Telegram Web Link
የኮሪደር ልማት የፍራስራሽ ግምትን ለግል ጥቅማቸው ለማዋል የሞከሩ አመራሮች በቁጥጥር ስር ዋሉ


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እያካሄደው ባለው የኮሪደር ልማት ሥራ ከተማዋን የሚመጥኑ ሰፋፊ የመንገድ መሠረት ልማቶችን እና ግዙፍ ተሻጋሪ ፕሮጀክቶችን በመገንባት ላይ መሆኑን ባወጣው መግለጫ አንስቷል።

በተለይ በየካ ክፍለ ከተማ በካዛንችስ የኮሪደር ልማት ሥራ መንግሥትና ህዝብ የጣለባቸውን ኃላፊነት ወደ ጎን በመተው ከልማቱ ፍራስራ ላይ ለግል ጥቅማቸው ሊያውሉ የነበሩ የወረዳ 06 አመራሮች አስተዳደሩ በዘረጋው የህዝብ ቀጥተኛ ተሳትፎ በትናንትናው ዕለት በፀጥታ አካላት በቁጥጥር ስር በማዋል ሌብነት የልማቱ እንቅፋት እንዳይሆን ተገቢውን እርምጃ መውሰዱን አስተዳደሩ አስታውቋል።

በዚሁ መሠረት በየካ ክፍለ ከተማ የወረዳ 06 ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ራሄል ኃ/ኢየሱስ፣ የወረዳው ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደበበ ጉልማ፣ የወረዳው የፋይናስ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ታደለ ግዛቸው በቁጥጥር ስር ውለዋል ብሏል መግለጫው።

ግለሰቦቹ የኮሪደር ልማትን መነሻ አድርገው የፍራስራሽ ግምትን ለግል ጥቅማቸው ለማዋል በመሞከር ላይ እያሉ የከተማዋ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ እስከ ክፍለ ከተማ ያለውን መዋቅሩን በመጠቀምና ክትትል በማድረግ ተጠርጣሪዎቹን በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ማድረጉን ገልጿል።

የወንጀል ማጣራት ሥራው በሚመለከተው አካል እየተካሄደ መሆኑን የጠቀሰው መግለጫው፥ ሌብነትን እና ብልሹ አሰራርን ለማስቀረት የሚደረገው ትግል ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቁሞ፤ ህብረተሰቡም ጥቆማ በመስጠት የሚያደርገውን ትብብር አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርቧል።

https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
በአዲስ አበባ በስድስት ክፍለ ከተሞች የሥምና ንብረት ዝውውር ታገደ!

በአዲስ አበባ ከተማ ለመሬት ይዞታ ማረጋገጥ ሥራ ሲባል ለቀጣይ 5 ወራት በስድስት ክፍለ ከተሞች እና በተመረጡ ወረዳዎች የሥምና ንብረት ዝውውር መታገዱን የከተማዋ መሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጄንሲ አስታውቋል።ኤጄንሲው ከመሬት ይዞታ ጋር ተያይዞ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የገለጸ ሲሆን፤ ለዚህም ዘመናዊ ሁለገብ ካዳስተር ግንባታ ስርዓት በመዲናዋ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ለማድረግ ሥራ መጀመሩን አመልክቷል፡፡

አሁን ላይ ከአዲስ አበባ ጠቅላላ የቆዳ ስፋት ውስጥ 54 በመቶ ለሚሆነው የመሬት ይዞታ ማረጋገጥ ሥራ መሰራቱን ገልጿል።በተያዘው በጀት ዓመት ለመጨረሻ ጊዜ በ136 ቀጠናዎች የሚገኙ ይዞታዎችን አረጋግጦ ለመመዝገብ እየተሰራ መሆኑንም አመላክቷል።በዚህ መሠረትም የይዞታ ማረጋገጥ ሥራው በተመረጡ ስድስት ክፍለ ከተሞች በቀጣይ አምስት ወራት ውስጥ እንደሚከናወን ተጠቅሷል።

ክፍለ ከተሞችም የካ፣ ለሚ ኩራ፣ አቃቂ ቃሊቲ፣ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ፣ቦሌ እና ኮልፌ ቀራኒዮ መሆናቸው ተገልጿል።ለመሬት ይዞታ ማረጋገጥ ሥራው ሲባልም ምዝባ በሚካሄድባቸው የክ/ከተሞቹ ወረዳዎች እስከ ቀጣዩ ሚያዝያ ወር ድረስ የሥምና ንብረት ዝውውር መታገዱ ተገልጿል።ባለይዞታዎች ከታሕሣሥ 20 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 ቀናት የይዞታ ይረጋገጥልኝ ማመልከቻ እንዲያቀርቡም ጥሪ ቀርቧል።

Via Ahadu

https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የበርካታ ገዳማት ባለቤት ነች፡፡


በፈቃደ እግዚአብሔር ከ5ተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ጀምሮ በመላው ሀገሪቱ እየተስፋፉና እያደጉ የመጡት እነዚሁ ገዳማት የምናኔና የጸሎት እንዲሁም ድኀነተ ሥጋ ወነፍስ የሚገኝባቸው ቦታዎች ናቸው፡፡ ለቤተ ክርስቲያናችን ዘርፈ ብዙ አገልግሎት ከመስጠት ጎን ለጎን የሊቃውንት መፍለቂያና የበርካታ ቅዱሳን ምንጭ በመሆንም ሲያገለግሉ እንደኖሩ ይታወቃል፡፡


በሀገሪቱ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኀበራዊ እንቅስቃሴዎች ውስጥ አዎንታዊ ተፅዕኖ ከመፍጠራቸውም በላይ የሀገሪቱ የትምህርትና የሥልጣኔ ማእከላት በመሆን አገልግለዋል ፡፡ ገዳማት የቤተክርስቲያን ስውር ጓዳዎችና የሚስጥር መዝገቦች ናቸው ፤ ገዳማት የመማፀኛ ከተማ ናቸው ፤ ገዳማውያን ለእግዚአብሄር የሚቀርቡ አስራት በኩራት ናቸው ።

ይህ በዚህ እንዳለ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ገዳማት በተለያዩ አዝማናት በሀገሪቱና በቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ በደረሱ ውጪያዊና ውስጣዊ የጥፋት ዘመቻዎች ቀጥተኛ ተጠቂዎችም ነበሩ፡፡ ተፈጥሮአዊ በሆኑ ችግሮችም እንደየአካባቢው መልክአ ምድራዊ አቀማመጥ ተጋላጭ ሆነው ኖረዋል፡፡

አጽራረ ቤተ ክርስቲያንም በየጊዜው በተለያየ ስልት የገዳማውያኑን አኗኗር፣ ሥርዓትና ትውፊት ለመበረዝ ሲንቀሳቀሱና ገዳማቱን ሲዋጉ እንደኖሩ ግልጽ ነው፡፡


በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ምስራቅ በለሳ ወረዳ የሚገኘው ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም ከዘጠና በላይ ገዳማውያን መነኮሳት ያሉበት ልዩ ስፍራ ነው፡፡

ከዓለት መሀል በመነኮሳት ፀሎት ብቻ በሚቆረጥ የማር እምነትና ድውያንን የሚፈውስ ድንቅ ጸበል ያለበት፤ ስለ ዓለምና ስለ ሀገራችን ሌት ተቀን የሚጸልዩበት ቅዱስ ስፍራ ነው፡፡ በተደጋጋሚ ባደረግነው ጥሪ መሠረትም የዘረጋችሁት እጃችሁ ድንቅ ነገር ሰርቷል፡፡ የእናት ገዳማውያን መኖሪያ ባማረና በዘመነ ሁኔታ ተሰርቶ፣ የሶላር ኃይል ተገጥሞለት ጭምር ተጠናቋል፡፡


ለዚህም ባወጣችሁት አብዝቶ ይተካ፣ በዘረጋችሁት እጅ ማለቂያ የሌለው በረከት ያሳፍሳችሁ ለማለት እንወዳለን ፤ አመስጋኝ ልብ የአንድ አማኝ ቀዳሚ መለያ ባህሪ ነውና በመልዓኩ በቅዱስ ሚካኤል ስም ከልብ እናመሰግናለን ፡፡ አሁን እየተሰሩ ካሉ ስራዎች አኳያ ገዳሙ የሚያስፈልገውን ያህል ባይሆንም " ጋን በጠጠር ይደገፋል " እንዲሉ የተቻለውን አገልግሎት ለመስጠት ጥረት ሲደረግ ቆይቷል  አሁንም ይህ ልግስናችሁ ተጠናክሮ ይቀጥል፡፡


አንድ ትልቅ ምዕራፍ ብንጓዝም ለመስራት ከታሰበው ግማሽ ያህል እንኳ አልተጠናቀቀምና ገዳማውያኑ ልገሳችሁን ይሻሉ፡፡ ከላይ እንዳልነው ገዳማውያን ለእግዚአብሄር የሚቀርቡ አስራት በኩራት ናቸውና አሁንም ከጎናቸው በመቆም አለን እንበላቸው ፡፡  

ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም


ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444


የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444
ትራምፕ የፓናማ ቦይን መልሰን ልንቆጣጠር እንችላለን ሲሉ ዛቱ

ትራምፕ ይህን ያሉት የፓናማ መንግስት በቦዩ በሚያልፉ መርከቦቻችን ላይ የበዛ ክፍያ እያስከፈለን ነው በሚል መሆኑ ተገልጿል።

“በባሕር ኃይላችንና ንግዳችን ላይ ከፍተኛ ኢፍትሃዊነት ተፈጽሞበታል፤ የፓናማ መንግስት የሚያስከፍለን ክፍያ የበዛ ነው” ሲሉም ተናግረዋል ተመራጩ ፕሬዚዳንት።

ይህ በአሜሪካ ላይ እየተደረገ ያለው የለየለት ዘረፋ በአስቸኳይ መቆም አለበት ያሉት ፕሬዚዳንቱ ጠንከር ባሉ ቃላትም አስጠንቅቀዋል።

አሜሪካ የፓናማ ቦይን በፈረንጆቹ 1914 ገንብታ ለበርካታ አስርት ዓመታት ስታስተዳደር የቆየች ሲሆን÷በ1999 ደግሞ ለፓናማ መንግስት ማስረከቧ ይታወሳል፡፡

በተያያዘም ዶናልድ ትራፕም ቻይና በአካባቢውና በፓናማ ቦይ አካባቢ ተፅዕኖዋ እያደገ መሆኑን ጠቁመው÷ “ ቦዩን ፓናማ ብቻ ነበር ማስተዳደር ያለባት፤ ቻይና ወይም ሌላ አይደለም ብለዋል።

ቦዩ በፍጹም በማይመለከተው አካል እጅ እንዲወድቅ አንፈቅድም” ሲሉም አጽንኦት ሰጥተዋል።

ትራምፕ “የሥነ ምግባር እና የሕግ መርሆች ካልተከበሩ የፓናማ ቦይ ሙሉ በሙሉ እና ያለጥያቄ እንዲመለስልን እንጠይቃለን” ማለታቸውን አልጃዚራ ዘግቧል።

የፓናማ ፕሬዚዳንት ሁሴ ራውል ሙሊኖ በበኩላቸው÷ የትራምፕን ማስፈራሪያ ተቀባይነት የሌለው ሲሉ አጣጥለውታል።

https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
ከቦታና ከቤት ግብር ገቢ 1.98 ቢሊዮን ብር መሰብሰቡን የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ አስታወቀ

👉 ክፍያ እስከ የካቲት 30 ቀን መፈፀም ይኖርበታል

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ  የቦታና የቤት ግብር የመክፈያ ጊዜ በበጀት  ዓመቱ እስከ የካቲት 30 ቀን 2017 ዓ.ም መሆኑን አሳስቧል።

ቢሮው  በ2017 በጀት ዓመት 5 ወራት ከቦታና ከቤት ግብር ለመሰብሰብ ከታቀደው ገቢ 1.98 ቢሊዮን ብር  መሰብሰቡን በቢሮው የግብር አወሳሰን ድጋፍ ክትትል ቡድን አስተባባሪ አቶ ኸይሩ ሁሴን ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።

የቦታና የቤት ግብር አዋጅ ቁጥር 80/1968 መሰረት ማንኛውም ባለይዞታ የቤትና የቦታ ግብር እንዲከፍል የሚደነግግ ሲሆን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ ሚያዚያ 2015 ዓ.ም በተደረገ የክፍያ ማሻሻያ መሰረት ግብሩ እየተሰበሰበ መሆኑን አስታውቋል ።

በአዋጁ በተቀመጠው መሠረት የቦታና የቤት ግብር የመክፈያ ጊዜ በበጀት  ዓመቱ እስከ የካቲት 30 ቀን 2017 ዓ.ም መሆኑን የጠቀሱት  አቶ ኸይሩ የይዞታ ባለቤቶች መጨረሻ ከሚፈጠር መጨናነቅና ቅጣት ለመዳን የሚጠበቅባቸውን ትክክለኛውን የቦታና የቤት ግብር ከወዲሁ መክፈል እንደሚገባቸው አሳስበዋል ።

በቢሮው በበጀት ዓመቱ 5 ወራት ከቤትና ከቦታ ግብር 2 ነጥብ 72 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ 1 ነጥብ 98 ቢሊዮን ብር  ወይም የዕቅዱን 73ነ ጥብ 25 በመቶኛ ተሰብስቧል።

ቢሮው መረጃዎችን በማጥራት ከዚህ በፊት ተለክተው ክፍተት ያለባቸውን ይዞታዎች በድጋሚ የመለካትና ከዚህ በፊት ያልተካተቱትን ደግሞ  ልኬት በመስራት  ወደ ግብር ስርአት እያስገባ መሆኑ ተገልጿል።

በበጀት ዓመቱ ቢሮው ከቦታና ከቤት ግብር በአጠቃላይ 8 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር ሊሰበሰብ እንደታቀደ ተጠቁሟል።

https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
የኦሮሚያ ክልል የምክክር ተሳታፊዎች፣ አዲስ አበባ፣ ሐረርና ሞያሌ ከተሞች በኦሮሚያ ክልል ሥር እንዲተዳደሩ ለአገራዊ ምክክር ኮሚሽን አጀንዳ ማቅረባቸውን ከተሳታፊዎቹ መስማቱን ጠቅሶ ሪፖርተር ዘግቧል።

አዲስ አበባ በሕገመንግሥቱ መሠረት በፌደራል መንግሥቱ ሥር የምትተዳደር ሲኾን፣ ሐረር ደሞ የሐረሬ ክልል ዋና ከተማ ናት።

ባንጻሩ በሱማሌና ኦሮሚያ ክልሎች መካከል ለዓመታት የግጭት ማዕከል የነበረችው ሞያሌ፣ ባኹኑ ወቅት ከኹለት ተከፍላ የኹለቱም ክልሎች ባንዲራዎች እንደሚውለበለቡባት ይታወቃል።

የክልሉ የምክክር ተሳታፊዎቹ፣ በክልሎች የወሰን አከላለል፣ ኦሮምኛን የፌደራል የሥራ ቋንቋ በማድረግና ኹሉንም ብሄረሰቦች የሚያግባባ ብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ እንዲኖር በማድረግ ዙሪያ አጀንዳዎችን ማቅረባቸውንም መናገራቸውን ዘገባው ጠቅሷል።

ባንጻሩ፣ በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 39 የተቀመጠው የመገንጠል መብት ባለበት እንዲቀጥል ተሳታፊዎቹ አጀንዳ አቅርበዋል ተብሏል።(wazema)

@Sheger_press
@Sheger_press
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሃድያ ዞን ጊቤ ወረዳ በሚገኙ 12 ቀበሌዎች ካለፈው ዓመት ጀምሮ በመንግሥት ሥር እየተዳደሩ እንዳልኾነ ዋዜማ ከነዋሪዎች ሰምታለች።

መንግሥት በ12ቱ ቀበሌዎች የ2016 በጀት ዓመት ግብር አለመሰብሰቡንና የፖሊስ መዋቅሩ መደበኛ የጸጥታ ማስከበር ሥራውን እንደማያከናውን ዋዜማ ተረድታለች። በቀበሌዎቹ የመንግሥት መዋቅር የፈረሰው፣ ማኅበረሰቡ መንግሥት የወረዳ ጥያቄችን አልተቀበለም በማለት ተቃውሞ ማሰማቱን ተከትሎ እንደኾነ ታውቋል።

በቀበሌዎቹ ውስጥ የሚገኙ መምህራንና የጤና ባለሙያዎች ከደሞዝ ጋር በተያያዘ ያነሱት ጥያቄ ምላሽ ባለማግኘቱ፣ ትምህርት ቤቶች ተዘግተው ነበር፤ የጤና ጣቢያዎች አገልግሎትም ተስተጓጉሎ ነበር ተብሏል።

ከአንድ ወር በፊት ከፌደራል ተቋማት ወደ አካባቢው ለሥራ ተጉዘው የነበሩ ሠራተኞችን የአካባቢው ማኅበረሰብ አስሯቸው እንደነበርም ዋዜማ ተምታለች።

https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
Online ተጨማሪ ገቢ ለማግኘት ምን ልስራ ብላቹ ብትጠይቁ በጣም ብዙ ምርጫዎች አሉ።

ትርፋማ ሊያደርገኝ የሚችለው የትኛው Skill ነው?
የት ሄጄ ልማረው እችላለው?
በአጭር ጊዜስ ወደ ስራ ለመግባት እና ገንዘብ ለመስራት ምንድን ነው ማድረግ ያለብኝ?

እነዚህን ጥያቄዎቻቹን ለመመለስ የፊታችን ታህሳስ 16, 18 እና 20 ነጻ Online Webinar አዘጋጅቼላቹሃለው!

በዚህ Webinar የራሴን ልምድ እንዲሁም በዙሪያየ ያሉ ስኬታማ ሰዎችን ልምድ አምጥቼ እያንዳንዱን ነገር ብትንትን እያደረግን እንመለከታለን

ለመሳተፍ ከእናንተ የሚጠበቀው ኢንቴርኔት እና ስልክ ወይም ላፕቶብ በቂ ነው።
ታህሳስ 16, 18 እና 20, ከምሽቱ 2፡00ሰዓት
በሰሜን ሸዋ ዞን በሴቶችና ህፃናት ላይ ጥቃት ፈፃሚዎችን ከእድር የማባረርና የቀብር ስነ ስርዓት እንዳይከናውንላቸው ተፅዕኖ የመፍጠር ስራ ተጀመረ

በሰሜን ሸዋ ዞን 31 ወረዳዎች ዉስጥ 9 የከተማ  አስተዳደሮች ይገኛሉ።በዞኑ በሴቶችና ህፃናት ላይ የሚደርሰዉ ጥቃት ካለዉ የሰላም እጦት ጋር ተያይዞ ካለፉት አመታት ጋር ሲነፃፀር ቁጥሩ እንደጨመረ ተገልጿል።

በ2016 ዓ.ም 64 ሴቶችና ህፃናት ለፆታዊ ጥቃት ተጋላጭ የሆኑ ሲሆን ከዚህ ዉስጥም 23ቱ ህፃናት ናቸው ።በጥቃቱ ላይ ተሳታፊ የነበሩ ከ31 በላይ ግለሰቦች በህግ ቁጥጥር ስር ይገኛሉ። ጥቃቱን ለመከላከል ከበጎ አድራጎትና መንግስታዊ ድርጅቶች ጋር ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን አስወጋጅ ኮሚቴ በማቋቋም በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን የዞኑ ሴቶችና ህፃናት ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ የሮምነሽ ጋሻዉጠና ከብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን ጋር በነበራቸዉ ቆይታ ገልፀዋል ።

በቅንጅት ከሚሰራባቸዉ ስራዎች መካከል ዋነኛዉ ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራ ሲሆን በሚፈጠረው ግንዛቤ ልክ ግን ጥቃቱን ማስቆም አለመቻሉ ተገልጿል ። ዞኑ ከፖሊስና ፍርድ ቤቶች ጋር በመቀናጀት የምክር ፣የስነ ልቦናና የህክምና አገልግሎት እየሰጠ ሲሆን እንደ ዞን ደብረብርሀን ከተማ ላይ ለሁለቱ ዞኖች የሚያገለግል የሴቶች ማገገሚያ ወይም ማረፊያ ተገንብቷል።

በማገገሚያዉ ዉስጥ ከህክምና እና ስነልቦናዊ ድጋፍ በተጨማሪ ተጠቂዎቹ ለሶስት ወራት የተለያዩ ስልጠናዎችን በመዉሰድ ወደ መደበኛ ህይወታቸዉ እንዲመለሱ ይሰራል።በእምነት ተቋማትና በዕድር ቦታዎችም ላይ ስለጥቃቱ በተሻለ መልኩ ትምህርቶች የሚሰጡ ሲሆን ጥቃቱን የፈፀመ ከእድር እንደሚባረርና የቀብር ስርዓት እንደማይከናወንለት ተፅዕኖ የመፍጠር ስራ ከህግ ጎን ለጎን በስፋት እየተሰራበት ይገኛል።

አሁን ላይ ከፖሊስ ፣ፍርድቤትና ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር የምክክር ሰነድን በመፈራረም ወደ ስራ መግባታቸዉን በቀጣይም በደንብ ወደታች ወርዶ ለመስራት የተቀናጀ ዕቅድ መኖሩን ገልፀዋል ። ስለ ፆታዊ ጥቃት የተለያዩ ስልጠናዎችን የሚሰጡ ድርጅቶች ዞኑ ላይ አስፈላጊ በመሆናቸዉ ፍላጎት ያላቸዉን ድርጅቶች አጋርነት እንደሚሹ ወ/ሮ የሮምነሽ ጨምረዉ ለጣቢያችን ገልጸዋል ።

@Sheger_press
@Sheger_press
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የበርካታ ገዳማት ባለቤት ነች፡፡

በፈቃደ እግዚአብሔር ከ5ተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ጀምሮ በመላው ሀገሪቱ እየተስፋፉና እያደጉ የመጡት እነዚሁ ገዳማት የምናኔና የጸሎት እንዲሁም ድኀነተ ሥጋ ወነፍስ የሚገኝባቸው ቦታዎች ናቸው፡፡

ለቤተ ክርስቲያናችን ዘርፈ ብዙ አገልግሎት ከመስጠት ጎን ለጎን የሊቃውንት መፍለቂያና የበርካታ ቅዱሳን ምንጭ በመሆንም ሲያገለግሉ እንደኖሩ ይታወቃል፡፡


በሀገሪቱ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኀበራዊ እንቅስቃሴዎች ውስጥ አዎንታዊ ተፅዕኖ ከመፍጠራቸውም በላይ የሀገሪቱ የትምህርትና የሥልጣኔ ማእከላት በመሆን አገልግለዋል ፡፡ ገዳማት የቤተክርስቲያን ስውር ጓዳዎችና የሚስጥር መዝገቦች ናቸው ፤ ገዳማት የመማፀኛ ከተማ ናቸው ፤ ገዳማውያን ለእግዚአብሄር የሚቀርቡ አስራት በኩራት ናቸው ።

ይህ በዚህ እንዳለ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ገዳማት በተለያዩ አዝማናት በሀገሪቱና በቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ በደረሱ ውጪያዊና ውስጣዊ የጥፋት ዘመቻዎች ቀጥተኛ ተጠቂዎችም ነበሩ፡፡

ተፈጥሮአዊ በሆኑ ችግሮችም እንደየአካባቢው መልክአ ምድራዊ አቀማመጥ ተጋላጭ ሆነው ኖረዋል፡፡ አጽራረ ቤተ ክርስቲያንም በየጊዜው በተለያየ ስልት የገዳማውያኑን አኗኗር፣ ሥርዓትና ትውፊት ለመበረዝ ሲንቀሳቀሱና ገዳማቱን ሲዋጉ እንደኖሩ ግልጽ ነው፡፡

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ምስራቅ በለሳ ወረዳ የሚገኘው ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም ከዘጠና በላይ ገዳማውያን መነኮሳት ያሉበት ልዩ ስፍራ ነው፡፡ ከዓለት መሀል በመነኮሳት ፀሎት ብቻ በሚቆረጥ የማር እምነትና ድውያንን የሚፈውስ ድንቅ ጸበል ያለበት፤ ስለ ዓለምና ስለ ሀገራችን ሌት ተቀን የሚጸልዩበት ቅዱስ ስፍራ ነው፡፡


በተደጋጋሚ ባደረግነው ጥሪ መሠረትም የዘረጋችሁት እጃችሁ ድንቅ ነገር ሰርቷል፡፡ የእናት ገዳማውያን መኖሪያ ባማረና በዘመነ ሁኔታ ተሰርቶ፣ የሶላር ኃይል ተገጥሞለት ጭምር ተጠናቋል፡፡ ለዚህም ባወጣችሁት አብዝቶ ይተካ፣ በዘረጋችሁት እጅ ማለቂያ የሌለው በረከት ያሳፍሳችሁ ለማለት እንወዳለን ፤ አመስጋኝ ልብ የአንድ አማኝ ቀዳሚ መለያ ባህሪ ነውና በመልዓኩ በቅዱስ ሚካኤል ስም ከልብ እናመሰግናለን ፡፡


አሁን እየተሰሩ ካሉ ስራዎች አኳያ ገዳሙ የሚያስፈልገውን ያህል ባይሆንም " ጋን በጠጠር ይደገፋል " እንዲሉ የተቻለውን አገልግሎት ለመስጠት ጥረት ሲደረግ ቆይቷል  አሁንም ይህ ልግስናችሁ ተጠናክሮ ይቀጥል፡፡ አንድ ትልቅ ምዕራፍ ብንጓዝም ለመስራት ከታሰበው ግማሽ ያህል እንኳ አልተጠናቀቀምና ገዳማውያኑ ልገሳችሁን ይሻሉ፡፡ ከላይ እንዳልነው ገዳማውያን ለእግዚአብሄር የሚቀርቡ አስራት በኩራት ናቸውና አሁንም ከጎናቸው በመቆም አለን እንበላቸው ፡፡  


ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም


ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444


የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444
በቱርክ በደረሰ ፍንዳታ የ12 ሰዎች ሕይወት አለፈ

በሰሜን-ምዕራብ ቱርክ ባሊኬሲር ከተማ በአንድ የጦር መሣሪያ እና ፈንጂ ፋብሪካ ውስጥ በደረሰ ፍንዳታ የ12 ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ በአራት ሰዎች ላይ ጉዳት ደረሰ፡፡

የአዳጋው መንስዔ አለመታወቁን እና ተጨማሪ አደጋ እንዳይከሰት ሁኔታውን መቆጣጠር መቻሉን የቱርክ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር አሊ ዬርሊካያ ተናግረዋል፡፡

አደጋውን ተከትሎ የእሳት አደጋ ቡድንን ጨምሮ የደኅንነት እና የጤና ባለሙያዎች ወደ ስፍራው ማምራታቸውን የገለጹት ደግሞ የባሊኬሲር ከተማ ከንቲባ ኢስማኤል ኡስታኦግሉ ናቸው፡፡

የአደጋውን መንስዔ ለማወቅ ተጨማሪ ምርመራዎች እየተደረጉ ነው ማታቸውን ጠቅሶ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ፍንዳታው ባስከተለው የእሳት ቃጠሎም የፋብሪካው ግማሽ ክፍል መውደሙን ከተንቀሳቃሽ ምስሎች ለማየት ተችሏል፡፡
ይህንን ያውቁ ኖሯል?

በፈስ መፍሳት መሀል ጥቅሙ በጥቂቱ

የደም ግፊትን መቀነስ ፣ የኩላሊት ጥንካሬን ማሻሻል እና የእርጅና ምልክቶችን መቀነስ ከጥቅሞቹ መሀል ይካተታሉ።

https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የስራ አመራር ቦርድ ለአምስት የዩኒቨርሲቲው ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ መስጠቱን አስታውቋል፡፡

በዚህም መሰረት፡-
1. ዶ/ር አለማየሁ ተ/ማሪያም……. በስፔሻል ኒድስ ኤጁኬሽን
2. ዶ/ር አስራት ወርቁ ……………. በጂኦቴክኒክስ ኢንጂነሪንግ
3. ዶ/ር መኮንን እሸቴ ……………. በፕላስቲክ ሰርጀሪ
4. ዶ/ር ሚርጊሳ ካባ ……………… በፐብሊክ ሄልዝ
5. ዶ/ር ተባረክ ልካ ………………. በዴቨሎፕመንት ጂኦግራፊ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ አግኝተዋል።

https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
አንድ የዓለም ባንክ ባለሙያና አንድ የባንኩ አማካሪ፣ ባንኩና ዓለማቀፉ የገንዘብ ድርጅት ባለፈው ሐምሌ ያዘጋጁት የዕዳ ዘላቂነት የትንተና ሰነድ ችግሮች እንዳሉበት በጽሁፍ መግለጣቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።

የዕዳ ትንተና ሰነዱ አገሪቱ የአጭር ጊዜ እና የረጅም ጊዜ ዕዳዎችን የመክፈል ችግሮች እንደገጠሟት የሚያብራራ ሲኾን፣ ኹለቱ ባለሙያዎች ግን የአገሪቱ ችግር በዋነኛነት የአጭር ጊዜ ብድር የመክፈል አቅም ውስንነት ብቻ ነው ማለታቸውን ዘገባው ጠቅሷል።

ባለሙያዎቹ፣ ኢትዮጵያ 1 ቢሊዮን ዶላር የዩሮ ቦንድ ዕዳ የያዙባትን ዓለማቀፍ ኢንቨስተሮች መጠየቅ ያለባት የዕዳ መክፈያ ጊዜው እንዲራዘምላት እንጅ የቦንዱ ዋጋ እንዲቀነስላት መኾን የለበትም ማለታቸውንም ዘገባው አመልክቷል።

የገንዘብ ሚንስትር ደኤታ እዮብ ተካልኝ በበኩላቸው፣ የዓለም ባንክና የዓለማቀፉ ገንዘብ ድርጅት ባለሙያዎች የዕዳ ትንተና ሰነዱን በቅርቡ በድጋሚ ከልሰውት እንደነበርና፣ ኾኖም ግዙፍ ለውጥ እንደሌለ ተናግረዋል ተብሏል።

ዓለማቀፍ ቦንድ ያዦቹ ከመንግሥት ጋር ያላቸው ልዩነት፣ አገሪቱ በትክክል የገጠማት የአጭር ጊዜ ወይስ የረጅም ጊዜ ዕዳ የመክፈል አቅም ውስንነት ነው? የሚለው ጥያቄ እንደኾነ ይታወቃል።

መንግሥት፣ የዕዳ ትንተና ሰነዱን በመንተራስ በቦንዱ ዋጋ ላይ ቅናሽ እንዲያደረግለት መጠየቁና ቦንድ ያዦቹም ጥያቄውን ውድቅ ማድረጋቸው ይታወሳል።

https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
2024/12/25 06:18:57
Back to Top
HTML Embed Code: