Telegram Web Link
ኢትዮ መረጃ - NEWS
Photo
የምዕራብ ካናዳ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ  በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በምስራቅ በለሳ ወረዳ ቤተ ክህነት ሥር በሚገኘው የሙት አንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል የአንድነት ገዳም በመገኘት ጉብኝት አደረጉ።

የምዕራብ ካናዳ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል የሆኑት ብፁዕ አቡነ መቃሪዮስ በሙት አንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል የአንድነት ገዳም በመገኘት የተጀመሩ ልማታዊ ስራዎችን በመጎብኘት እና ቡራኬ በመስጠት አባታዊ መልእክት አስተላልፈዋል።

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በምስራቅ በለሳ ወረዳ ቤተ ክህነት ስር የሚገኘው የሙት አንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል የአንድነት ገዳም በስሩ ከዘጠና በላይ አባት እና እናት መነኮሳት በአንድነት የሚኖሩበት ቅዱስ ስፍራ ሲሆን ገዳሙ በመብል እጥረት እና በባዕት አለመኖር እንዲሁም ተያያዥ በሆኑ ምክንያቶች ገዳማውያኑ በከፍተኛ ችግር ውስጥ የሚገኙ መሆኑን በ2016 ዓ.ም በማኅበረ መነኮሳቱ በተደገ የይድረሱልን ጥሪ ሁላችንም የምናስታውሰው ልብን የሚነካ እና ከአዕምሮ የማይጠፋ ክስተት ነበር።

በዚህ ጥሪ መሰረት በከፍተኛ ደረጃ በተደረገ የማኅበራዊ ዘመቻ ንቅናቄ መሰረት በዋናነት ባለ አስራ ስምንት ክፍል የእናቶች ባዕት የተገነባ መሆኑን ገዳማውያኑ አሳውቀዋል።

በመሆኑም ብፁዕነታቸው እነዚህን የእናቶች ማረፊያ በመባረክ እና በመጎብኘት በእናቶች በኩል የተከናወኑ ተግባራትን አድንቀዋል።

ብፁዕነታቸው በዚህ  መንፈሳዊ ሥራ ላይ የማኅበራዊ ትስስር ድረገፆችን በመጠቀም ሱታፌ ያደረጉ ምዕመናን ያመሰገኑ ሲሆን እገዛችሁ ለፍሬ በመብቃቱ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።
አያይዘውም በማስተባበር ሂደት ታላቅ እንቅስቃሴ ያደረጉ የተለያዮ የማኅበራዊ ትስስር ገፅ ባለቤት ለሆኑ አካላት እና ተቋማት ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋፅኦ አመስግነዋል።

ብፁዕነታቸው እንዳሉት የሙት አንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል አንድነት ገዳም የአባቶች ባዕት ያለበት ሁኔታ እጅግ አሰቃቂ እና አሳዛኝ ከመሆኑም በላይ አባቶችን የማደራጀት እና የማቋቋም ስራ እንዲሁ አፋጣኝ እርብርብ የሚሻ ጉዳይ ነው ብለዋል።
ከዚሁ ጋር ተያይዞ በአጠቃላይ ማኅበረ መነኮሳትን ለማጽናት፣ በዘለቄታዊነት ካሉበት ችግር ለማላቀቅ በሚደረገው ጥረት ሁሉ እገዛችሁ ያስፈልገናልና የድጋፍ እጃችሁ አይታጠፍ፣ ልገሳችሁን አጠናክራችሁ ልትቀጥሉ ይገባል ብለዋል።

አክለውም የምዕራብ ካናዳ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል የሆኑት ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ በችግር ላይ የሚገኙ ገዳማትን እና እድባራትን መርዳት የእያንዳንዱ ክርስቲያን ግዴታ መሆኑን የገለፁ ሲሆን ገዳማውያኑ ለሚያቀርቡት የድጋፍ ጥሪ ሁሉም ህዝበ ክርስቲያን የቀድሞውን እርብርብ በአባቶች ገዳም የባዕት ግንባታ ላይም በገንዘብ፣በዕውቀት፣በጉልበት በመርዳት የበኩላችንን ሀላፊነት እንወጣ ዘንድ አባታዊ መልዕክታቸውን በጥብቅ አሳስበዋል።

ከዚሁ ጋር ተያይዞ ድጋፍ ለማድረግ ሙትአንሳ  ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም:-

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ:-1000442598391

ወይም
አቢሲኒያ ባንክ:-141029444

ለማንኛውም አይነት መረጃ:-
09 18 07 79 57 ወይም 09 38 64 44 44 መደወል የምትችሉ መሆኑን ያሳዉቁ ሲሆን ጅማሬያችን ታናሽ ቢሆንም ፍፃሜያችን ታላቅ ነው እና የጀመርነውን እንፈፅም ዘንድ አሳስበዋል።

በመጨረሻም የምዕራብ ካናዳ ሀገረ ስብከት እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በሆኑት በብፁዕ አቡነ መቃርዮስ አባታዊ ፀሎት እና ቡራኬ  የዕለቱ መርሐ ግብር ተጠናቋል።

                              ፳፫/፬/፳፻፲፯ ዓ.ም
                                ጎንደር ኢትዮጵያ
ኢትዮጵያ እና የዓለም ባንክ የፋይናንስ ዘርፉን ለማጠናከር የ700 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የብድር ስምምነት ተፈራርሙ

ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሽዴ እና የዓለም ባንክ የኢትዮጵያ፣ የኤርትራ፣ የሱዳንና የደቡብ ሱዳን ዳይሬክተር መሪየም ሳሊም ፈርመውታል።

የብድር ስምምነቱ ለፋይናንስ ዘርፍ ማጠናከሪያ ፕሮጀክት የሚውል ነው።

ፕሮጀክቱ የኢትዮጵያን የፋይናንስ ዘርፍ ዘላቂነትና መረጋጋት ማሻሻልን አላማ ያደረገ ነው።

ፕሮጀክቱ ቁልፍ የሚባሉ የፋይናንስ ዘርፍ ሪፎርሞች እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክና የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የካፒታልና የፋይናንስ መዋቅር ለማረጋጋት ለሚደረጉ ጥረቶችን ለመደገፍ ስትራቴጂካዊ በሆነ ሁኔታ መዘጋጀቱ ተገልጿል።

ገንዘቡ መንግሥት በቅርቡ የባንኩን ዘርፍ ለማዘመንና የውጭ ባንኮች ወደ ኢትዮጵያ እንዲገቡ የፈቀደበት ጠንካራ ሪፎርም እንደሚደግፍ የገንዘብ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።
"የአክሱም ከተማ ሙስሊም ነዋሪዎች ችግር እልባት ያልተሰጠበት እና ወደባሰ ሁኔታ እየሄደ ነው"--- የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የአክሱም ከተማ ሙስሊም ነዋሪዎች ለዘመናት የነበረባቸውን የእምነት ነፃነት፣ የመስገጃ ቦታ ችግር እና የቀብር ቦታ ችግር እልባት ያልተሰጠበት እና ወደባሰ ሁኔታ እየሄደ ነው አለ።

ምክር ቤቱ ዛሬ መግለጫውን ያወጣው በከተማው የሚገኙ ሴት ተማሪዎች ሂጃባቸውን አድርገው ትምህርት መከታተል እንዳልቻሉ ከሰሞኑ መሰማቱን ተከትሎ ነው።

"በዚህ ዘመን በጋራ እምነቶች ተከባብረው በሚኖሩበት አገር እሴቱን የሚሸረሽር ተግባር መፈፀሙን በፅኑ እናወግዛለን" ያለው ምክር ቤቱ የሙስሊሙ ማህበረሰብ መብቶች ሳይሸራረፉ ተግባራዊ እንዲደረጉ እና መንግስትም ይህን እንዲያስፈፅም ጥያቄ አቅርቧል።

የትግራይ ትምህርት ቢሮ በበኩሉ አዲስ የወጣ የአለባበስ መመርያም ሆነ ማስፈፀሚያ ደንብ እንዳልወጣ የጠቀሰበት ደብዳቤ ማውጣቱን ተመልክተናል።

@sheger_press
"..ማንኛውም አካል ወይም ግለሰብ ይህንን የፈጣሪያችንን ግዴታ (ትዕዛዝ) መአልከልም ሆነ ማደናቀፍ እንደሌለበት እናሳስባለን>>የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የዑለማ ጉባዔ

ጉባኤው ዛሬ ሶላትንና ሂጃብን በተመለከተ ፈትዋ ሰጥቷል!

ዝርዝሩ የሚከተለው ነው

"ከላይ እንደተጠቀሰው በተለያዩ የመንግስትና መንግስታዊ ባልሆኑ መስሪያ ቤቶች ተቀጥረው የሚሰሩ ሙስሊም ሰራተኞች እንዲሁም በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ማለትም በዩኒቨርሲቲዎችና በተለያዩ መደበኛ ትምህርት ቤቶች ውስጥ የሚማሩ ተማሪዎች እና ሰራተኞች በሃይማኖቱ ግዴታ የሆኑት ሶላትንና ሂጃብን አስመልክቶ በተደጋጋሚ የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች ፈትዋ እንዲሰጥበት ለኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዩች ጠቅላይ ምክር ቤት የዑለማ ጉባኤ የፈትዋ ጽ/ቤት አቅርበዋል፡፡

ስለሆነም ይህ ጉዳይ:-

1. የእለት ተዕለት ሶላትን በተመለከተ፦

1.1 አላህ (ሱ.ወ) በተአበረው ቁርኣን በ 5ኛው ምዕራፍ በ103ኛው አንቀጽ ላይ « ሶላት በምዕመናን ላይ በጊዜ የተወሰነች ግዴታ ናት ይላል፡፡ ስለዚህ ማንኛጡም ሙስሊም አምስት ወቅት ሶላት ከደረሰበት በየትኛውም ቦታ መስገድ ግዴታ አለበት፡፡

1.2 የጁምዓ ቀን ሶላትን በተመለከተም፦

አላህ (ሱ.ወ) በተከበረው ቁርኣኑ በ62ኛው ምዕራፍ በ9ኛው አንቀጽ “እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በአርብ ቀን ለጁምኣ ጥሪ በተደረገ ጊዜ ወደ አላህ ማውሳት (ኹጥባ ለማዳመጥ ለሶላት) ሂዱ።መሸጥንም ግብይትንም ተዉ» ይላል፡፡ ስለዚህ የጁምዓ ሶላት የደረሰበት ሰው ወደ መስጂድ ሂዶ መስገድ ግዴታው ነው፡፡

2. ሂጃብን በተመለከተኑ

አላህ (ሱ.ወ) በተከበረው ቁርኣን በ33ኛው ምዕራፍ በ59ኛው አንቀጽ ላይ «አንተ ነብይ ሆይ!ለሚስቶችህ! ለሴቶች ልጆችሀም፣ሰምዕመናን ሴቶችም፣ ከመከናነቢያዎቻቸው በላያቸው ላይ እንዲለቁ ንገራቸው» ይላል፡፡

ስለሆነም ማንኛዋም ሙስሊም ሴት በማንኛውም ቦታና ሁኔታ እስላማዊ አለባበስን የመጠበቅ ግዴታ አለባት ፡፡ በአጠቃላይ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ሐይማኖታዊ ግዴታዎችንና መገለጫዎችን ማክበርና መተግበር ግዴታ እንዳለበት እያሳሰብን ማንኛውም አካል ወይም ግለሰብ ይህንን የፈጣሪያችንን ግዴታ (ትዕዛዝ) መአልከልም ሆነ ማደናቀፍ እንደሌለበት እናሳስባለን ብሏል፡፡

https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
ኢትዮ መረጃ - NEWS
Photo
የምዕራብ ካናዳ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ  በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በምስራቅ በለሳ ወረዳ ቤተ ክህነት ሥር በሚገኘው የሙት አንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል የአንድነት ገዳም በመገኘት ጉብኝት አደረጉ።

የምዕራብ ካናዳ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል የሆኑት ብፁዕ አቡነ መቃሪዮስ በሙት አንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል የአንድነት ገዳም በመገኘት የተጀመሩ ልማታዊ ስራዎችን በመጎብኘት እና ቡራኬ በመስጠት አባታዊ መልእክት አስተላልፈዋል።

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በምስራቅ በለሳ ወረዳ ቤተ ክህነት ስር የሚገኘው የሙት አንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል የአንድነት ገዳም በስሩ ከዘጠና በላይ አባት እና እናት መነኮሳት በአንድነት የሚኖሩበት ቅዱስ ስፍራ ሲሆን ገዳሙ በመብል እጥረት እና በባዕት አለመኖር እንዲሁም ተያያዥ በሆኑ ምክንያቶች ገዳማውያኑ በከፍተኛ ችግር ውስጥ የሚገኙ መሆኑን በ2016 ዓ.ም በማኅበረ መነኮሳቱ በተደገ የይድረሱልን ጥሪ ሁላችንም የምናስታውሰው ልብን የሚነካ እና ከአዕምሮ የማይጠፋ ክስተት ነበር።

በዚህ ጥሪ መሰረት በከፍተኛ ደረጃ በተደረገ የማኅበራዊ ዘመቻ ንቅናቄ መሰረት በዋናነት ባለ አስራ ስምንት ክፍል የእናቶች ባዕት የተገነባ መሆኑን ገዳማውያኑ አሳውቀዋል።

በመሆኑም ብፁዕነታቸው እነዚህን የእናቶች ማረፊያ በመባረክ እና በመጎብኘት በእናቶች በኩል የተከናወኑ ተግባራትን አድንቀዋል።

ብፁዕነታቸው በዚህ  መንፈሳዊ ሥራ ላይ የማኅበራዊ ትስስር ድረገፆችን በመጠቀም ሱታፌ ያደረጉ ምዕመናን ያመሰገኑ ሲሆን እገዛችሁ ለፍሬ በመብቃቱ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።
አያይዘውም በማስተባበር ሂደት ታላቅ እንቅስቃሴ ያደረጉ የተለያዮ የማኅበራዊ ትስስር ገፅ ባለቤት ለሆኑ አካላት እና ተቋማት ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋፅኦ አመስግነዋል።

ብፁዕነታቸው እንዳሉት የሙት አንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል አንድነት ገዳም የአባቶች ባዕት ያለበት ሁኔታ እጅግ አሰቃቂ እና አሳዛኝ ከመሆኑም በላይ አባቶችን የማደራጀት እና የማቋቋም ስራ እንዲሁ አፋጣኝ እርብርብ የሚሻ ጉዳይ ነው ብለዋል።
ከዚሁ ጋር ተያይዞ በአጠቃላይ ማኅበረ መነኮሳትን ለማጽናት፣ በዘለቄታዊነት ካሉበት ችግር ለማላቀቅ በሚደረገው ጥረት ሁሉ እገዛችሁ ያስፈልገናልና የድጋፍ እጃችሁ አይታጠፍ፣ ልገሳችሁን አጠናክራችሁ ልትቀጥሉ ይገባል ብለዋል።

አክለውም የምዕራብ ካናዳ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል የሆኑት ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ በችግር ላይ የሚገኙ ገዳማትን እና እድባራትን መርዳት የእያንዳንዱ ክርስቲያን ግዴታ መሆኑን የገለፁ ሲሆን ገዳማውያኑ ለሚያቀርቡት የድጋፍ ጥሪ ሁሉም ህዝበ ክርስቲያን የቀድሞውን እርብርብ በአባቶች ገዳም የባዕት ግንባታ ላይም በገንዘብ፣በዕውቀት፣በጉልበት በመርዳት የበኩላችንን ሀላፊነት እንወጣ ዘንድ አባታዊ መልዕክታቸውን በጥብቅ አሳስበዋል።

ከዚሁ ጋር ተያይዞ ድጋፍ ለማድረግ ሙትአንሳ  ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም:-

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ:-1000442598391

ወይም
አቢሲኒያ ባንክ:-141029444

ለማንኛውም አይነት መረጃ:-
09 18 07 79 57 ወይም 09 38 64 44 44 መደወል የምትችሉ መሆኑን ያሳዉቁ ሲሆን ጅማሬያችን ታናሽ ቢሆንም ፍፃሜያችን ታላቅ ነው እና የጀመርነውን እንፈፅም ዘንድ አሳስበዋል።

በመጨረሻም የምዕራብ ካናዳ ሀገረ ስብከት እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በሆኑት በብፁዕ አቡነ መቃርዮስ አባታዊ ፀሎት እና ቡራኬ  የዕለቱ መርሐ ግብር ተጠናቋል።

                              ፳፫/፬/፳፻፲፯ ዓ.ም
                                ጎንደር ኢትዮጵያ
በሕገ-ወጥ አዘዋዋሪዎች ተታለው ከሀገር የወጡ ከ152 ሺሕ በላይ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገር መመለሳቸው ተገለጸ

ከ2016 ዓ.ም. ጥቅምት ወር ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ በሕገ-ወጥ አዘዋዋሪዎች ተታለው ከሀገር የወጡ 152 ሺሕ 349 ሰዎች ወደ ሀገር ቤት መመለሳቸውን የሴቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚንስቴር አስታውቋል።

ሚኒስቴሩ ዜጎች ለሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር እንዳይጋለጡ ከሚመለከተው አካል ጋር በመተባበር እየሰራ እንደሚገኝ ለአሐዱ ገልጿል፡፡

የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር መከላከል እና የተመላሽ ዜጎች ጉዳይ መሪ ሥራ አስፈጻሚ ደረጄ ተግይበሉ፤ በሕገ-ወጥ ስደት ከሀገር ወጥተው ከተመለሱት ዜጎች መካከል 11 ሰዎች ከባድ የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸውና 1 ሺሕ 760ዎቹ ሕጻናት እንደሆኑ ተናግረዋል።

ለችግር ለተጋለጡት ከስደት ተመላሾች ማኅበራዊ ድጋፍ በማድረግ እንዲሁም ከሚመለከተው አካል በጋራ በመሆን የሥራ እድል እንዲፈጠርላቸው ተደርጓል ብለዋል፡፡

በተጨማሪም ከፋይናስ ተቋማት ጋር በመተባበር ብድር እንድያገኙ፣ የመስሪያ ቦታዎች እንዲመቻችላቸው፣ እንዲሁም የሥነ-ልቦና ጫና እንዳይደርስባቸው የክትትል ሥራዎች እየሰሩ ስለመሆኑም ገልጸዋል።

ሥራ አስፈጻሚው በተጨማሪም፤ ማኅበረሰቡ መደበኛ ካልሆነ ፍልሰት እና ከሐሰተኛ መረጃዎች እንዲጠነቀቅ አሳስበዋል።

ከ2014 ዓ.ም. እስከ 2015 ዓ.ም. ድረስ 133 ሺሕ ዜጎች ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ መደረጉ የገለጹ ሲሆን፤ ተመላሾች የትምህርት እና ስልጠና ዕድሎች እንዲያገኙ የሚደረጉ ሥራዎችም ተጠናክረው መቀጠላቸውንመረ ተናግረዋል።
በሰው መግደል ወንጀል ተከሶ የነበረ ግለሰብ ንጹህ ሆኖ በመገኘቱ በነፃ ተሰናበተ

በፌደራል ከፍተኛ  ፍርድ ቤት አርባ ምንጭ እና አካባቢው ተዘዋዋሪ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 327081 በእነ ቨሉ ደር ሁልግደን ሁለት ሰዎች በተከሳሱበት የወንጀል ህግ አንቀጽ 539/1/ሀ ላይ የተመለከተዉን ድንጋጌ በመተላለፍ ከባድ የሰው መግደል ወንጀል ፈጽመዋል ተብሎ በዓቃቤ ህግ ክስ ተመስርቶባቸው የነበረ መሆኑ ተገልጿል ።

ተከሳሾች 1ኛ ቨሉ ደር ሁልግደን እና 2ኛ ባርዶሌ ማጉለኝ ጠበቃ የማቆም አቅም ስለሌላቸው ያለ ጠበቃ ቢከራከሩ  የፍትህ መጓደል እንዳይፈጠር የፌደራል ተከላካይ ጠበቆች ጽ/ቤት ተከላካይ ጠበቃ እንዲመድብላቸው ችሎቱ  በሰጠዉ ትዕዛዝ መሠረት ተከላካይ ጠበቆች ተመድቦላቸው በተከላካይ ጠበቆች እየታገዙ የተከሰሱበትን የወንጀል ክስ ሲከራከሩ እንደነበር ብስራት ሬዲዮ  እና ቴሌቪዥን ሰምቷል።

ተከሳሾች ላይ ዓቃቤ ሕግ ባቀረበው ከባድ የሰው መግደል ወንጀል ክስ ጥፋተኛ ሆነው ቢገኙ ዕድሜ ልክ ጽኑ እስራት ወይም በሞት ሊያስቀጣ የሚችል ድንጋጌ የነበረ መሆኑን ተጠቁሟል።  ተከሳሾች በተከላካይ ጠበቆች በመታገዝ በተደረገ ሰፊ ክርክር የከሳሽ ዓቃቤ ህግ ምስክሮች እና የሰነድ ማስረጃዎች ከተሰማ በኋላ ዓቃቤ ሕግ ክሱን በበቂ ሁኔታ በማስረጃ ያላስረዳ በመሆኑ ከተከሳሾች መካከል 2ኛ ተከሳሽ ባርዶሌ ማጎለኝ  መከላከል ሳያስፈልግ ከቀረበበት ከባድ የሰው መግደል ወንጀል ክስ በነጻ ተሰናብቷል፡፡

አንደኛ ተከሳሽ ቨሉ ደር ሁልግደን በ113/2 መሠረት ድንጋጌው ተቀይሮለት በወንጀል ህግ አንቀጽ 540 ሥር ተራ የሆነ የሰው መግደል ወንጀል እንዲከላከል የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት አርባ ምንጭ እና አካባቢው ተዘዋዋሪ ችሎት ታህሳስ  21ቀን 2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሙሉ ድምጽ  ብይን ሰጥቷል። 

በተከላካይ ጠበቆች በመታገዝ ሲከራከር ቆይቶ በብይን በነፃ የተሰናበተው ተከሳሽ የተከሰሰበት ወንጀል ከባድ እና የሰው ሕይወት ያለፈበት በመሆኑ የዋስትና መብቱን ተነፍጎ ከግንቦት ወር 2016 ዓ/ም ጀምሮ በደቡብ ኦሞ ዞን በፖሊስ ጣቢያ እና በጋሞ ዞን አርባ ምንጭ ማረሚያ ተቋም ታስሮ የቆየ መሆኑ ብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን  ከፌደራል ጠቅላይ ፍረድ ቤት  ያገኘው መረጃ ያመላክታል።

@sheger_press
@sheger_press
ጥቆማ‼️

በሀገራችን እዉቅ ጋዜጠኞች የተመሰረተና የመረጃ አነፍናፊና አዲሱ tikvah የተባለለት የቴሌግራም ቻናል እናስተዋዉቃችሁ

እውነተኛ መረጃ ከፈለጋቹ በፍጥነት ይህን ቻናል መቀላቀል ይኖርባችኋል።

በዚ LINK ግቡ👇
👇👇👇
https://www.tg-me.com/+gPveFwjiiXdiMDE0
https://www.tg-me.com/+gPveFwjiiXdiMDE0
🔴 ጀግናው አባት በጎንደር ...

     የጎንደር ክፉ አጋቾች ግፍ አይፈሩምና ወደ ጡረተኛው የሀገር ሽማግሌ ቤት ሄደው ለእገታ ቤት የአባዎራውን ቤት አንኳኩ ። አባ ዎራው በራቸውን ሳይከፍቱ  "ጥሬ ግሬ ልጆቸን ከማሳደግ ውጭ ምንም የማላውቅ ንጹህ ና ምስኪን አባታችሁ ነኝና ተውኝ እባካችሁ " ሲሉ አጋቾችን ተማጸኗቸው ።
   
   አጋቾች የአባዎራውን ቤት ላይ ቦንብ አከታትለው ወረወሩ። የተወረወረው ቦንብ በቤት ውስጥ የነበሩ ሁለት ሴት ልጆቻቸውን ያቆሰለ። ጀግና አባት በልጆቸ ከመጣችሁ  ቁርጥ ነው" ብለው የራስ መከላከያ ጠመንጃ አቀባብለው አከታትለው በመተኮስ ሁለቱን ነውረኛ አጋች  ከቤታቸው በራፍ አይቀጡ ቅጣት ቀጥተው እስከ ወዲያኛው ሸኟቸው ።
በእርምጃቸው  የተደናገጡት አጋቾች  እግሬን አውጭኝ ብለው ፈርጥጠው ማምለጣቸውን ሰምቻለሁ ...

የጀግናው አባት ምስል ለደህንነታቸው ሲባል እዚህ ላይ አላወጣሁትም ነቢዩ ሲራክ
ታህሳስ 24 ቀን 2017

@sheger_press
@sheger_press
ኢትዮ መረጃ - NEWS
Photo
2 ቀናት ብቻ‼️

እሁድ መድኃኔዓለም ነው:: ደግሞም ቦሌ መድኃኔዓለም ትልቅ መንፈሳዊ ጥሪ አለብን::  ጠዋት ለቅዳሴ ከሰዓት ደግሞ የዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብን ምርቃት ለመታደም በመድኃኔዓለም ቤት እንዋል::

''ተመስገን'' የተሰኘው የዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ ቁጥር 2 የዝማሬ አልበም እሁድ ታኅሣሥ 27 ከቀኑ 6:00 ጀምሮ በቦሌ መድኃኔዓለም ካቴድራል አዳራሽ በታላቅ ድምቀት ይመረቃል::

በፍላሽ የተዘጋጀውን የዝማሬውን አልበም ገዝተው 16ቱን መዝሙራት ለመስማት ቀዳሚ ይሁኑ:: መዝሙራቱ  በሁሉም የCD Distribution  አማራጮችና  (spotify, itunes…) በተለያዩ መተግበሪያዎች ይገኛሉ:: በመላው ዓለም ለማከፋፍል በ+251941518851/ +1 469 733 0150 ይደውሉ ወይም [email protected] ይጻፉልን::

ተመስገን ተመስገን
ለምስጋና ስላሰባሰብከን
እግዚአብሔር ተመስገን
የዩኒቨርሲቲ አመራሮች በአካባቢያዊነት የሚመደቡበትን ሥርዓት ለማቆም እየተሰራ ነው ተባለ

የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ከጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አባላት ጋር ተወያይተዋል፡፡

ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በዚህ ወቅት÷ትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ በርካታ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን አንስተዋል፡፡

በተለይም የዩኒቨርሲቲ አመራሮች በአካባቢያዊና በመንደር የሚመደቡበት ሥርዓት መቆም አለበት በሚል በርካታ እርምጃዎች እየተወሰዱ ነው ብለዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲዎች የዓለም አቀፍ እውቀት መማሪያና የማስተማሪያ ተቋማት እንጂ የአንድ አካባቢን ሰዎች ተቀብለው የሚያስተናግዱ አይደሉም ነው ያሉት ሚኒስትሩ፡፡

አሰራሩ ከዩኒቨርሲቲ መሰረታዊ ተልዕኮ ጋር እንደማይሄድ ጠቁመው÷አዲስ የሚመደቡና የሚቀየሩ የዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንቶች እንደ መርሕ በችሎታና በውድድር ብቻ የመመደብ ሥራ እየተሰራ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡

በዚህም የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲን ካለበት መሰረታዊ ችግር ለማላቀቅ የአመራር ለውጥ ከተደረገ በኋላ ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴዎች እየተደረጉ መሆኑን አብራርተዋል።

ዩኒቨርሲቲዎች እውቀትና እውነት የሚገበይባቸው ትክክለኛ የማስተማሪያና የምርምር ተቋማት ሊሆኑ እንደሚገባም አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ድሪባ ኢቲቻ (ዶ/ር) በበኩላቸው÷ አዲስ አመራር ከተመደበ በኋላ ዘርፈ ብዙ ችግሮችን ለመቅረፍ በርካታ ሥራዎች እንደተከናወኑ መናገራቸውን የሚስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

Via: ፋና

https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
500 ኪ.ግ የሚመዝን የጋለ ብረት መውደቁ ተነገረ
በአጎራባቿ ኬንያ 500 ኪሎ ግራም ሊመዝን የሚችል ብረት ከሰማይ ወድቋል ነው የተባለው።

ቀለበታማ ብረቱ የወደቀው ሙኩኩ በተሰኘች መንደር እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን ብረቱ የ2 ነጥብ 5 ሜትር ስፋት ወይም ዲያሜትር ያለው መሆኑ ተመላክቷል።

የኬንያ ስፔስ ኤጀንሲ ብረቱ በስፔስ ላይ ከሚገኙ ሮኬቶች ተገንጥሎ የወደቀ ሊሆን እንደሚችል አስታውቋል።

https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
2025/01/09 12:15:58
Back to Top
HTML Embed Code: