመልክቶ በሰራው ዘገባው ላይ የጊዝያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝደንት አቶ ጌታቸው ረዳ የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር ሆነው እንዲሰሩ መሾማቸውን ለፓርቲው ቀረቤታ ካላቸው ሰዎች ለማወቅ ችያለው ሲል መዘገቡን ዳጉ ጆርናል ተመልክቷል።

የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ ወይዘሮ ፈትለወርቅ ገ/እግዚአብሔር ፣ ኢሳይያስ ታደሰ እና ወይዘሮ አልማዝ ገብረፃዲቅን ፓርቲው ለሚያካሂደው 14ኛው ፓርቲ ጉባኤ አዘጋጅ የኮሚቴዉ አባል አድርጎ መረጡ የሚታወስ ሲሆን ምናልባትም በባለፈው ስብሰባ የተደረገው የስልጣን ሽግሽግ በፓርቲው አሰራር መሰረት በጉባኤው ይፀድቃል ተብሎም ይጠበቃል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የኳታር እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ አይሮፕላኖች በሶማሊያ አየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ስህተት ምክንያት ከመጋጨት መትረፋቸዉ ተሰማ!።

በተመሳሳይ ከፍታ ርቀት ላይ በመጓዝ ላይ የነበሩት የኳታር እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ስህተት ምክንያት ከመጋጨት ለጥቂት መትረፋቸዉ ተነግሯል።

ንብረትነቱ የኳታር አየር መንገድ የሆነዉ አዉሮፕላን ( ኳታር 6 ዩ) ከዶሃ ተነስቶ ወደ ኡጋንዳ ኢንቴቤ በ 38,000 ጫማ ከፍታ ላይ ሲበር የነበረ ቢሆንም በሞቃዲሾ የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች አዉሮፕላኑ ወደ 40,000 ጫማ ወደላይ እንዲወጣ ተነግሮታል።

በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከቀኑ 6 : 32 ገደማ በተመሳሳይ በ39,000 ጫማ ከፍታ ርቀት ላይ ከአዲስ አበባ ተነስቶ ወደ ዱባይ ሲጓዝ ከነበረዉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዉሮፕላን ( ኢቲ 602) ጋር የተፋጠጠዉ የኳታር አዉሮፕላን ከመጋጨት ለጥቂት መትረፉ ተዘግቧል።

ሁለቱ ካፒቴኖች ስለ ክስተቱ ሲነጋገሩ የተቀረጹት ቅጂዎች ሁለቱም በሞቃዲሾ ከሚገኙ የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች የተሳሳተ መመሪያ እንደተቀበሉ ያሳያል ተብሏል።

በሁለቱም አውሮፕላኖች ላይ የተገጠመው የግጭት ማስወገጃ ሲስተም (TCAS) ወዲያውኑ ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል፣ ይህም በታዘዘው ከፍታ ላይ ሌላ አውሮፕላን መኖሩን በማመልከቱ ምክንያት በመቶዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ህይወት እንዲተርፍ ለማድረግ መቻሉ ዝግባዎች አመላክተዋል።

ይህን ተከትሎ በሞቃዲሾ የሚገኙት የፀጥታ ኃይሎች በሶማሊያ የሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን የሆኑትን ሙባረክ ኑር አሊን በቁጥጥር ስር እንዲዉል አደርገዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
አሳዛኝ መረጃ‼️

በዎላይታ ዞን ማምሻውን ባጋጠመ አስከፊ የትራፊክ አደጋ የ8 ሰው ሕይወት ማለፉ ተነገረ

በዛሬው ዕለት ምሽት 12:30 ገደማ መነሻውን ከአርባምንጭ ከተማ ወደ ሐዋሳ ከተማ በመጓዝ ላይ የነበረ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3 A 01784 ተሽከርካሪ በመገልበጡ በውስጡ የነበሩ የጤና ቡድን ስፖርተኞች ) ከተለያዩ ከመንግሥት ሠራተኞችና ከባለሀብት የተወጣጡ) በድንገተኛ የመኪና አደጋ በዎላይታ ዞን ዱጉና ፋንጎ ወረዳ ፋንጎ ኮይሻ ቀበሌ ልዩ ስሙ ዞንጋ ተብሎ በሚጠራበት አከባቢ የ8 ሕይወታቸው ስያልፍ ፣ 13 ከባድእና በ6ቱ ቀላል የአካል ጉዳት እንዳጋጠማቸው ሸገር ፕረስ ከዎላይታ ታይምስ ዘገባ ተመልክቷል።

በዎላይታ ዱጉና ፋንጎ ወረዳ ከፋንጎ ሁምቦ ቀበሌ እስከ ድምቱ እንዲሁም ከኤቱና ዳገት እስከ ቀርጨጬ ከተማ ድረስ ያለውን ጠመዝማዛና ቁልቁለታማ መንገድን በከፍተኛ ጥንቃቄ የሚያስፈልግበት ተብሏል።

Via Wolaita Times

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
3 ሚሊዮን‼️

ለ 4 ዓመታት ሲካሄድ የነበረው ባላገሩ ምርጥ ውድድር አክሊሊ አስፋው አሸናፊ ሆኗል::

በአጠቃላይ የ3 ሚሊዮን ብር ተሸላሚ ሆኗል::


በውጤቱ መሰረት

1ኛ አክሊሉ አስፋው
2ኛ ብሩክ ሙሉጌታ
3ኛ ቅዱስ ዳምጤ እና እስማኤል መሀመድ

እንኳን ደስ ያለህ @ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በጉራጌ ዞን በደረሰ የትራፊክ አደጋ የስድስት  ሰዎች ህይወት አለፈ

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምስራቅ ጉራጌ ዞን በመስቃን ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የስድስት ሰዎች ህይወት ማለፉን የክልሉ ፖሊስ ገልጿል።

በመስቃን ወረዳ  ጆሌ ቀበሌ ዲራማ ተብሎ በሚጠራዉ አካባቢ ትላንት እሁድ ከቀኑ 10 :00 ሰዓት ላይ አደጋ መድረሱን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ መምሪያ የሚዲያ ክፍል ኃላፊ ኮማንደር ታጁ ነጋሽ ለብስራት ሬድዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።

ከአዲስ አበባ ወደ ቡታጅራ ይጓዝ የነበረ ተሳቢ ከባድ ተሽከርካሪ ሰባት ሰዎችን ካሳፈረ ባለሶስት እግር ተሽከርካሪ በተለምዶ ባጃጅ ታክሲ ጋር በመጋጨቱ የአምስት ሰዎች ህይወት ወዲያዉኑ  አልፏል።

ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዉ ወደ ወራቤ ሪፈራል ሆስፒታል ከተላኩ ሁለት ሰዎች መካከል ደግሞ  የአንዱ ህይወት በማለፉ በአደጋዉ በአጠቃላይ የስድስት ሰዎች ህይወት ማለፉን ገልፀዋል።

አንድ ከባድ ጉዳት የደረሰበት ተጎጂ  በወራቤ ሪፈራል ሆስፒታል በህክምና እየተረዳ ይገኛል።በአደጋዉ ህይወታቸዉ ካለፈዉ ስድስቱ ሰዎች ሶስት ሴቶችና ሶስት ወንዶች  ናቸው። የአደጋዉ መንስኤ  እየተጣራ መሆኑን  ም/ኮማንደር ታጁ ነጋሽ ለብስራት ሬድዮና ቴሌቭዥን ጨምረው ተናግረዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በአማራ ክልል ከሕግ ውጪ ግድያ እንዲቆም እና ፈጻሚዎች ለሕግ እንዲቀርቡ አምነስቲ ጠየቀ‼️

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በአማራ ክልል እየተካሄደ ካለው ግጭት ጋር በተያያዘ በሰላማዊ ሰዎች ላይ ከሕግ ውጪ ይፈጽማል ያለውን ግድያ እንዲያቆም እና በድርጊቱ የተሳተፉ ተጠያቂ እንዲሆኑ ዓለም አቀፉ የመብት ተሟጋች አምነስቲ ኢንተርናሽናል ጠየቀ።

አምነስቲ ዛሬ ባወጣው አጭር ሪፖርት ላይ በአማራ ክልል ዋና ከተማ ባሕር ዳር በሰላማዊ ሰዎች ላይ ተፈጸሙ ያላቸውን እና መረጃ ያሰባሰበባቸውን ግድያዎችን በመጥቀስ የደረሱ ጉዳቶችን አቅርቧል።

በተለይ በግጭቱ የመጀመሪያ ወራት በባሕር ዳር እና አካባቢዋ በመከላከያ ሠራዊት ከሕግ ውጪ ግድያዎች መፈጸማቸውን የጠቀሰው አምነስቲ፣ በአንዳንድ ሁኔታዎች “ቤተሰቦች የሟቾችን አስከሬን በማንሳት እንዳይቀብሩ” እንደተከለከሉ በሪፖርቱ ላይ ገልጿል።

በሪፖርቱ ላይ የመከላከያ አባላት ባለፈው ዓመት ነሐሴ ላይ ቀበሌ 08 በተባለው አካባቢ አቡነ ሃራ እና ልደታ በተባሉ ሰፈሮች በስድስት ሰዎች ላይ የፈጸሟቸውን ከሕግ ውጪ የሆኑ ግድያዎችን መዝግቧል። በተጨማሪም በጥምት ወር መጀመሪያ ላይ ሰባታሚት በተባለ ስፍራ ሌሎች ስድስት ሰዎችን መግደላቸውን አመልክቷል።

በአማራ ክልል በመከላከያ ሠራዊት እና በፋኖ መካከል እየተካሄደ ባለው እና ወራትን ባስቆጠረው ግጭት ምክንያት ሰላማዊ ሰዎች ሰለባ መሆናቸውን ያመለከተው አምነስቲ፣ አስተማማኝ መረጃ ለማግኘት እንቅፋቶች እንዳሉም ጠቁሟል።

ግጭቱ በሰብአዊ መብቶች ላይ ያሳደረገውን ተጽእኖ ለመረዳት በመገናኛ ዘዴዎች መቋረጥ እና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የመናገር እንዲሁም የመገናኛ ብዙኃን ነጻነት ላይ ጫና በመፍጠር እና የበቀል እርምጃን መፍራት መረጃዎች በአዝጋሚ ሁኔታ እንዲወጡ እያደረገ ነው ብሏል።

አምነስቲ የአፍሪካ ቀንድ ተጠሪው ሱዑድ ኑር እንዳሉት የኢንተርኔት መቋረጥ ባለበት ሁኔታ ከርቀት ምርመራ ማካሄድ ከፍ ያለ ጥንቃቄን የሚሻ መሆኑን አመልክተው፣ ነገር ግን “በክልሉ እና በአገሪቱ ውስጥ ከሚካሄዱ ወታደራዊ ግጭቶች ጋር በተያያዘ የሚከሰቱ የመብት ጥሰቶችን መከታተላችንን እንቀጥላል” ብለዋል።

አምነስቲ ባሰባሰበው መረጃ መሠረት ከሕግ ውጪ የሚፈጸሙት ግድያዎች የሰዎችን በሕይወት የመኖር መብት ጥሰት እና ከባድ ዓለም አቀፍ የሰብአዊነት ሕግ ጥሰቶች መፈጸማቸቀውን እንደሚያመለክቱ በመግለጽ፣ እነዚህም በዓለም አቀፍ ሕግ መሠረት ከጦር ወንጀል ጋር የሚስተካከሉ ሊሆኑ ይችላሉ ብሏል።

የመብት ተቆርቋሪው ድርጅት በኢትዮጵያ የእንዲህ ዓይነት ወንጀል ፈጻሚዎችን ተአማኒ በሆነ የፍትህ ሥርዓት ተጠያቂ ባለመሆናቸው ተደጋግመው እንዲፈጸሙ ምክንያት መሆኑን ጠቅሶ፣ “በመላው አገሪቱ የሚታየውን የፍትህ መጓደል እንዲያበቃ እና ተጠቃቂነት እንዲሰፍን” ጥሪ አቅርቧል።
አምነስቲ ባለፈው ዓመት ነሐሴ እና በዚህ ዓመት ጥቅምት ወር ባሕር ዳር ውስጥ በመንግሥት ኃይሎች የተገደሉትን ሰዎች ቤተሰቦች እና የዐይን እማኞችን በማነጋገር ምስክርታቸውን በሪፖርቱ ውስጥ አካቷል።

በወታደሮች ግድያዎች ከተፈጸመ በኋላ ቤተሰቦች የሟቾችን አስከሬን እንዳያነሱ መከልከላቸውን እና ወታደሮቹ ከአካባቢው አስኪሄዱ ለረጅም ሰዓታት መጠበቅ እንደነበረባቸው እንዲሁም በተፈጠረባቸው ስጋት ሟቾችን በድብቅ ለመቅበር መገደዳቸውን ተናግረዋል ብሏል።

በዚህ ሪፖርት የመጀመሪያ ግኝት ላይ ከኢትዮጵያ መንግሥት ምላሽ ለማግኘት አምነስቲ ኢንትርናሽናል ቅጂውን ለፍትህ ሚኒስቴር እና ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መላኩን ነገር ግን ምላሽ አለማግኘቱን አመልክቷል።
አምነስቲ በክልሉ ውስጥ የሚፈጸሙ የሰብአዊ መብቶች እና ዓለም አቀፍ ሕግ ጥሰቶችን የሚያመለክቱ በርካታ ክስተቶች አየደረሱት መሆኑን ለቢቢሲ ገልጾ፣ በአማራ ክልል ሆነ በመላው አገሪቱ ሌሎቹንም የመብት ጥሰቶችን በምርመራ ይፋ ለማድረግ እየሠራ መሆኑን ሱዑድ ኑር ተናግረዋል።

ድርጅቱ በቅርቡ በሰሜን ጎጃም መርዓዊ ውስጥ ስለተፈጸመው ከሕግ ውጪ ግድያን በተመለከተ ሪፖርቶች እንደደረሱትን እና በአገሪቱ ውስጥ ሌላ ግድያ መከሰቱን መስማታቸው እንዳሳሰባቸው የጠቀሱት ሱዑድ፣ ክስተቱን መከላታላቸውን መቀጠላቻውን ገልጸዋል።

ከአማራ ክልል ዋና ከተማ ባሕር ዳር በቅርብ ርቀት ላይ በምትገኘው መርዓዊ ከተማ ጥር 20/2016 ዓ.ም. የመከላከያ ሠራዊት አባላት ቤት ለቤት አሰሳ በማካሄድ እና መንገድ ላይ ያገኟቸውን በርካታ ሰዎች መግደላቸውን ቤተሰቦች፣ የጤና ባለሙያዎች እና ነዋሪዎች ለቢቢሲ መግለጻቸው ይታወሳል።

የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ግን በሠራዊቱ ላይ ጥቃት ፈጽመው ወደ መኖሪያ አካባቢዎች ከገቡ ከፋኖ ጋር በተደረገ የተኩስ ልውውጥ የተገደሉት ታጣቂዎች ናቸው ሲል በሠራዊቱ ላይ የቀረበውን ክስ አስተባብሏል።

ካለፈው ዓመት አጋማሽ በኋላ የክልሉን ልዩ ኃይል ለመበተን እና ታጣቂዎችን ትጥቅ ለማስፈታት በመንግሥት የተላለፈውን ውሳኔ ተከትሎ በተለያዩ የአማራ ክልል አካባቢዎች የሚንቀሳቀሱት ግጭት ውስጥ መግባታቸው ይታወሳል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ያሳዝናል😭

ሰሞኑን እየሰማን የምንገኘው የመኪና አደጋ በጣም አስከፊ ሁኔታ ላይ ደርሷል‼️

በዱከም በደረሰ የመኪና አደጋ 7 ሰዎች በላይ ወዲያው ሲሞቱ፣ 11 ሰዎች ላይ ከባድ ለህይወት የሚያሰጋ ጉዳት ደርሷል።

ትናንት ከአርባምንጭ እየተመለሱ የነበሩ የሀዋሳ የጤና ቡድን የግርኳስ አባላት በመኪና አደጋ ህይወታቸው ማለፉ ይታወሳል።

እንዲሁ ትናንት በጉራጌ ዞን የስድስት  ሰዎች ህይወት ማለፉ መዘገባችን አይዘነጋም።

በመኪና አደጋ በአመት ከ 5000 በላይ ዜጎቻችንን እንደምናጣ ጥናቶች ያሳያሉ። ዋናው ምክንያት ከተገቢ ፍጥነት በላይ ማሽከርከር ነው።

ግድ የለም መድረሳችን ስለማይቀር
እባካቹ ያገራችን ሹፌሮች በርጋት አሽከርክሩ።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ትምህርት ሚኒስቴር በቅርቡ የተሰጠውን የመውጫ ፈተና የወሰዱ የግል እና የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎችን ውጤት ይፋ አድርጓል፡፡

በ2016 ዓ.ም አጋማሽ ዓመት የመውጫ ፈተና የወሰዱ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ከቅዳሜ የካቲት 16/2016 ዓ.ም ጀምሮ ውጤታቸውን ሲመለከቱ ቆይተዋል፡፡

የመውጫ ፈተናውን የወሰዱ የግል እና የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ውጤታቸውን ከዛሬ ጀምሮ መመልከት እንደሚችሉ ሚኒስቴሩ ከደቂቃዎች በፊት አሳውቋል፡፡

ውጤት ለማየት ተከታዩን ሊንክ ይጠቀሙ

https://result.ethernet.edu.et

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የአየር መንገዱ የሀገር ውስጥ መንገደኞች ማስተናገጃ ተርሚናል-1 ከነገ ጀምሮ ክፍት ይሆናል

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሀገር ውስጥ መንገደኞች ማስተናገጃ ተርሚናል-1 ከነገ ጀምሮ ለአገልግሎት ክፍት እንደሚሆን አየር መንገዱ አስታውቋል፡፡

የአየር መንገዱ የሀገር ውስጥ መንገደኞች ማስተናገጃ ተርሚናል-1 ከእድሳትና የማስፋፋት ስራ ሙሉ በሙሉ ለአገልግሎት ክፍት እንደሚሆን አየር መንገዱ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ይፋ አድርጓል።

በአየር መንገዱ ከአዲስ አበባ ወደ ሁሉም የሀገር ውስጥ መዳረሻዎች እንዲሁም ከሀገር ውስጥ ወደ አዲስ አበባ የሚያደረጉ በረራዎችን በዚህ ዘመናዊ ተርሚናል-1 ደንበኞቹ የተቀላጠፈ አገልግሎት እንደሚያገኙም ገልጿል፡፡

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በአማራ ክልል በጎጃም፣ ሰሜን ሸዋ፣ በሰሜን ወሎ እና በጎንደር ዞኖች በበርካታ አካባቢዎች በመንግሥትና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ግጭቶች ሲካሄዱ እንደሰነበቱ መስማቱን ጠቅሶ ቢቢሲ ዘግቧል።

ኹለቱ ወገኖች ካለፈው ሳምንት መጨረሻ ጀምሮ ከባድ ውጊያ ካካሄዱባቸው አካባቢዎች መካከል፣ በጎጃም ዞኖች መርዓዊ፣ ቋሪት፣ ደቡብ ሜጫ እና ደጋ ዳሞት፣ በሰሜን ሸዋ ዞን ሸዋ ሮቢትና አንጾቂያ እንዲኹም በሰሜን ወሎ ዞን የላሊበላ ዙሪያ አካባቢዎች እንደሚገኙበት ዓይን ምስክሮች መናገራቸውን ዘገባው አመልክቷል።

በሰሜን ጎጃሙ ግጭት ሳቢያ፣ መራዊ ከተማን ከባሕርዳር እና ፍኖተሰላም ጋር የሚያገናኙ መንገዶች ተዘግተዋል ተብሏል። መከላከያ ሠራዊት፣ በደቡብ ሜጫ "ጽንፈኛ" ባላቸው ኃይሎች ላይ ርምጃ እየወሰደና መንገዶችን እያስከፈተ መኾኑን ትናንት አስታውቆ ነበር።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የኢትዮጵያ የኃይማኖት ተቋማት ጉባዔ፣ ባለፈው ሳምንት በኦሮሚያ ክልል፣ ምሥራቅ ሸዋ ዞን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በዝቋላ ገዳም ባለፈው ሳምንት በአራት መነኮሳት ላይ የተፈጸመውን ግድያ ትናንት ባወጣው መግለጫ አውግዟል።

ጉባዔው፣ መንግሥት በመነኮሳቱ ላይ የተፈጸመውን የግፍ ግድያ አጣርቶ ተጠያቂዎችን ለፍርድ እንዲያቀርብና በስጋት ቀጠና ውስጥ ለሚገኙ አብያተ ክርስቲያናትና ሌሎች የኃይማኖት ተቋማት አስፈላጊውን ጥበቃ እንዲያደርግ ጠይቋል።

ጉባዔው ጨምሮም፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሐይማኖት ተቋማትና አባቶች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች፣ ግድያዎች፣ ኢሰብዓዊ አያያዞችና መዋቅራዊ በደሎች ሕጋዊ ተጠያቂነትን የሚያስከትሉ ኢፍትሃዊ ተግባራት እንደኾኑም ገልጧል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
2024/10/04 15:32:37
Back to Top
HTML Embed Code: