Telegram Web Link
ፍርድ ቤቱ ፖሊስ በእነ ዮሐንስ ዳንኤል ላይ በጠየቀው የጊዜ ቀጠሮው ላይ ብይን ለመስጠት ለነገ ቀጠሮ ያዘ !

የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተረኛ ችሎት የፌዴራል ፖሊስ በእነ ዮሐንስ ዳንኤል ላይ በጠየቀው የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ላይ የግራቀኙን ሰፊ ክርክር ካዳመጠ በኋላ ብይን ለመስጠት ለነገ ነሐሴ 21ቀን 2016 ዓ.ም ቀጠሮ ይዟል።

ተጠርጣሪዎቹ በጠበቆቻቸው በኩል የዋስትና መብት እንዲፈቀድላቸው ጠይቀዋል።

የፌዴሬል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቡድን ተጠርጣሪዎቹ ላይ የአቪዬሽን አሰራር ሕግ ከመጣስ ባለፈ በሽብር ወንጀልም ምርመራ ስለጀመርኩ የዋስትና ጥያቄያቸው ውድቅ ይደረግ በማለት ተከራክሯል።

ዛሬ ፍርድ ቤት የቀረቡት ተጠርጣሪዎች ዮሐንስ ዳንኤል በርሄ፣ አማኑኤል መውጫ አብርሃ፣ ናትናኤል ወንድወሰን ሹሜ፣ ኤልያስ ድሪባ በዳኔ፣ ይዲድያ ነጻነት አበበ እና እሌኒ ክንፈ ተክለአብ ናቸው።

የፌዴራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ የምርመራ መዝገብ እንደሚያሳየው እነዚህ ተጠርጣሪዎች ተፈጥሮ በፈጠረው የአየር መዛባት ምክንያት አውሮፕላኑ መብረር አይችልም እየተባለ፣ አስገድዶ ለማስኬድ የፈጠሩት አምባጓሮ በወንጀል ሕጉ ተጠያቂ ያደርጋቸዋል ብሏል።

የፖሊስ የምርመራ ቡድን ተጠርጣሪዎች ላይ በወንጀል ተጠያቂ ለማድረግ ከተጀመረው ምርመራ ባሻገር፣ ከጸረሰላም ኃይሎች ተልዕኮ ተቀብለው የተንቀሳቀሱ በመሆናቸው፤ በሽብር ወንጀልም መጠርጠራቸውን ነው የሚያመላክተው።በወቅቱ አየር መንገዱ ከደህንነት ኃይሎች ጋር በመሆን በትዕግስት ቢማጸናቸውም፤ ድብቅ አጀንዳቸውን እያራመዱ በመሆናቸው አሻፈረን ማለታቸውንም በምርመራ መዝገቡ አካቷል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
6ኛ እና 8ኛ ክፍል የማለፊያ ነጥብ ይፋ ሆኗል

በ2016 ዓ.ም በተሰጠው ክልል አቀፍ 6ኛ እና 8ኛ ክፍል ከተመዘገበው ውጤት አንጻር ዝቅተኛ የማለፊያ መቁረጫ ነጥብ አማካኝ ውጤት
👉ለ6ኛ ክፍል
   ✍️ለወንድ 46
    ✍️ለሴት 45
ለአይነ ስውራን ተማሪዎች
✍️ ለወንድ 45
✍️ ለሴት 44 ሆኗል።
👉ለ8ኛ ክፍል
✍️ለወንድ 46
✍️ለሴት 45
👉ለአይነ ስውራን ተማሪዎች
✍️ ለወንድ 45
✍️ለሴት 44 እንዲሆን የተወሰነ መሆኑን የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ አሳውቋል።

@sheger_press
@sheger_press
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የኦሞ ወንዝ ባስከተለው መጥለቅለቅ ሳቢያ ጎርፍ ወደ ዳሰነች ወረዳ ዋና መቀመጫ ኦሞራቴ ከተማ በመቃረብ ላይ እንደኾነ ተነግሯል።

ወንዙ ያስከተለው መጥለቅለቅ ከአቅም በላይ እንደኾነ የገለጸው የዞኑ አስተዳደር፣ ጉዳይ የሚመለከታቸው አካላት ለችግሩ ዘላቂ መፍትሄ እንዲፈልጉ ጠይቋል።  

የወንዙ ውሃ መንደሮችን ከጎርፍ ለመከላከል የተሠሩ የአፈር ግድቦችን በመጣስ፣ አዳንዳንድ ቀበሌዎችን ማጥለቅለቅ እንደጀመረ የዞኑ አስተዳደር ገልጧል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
📹የሚሸጥ የዩቱብ ቻናል
https://www.youtube.com/@ayatdaily602
  🔹 STRICK FREE
  🔹COPYRIGHT FREE
  🔹 MONITIZED የሆነ 💰50 በውስጡ አለው
  🔹Passport Done
  🔹Pin verified

🛑 channel እንፈልጋለን ላላቹኝ

🔔• 9,514 SUBSCRIBE

•➤አሁኑኑ ያናግሩን 👇

📩 •➤ 𝐈𝐧𝐛𝐨𝐱 𝐌𝐞
@ETHIO_JOURNAL
ደብረብርሃን ባጃጆች ከጠዋቱ 12:00 ሰአት እስከ ምሽቱ 12:00 ሰአት ብቻ እንዲሰሩ ተወሰነ።

የደብረ ብርሃን ከተማ  የጸጥታ ምክር ቤት  ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ባጃጅ ተሽከርካሪን በመጠቀም በማህበረሰቡ ላይ ስርቆትን ጨምሮ የተለያዩ ወንጀሎችን ለመከላከል ለባጃጅ አሽከርካሪዎች የተለያዩ ክልከላዎችን አስቀምጠ።

በዚህ ወንጀል የተሠማሩ አካላት የባጃጅ ተሽከርካሪዎቹን ማሟላት ያለባቸውን ህጋዊ ሰውነት ተሽከርካሪዎቹ ሳያሟሉ እንደሚያሽከረክሩም የጸጥታው ምክር ቤት እንደደረሰባቸው አንስቷል።

ለህዝብ ሰላም ሲባል የጸጥታ ምክር ቤቱ ህግና ስርአት ለማስከበር ያመች ዘንድ ማንኛውም የባጃጅ አሽከርካሪ በተሽከርካሪው ላይ ስቲከር መለጠፍ ፣ መጋረጃ መጠቀም እንደማይቻል በክልከላው ገልጿል።

ያለስምሪት ፣ የጎን ቁጥርና ታርጋ  ሳይጠቀሙም ማሽከርከር በጥብቅ የተከለከለ መሆኑን፣

ከዛሬ 4:00 ጀምሮ የባጃጅ ተሽከርካሪ እንቅስቃሴ ከጠዋቱ 12:00 ሰአት እስከ ምሽቱ 12:00 ሰአት ብቻ ማሽከርከር  እንደሚቻል፣

ከዚህ ሰአት ውጭ ወይም ከላይ መደረግ ያለባቸውን ያላሟላ ባጃጅ ሲንቀሳቀስ ቢገኝ የማያዳግም ህጋዊ እርምጃ በባጃጅ አሽከርካሪውና ባለንብረቱ ላይ እንደሚወሰድ ከከተማ አስተዳደሩ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘሁት መረጃ ያመላክታል።
Cats በ Pre market 🔥🔥

ያልጀመራቹ ጀምሩ ቀጣዮ DOGS 👇👇

http://www.tg-me.com/catsgang_bot/join?startapp=xkQP3ezHQcUYeSPyt_-Hv
ለፖሊስ የ14 ቀን የግዜ ቀጠሮ ተፈቀደ

የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዛሬ በዋለው ችሎት የፌዴራል ፖሊስ በእነ ዮሀንስ ዳንኤል ላይ የጠየቀውን የ14 ቀን የግዜ ቀጠሮ ፈቅዷል።

ተጠርጣሪዎቹ የዋስትና መብት እንዲፈቀድላቸው በጠበቆቻቸው አማካኝነት የጠየቁ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ የፖሊስን የምርመራ ውጤት ለመጠባበቅ ለጳጉሜ 4 ቀን 2016 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል።

ዛሬ ፍርድ ቤት የቀረቡት ተጠርጣሪዎች ዮሀንስ ዳንኤል በርሄ፣ አማኑኤል መውጫ አብርሃ፣ ናትናኤል ወንድወሰን ሹሜ፣ ኤልያስ ድሪባ በዳኔ፣ ይዲድያ ነጻነት አበበ እና እሌኒ ክንፈ ተክለአብ ናቸው።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ሦስት ጊዜ የሞት ፍርድ የተፈረደበት ነው! ~ ፖሊስ

በሽብርና በሲቪል አቪየሽን ሕግ ጥሰት ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር ከዋሉት መካከል ኤሊያስ ድሪባ በዳኔ የተባለው ተጠርጣሪ ከዚህ ቀደም በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ ከባድ ወንጀሎች ተከሶ ዳዊት ድሪባ በዳኔ በሚል ስም ሦስት ጊዜ የሞት ፍርድ የተፈረደበት ደጋጋሚ ወንጀለኛ መሆኑን ፖሊስ አስታወቀ

በሽብርና በሲቪል አቪየሽን ሕግ ጥሰት ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር ከዋሉት መካከል ኤሊያስ ድሪባ በዳኔ የተባለው ተጠርጣሪ ከዚህ ቀደም በአዲስ አበባ ከተማ ከ1989 ዓ ም ጀምሮ እሰከ 1999 ዓ ም በተለያዩ ከባድ ወንጀሎች ተከሶ ዳዊት ድሪባ በዳኔ በሚል ስም ሦስት ጊዜ የሞት ፍርድ የተፈረደበት ደጋጋሚ ወንጀለኛ መሆኑን ፖሊስ አስታወቀ።

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 2ኛ ወንጀል ችሎት ታህሳስ 25 ቀን 1999 ዓ.ም በዋለው ችሎት በዘረፋ፣ በቅሚያ፣ በሌብነት፣ በቤት ሰብሮ ስርቆት እና በደንብ መተላለፍ በዕድሜ ልክ ፅኑ እስራት እንዲቀጣ መወሰኑን ከፖሊስ የምርመራ ማህደር ማረጋገጥ ተችሏል።

ተጠርጣሪው ኤሊያስ ድሪባ በዳኔ ፣ ጀማል ኑሩ እና ዳዊት ድሪባ በዳኔ የሚሉ ስሞችን በመጠቀም 11 ጦር መሣሪያ መዝረፍ ወንጀል፣ 6 ቅምያ ወንጀል፣ 3 ሌብነት ወንጀሎች፣ 3 ሰው መግደል ወንጀል፣ 2 ስርቆትና ቤት ሰብሮ ስርቆት ወንጀሎች፣ አንድ ሐሰተኛ ሰነድ መገልገል ወንጀል፣ ከእስር ማምለጥ ወንጀል እና አንድ ደንብ መተላለፍ የወንጀል ሪከርድ በአጠቃላይ 28 የወንጀል ሪካርዶች ያሉበት እንደሆነና ከዚህ ውስጥ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 2ኛ ወንጀል ችሎት መጋቢት 24 ቀን በዋለው ችሎት ስድስት መዝገቦችን ሦስት ጊዜ አጣምሮ ሦስት ጊዜ በሞት እንዲቀጣ ውሳኔ የተላለፈበት መሆኑን ከፖሊስ የምርመራ ማህደር መገንዘብ ተችሏል።


ኢ.ፌ.ፖ.ሚ
አቶ ታዮ በዋስ እንዲለቀቁ ያቀረቡት አቤቱታ ውሳኔ አላገኘም!

በተለያዩ ወንጀሎች ጥርጣሬ ተከስሰዉ የታሰሩት የቀድሞ የኢትዮጵያ የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ታዬ ደንደዓ በዋስ እንዲለቀቁ ያቀረቡት አቤቱታ ዛሬም ዉሳኔ አላገኘም።ባለፈዉ ሐምሌ 30፣ 2016 አዲስ አበባ ያስቻለው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የሕገ መንግስትና ሕገ-መንግስት ስርዓት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀል ጉዳዮች ችሎት አቶ ታዬ ላይ ከተመሠረተባቸዉ ሶስት ክሶች ከሁለቱ በነጻ አሰናብቷቸዉ ነበር።

ይሁንና ፍቃድ ሳይኖራቸው የጦር መሳሪያ ይዘው ተገኝተዋል በሚል የቀረበባቸውን 3ኛ ክስ ግን እንዲከላከሉ ፍርድ ቤቱ በይኖ ነበር፡፡ የአቶ ታዬ ባለቤት ወይዘሮ ስንታየሁ ዓለማየሁ ለአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ስዩም ጌቱ እንደነገሩት አቶ ታዬ ሥስተኛዉን ክስ በዋስ ተለቅቀዉ እንዲከራከሩ ያቀረቡትን ጥያቄ ፍርድ ቤት ዉድቅ አድርጎባቸዋል።

በዚሕም ምክንያት ተከሳሹ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ሁለተኛ ወንጀል ችሎት ይግባኝ ጠይቀዉ ፍርድ ቤቱ ለዛሬ ቀጠሮ ሰጥቷቸዉ ነበር።ወይዘሮ ስንታየሁ እንዳሉት ፍርድ ቤቱ አቤቱታን ዛሬ ማየት አልቻለም። አቶ ታዬ ደንደዓ የተመሰረተባቸዉን ክስ ያለጠበቃ በራሳቸዉ እየተከራከሩ ነዉ።

የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ስዩም ጌቱ እንደዘገበዉ አቶ ታዬ የጥብቅና መብት ለመከልከላቸው መንግስትን ተጠያቂ አድርገው፣የብሔራዊ መረጃ ደህንነት ያሉትን ተቋም መክሰሳቸው አይዘነጋም፡፡አቶ ታዬ የገዢዉ የብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ ባለሥልጣን፣ የኦሮሚያ ምክር ቤት አባልና ሚንስትር ደ ኤታ ነበሩ።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የ3 አመት ልጅ የደፈረው የእድሜ ልክ እስራት ተቀጣ

በጋሞ ዞን ዲታ ወረዳ የግብረስጋ ድፍረት በደል የፈጸመው ተከሳሽ በዕድሜ ልክ ጽኑ እስራት ተወስኗል።

ተከሳሽ አቶ ቱካ ቱጋሞ ዕድሜ 45 ስሆን በ1996ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ህግ አንቀጽ 627(5) ስር የተመለከተውን ድንጋጌ በመተላለፍ የዲታ ወረዳ አቃቤ ህግ ክስ ተመስርቶበታል፡፡

የአቃቤ ህግ የክስ መዝገብ እንደሚያስረዳው ተከሳሽ የግብረስጋ ግንኙነት በመፈጸሙ ነሀሴ 5/ 2016ዓ.ም ዕሁድ ከቀኑ 9:00 የሚሆንበት ጊዜ በዲታ ወረዳ ዛዳ ከተማ ቀበሌ ልዩ መጠሪያው ሚሽዳ ቀጠና ተብሎ የሚጠራበት አከባቢ የ3አመት ልጅ የሆነችውን የግል ተበዳይ

ህፃን ብርቱ ገነነ ዕድሜ ሦስት ዓመት የሆነችው ልጅ ከሌሎች ልጆች ጋር ከብቶችን በሚያግዱበት ቦታ ተከሳሽ አንቀላፍታለች በማለት አቅፎ ወደ ተበዳይ ወላጅ አባቷ ቤት ድረስ በማምጣት አስገድዶ በመድፈር የከባድ አካል እና ሥነ ልቦና ጉዳት ያደረሰባት በመሆኑ የፈፀመው በህፃን ልጆች ላይ የሚፈፀም የግብረስጋ ድፍረት ወንጀል ክስ አቅርቧል።

ዐቃቤ ህግ የተከሳሽን ጥፋተኝነት ያስረዱልኛል ያላቸውን ዝርዝር የሰው እና የሰነድ ማስረጃዎች ለፍርድ ቤቱ በማቅረብ የተከሳሽን ጥፋተኝነት ያሰረዳ ሲሆን ተከሳሽም ወንጀሉን ስላለመፈጸሙ ማስረጃ አቅርቦ ያላሰተባበለ በመሆኑ ፍርድ ቤቱም የዐቃቤ ህግን የሰውና የሰነድ ማስረጃ መሰረት በማድረግ ተከሳሽን ጥፋተኛ በማለት ነሀሴ 22/2016 ዓ.ም በዕድሜ ልክ ጽኑ እስራት እዲቀጣ ተወስኖበታል ፡፡

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ጥቆማ‼️

ቴሌግራምን በመጠቀም ብቻ በርካቶች በርካታ ብር በማግኘት ላይ ናቸው።

እናንተም ይህን ቻናል በመቀላቀል ሙሉ ትምህርት ማግኘት ትችላላቹ።

Join us👇👇👇👍
https://www.tg-me.com/+fzeZ2gn56UE3NTI0
https://www.tg-me.com/+fzeZ2gn56UE3NTI0
ታዋቂዋ አቀንቃኝና የግጥም ፀሃፊ
Cardi B በ X ገጿ ላይ ለህፃን ሔቨን ድምፅ ሆናለች።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
2024/10/01 07:24:29
Back to Top
HTML Embed Code: