Telegram Web Link
ተመሳሳይ ፈተና ለተለያዩ የሥራ ዘርፎች ነው የተሰጠው- የከተማ አስተዳደሩ ሠራተኞች ቅሬታ ለአዲስ ማለዳ

አዲስ ማለዳ የፈተና ጥያቄዎቹን ለማየት ያደረገችው ሙከራ ከተፈታኞች በኩል ወረቀቱ እዛው በመሰብሰቡ ማሳየት አልቻልንም በማለታቸው አልተሳከም፤ ነገር ግን ፈተናው የሙያ ወይንም የባህሪ ጥያቄዎችን ሳይጨምር አምስት ጥያቄዎችን ብቻ የያዘ መሆኑን ተናግረዋል።

በዚህም ዕውቀትና ብቃት ያላቸው ሠራተኞች ወድቀው ችሎታ የሌላቸው ሰዎች እያለፉ ነው ሲሉ ቅሬታቸውን ገልጸው “አንድ ፈተና አንድን ሠራተኛ በትክክል እንዲመዝን ከተፈለገ የሙያውን በርካታ ዘርፎች የዳሰሰና ሰፋ ያለ መሆነ ሲጠበቅበት በዘርፉ ከአምስት የማይበልጡ ጥያቄዎች ማውጣት ተገቢ አይደለም።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የህወሓት ታጣቂዎች እንዲበተኑ የፌዴራል መንግሥት ጠየቀ

የፌዴራሉ መንግሥት ህወሓት የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ሙሉ በሙሉ ይፈጸም ሲሎ ላወጣው መግለጫ ምላሽ ተሰጥቷል።

ህወሓት ለ40 ቀናት ያካሄደውን የማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ መጠናቀቅ አስመልክቶ፣ ትላንት ባወጣው መግለጫ ስምምነቱ በሚገባው ልክ አልተፈጸመም ሲል ወቀሳ አቅርቧል።

የፌዴራል መንግሥቱ በበኩሉ ባወጣው መግለጫ የህወሓትን መግለጫ በአንክሮ ተመልክቼዋለሁ ተብሏል። የስምምነቱ ተግባራዊነት ከሚጠበቅብኝ ርቀት በላይ ተጉዣለሁ ያለው መንግሥት፣ አሁንም ስምምነቱ ሙሉ በሙሉ እንዲፈጸም ቁርጠኛ ነኝ ብሏል።

በስምምነቱ መሰረት በአጭጪጊዜ ይፈጸማል የተባለው የህወሓት ትጥቅ መፍታትና ተዋጊዎችን መበተን እስካሁን ሙሉ በሙሉ አልተፈጸመም።

ስምምነቱን ተግባራዊ ከማድረግ ውጭ አማራጭ የለም ያለው የፌዴራሉ መንግሥት፣ ህወሓት ተዋጊዎቹን ወደ ሰላማዊ ህይወታቸው መመለስ አለበት ብሏል።

በአማራና ትግራይ ክልል መካከል ውዝግብ የፈጠሩ እንደ ወልቃይት፣ ጠለምትና ራያ አላማጣ አካባቢ በህዝብ ውሳኔ እንዲፈጸም መወሰኑን ጠቁሟል።

በውሳኔው ላይ ከሚመለከታቸው የሁለቱ ክልሎች አካላት ጋር መግባባት ተፈጥሮ ነበርም ብሏል። ይሁን እንጂ ተፈጥሮ ነበር የተባለው መግባባት በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ አልተገለጸም።

የፌዴራሉ መንግሥት ውዝግቡ በሕዝበ ውሳኔ እንዲፈታ ቢወስንም፣ በሁለቱም ወገኖች በኩል መጓተቶች ተፈጥረዋል። በትግራይ በኩል አካባቢዎቹ ወደ ትግራይ ሳይመለሱ ሕዝበ ውሳኔ አይካሄድም ሲባል፣ አካባቢዎቹን በተቆጣጠሯቸው በአማራ ኃይሎች በኩል ደግሞ ነጻነታችንን አሳልፈን አንሰጥም የሚል ነው።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
#አቢሲንያ_ባንክ

አሁን ባሉበት ሆነው የአፖሎ አካውንት ለመክፈት የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ቁጥር ብቻ በቂ ሆኖዋል። የባንክ አካውንት ለመክፈት ይህን ያህል ቀሏል።
አሁኑኑ መተግበሪያውን በማውረድ የ9% ወለድ፣ አነስተኛ ብድርና ሌሎች አገልግሎቶችን ያግኙ።
ለአንድሮይድ ስልኮች https://play.google.com/store/apps/details?id=com.boa.apollo&hl=en&gl=US

ለአፕል ስልኮች https://apps.apple.com/us/app/apollo-digital/id1601224628

#Apollodigitalbank #Apollodigitalproduct #Abyssiniabank #poweredbybankofabyssinia #BankofAbyssinia #የሁሉም_ምርጫ #The_Choice_For_all
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ሊራዘም ነው

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ አርብ ጥር 24፤ 2016 በሚያካሄደው ልዩ ሰብሰባው፤ ለስድስት ወራት ታውጆ የነበረውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሊያራዝም ነው። ምክር ቤቱ በስብሰባው ሌሎች አራት አጀንዳዎችንም ይመለከታል።

የተወካዮች ምክር ቤት በዋነኛነት በአማራ ክልል ተፈጻሚ እንዲሆን በሚኒስትሮች ምክር ቤት የቀረበለትን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ያጸደቀው ሐምሌ 28፤ 2015 ነበር። ለስድስት ወራት የተደነገገው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቀነ ገደብ በትናንትናው ዕለት መጠናቀቁን ተከትሎ፤ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለዛሬ “ልዩ ስብሰባ” መጥራቱን አራት የፓርላማ አባላት ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” አረጋግጠዋል።

የፓርላማ አባላቱ ለዛሬው ስብሰባ አጀንዳ የተላከላቸው፤ ትናንት ምሽት አንድ ሰዓት ገደማ እንደነበር አንድ የተወካዮች ምክር ቤት አባል ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል። ለልዩ ሰብሰባው ከተያዙ አምስት ጉዳዩች መካከል፤ በአጀንዳ ዝርዝር ላይ በቀዳሚነት የተቀመጠው “የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን ማራዘም” የሚለው እንደሆነ እኚሁ አባል ገልጸዋል።
(ኢትዮጵያ ኢንሳይደር

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ኢትዮ መረጃ - NEWS
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ሊራዘም ነው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ አርብ ጥር 24፤ 2016 በሚያካሄደው ልዩ ሰብሰባው፤ ለስድስት ወራት ታውጆ የነበረውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሊያራዝም ነው። ምክር ቤቱ በስብሰባው ሌሎች አራት አጀንዳዎችንም ይመለከታል። የተወካዮች ምክር ቤት በዋነኛነት በአማራ ክልል ተፈጻሚ እንዲሆን በሚኒስትሮች ምክር ቤት የቀረበለትን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ያጸደቀው ሐምሌ 28፤ 2015…
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ከስድስት ወራት በፊት የተደነገገው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መራዘሙ አሳሳቢ ነው አሉ።

የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) መንግሥት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን የሚያራዝመው ከሆነ በሰብዓዊ መብቶች አያያዝ ላይ ሊያስከትል የሚችለው አሉታዊ ተጽእኖ አሳሳቢ ነው ብለዋል።

ዋና ኮሚሽነሩ ይህን ያሉት ዛሬ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአማራ ክልል የተከሰተውን አለመረጋጋት ተከትሎ ባለፈው ዓመት ማብቂያ ገደማ ያጻደቀውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለማራዘም በሚቀርብ የውሳኔ ሐሳብ ላይ ውይይት እንደሚያደርግ ከተገለጸ በኋለ ነው።

ምክር ቤቱ ለዛሬ አርብ ጥር 24/2016 ዓ.ም. በጠራው ልዩ ስብሰባው አባላቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ለማራዘም በሚቀርብ የውሳኔ ሐሳብ ላይ ውይይት በማድረግ ድምጻቸውን ይሰጣሉ።
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተግባራዊነት ለማራዘም የሚቀርበው የውሳኔ ሐሳብ ሁለት ሦስተኛ የሚሆኑት የሕዝብ እንደራሴዎችን ድጋፍ ካገኘ ተፈጻሚነቱ ይረዘማል።

ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የሚራዘም ከሆነ የግጭት ተጎጂ በሆኑ፣ በሰብዓዊ ቀውስ ውስጥ ባሉ እና ለፍርድ ሳይቀርቡ ለረዥም ጊዜያት በእስር ላይ በሚቆዩ ሰዎች የሰብዓዊ መብት አያያዝ ላይ የሚያመጣው አሉታዊ ተጽእኖ አሳሳቢ ብለዋል።

የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) በኤክስ ገጻቸው “የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና መንግሥት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አስፈላጊነት፣ ሕጋዊነት እና ተመጣጣኝነትን በአግባቡ ማጤን ይኖርባቸዋል” ብለዋል።

ኮሚሽነሩ አክለውም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲደነገግ ላስገደደው ችግር “ውይይት ቁልፍ” መፍትሄ ነው ሲሉ መክረዋል።
በአማራ ክልል በመንግሥት ኃይሎች እና በታጣቂዎች መካከል እየተባባሰ የሄደውን ግጭት ተከትሎ ክልሉ የፌደራል መንግሥቱ ጣልቃ እንዲገባ ባቀረበው ጥሪ ነበር የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የተደነገገው።

በአማራ ክልል ውስጥ እንዲሁም “እንዳስፈላጊነቱ በሌሎችም የአገሪቱ ክፍሎች” ውስጥ ተግባራዊ እንዲሆን የወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በሚቀጥለው ሳምንት የሚያበቃ በመሆኑ ነው ምክር ቤቱ ለማራዘም ስብሰባ የጠራው።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ተራዘመ‼️

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለተጨማሪ አራት ወራት እንዲራዘም ተወሰነ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 1ኛ ልዩ ስብሰባ አካሂዷል።

በስብሰባውም የሚኒስትሮች ምክር ቤት ሐምሌ 28 ቀን 2015 ባደረገው ስብሰባ የህሕዝብን ሰላም እና ደህንነት ለማስጠበቅ ያወጣውን አዋጅ ቁጥር 1299/2015 ለማራዘም የቀረበውን ውሳኔ መርምሮ አፅድቋል።

በዚህም ተጥሎ የነበረውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ 1299/2015 በሁለት ተቃውሞ በሶስት ድምፀ ተአቅቦ በአብላጫ ድምፅ ለአራት ወራት እንዲራዘም አፅድቋል።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቦርድ አባላት የሥራ ጊዜ ለማራዘም የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ የሥራ ጊዜያቸውን እንዲራዘም አፅድቋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከፓርላማ አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች፤ በመጪው ማክሰኞ ምላሽ ሊሰጡ ነው 

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከፓርላማ አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች፤ በመጪው ሳምንት መጀመሪያ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በመገኘት ምላሽ እና ማብራሪያ እንደሚሰጡ ምንጮች ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናገሩ። የፓርላማ አባላቱ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚቀርቡ ጥያቄዎችን አስገብተው ያጠናቀቁት በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ነው።

“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ያነጋገረቻቸው ሶስት የፓርላማ አባላት፤ ጥያቄዎችን እንዲያቀርቡ የተሰጣቸው ቀናት ብዛት ሶስት ብቻ እንደነበር ገልጸዋል። በዚህም መሰረት የፓርላማ አባላቱ ከባለፈው ሳምንት ቅዳሜ ጥር 18 ጀምሮ እስከዚህ ሳምንት ሰኞ ጥር 20 ድረስ ጥያቄዎቻቸውን ማስገባታቸውን አስረድተዋል።

በ2008 ዓ.ም የወጣው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአሰራር እና የአባላት ስነ ምግባር ደንብ፤ “ማንኛውም የቃል መልስ የሚፈልግ ጥያቄ የሚያቀርብ አባል፤ ጥያቄውን ቢያንስ ከአስር ቀናት በፊት ለአፈ ጉባኤው በጽሁፍ ማሳወቅ አለበት” ሲል ይደነግጋል። የፓርላማው አፈ ጉባኤ፤ ከምክር ቤቱ አባላት የቀረቡላቸውን ጥያቄዎች መርምረው የመቀበል ወይም ውድቅ የማድረግ ስልጣን በደንቡ ተሰጥቷቸዋል።

Via Ethiopian Insider

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የዕለቱ ሰበር መረጃዎች‼️

የዕለተ ዓርብ የምሽት አንኳር ዜናዎች በዝርዝር እነሆ

በዚ ሊንክ ይመልከቱ👇👇
https://youtu.be/Zti3VT4sWYE
https://youtu.be/Zti3VT4sWYE
የምሥራቅ ወለጋ ዞን መቀመጫ በሆነችው ነቀምት ከተማ የእጅ ቦንቦች በተደጋጋሚ እየተጣሉ እንደሆነና ይህም ከፍተኛ ስጋት እንደፈጠረባቸው ነዋሪዎች ለዋዜማ ተናግረዋል።

ባልተለመደ መልኩ ከምሽቱ 12 ሰዓት በኋላ በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች የሚጣለው የእጅ ቦንብ፣የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ጠርቶታል ከተባለው አድማ ጋር የተያያዘ ሳይሆን እንዳልቀረ ነዋሪዎቹ ጠቁመዋል።

በሌላ በኩል ማክሰኞ ጥር 21/2016 ዓ.ም. የተጠራውን አድማ ጥሳችኋል በማለት በከተማዋ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ሁለት ባለ ሦስት እግር ተሽከርካሪዎች በታጣቂ ቡድኑ እንደተቃጠሉም አስረድተዋል።

በከተማዋ መደበኛ እንቅስቃሴ ከተቋረጠ ዛሬ አምስተኛ ቀኑን መያዙን የገለጹት ነዋሪዎች; ምሽት ላይ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እና በታጣቂ ቡድኑ አባላት መካከል ከፍተኛ የሆነ የተኩስ ልውውጥ እንደሚደረግ ተናግረዋል።

ከሰኞ ጥር 20/2016 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ባንኮች፣ትምሕርት ቤቶች፣የንግድ ቤቶች እና ሌሎች አገልግሎት ሰጪ ተቋማት በአመዛኙ ዝግ መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን፣ በመንግሥት ኃይሎች በኩል ተቋማቱን እንዲከፍቱ ከፍተኛ ጫና እየተደረገ መሆኑን ዋዜማ ከነዋሪዎቹ ካሰባሰበችው መረጃ መረዳት ችላለች።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
መርጌታ ቃለ ህይወት  የባህል መዳኒት ቀማሚ እና መስተፋቅር እንሰራልን በሁሉም ከተሞች ያላችሁ አናግሩኝ:

መርጌታ ቃለ ህይወት የባህል መድህኒት አስማት እና ጥበብ ይፈልጋሉ:
የምንሰጣቸው የጥበብ አገልግሎቶች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል
1 ለመፍትሔ ስራይ
2 ለህማም
3 ጋኔን ለያዘው ሰው
4 ቡዳ ለበላው
5 ለቁራኛ
6 የዛር ውላጅ ለተዋረሰው
7 ለአይነ ጥላ
8 ነገረ ራዕይ(ራዕይ የሚያሳይ)
9 ለዓቃቤ ርዕስ
10 ለመክስት
11 ለቀለም(ለትምህርት)
14 ለመስተፋቅር
15 ለሁሉ ሠናይ
16 ለገብያ
17 ለአምፅኦ ብእሲት(ፍቅረኛ ላጣ ወይም ላጣች የሚሰራ)
18 ለመድፍነ ፀር
19 ሌባ የማያስነካ
20 ለበረከት

ውድ  ቤተሰቦች  ለማንኛውም ነገር ያማክሩን    ከስላምታ ጋር።
ከምሰጣቸው በትንሹ ይህን ይመስላል 
ለጥያቄወ 09 75-90-23-15
በነዳጅ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ወደአገር እንዳይገቡ ሙሉ በሙሉ ያለመከልከሉን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ በሚል የሪፖርተር ጋዜጣ ባቀረበው ዜና ላይ የተሰጠ ማብራሪያ

ጥር 22 ቀን 2016 ዓ.ም ታትሞ የወጣው የሪፖርተር ጋዜጣ በነዳጅ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ወደአገር እንዳይገቡ ሙሉ በሙሉ ያለመከልከሉን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ በሚል ያወጣው ዜና በህብረተሰቡ ዘንድ መደናገርን ያስከተለ በመሆኑ የሚከተለውን ማብራሪያ መስጠት አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል።

የውጭ ምንዛሪን በቁጠባ መጠቀም እንዲቻል ከዚህ በፊት በወጣው መመሪያ የተዘረዘሩ እቃዎች ላልተወሰነ ጊዜ የውጭ ምንዛሪ ተመድቦላቸው የውጭ ምንዛሪ እንዳይፈቀድላቸው በመንግስት የተወሰነ ሲሆን፤ ከእነዚህ እቃዎች መካከል በጉምሩክ ታሪፍ መጽሐፍ አንቀጽ 87.03 የተመደቡ በነዳጅ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ይገኙበታል።

ስለዚህ በልዩ ሁኔታ ከሚፈቀድላቸው በስተቀር በነዳጅ የሚሰሩ በጉምሩክ ታሪፍ መጽሐፍ አንቀጽ 87.03 የተመደቡ ተሽከርካሪዎች የውጭ ምንዛሪ ተፈቅዶ ወደአገር እንዳይገቡ የተጣለው ገደብ ተፈጻሚነት የሚቀጥል መሆኑን እንገልጻለን::

Ministry of finance Ethiopia
በቢጂአይ ኢትዮጵያ ስር የሚገኙት አምስት የቢራ ፋብሪካዎች በጥሬ ዕቃ እጥረት ምክንያት ከፍተኛ የምርት መስተጓጎል እንደገጠማቸው ዋዜማ ከፋብሪካው ሠራተኞች ሰምታለች።

እንደ ገብስ፣ብቅል፣ጌሾ፣በቆሎ እና ሌሎችም ለምርት አስፈላጊ የሆኑ ኬሚካሎችን ለፋብሪካዎቹ ለማቅረብ እጅግ አዳጋች መሆኑን የፋብሪካው ሠራተኞች ለዋዜማ ተናግረዋል።

አብዛኞቹ የጥሬ ዕቃ ግብዓቶች የሚመጡት ከኦሮሚያ እና ከአማራ ክልሎች ቢሆንም ክልሎቹ ላይ ባለው የጸጥታ ችግር ምክንያት ጥሬ ዕቃዎችን ማቅረብ አለመቻሉን ጠቁመዋል።

ለአብነትም ከአሰላ ይመጣ የነበረው የገብስና የብቅል ግብዓት ባለፈው አንድ ወር አለመቅረቡን ሠራተኞቹ ለዋዜማ  ገልጸዋል።
በተመሳሳይ ባሕርዳር ከሚገኘውና የበቆሎ ቅንጬ ከሚያመርተው ጨጨሆ ፋብሪካ ምርቱን ይቀበሉ እንደነበር በመግለጽ፣በአካባቢው ካለው የጸጥታ ሁኔታ ጋር በተገናኝ ምርቱን ማቅረብ አዳጋች መሆኑን አስረድተዋል። ጌሾ እና ሌሎች አስፈላጊ ኬሚካሎችም ከአሜሪካና ከጀርመን ይገቡ ነበር ያሉት ሠራተኞቹ፣ በውጭ ምንዛሬ እጥረት ሳቢያ መቆሙን ተናግረዋል።

አልፎ አልፎም ቢሆን በከፍተኛ የጭነት ዋጋና በሌሎች ተለዋዋጭ መንገዶች ጥሬ እቃዎቹን ለማቅረብ የተሞከረ ሲሆን፣ይህም ከፍተኛ ኪሳራ ማስከተሉን ጠቁመዋል።ይህን ለማካካስ በቢራ ዋጋ ላይ ጭማሪ ለማድረግ ቢወሰንም፣ በመንግሥት ክልከላ ምክንያት ጭማሪው እስካሁን አለመደረጉን ዋዜማ ከሠራተኞቹ ሰምታለች።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በሀገር ዓቀፍ ደረጃ ከሁለት ሳምንት በኋላ ለሚሰጠው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመውጫ ፈተና የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተጠናቀቁ መሆናቸውን ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

ከየካቲት 6 እስከ 9 ቀን 2016 ዓ.ም ለሚሰጠው ፈተና ከ112 ሺህ በላይ ነባርና አዳዲስ ተማሪዎች ምዝገባ ማድረጋቸውን በሚኒስቴሩ የከፍተኛ ትምህርት ጥራትና ብቃት ማሻሻያ ዴስክ ኃላፊ ሰዒድ መሃመድ ተናግረዋል።

የፈተና ጥያቄዎች ፣ የኮምፒውተር ፣ ፈተና የሚሰጥባቸው የትምህርት መስኮች ልየታን ጨምሮ አብዛኛዎቹ የዝግጅት ስራዎች እየተጠናቀቁ መሆኑን ነው ኃላፊው የገለፁት።

ባለፈው ዓመት በፈተና አሰጣጥ ሂደትያጋጠሙ ችግሮች ዘንድሮ እንዳይደገሙ በቂ ዝግጅት መደረጉን አቶ ሰኢድ ተናግረዋል፡፡

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
አሜሪካ በኢትዮጵያ የሚስተዋሉ ግጭቶችን ለማስቆም በአስቸኳይ ንግግር  እንዲጀመር ጥሪ አቀረበች

የአሜሪካ መንግሥት በኢትዮጵያ የሚስተዋሉ ግጭቶችን ለማስቆም በአስቸኳይ ንግግር እንዲጀመር ጥሪ ያቀረበችው ለስድስት ወራት ተጥሎ የነበረው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መራዘሙን ተከትሎ ነው።

የአገሪቱ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ቢሮ፣ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ዋና ኮሚሽነር ከስድስት ወራት በፊት የተደነገገው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መራዘሙ አሳሳቢ ነው ማለቱን ተጋርቶታል።

የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) ትላንት ረፋድ መንግሥት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን የሚያራዝመው ከሆነ በሰብዓዊ መብቶች አያያዝ ላይ ሊያስከትል የሚችለው አሉታዊ ተጽእኖ አሳሳቢ ነው ብለው ነበር።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤቱ ትላንት ዐርብ ጥር 24፣ 2016 በጠራው ልዩ ስብሰባው አባላቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ለማራዘም በሚቀርብ የውሳኔ ሐሳብ ላይ ውይይት አድርገው ለአራት ወራት አራዝሞታል።

የኢሰመኮ ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) ቀድመው ባሠፈሩት ጽሑፍ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የሚራዘም ከሆነ የግጭት ተጎጂ በሆኑ፣ በሰብዓዊ ቀውስ ውስጥ ባሉ እና ለፍርድ ሳይቀርቡ ለረዥም ጊዜያት በእስር ላይ በሚቆዩ ሰዎች የሰብዓዊ መብት አያያዝ ላይ የሚያመጣው አሉታዊ ተጽእኖ አሳሳቢ ብለው ነበር።

ኮሚሽነሩ አክለውም የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና መንግሥት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አስፈላጊነት፣ ሕጋዊነት እና ተመጣጣኝነትን በአግባቡ ማጤን እንደሚኖርባቸው በማስታወ፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲደነገግ ላስገደደው ችግር ውይይት ቁልፍ መፍትሄ ነው ሲሉ መክረዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
መረጃ‼️

በዩትዩብ ገፃችን በቪድዮ የተዘጋጁ
የዕለቱ ሰበር አንኳር መረጃዎች እነሆ👇👇

ዝርዝሮቹን ይመልከቱ👇👇
https://youtu.be/TbU3plz-bSE
https://youtu.be/TbU3plz-bSE
2024/10/05 09:27:11
Back to Top
HTML Embed Code: