Telegram Web Link
30 ሺ ብር ዋጋ ያላቸው ሞባይል ስልኮችን የቀማው ግለሰብ ወንጀሉን በፈፀመ በሁለተኛው ቀን በእስራት ተቀጣ፡፡
**
ሬድዋን ከማል የተባለው ግለሰብ ጥር 15 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ በኮልፌ ቀራኒዩ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ጦር ኃይሎች ሙሉ ወንጌል አካባቢ ከሁለት ሴቶች ግምታቸው 30ሺ ብር የሚያወጡ ሁለት የሞባይል ስልኮችን ቀምቶ ይሮጣል።

ስልካቸው የተቀማው የግል ተበዳዮችም ያሰሙትን የድረሱልን ጥሪ የሰሙ የፖሊስ አባላት እና በአካባቢው የነበሩ ግለሰቦች ወንጀል ፈፃሚውን እጅ ከፍንጅ እንደያዙት በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የአጉስታ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ የወንጀል ምርመራ ማስተባበሪያ ሃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ፍቃዱ ቡሹራ ገልፀዋል።

ፖሊስ በፍጥነት አስፈላጊውን ማስረጃ በማደራጀት የምርመራ መዝገቡን ለአቃቢ ህግ አቅርቦ ክስ ከመሰረተባቸው በኃላ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ኮልፌ ምድብ ችሎት ጉዳዩን ተመልክቶ ግለሰቡ ወንጀሉን በፈፀመ በሁለተኛ ቀን ውስጥ ጥር 17 ቀን 2016 ዓ/ም በዋለው ችሎት ሬዲዋን ከማል በአንድ ዓመት ከ6 ቀር እስራት እንዲቀጣ የወሰነበት መሆኑን ሃላፊው አክለው ተናግረዋል ፡፡

ወንጀል ፈፃሚው ወንጀሉን በፈፀመ በሁለተኛ ቀን ውሳኔ ማግኘቱ የፍትህ ስርዓቱ ፖሊስ ወንጀልን ለመከላከል የሚያከናውነውን ተግባር በከፍተኛ ሁኔታ የሚያጠናከር መሆኑን የምርመራ ሐላፊው መግለፃቸውን ኢፕድ ዘግቧል።

 @ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
አሳዛኝ ዜና‼️

በቦሰት ወረዳ ቤተ ክህነት የመርቆ መካነ ሕይወት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን በታጠቁ ኃይሎች ተቃጠለ!!

በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት በቦሰት ወረዳ ቤተ ክህነት የመርቆ መካነ ሕይወት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን በታጠቁ ኃይሎች ትናንት ጥር 17/2016 ዓ.ም አመሻሽ ላይ ተቃጥሏል፡፡

እንደመረጃው ከሆነ በቦታው ላይ በተደጋጋሚ ጊዜ ዛቻና ማስፈራሪያ ሲያደርጉ የቆዩ ቢሆንም በትናንትናው ዕለት ሙሉ በሙሉ ንዋዬ ቅድሳቱ የተቃጠለ ሲሆን የቤተ መቅደሱ የውስጥና የውጭ ክፍል ጉዳት ያደረሰ ከፍተኛ ቃጠሎ አድርሰዋል፡፡ በጉዳዩ ላይ ሀገረ ስብከቱ አስፈላጊውን የማጣራት ሥራ እየሠራ ይገኛል፡፡

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ፣ በግማሽ በጀት ዓመቱ ለመሰብሰብ ካቀደው አጠቃላይ የገቢ መጠን ውስጥ የሰበሰበው ግማሹን ብቻ እንደኾነ አስታውቋል።

በበጀት ዓመቱ ለመሰብሰብ ያቀደው ገቢ 72 ቢሊዮን ብር መኾኑን የጠቀሰው ቢሮው፣ በግማሽ ዓመቱ የሰበሰበው ገቢ ግን 17 ቢሊዮን ብር ገደማንቾ ብቻ እንደኾነ ገልጧል።

ባለፉት ስድስት ወራት የተሻለ የገቢ አሰባሰብ አፈጻጸም ያስመዘገቡት፣ ሰሜን ወሎ፣ ደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ጎንደር፣ ምዕራብ ጎንደርና ማዕከላዊ ጎንደር ዞኖች እንዲኹም የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ናቸው ተብሏል።

ቢሮው ዝቅተኛ ገቢ የሰበሰበው፣ በዋናነት በክልሉ በተፈጠረው ግጭት ሳቢያ መኾኑን ጠቅሷል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በታጣቂዎች መንገድ ላይ “እየተዘረፍን” እና እየተንገላታን ነው ሲሉ ተማሪዎች


በአማራ ክልል ከተለያዩ ስፍራዎች ወደ መቅደላ አምባ ዩንቨርስቲ የሚገቡ ተማሪች በመንገድ ላይ በታጣቂዎች የሚደረግ ፍተሻ መኖሩንና ተማሪዎች እንዲሁም መምህራን እንዳያልፉ እየተከለከሉ መሆኑን አዲስ ማለዳ ሰምታለች። ለአዲስ ማለዳ ሃሳባቸውን የሰጡ ተማሪዎች እንደገለጹት ታጣቂዎቹ “ተማሪዎች እና መምህራን እንዲያልፉ አይፈልጉም”።

ከጎንደር መነሻውን ያደረገ ሌላ የመቅደላ ዩኒቨርሲቲ ተማሪም ደብረ ታቦር ሲደርሱ ከፊት ለፊታቸው በመኪና መንገድ እንደተዘጋባቸው ይገልጻል። “ከተሳፋሪዎቹ መካከል የሱዳን ስደተኞች ሲቀሩ ሌላውን ተሳፋሪ ስልክ፣ ገንዘብ እና ሌሎች ነገሮችንም” እንደወሰዱ ገልጾ ከዛ በኋላ ግን ከመከላከያ ሠራዊት ጋር በመሆን መጓዛቸውን ለአዲስ ማለዳ ተናግሯል።

ተማሪዎች በተለይም ከመካነ ሰላም እና መርጡ ለማርያም አካባቢዎች ወደ ዩኒቨርሲቲው የመጡ ጥቂት ሲሆኑ፤ በርከት ያለ ቁጥር ያላቸው ተማሪዎች ከመንገድ እንዲመለሱ መደረጋቸውን አዲስ ማለዳ ማወቅ ችላለች።

አዲስ ማለዳ “ታጣቂዎቹ እነማን ናቸው? ምን ዓይነት ናቸው?” በሚል ለተማሪዎች ላቀረበችው ጥያቄ “ማንነታቸውን በእርግጠኝነት መናገር ይከብዳል፤ ነገር ግን ሬንጀር ዩኒፎርም የለበሱም፤ ሲቪሎች እንዲሁም ልብስ ያልበሱ ጭምር አሉ” መኖራቸውን ተማሪዎቹ ያነሳሉ።

በተጨማሪም ታጣቂዎቹ “ተማሪዎች ወደ ተቋማት እንዳይገቡ ብለን ነበር፤ አንድ ዩኒቨርሲቲዎቹ ላይ ችግር ቢፈጠር የምትጎዱት እናንተ ናቹ፤ ለዚህ ነው የምንመልሳቹ” ሲሉ ለተማሪዎች መናግራቸውን አዲስ ማለዳ ሰምታለች።

የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹ ሲመጡ ለደህንነታቸው ኃላፊነት መውሰድ ያለባቸው እራሳቸው ተማሪዎቹ እንደሆኑ በይፋ መግለጹ የሚታወስ ሲሆን፤ በዚህ ሳምንት ጥር 15 ቀን 2016 ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ዘንዘልማ ካምፓስ ተኩስ ተከፍቶ እንደነበር ምንጮች ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል።

በካምፓሱ ያለው ሁኔታ አስጊ በመሆኑም ተማሪዎችን በጊዜያዊ ምደባ ወደ ፖሊ ካምፓስ እንዲዘዋወሩ የተደረገ ሲሆን ተማሪዎች ጊቢውን ለቀው እንዲወጡ የሚያዝ ወረቀት መለጠፉን አዲስ ማለዳ ከተማሪዎች ብትሰማም ወረቀቱን ዩኒቨርሲቲው አልያም ሌላ አካል ይለጥፈው ማወቅ አልተቻለም።

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹን ለመቀበል ሶስት ቀናት ሲቀረው የአዲስ እና የሬሜዲያል ተማሪዎችን መግቢያ ቀን ላልተወሰነ ጊዜ ማራዘሙን ሲገልጽ ለምን እንድተራዘመ የሰጠው ማብራሪያ የለም። በተያያዘ ከቀናት በፊት የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ በማንኛውም ጊዜ የፀጥታ ችግር ቢከሰት ሃላፊነቱን አልወስድም ማለቱም አይዘነጋም።

አዲስ ማለዳ ያነጋገረቻቸው ተማሪዎች ከመርጡ ለማርያም ተነስተው ወደ መካነ ሰላም ለመጓዝ ዓባይ ወንዝ ላይ ከባድ ፍተሻ በታጣቂዎች እንደሚከናወን ገልጸው ከመርጡ ለማሪያም ወደ መቅደላ ለመሄድ ሾፌሮችም ፈቃደኛ አለመሆናቸውን ተናግረዋል።

“የተማሪነት መታወቂያ እና የትምህርት ማስረጃ የያዘ ሰው ማለፍ ቀርቶ፣ የሚወርድበት የዱላ መዓት አይጣል ነው” የሚለው የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ ለመጀመሪያ ዓመት ምዝገባ የሚያስፈልገውን የትምህርት ማስረጃ ይዞ በመጓዝ ላይ ነበር። መንገድ ላይ መኪናውን ያስቆሙት ታጣቂዎች ግን ቦርሳውን በመፈተሽ ማስረጃዎቹ በሙሉ ከፊቱ ለፊቱ ቀደው እንደጣሉበት ለአዲስ ማለዳ ገልጿል።

ዩኒቨርሲቲ ከደረሰ በኋላ የትምህርት ማስረጃ ማቅረብ ባለመቻሉ መታወቂያ እና ምዝገባ ማካሄድ አትችልም ተብሎ በዩኒቨርሲቲ ውስጥ መቆየት አትችልም ተብሏል። ይሄው ወጣት፤ ባለው አስቸጋሪ የኢንተርኔት መቆራረጥ ማስረጃውን ከቤተሰብ እንዲላክለት ማድረጉን ጨምሮ ለአዲስ ማለዳ ገልጿል።

ታጣቂዎቹ ሾፌሮችን ገንዘብ እንደሚቀበሏቸው የተገለጸ ሲሆን የተወሰኑ መምህራን የሥራ መታወቂያቸውን ደብቀው በነዋሪነት መታወቂያ ማለፍ ችለዋል ተብሏል። ከተለያዩ አካባቢዎች ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚያቀኑ ተማሪዎች በታጣቂዎች የመታገት፣ የዘረፋ እና ወደመጡበት እንዲመለሱ እየተደረጉ መሆኑን ተማሪዎች ያነሳሉ።

በአማራ ክልል በተፈጠረው የጸጥታ ችግር ምክንያት በክልሉ የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች በ2016 የትምህርት ዘመን የመጀመሪያዉ ወሰነ ትምህርት ተማሪዎቻቸውን ለመጥራትና መደበኛ የመማር ማስተማር ስራቸዉን ሙሉ ለሙሉ ለመጀመር አለመቻላቸው አይዘነጋም።

ሆኖም የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፣ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ፣ የአስሩ ዩኒቨርሲቲዎች ፕሬዝዳንቶችና ጉዳዩ የሚመለከታቸው የክልሉ ጸጥታ አካላት ታህሳስ 18 ቀን 2016 አደረጉ በተባለው ምክክር ተቋማቱ ተማሪዎችን እንዲቀበሉ መወሰኑን ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

አዲስ ማለዳ በጉዳዩ ላይ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ጌታቸው ቢያዝንን ለማነጋገር ያደረገችው ሙከራ ሳይሳካ ቀርቷል።

በውሳኔያቸው ግን “በክልሉ አንጻራዊ ሰላም የተፈጠረ በመሆኑ ዩኒቨርስቲዎቹ ተማሪዎችን መጥራትና ማስተማር ይችላሉ” የተባለ ሲሆን ከጥር 1 ቀን 2016 ጀምሮ ባሉ ሁለት ሳምንታት ጊዜ ውስጥ ዩኒቨርስቲዎቹ ተማሪዎችን ጠርተው የመማር ማስተማር ስራቸውን እንደሚጀምሩ ተገልጾ ነበር።

ይሁን እንጂ በክልሉ ያለው ወቅታዊ ሁኔታ መደበኛ የመማር ማስተማር ስራዎች ለመስራት አስቸጋሪ ስለመሆኑ ለአዲስ ማለዳ የደረሱ መረጃዎች ያመለክታሉ። የሚኒስቴሩን ውሳኔ የአማራ ክልል ተማሪዎች ማህበር በክልሉ ያለው የፀጥታ ችግር ባለበት እንደቀጠለ መሆኑ እየታወቀ የትምህርት ሚኒስቴር ትምህርት ይጀምሩ ማለቱ ትክክል አይደለም በማለት ተቃውሞ ነበር።

ከምንም ነገር በላይ የተማሪዎቹን ደህንነት መጠበቅ የሚቀድም በመሆኑ ማህበሩ እንደ ተቋም ከሚኒስቴሩና ከትምህርት ተቋማት ጋር በመነጋገር ውሳኔውን ለማስቀልበስ የበኩሉን ጥረት እንደሚያደርግም አስታውቋል።

Via:አዲስ ማለዳ

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
#አቢሲንያ_ባንክ
አቢሲንያን የሞባይል ባንክ አገልግሎት ወደ *815# በመደወል ብቻ ያለ ኢንተርኔት ወይም በስማርት ፎን መገልገል ይቻላል።ለበለጠ መረጃ የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ!

#BoAmobile #mobilebanking #BoA #bankinginethiopia #banksinethiopia #bankofabyssinia #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
ሶስቱም መሪዎች ሮም ሊገናኙ ነው ተብሏል።

እስካሁን የኤርትራው ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ በአፍሪካ-ጣሊያን ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ዛሬ ሮም መግባታቸው ተሰምቷል።

የኢትዮጵያው ጠ/ሚ አብይ አህመድ እና የሶማሊያ ፕሬዝደንት ሀሰን ሸህ መሀመድ በጉባኤው እንደሚሳተፉ ዘገባው አመልክቷል።

በአፍሪካ ጣሊያን ጉባኤ የበርካታ አፍሪካ ሀገራት መሪዎች ይሳተፋሉ።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በታሸገ ውሃ ላይ የዋጋ ጭማሪ ሊደረግ ነው‼️

የታሸገ ውሃ አምራቾች በወራት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ የዋጋ ጭማሪ ለማድረግ መወሰናቸውን ታማኝ ምንጮች ነገሩኝ ሲል ካፒታል አስነብቧል።

በቀጣዩ ሳምንት ተግባራዊ ሊደረግ እንደሚችል የሚጠበቀው የታሸገ ውሃ የማከፋፈያ ዋጋ ጭማሪ ለምሳሌ በሁለት ሊትር በሚታሸግ ውሃ ላይ የ20 በመቶ ገደማ ጭማሪ ሊኖረው እንደሚችል ነው ምንጮች ነገሩኝ ሲል ካፒታል የዘገበው።

በውሃ አምራቾቹ ባለፈው ህዳር በተደረገው የዋጋ ማሻሻያ የ22.5 በመቶ ጭማሪ ተደርጎ እንደነበር ይታወሳል።

በወቅቱ ለዋጋ ማስተካከያው የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ እና ሌሎች ግብአቶች ወጪያቸው መናሩ በምክንያትነት ተቀምጦ ነበር።

በቀጣይ ሳምንት ተግባራዊ ይደረጋል የተባለው ጭማሪ ግን ምክንያታዊነቱ ላይ ጥያቄ የሚነሳበት ነው ሲሉ ዘርፉን የሚከታተሉ አካላት ገልፀውልኛል ያለው ዘገባው አዲሱ ጭማሪ የሁለት ሊትር ውሃ በወል እሽጉ (6 ፍሬ) አሁን ካለበት 125 ብር ለአከፋፋይ ማስረከቢያ ዋጋ ወደ 150 ብር ከፍ የሚል ይሆናል ብሏል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ጋዜጠኛ ገነነ መኩሪያ የራሱን ህይወት እንዳጠፋ  ተነገረ‼️
ባሳለፍነው ሳምንት በሞት ያጣነው ተወዳጀ  ጋዜጠኘ ገነነ መኩሪያ (ሊብሮ) ራሱን በገመድ አንቆ ህይወቱን እንዳጠፋ ኢትዮጲካሊንክ የተሰኘ የሬዲዮ ኘሮግራም አሳወቀ።

የዛሬ 6 ወር ገደማ ስኳር ህመም እንዳለበት ያወቀው ገነነ በተያያዥ በሽታ አንድ እግሩን ይቆረጣል ከዛ በኋላ ህይወት እንዳስጠላውና ሲንቀሳቀስ ባለቤቱ እሷ መኪና እየነዳች እንደምታደርሰው ኢትዮጲካሊንክ አሳውቆ።  አንድ ቀን ግን ባለቤቱን ግዬን ሆቴል ስራ አለብኝ አድርሺኝ ብሏት አድርሳው ወደ ቤት ብትመለስም እሱ ግን ወደ ሌላ ቦታ በመሄድ ስልኩን በማጥፋት ሆቴል ይዞ ተደብቆ ትንሽ ቀናትን ቆይቷል::

ከዛ ግን ለጋዜጠኛ ሰይድ ኪያር ደውሎ ያለበትን ቦታ ነግሮት ሰይድም ወዲያው መጥቶ ስኳሩ በጣም እንደወረደና ባለቤቱ ጋር ደውሎ ስኳሩ በጣም ወርዷል ሲላት ባለቤቱም " በቃ ሚሪንዳ " ይጠጣበት ብላ እንደመለሰች ከዛ ግን ሄዳ እንኳን እንዳላየችው ታውቋል::

ብቻውን እዛ ክፍል ውስጥ የከረመው ይህ ታላቅ ሰው ገነነ  ምን እንደሆነ  ለምን እንደዚህ ውሳኔ እንደወሰነ ባይታወቅም ራሱን በገመድ አንቆ እንደገለ በምርምራ ታውቋል።

በጣም የሚያሳዝነው  ግን ባለቤቱ ሞቱን ስትሰማ ወደ አረፈበት ሆቴል በመሄድ ለፖሊስ መናገር ና ማሳወቅ ሲገባት ሬሳውን ወደ ቤቷ አምጥታ ስታለቅስ የጎረቤት ሰዎች ለፖሊስ አመልክቺ እንጂ ብለው ሲጠይቋት ለፖሊስ ያመለከተች ሲሆን ፖሊስም እንዴትት የሞተ ሰውን አስክሬን ለፖሊስ መናገር ና ማሳወቅ ሲጋባሽ አስክሬኑን ይዘሽ ወደ መኖሪያ ቤትሽ ትሄጃለሽ ብሎ አንድ ቀን እስር ቤት አውሏት እንደነበር የሬዲዬ ፕሮግራሙ ዘገባ አመልክቷል።

@ethio_mereja_news
ሀሺሽ በመኮረኒ ወደ ፖሊስ ጣቢያ


በምግብ ውስጥ አደንዛዥ ዕፅ ደብቆ ተጠርጣሪ ለመጠየቅ ወደ ፖሊስ ጣቢያ የሄደው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ ።


ግለሰቡ ከናቢስ የተባለውን አደንዛዥ ዕፅ ይዞ በወንጀል ተጠርጥሮ የታሰረ ጓደኛውን ለመጠየቅ የሄደው ወደ ቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ነበር፡፡

ከክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው በወንጀል ተጠርጥሮ የታሰረ ጓደኛውን ለመጠየቅ ምግብ ይዞለት የሄደው ይኸው ተጠርጣሪ ከድፍረትም ድፍረት የሚያሰኝ ተግባር ነበር የፈፀመው፡፡


በወቅቱ በሳህን የተቋጠረው ምግብ እንጀራ ፍርፍር በማካሮኒ ነበር፡፡ በእነዚያ የማካሮኒ ቀዳዳዎች ውስጥ የሚያብለጨልጩ ነገሮች ተወታትፈዋል፡፡

ምግቡን ፈትሸው የሚያስገቡት የፖሊስ አባላት ባዩት ነገር ተጠራጥረዋል፤ ምግቡ ተዘርግፎ ሲፈተሽ ብዛት 51 የማካሮኒ ፍሬዎች በተጠቀለሉ የአልሙኒየም ወረቀቶች አባብጠዋል፡፡

ወረቀቶቹን በመፍታት ለማየት ሲሞከርም ካናቢስ የተባለው አደንዛዥ ዕፅ ሆኖ ተገኝቷል፡፡

ግለሰቡ ከዚህ በፊት በወንጀል ድርጊት ተጠርጥሮ በዚያው ፖሊስ መምሪያ ታስሮ እንደነበር የተገለፀ ሲሆን ድፍረት በተቀላቀለበት ሁኔታ አደንዛዥ ዕፁን በምግብ ውስጥ ደብቆ ወደ ተጠርጣሪ ማቆያ ቤት ለማስገባት የሞከረው ጠያቂ ሰዎች የሚበዙበትን ሠዓት በማጥናትና የፖሊስ አባላት በዚያ ሰዓት ሊዘናጉ ይችላሉ ብሎ በማሰብ መሆኑም ታውቋል፡፡

በፈፀመው ወንጀል የምርመራ መዝገብ ተደራጅቶበት ጉዳዩ በፍርድ ቤት እየታየ ይገኛል፡፡

Via:የአዲስ አበባ ፖሊስ
«ኦሮሞን ጠልተህ ኢትዮጵያዊ ፣ ኢትዮጵያን ጠልተህ ኦሮሞ መሆን አትችልም» ~ ጀግናዋ አትሌት ደራርቱ ቱሉ በገመዳ ሾው

ገመዳ:– ሰዎች ኦሮሞ መሆን ኢትዮጵያዊን መጥላት እንዲሁም ብሄራቸውን መውደድ ኢትዮጵያዊነትን መጥላት ነው ብለው ያስባሉ ይሄን እንዴት ታይዋለሽ?"

ደራርቱ:- «ኦሮሞነትን መርጬ አይደለም ያገኘውት፣ ፈጣሪ ኦሮሞ አድርጎ ፈጥሮኛል፣ ኢትዮጵያዊ ደግሞ ነኝ ይህ እውነታ ነው:: ኦሮሞን ጠልተህ ኢትዮጵያዊ ፣ ኢትዮጵያን ጠልተህ ኦሮሞ መሆን አትችልም :: ይህ የማያከራክር ነገር ነው ኦሮሞንም መላውን የኢትዮጵያን ህዝብ እወዳለሁ አከብራለሁ::

ኦሮሞ መሆን እኮ ኢትዮጵያዊነት ውስጥ ነው ያለው ይሄን ደግሞ መካድ እና መነጣጠል አትችልም ራስህን ከወደድክ ቤተሰብህን ትወዳለህ፣ ቤተሰብህን ከወደድክ ማህበረሰብህን ትወዳለህ፣ ማህበረብህን ከወደድክ ህዝብህን ትወዳለህ፣ ህዝብህን የምትወድ ከሆነ ደግሞ ሀገርህን ትወዳለህ»

@merkato_media
@merkato_media
በኦሮሚያ ክልል ለኹለተኛ ዙር የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ጠርቶታል በተባለው የተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ አድማ ከዛሬ ጀምሮ ላልተወሰኑ ቀናት ተግባራዊ መኾን መጀመሩን ዋዜማ ካሰባሰበቻቸው መረጃዎች መረዳት ችላለች።

በምሥራቅ ወለጋ ዞን ነቀምት ከተማ የተሽከርካሪዎችን እንቅስቃሴ ጨምሮ እስከ ዛሬ እኩለ ቀን ድረስ ባንኮች፣ ንግድ ቤቶች፣ የመንግሥት መስሪያ ቤቶች እና ሌሎች አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ሙሉ ለሙሉ ዝግ መኾናቸውን ዋዜማ ከምንጮቿ ሰምታለች።

በምዕራብ ወለጋ ዞን ደምቢዶሎ ከተማ እንዲኹም መነሲቡ እና ቆንዳላ ወረዳዎች፣ በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ሻምቡ ከተማ እና የተለያዩ ወረዳዎች፣ በምዕራብ እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች የተለያዩ ወረዳዎች እንዲኹም በምዕራብ ሐረርጌ ዞን ከጭሮ ከተማ ወደ ድሬዳዋ መሉ ለሙሉ የተሽከርካሪ እንቅስቃሴዎች መቆሙን ለማወቅ ተችሏል።

በምሥራቅ ሸዋ ዞን ከአምቦ ከተማም፣ የሚወጣም ኾነ የሚገባ ተሽከርካሪ እንደሌለ ዋዜማ ባደረገችው ማጣራት የተረዳች ሲኾን፣ ወደ አዳማ እና አዲስ አበባ የሚገቡ ተሽከርካሪዎች ብዛትም በአንጻራዊነት መቀነሱን ምንጮች ገልጸዋል።

በተጠቀሱት አካባቢዎች የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ቤት ለቤት በመሄድ ባለንብረቶች ተሽከርካሪዎቻቸውን እንዲያወጡና የንግድ ቤቶችን እንዲከፍቱ ጫና እያደርጉ እንደኾነ ዋዜማ ተረድታለች።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ዕለታዊ ዜናዎች‼️

1፤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣   የብቃት ምዘና ከወሰዱ 3 ሺህ 861 የሦስት ተቋማት አመራሮችና ሠራተኞች ምዘናውን ያለፉት 1 ሺህ 680 ወይም 44 ነጥብ 39 በመቶዎቹ ብቻ እንደኾኑ አስታውቋል። ተፈታኞቹ ከመሬት ይዞታ፣ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ ቢሮ፣ ከመሬት ልማት አስተዳደር ቢሮና ከከንቲባ ጽሕፈት ቤት የተውጣጡ እንደኾኑ የከተማዋ ፐብሊክ ሰርቪስ ቢሮ ገልጧል። ምዘናውን ያለፉት፣k9 ከማዕከል አስከ ቅርንጫፍ ክፍለ ከተሞችና ወረዳዎች በሚገኙ ጽሕፈት ቤቶች እንደሚደለደሉ ተነግሯል። ከ30 አስከ 35 በመቶ ውጤት የሚያዘው ከመመዘኛ ፈተናው ውጤት መኾኑን የገለጠው፣ ቀሪው የሥራ አፈጻጸም፣ የሥራ ልምድና ስነ ምግባር መሠረት ያደረገ ይኾናል ብሏል።

2፤ በአዋሽ አርባ ወታደራዊ ካምፕ ታስረው የቆዩት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባሉ ክርስቲያን ታደለና የአማራ ክልል ምክር ቤት አባሉ ዮሃንስ ቧያለው ዕሁድ'ለት ወደ አዲስ አበባ መዛወራቸውን ቢቢሲ አማርኛ ምንጮቹን ጠቅሶ ዘግቧል። ኸለቱ ግለሰቦች ባኹኑ ወቅት ፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ ታስረው እንደሚገኙ መስማቱን ዘገባው ጠቅሷል። የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አባሉ ካሳ ተሻገር እና የበይነ መረብ ጋዜጠኛ በቃሉ አላምረው ደሞ፣ ለሕክምና ከአዋሽ አርባ ወደ አዲስ አበባ የተዛወሩት ከኹለት ሳምንት በፊት እንደኾነ ምንጮች መናገራቸውን ዘገባው ጨምሮ አመልክቷል። ካሳ ለሕክምና ወደ አዲስ አበባ ተዛውረው ፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ ውስጥ ታስረው እንደሚገኙ ዋዜማ ባለፈው ሳምንት መዘገቧ ይታወሳል።

3፤ የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የሞባይል ኤምፔሳ አገልግሎት ተመዝጋቢዎች ቁጥር በአራት ወራት ውስጥ በሦስት እጥፍ ጨምሮ ወደ ሦስት ነጥብ 1 ማሽቀቡን ቢዝነስ ደይሊ ዘግቧል። ኤምፔሳ በመስከረም መጨረሻ የነበረው የደንበኞች ብዛት 1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ነበር። ኩባንያው፣ ከተጀመረበት ነሃሴ እስከ መስከረም መጨረሻ ያዘዋወረው የገንዘብ መጠን 18 ነጥብ 7 ሚሊዮን ዶላር ሲኾን፣ ገንዘቡ በታኅሳስ መገባደጃ ላይ ወደ 115 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዶላር ማደጉን ዘገባው ጠቅሷል። ኩባንያው፣ ከኤምፔሳ አገልግሎቱ ከነሃሴ እስከ ታኅሳስ መጨረሻ ድረስ 280,625 ዶላር ገቢ አስገብቷል ተብሏል።

4፤ የደቡብ አፍሪካ ፖሊስ በሕገወጥ መንገድ ወደ አገሪቱ በተሽከርካሪ ሲገቡ የነበሩ 25 ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞችን ቅዳሜ'ለት በቁጥጥር ስር ማዋሉን የዚምባብዌው ክሮኒክል ጋዜጣ ዘግቧል። ኢትዮጵያዊያኑ ፍልሰተኞች ከዚምባብዌ ወደ ደቡብ አፍሪካ ሲገቡ የተያዙት፣ በኹለት ተሽከርካሪዎች ሕገወጥ የሰው አዘዋዋሪዎች እንደኾኑ በተጠረጠሩ የታጠቁ ግለሰቦች ታጅበው እንደኾነ ዘገባው አመልክቷል። ፍልሰተኞቹ ዕድሜያቸው ከ20 እስከ 40 መኾኑን የደቡብ አፍሪካ ፖሊስ መናገሩን የጠቀሰው ዘገባው፣ በሕገወጥ መንገድ ወደ አገሪቱ በመግባት ክስ እንደተመሠረተባቸው አመልክቷል።

5፤ የተመድ ጸጥታው ምክር ቤት ትናንት ምሽት በኢትዮጵያና ሱማሊያ ውዝግብ ላይ መክሯል። ከምክር ቤቱ ስብሰባ ቀደም ብሎ የምክር ቤቱ የወቅቱ ሊቀመንበር ፈረንሳይ፣ አፍሪካዊያኑን የምክር ቤቱ ተለዋጭ አባላት አልጀሪያን፣ ሞዛምቢክንና ሴራሊዮንን እንዲኹም ጉያናን በጉዳዩ ዙሪያ በዝርዝር ያማከረች ሲኾን፣ አራቱ አገራትም ኢትዮጵያንና ሱማሊያን ማነጋገራቸው ተገልጧል። ዓረብ ሊግና የእስልምና አገራት ካውንስል፣ የሱማሊያ ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት እንዲከበር ለጸጥታው ምክር ቤት ቀደም ሲል ደብዳቤ አስገብተው ነበር። ከዓረብ አገራት መካከል፣ የጸጥታው ምክር ቤት አባል የኾነችው አልጀሪያ ብቻ ናት። የስብሰባው ውጤት ይህን ዘገባ እስካጠናቀርንበት ሰዓት ድረስ አልተገለጠም።

6፤ የጣሊያን ጠቅላይ ሚንስትር ጆርጂያ ሜሎኒ፣ ጣሊያን ከአፍሪካ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር ለኢንቨስትመንት የ5 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዩሮ መመደቧን አስታውቀዋል። ጣሊያን የመደበችው ገንዘብ፣ የኢነርጂ ትስስሮችን ለማጎልበትና ሕገወጥ ስደትን ለመቆጣጠር የሚውል እንደኾነ ተገልጧል። ሮም ላይ ለኹለት ቀናት በተካሄደው የጣሊያንና አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ላይ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይንና ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂን ጨምሮ የ25 አገራት መሪዎች ተሳትፈዋል።[ዋዜማ]

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የብቃት ምዘና ከወሰዱ 3 ሺህ 861 የሦስት ተቋማት አመራሮችና ሠራተኞች ምዘናውን ያለፉት 1 ሺህ 680 ወይም 44 ነጥብ 39 በመቶዎቹ ብቻ እንደኾኑ አስታውቋል።

ተፈታኞቹ ከመሬት ይዞታ፣ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ ቢሮ፣ ከመሬት ልማት አስተዳደር ቢሮና ከከንቲባ ጽሕፈት ቤት የተውጣጡ እንደኾኑ የከተማዋ ፐብሊክ ሰርቪስ ቢሮ ገልጧል።

ምዘናውን ያለፉት፣ ከማዕከል አስከ ቅርንጫፍ ክፍለ ከተሞችና ወረዳዎች በሚገኙ ጽሕፈት ቤቶች እንደሚደለደሉ ተነግሯል።

ከ30 አስከ 35 በመቶ ውጤት የሚያዘው ከመመዘኛ ፈተናው ውጤት መኾኑን የገለጠው፣ ቀሪው የሥራ አፈጻጸም፣ የሥራ ልምድና ስነ ምግባር መሠረት ያደረገ ይኾናል ብሏል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
2024/10/05 17:37:22
Back to Top
HTML Embed Code: