Telegram Web Link
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ።

መልካም በዓል!

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ፎቶ ፦ የ2017 ዓ/ም የመስቀል ደመራ አከባበር በዓል በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ።

photo - tikvah

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
አረጋዊ ካህን ዐራት ቤተሰባቸውን ጨምሮ ማንነታቸው ባልታወቁ ኃይሎች በአሰቃቂ ሁኔታ ተገደሉ

መልአከ/መ/ ቀሲስ ወልደ ኢየሱስ አያሌው የተባሉ በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት በሉሜ ( ሞጆ ) ወረዳ ቤተ ክህነት በቢቃ ደ/መ/ቅ/ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ለ 41 ዓመታት ያህል ከዲቁና እስከ ደብር አስተዳዳሪነት ድረስ በትሕትና ሲያገለግሉ መቆየታቸው ተገልጿል፡፡

ካህኑ ከባለቤታቸውና ከሦስት ልጆቻቸው ጋር ባሰቃቂ ሁኔታ ማንነታቸው ባልታወቁ ኃይሎች በግፍና በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸውን የሉሜ ወረዳ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት የገለጸ ሲሆን ልጃቸው ዲ/ን መልአክ ወልደ ኢየሱስም የቤተ ክርስቲያን አገልጋይ እንደነበር ተጠቅሷል፡፡

ጸሎተ ፍትሐት ሥርዓቱም የሞጆ ሉሜ ወረዳ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ መልአከ ሰላም ቆሞስ አባ ሰይፈ ገብርኤል ገረመው፣ የአድባራት አስተዳዳሪዎች ፣ አበው ካህናት ሊቃውንት ፣ በርካታ ምእመናን በተገኙበት በሞጆ ደ/ብ/ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን በብፁዕነታቸው መሪነት እየተከናወነ ይገኛል።

ዘገባው የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሚዲያ ነው

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የሸዋ አማራ የጦር ግንባር ዉሎዎችን በሚዛናዊነት እየተከታተለ የሚያቀርብ ቻናል ልጠቁማችሁ👇👇
https://www.tg-me.com/SNN_merja
እስራኤል በዛሬው እለት በደቡባዊ ቤይሩት ከተማ የሂዝቡላህ ዋና መስሪያቤትን ጨምሮ ሶስት ህንፃዎችን ሙሉ በሙሉ በማውደም በርካታ ሰዎች ህይወት አልፏል።

የጥቃቱ ኢላማ የሂዝቡላሁ መሪ ሰይድ ሀሰን ነስረላህ የነበረ ሲሆን ኢላማዋ አለመሳካቱን ቡድኑ አስታውቋል።

ሂዝቡላህ ከጥቃቱ በሗላ በሰጠው አጭር መግለጫ ሰይድ ሀሰን ነስረላህ ደህንነቱ በተጠበቀ ቦታ ነው ብሏል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚንስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት(ተመድ) 79ኛ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ተገኝተው ስሜት የተሞላበት ንግግር አድርገዋል፡፡ 

“ዘንድሮ በጉባኤው የመሳተፍ እቅድ አልነበረኝም፤ ሀገሬ በከፍተኛ ውጥረት ውስጥ በምትገኝበት ጊዜ እዚህ የተገኘሁት በመድረኩ ከተለያዩ አካላት ለቀረበብን ወቀሳ ምላሽ ለመስጠት ነው” በሚል ንግራቸውን የጀመሩት ጠቅላይ ሚንስትሩ እየተዋጋን ያለነው ከምድረ ገጽ ሊያጠፉን ከሚሹ “አረመኔ ጠላቶች” ጋር ነው ብለዋል።

“እስራኤል ኢራን በከፈተችው 7 አውደ ውግያዎች እየተዋጋች ትገኛለች፤ ተሄራን ከምታሰማራቸው ርህራሄ የለሽ ገዳዮች እራሳችንን መከላከላችንን እንቀጥላለን፡፡ ይህ ሲሆን በኢራን ውስጥ የእስራኤል ረጅም ክንድ የማይደርስበት ቦታ አለመኖሩ ሊታሰብበት ይገባል” ነው ያሉት

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ኢትዮጵያ በሶማሊያ የደረሰውን የሽብር ጥቃት አወገዘች

የኢትዮጵያ መንግሥት በሶማሊያ ሞቃዲሾ የደረሰውን የሽብር ጥቃት አወግዟል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው የሐዘን መግለጫ÷ በተፈጸመው የሽብር ጥቃት ሕይወታቸውን ላጡ ቤተሰቦች መጽናናትን ተመኝቷል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት የተፈጸመውን ጥቃት በማውገዘ ሽብርተኝነትን በመታገል ረገድ ከሶማሊያ መንግሥትና ሕዝብ ጎን መሆኑንም አረጋግጧል፡፡
ወልቂጤ ከተማ በይፋ ከሊጉ ተሰርዟል

የወልቂጤ ከተማ እግር ኳስ ክለብ አስፈላጊው የመወዳደሪያ መስፈርት ባለሟሟላቱ በሊጉ የመጀመሪያ ሳምንታት ሁለት ጨዋታዎች ላይ ሳይካፈሉ ቀርተዋል።

የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ አክስዮን ማህበር የውድድር ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ባስተላለፈው ውሳኔ ክለቡ “ ከ 2017 የ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ እንዲሰረዝ “ ወስኛለሁ ብሏል።

የወልቂጤ ከተማ ክለብ ለውድድር ዓመቱ የሚያስፈልገውን የክለብ ላይሰንሲንግ የምዝገባ ሂደት ማሟላት ሳይችሉ መቅረታቸው የሚታወስ ነው።

የወልቂጤ ከተማን ከሊጉ መሰረዝ ተከትሎ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ በቀጣይ በአስራ ስምንት ክለቦች መካከል የሚካሄድ ይሆናል።

@sheger_press
@sheger_press
በሲዳማ ክልል ደቡባዊ ዞን ዳራ ወረዳ በዚህ ወር ብቻ ከ25 በላይ ህፃናት በጅብ ተበልቷል ይለናል የዳውሮ ኮሚኒኬሽን‼️

ለዚህም የክልሉ መንግሰት ልዩ ትኩረት እንዲሰጥ ተጠይቋል።

ጅቦቹ በአካባቢው በቀን እየወጡ በተደጋጋሚ ጥቃት እያደረሱ መሆኑን በመጠቆም የክልሉ መንግሰት ልዩ ትኩረት እንዲሰጥ ተጠይቋል።
በሲዳማ ክልልም በቀን ጭምር የጅብ ጥቃት እንደቀጠለ ነው።

@sheger_press
@sheger_press
2024/11/18 17:52:57
Back to Top
HTML Embed Code: