Telegram Web Link
ሹመት‼️

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ ጥር 30፣ 2016 የሰጧቸው ሹመቶች፡

1. አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን - የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይረክተር
2. ትዕግስት ሃሚድ - የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢንሳ) ዋና ዳይረክተር

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ከኦነግ ጋር የተድረሰውን የአስመራ ስምምነት ያፈረሰው ዐቢይ አህመድ የሚመሩት መንግስት ነው- የኦሮሞ ነጻነት ግንባር

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ “ኦነግ ስራውን በሠላማዊ መንገድ እያካሄደ ነው፤ የፈረሰ ስምምነት የለም ” በማለት የምክር ቤቱ ስብሰባ ላይ የተናገሩትን የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) አወገዘ።

"ከፓርቲው እራሳቸውን ያገለሉና ብልጽግና የሾማውቸው ግለሰቦች ካልሆኑ በስተቀር፣ ከብልጽግና መንግስት ጋር ሥልጣን ተጋርተው በስራ ላይ ያሉ የኦነግ አመራሮች የሉም" ሲል የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ማስታወቁን አዲስ ማለዳ ዛሬ ካወጣው መግለጫ ተመልክታለች።

ኦነግ በመግለጫው “የኦሮሞ ነጻነት ግንባር እና በኢትዮጵያ መንግስት መካከል በአስመራ ተደርሶ የነበረውን ስምምነት ያፈረሰው ዐብይ አሕመድ ዋና መሪ የሆኑበት የኢትዮጵያ መንግስት ነው” ሲልም ወቅሷል።

የኢትዮጵያ መንግስት የጸጥታ ኃይሎች ለየትኛውም የፖለቲካ ድርጅት እና ቡድን ሳያደሉ የአገሪቱን ህገ መንግስት እና ህግጋት በማክበር ሁሉንም በእኩልነት እንዲያገለግሉ በወቅቱ ስምምነት ላይ ተደርሶ ነበር ሲልም የፖለቲካ ድርጅቱ አስታውሷል።

"በኦሮሞ ነጻነት ግንባር ስር ተደራጅቶ የሚገኘው ሠራዊት" (የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት) በተመለከተ ኦነግ ወደ ሃገር ቤት ሲገባ አብረው የጋራ ኮሚቴ  አቋቁመው ዓለም አቀፍ ህጎችን እና ደንቦችን በተከተለ ሁኔታ የታጠቁ ኃይሎች የሚዋሀዱበትን ስርዓት ተከትሎ እንዲፈጸም መግባባት ተችሎ እንደነበረም ገልጿል።

ሆኖም ግን “ኦነግ ከገባ በኋላ የሆነው እና ኦነግ ላይ የተፈጸመውን ክህደት መላው ህዝብ ሙሉውን መረጃ እንዳለው እናምናለን”  ሲል ኦነግ መግለጹን አዲስ ማለዳ ከመግለጫው ተመልክታለች።

በዚህም ኦነግ እንዳይንቀሳቀስ መከልከሉን እንዲሁም በተለያዩ ቦታዎች የሚገኙ ጽህፈት ቤቶች በጦር ሃይል እና ፖሊስ እንዲዘጉ መደረጋቸው፣ ዋናው መሥሪያ ቤት ከፍተኛ የድርጅቱ አመራሮችን ጨምሮ ሁሉም "በፊንፊኔ ፖሊስ ኃይል" እንዲወጡ ተደርገው እስከዛሬ ማንም ሰው እንዳይገባ ጽሐት ቤቱ ፊት ለፊት በፖሊስ እንደሚጠበቅ መደረጉን አመላክቷል።

የኦነግ አመራሮች እና የፖለቲካ ኦፊሰሮችና ባለስልጣናት ከመላው ኦሮሚያ ያልታሰሩበት የለም የሚለው ኦነግ፤ ይህን ጉዳይ እና ያለውን እውነታ በምርጫ ቦርድ የተቋቋመው ኮሚቴ ጉዳዩን መርምሮ ሪፖርቱን ለፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት እና ለሀገሪቱ ፓርላማ የዲሞክራሲ ኮሚቴ ሪፖርት ማስገባቱን ጠቁሟል።

እንዲሁም “በመላው አገሪቷ ውስጥ የተሰማሩት የብልጽግና ጦር፣ ፓርቲ ፖሊስ እና ሚሊሻ ኃይሎች ዜጎችን በፈለጉበት ቦታ መግደል፣ መደብደብ፣ መዝረፍ እና ቤቶቻቸው ማቃጠልን የእለት ተእለት ስራቸው አድርገውታል” ሲል ወቅሷል።

አዲስ ማለዳ ከመግለጫው እንደተመከተችው ኦነግ “የኢትዮጵያ መንግስታት የፖለቲካ ማምታታት ውጤት ኢትዮጵያን ለጦርነት፣ ረሃብ፣ ድህነት፣ መፈናቀል እና ውድመት የዳረገ እንደሆነ የአገሪቱ እና የመሪዎቿ ታሪክ ይገልጻል” ሲልም አክሏል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
መረጃዎች‼️

የዕለተ ሀሙስ መደመጥ ያለባቸው የምሽት ሰበር መረጃዎች አነሆ👇👇

በዚ ሊንክ ይመልከቱ👇👇

https://youtu.be/utf6X-RgSp8
https://youtu.be/utf6X-RgSp8
① በሕገወጥ ሰው አዘዋዋሪዎች አማካኝነት ወደ ኬንያ የገቡ ሦስት ኢትዮጵያዊያን ትናንት ሜሩ አውራጃ ውስጥ በተሽከርካሪ አደጋ ሕይወታቸው ማለፉን ዘ ስታር ጋዜጣ ፖሊስን ጠቅሶ ዘግቧል።

በአደጋው ሌሎች ስምንቱ ከባድ የመቁሰል አደጋ እንደደረሰባቸውና ወደ ሆስፒታል እንደተወሰዱ ዘገባው አመልክቷል።

በተያያዘ፣ ባለፈው ማክሰኞ በሰሜን ምሥራቅ ኬንያ ኢሴሎ አውራጃ ወደ ናይሮቢ በሕገወጥ ሰው አዘዋዋሪዎች አማካኝነት በታጠቁ ግለሰሶች ታጅበው በሞተር ሳይክል ሲጓዙ የነበሩ ስምንት ኢትዮጵያዊያን በፖሊስ እንደተያዙና ሌሎች ሰባት ኢትዮጵያዊያን ግን በታጠቁ አጃቢዎቻቸውና በፖሊስ መካከል የተኩስ ልውውጥ ሲደረግ ከአካባቢው እንዳመለጡ ተገልጧል። በመርሳቢት ግዛትም፣ በተመሳሳይ በታጣቁ ግለሰቦች ታጅበው ሲጓዙ የነበሩ 25 ኢትዮጵያዊያን ተይዘዋል ተብሏል።

② 42 ሱዳናውያንን አሳፍራ ስትጓዝ የነበረችው ጀልባ በትናንትናው እለት ጃቢኒያና በተሰኘ የቱኒዚያ የባህር ዳርቻ መስጠሟ ተገልጿል።

ከአደጋው ማትረፍ የተቻለው የሁለት ሰዎችን ህይወት ብቻ ሲሆን፥ የ27ቱ አስከሬን እስካሁን ባለመገኘቱ ህይወታቸው እንዳለፈ ተገምቷል።

የመንግስታቱ ድርጅት የፍልስተኞች ድርጅት መረጃ እንደሚያሳየው በ2023 በሜዲትራኒያን በኩል ወደ አውሮፓ ለመግባት የሞከሩ ከ2 ሺህ 270 በላይ ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።

ይህም ከ2022 በ60 በመቶ ጭማሪ አለው ያለው ድርጅቱ ሱዳንን ጨምሮ በበርካታ የአፍሪካ ሀገራት የሚታየው የሰላም መደፍረስ በርካቶች አደገኛውን ጉዞ እንዲመርጡ ምክንያት መሆኑን ገልጿል።(ዋዜማ እና አልአይን)

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ጋምቤላ ሙቀት በመጨመሩ የሥራ ሰዓት ለውጥ ተደረገ

በጋምቤላ ክልል የሙቀት መጠን እየጨመረ በመምጣቱ የመንግስት የስራ ሰዓት ላይ ከዛሬ ጀምሮ ለውጥ እንደሚደረግ የክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት አስታወቀ።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፒተር ሆው እንደገለጹት÷ በክልሉ የሙቀቱ መጨመር ለስራ ምቹ ባለመሆኑ ከየካቲት 1 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ለሶስት ወራት የሚቆይ የስራ ሰዓት ለውጥ ይደረጋል። በዚሁ መሰረትም ቀደም ሲል የመደበኛው የስራ ሰዓት ከጠዋቱ አንድ ሰዓት እስከ ስድስት ሰዓት ተኩል የነበረው ከአንድ ሰዓት እስከ አምስት ሰዓት ተኩል እንደሚሆን አስታውቀዋል።

እንዲሁም ከሰዓት በኋላ ከዘጠኝ ሰዓት እስከ አስራ አንድ ተኩል የነበረው ከአስር ሰዓት እስከ አስራ ሁለት ሰዓት ተኩል እንዲሆን መወሰኑን ገልጸዋል። የስራ ሰዓት ለውጡ በማጃንግ ዞን የመንገሽና የጎደሬ ወረዳዎችን እንደማይጨምር መግለጻቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

በተደረገው የሰዓት ማስተካከያ መሰረትም የክልሉ የመንግስት ሰራተኞች በተጠቀሰው የስራ ስዓት በተቋማቸው በመገኘት ሥራቸውን እንዲያከናውኑ አሳስበዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የአሜሪካ ኢምባሲ በኢትዮጵያ በአማራ ክልል ሰሜን ጎጃም መራዊ ከተማ የተፈፀመው ጥቃት በእጅጉ እንዳሳሰበው ገለፀ!!

የአሜሪካ ኤምባሲ በኢትዮጵያ ያለው ግጭት በአስቸኳይ እንዲቆምም ጠይቋል።
በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች ያሉት ግጭቶች፣ ከፍተኛ ሰብአዊ ሥቃይ እያስከተሉ መሆኑ በእጅጉ እንዳሳሰበው የገለጸው በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ፣ በአስቸኳይ እንዲቆሙ ጠይቋል፡፡

በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ጆሴ ማሲንጋ ሁለቱ ሀገራት የዲፕሎማሲ ግንኙነት የጀመሩበትን 120ኛ ዓመት አስመልክቶ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ደብዳቤ የጻፉት፣ አገራቸው በኢትዮጵያ ሰላም እና ልማት እንዲረጋገጥ ድጋፍ እያደረገች እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

በአምባሳደሩ ስለተጻፈው ደብዳቤ ለአሜሪካ ድምፅ ማብራሪያ የሰጡት፣ በኤምባሲው የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ኃላፊ ናዮሚ ፌሎውስ፣ በኢትዮጵያ ያሉት ግጭቶች በሰላም እንዲፈቱ አገራቸው ጥረት እንደምታደርግ ተናግረዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት ጌታቸው ረዳ፣ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል፣ጄኔራል ፃዳቅን እና ጄኔራል ታደሰ ወረደ አዲስ አበባ ገብተዋል!!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ የነበሩትን ስራዎች እና መሻሻሎች በጥልቀት እየገመገሙ ነው።

ባሳለፍነው ሳምንት የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር የፕርትሪያውን ስምምነት በተመለከተ ስለ ተፈናቃዮች መመለስ እንዲሁም በትግራይ ስለተከሰተው ድርቅ እና ርሃብ የፌደራል መንግሥት ያወጣቸውን መግለጫዎች መቃወሙ ይታወሳል።

ይህን ተከትሎ በተፈጠረው አለመግባባት ዛሬ አጠቃላይ ግምገማ ጀምረዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በምዕራብ ወለጋ ዞን እና በካማሽ መካከል በጸጥታ ችግር ተቋርጦ የነበረው የንግድና የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ- መከላከያ ሠራዊት

በካማሽ እና በምዕራብ ወለጋ ዞን መካከል በትጥቅ ውጊያ ሳቢያ ተቋርጦ የነበረዉ የንግድ እና የትራንስፖርት አገልግሎት መጀመሩን መከላከያ ሠራዊት ገለጸ።

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት እንዳስታወቀው በአካባቢው የተሰማራው ክፍለ ጦር የወሰዳቸው እርምጃዎች "በአሸባሪው" የሸኔ ቡድን ተዘግተው የቆዩ መንገዶች እንዲከፈቱ አድርጓል።

ቁጥሩ በወል ባልተገልጹ "ባለፉት ጥቂት ወራት" ውስጥ ከ200 በላይ የሸኔ አባለት ሲገደሉ የነፍስ ወከፍ መሳሪያዎችን ተተኳሾችንና ቦምቦችን መማረክ መቻሉን መከላከያ አሳውቋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ፓስፖርት‼️

ለተከበራችሁ ደንበኞቻችን፣ የፓስፖርት አቅርቦት ላይ ያሉ መዘግየቶችን እንረዳለን፣ ይህ ለሚፈጥረውም ቅሬታ ከልብ ይቅርታ እንጠይቃለን።

ተቋማችን ይህንን በፍጥነት ለመፍታት፣ ከኋላ ጀምረን ያልተመለሱ የፓስፖርት ጥያቄዎችን በመገምገም እና ምላሽ በመስጠት ያለመታከት 24 ሰአት እየሰራን እንገኛለን ሲል ኢሚግሬሽን አሳውቋል።

Notice

ዘወትር ቅዳሜ አዲስ ፖስፖርት አመልክተው አሻራ እና ፎቶ ሳይሰጡ እስከ 3 ወር ያለፈባቸውን ተገልጋዮች የምናስተናግድ መሆኑ ይታወቃል፡፡
ነገር ግን የፊታችን ቅዳሜ የካቲት 2/2016 ዓ.ም አገልግሎቱን የማንሰጥ ስለሆነ ይህንን አውቃችሁ ለአላስፈላጊ ወጭ እና እንግልት እንዳትዳረጉ እናሳስባለን ብሏል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
መረጃ‼️

የዕለተ ዓርብ መደመጥ የሚገባቸው ወሳኝ መረጃዎች እነሆ

በዚ ሊንክ ያድምጡ👇👇
https://youtu.be/9iAXevRQVYQ
https://youtu.be/9iAXevRQVYQ
በሸገር ከተማ የታሰሩ የሃይማኖት አባቶች ተጨማሪ አምስት ቀናት ተጠየቀባቸው

“መንበረ ጴጥሮስ” የተሰኘ “የኦሮሚያ ሲኖዶስ” ማቋቋማቸውን ተከትሎ፣ በኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ አስተዳደር በእስር ላይ የሚገኙት 11 የሃይማኖት አባቶች እና መዘምራን፣ ከትናንት በስቲያ ረቡዕ ለሁለተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ቀረቡ።

ጠበቃቸው አቶ ዮሐንስ ጌታሁን ለአሜሪካ ድምፅ ዘጋቢ እንደገለፁለት ከሆነ ፍርድ ቤቱ ለፖሊስ ተጨማሪ ምርመራ አምስት ቀናት በመፍቀድ ለየካቲት 5 ቀን 2016 ዓ.ም. ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ተጨማሪ 30 ቀናት ተሰጠ!

የኢትዮጵያ ዜግነት ሳይኖራቸው ከተፈቀደላችሁ ጊዜ በላይ በኢትዮጵያ ለቆዩ፣ ሀሰተኛ የትውልደ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ይዘው እየተንቀሳቀሱ ለሚገኙ፣ ሀሰተኛ የካምፓኒ ምዝገባ በማድረግ ቪዛ እና የመኖሪያ ፍቃድ ለወሰዱ፣ እንዲሁም ሌሎችም ህጋዊ ያልሆኑ መረጃዎችን ይዘው ለሚንቀሳቀሱ ሁሉ!  ከጥር 1 እስከ ጥር 30 ቀን 2016 ዓ.ም ባሉት 30 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋናው መ/ቤት በአካል ቀርበው  ህጋዊ ሰነድ መያዛቸውን እንዲያረጋግጡ የጊዜ ገደብ መሰጠቱ ይታወሳል።ሆኖም የተሰጠው ጊዜ እንዲራዘም የተለያዩ ጥያቄዎች በመቅረባቸው ተቋሙ ቀኑን ማራዘም አስፈላጊ ሆኖ አግኝቶታል።

በመሆኑም  አስቀድሞ እስከ ጥር 30 ብቻ የተባለው ለአንድ ተጨማሪ ወር መራዘሙን የኢግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት እያሳወቀ በዚህ መሰረት እስከ የካቲት 30 ቀን 2016 ባሉት ተከታታይ የስራ ቀናት በዋናው መ/ቤት በአካል በመቅረብ ወደ ህጋዊ ስርዓት እንዲገቡ ጥሪ የሚያቀርብ ሲሆን  ይህን በማያደርጉ አካላት ላይ ተቋሙ በህግ በተሰጠው ስልጣን መሰረት እርምጃ እንደሚወስድ በጥብቅ ያሳውቃል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ወራቤ ዩኒቨርስቲ‼️

በወራቤ ዩኒቨርሲቲ ዶርም የእሳት አደጋ መነሳቱ ተሰማ።

በዛሬው ዕለት በወራቤ ዩንቨርስቲ ብሎክ 10 ተብሎ የተሰየመው እና የሬሚዳል ወንዶች ይኖሩበት የነበረው ህንፃ ላይ የእሳት አደጋ ተነስቷል። እስከአሁን ያልጠፋ ሲሆን የብዙ ተማሪዎች ንብረት ወድሟል ተብሏል። እሳቱን ለማጥፋት እየተረባቡ ነው።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
መርጌታ ቃለ ህይወት  የባህል መዳኒት ቀማሚ እና መስተፋቅር እንሰራልን በሁሉም ከተሞች ያላችሁ አናግሩኝ:

መርጌታ ቃለ ህይወት የባህል መድህኒት አስማት እና ጥበብ ይፈልጋሉ:
የምንሰጣቸው የጥበብ አገልግሎቶች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል
1 ለመፍትሔ ስራይ
2 ለህማም
3 ጋኔን ለያዘው ሰው
4 ቡዳ ለበላው
5 ለቁራኛ
6 የዛር ውላጅ ለተዋረሰው
7 ለአይነ ጥላ
8 ነገረ ራዕይ(ራዕይ የሚያሳይ)
9 ለዓቃቤ ርዕስ
10 ለመክስት
11 ለቀለም(ለትምህርት)
14 ለመስተፋቅር
15 ለሁሉ ሠናይ
16 ለገብያ
17 ለአምፅኦ ብእሲት(ፍቅረኛ ላጣ ወይም ላጣች የሚሰራ)
18 ለመድፍነ ፀር
19 ሌባ የማያስነካ
20 ለበረከት

ውድ  ቤተሰቦች  ለማንኛውም ነገር ያማክሩን    ከስላምታ ጋር።
ከምሰጣቸው በትንሹ ይህን ይመስላል 
ለጥያቄወ 09 75-90-23-15
በኢትዮጵያ የሚሰሩ ፊልሞች የአገርን ገጽታ ከማስተዋወቅ አንጻር ክፍተቶች እንዳሉባቸው ተጠቆመ

በኢትዮጵያ ተሰርተው ለእይታ የሚበቁ ፊልሞች በበርካታ ችግሮች የተተበተቡ ስለመሆናቸው የዘርፉ ባለሙያዎች ይገልጻሉ፡፡ የበጀት እጥረት፣ ለፊልም ኢንዱስትሪው የተሰጠው ትኩረት፣የይዘት ችግርና ኢትዮጵያዉያን ወግን ከግምት ያስገቡ ፊልሞች አለመሰራት ዋነኛ ችግር ተደርገውም ይነሳሉ፡፡

የፊልም ዳይሬክተርና ደራሲ አብዲሳ ምትኩ ለፊልም ኢንዱስትሪው አለማደግ ዋነኛ ተጠያቂ የዘርፉ ባለሙያ መሆኑን በመግለጽ ከይዘት አለማደግና ተገቢውን መልእክት በፊልሙ አለማስተላለፍ መቻል የኢትዮጲያ ፊልሞች አይነተኛ መገለጫ መሆኑን በመግለጽ ይህን ችግር ለመፍታት የተሄደበት ርቀት እዚህ ግባ የሚባል አለመሆኑን ያነሳል፡፡

ሌላኛው የፊልም ባለሙያ ሳሙኤል እንዳልካቸው ከፍተኛ የሃሳብ ውስንነት በፊልሞቻችን ላይ እንደሚስተዋል በመግለጽ ይህን ችግር ለመፍታት አይነተኛ መፍትሄው የሃሳብ ፈጠራ አቅምን ማሳደግ ሊሆን እንደሚገባ ይገልጻል፡፡

የሌሎች አገራት ተሞክሮ የሚነሳው ባለሙያው ኢትዮጵያዊ የፊልም ባለሙያም ለፊልም ስራ ተገቢውን ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባው አንስቷል፡፡

ባለፉት 4 ዓመታት ኮቪድ 19 ወረርሽኝና ከሲኒማ ቤቶች ጋር ያለው የትርፍ ክፍፍል ፍትሃዊ አለመሆን በፊልም ስራው ላይ የራሱን አሉታዊ ተጽእኖ እንዳሳደረ ይገለጻል፡፡ በመንግስት በኩልም ለፊልም ስራ የተሰጠው ትኩረት አናሳ መሆን ዘርፉን እንደጎዳው ተደጋግሞ የሚገለጽ ጉዳይ ነው፡፡

በተጨማሪም ገንዘብ ተኮር ብቻ የሆኑ የፊልም ስራዎች በስፋት መሰራታቸዉ ለፊልም ኢንደስትሪዉ መዳከም አንዱ ምክንያት ነዉ፡፡

(መናኸሪያ ሬዲዮ)

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
2024/10/05 03:23:31
Back to Top
HTML Embed Code: