ንግድ ባንኮች ላይ ተጥሎ የነበረው የ14 በመቶ የማበደር አመታዊ እድገት ወደ 18 በመቶ ከፍ እንዲል መደረጉ ተገለጸ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ፣ ንግድ ባንኮች በየአመቱ እንዲያበድሩ የሚፈቅደውን 14 በመቶ የብድር አመታዊ ዕድገት ላይ ማሻሻያ በማድረግ ወደ 18 በመቶ ከፍ እንዲል ማድረጉን አስታውቋል።
በዚህም መሰረት የተሻሻለው የብድር ዕድገት መጠን ከትላንት ታህሳስ 22 ቀን 2017 ዓ.ም ተግባራዊ መደረጉን ብሔራዊ ባንክ ትላንት የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴ የመጀመሪያ ስብሰባውን ማካሄዱን ተከትሎ ባወጣው መግለጫው ገልጿል።
የንግድ ባንኮች ከ14 በመቶ በላይ አመታዊ የማበደር አቅማቸው እንዳያድግ የተደረገው ባሳለፍነው አመት 2017 ዓ.ም ህዳር ወር ላይ ሲሆን በወቅቱም የተሰጠው ምክንያት በሀገሪቱ ከግዜ ወደ ግዜ እየተባባሰ የመጣውን የዋጋ ግሽበት ለመቆጣጠር በማለም የሚል ነበር።
ባንኩ በመግለጫው ሀገራዊ የዋጋ ግሽበቱ እየቀነሰ መጥቷል ሲል አስታውቋል፤ ሀገራዊ ዓመታዊ የዋጋ ግሽበት እየቀነሰ በህዳር ወር 2017 መጨረሻ 16.9 በመቶ ደርሷል ብሏል።
ይህም ባለፉት አምስት ዓመታት ከተመዘገበው አሃዝ ዝቅተኛው ነው ሲል የገለጸው ብሔራዊ ባንክ ለዚህም ከምርታማነት ባሻገር ብሔራዊ ባንክ ከነሐሴ 2015 ጀምሮ ተግባራዊ ባደረገው ጥብቅ የገንዘብ ፖሊሲ ምክንያት መሆኑን ጠቁሟል።
ምግብ ነክ የዋጋ ግሽበት አሁንም ከፍተኛና 18.5 በመቶ ቢሆንም፣ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር ግን የመቀነስ አዝማሚያ አሳይቷል ያለው የባንኩ መግለጫ ምግብ ነክ ያልሆነ የዋጋ ግሽበት ባለፈው ወር ከነበረው 11.6 በመቶ ጋር ሲነጻጸር መጠነኛ ጭማሪ በማሳየት በህዳር ወር 2017 መጨረሻ 14.4 በመቶ መድረሱን አስታውቋል።
https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news

ሊመረቅ 4 ቀን ቀረው‼️
''ተመስገን'' የተሰኘው የዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ ቁጥር 2 የዝማሬ አልበም የፊታችን እሁድ ታኅሣሥ 27 ከቀኑ 6:00 ጀምሮ በቦሌ መድኃኔዓለም ካቴድራል አዳራሽ ይመረቃል::
በፍላሽ የተዘጋጀውን የዝማሬውን አልበም ገዝተው 16ቱን መዝሙራት ለመስማት ቀዳሚ ይሁኑ:: መዝሙራቱ በሁሉም የCD Distribution አማራጮችና (spotify, itunes…) በተለያዩ መተግበሪያዎች ይገኛሉ::
በመላው ዓለም ለማከፋፍል
በ+251941518851/ +1 469 733 0150 ይደውሉ ወይም [email protected] ይጻፉልን::
ተመስገን ተመስገን
ለምስጋና ስላሰባሰብከን
እግዚአብሔር ተመስገን

የባንክ ሒሳብ ለመክፈት የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ይዞ መቅረብ ያስፈልጋል አስፈላጊ ነው ብሏል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ
በአዲስ አበባ በሚገኙ ባንኮች የባንክ ሒሳብ ለመክፈት ከዛሬ ጀምሮ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ይዞ መቅረብ እንደሚያስፈልግ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አስታውቋል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባወጣው መመሪያ መሠረት ከዛሬ ታህሳስ 23/2017 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ አበባ በሚገኙ በሁሉም ባንኮች አዲስ የባንክ ሒሳብ ለመክፈት የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ (የፋይዳ ቁጥር) ይዞ መቅረብ እንደ መጀመሪያ ቅድመ ሁኔታ ተግባራዊ መሆኑን አስታውቋል።

በአማራ ክልል ባለፋት ስድስት ወራት ከ1 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በወባ በሽታ መያዛቸዉ ተነገረ
በአማራ ክልል እየጨመረ የመጣውን የወባ በሽታ ስርጭትን ተከትሎ ባለፋት ስድስት ወራት ከ1 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በወባ በሽታ መያዛቸውን የክልሉ ህብረተሰብ ጤና ኢንስትቲዮት አስታውቋል።በኢንስቲትዮቱ የወባ መከላከልና መቆጣጠር ፕሮግራም አስተባባሪ አቶ ዳምጤ ላንክር ለብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን እንደተናገሩት በክልሉ የወባ በሽታ ስርጭት ከፍ እያለ በመምጣቱ በርካታ ዜጎች በበሽታው እየተያዙ ይገኛሉ።
ካለፈው ሀምሌ ወር አንስቶ እስካለንበት የታህሳስ ወር ድረስ በክልሉ 1 ሚሊዮን 3 መቶ 38 ሺህ 171 ዜጎች በበሽታው መያዛቸዉን ገልፀዉ በአሁኑ ወቅት የምርመራ ህክምና አገልግሎትን እንዲያገኙ መደረጉን ተናግረዋል።ይህም ካለፈዉ ከ2016 በጀት አመት ጋር ሲነፃፀር የበሽታው ስርጭት በ65 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል።በባለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ላይ 8 መቶ 11 ሺህ 91 ህሙማን በበሽታው ተይዘው እንደነበር አስታውሰዋል።
አያይዘውም በባለፈው ሳምንት ብቻ 52 ሺህ 4 መቶ 78 ሰዎች በበሽታው መያዛቸዉ ሪፓርት ተደርጓል፡፡ በክልሉ 40 ወረዳዎች 70 በመቶ የሚሆነውን ህሙማን ሪፖርት አድርገዋል የተባለ ሲሆን የበሽታው ጫናም በምእራብ የአማራ ክልል፣ በምስራቅ ጎጃም፣ በምእራብ ጎጃም አዊ ፣የሰሜን ጎጃም ባህርዳር ከተማ አስተዳደር እንዲሁም በማዕከላዊ፣በደቡብ እና ሰሜን እና ምእራብ ጎንደር ዞኖች ላይ በስፋት ይስተዋላል።የእነዚህ ዞኖች ወረዳ 90 በመቶ የሚሆነውን የህሙማን ቁጥር ይሸፍናሉ በማለት ያስረዱት አቶ ዳምጤ የአየር ንብረት ለውጥ መኖርን ተከትሎ ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ በመከሰቱ በርካቶች በበሽታው እንዲጠቁ አድርጓል።
የበሽታውን ስርጭት ለመከላከልና ለመቆጣጠር ኢንስቲትዮቱ በርካታ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ ተገልጻል።ሁሉም የማህበረሰብ ክፍል በአካባቢ ቁጥጥር ስራ ላይ እንዲሰማራ ተደርጓል በማለት አስተባባሪው የገለፁ ሲሆን በዚህም አንፃራዊ በሆነ መልኩ የወባ ህሙማን ቁጥር የመቀነስ አዝማሚያ አሳይቷል ሲሉ አቶ ዳምጤ ላንክር ጨምረዉ ለብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል፡፡

ፀደቀ‼️
በኢትዮጵያ የወንድ የዘር ፈሳሽ ልገሳ፣ የሰውነት አካል መለገስ እና በህክምና የታገዘ ሞት እንዲጀመር የሚፈቅደው ህግ ጸደቀ። የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጤና አገልግሎት እና አስተዳድር ረቂቅ አዋጅን አጽድቋል።
አዋጁ ከዚህ በፊት በኢትዮጵያ ተጀምረው የማያውቁ እና አዳዲስ አገልግሎቶችን መስጠት የሚያስችሉ የጤና አገልግሎቶች እንዲጀመሩ የሚያደርግ ነው።
ለአብነትም መዳን በማይችል እና በስቃይ ውስጥ ያሉ ታማሚዎች በሀኪሞች እርዳታ እንዲሞቱ የሚፈቅደው፣ የሰውነት አካልን ያለ ክፍያ መለገስ፣ የወንድ የዘር ፍሬ እንዲለገስ እና ሌሎችም አዳዲስ የህክምና አገልግሎቶችን ይፈቅዳል።
ምክር ቤቱ ላለፉት ወራት የተለያዩ ውይይቶችን ሲያደርግ ቆይቷል።

#ሠላሳ፣ ስልሳ፣ መቶም ያማረ ፍሬ ይስጣችሁ
ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ መስጠትን ከዘር ጋር አነጻጽሮ በምሳሌ ያስተምራል፡፡
ዘር በእጅ የያዙትን ይበዛልኛል፣ ስለ አንዷ ሰላሳ፣ ስልሳ፣ መቶም ያማረ ፍሬ አፈራለሁ ብሎ በእምንት በእርሻ ቦታ መበተንን ይጠይቃል፡፡
መስጠትም ይህን ይመስላል፡፡ በእጅ ያለውን በልግስና አሳልፎ ሰጥቶ ከእግዚአብሔር ሰፊ በረከት አገኛለሁ ብሎ በእምነት መስጠት፡፡
ይህን ቅዱስ ቃል አምናችሁ በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ምስራቅ በለሳ ወረዳ ለሚገኘውና ከዘጠና በላይ ገዳማውያን መነኮሳት ላሉበት ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አድነት ገዳም ያደረጋችሁት በአይነት የእህል ልገሳ በዚህ መልኩ ተጭኖ ለገዳሙ ተልኳል፡፡
“በጥቂት የሚዘራ በጥቂት ያጭዳል፤ በበረከትም የሚዘራ ደግሞ በበረከት ያጭዳል፤ እግዚአብሔር በደስታ የሚሰጠውን ይወዳልና እያንዳንዱ በልቡ እንዳሰበ ይስጥ፥ በኀዘን ወይም በግድ አይደለም።” (2ኛ ቆሮ 9፥7) እንዲል፤ ስለ መስጠትና መቀበል በሰፊው አስተምሮበታል፡፡
የዘራ እንደሚሰበስብ፣ የሰጠም ዋጋውን አያጣምና የተዘራባት ምድር የዘሩባት አብዝታ እንደምትሰጥ፣ በልግስና የሰጣችኋቸው ገዳማውያን በጸሎታቸው ትልቅ ዋጋ፣ በሚያልፍ ስጦታ የማያልፍ በረከት፤ በሚያልቅ ልግስና የማያልቅ ዋጋ ያስገኛሉና፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ምጽዋትን በዘር መስሎታል፡፡
እኛም እንላለን፣ ስለሰጣችሁት እያንዷንዷ ቅንጣት የእህል ዘር ስለአንዱ ፋንታ ሰላሳ፣ ስልሳ፣ መቶም ያማረ ፍሬ ይስጥልን፡፡ በወጣ አብዝቶ ይተካ፡፡ በዚህ አጋጣሚ የተሰራው ከታቀደው አንጻር ገና ብዙ ይቀረዋልና ገዳማውያኑን በዚህ መልኩ በአይነት ማለትም ቀለብ በመስፈር፣ የግንባታ እቃዎች ጠጠር፣ አሸዋ፣ ሲሚንቶ፣ ብረት በልባችሁ እንዳሰባችሁ በመስጠት መደገፍ የምትፈልጉ ካላችሁ በደስታ እንቀበላለን፡፡ በገንዘብ ድጋፍ ለምታደርጉም የገዳሙ አካውንት ከታች ተቀምጧልና የቻላችሁትን እንድታደርጉ ገዳማዊያኑ እየተጣሩ ነው።
ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

ተፈናቃዮችን በአጀንዳ ማሰባሰቡ ላይ ማሳተፉን የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ገለጸ
ታሕሳስ 23/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በየክልሎች ባደረገው የአጀንዳ ማሰባሰብ ላይ ቁጥራቸውን በውል የማይታወቁ ተፈናቃዮችን ማሳተፉን ለአሐዱ ገልጿል።
የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን እያካሄደ ባለው ምክክር አሳታፊ እና አካታች ለማድረግ ከሚሰራቸው ሥራዎች መካከል ተፈናቃዮችን ያማከለ ሥራ መሆኑን የተናገሩት የኮሚሽኑ ቃል አቀባይ አቶ ጥበቡ ታደሠ፤ በአብዛኛው በየክልሉ በተካሄዱ አጀንዳ ማሰባሰብ ሂደቶች ላይ ተፈናቆዮችን ማካተታቸውን ተናግረዋል።
በመሆኑም ተፈናቃዮች ባሉባቸው ክልሎች አካባቢዎች በተወካዮቻቸው አማካኝነት እንደሌላው የማህበረሰብ ክፍል ሁሉ እንዲሳተፉ እየተደረገ መሆኑን አቶ ጥበቡ ገልጸዋል።
ቁጥራቸውን በሚመለከት ከክልል ክልል የተለያየ ቁጥራዊ መረጃዎች እንደሚኖሩ የተናገሩት ቃል አቀባዩ፤ አንድ አንድ ክልሎች ላይ በተለይም ግጭት ባለባቸው ላይ በርከት የማለት ነገር መኖሩን ተናግረዋል።
በሌሎች አካባቢዎች ደግሞ ቁጥሩ ሊያንስ እንደሚችል በማንሳት፤ በአጠቃላይ በአጀንዳ ማሰባሰብ የተሳተፉ ተፈናቆዮችን ቁጥር ማወቅ እንደማይቻል ገልጸዋል።
የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ በአስር ክልሎችና በሁለት ከተማ አስተዳደሮች የአጀንዳ ማሰባሰብ ሥራውን ያከናወነ ሲሆን፤ በቀጣይ በአማራ እና ትግራይ ክልል ለማካሄድ እቅድ እንዳለዉ ተናግሯል፡፡
"ለመሆኑ ምክክር ኮሚሽኑ በተለያዩ ክልሎች የሚገኙ ተፈናቃዮችን በክልል ደረጃ ሳይሆን እንደ አንድ ባለድርሻ በመቁጠር አጀንዳቸውን ለምን መሰብሰብ አልተቻለም?" ሲል አሐዱ ጠይቋል።
ቃል አቀባዩ በምላሻቸው፤ "ከአስር የማህበረሰብ ክፍሎች እንደ አንድ ተቆጠረው አጀንዳቸውን እያስረከቡ ነው" ሲሉ መልሰዋል።
በሌሎች ክልሎች እንደተደረገው ሁሉ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በተለይም 'በርካታ ተፈናቃይ ይገኝበታል' ተብሎ በሚታሰቡት በአማራ እና ትግራይ ክልልም አጀንዳ የማሰባሰቡ ላይ ተሳትፎ እንዲኖራቸው እንደሚሰራ ተናግረዋል።
የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአሁን ሰዓት ከክልሎች በተጨማሪ በቀጣይ ከፌደራል ተቋማት የአጀንዳ ማሰባሰብ ሥራውን እንደሚሰራ ማስታወቁ አይዘነጋም።
ኮሚሽኑ በታሕሳስ ወር ሦስት ዓመቱን የሚደፍን ሲሆን የቆይታው ግዜ የሚጠናቀቅ በመሆኑ፤ የተወካዮች ምክር ቆይታውን እንደሚያራዝምለት ይጠበቃል።

ጥቆማ‼️
በሀገራችን እዉቅ ጋዜጠኞች የተመሰረተና የመረጃ አነፍናፊና አዲሱ tikvah የተባለለት የቴሌግራም ቻናል እናስተዋዉቃችሁ
እውነተኛ መረጃ ከፈለጋቹ በፍጥነት ይህን ቻናል መቀላቀል ይኖርባችኋል።
በዚ LINK ግቡ👇
👇👇👇
https://www.tg-me.com/+gPveFwjiiXdiMDE0

የኮንዶም እጥረት‼️
በኢትዮጵያ በዓመት ወደ 270 ሚሊዮን ገደማ ኮንዶም ያስፈልጋል።
በየጊዜው ኮንዶሞችን ወደ ሀገር ውስጥ በማስገባት ለተጋላጭ የማህበረሰብ ክፍሎች የሚያቀርበው ኤድሰ ሄልዝ ኬር ፋውንዴሽን አሁንም በኢትዮጲያ ወስጥ የኮንዶም አቅርቦት እጥረት ስለመኖሩ ገልፆል።
ድርጅቱ በየዓመቱ ወደ 3 ሚልየን የሚጠጋ ኮንዶም ወደ ሀገር ውስጥ እያስገባ ይገኛል፤ ነገር ግን በኮንዶም ስርጭት ስራ የተሰማሩ ድርጅቶች ወደ ኢትዮጵያ የሚያስገቡት የኮንዶም ቁጥር ተደምሮ የሀገሪቱን የኮንዶም ፍላጎት መሙላት አልተቻለም::

ደርሰ‼️ደረሰ‼️ደረሰ‼️
ተመስገን 3 ቀናት ብቻ ቀሩት
የፊታችን እሁድ ታኅሣሥ 27 በመድኃኔዓለም በዕለተ ቀኑ ቦሌ መድኃኔዓለም አዳራሽ ምን ተደግሷል? የሰማችሁ ላልሰሙት በማወጅ ይህንን አዋጅ ንገሩ‼️
''ተመስገን'' የተሰኘው የዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ ቁጥር 2 የዝማሬ አልበም የፊታችን እሁድ ታኅሣሥ 27 ከቀኑ 6:00 ጀምሮ በቦሌ መድኃኔዓለም ካቴድራል አዳራሽ ይመረቃል::
በፍላሽ የተዘጋጀውን የዝማሬውን አልበም ገዝተው 16ቱን መዝሙራት ለመስማት ቀዳሚ ይሁኑ:: መዝሙራቱ በሁሉም የCD Distribution አማራጮችና (spotify, itunes…) በተለያዩ መተግበሪያዎች ይገኛሉ:: በመላው ዓለም ለማከፋፍል በ+251941518851/ +1 469 733 0150 ይደውሉ ወይም [email protected] ይጻፉልን::

ከፊታችን የሚከበሩት የገና እና የጥምቀት በዓላት ያለምንም የአደጋ ክስተት በሰላም እንዲጠናቀቁ በቂ ዝግጅት ማድረጉን የአዲስ አበባ እሳት እና አደጋ ስራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
ኮሚሽን መስሪያ ቤቱ በዓላቱ በሰላም እንዲጠናቀቁ በአደጋ ቅነሳ እና በአደጋ ምላሽ ዘርፎች በቂ ዝግጅት አድርጎ ወደ ስራ መግባቱን፤ የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡
ህብረተሰቡ ለአደጋ ከሚያጋልጡ አሰራሮች እንዲቆጠብ እና በዓሉ ሲከበርም ምን አይነት ጥንቃቄዎች መደረግ አለባቸው የሚለውን የኮሚሽኑ የአደጋ ቅነሳ ባለሙያዎች በተለያየ መልክ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን እየሰሩ ነው ብለዋል፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ አደጋ ከተከሰተ በኋላ አደጋው ቦታ በፍጥነት በመድረስ የጉዳት መጠንን ለመቀነስ የሚያስችል ስራ እንደሚሰራም የህዝብ ግንኙነት ባለሙያዉ አቶ ንጋቱ ተናግረዋል፡፡
በአስራ አንዱም የኮሚሽኑ ቅርንጫፎች እንዲሁም በማዕከል የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ፤ ማሽነሪዎች እና የአምቡላንስ አገልግሎት ቅድመ ዝግጅታቸውን ማጠናቀቃቸውንም አስታውቀዋል፡፡
ህብረተሰቡ ከኮሚሽን መስሪያቤቱ የሚተላለፉ የጥንቃቄ መልዕክቶችን መስማት እና መተግበር እንዳለበትም አሳስበዋል፡፡
ምግብ ለማብሰል በሚደረግ ጥረት በአንድ ኤሌክትሪክ ሶኬት ላይ አራት እና ከዛ በላይ የሆኑ ሶኬቶችን ከመጠቀም መቆጠብ፣ከሰል ጭስን በአግባቡ በመጠቀም ጉዳት እንዳያደርስ ማድረግ፣የልደት በዓል እንደመሆኑ የሻማ አጠቃቀም ላይ ህብረተሰቡ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለበትም ገልጸዋል፡፡
Ethio Fm