Telegram Web Link
በአዋሽ አርባ ወታደራዊ ካምፕ ታስረው የቆዩት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባሉ ክርስቲያን ታደለና የአማራ ክልል ምክር ቤት አባሉ ዮሃንስ ቧያለው ዕሁድ'ለት ወደ አዲስ አበባ መዛወራቸውን ቢቢሲ አማርኛ ምንጮቹን ጠቅሶ ዘግቧል።

ኸለቱ ግለሰቦች ባኹኑ ወቅት ፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ ታስረው እንደሚገኙ መስማቱን ዘገባው ጠቅሷል።

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አባሉ ካሳ ተሻገር እና የበይነ መረብ ጋዜጠኛ በቃሉ አላምረው ደሞ፣ ለሕክምና ከአዋሽ አርባ ወደ አዲስ አበባ የተዛወሩት ከኹለት ሳምንት በፊት እንደኾነ ምንጮች መናገራቸውን ዘገባው ጨምሮ አመልክቷል።

ካሳ ለሕክምና ወደ አዲስ አበባ ተዛውረው ፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ ውስጥ ታስረው እንደሚገኙ ዋዜማ ባለፈው ሳምንት መዘገቧ ይታወሳል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ኢትዮ መረጃ - NEWS
በአዋሽ አርባ ወታደራዊ ካምፕ ታስረው የቆዩት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባሉ ክርስቲያን ታደለና የአማራ ክልል ምክር ቤት አባሉ ዮሃንስ ቧያለው ዕሁድ'ለት ወደ አዲስ አበባ መዛወራቸውን ቢቢሲ አማርኛ ምንጮቹን ጠቅሶ ዘግቧል። ኸለቱ ግለሰቦች ባኹኑ ወቅት ፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ ታስረው እንደሚገኙ መስማቱን ዘገባው ጠቅሷል። የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አባሉ ካሳ ተሻገር እና የበይነ…
ተጨማሪ‼️

አዋሽ አርባ ታስረዉ የነበሩ የም/ቤት አባላት እና ጋዜጠኛ ወደ አዲስአበባ ተዘዋወሩ

ከወራት በፊት በፀጥታ ኃይሎች ተይዘው አዋሽ አርባ በሚገኘው የመከላከያ ሠራዊት ማዕከል ውስጥ በእስር ላይ ከሚገኙት ሰዎች መካከል የምክር ቤት አባሎች እና አንድ ጋዜጠኛ ወደ አዲስ አበባ መዘዋወራቸው ተነገረ።

በአማራ ክልል በተከሰተው የፀጥታ ችግር ምክንያት ከታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር ውለው አዋሽ አርባ ወታደራዊ ካምፕ ውስጥ ለወራት ከቆዩት ታሳሪዎች መካከል፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባሉ አቶ ክርስቲያን ታደለ እና የአማራ ክልል ምክር ቤት አባል አቶ ዮሐንስ ቧያለው ወደ አዲስ አበባ መዘዋወራቸውን ምንጮች ለቢቢሲ ገለጹ።

በተጨማሪም የአዲስ አበባ ምክር ቤት አባሉ ዶ/ር ካሳ ተሻገር እንዲሁም ጋዜጠኛ በቃሉ አላምረውም በተመሳሳይ ከሁለት ሳምንት በፊት ወደ አዲስ አበባ መዘዋወራቸውን ቢቢሲ ለታሳሪዎቹ ቅርበት ካላቸው ምንጮች ማረጋገጥ ችሏል።

ስድስት ወራት ሊሞላው የተቃረበውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተከትሎ የታሰሩት አቶ ክርስቲያን እና አቶ ዮሐንስ በአዲስ አበባ ሜክሲኮ አካባቢ ወደሚገኘው የፌደራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ የተዘዋወሩት ትላንት እሁድ ጥር 19/2016 ዓ.ም. መሆኑን ማንነታቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ ሦስት የተለያዩ የቢቢሲ ምንጮች አረጋግጠዋል።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል እና በምክር ቤቱ የመንግሥት ወጪ፣ አስተዳደር እና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ እንዲሁም በምክር ቤቱ ውስጥ በሚሰነዝሯቸው ትችት እና አስተያየቶች የሚታወቁት የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) አባሉ አቶ ክርስቲያን፤ በአዲስ አበባ ከተማ በቁጥጥር ስር የዋሉት ባለፈው ዓመት ሐምሌ መጨረሻ ላይ ነበር።

የገዢው ብልጽግና ፓርቲ አባል እና በአማራ ክልል ምክር ቤት የሕዝብ እንደራሴ የሆኑት አቶ ዮሐንስ ቧያለው ደግሞ በነሐሴ ወር የተያዙት በአማራ ክልል ዋና ከተማ ከባሕር ዳር ከተማ ነበር።ፖለቲከኞቹ በተለያዩ ከተማዎች ቢያዙም ከነሐሴ 15 እስከ ነሐሴ 24/2015 ዓ.ም. ባሉ ቀናት አፋር ክልል አዋሽ አርባ አካባቢ ወደሚገኘው የመከላከያ ሠራዊት የምዕራብ ዕዝ ወታደራዊ ማሠልጠኛ ካምፕ መወሰዳቸውን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ነሐሴ ወር ላይ ባወጣው መግለጫ አስታውቆ ነበር።

ላለፉት አምስት ወራት በወታደራዊው ካምፕ ውስጥ በእስር ላይ የቆዩት የምክር ቤት አባላቱ “ሰውነታቸው እንደከሳ እና እንደተጎሳቆለ” ምንጮች ለቢቢሲ ገልጸዋል። ሁለቱ ፖለቲከኞች በትላንትናው ዕለት ወደ ፌደራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ ሲገቡ በቦታው የነበሩ አንድ ምንጭ “ሁሉም ሌላ ሰው ነው የሚመስሉት” ሲሉ በታሳሪዎቹ የሰውነት ገጽታ ላይ የተመለከቱትን ለውጥ ገልጸዋል።

አቶ ዮሐንስ እግራቸው ላይ ባጋጠማቸው ህመም ምክንያት ከሁለት ወራት ገደማ በፊት ወደ አዲስ አበባ መጥተው እንደነበር ያስታወሱ አንድ ምንጭ፤ በወቅቱ ለአንድ ሳምንት ከቆዩ በኋላ “ህክምናቸውን ሳይጨርሱ” ወደ ወደ አዋሽ አርባ እንዲመለሱ መደረጉን ተናግረዋል። በዚህም ምክንያት አሁንም ይህ በሽታ እያገረሸባቸው መሆኑን አክለዋል።

በአሁን ወቅት ፖለቲከኞቹ በምን ምክንያት ወደ አዲስ አበባ እንዲዘዋወሩ እንደተደረገ እስካሁን ድረስ እንዳልተገለጸላቸው ምንጮቹ ገልጸዋል።

በተመሳሳይ መልኩ በወታደራዊ ካምፕ ውስጥ ለአምስት ወራት ገደማ ታስረው የቆዩት የአዲስ አበባ ምክር ቤት አባሉ ዶ/ር ካሳ እና ጋዜጠኛ በቃሉ ለህክምና ወደ አዲስ አበባ መዘዋወራቸውን ቢቢሲ ከምንጮቹ አረጋግጧል።

እንደ ምንጮቹ ገለጻ በአዋሽ አርባ የነበሩት ዶ/ር ከሳ እና ጋዜጠኛ በቃሉ ወደ አዲስ አበባ የመጡት ከሁለት ሳምንት ገደማ በፊት ነው። ሁለቱም ታሳሪዎች በመዲናዋ በሚገኘው የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ሪፈራል ሆስፒታል ህክምና እየተከታተሉ መሆኑ ተነግሯል።

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ባለፈው ዓመት መጨረሻ ላይ ባወጣው መግለጫ በአዋሽ አርባ ካምፕ ውስጥ 53 ታሳሪዎችን መጎብኘቱን ገልጾ ነበር። ኢሰመኮ በዚህ መግለጫው ታሳሪዎቹ ወደ አዋሽ አርባ እንዲታሰሩ የተደረገው በአዲስ አበባ ያለው የፌዴራል ፖሊስ ማቆያ ጣቢያ “በመጣበቡ ነው” የሚል ማብራሪያ ከፌዴራል ፖሊስ ማግኘቱን አስታውቆ ነበር።

በአዋሽ አርባ ታስረው አሁን ወደ አዲስ አበባ የተዘዋወሩት ፖለቲከኞች እና የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያ እስካሁን ድረስ ፍርድ ቤት ያልቀረቡ ሲሆን ለረጅም ጊዜም ከቤተሰብ እና ጠበቃ ጋር መገናኘት አልቻሉም ነበር።

በአማራ ክልል እንዲሁም እንደ አስፈላጊነቱ በመላው አገሪቱ ተግባራዊ እንዲሆን ለስድስት ወራት የተደነገገው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በሚቀጥለው ሳምንት ስድስት ወር የሚሆነው ሲሆን፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲያበቃ ወይም እንዲራዘም ሊያደርግ ይችላል።

Via BBC Amharic

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ኢሰመጉ በአማራና ትግራይ ክልሎች የሚገኙ ተፈናቃዮች ወደቀያቸው ባለመመለሳቸው ለሞት፣ ለከፍተኛ ርሃብ እና የተለያዩ ሰብዓዊ ቀውሶች ተጋልጠዋል ሲል ዛሬ ባወጣው መግለጫ ገልጧል።

ኢሰመጉ፣ በትግራይ ክልል በሽረ፣ አክሱም፣ አቢአዲ፣ መቀሌ እና አዲግራት ከተሞች የሚገኙ ተፈናቃዮች፣ የረድዔት ድርጅቶች የምግብ ዕርዳታ በመቋረጡና የፌደራሉና የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር በቂ ሰብዓዊ ድጋፍ ባለማቅረባቸው፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በርሃብ ለሞት እንደተዳረጉ አረጋግጫለኹ ብሏል።

በአማራ ክልልም በማዕከላዊ ጎንደር፣ በደቡብ ወሎ፣ በኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን፣ በዋግኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞንና በሰሜን ጎንደር ዞን የጃናሞራና ጠለምት አካባቢዎች፣ ከባድ ድርቅ እንደተከሰተ ኢሰመጉ አስታውቋል።

በድርቁ ሳቢያ በርካታ ሰዎችና እንስሳት እየሞቱ ነው ያለው ኢሰመጉ፣ ባካባቢዎቹ ባለው የጸጥታ ኹኔታ ሳቢያ በቂ ሰብዓዊ ድጋፍ ለማቅረብ እንዳልተቻለ መረዳቱንም ኢሰመጉ ጠቅሷል።(ዋዜማ)

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ኢትዮጵያ ከብሪክስ አባል ሀገራት ጋር ትብብሯን ለማጠናከር ቁርጠኛ ናት - የብሄራዊ ባንክ ገዢ ማሞ ምህረቱ

ኢትዮጵያ ከብሪክስ አባል ሀገራት ጋር ትብብሯን ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆኗን የብሄራዊ ባንክ ገዢ ማሞ ምህረቱ ገለጹ።

በሩሲያ ሞስኮ በተጀመረው የብሪክስ አባል ሀገራት ተወካዮች የዓመቱ የመጀመሪያ  ከፍተኛ ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያ እየተሳተፈች ነው። በጉባኤው ላይ የብሄራዊ ባንክ ገዢ ማሞ ምህረቱ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ኢትዮጵያን ወክለው በመሳተፍ ላይ ናቸው።

የብሄራዊ ባንክ ገዢ ማሞ ምህረቱ በጉባኤው መክፈቻ ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ ከብሪክስ አባል ሀገራት ጋር ተቀራርቦ በመስራት የኢኮኖሚ ትብብሯን ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆኗን ተናግረዋል። ብሪክስ ኢትዮጵያ ለተያያዘችው የልማት ስራዎች አዳዲስ እድሎችን ይፈጥራል ያሉት የባንኩ ገዥው ምጣኔ ሃብትን በማዘመን፣ የፋይናንስ ጉድለትን በመሙላት እና የኢንቬስትመንት መዋዕለንዋይን በማሳደግ ተጨማሪ የልማት ግብዓቶችን እንደሚፈጥር ገልፀዋል።

የባለብዙ ወገን ተቋማት አካታች፣ ፍትሃዊ እና ውጤታማ እንዲሆኑ ማድረግ እንደሚገባም ማስታወቃቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡ ኢትዮጵያ ብሪክስን ከተቀላቀለች ወዲህ እንዲህ ባለ ጉባኤ ላይ ስትሳተፍ የመጀመሪያዋ ሲሆን በሩሲያ ሊቀመንበርነት በመካሄድ ላይ እንደሚገኝ ታውቋል። ጉባኤው የባለብዙ ወገን ግንኙነትን በማጠናከር ፍትሃዊ እድገት እና ደህንነትን በአለም ማስፈን በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ እየመከረ መሆኑም ተገልጿል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በትግራይና አማራ ክልሎች 400 የሚጠጉ ሰዎች በረሃብ መሞታቸውን የህዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም ገለጸ።

ተቋሙ ድርቅ ወደ ተከሰተባቸው አካባቢዎች ባለሙያዎችን ልኮ ምልከታ ማድረጉን ባስታወቀበት መግለጫው፥ የአሰራር ክፍተቶች ናቸው ያላቸውን ጉዳዮች በዝርዝር አመላክቷል።

የህዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም በትግራይና አማራ ክልሎች የተከሰተው የድርቅ አደጋ በሰው ህይወትና በንብረት ላይ ያደረሰውን ጉዳትም በመግለጫው ጠቁሟል።

ተቋሙ በትግራይ ክልል በአበርገሌና ኢስራ ወአዲ ወጅራት ወረዳዎች በተከሰተው ድርቅ ምክንያት 351 ሰዎች መሞታቸውን አረጋግጫለሁ ብሏል።ከ15 ሺህ በላይ ከወረዳዎቹ መፈናቀላቸውንና በሺዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች በድርቁ ምክንያት 5 ሺህ 518 ታዳጊዎች ከትምህርት ገበታ ውጭ መሆናቸውንም ገልጿል።

የህዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም በአማራ ክልልም ከተከሰተው ድርቅ ጋር በተያያዘ የ44 ሰዎች ህይወት ማለፉን ነው በመግለጫው የጠቆመው።በክልሉ ዘጠኝ ዞኖች ውስጥ በሚገኙ 43 ወረዳዎች ከ325 ሺህ ሄክታር በላይ የሰብል ማሳ ሙሉ በሙሉ ከምርት ውጪ በመሆኑ ከ1 ነጥብ 8 ሚሊየን በላይ ሰዎች ለችግር መጋለጣቸውን ነው ያብራራው።የክልሉ መንግሥት በድርቅ ምክንያት የሞተ ሰው የለም የሚል መግለጫን ቢያወጣም ተቋሙ ናሙና ወሰድኩባቸው ባላቸው የሰሜን ጎንደር እና የዋግኽምራ ዞኖች 21 ሰዎች በረሃብ መሞታቸውን ማረጋገጡንም ጠቁሟል።

በዋግህምራ ዞን አበርገሌ ወረዳ 12 ሺህ 270 ፤በሰሜን ጎንደር ዞን ደግሞ 9100 ሰዎች መፈናቀላቸውንና ይህም የክልሉ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ፕሮግራም ማስተባበሪያ ከገለጸው መረጃ የሚቃረን መሆኑንም በማንሳት።የክልሉ መንግስት የመጠለያ ጣቢያ አያስፈልግም የሚል አቅጣጫ መስጠቱም ተፈናቃዮች በተደራጀ መልኩ አገልግሎት እንዳያገኙ አድርጓል ሲል ወቅሷል።

@ethio_mereja_news
#TPLF #ህወሓት

ክልላዊ ፣ አገራዊ ፣ አህጉራዊ እና ዓለምአቀፋዊ ጉዳዮች ባካተቱ 6 ነጥቦች ላለፉት ከ41 ቀናት በላይ ስብሰባ መቀመጡን የገለፀው ህወሓት ዛሬ ባለ 6 ገፅ መግለጫ አውጥቷል።

ጥር 22/2016 ዓ.ም ባወጣው መገለጫ እንዳስታወቀው ረጅም ጊዚያት ወስዶ ያካሄደው የድርጅቱ የፓሊትና የማእከላይ ኮሚቴ  የግምገማ ፣ የሂስና የግለሂስ መድረክ ወደ ቀጣዩ ጉባኤ የሚያሸጋግሩ ወሳኔዎች የተወሰኑበት ነው ብሏል።

ህወሓት በመግለጫው  ፦
- ለትግራይ ህዝብ
- ለድርጅቱ አመራርና አባላት
- ለኢትዮጵያ ህዝቦችና ብሄር ብሄረሰቦች
- ለኤርትራ ህዝብ
- ለዓለም ማህበረሰብና ለትግሉ ደጋፊዎች እንዲሁም ሌሎችም አካላት መልእክት አስተላልፈዋል። 

ህወሓት በተለይ ለኢትዮጵያ ህዝቦችና ብሄር ብሄረሰቦች ባስተላለፈው መልእክት ፤ " ህወሓት ለትግራይ ፣ ለኢትዮጵያ ህዝቦችና ብሄር ብሄረሰቦች የሰላም ስትራቴጂክ አማራጭ ከመሆን በዘለለ በማንም ህዝብ ላይ ጥላቻ አንደሌለው አረጋግጣለሁ " ብሏል።

" ከኤርትራ ህዝብ የጋራ ጥቅም መሰረት ያደረግ የትግል አጋርነት ነበረን አጋርነቱና የጋራ ጥቅም መሰረት ያደረገ መደጋገፉ ይቀጥላል " ያለው ህወሓት " የኤርትራ ህዝብ የኤርትራ ሰራዊት በሃይል ከያዛቸው የትግራይ ግዛቶች ለቆ እንዲወጣ ጫና እንዲያሳድር የሚያስታውስ ጥሪ አስተላልፈዋል። 

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ባይቶና የሀገር አቀፍ ፖለቲካ ፓርቲ ህጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት እንዳገኘ አስታወቀ

በትግራይ ክልል ከሚንቀሳቀሱ የፓለቲካ ፓርቲዎች መካከል አንዱ የሆነው ብሄራዊ ባይቶ ዓባይ ትግራይ (ባይቶና) ምንም እንኳ ከሁለት ዓመት በላይ በትግራይ ፓለቲካ ላይ ተሳትፎ የነበረው እንዲሁም በተቋቋመው ጊዝያዊ አስተዳደር ላይ ቦታ የተሰጠው ቢሆንም እስካሁን ድረስ ግን ከኢትዮጲያ ምርጫ ቦርድ ህጋዊ የሰውነት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀትም ሆነ እውቅና ሳይሰጠው የቆየ ነው።

ፓርቲው ህጋዊ እውቅና ለማግኘት አስፈላጊዎቹን መስፈርቶች በማሟላትና ከጥቅምት 17-18 2016 ዓ/ም የመስራች ጉባኤውን ካካሄደ በኃላ ከጥር 20 2016 ዓ/ም ጀምሮ ከምርጫ ቦርድ የሀገር አቀፍ ፖለቲካ ፓርቲነት ህጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ማግኘቱን ዳጉ ጆርናል ሰምቷል። ፓርቲው ህጋዊ ሰዉነት ማግኘቱን ቢገልፅም የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እስካሁን ያለዉ ነገር የለም።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ሂውማን ራይትስ ዎች የዓለም እርሻ ድርጅት (ፋኦ) ጥር 19 ለጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ የሰጠው ሽልማት በአገሪቱ ያለውን የሰብዓዊ ቀውስ እና በጦርነት ጊዜ የተፈጸሙ ግፎችን ችላ ያለ ነው ሲል ትናንት ባወጣው መግለጫ ከሷል።

ተቋሙ፣ በኢትዮጵያ ካለው አስከፊ ሰብዓዊ ቀውስ እና መጠነ ሰፊ የምግብ ዋስትና እጦት አንጻር ሽልማቱ ያልተጠበቀ ነውም ብሏል።

የኢትዮጵያ አደጋ መከላከል ኮሚሽን በቅርቡ ካወጣው መረጃ; ለኹለት ዓመታት በዘለቀው ጦርነት ሳቢያ በሰሜን ኢትዮጵያ 4 ሚሊዮን የሚጠጉ ዜጎች አስቸኳይ የምግብ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው እንዲሁም በኦሮሚያ እና ደቡብ ክልሎችም ብዙ የተራቡ ዜጎች መኖራቸውን ተረድቻለሁ ብሏል።

ተቋሙ፣ የዓለም መሪዎች መሰረታዊ ፍላጎቶቻቸውን ለማሟላት ስለሚታገሉ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን አስከፊ የሰብዓዊ ቀውሱ እውነታ; እንዲኹም በመንግሥት አካላት ሆን ተብለው ስለሚወሰዱ ቀውሱን የሚያባብሱ እርምጃዎችን መገንዘብ ይኖርባቸዋል ሲል ገልጿል።

ፋኦ፣ ለጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ "አግሪኮላ" የተባለውን ትልቁን ሽልማቱን የሰጣቸው፣ በምግብ ዋስትና፣ በግብርና ምርታማነት እና የተመጣጠነ የምግብ አቅርቦትን ለማሳደግ ላሳዩት አመራር እና ቁርጠኝነት እንደኾነ መግለጡ ይታወሳል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
መርጌታ ቃለ ህይወት  የባህል መዳኒት ቀማሚ እና መስተፋቅር እንሰራልን በሁሉም ከተሞች ያላችሁ አናግሩኝ:

መርጌታ ቃለ ህይወት የባህል መድህኒት አስማት እና ጥበብ ይፈልጋሉ:
የምንሰጣቸው የጥበብ አገልግሎቶች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል
1 ለመፍትሔ ስራይ
2 ለህማም
3 ጋኔን ለያዘው ሰው
4 ቡዳ ለበላው
5 ለቁራኛ
6 የዛር ውላጅ ለተዋረሰው
7 ለአይነ ጥላ
8 ነገረ ራዕይ(ራዕይ የሚያሳይ)
9 ለዓቃቤ ርዕስ
10 ለመክስት
11 ለቀለም(ለትምህርት)
14 ለመስተፋቅር
15 ለሁሉ ሠናይ
16 ለገብያ
17 ለአምፅኦ ብእሲት(ፍቅረኛ ላጣ ወይም ላጣች የሚሰራ)
18 ለመድፍነ ፀር
19 ሌባ የማያስነካ
20 ለበረከት

ውድ  ቤተሰቦች  ለማንኛውም ነገር ያማክሩን    ከስላምታ ጋር።
ከምሰጣቸው በትንሹ ይህን ይመስላል 
ለጥያቄወ 09 75-90-23-15
በነዳጅ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎች አገር ውስጥ እንዳደይገቡ በመከልከል የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ብቻ እንዲገቡ ይደረጋል በሚል የተሰራጨው መረጃ ትክክል እንዳልሆነ የገንዘብ ሚኒስቴር ከፍተኛ የሕግ አማካሪ ዋሲሁን አባተ ለሪፖርተር ተናግረዋል።

ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን ማገድ በዓለም የንግድ ድርጅት ሕግ መሠረት የማይቻል ነው ያሉት አማካሪው; የአገሪቱን የቀረጥ ሥርዓት በመጠቀም ኢኮኖሚ ለማሳደግ የሚጠቅሙትን ማበረታት፣ ጎጂ የሆኑትን ደግሞ እንዳይስፋፉ የማድረግ ሥራ እየተከናወነ ነው ብለዋል፡፡

በገንዘብ ሚንስቴር በኩል ያለው አሰራር የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች እንዲገቡ ለማበረታታት እና በነዳጅ የሚሠሩት በብዛት እንዳይገቡ ለማድረግ ብቻ እንደሆነም ዋሲሁን ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ጥቅምት 4/2015 ዓ.ም ይፋ እንዳደረገው ወደ አገር እንዳይገቡ ክልከላ ከተደረገባቸው 38 ምርቶች ውስጥ በነዳጅ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎችን አላካተተም ሲሉም ጨምረው ተናግረዋል።

የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትሩ ዓለሙ ስሜ; ከትላንት በስቲያ የስድስት ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ሲያቀርቡ፣ በነዳጅ የሚንቀሳቀሱ አውቶሞቢሎች ወደ አገር ውስጥ እንዳይገቡ ውሳኔ መተላለፉን መናገራቸው ይታወሳል።

@sheger_press
@sheger_press
4 አጫጭር ዜናዎች‼️

1. የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ተግባራዊ እንዲሆን፣ ተፈኗቅዮች ወደ መኖሪያቸው እንዲመለሱና ከፌደራል መንግስቱ ጋር ውይይት እንዲጀመር የትግራይ ተወላጆች ግፊት እንዲያደርጉ የትግራይ ክልል የቀድሞው ገዥ ፓርቲ ሕወሓት ጠየቀ። የፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ ለ40 ቀናት ያደረገውን ጉባዔ ሲያጠናቅ ቅ ባወጣው መግለጫ የትግራይ ክልል ሉዐላዊነት እንዲከበርና በጦርነቱ ወቅት የመብት ጥሰት የፈፀሙ በዓለማቀፍ ደረጃ እንዲጠየቀ መደረግ አለበት ብሏል። ከኤርትራ ሕዝብ ጋር በጋራ ጥቅም ላይ የተመሰረተ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነትን ለመቀጠል ዝግጁነቱን ገልፆ፣ በመላው አለም የሚኖሩ ኤርትራውያን የኤርትራ ጦር ከትግራይ ሙሉ በሙሉ ለቆ እንዲወጣ ግፊት እንዲያደርጉ ጠይቋል።

2. በሜድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ስር ያለው ሞሐ የለስላሳ መጠጦች ፋብሪካ በፀጥታ ችግር ምክንያት ሦስት ፋብሪካዎቹን ሥራ ማስጀመር አልቻልኩም ማለቱን ካፒታል ጋዜጣ ዘግቧል። የሜድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ አካለወልድ አድማሱ፣ ባለዉ የፀጥታ ችግር ምክንያት ሦስቱን ፋብሪካዎች ሥራ አልጀመሩም ማለታቸውን ዘገባው ገልጿል። አካላወልድ ለሦስቱ ፋብሪካዎች ጥሬ እቃ መጓጓዝና ምርቱን ማከፋፈል እንዳልተቻለ መናገራቸው የጠቀሰው ዘገባው፣ የሞሐ ለስላሳ መጠጦች ኢንዱስትሪ በተቀሩት ፋብሪካዎቹ በተወሰነ ደረጃ ምርት መጀመሩን አመልክቷል።

3. ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለሶስት አዳዲስ የፖለቲካ ፓርቲዎች ዕውቅና (የምዝገባ ሰርተፍኬት)  ሰጠ። ዕውቅና የተሰጣቸው የፖለቲካ ፓርቲዎች ‘የወሎ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ’ (ሀገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲ) ፤‘የኩሽ ህዝቦች ብሔራዊ ንቅናቄ’ (ክልላዊ የፖለቲካ ፓርቲ) እና ‘ብሔራዊ ባይቶ ዓባይ ትግራይ’ ( ሀገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲ) ነው፡፡

4. ኬንያ 2 ቢሊየን  ዩሮቦንድ ልትገዛ ነው። ኬንያ 300 ሚሊየን ዶላር ዩሮቦንድ ባለፈው ሐምሌ ወር ልትገዛ አቅዳ በወለድ መብዛት ሳቢያ ሳይሳካ መቅረቱት የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ዊልያም ሩቶ ለሮይተርስ ተናግረዋል። አሁን ያለው የገበያ ሁኔታ የሚያደፋፍር ስለሆነ ቢበዛ በሁለት ወር ጊዜ ውስጥ ኬንያ 2 ቢሊየን ዩሮ ቦንድ ለመግዛት ወስናለች። ዕዳዋን መክፈል ያቅታት እንደሆነ የተጠየቀት ሩቶ፣ የሚያሰጋን ነገር የለም ብለዋል። [ዋዜማ]

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በባለፉት ስድስት ወራት በመዲናዋ የሚገኙ 38 ቅርሶች በቅርስነት መመዝገባቸው ተገለጸ

የአዲስ አበባ ከተማ ባሕል፣ ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ በአዲስ አበባ የሚገኙ 38 ቅርሶችን በቅርስነት መመዝገቡን ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቋል፡፡ የቢሮው የቅርስ ጥበቃና እንክብካቤ ዳይሬክተር አቶ ደጀኔ ወለደጨርቆስ በከተማዋ ውስጥ የሚገኙ ቅርሶችን የመለየት ፤ የማጥናት ፤ የመጠበቅ እንዲሁም የመንከባከብ ስራ እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በተለይ አዲስ አበባ የዘመን ምልክት የሆኑ ቅርሶች መገኛ እንደመሆኗ መጠን በዚህ ረገድ ምን እየተሰራ ይገኛል ያልናቸው ኃላፊው ቅርሶችን በመለየት የመመዝገብ ስራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ ብለዋል፡፡

በመዲናዋ ውስጥ የሚገኙ ቅርሶች የመመዝገቢያ መስፈረቶቻቸው ምንድነው እንዲሁም ተመዝገበው ከሚገኙ ቅርሶችስ የትኞቹ ከፍተኛው ቁጥር ይዛሉ ያልናቸው ኃላፊው በዓለም አቀፍ መመዘኛዎችን መሰረት ምዝገባው እንደሚካሄድ ጠቁመዋል፡፡

አሁን በአጠቃላይ በአዲስ አበባ 316 ቅርሶች በቅርስነት ተመዝግበው እንደሚገኙ የተገለጸ ሲሆን በባለፉት ስድስት ወራት ደግሞ ወደ 38 የሚሆኑ ቅርሶች በቅርስነት ተመዝግበዋል ተብሏል፡፡

መናኸሪያ ሬዲዮ

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ከ700 በላይ ተጠርጣሪዎች የሰብዓዊ መብት አያያዝ ሁኔታ ተመርምሮ ለአስቸኳይ ጊዜ አስፈጻሚ እዝ ቀርቧል - ጌዴዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር)

ከ700 በላይ ተጠርጣሪዎች የሰብዓዊ መብት አያያዝ ሁኔታ ተመርምሮ ለአስቸኳይ ጊዜ አስፈጻሚ እዝ መቅረቡን የፍትህ ሚኒስትር ጌዴዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ገለጹ።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት እያካሄደ ባለው 13ኛ መደበኛ ስብሰባ የፍትህ ሚኒስቴር የ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርትን እያዳመጠ ይገኛል።

ሚኒስትሩ ጌዴዮን ጤሞቲዎስ (ዶ/ር) የሚኒስቴሩን አፈጻጸም ባቀረበው ሪፖርት በባህር ዳር፣ ጎንደር እና ኮምቦልቻ ከተሞች በሚገኙ የማቆያ ስፍራዎች የ706 ተጠርጣሪዎች የሰብዓዊ መብት አያያዝ ሁኔታ ተመርምሮ ለአስቸኳይ ጊዜ አስፈጻሚ እዝ እንዲቀርብ መደረጉን ገልጸዋል፡፡

በሌላ በኩል የሀብት ምርመራ መዛግብት ውሳኔ የመስጠት ምጣኔ በሚመለከት ምርመራቸው ተጠናቆ ለሀብት ማስመለስ ዐቃቤ ሕግ ተላልፈው በተቀመጠው ጊዜ ውሳኔ የተሰጠባቸው 137 መዛግብት ውስጥ በ120 መዛግብት ላይ ውሳኔ መሰጠቱንም ማብራራታቸውን የምክር ቤቱ መረጃ አመላክቷል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በቅርቡ ጸድቆ ወደ ትግበራ ሊገባ ነው የተባለለት የ2 ቁጥር ተሽከርካሪን በሚመለከት የወጣው መመሪያ በውል ያልተጠናና ለማንም የማይጠቅም ነው ተባለ

የ2 ቁጥር ተሸከርካሪን ጠዋትና ማታ በስራ ሰአት መውጫና መግቢያ እንዳይንቀሳቀሱ ማገድ ፈጽሞ ሊተገበር የማይገባው የሰዎችን የኑሮ ሁኔታ ያላገናዘበ መመሪያ ነው ሲሉ አሽከርካሪዎቹ ለመናኸሪያ ሬዲዮ በሰጡት ሀሳብ ገልጸዋል፡፡

ህጎች ሲወጡ መጀመሪያ መታየት ያለበት ማንን ለመጠቅም ነው የሚለው መሆን እንዳለበት አሽከርካሪዎች ተናግረዋል።

በ 2 ቁጥር ተሸከርካሪ የህክምና ባለሙያዎች፣ መምህራን፤ ጠበቆች እና ሌሎችም ሰራተኞች ተጉዘው ህዝብን እንደሚያገለግሉ የተዘነጋበት መመሪያ ነው ሲሉ ከመናኸሪያ ሬዲዮ ጋር ቆይታ ያደረጉ አሽከርካሪ ተናግረዋል፡፡

በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ ሃሳብ የሚያነሱት ሌላኛው አሽከርካሪ በአብዝሃኛው የመንግስትና የግል ሰራተኛ የሚያሽከረክሩት የሁለት ቁጥር ተሸከርካሪ መሆኑን ገልጸው፤ በትራንስፖርት እና ሎጀስቲክ ሚኒስቴር የቀረበው መመሪያ የአብዝኛውን ሰራተኛ ስራ የሚያጓትትና ኑሮውን የሚያስተጓጉል ነው ይላሉ።

ይህንን ይጸድቃል ተብሎ የሚታሰበውን መመሪያ ተከትሎ የምጣኔሃብት ባለሙያዎች ምን ይላሉ ሲል መናኸሪያ ሬዲዮ ባለሙያዎቹን አነጋግሯል።

የፋይናንስና ኢንቨስትመንት ረዳት ፕሮፌሰሩ ዶ/ር ሰዋለ አባተ ጉዳዩ ከአሉታዊ የምጣኔ ሃብት ተጽእኖም በተጨማሪ የመንቀሳቀስ መብትን የሚገድብ ነው ብለዋል።

አክለውም በራሱ ትራንስፖርት ሲንቀሳቀስ የነበረን ሰው በማገድ ወደ ሌላው የህዝብ ትራንስፖርት በመሄድ ጫና መፍጠር ወጭ ይበዛበታል ከተባለው ነዳጅ ተለይቶ አይታይም በማለት ህጉ መጽደቅ እንደሌለበት ይናገራሉ።

ሌላኛው የምጣኔ ሃብት ባለሙያ አቶ ያሬድ ሃይለመስቀል በበኩላቸው ጉዳዩ በድጋሜ ሊጠና እንደሚገባው ተናግረዋል።

እንደ አቶ ያሬድ ሀሳብ አሁን ባለበት ሁኔታ መመሪያው የሚጸድቅ አይደለም፤ ይኸው መመሪያ ማንንም ወገን እንደማይጠቅም እና ጉዳቶቹ በግልጽ የሚታዩ መሆናቸውን ባለሙያው ተናግረዋል፡፡

ህዝብን ያላማከል ውሳኔ በድንገት በመወሰን ማህበረሰቡን ለተጨማሪ ምሬት መዳረግ አግባብ እንዳልሆነ በባለሙያዎችም ሆነ በቅሬታ አቅራቢዎች ተመላክቷል።
(መናኸሪያ ኤፍ ኤም)

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ትናንት ምሽት መታሰራቸዉ ተነገረ

አብንን ወክለው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የሆኑት ደሳለኝ ጫኔ እንደታሰሩ ቤተሰባቸው ተናገሩ። በ2013 በተካሄደው ስድስተኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ በባህርዳር ከተማ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ፓርቲን ወክለው ተወዳድረው የተመረጡት እና የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የሆኑት ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) መታሰራቸውን ቤተሰባቸው ተናግሯል።

ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) ቤተሰብ አባል ለአልዐይን እንዳሉት ከሆነ "ትናንት ጥር 22 ቀን 2016 ዓ .ም ምሽት 3:30 ላይ የፌደራል ፖሊስ አባላት የጸጥታ ሀይሎች መጥተው ደሳለኝ ጫኔን ለጥያቄ እንፈልግሀለን ብለው ወስደውታል" ብለውኛል ሲል አል አይን ዘግቧል።

ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) ሜክሲኮ በሚገኘው የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል ምርመራ ቢሮ ታስረው እንደሚገኙ የነገሩን እኝህ የቤተሰብ አባል የፌደራል ፖሊሶቹ ለጥያቄ እንፈልግሀለን ከማለት ውጪ ምንም ያሉት ነገር የለም ሲሉም ነግረውኛል ሲል አል አይን ዘግቧል። ዛሬ ጠዋት ጀምሮም ተጨማሪ የፌደራል ፖሊስ አባላት ወደ መኖሪያ ቤቱ መጥተው ፍተሻ በማድረግ ላይ መሆናቸውንም ተነግሯል።

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ጀይላን አብዲ ስለ ጉዳዩ መረጃ እንዲሰጡን ላቀረብንላቸው ጥያቄ "አሁን ላይ ስለ ጉዳዩ መረጃ የለኝም" ሲሉ ተናግረዋል።

Via አል አይን
@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ምክንያቶች ስራ ያቆሙ የነዳጅ ማደያዎችን ቢኖሩም ሄዶ ለማየት አስቸጋሪ ሆኖብኛል ሲል የነዳጅ እና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን ገልፅዋል፡፡

በኦሮምያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የተዘጉ የነዳጅ ማደያዎች አሉ ነገር ግን ተንቀሳቅሶ ለማየት እና ያሉበትን ሁኔታ ለማወቅ የሰላም እና ፀጥታ ጉዳይ እንቅፋት ሆኖብኛል ሲል ባለስልጣኑ ቅሬታውን አስታውቋል፡፡

በዚህ ሁኔታ ዉስጥም ቢሆን ከተለያዩ የፀጥታ አካላት ጋር በመሆን የነዳጅ ስርጭቱን ለማዳረስ ጥረት እየተደረገ ነው ሲሉ የገለፁት የነዳጅ እና ኢነርጅ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሳህረላ እብዱላሂ ናቸዉ፡፡

ተዘግተዉ የነበሩ የነዳጅ ማደያዎች ዳግም ወደ ስራ የሚገቡበትን ሁኔታ ለማመቻቸት ስራዎች እየተሰሩ ነው ያሉት ዋና ዳይሬክተሯ ለመሳካቱ ግን ሰላምን ቀዳሚ ጉዳይ ነው ብለውታል፡፡

[Ahadu]
@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
2024/10/05 11:19:04
Back to Top
HTML Embed Code: