በእሳት አቃጠሉት ‼️
በብራዚል የአንድ አመት እና የሰባት ወር ህፃናትን በደፈረ ግለሰብ የተቆጡ ሰዎች ፖሊስ ጣብያውን ሰብረው በመግባት ደፋሪውን ከነ ህይወቱ አቃጥለውታል።
@sheger_press

ከእኛ ጋር የሰሩ ምስክሮቻችን ናቸዉ!
ደንበኞችን ካሉበት ወደ እርሶ ማድረሱን ተክነንበታል።
ከርሶ እሚጠበቀዉ ወደ እኛ መምጣት ብቻ ነው!
አድራሻችን:22 ማዞሪያ ኮሜት ህንጻ፣ ቢሮ ቁጥር 206
ስልክ፡ 0988800031
ኢ-ሜል፡ [email protected]
ቴሌግራም: @AiQEMContact
Telegram
Facebook
LinkedIn
Twitter
ደንበኞችን ካሉበት ወደ እርሶ ማድረሱን ተክነንበታል።
ከርሶ እሚጠበቀዉ ወደ እኛ መምጣት ብቻ ነው!
አድራሻችን:22 ማዞሪያ ኮሜት ህንጻ፣ ቢሮ ቁጥር 206
ስልክ፡ 0988800031
ኢ-ሜል፡ [email protected]
ቴሌግራም: @AiQEMContact
Telegram
ቤንዚን እና ጥቁር ገበያው❓❓
በአዲስ አበባ ቤንዚን ረጅም ሰዓት ሰልፍ ሳይሰለፉ ማግኘት ዘበት ከሆነ ሰነባብቷል።
ባለፉት ሳምንታት በትንሽ በትንሹ የጀመረው የቤንዚን ሰልፍ ከሰሞኑን እጅግ ብሶበታል።
በአንዳንድ ማደያዎች " ቤንዚን የለም " እየተባለ ሲለጠፍ ቤንዚን ያለባቸው ማደያዎች እጅግ በጣም ረጅም ሰልፍ ነው ያለው።
በዚህም ምክንያት የመኪና አሽከርካሪዎች ቀናቸውን በቤንዚን ሰልፍ ለማሳለፍ እየተገደዱ ይገኛሉ።
በሜትር ታክሲ አገልግሎት ላይ የተሰማሩ ዜጎችም ስራቸውን በአግባቡ ለመስራት ተቸግረዋል። ቀናቸውን ሁሉ በቤንዚን ሰልፍ ለማሳለፍ እየተገደዱ ናቸው።
በክልል ከተሞችም የቤንዚን ነገር ብሶበታል።
ቀድሞውንም ቤንዚን በማደያ እንደልብ በማንኛውም ሰዓት ማግኘት የማይቻልባቸው የክልል ከተሞች አሁንም ችግሩ እንዳለ ነው።
በክልል ከተሞች አሽከርካሪዎች ቤንዚን በማደያ " የለም " የሚባሉ ሲሆን በጀርባ ግን በየቦታው በህገወጥ መንገድ በጥቁር ገበያ ቤንዚን ሲቸበቸብ ይታያል።
ይህ ህዝብን እያማረረ ያለው የጥቁር ገበያ የነዳጅ ሰንሰለት መቼ እንደሚበጠስ አይታወቅም። ከዚህ ጀርባ እጃቸው የረዘመ አካላት መኖራቸውን ግን አሽከርካሪዎች ይናገራሉ።
ቤንዚን በክልል ከተሞች ከማደያ ውጭ በእጥፍ ዋጋ ነው የሚቸበቸበው።
ስራ ቀይረው በጥቁር ገበያው ቤንዚን ነጋዴ የሆኑም በርካቶች ናቸው።

ሁሌ እንደማደርገው አይቼ ላልፈው ነበር...!
"በነፃነት ያሻን ቦታ መሄድ" የሚለውን ሳይ ግን...
አሁን ላይ ስንቱ ወገን ነው ጠግቦ በልቶ እያደረ ያለው? ስንቱ ነው በነፃነት እያሰበ እና እየተናገረ ያለው? ማነው ከአዲስ አበባ ውጪ ንቅንቅ ብሎ ያሻው ቦታ የሚሄድ? ስንቱ ነው ለፍቶ ጥሮ ያገኘውን ጥሪት በልማት ስም እየተቀማ እና እየፈረሰበት ያለ?
ይሄ አላማ ከስንት አመት በኋላ ይሳካ ይሆን?
መሬት ላይ ካለው ችግር ይልቅ እንዲህ አይነት የተስፈኛ አካሄድ እጅጉን ያስፈራል፣ የባሰው ችግር ገና ወደፊት እንደሆነም ያመላክታል።
#Ethiopia eliasmeseret

በመስቀል ደመራ በዓል የተከለከሉ ነገሮችን ለብሶም ሆነ ይዞ መምጣት ክልክል ነው
የዘንድሮው የመስቀል ደመራ በዓል በሰላም ተከብሮ እንዲያልፍ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ተደርጎ ወደ ሥራ መገባቱን ጥምር የፀጥታ ኃይሉ አስታውቋል፡፡
በዓሉ ወደሚከበርበት ስፍራ ከበዓሉ አከባበር ጋር ግንኙነት የሌላቸውን ነገሮች ይዞ መምጣት አመፅን የሚቀሰቅሱ እና ተከባብሮ የመኖር እሴትን የሚሸረሽሩ ፅሁፎች ያሉባቸውን አልባሳት ለብሶ መምጣት በአጠቃላይ የተከለከሉ ነገሮችን
ይዞ መምጣትና እንዲሁም ደመራ የማብራት ስነ ስርዓት በሚከናወንባቸው የተለያዩ ቦታዎች ላይ ርችት ማፈንዳት ክልክል መሆኑን ህብረተሰቡ ተገንዝቦ ለፀጥታ ሃይሎች ሥራ ተባባሪ እንዲሆን ጥምር የፀጥታ ኃይሉ አሳስቧል፡፡

News ‼️
ግዙፉ መንግስታዊ የቴሌኮም አቅራቢ ድርጅት የሆነዉ ኢትዮቴሌኮም በተወሰኑ ምርትና አገልግሎቶቹ ላይ የታሪፍ ማሻሻያ ሊያደርግ እንደሚችል አስታዉቋል
ተግባራዊ ከተደረገ አንድ ወር ያለፈዉ የማክሮኢኮኖሚ ፖሊሲ ማሻሻያ ተከትሎ የደበንኞችን የመክፈል አቅም ያገናዘበ የታሪፍ ማሻሻያ ለማድረግ መታሰብ ተቋሙ ገልጿል።
የኢትዮቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ እንደተናገሩት ሁሉም ደንበኞች እና አገልግሎቶች ላይ ዋጋ አንጨምርም ነገር ግን የደንበኞችን የመክፈል አቅም ያገናዘበ በአንድአንድ ምርትና አገልግሎቶች ላይ የታሪፍ ማሻሻያ ይደረጋል ብለዋል።
የኢኮኖሚ ሪፎርሙን ተከትሎ ወዲያዉ ያልተስተካከለበት ምክንያት የደንበኞቹን አጠቃላይ ደግሞ የማክሮኢኮኖሚ ለዉጥ እንዲረጋጋ በማሰብ መሆኑ ተነግሯል ።
ባለፉት ሁለት አስርት አመታት የብር ዋጋ ከ750% በላይ ሲቀንስ ኢትዮቴሌኮም ባለፉት ስድስት አመታት በከፍተኛ ደረጃ የዋጋ ቅናሽ በማሳየቱ ዋጋው ከአለም ዝቅተኛው እና ለተጠቃሚዎች በጣም ተመጣጣኝ እንዲሆን አድርጎታል።
እንደ ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ገለፃ እ.ኤ.አ በ 2018 ላይ ከ 40 እስከ 50 በመቶ የታሪፍ ቅናሽ ያደረገ ሲሆን በሂደትም የተለያዩ የታሪፍ ማሻሻዎችን ማድረጉን እንዲሁም ፤ የቅርብ ጊዜ ሪፖርቶችንም ደግሞ ከተመለከትን ኢትዮ ቴሌኮም ዝቅተኛ ዋጋ የሚያስከፍል መሆኑን ነው የሚያሳየው ብለዋል።
"ዘለን ታሪፉን ያላስተካከለው የደንበኞቻችንን እንዲሁም በአጠቃላይ የማክሮ ኢኮኖሚ ለውጡ እንዲረጋጋ እና ጤናማ እንዲሆን ስለምንፈልግ ነው” በማለትም ተናግረዋል።
አሁን ላይ ተቋሙ በተለይ በድምፅና በዳታ አገልግሎት ላይ የሚያስከፍለዉ ታሪፍ ርካሽ እንደሆነ ያነሱት ዋና ስራ አስፈፃሚዋ አዲስ የታሪፍ ለማድረግ እንደታሰበ ከመናገር ዉጪ መቼ እንደሚተገበር ግን ከመናገር ተቆጥበዋል።

#ሶማሊላንድ #ግብፅ ወደ ሞቃዲሹ ከባድ የጦር መሳሪያ ማስገባቷን ተከትሎ ማስጠንቀቂያ ሰጠች‼️
የሶማሌ ላንድ መንግስት ግብፅ ለሶማሊያ የምታቀርበውን ከባድ የጦር መሳሪያ አሳሳቢነት በመግለጽ እርምጃው ቀድሞውንም ደካማ የነበረውን የቀጠናውን ደህንነት ይበልጥ አደጋ ላይ ይጥላል ስትል አስጠንቅቃለች።
የሶማሊላንድ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው ይፋዊ መግለጫ፣ “በተለይ የሞቃዲሾ አስተዳደር በብቃት ለማስተዳደር ወይም ለመጠበቅ የሚያስችል አቅም ስለሌለው የእነዚህ መሳሪያዎች ዝውውር በእጅጉ አስደንግጦናል ብለዋል።
ሶማሊላንድ በተጨማሪም ይህ የጦር መሳሪያ ዝውውር የአፍሪካ ቀንድን ወደ አልተረጋጋ ቀውስ እና የጦር መሳሪያ እሽቅድምድም እድልን ከፍ እንደሚያደርግ አፅንዖት ሰጥታለች።

"ጄኔራል ፃድቃን ከማን ጋር ነው የምንደራደረው ? ብሎናል " ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር)‼️
ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ፤ ጄነራል ጻድቃን ገ/ትንሳኤን ስልጣን ለመጠቅለል በማቀድና የቆየ ቂም ለመወጣት በሚል ከሰሱ።
ቅዳሜ በመቐለ በተካሄደና የህወሓት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረጽዮን ህወሓትን ለማጥፋት፣ ስልጣን ለመጠቅለል የሚንቀሳቀሱ ተብለው የተገለፁ አመራሮች በስም እየተጠቀሱ ወቀሳ ሲሰነዘርባቸው ተሰምቷል።
በዚሁ መድረክ ደብረፅዮን (ዶ/ር) ፥ የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዝደንት የሆኑት ጀነራል ፃድቃን ገብረትንሳኤን፥ ስልጣን ለመጠቅለል በማቀድ፣ የቆየ ቂም በመወጣት እና ሌሎች በርካታ ጉዳዮች በማንሳት እንዲሁም ከዚህ በፊት በይፋ ያልተሰሙ መረጃዎች በመግለፅ ሲተቹ ተደምጠዋል።
በንግግራቸው እርሳቸው የሚመሩትን ህወሓት ሰላም የማይፈልግ አድርጎ የማቅረብ የተሳሳተ ፍረጃ ከትግራይ ባለስልጣናት በኩል እየቀረበበት መሆኑ ገልጸው " ይህ ውሸት ነው " በማለት አጣጥለዋል።
ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ፤ " ለምሳሌ በደቡባዊ ዞን በተደረገ መድረክ ጀነራል ጻድቃን እኛ ሰላም እንፈልጋለን፣ እነሱ የሚሹት ጦርነት ነው ሲል ሰምታችሁታል። በጦርነቱ ወቅት ደሴ ተሻግረን ሰሜን ሸዋ ስንጠጋ፥ ድርድር ያስፈልጋል ወይ ሲባል እኔ አዎን ያስፈልጋል ነው ያልኩት። በሰላም ሊፈታ ስለሚገባው። እሱ ግን ከማን ጋር ነው የምንደራደረው፣ ውጊያው አልቋል ሲል የነበረ ነው። አሁን ግን እኔ ሰላም ነኝ እነሱ ጦርነት ናቸው የሚፈልጉ ማለት ጀመረ " ብለዋል። #ዶቼቨለ

#ግብፅ
በርካታ ከባድ የጦር መሳሪያዎችን የጫነች የግብጽ መርከብ ሞቃዲሾ ወደብ መድረሷ ተገለጸ።
ካይሮ የላከቻቸው የአየር እና የታንክ መቃወሚያዎችን ጨምሮ ሌሎች ከባድ የጦር መሳርያዎች ወደ ሀገሪቱ መከላከያ ሚኒስቴር መስርያ ቤትና የተለያዩ የጦር ካምፖች መጓጓዛቸውም ተዘግቧል።
ግብጽ በነሀሴ ወር በሁለት ወታደራዊ አውሮፕላኖች ለሶማሊያ የጦር መሳርያና ወታደሮችን ልካለች መባሉ የሚታወስ ሲሆን፥ ሞቃዲሾ ግን የወጡትን ዘገባዎች ማስተባበሏ አይዘነጋም።
በሶማሊላንድ እና በኢትዮጵያ መካከል የወደብ የመግባብያ ስምምነት መፈረሙን ተከትሎ የአዲስ አበባ እና ሞቃዲሾ ግንኙነት መሻከሩን ተከትሎ የግብጽና ሶማሊያ ወታደራዊ ትብብር እያደገ ይገኛል።
ከግብጽ የተላኩትን የጦር መሳርያዎች ከትላንትናው እለት ጀምሮ ከሞቃዲሾ ወደብ የማራገፍ ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ ሲነገር፤ ወደ ሀገሪቱ መከላከያ ሚንስትር መስርያ ቤት እና በአካባቢው ወደሚገኙ የጦር ካምፖች ጦር መሳርያዎቹን እየተጓጓዙ ነው ተብሏል፡፡
ይህን ተከትሎም ወደቡ እና ዋና ዋና መንገዶች ለንግድ እና ለሲቪሊያን እንቅስቃሴዎች ዝግ መደረጋቸውን ዘገባው ጨምሮ አስነብቧል።በሶማሊላንድና በኢትዮጵያ መካከል የወደብ የመግባብያ ስምምነት መፈረሙን ተከትሎ የአዲስአበባና ሞቃዲሾ ግንኙነት መሻከሩ ይታወሳል፡፡
በዚህም የአባይ ውሀን ከመቆጣጠር ጋር በተያያዘ ከኢትዮጵያ ጋር ቆየት ያለ ባላንጣነት ያላት ካይሮ ወደ አፍሪካ ቀንድ እየቀረበች እንደምትገኝ ተንታኞች ይናገራሉ፡፡በሶማሊያ የአፍሪካ ህብረት የሽግግር ተልዕኮ (አትሚስ) በቀጣይ የሚኖረው አዲስ የሰላም ተልዕኮ አወቃቀር ላይ የኢትዮጵያን ወታደሮች መካተት አልቀበልም ያለችው ሶማሊያ ግብጽ በሰላም አስከባሪ ሀይሉ ውስጥ እንድትሳተፍ ፍላጎቷ መሆኑን ተናግራለች፡፡(አልአይን)

ቴሌግራም የተጠቃሚዎቹን መረጃ ለመንግስታት አሳልፎ ሊሰጥ ነው
ቴሌግራም የተጠቃሚዎቹን መረጃ ህግን በተከተለ መልኩ ሲጠየቅ ለመንግስት ተቋማት አሳልፎ ሊሰጥ እንደሚችል አስታወቀ።
ውሳኔው ድርጅቱ ለረጅም ዓመታት ይዞት የነበረውን የደንበኞቹን መረጃ አሳልፎ ያለመስጠት ፖሊሲ የሻረ መሆኑ ተገልጿል።
በዚህም ድርጅቱ ህግን የተከተለ ጥያቄ ሲቀርብለት የተጠቃሚዎቹን አይ ፒ አድራሻ፣ ስልክ ቁጥር እና ሌሎች መረጃዎችን አግባብ ላላቸው የመንግስት አካላት እንደሚሰጥ አስታውቋል።
ቴሌግራም እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው መስራቹና ዋና ስራ አስፈጻሚው ፓቬል ዱሮቭ ባለፈው ነሐሴ ወር በፈረንሳይ መንግስት መታሰሩን ተከትሎ መሆኑ ተጠቅሷል።
በመተግበሪያው ላይ የሚሰራጩ ፅንፈኛ አቋም ያላቸው ይዘቶችን አልተቆጣጠረም በሚል ክሱ የተመሰረተበት ዋና ስራ አስፈጻሚው በዋስ ተፈቶ ከአገር እንዳይወጣ መታገዱ ይታወሳል።
ውሳኔውን አስመልክቶ ፓቬል ዱሮቭ ይፋዊ የቴሌግራም ቻናሉ ላይ ባሰፈረው መረጃ “የቴሌግራምን ህግ የሚጥሱ ተጠቃሚዎች የስልክ ቁጥርና አይፒ አድራሻ ህግን ተከትለው ጥያቄ ላቀረቡ አካላት አሳልፈን እንደምንሰጥ ግልፅ አድርገናል” ብለዋል።

የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ፣ በተያዘው ዓመት ዕድሜያቸው ከ4 እስከ 6 ዓመት የኾናቸውን 1 ሚሊዮን 760 ሕጻናትን ለመመዝገብ ታቅዶ፣ 324 ሺሕ ብቻ እንደተመዘገቡ አስታውቋል፡፡
ከ1ኛ እስከ 8ኛ ባሉት ክፍሎች፣ 4 ሚሊዮን 800 ሺሕ ተማሪዎች እንደሚመዘገቡ ተጠብቆ እንደነበር የጠቀሰው ቢሮው፣ ባለፉት 20 ቀናት የተመዘገቡት ከ1 ሚሊዮን 300 ሺሕ አይበልጡም ማለቱን ዘገባው አመልክቷል።
በተመሳሳይ በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 1 ሚሊዮን 200 ሺሕ ተማሪዎችን ለመመዝገብ ታቅዶ፣ ወደ ትምህርት ቤት ገበታ የተመለሱት ግን 300 ሺሕ ብቻ እንደኾኑ ተነግሯል።
የተማሪዎች ቁጥር የቀነሰው በዋናነት በጸጥታ ችግር የተነሳ እንደኾነ ቢሮው ተናግሯል ተብሏል።
@ethio_mereja_news

ጸጥታ ኃይሎች ሰሞኑን በአዲስ አበባ ወጣቶችን በጅምላ እያሠሩ መኾኑን ዋዜማ ተረድታለች። የጅምላ እስሩ ከደመራ እና እሬቻ በዓላት ጋር የተያያዘ ሳይኾን እንደማይቀር ተገምቷል።
የታሳሪ ቤተሰቦች፣ ጸጥታ ኃይሎች ለእስሩ የሰጧቸው ምክንያት፣ "ከወቅታዊ ሁኔታ ጋር በተያያዘ" የሚል እንደኾነ ለዋዜማ ተናግረዋል።
በርካታ ወጣቶች ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ወይም ክስ ሳይመሠረትባቸው፣ ለሁለት ሳምንታት ያህል እንደታሠሩ ለማወቅ ተችሏል።
ዋዜማ ከፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ቃል አቀባይ ጀላን አብዲ እና ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ቃል አቀባይ ማርቆስ ታደሠ አስተያየት ለማግኘት ያደረገችው ጥረት፣ ስልካቸውን ባለማንሳታቸው አልተሳካም።

በአማራ ክልል ከ 4መቶ ሺህ በላይ የወባ ህሙማን ሪፖርት መደረጉ ተነገረ
በአማራ ክልል የተለያዩ ቦታዎች በተከሰተዉ የወባ በሽታ በሀምሌ እና ነሀሴ ወራት ከ 4መቶ ሺህ በላይ የወባ ህሙማን ሪፖርት መደረጋቸዉ ተነግሯል ፡፡
የአማራ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የወባ መከላከል እና መቆጣጠር ፕሮግራም አስተባባሪ አቶ ዳምጤ ላንከር ለጣቢያችን እንደተናገሩት ፤ አዊ ዞን፡ደቡብ ጎንደር ዞን እና ማእከላዊ ጎንደር ዞኖች በክልሉ በቀዳሚነት የበሽታዉ ስርጭት ተጠቂዎች ሆነዋል ሲሉ ጠቅሰዋል ፡፡
የበሽታዉን ስርጭት ለመቆጣጠር ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር በመሆን የሳምንታዊ ክትትል ስራ እና በ22 ወረዳዎች እንዲሁም በ 233 ቀበሌዎች የኬሚካሌ እርጭት መደረጉን የፕሮግራሙ አስተባባሪ አንስተዋል ፡፡
በተጨማሪም ከ1ሚሊዮን 1መቶ ሺህ በላይ የህብረተሰብ ክፍል በኬሚካል እርጭት ተጠቃሚ ይሆናሉ ተብሎ እንደሚገመት ተናግረዋል ፡፡
የላብራቶሪ መመርመሪያ ቁሳቁሶች እና ለእርጭት የሚሆኑ ኬሚካሎች የግብአት እርዳታ መንግስት እንዲደረግላቸዉ የፕሮግራሙ አስተባባሪ አቶ ዳምጤ ላንከር ጠይቀዋል ፡፡
አቤል እስጢፋኖስ ] ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8

በሊባኖስ ባለዉ ግጭት ምክንያት በሀገሪቱ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉን ዜጎች ስጋት ዉስጥ መሆናቸዉ ተነገረ
በቤይሩት የኢትዮጵያ ቆንፅላ ፅ/ቤትም በሊባኖስ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን የጥቃት ዒላማ ሊሆኑ ይችላሉ ተብሎ ከሚታሰቡ ቦታዎች ራሳቸውን እንዲያርቁ አሳስቧል፡፡
ሀገረ ሊባኖስ የጋዛዉ እጣፋንታ ደርሶባት ዜጎቿን በአሰቃቂ ጥቃት እየተነጠቀች ስለመሆኑ ከስፍራዉ የሚወጡ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡
የሊባኖስ ባለስልጣናት፤ እስራኤል ሂዝቦላ ላይ ያነጣጠረ ነዉ ባለችዉ ጥቃት በአንድ ቀን ብቻ 500 የሚጠጉ ሰዎች እንደተገደሉ ተናግረዋል።
ቀጣይ ደረጃ ብላ እስራኤል በሰየመችዉ እስራኤል በሊባኖስ ሄዝቦላን ለማጥቃት እንደምትገፋበት እየገለጸች ነዉ፡፡
ይህ ብቻ አይደለም በደቡባዊ ሊባኖስ የሚገኙ ዜጎች አካባቢያቸዉን ለቀዉ እንዲወጡ በሚል ለ80 ሺህ ዜጎች በእጅ ስልካቸዉ የማስጠንቀቂያ መልዕክት ማስተላለፏም ተሰምቷል፡፡
በሀገረ ሊባኖስ ከ 50 ሺህ በላይ ዜጎች እንደሚኖሩ መረጃዎች ያሣያሉ፡፡
የተለያዩ ሀገራት ሁኔታዉ ከዚህ የከፋ ሊሆን ይችላል በሚል ስጋት ዜጎቻቸዉ ሊባኖስን በአስቸኳይ ለቀዉ እንዲወጡ እያስጠነቀቁ ይገኛሉ፡፡
በተለይም በደቡባዊ ሊባኖስ የሚኖሩ ዜጎች ወደተያዩ ስፍራዎች በፍጥነት እየተመሙ ነዉ ተብሏል፡፡
ይሁንና ከፍተኛ የትራፊክ መጨናነቅ በመፈጠሩ አካባቢዉን ቶሎ ጥሎ ለመዉጣት አስቸጋሪ መሆኑም እየተነገረ ነዉ።
በቤይሩት የሚገኙ ኢትዮ ኤፍ ኤም ያናገራቸዉ ነዋሪዎችም ይህንኑ አረጋግጠዋል፡፡
በመካከለኛዉ ምስራቅ የሚታየዉ ግጭት እና ዉጥረት እየሰፋ እንዳይሄድ የዓለምን ህዝብ አስግቷል።
በደቡባዊ ሊባኖስ በአሥር ሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ንብረቶቻቸዉን በመኪና እየጫኑ ወደ ሰሜን የአገሪቱ ክፍል ለማቅናት እየሞከሩ ነዉ።
በሊባኖስ በአስር ሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዉያን በሊባኖስ ይኖራሉ።
በሊባኖስ ያለዉን ስጋት አስመልክተዉ ማብራሪያ የሰጡት የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነቢያተ ጌታቸዉ የዜጎችን ደህንነት ለማስጠበቅ የተለያዩ ጥረቶች እየተደረጉ ነዉ ብለዋል፡፡
በቤይሩት የኢትዮጵያ ቆንፅላ ፅ/ቤት በበኩሉ በሊባኖስ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን የጥቃት ዒላማ ሊሆኑ ይችላሉ ተብሎ ከሚታሰቡ ቦታዎች ራሳቸውን እንዲያርቁ አሳስቧል፡፡
በሊባኖስና በቀጠናው ያለው ወቅታዊ የፀጥታ ስጋት እንዲሁም ውጥረት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየከፋ መጥቷል ያለው ቆንፅላ ፅህፈት ቤቱ በተለይ በደቡባዊ ሊባኖስ እና በቤይሩት አንዳንድ አካባቢዎች ላይ የሚደርሰው ጥቃት ተጠናክሮ ቀጥሏል ብሏል፡፡
ቆንፅላ ፅህፈት ቤቱ ጉዳዩ አሳሳቢ መሆኑ ተረድቶ የዜጎችን ደህንነት ለመጠበቅ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር እየሰራ እንዳለ በፌስ ቡክ ገጹ ላይ ባወጣው መግለጫ አስረድቷል፡፡
የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ የሊባኖስ ህዝብ “ጥቃት ከሚሰነዘርባቸው አካባቢዎች በፍጥት እንዲወጡ አሳስበዋል።
ለረዥም ጊዜ ሄዝቦላህ እናንተን እንደ ጋሻ ሲጠቀምባችሁ ቆይቷል። በመኖሪያ ክፍሎቻችሁ ውስጥ ሮኬቶችን እና ሚሳኤሎችን አስቀምጧል።
ህዝባችንን ከሄዝቦላህ ጥቃት ለመከላከል እነዚህን መሳሪያዎች ማስወገድ አለብን ብለዋል።
በቤይሩት የኢትዮጵያ ቆንፅላ ፅ/ቤት ከሊባኖስ መንግስት የሚሰጡ መመሪያዎችን መተግበር የከፋ ነገር በሚያጋጥምበት ወቅት ደግሞ በቆንፅላው የቀጥታ የስልክ መስመር ዜጎች እንዲደውሉ ፅህፈት ቤቱ ጠይቋል፡፡
ችግሩ እየከፋ የሚሄድ ከሆነ ወደፊት የሚወሰዱ እርምጃዎችን በፌስ ቡክ የማህበራዊ ትስስር ገፅ ላይ የማሳውቅ ይሆናል ብሏል፡፡
አባቱ መረቀ
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8

በትራፊክ አደጋ የ28 ሰዎች ሕይወት አለፈ
ከወላይታ ሶዶ ከተማ ወደ ዳውሮ ዞን ሲጓዝ የነበረ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ተገልብጦ የ28 ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡
በወላይታ ዞን ፖሊስ መምሪያ የትራፊክ አደጋ መከላከልና ቁጥጥር ዲቪዥን ኃላፊ ኢንስፔክተር ወልዴ ቢሊሶ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት÷ ከሟቾች በተጨማሪ በ29 ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሷል፡፡
አደጋው ዛሬ ቀን 7 ሠዓት ላይ በወላይታ ዞን ኪንዶ ዲዳዬ ወረዳ ፈታታ ቀበሌ መከሰቱንም አረጋግጠዋል፡፡
የተከሰተው አደጋ ከባድ መሆኑን ጠቅሰው የሟቾች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል አመላክተዋል፡፡
Via fbc