Telegram Web Link
በደሴ ዙሪያ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ13 ሰዎች ህይወት አለፈ

መነሻውን ደሴ መድረሻው አቀስታ ያደረገና 21 ተሳፋሪዎችን ጭኖ ሲጓዝ የነበረ በተለምዶ "አባዱላ" እየተባለ የሚጠራ ተሽከርካሪ እግብ ከቀኑ 5:45 ሰዓት በደሴ ዙሪያ ወረዳ 034 ቀበሌ አደይ ት/ቤት አካባቢ ባደረሰው አደጋ የ12 ሰዎች ሕይወታቸው ወዲያውኑ አልፏል።

አንድ ሰው ለህክምና በመንገድ ላይ እንዳለ ሕይወቱ ማለፉን በደሴ ዙሪያ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት የትራፊክ ባለሙያ ዋና ሳጅን ኤፍሬም ይመር ገልጸዋል።

7 ሰዎች ደግሞ ከባድ ጉዳት ደርሶባቸው በደሴ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው እንደሚገኝና የአደጋው መንስዔ እየተጣራ መሆኑን ባለሙያው ጠቁመዋል።

መረጃው የዞኑ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ነው

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ቦርድ የገለልተኝነት ጥያቄ ተነሳበት!!

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሀን ቦርድ  የፖለቲካ ፓርቲ አባላት ጣልቃ ገብነት አለበት ተባለ፡፡

የመገናኛ ብዙሀን ቦርድ  ከፖለቲካ ፓርቲ ነፃ በሆኑ ሰዎች መቋቋም እንዳለበት ቢቀመጥም ተግባራዊ መሆን ሳይችል ቀርቷል ተብሏል፡፡

ይህን ያሉት የህግ ባለሙያዎች ለሰብዓዊ መብቶች ድርጅት ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ አምሃ መኮንን  ናቸው፡፡
ዋና ዳሬክተሩ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዝሀን ቦርድ ገለልተኝነት ጥያቄ ይነሳበታል ብለዋል፡፡

ቦርዱ ቀላል የማይባሉ አባላቱ የፖለቲካ ፓርቲ አባላት የሆኑ ባለስልጣኖች የተካተቱበት በመሆኑ ቦርዱ እንደታሰበው ገለልተኛ መሆን አልቻለም ብለዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ የኢትዮጲያ መገናኛ ብዙሃን ህግ በመንግስት እየተጣሰ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ጋዜጠኞች የተጠረጠሩበት ወንጀል ቢኖር እንኳን መታሰር ሳያስፈልጋቸው ተጣርቶ ክስ መቅረብ እንዳለበት አዲሱ የሚዲያ ህግ ቢያስቀምጥም መሬት ላይ ያለው እውነት ግን ከዚህ የራቀ መሆኑን አቶ አምሃ ለጣብያችን ይናገራሉ፡፡

ከህጉ ድንጋጌ ውጪ በርካታ ጋዜጠኞችና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ሲታሰሩ፣ታስረውም ለረጅም ግዜ ምርመራ ሲቆዩ አንዳዶቹም ከሀገር ሲሰደዱና ህይወታቸው ሲያልፍ ጭምር እየታየ መሆኑን ያስረዳሉ፡፡

የመብት ተሟጋቹ ይህ ሁኔታ መቆም አለበት ያሉ ሲሆን ጉዳዩ የጋዜጠኞች የግል የፍትህ ጥያቄ ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ የህብረተሰቡ መረጃ የማግኘት መብት ላይ ጫና የሚፈጥር ነው ሲሉ ለጣብያችን ተናግረዋል፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘም  የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች (ሲፒጄ) ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ባወጣው ዓመታዊ ሪፖርት በጋዜጠኞች እስር ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ሃገራት ሶስተኛ ደረጃ ላይ መቀመጧን አስታውቋል፡፡

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
" የኦሮሚያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መንበረ ጵጥሮስ " አቋቁመናል ካሉት ውስጥ ሶስቱ መታሰራቸውን የእንቅስቃሴው አስተባባሪ ነኝ ያሉ ዲያቆን አክሊሉ ዓለሙ የተባሉ ግስለሰብ ለቪኦኤ ሬድዮ በሰጡት ቃል ተናግረዋል!!

ሶስቱ አባቶች የታሰሩት " መንበረ ጴጥሮስ " አቋቁመናል የሚል መግለጫ ከሰጡ በኃላ ሸገር ከተማ አስተዳደር በሚገኘው ቢሯቸው እንደሆነ እኚሁ አስተባባሪ ተናግረዋል።

የታሰሩት ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ማዕረጋቸውን ገፍፌዋለሁ ያለቻቸው አባ ገብረማርያም ነጋሳ፣ አባ ወልደ ኢያሱስ ኢፋ እንዲሁም አባ ወልደኢየሱስ ተስፋዬ እንደሆኑ ለመረዳት ተችሏል።

ሌሎችም አብረው የነበሩ ግለሰቦች መያዛቸውም ተነግሯል።

የሸገር ከተማ አስታዳደር ፖሊስ ስለጉዳዩ ምንም ያለው ነገር የለውም።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ትላንት ተቋቁሟል የተባለውን " መንበረ ጴጥሮስ " አውግዛ ፤ አሁን በሕገወጥ ድርጊታቸው የቀጠሉትን ቡድኖች በፍርድ እንደምትጠይቅ አሳውቃ ነበር።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የአውሮፓ ኅብረት የሰብዓዊ መብቶች ልዩ መልዕክተኛ ኤሞን ጊልሞር ትናንት በኢትዮጵያ ጉብኝት አድርገዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ደኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አረጋ ትናንት በጽሕፈት ቤታቸው ከልዩ መልዕክተኛው ጋር እንደተወያዩ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ገልጧል።

ውይይቱ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት በነደፈው የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ፣ በፕሪቶሪያው የግጭት ማቆም ስምምነት አተገባበርና በቀጠናዊና ዓለማቀፋዊ ጉዳዮች ዙሪያ ያተኮረ ነበር ተብሏል።

ሌሎች የኢትዮጵያ መንግሥት የሰብዓዊ መብት አያያዝ ጉዳዮች በውይይቱ ይነሱ አይነሱ አልተገለጠም።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በአዲስ አበባ ከተማ የደም ግፊት በሽታ በአሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ተነገረ

👉 በከተማዋ ከአንድ መቶ ሰዎሽ 23 በሚሆኑት ላይ በደም ግፊት በሽታ እንደሚያዙ ተጠቁሟል


በአዲስ አበባ ከተማ  በደም ግፊት በሽታ እየተያዙ ያሉ ሰዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን ተከትሎ ሁኔታው አሳሳቢ ደረጃ ላይ ይገኛል ሲል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ አስታውቋል።በቢሮው ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ወንድወሰን በርሄ ለብስራት ሬድዮና ቴሌቪዥን እንደገለጹት በተደረገው ጥናት መሰረት እንደ ሃገር ከአንድ መቶ ሰዎች በ16ቱ ላይ በሽታው እንዳለ ያሳያል።

በአዲስ አበባ ከተማ ደረጃ ደግሞ ከአንድ መቶ ሰዎች 23 የሚሆኑ በከፍተኛ የደም ግፊት በሽታ ይይዛሉ ፡፡የደም ግፊት በሽታ ስርጭት ከጊዜ ወደ ጊዜ በአዲስ አበባ ከተማ እየጨመረ በመምጣቱ በርካታ ዜጎች ለስነ ልቦና ፣ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግር እየዳረገ ይገኛል።

በሽታው ባህሪው ለረጅም ዓመታት ምንም አይነት ምልክትን ሳያሳይ በሰውነት ውስጥ መቆየቱ በበሽታው የመያዝና የመጠቃት እድልን ከፍተኛ እንዲሆን አድርጎታል ብለዋል።በተጨማሪም ጤናማ የአመጋገብ ስርዓትን  አለመከተል፣ አካላዊ እንቅስቃሴ አዘውትሮ አለማድረግ፣ ትምባሆ ማጨስ ፣ አልኮል መጠጥን አብዝቶ መጠጣት ፣ ጨው  እና  ስብ የበዛባቸውን ምግቦች አዘወትሮ መመገብ  ዋና ዋና የሚባሉ አጋላጭ መንስኤ እንደሆኑ አቶ ወንደሰን ጨምረው ለብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል፡፡

ቢሮው  በ2016 በጀት ዓመት ሶስት ወራት ውስጥ ብቻ  ለ560 ሺህ  ለሚሆኑ ነዋሪዎች  የደም ግፊት ልየታ እና ምርመራ ማድረግ መቻሉን ቡድን መሪው ገልጸዋል። በተደረገው ምርመራ 25 ሺህ 931 የሚሆኑ ሰዎች የደም ግፊታቸው ጨምሮ የተገኘ ሲሆን  ከእነዚህም ውስጥ 17 ሺህ 300  የሚሆኑ የህክምና አገልግሎት ክትትል መጀመራቸውን አመልክተዋል፡፡

ችግሩን ለመፍታት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳር ጤና ቢሮ  የደም ግፊትን ጨምሮ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን ለመከላከል ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል ተብሏል፡፡ከዚህ ቀደም በማዕከል ደረጃ ሲሰጥ የነበረውን የደም ግፊት የህክምና አገልግሎት በጤና ጣቢያዎች እንዲሰጥ እየተደረገ እንደሚገኝ የተገለጸ ሲሆን  ምርመራውም በነጻ እንዲሰጥ እየተሰራ ይገኛል፡፡

መረጃዎች እንደሚያሳዩት ማንኛውም እድሜው 30 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆኑ ሰዎች ሁሉ ለደም ግፊት የመጋለጥ እድል ሊኖራቸው ይችላል። የደም ግፊት ዋና ዋና ምልክቶች ራስ ምታት፣ ትንፋሽ ማጠር፣ ነስር፣ የድካም ስሜት፣ የደረት ህመም፣ የእይታ መድከም፣ በሽንት ውስጥ ደም መታየት መሆናቸውን የህክምና ባለሙያዎች ይገልጻሉ። የደም ግፊትን በመለካት፣ የደም ግፊት ህመም እንዳለ ወይም አለመኖሩን ማወቅ ተገቢ እንደሆነ የህክምና ባለሙያዎች ይመክራሉ፡፡

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
መረጃዎች‼️

የዕለተ ሀሙስ የምሽት ሰበር መረጃዎች እነሆ👇👇

ዝርዝሮቹን
ይመልከቱ👇
https://youtu.be/l5TwVOHTGFY https://youtu.be/l5TwVOHTGFY
“ 12 የኦሮሚያ ሚሊሻዎች ተገድለዋል ” - የትፋቴ ቀበሌ ሊቀመንበር

“ እውነት ነው። እኔ እንደ ባለሙያ ሁለት ሰዎች የተመቱ አይቻለሁ ” - የዓይን እማኝ የጤና ባለሙያ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን ሳርማሌ ወረዳ በትፋቴ ቀበሌ መንግሦት “ሸኔ” ብሎ የሚጠራቸው  ታጣቂዎች በድንገት አደረሱት በተባለ ጥቃት 12 የኦሮሚያ ክልል ሚሊሻዎች መገደላቸውን የዞኑ ሆስፒታል ባለስልጣንና የሆስፒታሉ ጤና ባለሙያ፣ የትፋቴ ቀበሌ ሊቀመንበርና የዓይን እማኞች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጠዋል።

የዓይን እማኞቹ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የገለጹት፣ 9ኙ ሚሊሻዎች እሬሳቸው ሆስፒታል አድሮ መሸኘቱን፣ 3ቱ ደግሞ በምዕራብ ጉጂ ዞን በጋላና አባያ ወረዳ ኤርጋንሳ ወይም ፃልቄ ቀበሌ መመለሳቸውን ነው።

ሚሊሻዎች ተገደሉ የሚባል መረጃ ደርሶናል እውነት ነው ? ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ ላቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምለሽ በኮሬ ዞን የትፋቴ ቀበሌ ሊቀመንበር አቶ መሐመድ ኪታሞ በሰጡት ቃል፣ “እውነት ነው ሚሊሻዎች ተገድለዋል” ብለዋል።

“ፃልቄ የሚባል አካባቢ (በገዳና ፃልቄ መካከል) ላይ 12 የኦሮሚያ ሚሊሻዎች ተገድለዋል” ያሉት ሊቀመንበሩ፣ ድርጊቱ የተፈጠረው “ሰኞ ዕለት (ጥር 13 ቀን 2016 ዓ/ም) ነው” ሲሉ ተናግረዋል።

አክለው ፤ “ሌሎች ታካሚዎችም አሉ። እኔ ከእነርሱ ጋር አይደለም የቆጠርኩት። የሞቱ ብቻ 12 ናቸው” ብለዋል።

ጥቃቱን ያደረሱት የ “ሸኔ” ታጣቂዎች ናቸው እንዴ ? ተብለው ሲጠየቁም፣ “አዎ የኦሮሚያ ሚሊሻዎች ከሸኔ ጋ ተገናኝተው” ብለዋል።

ስለ ጉዳዩ #ማረጋገጫ እንዲሰጡን ተመሳሳይ ጥያቄ ያቀረብንላቸው የኬሌ ከተማ ሆስፒታል ሥራ አስኪያጅ አቶ በለጠ በበኩላቸው ፤ “ እኛ ጋ በእርግጥ የህክምና አገልግሎት ለመቀበል የመጡ 2 በጥይት የተመቱ ነበሩ። ከዚያ ወጪ ዘጠኝ እሬሳ እንደመጣና በዚሁ እንዳለፈ ነው የምናውቀው” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

“ መረጃው የደረሰኝ ሁለቱ ተወግተው መጥተው አገልገሎት አግኝተው እንደሄዱና ዘጠኙ እሬሳ ግቢ ገብቶ (ለማሳደር ከምሽቱ 3 በኋላ ነው ያመጧቸው” ያሉት ሥራ አስኪያጁ፣ “አሁን ያሉበትን ደረጃ ባናውቅም ሁለቱ ታክመው ነው የሄዱት” ሲሉ ገልጸዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ተጨማሪ ማብራሪያ እንዲሰጡ ስለ ጉዳዩ ጥያቄ ያቀረበላቸው የሆስፒታሉ የጤና ባለሙያ አቶ ገዛኸኝ እንደሻ በበኩላቸው፣ “እውነት ነው። እኔ እንደ ባለሙያ ሁለት ሰዎች የተመቱ አይቻለሁ። ታክመው ለተጨማሪ ህክምና ሂደዋል ጠዋት። የእነርሱ አመራርሮችም (የታካሚዎቹ) መጥተው ነበር” ብለዋል።

አክለውም፣ “የእኛ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ነው። የእነርሱ ደግሞ ኦሮሚያ ክልል ስለሆነ በአቅራቢያ በሚገኘው ዞን መጥተው ነበር ወደ እኛ፣ ሲታከሙ አድረው ሂደዋል። የተመቱት የኦሮሚያ ጉጂ ዞን ሚሊሻዎች ናቸው” ሲሉ አስረድተዋል።

#tikvahethiopia

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ሰበር መረጃ‼️

አቶ ደመቀ መኮንንን ከኃላፊነታቸው ተሸኙ

የብልጽግና ማዕከላዊ ኮሚቴ አቶ ደመቀ መኮንንን ከኃላፊነታቸው በክብር በመሸኘት አቶ ተመስገን ጥሩነህን  ምክትል ፕሬዝዳንት አድርጎ መርጧል፡፡

የብልጽግና ማዕከላዊ ኮሚቴ የፓርቲውን የአመራር የመተካካት መርህን እና የአሰራር  ስርዓት በመከተል ዛሬ ባካሄደው ማጠቃለያ ስብሰባ፤ በሙሉ ድምፅ  አቶ ደመቀ መኮንን በክብር ሸኝቷል።

በምክትካቸውም የፓርቲው ስራ አስፈጻሚ የነበሩትን አቶ ተመስገን ጥሩነህን ምክትል ፕሬዝዳንት አድርጎ በአብላጫ ድምጽ መርጧል።

@merkato_media
@merkato_media
ሰበር‼️

እኛም ስልጣን እንልቀቅ አብይ አህመድ
የሽግግር መንግስት እናቋቁም ዐብይ

ሙሉውን በዚ
ሊንክ ያድምጡ👇👇
https://youtu.be/SF_jUi9s34U
https://youtu.be/SF_jUi9s34U
ከታጣቂ ቡድኖች ጋር የተጀመሩ ሰላማዊ አማራጮች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ የብልጽግና ማዕከላዊ ኮሚቴ ወሰነ

የብልጽግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ ከታጣቂ ቡድኖች ጋር የተጀመሩ ሰላማዊ አማራጮች እንዲጠናከሩ አቋም መያዙ ተገለጸ።

ፓርቲው የስብሰባው መጠናቀቅን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ የኢኮኖሚ ዕድገት ላይ ጫና እያሳደሩ ከሚገኙ ጉዳዮች አንዱ “በጠባብ ቡድናዊ ፍላጎት የተፈጠሩ ትሥሥሮች ያስከተሏቸው አካባቢያዊ ግጭቶች” ናቸው ሲል ገልጿል።

እነዚህን ግጭቶች በመፍታት” የብልፅግና ጉዞን” ይበልጥ ለማፋጠን እና የሕዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የተሟላ አገራዊ ሠላም ማስፈን እንዲቻል ከታጣቂ ቡድኖች ጋር የተጀመሩ ሰላማዊ አማራጮች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ አቅጣጫ ተቀምጧል ማለቱን አዲስ ማለዳ ከመግለጫው ተመልክታለች።

“በሰላማዊ የፖለቲካ መንገድ ጥያቄዎቻቸውን ለሚያቀርቡ አካላት ሰላማዊ መንገዶች እስከሚቻለው ድረስ እንዲመቻቹ፤ ዓላማቸው በነፍጥ ፍላጎታቸውን ማስፈጸም በሆኑ አካላት ላይ ደግሞ፣ ተገቢው ሕግን የማስከበር ሥራ በተጠናከረ መንገድ እንዲካሄድ” ሲልም የብልጽግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ ውሳኔ አሳልፏል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ከትግራይ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ጋር በጦርነቱ ምክንያት የተቋረጠውን የኹለትዮሽ ግንኙነት ለማስቀጠል ይቅርታ ጠይቋል።

ትግራይ ክልል በጦርነቱ ወቅት ችግር ላይ በነበረበት ወቅት ቁሳዊና መንፈሳዊ ድጋፍ አለማድረጉን የጠቀሰው ምክር ቤቱ፣ የግጭት ማቆም ስምምነቱ ከተፈረመ በኋላ በክልሉ ጉብኝት አለማድረጉ እንዲኹም የክልሉ የእስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት መግለጫ ሲያወጣ ምላሽ አለመስጠቱ ስሕተት እንደነበር ገልጧል።

ጠቅላይ ምክር ቤቱ፣ ከክልሉ እስልምና ምክር ቤት ጋር ተቋርጦ የቆየው ግንኙነት እንዲጠናከርና እንደገና በጋራ መስራት እንዲጀመር ጠይቋል።

የክልሉ ከፍተኛ ምክር ቤትም ይቅርታውን መቀበሉን አስታውቋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
መረጃ‼️

በመጨረሻም አቶ ደመቀ መኮነን እውነታው ተናገሩ::
ጦርነት ይቅር ስላልኩ አብይ አባረረኝ
የሚኒስትሮቹ ፍጥጫ👇👇

ዝርዝር መረጃዎቹን በዚ
ሊንክ ይመልከቱ👇👇
https://youtu.be/GrZ9w_RdaN0
https://youtu.be/GrZ9w_RdaN0
በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሐረርጌ ዞን ጎለ ኦዳ ወረዳ ቡርቃ ከተማ ሰሞኑን በተከሰተ የኮሌራ በሽታ ካለፉት ኹለት ወራት ወዲህ 14 ሰዎች ሕይወታቸው ማለፉን ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ አንድ በመንግሥት ጤና ጣቢያ ውስጥ የሚሠሩ የጤና ባለሙያ ለዋዜማ ተናግረዋል።

ከሟቾች መካከል ስምንቱ ወንዶች ሲኾኑ፣ ስድስቱ ሴቶች መኾናቸውን ባለሙያው ተናግረዋል።

ባለሙያው በሽታው ወደሌሎች አካባቢዎች ሊዘመት ይችላል የሚል ከፍተኛ ስጋት እንዳለ የገለጡት ባለሙያው፣ የበሽታው ምልክት በብዛት እየታየ ያለው በሕጻናትና በአረጋዊያን ላይ እንደኾነ ጠቅሰዋል።

በሽታው አጣዳፊና አስቸኳይ ሕክምና እንደሚፈልግ የገለጡት ባለሙያው፣ ታማሚዎች በሚፈለገው ፍጥነት ሕክምና አለማግኘታቸው የሟቾችን ቁጥር ከፍ ሊያደርገው እንደሚችል ስጋታቸውን ገልጸዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
#ሶማሌላንድ

" ከአካባቢው ጋር በተያያዘ ሰፊ ሌላ ዓላማ ላላቸው #ግብፆች ምን አስጨነቀን ? " - አምባሳደር አብዱላሂ ሞሀመድ

ኢትዮጵያ እና ሶማሊላንድ የተፈራረሙትን የመግባቢያ ስምምነት ለማጠናቀቅ " አሁን ከሁለቱም ወገኖች የቴክኒክ ኮሚቴ በመዋቀር ላይ ነው " ሲሉ በኢትዮጵያ የሶማሊላንድ ተወካይ አምባሳደር አብዱላሂ ሞሀመድ ተናገሩ።

አምባሳደር አብዱላሂ ይህን ያሉት ለዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ በሰጡት ቃል ነው።

የሶማሊላንዱ ተወካይ ፦ " ጉዳዩን ለማጠናቀቅ አሁን ከሁለቱም ወገኖች የቴክኒክ ኮሚቴ በማዋቀር ላይ ነን። እና ይህ ቀድሞውኑ በሂደት ላይ እንደሆነ እርግጠኛ ነኝ።

(ፊርማውን ትከትሎ) ግንኙነቶች ነበሩ። በሁለቱ ሀገሮች መካከል ጉብኝቶች ነበሩ።

የውጭ ጉዳይ እና የአለም አቀፍ ግንኙነት ሚኒስትራችን ባለፈው ሳምንት ነው የተመለሱት። እሳቸው እዚህ (አዲስ አበባ) ከእኔ ጋር ነበሩ። ዋና ተግባራቸውም ጉዳዩ መሠረት እንዲይዝ ከኢትዮጵያ አቻዎቻቸው ጋር ለመምከር ነበር።

ይዋል ይደር እንጂ ሁለቱ ኮሚቴዎች ወደ ስራ እንዲገቡ እናደርጋለን። ስለዚህ ይህ በጣም በቅርቡ ይከናወናል ብዬ አስባለሁ " ብለዋል።

ሶማሊላንድ አለምአቀፍ እውቅና ያገኘ ባይሆንም ባለፉት 30 ዓመታት ፦
* ራሱ የሚቆጣጠረው ድንበር ፣
* የራሱ ሰንደቅ ዓላማ ያለው
* ምርጫ ሲያካሂድ የነበረ ፣
* ሕዝቡንም ሲያስተዳድር የቆየ መንግሥት መሆኑን ነው ሲሉ ተናግረዋል።

ከሶማሊያ እና ሌሎች ሀገሮች የተነሳውን ተቃውሞ እንዴት እንደሚመለከቱት የተጠየቁት አምባሳደሩ ፦ " የዓረብ ሊግ፣ ግብፅና ሶማሊያን በተመለከተ፣ በኔ እምነት በዚህ ረገድ ምንም ማድረግ የማይችሉ ይመስለኛል። ያለቀለት የተደመደመ ጉዳይ ነው። ከአካባቢው ጋር በተያያዘ ሰፊ ሌላ ዓላማ ላላቸው ግብፆች ምን አስጨነቀን " ብለዋል።

በመግባቢያ ስምምነቱ መሠረት ሶማሌላንድ በአፀፋው ምን ታገኝ እንደሆንም ተጠይቀው ፥ " ለሶማሌላንድ ዕውቅና መስጠት። ይህ እርግጥ ነው። የዚህ ፕሮግራምም አካል ነው። የስምምነቱም ክፍል እና አካል ነው " ብለዋል።

አምባሳደር አብዱላሂ ሶማሊያ የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የቀጣናው አለመረጋጋት ምንጭ ናት ብለዋል።

ይልቁንም ሶማሊላንድ ለቀጣናው መረጋጋት ጉልህ ድርሻ ያላት መሆኑን ገልፀዋል።

" ኢትዮጵያም፣ ድንበሯም እንዲከበር እንጠብቃለን። ሁለተኛ ፣ ሶማሊላንድ በሕግ የፀና እውቅና ያለው ግዛት ሆኖ መታወቅ አለበት። ምክንያቱም እኛ የአካባቢው ጂኦ ፖለቲካዊ መረጋጋት አካል እና ባለድርሻ ነበርን። ባለፉት አመታት አልሸባብን እና ሽብርተኝነትን እየተዋጋን ነበር። " ብለዋል።

የሶማሊላንድ የኢትዮጵያ ተወካይ አምባሳደር አብዱላሂ ሞሀመድ ፤ " ሶማሊላንድ የሌሎች ሀገሮችም ድጋፍ አላት " ሲሉ ተናግረዋል።

" ሶማሊላንድ በቀጣዩ የአፍሪካ ሕብረት ጉባኤ ይህንን ጉዳይ በሚገባ ትይዘዋለች " ያሉት አምባሳደሩ ፤ " ኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ሌሎች ወዳጆችም አሉን። ከ5 የተለያዩ ክልሎች፤ ለጉዳያችን በጣም በጣም አዎንታዊ አመለካከት ያላቸው አባል ሀገራት (የአፍሪካ ሕብረት) አሉን። " ብለዋል።

" እኛ ሕጋዊ ጉዳይ አለን ፣ የሞራል ጉዳይም አለን ፣ የሚቀረው የፖለቲካ ጉዳይ ብቻ ነው። ለአካባቢው እና ለአህጉሪቱ የምናደርገው በጎ አስተዋፅኦ ተዘንግቷል። የትኛውም አካል የህዝባችን ውሳኔ ላይ ሊወስን አይችልም። ህዝባችን ሕዝበ ውሳኔ አድርጎል። 97.5 በመቶው ነፃ ሀገር መሆንን በመደገፍ ድምጽ ሰጥቷል " ሲሉ ሃሳባቸውን ደምድመዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህ ቃለምልልስ እና መረጃ የዶቼ ቨለ ሬድዮ መሆኑን ያሳውቃል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
አቶ ደመቀ መኮንን በአመራር ዘመናቸው “አጉድየዋለሁ” ላሉት ነገር በይፋ ይቅርታ ጠየቁ🙏

ትናንት ከገዢው ብልጽግና ፓርቲ የምክትል ፕሬዝዳንት ኃላፊነታቸው የተሰናበቱት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፤ በአመራር ዘመናቸው “አጉድየዋለሁ” ላሉት ነገር በይፋ ይቅርታ ጠየቁ። በኢትዮጵያ የሚስተዋለውን “የሀገረ መንግስት ግንባታ ፈተና” ለመሻገር፤ ሕገ መንግስትን ከማሻሻል ጀምሮ ሌሎች ስብራቶችን ማረም እንደሚያስፈልግም አቶ ደመቀ ገልጸዋል።

አቶ ደመቀ ይህን ያሉት በብልጽግና ፓርቲ ትናንት አርብ ጥር 17/2016በተደረገላቸው የሽኝት መርሃ ግብር ላይ ባደረጉት ንግግር ነው። በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ይፋዊ የፌስ ቡክ ገጽ የተጋራው የአቶ ደመቀ ንግግር፤ የኢትዮጵያ “ፖለቲካ እና የስልጣን ቅብብሎሽ” ከዚህ ቀደም “በመጠፋፋት” ላይ የተመሰረት እንደነበር ይጠቅሳል።

እርሳቸው በነበሩበት የአመራር ዘመን “ከሁሉም በላይ ትልቅ ቦታ” የሚሰጡት፤ ይህ አይነቱ አካሄድ “በትውልድ ቅብብሎሽ እና ስልጡን አግባብ መቀጠል ሲችል” እንደሆነ ምኞታቸውን ገልጸዋል። በዚህ ረገድ በዚህ ዘመን “በጎ ጅምር” እንዳለም በንግግራቸው ጠቁመዋል። የብልጽግና ፓርቲ አቶ ደመቀ ከምክትል ፕሬዝዳትነታቸው “በክብር የተሸኙት”፤ የፓርቲውን “የአመራር የመተካካት መርህን እና የአሰራር ስርዓት በመከተል” እንደሆነ አስታውቆ ነበር።

አቶ ደመቀ ለብልጽግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ ባደረጉት ንግግር፤ ለ31 ዓመት ተኩል በአመራርነት መቆየታቸውን አስታውሰዋል። ከኃላፊነት ለመሰናበት ያቀረቡት ጥያቄ “ክብር እና ዕውቅና”ተሰጥቶት፤በፓርቲው ተቀባይነት በማግኘቱ ምስጋናቸውን ገልጸዋል። ጥያቄያቸው ምላሽ በማግኘቱም “በጣም ደስተኛ ነኝ። በጣም ዕድለኛ ነኝ” ሲሉም ተደምጠዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
#አቢሲንያ_ባንክ
አቢሲንያን የሞባይል ባንክ አገልግሎት ወደ *815# በመደወል ብቻ ያለ ኢንተርኔት ወይም በስማርት ፎን መገልገል ይቻላል።ለበለጠ መረጃ የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ!

#BoAmobile #mobilebanking #BoA #bankinginethiopia #banksinethiopia #bankofabyssinia #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
ኑሮ ከበደኝ ያለው መምህር ራሱን አጠፋ😭

..............እስከመቼ

''ሬሳዬን ለቤተሰብ አድርሱልኝ ብሎ በብጣሽ ወረቀት አስፍሮ ራሱን የሰቀለው መምህር "እኔ የዚህችን ምድር ችግርና ንዴት መቋቋም ስላልቻልኩ ነው ራሴን ያጠፋሁት፣ መድረስ የምፈልግብት ቦታ ነበር ያ ግን አልተሳካም" ። ብሎ የዘመዶቹን አድራሻ ወረቀት ላይ አስቀምጦ ራሱን ሰቅሎ ገደለ።

እውቀት ዋጋው ስንት ነው?

መምህር እስከመቼ ትውልድ ለመቅረፅ ልጆቹን በረሃብ ይቅጣ፣ የቤት ኪራይ ደረሰ አለደረሰ ፍራቻ እያሳቀቀው እስከመቼ?፣በተራበ አንጀቱ እውቀትን መመገብ እንዴትስ ይቻለዋል? ሁሉን ቢያወሩ......... ትኩረት ለመምህራን‼️

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
2024/10/05 15:23:51
Back to Top
HTML Embed Code: