Telegram Web Link
ተቃዋሚዎቹ የትግራይ ነጻነት ፓርቲ፣ ባይቶና እና ዓረና ፓርቲ፣ ሕወሓት አዳዲስ ተዋጊዎችን በመመልመልና ነባሮችን በመቀስቀስ ለዳግም ጦርነት እየተዘጋጀ ነው በማለት ትናንት በሰጡት መግለጫ ከሰዋል። ፓርቲዎቹ፣ ሕወሓት በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች በሕዝብ ተመራጭ ሹሞች ላይ ማስፈራሪያ እየፈጸመ ይገኛል በማለትም ወንጅለዋል።

የትግራይ የፖለቲካና የጸጥታ ኃይል አመራሮች በሰሜን ምዕራብና ማዕከላዊ ዞኖች በመርዛማ ኬሚካሎች በመታገዝ ከፍተኛ የወርቅ ማዕድን ዝርፊያ እያካሄዱና የአካባቢ ብክለት እያደረሱ እንደኾነም ፓርቲዎቹ ገልጸዋል።

ፓርቲዎቹ፣ የክልሉን ችግር ለመቅረፍ ኹሉን አካታች የሽግግር አስተዳደር እንዲቋቋም በድጋሚ ጠይቀዋል።

https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
በቅናት በመነሳሳት ባለቤታቸውን እና የባለቤታቸው እህት የገደሉት የ73 ዓመት አዛውንት በእድሜ ልክ እስራት ተቀጡ 

የ73 ዓመት አዛውንት የሆኑት አቶ አህመድ  አደም እና ፋጡማ አህመድ ነዋሪነታቸው በምስራቅ ሀረርጌ ዞን በደኖ ወረዳ ሞጆ ቀበሌ ውስጥ ሲሆን ጥንዶቹ ትዳር  መስርተው ለ35 ዓመታት አብረው በመኖር  አምስት ልጆችን ማፍራት ችለዋል። 

ሁለቱ ጥንዶች  አብረው መኖር በጀመሩባቸው ዓመታት ከዘመዶቻቸው ጋር ተስማምተው  ተከባብረው  ይኖሩ ነበር። ይሁን እና እድሜያቸውን ሙሉ ከኖሩበት ትዳራቸው ላይ የሚያቃርናቸው ነገር ይፈጠራል። የ73  ዓመቱ አደም በባለቤታቸው ላይ መቅናት የጀመሩበት እና በዚህም ያልተገባ ጥርጣሬ እያደረባቸው  በመሆኑ  በተደጋጋሚ  መጋጨት መጀመራቸው  የምስራቅ ሀረርጌ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሳሊም ሱሌማን በተለይም ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል ።

በዚህ ጥርጣሬያቸው የወይዘሮ ፋጡማ ዘመዶች በመጥላት እቤታቸው እንዳይመጡ መከላከል ጀምሯል። የባለቤታቸው ታናሽ እህት የሆነችው ሂንድያ አህመድ  ባለቤቴን ይዛ የምትዞረው እሷ ናት በሚል ጥርጣሬ   ቅራኔ ውስጥ መግባታቸው ተጠቁሟል። ሚያዝያ  9 ቀን 2016 ዓ.ም  ወይዘሮ ፋጡማ  እና ሂንድያ አብረው ቆይተው ወደየቤታቸው ሲገቡ አቶ አህመድ ንዴት ውስጥ በመግባታቸው ወዲያውኑ ጸብ ይጀምራሉ  ። ከዛም በያዙት ስለታም ብረት  በመምታት ከጣሏቸው በኋላ እጃቸውን ከቤት ምሰሶ ጋር በማሰር  እርዳታ  እንዳያገኙ መብራት በማጣፋት  ከውጪ  በር ዘግተው የተጎጂ ታናሽ እህት ጋር በመሄድ እህትሽ ታማለች ጤና ጣቢያ እንውሰዳት በማለት አታለው  ወደራሳቸው ቤት ያመጧታል።

በተመሳሳይ እህቷን በስለታም ብረት መተው በመጣል ሁለቱንም አስረው በተደጋጋሚ በመምታት ህይወታቸው እንዲያልፍ አድርገዋል።ተከሳሹ ድርጊቱን ከፈጸሙ በኋላ ከአካባቢው ለመሰወር የሞከሩ ሲሆን  ነዋሪዎች በመጠራጠር ለአካባቢው የጸጥታ አካላት  በማመልከት ፖሊስ በሩን ከፍቶ ሲገባ ታላቅ እና ታናሽ ሁለቱም ህይወታቸው አልፎ በማግኘቱ ወዲያውኑ ጉዳዩን ማጣራት መጀመሩ ተገልጿል ።ፖሊስም አስከሬኑን በማስመርመር እና ጉዳዩን በማጣራት ላይ እያሉ የ73 ዓመቱ  ግለሰብ እጃቸውን ለፖሊስ  በመስጠት ቃላቸው ይሰጣሉ ።ፖሊስ መዝገቡን ሚያዚያ 30 ቀን 2016 ዓ.ም ለዓቃቢ ህግ  ይልካል  ። ከፖሊስ የቀረበለትን የክስ መዝገብ የተመለከተው ዓቃቢህግ በሁለት ሰዎች ከባድ የግድያ ወንጀል በመፈጸም በሚል ክስ ይመሰርታል።

የምርመራ መዝገቡን የተመለከተው  የምስራቅ  ሀረርጌ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት  ህዳር 26  ቀን 2017 ዓ.ም  በዋለው ችሎት የ73 ዓመት ግለሰብ የወንጀል ሪከርድ የሌለባቸው በመሆኑ እና አድሚያቸው እንደ ክስ ማቅለያ በማድረግ በመጨረሻም  ዓቃቢ ህግ ከጠየቀው  የሞት ቅጣት አንድ ደረጃ ዝቅ በማድረግ በእድሜ ልክ እስራት እንዲቀጡ ውሳኔ የተላለፈባቸው መሆኑን አቶ ሳሊም ሱሌማን ጨምረው ለብስራት  ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን  ተናግረዋል።

https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ይኖሩ የነበሩ የህግ ታራሚዎች ገላን አካባቢ ወደ ተገነባው አዲስ ማረሚያ ቤት ሊዘዋወሩ ነው፡፡

በዚህ ምክንያት ከዛሬ ታህሳስ 8 ቀን 2017 ዓ.ም እስከ ታህሳስ 13 ቀን 2017 ዓ.ም ደረስ የታራሚ ቤተሰብ ጥየቃም ሆነ የቢሮ አገልግሎት እንደማይኑር የፌደራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን አሳውቋል፡፡

የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ሁሉም እንዲያወቀው ሲል በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባሰራጨው መረጃ በአዲስ አበባ የህግ ታራሚዎች ቀደም ብለው ይኖሩበት ከነበረው አሮጌው የቃሊቲ ማረሚያ ማዕከል አዲስ ወደ ተገነባው ገላን አካባቢ ወደ ሚገኘው እና በተለምዶ አባ ሳሙኤል ተብሎ በሚጠራው የቃሊቲ ማረሚያ ማዕከል ከታህሳስ 8 እስከ 13 ቀን 2017 ዓ.ም የማዘዋወር ስራ ይሰራል ብሏል፡፡

በመሆኑም በአዲስ አበባ ቃሊቲ ማረሚያ ማዕከል ይሰጥ የነበረውን የታራሚ ቤተሰብ ጥየቃም ሆነ የቢሮ ስራ አገልግሎት ከታህሳስ 8 እስከ 13 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ተቋርጦ እንደሚቁይ አሳውቋል፡፡

ከዛሬ ታህሳስ 8 ቀን 2017 .ም ጀምሮ የሚቋረጠው አገልግሎት ከታህሳስ 14 ቀን 2017 ዓ.ም ወደ መደበኛ ስራው የሚመለስ በመሆኑ አገልግሎቱ በአዲሱ የቃሊቲ ማረሚያ ማዕከል ገላን አካባቢ በተለምዶ አባ ሳሙኤል ተብሎ በሚጠራው ማዕከል ማግኘት የሚቻል መሆኑን ገልጻል፡፡

https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
🙏🙏🙏❤️❤️❤️

እነሆ የገና ስጦታ

ከተወዳጁ ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ
እዲስ የዝማሬ አልበም

‘’በኃጢአተኛው ድንኳን ቅዱሱ ቆመሃል
ልጄ የት ነው ብለህ እኔን ፈልገኻል’’ በሚለው ዝማሬው የሁላችንንም ሕይወት የዳሰሰው…

አጋጣሚ አይደለም: ምልክቴ ነሽ ድንግል ለሕይወቴ፣ ማርያም ማርያም ልበል:
ይለይብኛል ሚካኤል፣ ምስጠረኛዬ ነሽ …..

ቀኑ ቀርቧልና በትዕግስት ጠብቁ‼️
“የውጭ ባንኮች ወደ ሃገር ውስጥ እንዲገቡ መፍቀድ  የግል ባንኮች ይጥፉ ብሎ የመወሰን ያክል አይደለም ወይ” የምክር ቤቱ አባል ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር)

#የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የባንክ ስራ ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ  እያደረገ ያለው ውይይት አሁንም እንደቀጠለ ነው፡፡

“የንግድ ባንክን አዳ ወደ ህዘቡ ሲዞር ይህንን ታስቦ ነው” ያሉት የመንክር ቤቱ አባል ለግል ባንኮች ግን አቅማቸውን እንዲያደረጁ እንኳን ድጋፍ አልተደረገላቸውም  ተብሏል፡፡

ዶ /ር ደሳለኝ የውጭ ባንኮችን ወደ ሃገር ውስጥ ማስገባት ”የግሉ ባንከ  ይጥፉ ብሎ እንደማሰብ አይቆጠርም ወይ”  ሲሉ ጠይቀዋል፡፡

የውጭ ባንኮች ወደ ሃገር ውስጥ መፈቀዱ አገልግሎቱን ከማሻሻል እና ካፒታል ከማምጣት ጥቅም ቢኖረውም የዝግጅት ማነስ ግን አንዱ ችግር ነው ብለዋል፡፡

በተለየም ሃገር ውስጥ የግል ባንኮች አጭር እድሜ ያስቆጠሩ ናቸው የሚሉት የምክር ቤቱ አባል ለአብነትም ብለው አማራ ባንከ፤ ስንቄ ባንክ እንዲሁም አሃዱን ባንክ አንስተዋል፡፡

በእንዚህ ባንኮች ውስጥ ደግሞ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ አክሲዎኖች በስራቸው እንዳሉ አንስተው  ጉዳዩ አሳሳቢ ነው ብለዋል፡፡

የምክር ቤቱ አባል ከዚህ ባለፈም በምን መልኩስ እንቆጣጠራቸዋልን ሲሉም ጠይቀዋል፡፡

ዶ/ር ደሳለኝ አያይዘውም የውጭ ባንኮች ምን አልባት ቢገቡ ሊያበድሩ የሚችሉት ከፍተኛ አቅም ላላቸው በመሆኑ ይህ ደግሞ አነስተና ገቢ ያላቸው እና ብድር የሚፈልጉትን እንደሚጎዳም ተናግረዋል፡፡›

https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
በሰዓት 130 ዶላር የሚከፈልበት የጀርባ ማከክ ስራ

ሴት ጀርባ አካኪዎችን የያዘው የዓለም የመጀሪያው የጀርባ ማከክ ቴራፒ ስቱዲዮም አገልግሎት እየሰጠ ነው።

በሰዓት 130 የአሜሪካ ዶላር ወይም 16 ሺህ ብር በመክፈል ጀርባ ማሳከክ ይቻላል ይላል ከሰሞኑ ከወደ አሜሪካ የተሰማ ዜና።

በሰዎች ዘንድ ስራ ይሆናል ተብለው የማይታሰቡ ተግራት በተለያዩ ጊዜያት ወደ ስራ ተቀይረው ለሰዎች መተዳደሪያ ገቢ ሲያስገኙ ይሰማል።

ከእነዚህም ውስጥ ለመታቀፍ ወፍራም ሰዎችን በሰዓት ከመከራየት ጀምሮ ተከፍሏቸው አልጋ እስከሚያሞቁ ሰዎች ድረስ ገቢ የሚያስገኙ ያተለመዱ ስራዎች መካከል ተጠቃሽ ናቸው።

ከሰሞኑ ከወደ አሜሪካ የተሰማው ወሬ ደግሞ ባለሙያ ሴቶች የሰዎች ጀርባ በማከክ በሰዓት 130 ዶላር ወይም 16 ሺህ ብር እያገኙ ነው ይለናል።

በዓለማችን የመጀመሪያው ፕሮፌሽናል ጀርባ የማከክ አገልግሎት በ55 ዓመቷ ቶኒ ጆርጅ የተመሰረተ ሲሆን፤ ሙሉ በሙሉ ሴት አካኪዎችን የያዘው የዓለም የመጀሪያው የጀርባ ማከክ ቴራፒ ስቱዲዮም አገልግሎእ እየሰጠ ነው ተብሏል።

ቶኒ ጆርጅ ስራውን እንዴት እንደጀመረች ስትናገርም “ጀርዬን ሲታከክልኝ በጣም ነው የሚያሰደስተኝ፤ ይህ ነገር ሌሎች ሰዎች እንደሚያሰደስት በመረዳት ወደ ስራ ለመቀየር ወሰንኩ” ትላለች።

የሰዎችን ጀርባ ለማከክ እስከ 3 ኢንች የሚረዝም አርቴፊሻል ጥፈር እንደምትጠቀም የተናገረቸው ጆርጅ፤ የሰዎችን ጀርባ ስታክ በሰዓት እስከ 130 ዶላር እንደምታስከፍል ተናግራለች።

ፕሮፌሽናል ጀርባ አካኪ ሴቶች፤ የደንኛቸውን ጀርባ በጥፍራቸው ጫፍ በቀስታ ከላይ እከ ታች የሚያኩ ሲሆን፤ ይህም ደንበኞቻቸው የጭንቀት ስሜት እንዲለቃቸው በማድረግ ዘና እንዲሉ ይረዳቸዋል ተብሏል።

ቶኒ ጆርጅ ስለ አዲሱ ስራዋ ስትናገርም “በሰዎች ዘንድ ያለው ተቀባይነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል” ብላለች።

ቶኒ ከጀርባ አከካ ባለሙያዎቿ ጋር በመሆን ከደንበኞች በሚቀርብላት ጥሪ መሰረት አገልግሎት ለመስጠት እንደ ኒው ዮርክ፣ ሎስ አንጀለስ እና ፊላዴልፊያ ያሉ ትላልቅ የአሜሪካ ከተሞች እንደመትሄድም ተናግራለች።

አል አይን ነው የዘገበው።

https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
#ግማሽ ክፍለ ዘመን እንቅልፍ ያላዩ ዓይኖች

ስምንት መቶ ሰባት ዓመታትን ወደኋላ ስንመለስ “ወላዴ አእላፍ ቅዱሳን” “የአእላፍ ቅዱሳን አባት” በመባል የሚታወቁት ታላቁ ጻድቅ የተወለዱበት ዓመት 1210 ዓ.ም ላይ እንገኛለን፡፡ ጎንደር ስማዳ ዳሕና ሚካኤል የተወለዱት አባት ገና በጉብዝናቸው ወራት በ30 ዓመታቸው ዓለምና አምሮቷን ንቀው ወደ ትግራይ “ደብረ ዳህምሞ” የአባታችን አቡነ አረጋዊ ገዳም ደብረ ዳሞ በመግባት ከጻድቁ አምስተኛ የቆብ ልጅ አባ ዮሐኒ ካልዕ ደቀ መዝሙር ሆኑ፡፡ በደብረ ዳሞም ቀኑን ለመነኮሳት በመታዘዝ፣ በመፍጨትና ውሃ በመቅዳት ሌሊቱን ደግሞ እኩሉን በጸሎት እኩሉን ቅዱሳት መጻሕፍትን በመገልበጥ ያሳልፉት ነበር፡፡ ከሰባት ዓመታት ተጋድሎ በኋላም በ37 ዓመታቸው ምንኩስና ተሰጣቸው፡፡

በዚው ዓመትም መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ብዙ ተአምራትና አገልግሎት የምትሰራበት ስፍራ እግዚአብሔር አዘጋጅቶልሀልና ወደ ወሎ ሐይቅ ሒድ አላቸው፡፡ ምንም እንኳን ደብረ ዳሞና ሐይቅ እስጢፋኖስ እጅግ የተራራቁ ቢሆኑም መልአኩ ነጥቆ የተፈቀደላቸው ስፍራ ላይ አደረሳቸው፡፡ በዚም ለሰባት ዓመታት ከሐይቁ በስተሰሜን በሚገኘው የጴጥሮስ ወጳውሎስ ገዳም በማስተማርና በማገልገል ስራቸውን ጀመሩ፡፡ በእነዚህ ዓመታት ሌሊቱን በሐይቁ ውስጥ ገብተው በመጸለይ ያሰዳልፉ ነበር፡፡ በኋላም ቅድስናቸውን የተመለከቱ አበው በብዙ ትግል አበምኔት አደርገው ሾሟቸው፡፡ ይህም የታላቁ ስራቸው መጀመሪያ ሆነ፡፡

አባታችን አቡነ ኢየሱስ ሞአ ከደሴ ከተማ በ30 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው ሐይቅ እስጢፋኖስ ገዳም 800 ደቀ መዛሙርትን በመሰብሰብና በማስተማር ዮዲት ጉዲት ለ40 ዓመታት ያፈረሰቻትን ቤተ ክርስቲያን ይገነቡ ጀመር፡፡ ታላላቅ መጻሕፍትን በማሰባሰብ የመገልበጥና የማባዛት ስራ ያሰሩ ሲሆን ደቀ መዛሙርቶቻቸውንም በማስተማር በመላው ሀገሪቱ ለሐዋርያዊ አገልግሎት አሰማርተው ቃለ እግዚአብሔር እንዲስፋፋ፣ ትምህርት ወንጌል እንዲሰርጽ አድርገዋል፡፡ ለ45 ዓመታት በዘለቀው የገዳሙ አበምኔትነት አገልግሎታቸው አይናቸው ከእንቅልፍ ጋር ተገናኝቶ እንደማያውቅ ገድላቸው ያስረዳል፡፡ እግዚአብሔር አምላክም ይህን ተጋድሏቸውን ለፍሬ አድርጎላቸው ታላላቅ ጻድቃን አባቶችን አፍርተዋል፡፡

ከእነዚህም መካከል የደብረ ሊባኖስ ኢትዮጵያዊው ሐዋርያ አቡነ ተክለ ሃይማኖት፣ አባ ኂሩተ አምላክ ዘጣና ሐይቅ፣ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ፣ አባ ዘኢየሱስ፣ አባ በጸሎተ ሚካኤል፣ አባ አሮን ዘደብረ ዳሬት ጥቂቶች ናቸው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ንጉሱ አፄ ይኩኖ አምላክንም በትምህርተ ሃይማኖት አንጸው ለክብር ያበቋቸው እርሳቸው ናቸው፡፡ የሚያርፉበት ጊዜ ሲደርስም ጌታችን ወርዶ ቃል ኪዳን ሰጥቷቸዋል፡፡ በተወለዱ በ82 ዓመታቸው በ1292 ዓ.ም ሕዳር 26 ቀን ወደ ማያልፈው ክብር ጌታችን ጠርቷቸዋል፡፡ አስገራሚው ነገር አበምኔት ከመሆናቸው በፊት ለሰባት ዓመታት በገዳሙ አስተዳዳሪነት ደግሞ ለ45 ዓመታት በጠቅላላው ለ52 ዓመታት በቆየው ተጋድሏቸው እንቅልፍ የሚባል በአይናቸው አልዞረም፡፡

ገዳማውያን ዓለምንና አምሮቷን ትተው ሲመንኑ የበለጠውን ክብር ሽተው፣ ከአምላካችን ከእግዚአብሔር ጋር ሰፊ ጊዜ ለማሳለፍ ፈልገው እንጂ ተሞኝተው አይደለም፡፡ መስቀሉን ተሸክመው ሲከተሉት ዓለም እንደ ሞኝነት ይቆጥርባቸዋል፡፡ በረከታቸው ግን ምዕተ ዓመታትን ተሻግሮ ድንቅ ይሰራል፡፡ አሁን በዘመናችን ያሉትን ገዳማትና መናንያን ስንደግፍም ይ ቃል ኪዳንና በረከት ከኛ ጋር ይሆናል፡፡            

ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም


ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444


የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444
ቴል አቪቭ በኢራን ሚሳኤል ሩምታ የተናወጠችበት ዜና ከመካከለኛው ምስራቅ ተሰምቷል።

የኢራኑ ሃውቲ የበረታ ክንዱን እስራኤል ላይ ማውረዱን ቀጥሎ ወደ መሃል ቴላቪቭ ረጅም ርቀት ተምዘግዛጊ ሚሳኤል ማስወንጨፉ ተዘግቧል። እንደ ሃውቲ ቃል አቀባይ ያህያ ሳሬ መግለጫ ከሆነ ሃውቲ ቴላቪቭ ጫፍ የሚገኝ የሞሳድ እና የእስራኤል ሚስጥራዊ ወታደራዊ ተቋም ላይ 2 ሃይፐርሶኒክ ሚሳኤል ተለቋቋል።

የተለቀቁት ሚሳኤሎች ፍልስጤም-2 የተባሉት ሃይፐሮኒክ ወይም ፍጡነ ድምጽ መሆናቸውን ያስታወሱት ቃል አቀባዩ ሚሳኤሎች ኢላማቸውን መተዋል ብለዋል።

"የየመን ታጣቂ ሃይሎች የሚሳኤል ወታደሮች በፈጸሙት ልዩ ወታደራዊ ኦፕሬሽን በጃፋ ሰፈር የፍልስጤም-2 ሃይፐርሶኒክ ባሊስቲክ ሚሳኤልን በመጠቀም የጠላት እስራኤል ወታደራዊ ኢላማ ላይ ጥቃት ሰንዝረዋል" ሲል ቃል በቃል የሃውቲ ንብረት የሆነው አል ማሲራህ የቴሌቪዥን ጣቢያ ተናግረዋል።

የእስራኤል መከላከያ ሃይል በትላንትናው እለት በመካከለኛው የሀገሪቱ ክፍል ከየመን ሚሳኤል መተኮስን ተከትሎ በበርካታ አካባቢዎች የሳይረን ድምጽ መሰማቱን አመላክቷል።

https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
ካርድ “አሰራሩን ባለማስተካከሉ” እና “ከዚህ ቀደም የፈጸማቸውን ጥፋቶች ቀጥሎ በመገኘቱ "በሚል ድጋሜ መታገዱ ተነግሯል።

በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን የተጣለበት እገዳ ባለፈው ሳምንት ተነስቶለት የነበረው የመብቶች እና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል (ካርድ) በድጋሚ መታገዱ ተሰምቷል።

የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ቢራቱ ፊርማ ያረፈበት የእግድ ደብዳቤ የተጻፈው በትላንትናው ዕለት ቢሆንም፤ ለካርድ አመራሮች የደረሰው ዛሬ ማክሰኞ ታህሳስ 8/ 2017 መሆኑን ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ ምንጮች ገልጸዋል።

ደብዳቤው ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በካርድ ላይ ባደረገው “የክትትል እና “የግምገማ ስራዎች”፤ ድርጅቱ ፈጽሟቸዋል ያላቸውን “የህግ ጥሰቶች” በመዘርዝር ማስጠንቀቂያ ሰጥቶ እንደነበር አስታውሷል። በዚህ መሰረት ድርጅቱ “በተቋቋመበት ዓላማ መሰረት”፤ “ህጋዊ ሂደትን ጠብቆ እንዲሰራ” “በጥብቅ ማሳሰቡንም” እንደጠቀሰ ኢንሳይደር ዘግቧል።

https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
የአንድ ሳምንት ልጇን አንቃ የገደለችው የ14 ዓመት ታዳጊ እናት በቁጥጥር ስር ዋለች

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በባስኬቶ ዞን ተጠርጣሪዋ የ14 ዓመት ታዳጊ ስትሆን  በላስካ ከተማ 02 ቀበሌ ልዩ ስሙ ባዳይስ መንደር ተብሎ በሚጠራዉ አካባቢ የወንጀል ድርጊቱ ተፈፅሟል።

የክስ ዝርዝሩ እንደሚያስረዳው ተከሳሽ  ሰናይት እንዳለ የተባለችዉ ታዳጊ የባስኬቶ ዞን ኗሪ ስትሆን በቁጥጥር ስር ልትዉል የቻለችዉ ልጇን በመግደልና በመጣል ወንጀል ተጠርጥራ መሆኑን የባስኬቶ ዞን ፖሊስ መምርያ አስታውቋል።

ግለሰቧ የመዉለጃ ጊዜዋ ሲቃረብ ከባስኬቶ ወደ ጅንካ በመሄድ ከቀናት በኋላ በጅንካ ሆስፒታል የወለደች ሲሆን  የሆስፒታሉ ሰራተኞች ብቻዋን መሆኗን አይተዉ ቤተሰብ የለሽም ወይ በማለት ሲጠይቋት ዘመድ የለኝም የሚል ምላሽ በመስጠቷ ሰራተኞቹ ልዩ ድጋፍና ክትትል ቢያደርጉላትም በሶስተኛዉ ቀን ከሆስፒታሉ በማምለጥ ወደ ባስኬቶ መመለሷ ተገልጿል።

በመቀጠልም ተከሳሽዋ የማሽላ እርሻ ዉስጥ ልጇን አንቃ በመግደልና በመጣል ወደ ትዉልድ ስፍራዋ መመለሷን የደቡብ ኢትዮጵያ ፖሊስ ኮሚሽን ህዝብ ግንኙነት እና ገጽታ ግንባታ ዳይሬክተር ኢንስፔክተር አሸናፊ ኃይሌ  ለብስራት ሬዲዮ ቴሌቪዥን ተናግረዋል ።

የእርሻዉ ባለቤቶች ለስራ ወደስፍራዉ ሲመጡ የህፃን ልጅ አስክሬን ማግኘታቸዉን ለፖሊስ በሰጡት ጥቆማ መሰረት ፖሊስ  አስክሬኑን በማንሳት አስፈላጊዉን ምርመራ በማድረግ ከላስካ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ጋር በመተባበር  ስረአተ ቀብር መፈፀሙን ገልጿል።ፖሊስ ተጠርጣሪዋን ለመያዝ ባደረገዉ ክትትል  በባስኬቶ ዞን ቦክቡጫ ቀበሌ በቁጥጥር ስር አዉሎ በምርመራ እያጣራ መሆኑን  ኢንስፔክተር አሸናፊ ኃይሌ ለብስራት ሬዲዮ ቴሌቪዥን ተናግረዋል።

https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ቡግና ወረዳ በድርቅና የምግብ እጥረት ሳቢያ ከ5 ዓመት በታች የኾኑ ሕጻናትን ጨምሮ 10 ሺሕ የሚኾኑ ሰዎች እንደተጎዱ የወረዳው ጤና ጥበቃ ጽሕፈት ቤት መናገሩን ቢቢሲ አማርኛ ዘግቧል።

ወረዳው ከአንድ ዓመት በላይ በፋኖ ታጣቂዎች ቁጥጥር ሥር ይገኛል። የጤና ጽሕፈት ቤቱ ሃላፊዎች ረድኤት ድርጅቶችና መንግሥት ከአዲሱ በጀት ዓመት ወዲህ የተመጣጠነ የሕጻናት ምግብ ግብዓቶችንና መድሃኒቶችን ማቅረብ ማቆማቸውን ገልጧል ተብሏል።

በወረዳው 7 ሺሕ ሕጻናትና ከ3 ሺሕ በላይ ነፍሰ ጡሮች በምግብ እጥረት መግለጡን ዘገባው አመልክቷል።

https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
ኢትዮ መረጃ - NEWS
Photo
ኦርቶዶክሳዊ መንፈሳዊ ጉዞ ወደ ቅዱስ ላሊበላ!

በነፍሳችን ዲያብሎስ ፣ በስጋችን ቄሳር እንዳይነግስ፣ ያለወንድ ዘር በረቂቅ ሚስጥር ከብጽዕት ማርያም የተወለደውን ወልድ እግዚአብሔርን ኑ በምስጋና እናንግሰው።

ንጉሧን ያላወቀች እስራኤል ከምድር ያሳደደችው ፣ በመስቀል ሆኖ "ንጉሥ" የተባለ ፣ በመላእክት የተበሰረ ዜና ልደቱን፣ በያሬዳዊ ዝማሬ በታሪካዊው ቅዱስ ላሊበላ በማክበር በረከተ ነፍስ በረከተ ስጋን እናትርፍ።

ለአረጋውያን ፣  ለነፍሰጡር ፣ ለህፃናት እና ለአካል ጉዳተኞች በጤና ባለሙያዎች ልዩ እንክባቤ እንሰጣለን። ስለማረፊያዎ አያስቡ፤ያሉን ቦታዎች ውስን ናቸውና ፈጥነው በመመዝገብ ቦታ ይያዙ።

የጉዞ መነሻ ቀን:- 24/04/17

የጉዞ መመለሻ ቀን:- 02/05/17

የጉዞ ዋጋ:- ምግብን ፣ ማረፊያን ፣ መስተንግዶን እና አስጎብኚን ጨምሮ :-6,500

ለበለጠ መረጃ:-0938944444

አዘጋጅ:- ማኀበረ ቁስቋም
የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ መንግሥት እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሽርክና ያቋቋሙት የኮንጎ አየር መንገድ ሥራ ጀመረ።

የኮንጎ አየር መንገድ በሁለት ቦይንግ 737 አውሮፕላኖች በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ውስጥ ባሉ ሰባት ኤርፖርቶች በረራ በማድረግ አገልግሎት መጀመሩን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይፋ ያደረገው ትናንት ማክሰኞ ነው።

በኮንጎ አየር መንገድ ውስጥ የኢትዮጵያ አየር መንገድ 49 በመቶ፣ የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ መንግሥት 51 በመቶ ድርሻ አላቸው።

ሁለቱ ሸሪኮች የተፈራረሙት ሥምምነት የአውሮፕላን ኪራይ እና አጠቃላይ ቴክኒካዊ ድጋፍን እንደሚያጠቃልል የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታውቋል።

በስምምነቱ መሠረት የኢትዮጵያ አየር መንገድ የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ዜጎች የአውሮፕላን አብራሪዎች፣ የበረራ አስተናጋጆች፣ የአገልግሎት ሠራተኞች እና የቴክኒክ ባለሙያዎች እንዲሆኑ ያሰለጥናል።
ከተጠርጣሪ ከሞባይል ባንኪግ ዘጠና ስድስት ሺህ ብር ያስተላለፈው የፖሊስ አባል በእስራትና በገንዘብ ተቀጣ፡፡

በካፋ ዞን ፍትህ መምሪያ የሙስና ነክ ወንጀሎች ዐቃቤ ህግ ናትናኤል ክፍሌ ለክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነትና ኮሚንኬሽን እንደገለፁት ተከሳሽ ረዳት ሳጅን ወገኔ ወልዴ በካፋ ዞን የዋቻ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ባልደረባ ሆኖ በሚሰራበት ወቅት የተሰጠውን ኃላፊነትና አደራ ወደጎን በመተው በስራ ተግባር የሚፈፀም የመውሰድና የመሰወር ወንጀል በመፈፀሙና ጥፋተኝነቱ በማስረጃ መረጋገጡን ተናግረዋል፡፡

የዋቻ ከተማ ፖሊስ በምርመራው እንዳረጋገጠው ተከሳሹ የዋቻ ከተማ ፖሊስ ጽ/ቤት በጥበቃ ስራ ላይ እያለ በወንጀል ተጠርጥሮ በፖሊስ ቁጥጥር ከዋለው በላቸው ባህሩ ወደ ማረፊያ ቤት ሲወሰድ ሞባይሉን አስረክቦ ሲገባ ረዳት ሳጅን ወገኔ ከሞባይል ላይ የተመዘገበውን የሞባይል ባንኪግ የሚስጥር ቁጥር በመውሰድ ሚያዝያ 10 ቀን 2016 ዓ.ም ለአንዷአለም ገረመዉ መኩሪያ ወደ ተባለ ግለሰብ ስልክ በመደወል የራስህን የባንክ ሂሳብ ቁጥር ላክልኝና ብር አንተ ጋር ላስቀምጥ እኔ ወደ ግዳጅ ስለሚሄድ በማለት ካሳመነዉ በኋላ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥሩን በመዉሰድ በሞባይል ባንክንግ ከግል ተበዳይ ሂሳብ ቁጥር 96‚000 (ዘጠና ስድስት ሺህ ብር) ገንዘቡን መላኩን ተረጋግጧል፡፡

ተከሳሹ በዚህ አላበቃም ያለው የፖሊስ የምርመራ ግኝት ረዳት ሳጅን ወገኔ በዚሁ ዕለት ከአንዷአለም ገረመው የባንክ ሂሳብ ላይ ወደ እራሱ የባንክ ሂሳብ ቁጥር ስልሳ ሁለት ሺህ ብር እንዲዛወርለት በማድረግ ወደ እራሱ ሂሳብ በማስገባት የተበዳይን 62‚000 ሺህ ብር ከንግድ ባንክ በማወጣት ለግል ጥቅሙ ማዋሉን በምርመራው ያረጋገጠዉ ፖሊስ ቀሪ 34 ሺህ ብር አንዷአለም እንዲመልስ መደረጉን ዐቃቤ ህግ ናትናኤል አስረድተዋል፡፡

በካፋ ዞን ፍትህ መምሪያ የሙስና ነክ ወንጀሎች ዐቃቤ ህግ የምርመራ መዝገቡን መርምሮ የሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ የወጣውን አዋጅ ቁጥረ 881/2007 አንቀፅ 15 ንዑስ አንቀፅ 2 ላይ የተመለከተውን ድንጋጌ ተላልፎ በመገኘቱተከሳሹ በፈፀመው በስራ ተግባር የሚፈፀም የመውሰድና የመሰወር ወንጀል ክስ መስርቶበት ከፍተኛው ፍርድ ቤት እንዲቀርብ ተደርጓል ብለዋል፡፡

የካፋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ግራ ቀኙን አስቀርቦ ሲያከራክር ቆይቶ የፖሊስ ባልደረባ የሆነው ረዳት ሳጅን ወገኔ ወልዴ በዐቃቤ ህግ የቀረበበትን የሰው እና የባንክ ሰነድ ማስተባበል ባለመቻሉ ፍርድ ቤቱ የጥፋተኝነት ብይን ሰጥቷል፡፡

በዚሁ መሰረት የካፋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ህዳር 30 ቀን 2017 ዓ.ም ባስቻለው ችሎት የዐቃቤ ህግን በተከሳሹ ላይ ፍርድ ቤቱ ቅጣቱን እንዲያከብድበት የፖሊስ አባላትን ስምና ዝና የሚያጎድፍ እና ህብረተሰቡ በፖሊስ እምነት እንዳይኖረው በማድረጉ ፍርድ ቤቱ ተከሳሹ ላይ አስተማሪ ቅጣት እንዲወስንበት ጠይቋል፡፡

የተከሳሹን የቅጣት ማቅለያ አስተያየት መርምሮ ተከሳሹንም ሆነ ሌሎችን ያስተምራል በሚል ተከሳሽ ወገኔ ወልዴ በሰባት አመት ፅኑ እስራትና በ2.000 ሺህ ብር እንዲቀጣ ፍርድ ቤቱ ሲወሰንበት በእግዚቭት የተያዘዉ 59 ሺህ ብር ለባለቤቱ እንዲመለስስለመ መወሰኑ ዐቃቤ ህግ ናትናኤል ክፍሌ ተናግረዋል ሲል የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ዘግቧል፡፡

https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
“ናሁ ቴሌቭዥን አልተዘጋም፤ የሳተላይት ቅያሪ ነው ያደረግነው” ሥራ አስኪያጁ

|በተለያዩ ማህበራዊ ትስስር ገፆች ከአውድ ውጪ የተተረጎሙ መረጃዎች እንደተሰራጩበት ናሁ ቴሌቭዥን አስታወቀ፡፡

በማህበራዊ የትስስር ገፆች፤ ናሁ ቴሌቭዥን እንደተዘጋ በማስመሰል የተሰራጨው መረጃ “የተሳሳተ ነው” ያለው ተቋሙ፤ የሳታላይት ቅያሪ ማድረጉን እወቁልኝ ብሏል፡፡

የኢትዮ ሳት ስርጭቱን ማቋረጡን ያስታወቁት የተቋሙ ስራ አስኪያጅ፤ በቀጣይ ስርጭቱን በዲ.ኤስ.ቲቪ እና በተለመዱ የማህበራዊ ትስስር ገፆች አማራጭነት እንደሚቀጥል አስታውቀዋል፡፡

ናሁ ቴሌቭዥን ከአስር አመት በላይ የተለያዩ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያ ይዘት ያላቸው ወቅታዊ እና አዳዲስ ሃገራዊ እና አለም አቀፋዊ ዜናዎችን እንዲሁም የመዝናኛ ፕሮግራሞችን ያላማቋረጥ ወደ ተመልካቾች ሲያደርስ መቆየቱ ይታወሳል፡፡

በእነዚህ ጊዚያትም በሃገሪቷ ጎልተው ከወጡ እና ተቀባይነት እንዲሁም ተወዳጅ መሆን ከቻሉት ጥቂት የቴሌቭዥን ጣቢያዎች ውስጥ አንዱ መሆን ችሏል፡፡

ነገር ግን ከሰሞኑ በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አውታሮች አማካኝነት "ናሁ ቴሌቭዥን ተዘግቷል" የሚሉ ወሬዎች ሲንሸራሸሩ ሰንብተዋል፡፡

በመሆኑም ናሁ ቴሌቭዥን እንዳልተዘጋ እና በተለያዩ ማህበራዊ ትስስር ገፆች ከአውድ ውጪ የተተረጎሙ መረጃዎች እንደተሰራጩበት የናሁ ቴሌቭዥን ከፍተኛ
የሥራ ሃላፊዎች አስታውቀዋል፡፡

https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
2024/12/26 20:24:59
Back to Top
HTML Embed Code: