Telegram Web Link
መንግሥት ከፋኖ ታጣቂ ጋራ ቀጥተኛ ውይይት እንዲያደርግ ተጠየቀ!!

ከኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት እና የክልል ርእሳነ መስተዳድሮች ጋራ የተወያዩት የአማራ ክልል ከተሞች ነዋሪዎች፣ መንግሥት ከፋኖ ታጣቂዎች ጋራ ቀጥተኛ ውይይት ቢያደርግ የተሻለ ሰላም ሊመጣ እንደሚችል ተናግረዋል፡፡

ባለሥልጣናቱ፣ ከክልሉ የ15 ከተሞች ነዋሪዎች ጋራ፣ ትላንት እሑድ በወቅታዊው የክልሉ የጸጥታ ችግሮች ላይ ተወያይተዋል።

ውይይቶቹን በበጎ እንደሚመለከቷቸው የገለጹ የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው ተሳታፊዎች፣ ሆኖም፣ “ከታጣቂ ቡድኑ ጋራ ቀጥተኛ ውይይት ቢደረግ የተሻለ ሰላምን ያመጣል፤” ብለዋል።

ውይይቶቹ የተካሔዱት፣ በክልሉ የታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ፣ ለተጨማሪ አራት ወራት ከተራዘመ ከሁለት ቀናት በኋላ ነው።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በፀጥታ ጉዳይ ጠቅላይ ሚንስተሩ ለፓርላማው ከሰጡት ማብራሪያ ዋና ዋና ነጥቦች

👉 የኢትዮጵያን ሰላም የሚያውኩ አንኳር ጉዳዮች የፖለቲካ ፍላጎትን ለማሳካት የሚኬድባቸው መንገዶች ችግር ያለባቸው መሆኑ ነው፤

👉 ማንኛውም ችግር ሲያጋጥም ያንን ችግር ለመፍታት በንግግር ለመፍታት ያለን ልምምድ እየቀነሰ መምጣትም ሌላው ችግር  ነው፤

👉 ለሰላም ለሚደረግን ጉዞ ወጥመድ የሚቀመጥበት ልምምዱም የሰፋ መሆኑ ሌላ ችግር ነው፤

👉 እነዚህ ችግሮች አብዛኛው የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ማዕከል አድርጎ የሚነሳ አይደለም፤ ቢሆን ኖሮ ለቀይ ባህር  እድል ለመፍጠር የምናደርገውን ጥረት ባልተቃወሙት ነበር፤

👉 ታንዛኒያ ከሸኔ ጋር የነበረውን ድርድር ስንጀምር ለመላው ህዝብ ነግረን አሳውቀን ሳንደብቅ ነው፤ ውጤቱ ግን ምንም የሚጨበጥ ስላልሆነ ምንም ማለት አልቻልንም፤

👉 ሸኔ በአስመራ በነበረው ድርድር ቃል የተገባው ሳይፈጸም ቀርቶ ከሆነ ጫካ የገባው፤ እታገላለሁ የሚልለትን ህዝብ ማገትና ማሰቃየት ላይ ነው፤ የራስን ህዝብ እያሰቃዩ እታገልልሃለሁ ማለት ዋጋ የለውም፤

👉  ከዚህ በኋላ ኢትዮጵያ ውስጥ በጠበንጃ ስልጣን መያዝ አይቻልም፤ የሚቻለው በሰላም በንግግር ነው፤

👉 በአማራ ክልል በሁሉም ዞኖች ከከሚሴ በስተቀር ከህዝብ ጋር ለመነጋገር እድል አግኝቻለሁ፤ ጥያቄያቸው የልማት፣ የወሰን ይገባኛል እና የህገ መንግስት ነው፤

👉 በአማራ ክልል ባለፉት አምስት አመታት 3 ሺህ 200 ኪሎሜትር መንግድ ጀምረነ እየሰራን ነው፤

👉 ይህ መንገድ በክልሉ ውስጥ  ዞንን ከዞን ወረዳን ከወረዳ  ጋር የሚያገናኝ ነው፤

👉 ይህ መንገድ አንድ ሽሮ ፈሰስ የሚባል አይደለምዐ ከትውልድ ትውልድ የሚተላለፍ ነው፤

👉 ከአማራ ክልል የተነሳውን የልማት ጥያቄ ለመመለስ መንግስት የሄደበትን ርቀት አመላካች ነው፤ በቂ አይደለም፤

👉 ከመንገድ ባሻገር በቱሪዝም መስክም የጎርጎራ ፕሮጀክት በአይነትና በደረጃው የትም ያልተሰራ ፕሮጀክት ሆኖ እየተሰራ ነው፤

👉 የላሊበላን ቅርስም ለማደስ የፈረንሳይን ፕሬዝዳንት ሳይቀር ይዘን ሄደነ አሳይተነ እያሰራን ነው፤ በሰላም ምክንያት ወጣ ገባ ቢልም፤

👉 ፋሲልንም የፈረሰውን ማስጎብኘት ተገቢ አይደለም ብለን፤ ስራውን ለማስጀመር ሙከራ አድረገነ ነበር፤ ነገር ግን በተለያዩ አሉባልታዎች ስራውን አስቁመውታል" ብለዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ድርቅን እንደ ፖለቲካ መጠቀም ፍፁም ስህተት ነው፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ከተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለተነሳላቸው ጥያቄዎች ምላሽ እየሰጡ ይገኛሉ፡፡

ድርቅን በተመለከተ ከሰጧቸው ምላሹች መካከል

•ዘንድሮ በትግራይ፣በአማራ እና ኦሮሚያ በተወሰነ አካባቢ ድርቅ ተከስቷል፡፡

•ለድርቁ ትኩረት መንግስት አልሰጠውም ይላሉ መንግስት ግን 15 ቢሊዮን ብር ወጮ አድጓል ሲሉ ተድምጠዋል፡፡

•በመሆኑም የተከሰተውን ድረቅ ለፖለቲካ መዋል ትክክል አየይደለም ሲሉም ተናግረዋል፡፡

•ወደ ትግራይ ክልል ከ500ሺህ ኩንታል በላይ ልከናል ይህንን የክልሊ መንግስት ከፍተኛ ችግር ወዳለባቸው ማከፋፈል ነው ያለበት ብለዋል፡፡

•ድርቅ በየአስር ዓመቱ በኢትዮጵያ ይከሰት ነበር ቀጥሎ በሰባት ዓመት ሆነ ቀጥሎ በሶስት ዓመት ድርቅ ይከሰታል፡፡

•ድርቅና ርሃብ የሚለውን ግን መለየት አለብን፡፡

•ተባብረን ሰው እንዳይሞት መረባረብ ነው ያለብን እንጂ ድርቁን ፖለቲካዊ ማድረግ ረገቢ አይደለም ብለዋል፡፡

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
“ኢትዮጵያ እዳዋን እንዳትከፍል ችግር የሆነባት አራጣ ነው”-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ

አራጣ(commercial loan) ማለት የተበደሩትን ገንዘብ በአብላጫ ጨምሮ መክፈል ሲሆን ችግር የሆነውም የብድሩ ገንዘብ የታሰበውን ስራ ሳይሰራ መመለስ አለመቻሉ ነው ሲሉ ጠቁመዋል።

አክለውም ኢትዮጵያ ከ2011 እስከ 2015 ዓ.ም ድረስ 9.9 ቢሊዮን ዶላር እዳ ከፍላለች ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ኢትዮጵያ መክፈል አቅቷታል የተባለው 33 ሚሊየን ዶላር የአየር መንገዳችን የሁለት ቀን ገቢ ነው ብለዋል።

በአንጻሩ የኢትዮጵያ መንግስት እ.ኤ.አ በ2014 በዩሮ ቦንድ ከተበደረዉ የ1 ቢሊዮን ዩሮ እና ወለዱን 33 ሚሊዮን ዶላር ገንዘብ የመክፈል አቅሙ በአበዳሪዎች ጥርጣሬ ዉስጥ መግባታቸዉ ይታወሳል።

በተጨማሪም ኢትዮጵያ ዛምቢያንና ጋናን በመከተል በአፍሪካ ዕዳቸውን መክፈል ካልቻሉ አገራት ተርታ ልትቀላቀል ከጫፍ የደረሰች መሆኑን በቅርቡ ብሉምበርግ ዘግቦ ነበር።

አዲስ ማለዳ

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ዝቅተኛ የደመወዝ ወለልና ግብር ቅነሳን በተመለከተ ምላሽ እየጠበቀ መሆኑን የሰራተኛ ማህበራት ኮንፌደሬሽን ገለጸ


ዝቅተኛ የደመወዝ ወለልና ግብር ቅነሳን በተመለከተ የፍትሕና የገንዘብ ሚኒስቴርን ምላሽ እየጠበቀ መሆኑን የኢትዮጵያ ሰራተኛ ማህበራት ኮንፌደሬሽን አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ሰራተኛ ማህበራት ኮንፌደሬሽን ለሰራተኞች የዝቅተኛ ደመወዝ ወለል እንዲቀመጥና ሰራተኛው ላይ የተጫነው ግብር እንዲቀነስ ጠቅላይ ሚኒስትሩን መጠየቁ ይታወሳል።

ይህንን ተከትሎ በሁሉም የቀረቡ ጥያቄዎች ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለተለያዩ ተቋማት አቅጣጫ ሰጥተዋል የሚሉት የኮንፌደሬሽኑ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አያሌው አህመድ እስካሁን የተሰጠ ምላሽ እንደሌለ ተናግረዋል።

አቅጣጫ ከተሰጣቸው ተቋማት መካከል የገንዘብ ሚኒስቴር እና የፍትህ ሚኒስቴር ተጠቃሽ ሲሆኑ ከተቋማቱ የሚሰጠውን ምላሽ እየተጠባበቅን ነው ብለዋል፡፡

ኮንፌዴሬሽኑ ጉዳዩን እየተከታተለ ነው ያሉት አቶ አያሌው፥ የሚዘገይ ከሆነ በድጋሚ ጠቅላይ ሚኒስትሩን እንደሚጠይቁም ገልፀዋል።

የኑሮ ውድነቱ በየጊዜው እየተባባሰ ሰራተኛው ቤተሰቡን ለማስተዳደደርም ሆነ እራሱን ለመደጎም መቸገሩን በመጥቀስም፥ ለዚህ ጉዳይ አፋጣኝ ምላሽ እንደሚያስፈልግ አንስተዋል።

Aradafm
ወደ አሜሪካ ተመልሰዋል 

ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገቡ በመከልከላቸዉ ወደ አሜሪካ መመለሳቸውን ተናግረዋል።
ወደ ሀገር እንዳይገቡ የተከለከሉበት ምክንያት እስካሁን አልታወቀም።

ወደ ሀገር እንዳልገባ ከልክለውኝ በመጣሁበት አውሮፕላን እየተመለስኩ ነው"--- ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ከደቂቃዎች በፊት በስልክ ከነገሩኝ የተወሰደ ሲል ኤሊያስ መሰረት በገፁ ያሰፈረው መረጃ ነው።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ጠ/ዩ ተሳደቡ‼️

ተዋርዳቹ እኔንም አዋረዳቹኝ ወራዶች ናቹ ዶ/ር ዐብይ በዝርዝር ያድምጡ👇👇

https://youtu.be/Oc7FZuMNqGc
https://youtu.be/Oc7FZuMNqGc
"የተገደሉ ሰዎች ቁጥር ከ157 በላይ ነው"--- በመርአዊ ከተማ የሚገኙ የህክምና ባለሙያ ከሰጡኝ መረጃ የተወሰደ

ባሳለፍነው ሳምንት ሰኞ እለት ከንጋት ጀምሮ በመንግስት ሀይሎች እና በፋኖ ታጣቂዎች መሀል በመርአዊ ከተማ የተካሄደን ውጊያ ተከትሎ በከተማዋ ነዋሪዎች ላይ በተፈፀመ ግድያ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 157 መሆኑን አንድ ለደህንነታቸው ሲባል ስማቸውንም ሆነ የሚሰሩበትን የጤና ማዕከል እንዳልጠቅስ የጠየቁኝ የህክምና ባለሙያ አሳውቀውኛል።

ባለሙያው ሁኔታውን ሲያብራሩ "አብዛኞቹ ሟቾችን መልካቸውን እንኳን ለመለየት አልተቻለንም ነበር... በህይወቴ አይቼው የማላውቅ ከባድ ነገር ነበር" ብለዋል።

አንድ ሌላ የከተማው ነዋሪ ደግሞ የመንግስት ሀይሎችን ለድርጊቱ ተጠያቂ አድርገው ቀደም ብሎ የፋኖ ታጣቂዎች የወታደሮች መኖርያ ላይ ጥቃት አድርሰው ነበር የሚባል መረጃ በህዝቡ ዘንድ እንዳለ ጠቅሰዋል።

"የተረሸኑት ንፁሀን ከቤታቸው ጭምር ተጎትተው እንዲወጡ ተደርጎ ነው፣ እስከ እሮብ ድረስ ሬሳ ከየቦታው ሲለቀም ነበር" ብለዋል። አሁን ላይ በድንጋጤ ላይ ያለው የከተማው ህዝብ የቻለው በቅርብ ርቀት ወደምትገኘው ባህር ዳር ከተማ እየሄደ እንደሆነ ጠቁመዋል።

በዚህ ዙርያ ተጨማሪ መረጃ ከመንግስት አካላት ለማግኘት ያደረግኩት ሙከራ አልተሳካም። ተጨማሪ መረጃ ካገኘሁ እመለስበታለሁ።

(Eliasmeseret)
@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
መርጌታ ቃለ ህይወት  የባህል መዳኒት ቀማሚ እና መስተፋቅር እንሰራልን በሁሉም ከተሞች ያላችሁ አናግሩኝ:

መርጌታ ቃለ ህይወት የባህል መድህኒት አስማት እና ጥበብ ይፈልጋሉ:
የምንሰጣቸው የጥበብ አገልግሎቶች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል
1 ለመፍትሔ ስራይ
2 ለህማም
3 ጋኔን ለያዘው ሰው
4 ቡዳ ለበላው
5 ለቁራኛ
6 የዛር ውላጅ ለተዋረሰው
7 ለአይነ ጥላ
8 ነገረ ራዕይ(ራዕይ የሚያሳይ)
9 ለዓቃቤ ርዕስ
10 ለመክስት
11 ለቀለም(ለትምህርት)
14 ለመስተፋቅር
15 ለሁሉ ሠናይ
16 ለገብያ
17 ለአምፅኦ ብእሲት(ፍቅረኛ ላጣ ወይም ላጣች የሚሰራ)
18 ለመድፍነ ፀር
19 ሌባ የማያስነካ
20 ለበረከት

ውድ  ቤተሰቦች  ለማንኛውም ነገር ያማክሩን    ከስላምታ ጋር።
ከምሰጣቸው በትንሹ ይህን ይመስላል 
ለጥያቄወ 09 75-90-23-15
ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በተለያዩ ርቀቶች ፈጣን ሰዓት በማስመዝገብ ድል አደረጉ 

በቶሩን፣ ፖላንድ እየተካሄደ ባለው የዓለም የቤት ውስጥ ሩጫ ውድድር በተለያዩ ርቀቶች ፈጣን ሰዓት በማስመዝገብ እና ክብረ ወሰን በመስበር ጭምር አሸንፈዋል።

አትሌት ፍሬወይኒ ኃይሉ በ1 ሺህ 500 የቤት ውስጥ ሩጫ በዓለም አራተኛውን ፈጣን ሰዓት  3:55.28 በማስመዝገብ አሸንፋለች ።

በሌላ በኩል አትሌት ቢኒያም መሐሪ ከ20 ዓመት በታች በተደረገ የ1 ሺህ 500 ሜትር ሩጫ 3:34.83 በሆነ ሰዓት በመግባት ክብረ ወሰን አሻሽሏል ።

በሴቶች የ800 ሜትር ሩጫ ደግሞ አትሌት ሀብታም ዓለሙ 1:57.86 የሆነ ፈጣን ሰዓት አስመዝግባ ውድድሩን አሸንፋለች።

ከዓለም አትሌቲክስ ያገኘነው መረጃ እንደሚያሳየው አትሌት ሰለሞን ባረጋ በወንዶች የ3 ሺህ ሜትር ሩጫ 7:25.82 በሆነ ሰዓት በመግባት ለራሱም አምስተኛው ፈጣን ሰዓት በማስመዝገብ አሸንፏል።
ከሱዳን ተጨማሪ 200 ሺህ ስደተኞች ወደ ኢትዮጵያ ሊገቡ ይችላሉ ተባለ

የዓለም ምግብ ፕሮግራም፣ በኢትዮጵያ የርሃብ አደጋ ላንዣበበባቸው ሦስት ሚሊዮን ሰዎች በቅርቡ የምግብ ዕርዳታ ሥርጭት ለመጀመር ጥረቱን ማጠናከሩን አስታውቋል። ኹለት ሚሊዮኑ ተረጂዎች በትግራይ ክልል እንደሚገኙ ድርጅቱ ገልጧል።

ድርጅቱ፣ እስከ ሰኔ ወር የምግብ ዕርዳታ ጉድለቱን ለመሙላት ተጨማሪ 142 ሚሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልገው አመልክቷል። ተጨማሪውን ገንዘብ ካላገኘኹ ሚያዝያ ወር በአገሪቱ ለተጠለሉ ስደተኞች የማቀርበውን የምግብ እርዳታ ለማቋረጥ እገደዳለኹ ያለው ድርጅቱ፣ ከሱዳን 200 ሺህ ተጨማሪ ስደተኞች ወደ ኢትዮጵያ ሊገቡ ይችላሉ ብሏል። 

ድርጅቱ፣ አዲስ የተረጂ ልየታ ሥርዓት ከዘረጋ ወዲህ፣ በትግራይ፣ አማራ፣ አፋርና ሱማሊያ ክልሎች 6 ነጥብ 2 የአደጋ ተጋላጮችን መመዝገቡንም ጠቅሷል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
"ኢትዮጵያ መክፈል አቅቷታል የተባለው 33 ሚሊየን ዶላር የእዳ ወለድ የአየር መንገዳችን የሁለት ቀን ገቢ ነው" ሲሉ ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

ኢትዮጵያ ከዩሮ ቦንድ ወለድ ጋር በተያያዘ መክፈል አቅቷታል የተባለው 33 ሚሊየን ዶላር የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሁለት ቀን ገቢ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በትናንትናው የም/ቤት ዉሏቸዉ ተናግረዋል፡፡

መንግስት እጅግ ከሚኩራራባቸው ስራዎች መካከል አንደኛው እዳ መክፈሉ ነዉ ያሉት ጠ/ሚኒስትሩ ከ2011 እስከ 2015 ባሉት ዓመታት ውስጥ መንግስታቸዉ 9.9 ቢሊየን ዶላር መክፈሉን መናገራቸውን ዳጉ ጆርናል ሰምቷል፡፡  ይህንና ሌሎች እዳዎችን መክፈል የቻለች ሀገር ግን 33 ሚሊየን ዶላር መክፈል አቅቷታል እያሉ ማውራት ያሳፍራል ሲሉም ተደምጠዋል፡፡

በአለም ላይ በፈጣን የአኮኖሚ እድገት ላይ ከሚገኙ ጥቂት ሀገራት ውስጥ አንዷ ኢትዮጵያ ናት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ኢትዮጵያ መክፈል አቅቷታል የተባለው 33 ሚሊየን ዶላርም የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሁለት ቀን ገቢ መሆኑን በንጽጽር አንስተዋል።

ኢትዮጵያ በዩሮ ቦንድ እዳ እና ወለድ አከፋፈል ዙሪያ በተደጋጋሚ ከአበዳሪ አካላት ጋር ምክክር ማድረጓ የተነገረ ሲሆን የ 33 ሚሊዮን ዶላር ወለድ አለመክፈሏ መነጋገሪያ ሆኖ ነበር። ፊች የተሰኘዉ የሀገራትን ብድር የመክፈል አቅም የሚለካዉ ተቋም በበኩሉ በቅርቡ ኢትዮጵያን ብድራቸዉን መክፈል ከማይችሉ ሀገራት ደረጃ ሰጥቷታል። በተጨማሪም ኢትዮጵያ ዛምቢያን እና ጋናን በመከተል በአፍሪካ ከከሰሩ ሀገራት ተርታ በቅርቡ ልትምደብ ትችላለች የሚልም ስጋት አለ።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በፍኖተ ሰላም ከተማ ዙሪያ ትናንት በመንግሥት ኃይሎችና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ግጭት መካሄዱ ተነገረ

በአማራ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች በመንግሥት ኃይሎችና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ግጭቶች መቀጠላቸውን ዋዜማ ከምንጮች ሰምታለች። በምዕራብ ጎጃም ዞን ፍኖተ ሰላም ከተማ ዙሪያ ትናንት ግጭት መካሄዱን ምንጮች ተናግረዋል።

በደቡብ ወሎ፣ በደቡብ ጎንደርና በሰሜን ጎንደር ዞኖች አንዳንድ አካባቢዎችም ግጭቶች መካሄዳቸው ተዘግቧል። ግጭቶች መቀጠላቸው የተሰማው፣ የፌደራልና የተለያዩ ክልሎች ከፍተኛ ባለሥልጣናት በክልሉ 15 ከተሞች በክልሉ ሕዝብ ጥያቄዎችና በመፍትሄ ሃሳቦች ዙሪያ ከሕዝቡ ጋር ውይይት ማድረጋቸው በተገለጠ ማግስት ነው።

በተያያዘ ዜና ኢሰመጉ ፤ በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን መርዓዊ ከተማ በመንግሥት ኃይሎችና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ጥር 20 ቀን የተካሄደውን ግጭት ተከትሎ የመንግሥት ጸጥታ ሃይሎች በበርካታ ንጹሃን ዜጎች ላይ ግድያ፣ የአካል ጉዳት ማድረስና ድብደባ ፈጽመዋል በማለት ከሷል። ጸጥታ ሃይሎች በከተማዋ የቤት ለቤት ፍተሻ በማድረግ በግጭቱ ምንም ዓይነት ተሳትፎ የሌላቸውን በርካታ ሰዎች መግደላቸውን ኢሰመጉ ዓይን እማኞችን ጠቅሶ ገልጧል።

ኢሰመጉ፣ በግጭቱ ወቅት በነበረው የተኩስ ልውውጥና በጸጥታ ኃይሎች ግድያ፣ ኹለት ሴቶችንና አንድ የ17 ዓመት ታዳጊን ጨምሮ በጠቅላላው ከ80 በላይ ንጹሃን መገደላቸውን ጠቅሷል። ጸጥታ ኃይሎች በርካታ ወንዶችን ከቤታቸው ካወጡ በኋላ በአደባባይ እንደረሸኗቸውና በማግስቱ በጅምላ መቃብር እንደተቀበሩ የዓይን እማኞች መናገራቸውን የገለጠው ኢሰመጉ፣ ድርጊቱን ተከትሎ ነዋሪዎች ከከተማዋ እየሸሹ ነው ብሏል።

Via ዋዜማ
@sheger_press
@sheger_press
ዶክተር ሊያ አመለከቱ

ዶ/ር ሊያ ታደሰ ከጤና ጥበቃ ሚኒስትርነታቸው ለመልቀቅ እንዳመለከቱ ተሰምቷል።

የመረጃ ምንጮች እንደተሰማው ከሆነ ዶ/ር ሊያ መልቀቂያ ያስገቡበት ምክንያት በሃርቫርድ ዩኒቨርስቲ ስራ እና ተጨማሪ የትምህርት ዕድል በማግኝታቸው ነው ተብሏል።

መንግስት በቅርብ ቀናት አዳዲስ ካቢኔዎችን ይፋ እንደሚያደርግ ይጠበቃል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
"ከሶማልያ ቶሎ ካልወጣችሁ መጥተን እናጠፋችኋለን ብለው እየዛቱብን ነው፣ ስለዚህ መንግስት በአስቸኳይ ወደ ሀገራችን ይመልሰን"--- በሶማልያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ካደረሱኝ መረጃ የተወሰደ

ከአራት ቀን በፊት የአልሸባብ አባላት እንደሆኑ የተገመቱ ታጣቂዎች ስድስት ኢትዮጵያውያንን እና አንድ የሶማልያ ዜጋን በለሊት ቤታቸው ድረስ በሞተር ሳይክል በመሄድ ከገደሉ በኋላ ተጨማሪ ዛቻ እና ማስፈራርያ እየደረሳቸው እንደሆነ እነዚህ ዜጎቻችን በቴሌግራም አሳውቀውኛል።

በደቡብ-ምዕራብ ሶማሊያ በለድ ሀዎ ከተማ በተፈፀመው በዚህ ጥቃት የኦሮሞ ተወላጆች ላይ ያነጣጠረ እንደነበር የታወቀ ሲሆን ይህ ጥቃት እንዲፈፀም በሶማልያ የማህበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎች እና በአንዳንድ የሀገሪቱ ፖለቲከኞች ጭምር ጥሪ ሲደረግ እንደነበር ይታወሳል።

እነዚህ በመዲናዋ ሞቃዲሾ እና ሌሎች በርካታ ስፍራዎች የሚኖሩ ዜጎች "በቅርቡ ተመሳሳይ ጥቃት ይፈፀምብናል ብለን ስጋት አለን፣ ስለዚህ መንግስት በአስቸኳይ ወደ ሀገራችን ይመልሰን" ብለዋል።

ኢትዮጵያ እና ሶማሊላንድ የወደብ አጠቃቀምን በተመለከተ ከአንድ ወር በፊት የተፈራረሙትን የመግባብያ ሰነድ ተከትሎ ሶማሊላንድ የሉአላዊ ግዛቴ አካል ነች በምትለው ሶማልያ እና ኢትዮጵያ መሀል በቅርብ አመታት ታይቶ የማይታወቅ ውጥረት እና ውዝግብ እንደተነሳ ይታወቃል።

via EliasMeseret
@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ሹመት‼️

ተምስገን ጥሩነህ የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲሁም አምባሳደር ታዬ አፅቀሥላሴ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ

6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን በ15ኛ መደበኛ ስብሰባ የአምባሳደር ታዬ አፅቀሥላሴን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ሹመት አጽድቋል።

ምክር ቤቱ በተመሳሳይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በዕጩ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርነት ያቀረቡት ተመስገን ጥሩነህ ሹመትንም ማጽደቁን ብሔራዊ ቴሌቭዥኑ ሰምተናል፡፡ የአምባሳደር ታዬ አፅቀሥላሴ የሥራ ልምድ ዘርዝረው ለምክር ቤቱ ባቀረቡት መሰረት ምክር ቤቱ በሙሉ ድምጽ ሹመቱን አጽድቋል፡፡
2024/10/05 05:28:38
Back to Top
HTML Embed Code: