Telegram Web Link
ኑሮ ውድነት በመቀሌ ምን ይመስላል?

በሰሜን ኢትዮጵያ ለሁለት ዓመት በቆየው ጦርነት ምክንያት ከተጎዱ ክልሎች መካከል አንዱ ትግራይ ሲሆን በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ዜጎች ከመሞታቸው በተጨማሪ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል፡፡

ይህ ጦርነት በደቡብ አፍሪካ በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት በተደረገው የፕሪቶሪያ ስምምነት መሰረት ጦርነቱ የቆመ ሲሆን አገልግሎት ሰጪ ተቋማትም ዳግም ስራ ጀምረዋል፡፡

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳድር ከተቋቋመ በኋላ ከፌደራል መንግስት እና ከሌሎች መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት ጋር በመቀናጀት ተጎጂዎችን ለመርዳት እየተሰራም ይገኛል፡፡

ቀስ በቀስ ህይወት በትግራይ ከጦርነቱ በፊት ወደ ነበረበት ሁኔታ ለመመለስ የተለያዩ ጥረቶች እየተካሄዱ ሲሆን ኢትዮ ነጋሪ ወደ ክልሉ አምርታ በበርካታ ጉዳዮች ዙሪያ ምልከታ አድርጋለች፡፡

ከታዘብናቸው ጉዳዮች መካከል ህይወት በትግራይ መዲና መቀሌ ምን ይመስላል? የሚለው ሲሆን የኑሮ ውድነቱ በሀገር አቀፍ ደረጃ እያሻቀበ ቢሆንም በትግራይም ይህን አስተውለናል፡፡

ከጦርነት በኋላ መልሶ ማገገም ላይ ያለችው የመቀሌ ከተማ መሠረታዊ ሸቀጦች የሚባሉት ላይ ከፍተኛ የሆነ የዋጋ ጭማሪ እየተስተዋለ ይገኛል፡፡

በዚህም ጉዳይ ነጋዴዎችም ሆነ ሸማቾች በዋጋ አለመረጋጋት እና ውድነት እየተማረሩ እንደሆነ ገልጸዋል።

በከተማዋ ያነጋገርናቸው ነጋዴዎች እና ሸማቾች እንደሚሉት ከሆነ በየእለቱ የዋጋ መቀያየር እና አለመረጋጋት እንዳለ አስረድተዋል።

ፍራፍሬ ነክ ምርቶች፣ ስጋ እና መሰል ምግቦች ዋጋቸው እንደሚቀያየር አንስተው አሁን ላይ በመቀሌ አንድ ኪሎ ሙዝ በ60 ብር ፣ብርቱካን ከ120 እስከ 140 ብር እየተሸጠ እንደሚገኝ በምልከታችን አረጋግጠናል፡፡

የበሬ ስጋ በኪሎ እስከ 600 መቶ ብር እንደሚሸጥ ያስተዋልን ሲሆን ገበያው ቋሚ የሆነ ዋጋ ስለሌለው በየጊዜው የሚቀያየር እና የሚለዋወጥ መሆኑን ነጋዴዎች አንስተዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የዜጎች እገታ እና ግድያ “መንግስት ኃላፊነቱን ባለመወጣቱ”  እየተባባሰ ነው- የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ

ኢሰመጉ በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ፤ በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች ዜጎች ላይ በታጠቁ ቡድኖች እየተፈጸመ ያለው እገታ እና ግድያ "ከጊዜ ወደጊዜ እየጨመረ የመጣ እና ከፍተኛ የሆነ የሰብአዊ መብት ጥሰት እያስከተለ"ሲሆን ይህም "መንግስት ያለበትን የዜጎችን ደህንነት የመጠበቅ ኃላፊነት በአግባቡ እየተወጣ ባለመሆኑ” የመጣ ነው ሲል ገልጿል።

ለአብነትም የካቲቲ 11 ቀን 2016 ታጣቂዎችች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም ላይ በሚገኙ አምስት አባቶች ላይ የተፈጽመውን ግድያ ጉባዔው አስታውሷል። የካቲት 6 ቀን 2016 ከአጣዬ ተነስተው ወደ ኤፍራታናግድም ወረዳ በርግቢ ወደሚባል ቀበሌ"በመጓዝ ላይ የነበሩ ስድስት ሰዎች ላይ በአካባቢው በነበሩ ታጣቂ ኃይሎች ተገድለዋል"ብሏል።

ግድያውን የፈጸሙት ታጣቂዎችም ጥቃቱን ከፈጸሙ በኋላ ከአካባቢው የተሰወሩ መሆኑን ኢሰመጉ ካሰባሰበው መረጃ ማወቅ መቻሉንም አንስቷል።

ስለሆነም በዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ተቋማት በተሰጠው ምክረ ኃሳብ መሰረት ሰዎችን አስገድዶ ከመሰወር ለመጠበቅ የወጣውን ዓለም አቀፍ ስምምነት የኢትዮጵያ መንግስት ማጽደቅ አለበት ሲል ኢሰመጉ አጽንዖት ሰጥቷል።የኦሮሚያ ክልል መንግስት በክልሉ በታጣቂ ቡድኖች እየተፈጸመ ያለውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት"ከማውገዝ ባለፈ ስር ነቀል ሁሉን አቀፍ ክትትል በማድረግ ወንጀለኞችን ለህግ እንዲያቀርብ" የጠየቀው የመብቶች ጉባዔው፤ዘላቂ ሰላም ይመጣ ዘንድ በተለያዩ ቦታዎች የሚቀሳቀሱ ታጣቂ ቡድኖች ሰላማዊ መንገድን እንዲመርጡ ጥሪውን አቅርቧል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
መረጃ‼️

የአማራ ክልል የዛሬ ውሎና የዕለቱ ሰበርና ወቅታዊ መረጃዎችን እነሆ 👇

በዚ ሊንክ በዝርዝር ይመልከቱ👇👇

https://youtu.be/Oqc8jzmgj48
https://youtu.be/Oqc8jzmgj48
ኢትዮጵያ ብሔራዊ የህፃናት እና የፍልሰት ፖሊሲ እያዘጋጀች መሆኑ ተጠቆመ

የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት ተወካዮች የተሳተፉበት በሀገራት መካከል የህገ ወጥ ፍልሰትን መከላከል ላይ ያተኮር አውደ ጥናት በአዲስ አበባ መካሄዱን ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ሁሪያ አሊ ድንበር ተሻጋሪ ህገ ወጥ የህፃናት ፍልሰት ተጨማሪ አደጋ ይዞ ከመምጣቱ በፊት ሀገራት በትብብር ሊሰሩ ይገባል ማለታቸውን አስታውቋል።

ህፃናት ለዳግም ስደት ጭምር እየተዳረጉ ለጉልበት ብዝበዛ፣ ለአካላዊ እና ፆታዊ ጥቃት እየተጋለጡ ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታዋ በህገ ወጥ ፍልሰት ውስጥ ህፃናት በራሳቸው መወሰን ሰለማይችሉ ጉዳዩ የተለየ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ሲሉ መናገራቸውን አካቷል።ይህንን ለመቆጣጠር ኢትዮጵያ ብሔራዊ የህፃናት እና የፍልሰት ፖሊሲ እያዘጋጀች መሆኑንም አብራርተዋል ብሏል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ፤ ከሰዓቱን ወደ ጎረቤት ሀገር ኬንያ አቅንተው ናይሮቢ ገብተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በኬንያ ለሚያደርጉት ይፋዊ ጉብኝት ወደ ዝናባማዋ ናይሮቢ ሲደርሱ፤ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ አቀባበል አድርገውላቸዋል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

[ፎቶ፦ ስቴት ሃውስ ኬንያ]

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ሳልሳይ ወያነ ትግራይ የፓለቲካ ፓርቲ ህጋዊ እውቅና አገኘ።

የፓርቲው ከፍተኛ አመራር አቶ ዓብለሎም መለስ ዛሬ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ፤ "ሳልሳይ ወያነ ትግራይ የክልላዊ ፓለቲካ ፓርቲ የምዝገባና ህጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት አግኝቷል " ብለዋል።

ፓርቲው የምዝገባና ህጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ለሰጠው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያመሰገኑት ከፍተኛ አመራሩ ፣ ፓርቲው ለሚያካሂደው ፓለቲካዊ ትግል እውቅናው ምቹነት ይፈጥርለታል ብለዋል። 

ብሄራዊ ባይቶና ዓባይ ትግራይ ( ባይቶና ) የተባለ የትግራይ ተፎካካሪ ፓርቲ ባለፈው ጥር ወር 2016 ዓ.ም ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የክልላዊ ፓለቲካ ፓርቲ የምዝገባና ህጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ማግኘቱ መረጃ መለዋወጣችን ይታወሳል።
                
በኢንዱስትሪ ፓርኮች  የሚፈፀሙ  ፆታዊ ጥቃቶች  አሳሳቢ ሆነዋል ተባለ፡፡

በኢንደስትሪ ፓርኮች ውስጥ  በሚሰሩ  ሴት ሰራተኞ ላይ የሚፈፀም  ፆታን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶች  አሳሳቢ ሆኗል ተብሏል፡፡

ስብስብ ለሰብዓዊ መብቶች በኢትዮጵያ    ፃታን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶች አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሳቸውን ለኢትዮ ኤፍኤም  አስታውቀዋል ።

በሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌደሬሽን መረጃዎችን በማሰባሰብ ፤ስብስብ ለሰብዓዊ መብቶች በኢትዮጵያ   እንዳስታወቀው    በአዲስ አበባ፣ በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች በሚገኙ ኢንደስትሪ ፓርኮች  በሚሰሩ ሰራተኞች  ላይ ፃታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች አሳሳቢ ሆነዋል፡፡

ነፍሰ-ጡር እናቶችን  ለስራ ቅጥር ካለመፈለግ  አንስቶ    እዕድሜያቸው የገፉ ሴቶችን ማግለል፤ ወሲባዊ ትንኮሳዎች   ፤መድሎዎች  እና  መገለሎች    በአጠቃላይ  ምርመራ በተደረገባቸው ሶስቱም ፓርኮች ላይ ፃታን መሰረት ያደረጉ   ጥቃቶች   መኖራቸውን   የስብስብ ለሰብዓዊ መብቶች በኢትዮጵያ   ዳይሬክተር መሠረት አሊ ለጣብያችን ተናግረዋል።

ዳይሬክተሯ ይህንን  ችግር ለመፍታት   የሰራተኛ ፌዴሬሽኖችንና ማህበራት በጋራ ሊሰሩ ይገባል ያሉ ሲሆን ሰራተኞች ችግር ሲያጋጥማቸው ፍትህ ሊያገኙበት የሚችል ቦታ  እና ስረዓት   ሊዘጋጅ ይገባልም ብለዋል፡፡

ፃታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች  ምርመራ ከተደረገባቸው  ኢንዱስትሪ ፓርኮች በተጨማሪ አዲስ በሚከፈቱ ፋብሪካዎች፣ በሆቴል እና ቱሪዝም ኢንደስትሪ ውስጥ መበራከታቸውንም ጣቢያችን ኢትዮ ኤፍ ኤም ሰምቷል፡፡

እንደ ኢትዮጵያ ዕንባ ጠባቂ ተቋምና የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን /ኢሰመኮ/ ያሉ ተቋማትም በሰራተኛው መብት ላይ የሚፈፀሙ ጥቃቶችን ለማስቆም   መፍትሄ መፈለግ ይኖርባቸዋል ተብሏል፡፡ethio fm

@ethio_mereja_news
ኢትዮ መረጃ - NEWS
Photo
አንዳንድ ሰራተኞቹ ፎርጅድ ወይም እውቅና የሌለው የትምህርት ማስረጃ አላቸው የሚል መረጃ በቅርቡ የወጣበት ኢቢሲ መረጃውን ያወጣብኝ የቀድሞ ሰራተኞዬ "ተአማኒነቴ እንዲቀንስ አድርጓል" በማለት 10 ሚልዮን ብር ካሳ ይክፈለኝ ብሎ ከሷል።

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) አቶ ወገን አበበ የተባለ ግለሰብ "የኢቢሲ 400 ሰራተኞች ፎርጅድ የትምህርት ማስረጃ ነው ያላቸው" በማለት ስሜን አጥፍቷል፣ በዚህም ምክንያት የደረሰብኝን የ10 ሚልዮን ብር ኪሳራ ይክፈለኝ ብሎ ክስ እንደመሰረተ ከፍርድ ቤት ምንጮች፣ ከራሱ የኢቢሲ ሰራተኞች እንዲሁም ከአቶ ወገን ያገኘሁት መረጃ ያሳያል።

ለፌደራል የመጀመርያ ፍርድ ቤት፣ ኮልፌ ምድብ ፍትሀብሄር ችሎት መስከረም ወር 2016 ላይ የቀረበው እና የተመለከትኩት ይህ አቤቱታ እንደሚያትተው መረጃው የወጣበት ሰሞን የአዲስ አመት መዳረሻ ስለነበር ተቋሙ ማግኘት የሚገባውን ከፍተኛ ገቢ አቶ ወገን እንዲያጣ አድርገዋል ይላል።

ክሱ አክሎም "ተከሳሽ በፈጠሩት የስም ማጥፋት ዘመቻ ምክንያት የከሳሽን መስሪያ ቤት ተአማኒነት ከፍተኛ ጥርጣሬ ውስጥ በመክተታቸው፣ ወቅቱም የበአል ሰሞን እንደመሆኑ ከብር አስር ሚልዮን በላይ የሚሆን ገቢ እንዲያጣ ምክንያት ሆነዋል" ይላል።

በዚህ ተመሳሳይ ጉዳይ ከዚህ በፊት በወንጀል ተከሰው፣ ኋላ ላይ ግን ነፃ ወጥተው የነበሩት አቶ ወገን አሁንም በህግ ፊት ራሳቸውን ለመከላከል ዝግጁ እንደሆኑ ነግረውኛል።

አቶ ወገን እና ሌላ አንድ ግለሰብ ለፌደራል የስነምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የአንዳንድ የኢቢሲ ሰራተኞችን የትምህርት ማስረጃ ሀሰተኛነት ማስረጃ ማስገባታቸው ታውቋል።

በማስረጃው ላይ (የተወሰነው በምስሉ ላይ ይታያል... ስማቸውን አስቀርቼዋለሁ) በወር እስከ 47,000 ብር የሚከፈላቸው የትምህርት ማስረጃቸው ፎርጅድ የሆኑ ወይም እውቅና የሌለው የሆኑ ሰራተኞች እንዳለ ግለሰቦቹ ለፀረ-ሙስና አስረድተዋል።

እነዚህ ሁለት ግለሰቦች ያቀረቡት መረጃ "የተጭበረበረ ዲግሪ እንዲሁም ማስተርስ የትምህርት ማስረጃ በማስገባት መስርያ ቤቱ ላይ ለከፍተኛ የደሞዝ ወጪ ከመዳረግ ጀምሮ የባሰ ወደሚባል ደካማ መስርያ ቤት እያረገው ይገኛል" ብለዋል።

አክለውም "አመራሮች እኛ ባሳየነው መንገድ ተጠቅመው ወደ 320 ሰራተኛ እንዲጣራ ወደ ኢ.ፌ.ድ.ሪ ትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን ተልከው ውጤቱም ፎርጅድ መሆኑ ተረጋግጦ፣ መካከለኛ አመራሩም እነሱም እንደማይቀርላቸው ሲያወቁ ጉዳዩን ለማፈን እየጣሩ ነው። የጠቆምናቸው ሰራተኞችም ዛቻና ማስፈራርያ እያደረሱብን ነው" ብለዋል።

EliasMeseret

@sheger_press
@sheger_press
ሳልሳይ ወያነ ትግራይ ክልላዊ ፖለቲካ ፓርቲ ሁኖ በምርጫ ቦርድ ዕውቅና ተሰጠው

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለ ‘ሳልሳይ ወያነ ትግራይ’ የክልላዊ ፖለቲካ ፓርቲ የምዝገባና የሕጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት የካቲት 18 ቀን 2016 ዓ.ም. መስጠቱን አስታወቀ።

በኢትዮጵያ የምርጫ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ስነ ምግባር አዋጅ ቁጥር 1162/2011 ዓ.ም ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በተሰጠው ስልጣን መሰረት ለሳልሳይ ወያነ ትግራይ የክልላዊ ፖለቲካ ፓርቲ የምዝገባ እና ህጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት እንደ ሰጠው ቦርዱ አመላክቷል።

ፓርቲው በበኩሉ በማህበራዊ ትስስር የፌስቡ ገጹ ባሰፈረው መልዕክት ከአራት አመታት በፊት መሰረቱን ትግራይ ላይ አድርጎ የፖለቲካ ትግል መጀመሩን አውስቶ የካቲት 18 ቀን 2016 ዓ.ም ከምርጫ ቦርድ እውቅና ተሰጥቶናል ብሏል። ይህ እንዲሆን ያለሰለሰ ትግል ላደረጉት የፓርቲው አመራሮች፣ አባላት እና ደጋፊዎቹ በማመስገን እንኳን ደስ አላችሁ ብሏል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
አውሮፕላኑ ከኳታር አውሮፕላን ጋር ሊጋጭ ተቃርቦ ነበር ስለመባሉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ምላሽ ሰጠ‼️
በሶማሊያ አየር ክልል ውስጥ ሲበሩ የነበሩት የኢትዮጵያ እና የኳታር አየር መንገድ አውሮፕላኖች በሞቃዲሾ የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ስህተት ምክንያት ሊጋጩ ተቃርበው ነበር በተባለው ክስተት ዙሪያ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ምላሽ ሰጠ።

ቅዳሜ የካቲት 16/2016 ዓ.ም. ከአዲስ አበባ ወደ ዱባይ ሲጓዝ የነበረው የበረራ ቁጥር 602 አውሮፕላኑ በነበረበት ከፍታ ላይ የኳታር አውሮፕላን እየቀረበው እንደነበር መረጃ እንደተቀበለ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለቢቢሲ ሶማሊ በሰጠው ምላሽ ገልጿል።

ክስተቱን በተመለከተ ለተጨማሪ ምርመራ እንዲሁም የእርምት እርምጃ እንዲወሰድ ለኢትዮጵያ እንዲሁም ለሶማሊያ የሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣናት ሪፖርት መደረጉንም አየር መንገዱ አመልክቷል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሶማሊላንድ አቪዬሽን ባለሥልጣን ሁለቱ አውሮፕላኖች ለመጋጨት በአደገኛ ርቀት ነበር ላይ ስለመባሉ ያለው ነገር የለም።

ንብረትነቱ የኳታር የሆነው (ኳታር 6ዩ) አውሮፕላን ከቀኑ 6፡32 አካባቢ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን እየበረረ በነበረበት ከፍታ ላይ እየተቃረበ ነው የሚልም የትራፊክ አድቫይዘሪ እንደደረሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለቢቢሲ ሶማሊ በኢሜይል በሰጠው ምላሽ ገልጿል።

ከዶሃ ወደ ኡጋንዳ እየበረረ የነበረው የኳታር አውሮፕላን መጀመሪያ ላይ በ38 ሺህ ጫማ ሲበር የነበረ ቢሆንም፣ በዳታ ሊንክ በተሰጠው መረጃ ወደ 40 ሺህ ጫማ ከፍ እንዲል ፍቃድ እንዳገኘ ሪፖርት ማድረጉን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ጠቅሷል።

ይህ ክስተት በተፈጠረበት ወቅት በሁለቱ አውሮፕላኖች መካከል የነበረው ርቀት 23 ኪሎ ሜትር ርቀት ነበር ብሏል።

“ሁለቱም አውሮፕላኖች እጅግ ዘመናዊ የሆነ የግጭት መከላከያ ሥርዓት (ትራፊክ አቮይዳንስ ኮሊዥን ሲስተም) የተገጠመላቸው ሲሆን ይህ ከስተት በተፈጠረበት ወቅትም በሁለቱ አውሮፕላኖች መካከል የነበረው ርቀት 13 ናውቲካል ማይልስ (23 ኪሎሜትር) ነበር” ብሏል።

በተጨማሪም ሁለቱም አውሮፕላኖች በከፍታ ብቻ ሳይሆን በተጨማሪ በአግድመት ያላቸውን ርቀት የሚያስጠብቀውን ስትራቴጂካል ላተራል ኦፍሴት ፕሮሲጀር ስሎፕ በመተግበር ላይ እንደነበሩም ገልጿል።

ሁለቱም አውሮፕላኖች ላይ የተገጠመው የግጭት መከላከያ ሥርዓት ለሁለቱም አውሮፕላን አብራሪዎች መደረግ ስላለባቸው ጉዳዮችን የትራፊክ ምክር መረጃዎችን በተመለከተ የሚሰጠው ለጥንቃቄ ያህል እንደሆነ ነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ምላሽ ያስረዳው።

አብራሪዎቹ ይዘውት የነበረውን የበረራ መስመር ከፍታን ጠብቀው ጉዟቸውን ቀጥለው በሰላም በመዳረሻቸው ማረፋቸውን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ገልጿል።

ሲበርበት ከነበረውን ከፍታ እንዲጨምር ተደርጓል የተባለው የኳታር አየር መንገድ በበኩሉ ይህ ክስተትን በተመለከተ ለሚመለከታቸው ባለሥልጣናት ሪፖርት እንደተደረገም ለቢቢሲ ሶማሊ ገልጿል።

“በወቅቱም ከኳታር አየር መንገድ አሰራር ጋር በተጣጣመ መልኩ በአውሮፕላኑ ሠራተኞች ምላሽ ተሰጥቷል። በተፈጠረው ሁኔታ የአውሮፕላኑን ሠራተኞችንም ሆነ ተሳፋሪዎችን ደኅንነት ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ ነገር አልገጠመም” ሲልም ለቢቢሲ ሶማሊ በላከው የኢሜይል መልዕክት ገልጿል።(BBC)

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የሶማሊያው ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀሙድ ኬንያ፣ ናይሮቢ ገቡ።

ፕሬዝዳንቱ ናይሮቢ ጆሞ ኬንያታ ኤርፖርት ሲደርሱ የኬንያ ምክትል ፕሬዜዳንት ሪጋቲ ጋቻጓ ተቀብለዋቸዋል።

ሀሰን ሼክ ሞሀሙድ ዛሬ ኬንያ የገቡት በኬንያ በሚካሄድ የተባበሩት መንግስታት የአካባቢ ጥበቃ ጉባኤ (UNEA-6) ስብሰባ ላይ ለመካፈል ነው።

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድም ለይፋዊ ስራ ጉብኝት ኬንያ እንደሚገኙ ይታወቃል።

በቅርቡ ከኢትዮ-ሶማሌላንድ የመግባቢያ ስምምነት ጋር በተያያዘ ከኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጋር ቅራኔ ውስጥ የገቡት የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀሙድ ናይሮቢ ውስጥ ተገናኝተው ይወያዩ እንደሆነ የታወቀ ነገር የለም።

ኬንያ ሁለቱን መሪዎች ለማቀራረብ ጥረት እያደረገች እንደሆነም የሚታወቅ ነገር የለም።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በአዲስ አበባ አስተዳደር አራዳ ክፍለ ከተማ የፒያሳና አራት ኪሎ ነዋሪዎች ለልማት ከመኖሪያቸው እንደሚነሱ የክፍለ ከተማው አስተዳደር በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል።

አስተዳደሩ ኹለቱን አካባቢዎች መልሶ በማልማትና ነዋሪዎችን በማስነሳት ዙሪያ ትናንት ከነዋሪዎች ጋር ውይይት እንዳደረገ ገልጧል። ውይይቱ፣ በንግድ የሚተዳደሩ ነዋሪዎች ንግዳቸውን በሚቀጥሉበትና ሌሎች ነዋሪዎች በመልሶ ማልማቱ ዕቅድ በሚስተነገዱበት ኹኔታ ነበር ተብሏል።

ነዋሪዎችን ለልማት የማንሳቱን ሂደት የሚከታትል ከአመራሩና ከነዋሪዎች የተውጣጣ ኮሚቴም እንደተዋቀረ ተገልጧል። በተለይ የፒያሳ ነዋሪዎች በሦስት ወራት ውስጥ አካባቢውን እንዲለቁ እንደተነገራቸው እንዳንድ የአገር ውስጥ ዜና ምንጮች ዘግበዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
አራት ህጻናት

በቤንች ሸኮ ዞን በሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ማስተማሪያ ሆስፒታል አንዲት እናት በአንድ ጊዜ አራት ህጻናትን በሰላም መገላገሏ ታውቋል።

በቤንች ሸኮ ዞን በሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ልዩ መጠሪያው ኮሰኮል አከባቢ ነዋሪ የሆነችው ይቺ እናት ሦስት ወንዶችና አንድ ሴት ልጆችን በሰላም ተገላግላለች።

ህጻናቱ በሆስፒታሉ የእናቶችና ጨቅላ ህጻናት ህክምና ክፍል ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑ ተጠቁሟል።

ህፃናቶቹ እያንዳንዳቸው ከ1.3 እስከ 1.7 ኪሎግራም ክብደት እንዳላቸው ተጠቅሷል።(ዳጉ ጆርናል)

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ኢትዮጵያንና ኬንያ የጋራ ትብብር በሚያደርጉባቸው መስኮች ዙሪያ ትናንት ሰባት የመግባቢያ ስምምነቶችን ተፈራርመዋል።

ኹለቱ አገሮች የተፈራረሟቸው የትብብር ስምምነቶች፣ በባሕል ልማት፣ በቱሪዝም፣ በዱር እንሳት ጥበቃ፣ በወህኒ ቤቶች አስተዳደር፣ በነዳጅና ኢነርጂ ልማትና አቅም ግንባታ ላይ ያተኮሩ እንደኾኑ የፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ቤተመንግሥት ባሠራጨው መረጃ አስታውቋል።

ከትናንት ወዲያና ትናንት በኬንያ ጉብኝት ያደረጉት ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ፣ ዛሬ ለሦስት ቀናት ይፋዊ ጉብኝት ወደ ታንዛኒያ ያቀናሉ። [ዋዜማ]

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ትግራይ‼️

በትግራይ ክልል መቐለ ከተማ የሚገኙ ጡረተኞች ዛሬ ሐሙስ ባካሄዱት ሰላማዊ ሰልፍ፤ የ18 ወራት የጡረታ አበል ባለማግኘታቸው በአስከፊ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ገለጹ። የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር የጡረተኞችን ጉዳይ አጽንኦት ሰጥቶ ግዴታውን እንዲወጣ ሰልፈኞቹ ጠይቀዋል።

ቁጥራቸው 250 ገደማ የሚሆኑት ሰልፈኞች፤ መፈክሮችን፣ የትግራይ ክልል እና የፌደራል መንግስት ባንዲራዎችን አንግበው ዛሬ ረፋዱን በመቐለ ከተማ ጎዳናዎች ተዘዋውረዋል።

ሰልፈኞቹ ከያዟቸው መፈክሮች መካከል፤ “መንግስት ለጡረተኞች ራሱ ያወጣውን አዋጅ እና ደንብ ያክብር”፣ “ባለውለታ ይከበራል እንጂ በረሃብ እና በበሽታ አይቀጣም” የሚሉት ይገኙበታል።

በመቐለ ከተማ ከሚገኙ የተለያዩ የጡረተኛ ማህበራት የተውጣጡት ሰልፈኞች፤ ጥያቄያቸውን በመያዝ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ጽህፈት ቤት አምርተዋል። ሰልፈኞቹ ለአንድ ዓመት ከስድስት ወር የዘገየው ውዝፍ የጡረታ አበል እንዲከፈላቸው እና የጡረተኞች ቦርድ አመራሮች ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥያቄ አቅርበዋል። በጥቅምት 2015 ዓ.ም. በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ የተፈረመው የግጭት ማቆም ስምምነትም በአስቸኳይ ሙሉ በመሉ ተግባራዊ እንዲደረግም ጠይቀዋል።

የሰሜን ሪጅን ማህበራዊ ዋስትና እና የመንግስት ሰራተኞች ኤጀንሲ ለሰልፈኞቹ ጥያቄዎች በሰጠው ምላሽ፤ ጡረተኞች እስካሁን ያልተከፈላቸውን አበል እንዲያገኙ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር እና የፌደራል መንግስት እየተነጋገሩ መሆኑን ገልጿል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ በርካታ መንገደኞችን በማጓጓዝ ቀዳሚ ሆኗል‼️

@ethio_mereja_news
2024/10/04 17:19:48
Back to Top
HTML Embed Code: