Telegram Web Link
መፍትሄ ያላገኘው የሂጃብ ጉዳይ‼️

በትግራይ ክልል የአክሱም ከተማ ሙስሊም ተማሪዎች በሂጃባቸው ምክንያት ትምህርት አቋርጠው ያለመፍትሔ መቀመጣቸውን ገልጸዋል።

"እኛ ከትምህርት ቤቶቹ ዩኒፎርም ጋር የሚመሳሰል ሀይማኖታችን በሚያዘው መሰረት ሂጃብ ለብሰን ትምህርታችንን እንማር ብለን ነው የጠየቅነው የሚሉት ተማሪዎቹ ነገር ግን ፀጉራቹሁ ካልታየ መማር አትችሉም ተብለን ከትምህርት ገበታ ተፈናቅለናል" ብለዋል።

የ12ኛ ክፍለ ዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተና ለመውሰድ ፎርም የሚሞላበት የመጨረሻ ቀን ነገ ረቡዕ እንደሆነ የገለፁት ተማሪዎች "ሂጃብ ካላወለቃችሁ" በመባሉ ምክንያት አንድም ሙስሊም ተማሪ ፎርሙን አለመሙላቱን ተናግረዋል።

https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
ኦርቶዶክሳዊ መንፈሳዊ ጉዞ ወደ ቅዱስ ላሊበላ!

በነፍሳችን ዲያብሎስ ፣ በስጋችን ቄሳር እንዳይነግስ፣ ያለወንድ ዘር በረቂቅ ሚስጥር ከብጽዕት ማርያም የተወለደውን ወልድ እግዚአብሔርን ኑ በምስጋና እናንግሰው።

ንጉሧን ያላወቀች እስራኤል ከምድር ያሳደደችው ፣ በመስቀል ሆኖ "ንጉሥ" የተባለ ፣ በመላእክት የተበሰረ ዜና ልደቱን፣ በያሬዳዊ ዝማሬ በታሪካዊው ቅዱስ ላሊበላ በማክበር በረከተ ነፍስ በረከተ ስጋን እናትርፍ።

ለአረጋውያን ፣  ለነፍሰጡር ፣ ለህፃናት እና ለአካል ጉዳተኞች በጤና ባለሙያዎች ልዩ እንክባቤ እንሰጣለን። ስለማረፊያዎ አያስቡ፤ያሉን ቦታዎች ውስን ናቸውና ፈጥነው በመመዝገብ ቦታ ይያዙ።

የጉዞ መነሻ ቀን:- 24/04/17

የጉዞ መመለሻ ቀን:- 02/05/17

የጉዞ ዋጋ:- ምግብን ፣ ማረፊያን ፣ መስተንግዶን እና አስጎብኚን ጨምሮ :-6,500

ለበለጠ መረጃ:-0938944444

አዘጋጅ:- ማኀበረ ቁስቋም
አሐዱ ራዲዮና ቴሌቭዥን የፖለቲከኛው ጀዋር መሐመድ ቃለመጠይቅ ላለማስተላለፍ መወሰኑን የጣቢያው የቅርብ ምንጮች ገልፀዋል።

አሐዱ ቃለመጠይቁን በኬንያ ናይሮቢ ተገኝቶ ከሰራ በኋላ እንደሚያስተላልፍም ማስታወቂያ ማስነገሩን አስታውሶ ሆኖም
አቶ ጀዋር ለቢቢሲ አማርኛ ተመሳሳይ ቃለመጠይቅ በመስጠቱ ምክንያት ለዚህ ውሳኔ እንዳበቃው ተጠቁሟል።

ከጣቢያው በጉዳዩ ላይ ይፋዊ ማብራሪያ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም።

አቶ ጀዋር መሐመድ ከሰዓታት በፊት ምንጮችና ራዊ ድረገፁ ባሰፈረው ሐተታ ቃለመጠይቁ ሳይከለከል እንዳልቀረ በመጥቀስ ቃለመጠይቁን በአማራጭ ሚድያ ለመልቀቅ እንደሚገደድ ፅፏል።
ባለፉት አምስት ወራት 380 ቢሊየን ብር ገቢ መሰብሰቡን የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና የገቢዎች ሚኒስትር ዓይናለም ንጉሴ ገለፁ።

ሚኒስትሯ ባለፉት የለውጥ አመታት የገቢ አሰባሰብ አፈጻጸምን በተመለከተ በሰጡት ማብራሪያ፤ በሀገር ደረጃ የተያዙ የልማት ዕቅዶችን ተግባራዊ ለማድረግ ዋነኛ አቅም ተደርጎ የሚወሰደው የሀገር ውስጥ ገቢን ማሻሻልና ማሳደግ ነው ብለዋል።

ይህም የህዝብ የልማት ፍላጎትን ደረጃ በደረጃ የሚመልሱ መሰረተ ልማቶችን መገንባት እንደሚያስችልም ገልጸው።

እንደ ሀገር የኢኮኖሚ ማሻሻያውን ሊደግፍ የሚችል እና አስተማማኝ የፋይናንስ ምንጭ እንዲኖር የገቢ አሰባሰብ ሂደት ላይ በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል።

ባለፉት የለውጥ ዓመታት የኢትዮጵያን የብልፅግና ጉዞ ሊደግፍ የሚችል የሀገር ውስጥ የፋይናንስ አቅም መገንባቱንም አረጋግጠዋል።

@Sheger_press
@Sheger_press
ጥንቃቄ‼️

ዛሬ ማለትም ታህሳስ 17 /2017 ዓ.ም ጀምሮ ብዙ የቴሌግራም አካውንቶች ከላይ በተጠቀሰው የማስገሪያ (phishing link) እና ሌሎች ተጨማሪ ማስገሪያዎች አማካኝነት መረጃዎች እየተመዘበሩ ስለሆነ ከማንኛውም የቴሌግራም ተጠቃሚ (ከምታውቁት እና ከማታውቁት ) ግለሰብ ሊንክ ቢላክላችሁ መክፈት እንደሌለባችሁ እና ወዲያውኑ እንድታጠፉት ይመከራል።

https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
በፕሮፌሺናል ጋዜጠኞች ተከፍቶ መረጃዎችን ተከታትሎ በሚዛናዊነት የሚያቀርብ ቻናል ልጠቁማችሁ ፡፡

ተማመኑበት ታተርፉበታላችሁ ተቀላቀሉት
👇👇👇
https://www.tg-me.com/+gPveFwjiiXdiMDE0
https://www.tg-me.com/+gPveFwjiiXdiMDE0
ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ከእስራኤል የአየር ጥቃት ለጥቂት መትረፋቸው ተነገረ

የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም በየመን በአየር ማረፊያ ሳሉ በደረሰ የአየር ጥቃት መትረፋቸውን አስታውቀዋል ፡፡

እስራኤል በየመን ዋና ከተማ ሰነዓ በሚገኙት የሀውቲ አማፂያን ወታደራዊ መሰረተ ልማቶች ላይ መጠነ ሰፊ የአየር ጥቃት መፈፀሟ ተሰምቷል፡፡

በዚህም በሰንዓ አየር ማረፊያ የነበሩት ዳይሬክተሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት እርሳቸውና ባልደረቦቻቸው ከጥቃቱ መትረፋቸውን ገልጸዋል፡፡

የሰነዓ አየር ማረፊያ ተጠግኖ አገልገሎት መስጠት እስከሚጀምርም ዋና ዳይሬክተሩ እና ቡድናቸው በሰነዓ እንደሚቆዩ  ተናግረዋል ፡፡

ዶክተር ቴድሮስ በአደጋው ህይዎታቸው ላለፉትና ለቤተሰቦቻቸው የተሰማቸውን ሐዘን ገልጸዋል፡፡(ethio fm)

https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
ጥንቃቄ‼️

ዛሬ ማለትም ታህሳስ 17 /2017 ዓ.ም ጀምሮ ብዙ የቴሌግራም አካውንቶች ከላይ በተጠቀሰው የማስገሪያ (phishing link) እና ሌሎች ተጨማሪ ማስገሪያዎች አማካኝነት መረጃዎች እየተመዘበሩ ስለሆነ ከማንኛውም የቴሌግራም ተጠቃሚ (ከምታውቁት እና ከማታውቁት ) ግለሰብ ሊንክ ቢላክላችሁ መክፈት እንደሌለባችሁ እና ወዲያውኑ እንድታጠፉት ይመከራል።

@Sheger_press
@Sheger_press
4.9 በሬክተር ስኬል የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ በድጋሚ አጋጠመ

ዛሬ ሌሊቱንም በድጋሚ በሬክተር ስኬል 4.9 የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥ ተሰምቷል። 11 ሰዓት ገደማ ላይ የተሰማዉ ንዝረቱ እስካሁን ከታዩት የመሬት መንቀጥቀጦች ዘለግ ላሉ ሰከንዶች የቆየም እንደነበር ተሰምቷል።

የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ የመሬት መንቀጥቀጡ ከመተሃራ አቅጣጫ በስተሰሜን 26 ኪሜ ርቆ መሆኑን እና 4.9 በሬክተር ስኬል የተለካ መሆኑን አሳዉቋል።

በተከታታይ የተከሰተዉ የመሬት መንቀጥቀጥ በሬክተር ስኬል 4.9 የተመዘገቡ ሲሆን በቀዳሚነት ከነበሩት ከፍ ያለ እና ሁነቱ አዲስ ሆኖ መታየት ከጀመረበት እና በወቅቱ ከታዩት የመሬት መንቀጥቀጥ ስሜቶች ጋር ተመሳሳይነት ያለዉ ነዉ።

https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
''ተመስገን''

መላእክቱና እረኞች በአንድነት ሆነው ''በሰማያት ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን...'' ብለው ያመሰገኑትን ጌታ እኛም  እንዲሁ እሁድ ታኅሣሥ 27 ከቀኑ 6:00 በቦሌ ደ/ሳ መድኃኔዓለም ካቴድራል አዳራሽ ተሰብስበን ''ተመስገን'' በተሰኘው የዘማሪ ዲ/ን አቤል መክብብ ቁጥር 2  የዝማሬ አልበም የተወለደውን አምላክ እናመሰግናለን::

በዕለቱም 16 መዝሙራትን የያዘው የዝማሬ አልበም ለሽያጭ ይቀርባል::


መዝሙራቱ በማኅቶት ቲዩብ የሚለቀቁ ሲሆን በሁሉም የCD Distribution  አማራጮችና  (spotify, itunes…) በተለያዩ መተግበሪያዎች ይገኛሉ::


በመላው ዓለም ለማከፋፍል በ+251941518851/ +1 469 733 0150 ይደውሉ ወይም [email protected] ይጻፉልን::


ተመስገን ተመስገን
ለምስጋና ስላሰባሰብከን
እግዚአብሔር ተመስገን
በመዲናዋ በአምስት ወራት ውስጥ ከ300 በላይ ሕጻናት በተለያዩ ቦታዎች ተትተው መገኘታቸው ተገለጸ‼️
👉ሕጻናትን ወልደው በተለያዩ ቦታዎች ላይ የሚተው ወላጆች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ማሳሰቢያ ተላልፏል

ታሕሳስ 17/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት አምስት ወራት ውስጥ ብቻ እድሜያቸው ከ8 ዓመት በታች የሆኑ ከ300 በላይ ሕጻናት በወላጆቻቸው የተለያየ ቦታዎች ላይ ተትተው መገኘታቸውን የከተማ አስተዳደሩ ሴቶችና ሕጻናት ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ገልጿል፡፡

ቢሮው የተለያዩ አካባቢዎች ላይ ሕጻናትን ወልደው የሚተው ወላጆች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ማሳሰቢያ አስተላልፏል፡፡

በወላጆቻቸው ተትተው የተገኙት ሕጻናትም፤ በክበበ ፀሀይ የሕጻናት መንከባከቢያ ማዕከል ውስጥ እንዲገቡ መደረጉንም አስታውቋል፡፡

በቢሮው የሕጻናት ደህነት መብት ማስጠበቅ ዳይሬክተር አቶ አንዷለም ታፈሰ ለአሐዱ እንደተናገሩት፤ ሕጻትን በተለያየ ቦታ በመተው እና ወላጅ አጥ ሆነው እንዲያደጉ ማድረግ በሀገር ላይ ሁለንተናዊ ተፅእኖ እያሳደረ ይገኛል፡፡

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ መሰል ችግሮች በመዲናዋ እየተስፋፉ መምጣታቸውን አንስተው፤ ከ3 መቶው ሕጻናት በተጨማሪ በቅርቡ አንድ መቶ አምሳ ሕጻናት ከተለያዩ አካባቢዎች ተገኝተው ወደ ማዕከሉ መቀላቀላቸውን ተናግረዋል፡፡

ወላጆች ሕጻናትን በተለያዩ ቦታዎች ለመተዋቸው ዋንኛው ምክንያት ድህነት መሆኑን የገለጹት ዳይሬክተሩ፤ መሰል ድርጊቶችን መፈጸም ከሀይማኖት እና ባህል ጋር የሚጣረስ እንዲሁም ፍጹም ከኢትዮጵያዊነት ያፈነገጠ በመሆኑ ወላጆች ከዚህ ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አሳስበዋል፡፡

በዚህ ማዕከል ውስጥ ሕጻናትን በመንከባከብ፣ በመጠበቅ እና በማስተማር ደረጃ በመንግሥት በኩል በርካታ ሥራዎች እየተሰሩ ስለመሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

ኃላፊው አያይዘውም የችግሩን መስፋፋት ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት በ3 ዓመታት ውስጥ ተጨማሪ አንድ ሺሕ የህፃናት ማቆያ ማዕከላት  እንደሚገነቡ ተናግረዋል።
#አሀዱ

https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
ልጄ ሆይ ልብህን ስጠኝ ያለህ እግዚአብሔር ቸርነትህን ይጠብቃል!


ከአለም ርቀው ስለፍቅሩ ሲሉ በየበርሀው እና በየገዳማቱ ባዕታቸውን ቀልሰው ሌት ከቀን ለሚማፀኑልን ሰርክ የሚጸልዩ ስለ ዓለሙ ምልጃ የሚተጉ የሚያነቡ  ገዳማውያን የልጆቻቸውን እጅ ናፍቀው ተጨነቁ ቢባል እግዜሩስ እንዴት ያየናል?!

ስለእኛ ለነፍሳችን በመድከም በመንፈሳዊ ህይወት መምህር የሚሆኑን የክርስቶስ እውነተኛ ሙሽሮች ገዳማውያን፣ ዛሬ ላይ ባለው  ሰው ሰራሽም ሆነ ተፈጥሯዊ ነባራዊ ሁኔታዎች የሚቀመስ እፍኝ ቆሎም ጠፍቶ ረሀብ ጥማቱ በብርቱ እየተፈታተናቸው ለጾም ለጸሎት መቆም ተስኗቸው  ከተፈጥሮ ጋር ግብ ግብን ይዘዋል።


እግዚአብሔርን የምትወዱ እርሱን ለመምሰል የምትተጉ ብጹዓን  ጥቂት በመራራት የቸርነት እጃችሁን ለእነዚህ  ገዳማውያን በመዘርጋት በረከተ እግዚአብሔርን ታገኙ ዘንድ እንጠይቃቹኋለን፡፡


ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም


ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444


የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444
                       
የጸጥታው ምክር ቤት የአፍሪካ ህብረት የሶማሊያ የሽግግር ተልዕኮ ተተኪን በተመለከተ ድምጽ ሊሰጥ ነው ተባለ፡፡

በተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት የአፍሪካ ህብረት የሶማሊያ የሽግግር ተልዕኮን (አትሚስ) የሚተካው ሌላኛው ተልዕኮ ላይ ድምጽ ለመስጠት ስብሰባ እንደሚያካሂድ ተገልጿል።

በምክር ቤቱ ጊዜያዊ የአሰራር ደንብ መሰረት በስብሰባው ላይ ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የአትሚስ ተልዕኮ ባለፈው ነሐሴ ወር ላይ እስከ ፈረንጆቹ ታህሳስ 31፣ 2024 ድረስ ተራዝሞ ነበር።

በዩናይትድ ኪንግደም የተዘጋጀው ረቂቅ የውሳኔ ሃሳብ፤ የአፍሪካ ህብረት የሰላም እና የፀጥታው ምክር ቤት አትሚስን በአፍሪካ ህብረት የሶማሊያ ድጋፍ እና ማረጋጋት ተልዕኮ (AUSSOM) ለመተካት ያሳለፈውን ውሳኔ የሚደግፍ ነው።

ከዚህ በተጨማሪም የአፍሪካ ህብረት አባላት በዚህ ረገድ ለ12 ወራት አስፈላጊውን ሁሉ እርምጃ እንዲወስዱ ስልጣን ይሰጣል።

ረቂቁ የአፍሪካ ህብረት አባል አገራት እስከ መጪው የአውሮፓውያኑ ሰኔ መጨረሻ ድረስ 1 ሺሕ 40 የፖሊስ አባላትን ጨምሮ እስከ 12 ሺህ ገደማ መለዮ ለባሽ የጸጥታ አካላት እንዲያሰማሩ ፈቅዷል።

የአፍሪካ ኅብረት የሰላም እና ፀጥታ ምክር ቤት ከተለያዩ አገራት የተወጣጣ ሰላም አስከባሪ ኃይል ለስድስት ወራት በሶማሊያ እንዲቆይ ማሰማራቱ ይታወቃል።

https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
ዳቦ ለመግዛት የሄደች 5 ዓመት ሕጻንን አስገድደው የደፈሩ ሁለት የዳቦ ቤት ሠራተኞች በ19 ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጡ

በደቡብ ኢትዮጵያ በጌዴኦ ዞን ወናጎ ከተማ አስተዳደር በ 5 ዓመት ሕጻን ልጅ ላይ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል የፈፀሙ ተከሳሾች በእስራት መቀጣታቸውን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል።

ተከሳሾች አቶ ኤልያስ ኤቶ እና አቶ ታምሩ ንጋቱ የተባሉ ሁለቱም ግለሰቦች የዳቦ መጋገሪያ ቤት ሠራተኞች ናቸው።

ወንጀሉ የተፈፀመው በወናጎ ከተማ አስተዳደር ቱቱፈላ ቀበሌ ኦዶላ ተብሎ በሚጠራበት አከባቢ ሲሆን፤ ተበዳይ የ5 ዓመት ሕጻን ሕዳር 14 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ሰዓት ዳቦ ለመግዛት በሄደችበት በሁለት ዳቦ ቤት ሠራተኞች መደፈሯ ተገልጿል።

ይህም ወንጀል መፈጸሙን ክሱ የደረሰው የወናጎ ከተማ አስተዳደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በቀረቡ የሰውና የሰነድ ማስረጃዎች ማረጋገጡን አስታውቋል።

በአስገድዶ መድፈር ወንጀል ጥፋተኛ ሆነው ክስ የቀረበባቸው ወንጀለኞች ታሕሳስ 17 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት ሁለቱም ተከሳሾች እያንዳንዳቸው በ 19 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጡ ፍርድ ቤቱ መወሰኑን አሐዱ ከዞኑ ፖሊስ መምሪያ የህዝብ ግንኙነት ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

በተጨማሪም ፍርድ ቤቱ በተመሳሳይ ቀን በዋለው ችሎት ተከሳሽ ወጣት ኤርምያስ ፀጋዬ 3 ዓመት ከ 6 ወር በሆነችው ተበዳይ ሕጸን ርኆቦት በለጠ ከምትጫወትበት ቦታ ወደ ኤት ኤል ትምህርት ቤት ይዞ በመሄድ የመድፈር ሙከራ ማድረጉን በምስክር ያረጋገጠው ፍርድ ቤት በ 10 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ መወሰኑ ተገልጿል።

https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
በምስራቅ ወለጋ ዞን በትራፊክ አደጋ የ11 ሰዎች ህይወት አለፈ

በምስራቅ ወለጋ ዞን ሲቡ ሲሬ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ11 ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡

አደጋው የተከሰተው በተለምዶ ሲኖ ትራክ በሚል የሚታወቅ የጭነት ተሸከርካሪ እና የህዝብ ማመላለሻ ሚኒ ባስ በመጋጨታቸው መሆኑ ተነግሯል፡፡

በአደጋው የ11 ሰዎች ህይወት ከማለፉ በተጨማሪ 12 ሰዎች ላይ ከባድ እና ቀላል የአካል ጉዳት እንዲሁም የንብረት ውድመት መድረሱን የሲቡ ሲሬ ወረዳ የትራፊክ ደህንነት ሃላፊ ኢንስፔክተር ፈዮ ቡሊ ገልጸዋል፡፡

Via ፋና
https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
2024/12/28 01:40:47
Back to Top
HTML Embed Code: