Telegram Web Link
004A1116.JPG
5.9 MB
የአባቶች ስቃይ

#ከራሱ ቆዳ የተሰራውን ስልቻ አሸዋ ሞልተው አሸከሙት


ከ12ቱ ቅዱሳን ሐዋርያት አንዱ ቅዱስ ቶማስ በተጣራራሪነቱ ይታወቃል፡፡

በቀዳሚ ስሙ ‘ዲዲሞስ’ ወይም ጨለማ ሲባል የነበረ ቢሆንም በኋላ ግን ቶማስ ወይም ፀሐይ ተብሏል፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ከተነሣ በኋላ በ8ኛው ቀን እሁድ ነው ያየው፡፡

እናም በጦር የተወጋ ጐኑን ዳስሶ ማረጋገጥ በመፈለጉ ዳሶ ሲያውቅ ግን ጌታዬ አምላኬ ያለ ነው፡፡ እመቤታችን ስታርግም ከሁሉም ቀድሞ ያየው  ነው፡፡

ወደ ሀገረ ስብከቱ ሕንድ የገባው እንደ ባሪያ በ30 ብር ተሽጦ ነበር፡፡ የገባበት አካባቢ አስተዳዳሪ ሉክዮስ አሳዳሪው ሆኖ በቤቱ ሲያገለግል ምን መሥራት እንደሚችል ሲጠይቀው ሕንፃ ማነጽ ሐውልት መቅረጽ እንደሚችል ስለነገረው ብዙ ወርቅና ብር ሰጥቶ ሰርቶ እንዲጠብቀው ነግሮት የተለየ ጥበብኛ ሰው አገኘሁ ለማለት ወደ ንጉሥ ሄደ፡፡


ቅዱስ ቶማስ ግን ገንዘቡን ለነዳያን መጸወተው በርካቶችንም አስተምሮ አሳምኗቸዋል፡፡ የሉክዮስ ሚስትና ልጆቿ ቤቱ ካሉ አገልጋዮች ጋር ሁሉ አምነው ተጠምቀዋል፡፡

ሉክዮስ ከሄደበት ተመልሶ ሕንጻውንና ሐውልቶቹን ለማየት ቢፈልግም ሐዋርያው በወርቅና በብርህ ያነጽኳቸው ሕንጻዎች እኒህ ናቸው ብሎ ያመኑትን አገልጋዮች አሳየው፡፡ ይህ ክፉ ባሪያ ተጫወተብኝ ብሎ እጅ እግሩን አሥሮ ቆዳውን አስገፍፎ ስልቻ አስፍቶ በአሸዋ መልቶ አሸክሞ በገበያው ሲያዞረው ሚስቱ አርሶንዋ አይታ በድንጋጤ ወድቃ ሞተች፡፡

መስፍኑም ደንግጦ ሚስቴን ካዳንካት እኔም በአምላክህ አምናለሁ አለው፡፡ ጌታ ቁስሉን እንደ ውኃ አቀዝቅዞለት ካለችበት ሄዶ ስልቻውን ቢያስነካት ተነሥታለች በዚህም ሉክዮስ አምኖ ተጠምቋል፡፡

ከዚህም በኋላ ስልቻውን ተሸክሞ ከቦታ ወደ ቦታ እየተዘዋወረ ሙት እያነሣ ድውይ እየፈወሰ አሕዛብን አሳምኖ አጠመቀ፡፡

በቀንጦፍያ የተገደሉ የአንድ ሽማግሌ ሰባት ልጆች ስልቻውን እያስነካ አስነሥቶለታል፡፡ በኢናስም የቃሉን ትምህርት የእጁን ተአምራት አይተው ከንጉሱ ሚስት ጀምሮ እስከ ተራ ገባር ድረስ ያሉት ሁሉ አምነው ተጠመቁ፡፡ በኋላም የጣኦት ካህናተ በተንኮል ከንጉሥና መኳንንቱ ጋር አጣልተው በሰይፍ አስመትተውታል፡፡

ዛሬም ድረስ ሕንድ ውስጥ በመንበሩ ላይ የጌታችንን የተወጋ ጎኑን የዳሰሰች የቅዱስ ቶማስ ቀኝ ቅድስት እጅ በሕይወት እንዳለች ሆና ትታያለች፡፡ በሕንድ ኦርቶዶክስ ቤ/ክ ፓትርያርክ ሲሾሙም የቅዱስ ቶማስን ቀኝ እጅ በሚሾመው ፓትርያርክ ላይ ጭነው ነው፡፡

ገዳማውያን እናቶችና አባቶች በብዙ ስጋዊ መከራ ውስጥ እንኳን አልፈው በእምነታቸው ጸንተው የክርስቶስን ወንጌል በሕይወታቸው ሰብከው፣ ወንጌልን ኖረው ነው የሚያልፉት፡፡ ታዲያ ገዳማቸውን ስንደግፍ፣ በዓታቸውን ስናጸና የእነርሱን በረከት እንታደላለን፡፡


ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም


ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444


የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444
ከ3 ሃኪሞች በስተቀር ሁሉም የ #ካምባ ወረዳ ሆስፒታል የህክምና ባለሙያዎች ሥራ በመልቀቃቸው ነዋሪዎች ለከፍተኛ እንግልት ተዳረጉ

#ደቡብ_ኢትዮጵያ ክልል #ጋሞ ዞን ካምባ ወረዳ የሚገኘው ብቸኛው የካምባ ወረዳ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል፤ በክፍያና ጥቅማጥቅም አለመፈጸም እንዲሁም “በወረዳው አመራር ያልተገባ ድርጊት” ምክንያት የሕክምና ባለሙያዎች ከሥራ በመልቀቃቸው በተከሰተ የባለሙያ እጥረት ህብረተሰቡ ለከፍተኛ እንግልት መዳረጉን ነዋሪዎች ገለጹ።

ሆስፒታሉ በአከባቢው ብቸኛ የሕዝብ መገልገያ የጤና ተቋም በመሆን ለካምባና ለጋርዳ ማርታ ወረዳዎች ግልጋሎት ሲሰጥ ቢቆይም አሁን ላይ 3 ሃኪሞች በቻ በመቅረታቸው የሕክምና አገልግሎት ወደ ማቆም ተቃርቧል ሲሉ ነዋሪዎች ገልጸዋል።

ሆስፒታሉ ታካሚዎችን ከካምባ ወረዳ በ105 ኮሎ ሜትር ርቀት ላይ ወደሚገኘው #አርባምንጭ ሆስፒታል በመንግስት አንቡላንስ  7000 ብር በማስከፈል ሪፈር  ያደርጋል ተብሏል።

የሆስፒታሉ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢዩኤል ቡጋ በበኩላቸው ከ2015 ዓ.ም የካቲት ወር ጀምሮ ችግሮች መኖራቸውን ጠቅሰው፤  የድንገተኛ ቀዶጥገና ህክምና የሚሰጥ ባለሙያ ባለመኖሩ ሆስፒታሉ መስጠት የሚገባውን አገልግሎት እየሰጠ አለመሆኑን ገልጸዋል።

https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
ኢትዮ መረጃ - NEWS
Video
#ሳይበሉ የሚጠግቡት፣ ሳይቀቡ የሚወዙት


ከክርስቶስ ልደት በፊት በ500 ዓመተ ዓለም ግንቦት 10 ቀን የእረፍታቸው መታሰቢያ ሲሆን፣ በየዓመቱ ታሕሣስ 02 ደግሞ ዓመታዊ መታሰቢያቸው ነው፡፡ በትንቢተ ዳንኤል ታሪካቸው በሰፊው ተጽፎ የሚገኘው “ሠለስቱ ደቂቅ” ወይም ሦስቱ ሕፃናት አናንያ፣ አዛርያ፣ ሚሳኤል የባቢሎኑ ንጉስ ናቡከደነጾር ኢየሩሳሌምን ባጠፋት ጊዜ ማርኮ ከወሰዳቸው እስራኤላውያን ውስጥ ይገኙበታል፡፡


በንጉሱ ቤት እንዲቀመጡ ከተመረጡት ምርኮኞች ውስጥም እነዚህ የይሁዳው ንጉስ የኢዮአቄም ልጆችና ነቢዩ ቅዱስ ዳንኤል ተጠቃሽ ናቸው፡፡


የሀገራቸው ነገር ዘወትር ያሳስባቸዋልና በጾምና በጸሎት ይተጉ ነበር፡፡ እናም በቤተ መንግስት ከሚዘጋጀው ምግብ ይልቅ ጥራጥሬ መብላት ነበር የመረጡት፡፡ በንጉሱ ፊት የሚቀርቡብት ቀን ሲደርስም ከሌሎቹ ሕፃናት ይልቅ ወዝተውና አምረው ይታዩ ነበር፡፡ በቤተ መንግስቱ ከሚኖሩ ወጣቶችና ከባቢሎናውያን ወገንም የእነርሱን ያህል ጥበበኛ አልተገኘም፡፡

ንጉስ ናቡከደነጾርም ወዷቸዋልና በአማልክቱ ስም ሲድራቅ፣ ሚሳቅና አብደናጎ ብሎ ሰየማቸው፡፡ ይህ በንጉሱ ዘንድ ያገኙት ተቀባይነት በባቢሎናውያኑ የቤተ መንግስቱ ሰዎች ዘንድ ከፍተኛ ቅናት ፈጠረ፡፡ እናም ነገር መጎንጎን ጀመሩ፡፡


ንጉሱ ለክብሩ መገለጫ ቁመቱ 60 ክንድ የሆነ የወርቅ ምስል አቁሞ ሕዝቡን ሁሉ እንዲያሰግድ፣ የማይሰግድ ቢኖር እስከ ሞት በሚደርስ ቅጣት እንዲቀጣ ምክር አቀረቡና አስተገበሩት፡፡ ሦስቱ ሕጻናት ግን ለመስገድ ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀሩ፡፡

ይህን ጊዜም በእሳት ተቃጥለው እንዲሞቱ ተፈረደባቸው፡፡ 49 ክንድ የሆነ እሳት ነዶም ወደዚያ ተጣሉ፡፡ እነርሱ ግን በእሳቱ ውስጥ ሆነው አምላካችን እግዚአብሔርን ያመሰግኑ ነበር፡፡ በዚህ መካከል ንጉሱ በእሳት ውስጥ አራት ሰዎች እየተመለከተ እንደሆነ ገለጸ፡፡


አራተኛወር ሊያድናቸው የመጣው ሊቀ ማላዕክት ቅዱስ ገብርኤል ነበር፡፡ ከልብሳቸው አንዲት ክር፣ ወይም ከጸጉራቸው አንዲት ነቁጥ ሳትቃጠል ወጥተዋል፡፡ ወደ እሳቱ የጣሏቸው ሰዎች ግን በወላፈኑ ተለብልበው ሞተዋል፡፡


በእሳቱ ላይ ሆነው ያደረሱት ምስጋና ዛሬም ድረስ በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን “የሶስቱ ሕጻናት ምስጋና” “ጸሎቱ ሰለስቱ ደቂቅ” ተብሎ ከመዝሙረ ዳዊት ጋር ይጸለያል፡፡ ታሕሣስ 2 ቀን መታሰቢያቸው የሚደረግላቸው እነዚህ ቅዱሳን ካረፉ በኋላ በዚያው በባቢሎን ተቀብረዋል፡፡

አስገራሚው ነገር ንጉሱ ናቡከደነጾር እጅግ ይወዳቸው ነበርና ሲሞት በመካከላቸው እንዲቀብሩት ትዕዛዝ በማስተላለፉ በእነርሱ መቃብር ነው የተቀበረው፡፡ ሳይበሉ የሚጠግቡት፣ ሳይቀቡ የሚወዙት ባደረባቸው መንፈሳዊ ኃይልና በእግዚአብሔር ቸርነት ነበር፡፡


አሁን በዘመናችንም ዓለምና አምሮቷን ንቀው፣ በገዳማትና በየዋሻው ያሉ አባቶቻችን በቀን አንድ ጊዜ መናኛ ነገር እየተመገቡ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ነው ጸንተው የሚኖሩት፡፡ የበረከታቸው ማሳያ የሆነው ደግሞ የጸሎታቸው ኃይል ነው፡፡ ድውያን ይፈወሳሉ፣ ተአምራት ያደርጋሉ፡፡ እነዚህን ገዳማት በመደገፍና በዓታቸውን በማጽናት የበረከቱ ተሳታፊ እንሁን፡፡    

    
ድጋፍ ለማድረግ :-ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም

                ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
                 1000442598391

                        ወይም

                   አቢሲኒያ ባንክ
                   141029444


ለተጨማሪ መረጃ:- 
   የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957     
                         ወይም 0938644444
❗️ፕሬዝዳንት ፑቲን የሩሲያ ኢኮኖሚያዊ እድገት በአብዛኛው የሉአላዊነቷ ውጤት ነው በማለት ተናገሩ

ሉአላዊነት በተለይም ለሩሲያ በጣም አስፈላጊ ነገር ነው፤  ምክንያቱም ሉአላዊነቷን ስታጣ ሀገር መሆኗን ታጣለች በማለት አክለዋል።

https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
አንድ ኩላሊቱን በመስጠት የሚስቱን ሩሀማ ህይወት የታደገው ሀብታሙ

ከDMC real estate የ1 ዓመት የቤት
ክራይ ሙሉ ብር ሰጥተውታል::(ጉርሻ)

https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
በናይሮቢ ሊካሄድ የነበረው የጃዋር መጽሐፍ ምርቃት "በደህንነት ስጋት" ምክንያት ተሰረዘ‼️

የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ አመራሩ ጃዋር መሐመድ 'አልጸጸትም' በሚል ርዕስ ሐሙስ፣ ታህሳስ 10/ 2017 ዓ.ም በናይሮቢ ሊያስመርቀው የነበረው መጽሐፍ ከተለያዩ አካላት በደረሱ ማስፈራሪያዎች እና ዛቻዎች ላልተወሰነ ጊዜ መተላለፉን የቢቢሲ ምንጭ ገለጹ።

ረቡዕ፣ ታህሳስ 9/ 2017 ዓ.ም ይፋዊ የሆነ ዛቻ/ተቃውሞ ከኢትዮጵያ መንግሥት መድረሱን እኚሁ ምንጭ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ መንግሥት አደረሰው የተባለው ይፋዊ የሆነው ዛቻ/ተቃውሞ ለየትኛው አካል እንደደረሰ ምንጩ በዝርዝር ከመናገር ተቆጥበዋል።

ቢቢሲ ከመንግሥት ደረሰ የተባለውን ዛቻ በገለልተኝነት ማረጋገጥ አልቻለም።

ቢቢሲ ለኢትዮጵያ መንግሥት ባለስልጣናት ጉዳዩን በሚመለከት ተደጋጋሚ ሙከራ ቢያደርግም ምላሽ ማግኘት አልቻለም።

ፖለቲከኛው ጃዋር መሐመድ በኬንያ መዲና ናይሮቢ ዛሬ ሐሙስ ታሕሳስ 10 2017 ዓ.ም. ሊካሄድ የነበረው የመፅሐፍ ምርቃት ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙን በይፋዊ የፌስቡክ ገጹ አስታውቋል ሲል ቢቢሲ አማርኛ ነው የዘገበው።

https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
ኢትዮ መረጃ - NEWS
Photo
የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለሃይማኖት ትንቢት ሊፈጸም ነው ????


በኢትዮጵያዊው ጻድቅ በብጹዕ አቡነ ተክለሃይማኖት በ12ኛው ክፍለ ዘመን መጨረሻ በ13ኛው ክፍለዘመን መጀመሪያ በወላይታ ሀገረ ስብከት በሶዶ ከ800 ዓመት በላይ ያስቆጠረውን  ደብረ መንክራት አቡነ ተክለሃይማኖት ገዳምን ገደሙ ።


ይህ ገዳም የጻድቁ አባታችን ተክለሃይማኖት   ቤተ ጣዖትን ቤተ መቅደስን ያሰሩበትን ንጉስ ሞቶሎሚን ከነ ሰራዊቱ ያጠመቁበት መስዋዕት መስቀል ሜሮን  ለአገልግሎት የሚያስፈልጉ ንዋያተ ቅድሳት መላእክት ከሰማይ ወርደው በካህናትና በዲያቆናት ፈንታ ከጻድቁ አባታችን ተክለሃይማኖት እንደ12ቱቅዱሳንሃዋርያትከእግዚአብሔር እጅ ጱጱስና የተሾሙበት
ወንጌልን እያስተማሩ ማታ በቆሙበት ሳይቀመጡ ከዘረጉ ሳይጥፉ እየጸለዩ እየሰገዱ የኖሩ በአታቸውን ነው።


እንዲሁም ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን 3ኛ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለሃይማኖት /ለአባ መላኩ በፈቃደ እግዚአብሔር ለፓትርያርክነት ከመመረጣቸው አስቀድሞ 42 አመታት እየጹሙ እየጸለዩ ወንጌልን እያስተማሩ የኖሩበት ገዳም ነው ።


ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለሃይማኖት አባ መላኩ ፓትርያርክ ከሆኑ  በኋላ 12 ብፁዓን አባቶችን አስከትለው ግንቦት 13/1980 ለገዳሙ አዲስ ግንባታ የመሰረተ ድንጋይ አኑረዋል ብፁዕ አባታች በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ ምዕመናንን ወደ ቅዱስነታቸው ቀርበው በአጭር ጊዜ ውስጥ ገንብተው ህንጻውን ለመፈጸም  ቅዱስነታቸውን ቢማጸኑም ይህ አሁን የሚሆን አይደለም ገና በእናታቸው ማህጸን ውሀ ሆነው ያሉ  ያልተወለዱ ህጻናትን ጨምሮ ኢትዮጵዊያን ልጆቼ ይሰራሉ ብለው ትንቢት ተናገሩ ።


ይህ ዛሬ የብፁዕነታቸውን ትንቢት ደርሶ የህንጻውን ግንባታ ሊያልቅ ከጫፍ የደረሰ ሲሆን በብፁዕ አቡነ ይስሐቅ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የወላይታ ሶዶ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የቅዱስ ሲኖዶስ ቋሚ አባል መልካም ፍቃድ ህንጻ መሰረት በተጣለበት በግንቦት 24 /2017 ዓ/ም ለማስመረቅ ቀን ተቆርጦ ቀሪ ስራዎችንን በማጠናቀቅ ላይ ይገኛል ህንጻውን ለመፈጸም በባለሞያ የተጠና ሲሆን አጠቃላይ ወጪ 49 ሚሊዮን ነው ስለሆነም በሀገር ውስጥና በሀገር ውጪ ያላችሁ የተዋሕዶ ልጆች በሙሉ የብፁዕ አባታችን አቡነ ይስሀቅን አባታዊ ጥሪ ተቀብላችሁ ይህንን ታሪካዊ ህንጻ ቤተክርስቲያን ከፍፃሜ እንዲደርስእጃችሁን እንድተዘረጉልን ስንል በጻድቁ አቡነ ተክለሀይማኖት ስም እንማጸናለን

አሐዱ ባንክ:-
0010183311801

ንግድ ባንክ:-
1000018099067

  እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ
ሊባኖስ የእስራኤል ጦር በየቀኑ የተኩስ አቁም ስምምነቱን እየጣሰ ነዉ አለች

የሊባኖሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናጂብ ሚካቲ እስራኤል የገባችዉን ስምምነት አልፎ አልፎ እየጣሰች ነዉ ሲሉ ወቅሰዋል፡፡

ከተርክየዉ ፕሬዝዳንት ጋር መግለጫ የሰጡት ሚካቲ ስምምነቱ ከተደረሰ 3 ሳምንት ቢቆጠርም አሁንም ግን በእስራኤል በኩል ሲጣስ እየተመለከትን ነዉ ብለዋል፡፡

የእስራኤል ጦር ከሊባኖስ ምድር ሙሉ በሙሉ መዉጣት እንዳለበትም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡

ቴል አቪቭ የተኩስ አቁም ስምምነቱን እንድታቆምም ጠይቀዋል፡፡

በሊባኖስ ተቀስቅሶ የነበረዉን የእስራኤል ሄዝቦላ ጦርነት ለማስቆም የ60 ቀናት የተኩስ አቁም ስመምነት ላይ መደረሱ የሚታወስ ነዉ፡፡

https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
የሽርካ ኦርቶዶክሳውያን ግድያ እንደቀጠለ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ገለጹ፡፡

በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት ሽርካ ወረዳ ታኅሣሥ 5 እና 6 ቀን 2017 ዓ.ም የወረዳ ቤተ ክህነቱን ሥራ አስኪያጅ ጨምሮ 20 ኦርቶዶክሳውያን በታጣቂዎች ግድያና እገታ እንደተፈጸመባቸው ነዋሪዎቹ ለማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ገልጸዋል፡፡

ከታገቱት ውስጥም የወረዳው ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅና ሌሎች 8 ኦርቶዶክሳውያን ገንዘብ ከፍለው የተለቀቁ ሲሆን ቁጥራቸው ያልታወቁ ሰዎች ግድያ እንደተፈጸመባቸው እንዲሁም ያሉበት እንደማይታወቅ ተሰምቷል፡፡

https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
መረጃ‼️

በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ግራር ጃርሶ ወረዳ የኢላሙ ቀበሌ አሥተዳዳሪ ክፍያለው ነጋሽ አማጺው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ትናንት በቢሯቸው አካባቢ በፈጸመው ጥቃት መገደላቸውን ዋዜማ ሰምታለች።

ከአሥተዳዳሪው ጋር የነበሩ በርካታ የጸጥታ ኃይል አባላት ቆስለው ለሕክምና ወደ ፍቼ ሆስፒታል መወሰዳቸውን የዓይን እማኞች አረጋግጠዋል።

በተመሳሳይ በደገም ወረዳ ሐምቢሶ ከተማ አማጺ ቡድኑ ትናንት ሌሊት በፈጸመው ጥቃት አንድ የሚሊሻ አባል ሕይወቱ ሲያልፍ፣ ሌሎች በርካቶች ታፍነው መወሰዳቸውን ዋዜማ ተረድታለች።

በገርበ ጉራቻ ወረዳ ኩዩ ከተማም በተመሳሳይ ሰዓት ቡድኑ የአፈና ድርጊት መፈጸሙን ዋዜማ ተረድታለች።

ቡድኑ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በዞኑ የተለያዩ አካባቢዎች በመንግሥት ኃላፊዎች ላይ ያነጣጠረ ግድያና ጥቃት በማድረስ ላይ ይገኛል።

@Sheger_press
@Sheger_press
የአባቶች ስቃይ

#ከራሱ ቆዳ የተሰራውን ስልቻ አሸዋ ሞልተው አሸከሙት


ከ12ቱ ቅዱሳን ሐዋርያት አንዱ ቅዱስ ቶማስ በተጣራራሪነቱ ይታወቃል፡፡

በቀዳሚ ስሙ ‘ዲዲሞስ’ ወይም ጨለማ ሲባል የነበረ ቢሆንም በኋላ ግን ቶማስ ወይም ፀሐይ ተብሏል፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ከተነሣ በኋላ በ8ኛው ቀን እሁድ ነው ያየው፡፡

እናም በጦር የተወጋ ጐኑን ዳስሶ ማረጋገጥ በመፈለጉ ዳሶ ሲያውቅ ግን ጌታዬ አምላኬ ያለ ነው፡፡ እመቤታችን ስታርግም ከሁሉም ቀድሞ ያየው  ነው፡፡

ወደ ሀገረ ስብከቱ ሕንድ የገባው እንደ ባሪያ በ30 ብር ተሽጦ ነበር፡፡ የገባበት አካባቢ አስተዳዳሪ ሉክዮስ አሳዳሪው ሆኖ በቤቱ ሲያገለግል ምን መሥራት እንደሚችል ሲጠይቀው ሕንፃ ማነጽ ሐውልት መቅረጽ እንደሚችል ስለነገረው ብዙ ወርቅና ብር ሰጥቶ ሰርቶ እንዲጠብቀው ነግሮት የተለየ ጥበብኛ ሰው አገኘሁ ለማለት ወደ ንጉሥ ሄደ፡፡


ቅዱስ ቶማስ ግን ገንዘቡን ለነዳያን መጸወተው በርካቶችንም አስተምሮ አሳምኗቸዋል፡፡ የሉክዮስ ሚስትና ልጆቿ ቤቱ ካሉ አገልጋዮች ጋር ሁሉ አምነው ተጠምቀዋል፡፡

ሉክዮስ ከሄደበት ተመልሶ ሕንጻውንና ሐውልቶቹን ለማየት ቢፈልግም ሐዋርያው በወርቅና በብርህ ያነጽኳቸው ሕንጻዎች እኒህ ናቸው ብሎ ያመኑትን አገልጋዮች አሳየው፡፡ ይህ ክፉ ባሪያ ተጫወተብኝ ብሎ እጅ እግሩን አሥሮ ቆዳውን አስገፍፎ ስልቻ አስፍቶ በአሸዋ መልቶ አሸክሞ በገበያው ሲያዞረው ሚስቱ አርሶንዋ አይታ በድንጋጤ ወድቃ ሞተች፡፡

መስፍኑም ደንግጦ ሚስቴን ካዳንካት እኔም በአምላክህ አምናለሁ አለው፡፡ ጌታ ቁስሉን እንደ ውኃ አቀዝቅዞለት ካለችበት ሄዶ ስልቻውን ቢያስነካት ተነሥታለች በዚህም ሉክዮስ አምኖ ተጠምቋል፡፡

ከዚህም በኋላ ስልቻውን ተሸክሞ ከቦታ ወደ ቦታ እየተዘዋወረ ሙት እያነሣ ድውይ እየፈወሰ አሕዛብን አሳምኖ አጠመቀ፡፡

በቀንጦፍያ የተገደሉ የአንድ ሽማግሌ ሰባት ልጆች ስልቻውን እያስነካ አስነሥቶለታል፡፡ በኢናስም የቃሉን ትምህርት የእጁን ተአምራት አይተው ከንጉሱ ሚስት ጀምሮ እስከ ተራ ገባር ድረስ ያሉት ሁሉ አምነው ተጠመቁ፡፡ በኋላም የጣኦት ካህናተ በተንኮል ከንጉሥና መኳንንቱ ጋር አጣልተው በሰይፍ አስመትተውታል፡፡

ዛሬም ድረስ ሕንድ ውስጥ በመንበሩ ላይ የጌታችንን የተወጋ ጎኑን የዳሰሰች የቅዱስ ቶማስ ቀኝ ቅድስት እጅ በሕይወት እንዳለች ሆና ትታያለች፡፡ በሕንድ ኦርቶዶክስ ቤ/ክ ፓትርያርክ ሲሾሙም የቅዱስ ቶማስን ቀኝ እጅ በሚሾመው ፓትርያርክ ላይ ጭነው ነው፡፡

ገዳማውያን እናቶችና አባቶች በብዙ ስጋዊ መከራ ውስጥ እንኳን አልፈው በእምነታቸው ጸንተው የክርስቶስን ወንጌል በሕይወታቸው ሰብከው፣ ወንጌልን ኖረው ነው የሚያልፉት፡፡ ታዲያ ገዳማቸውን ስንደግፍ፣ በዓታቸውን ስናጸና የእነርሱን በረከት እንታደላለን፡፡


ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም


ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444


የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444
2024/12/26 06:04:55
Back to Top
HTML Embed Code: