Telegram Web Link
በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን ለመቀጠር እስከ አንድ ሚሊየን ብር እጅ መንሻ እየተጠየቀ ነው ተባለ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ስር ባሉ የአዲስ አበባ ከተማ ሀገረ ስብከት አድባራትና ገዳማት ሥራ ለመቀጠር እንደየደረጃው ከ 3 መቶ ሺሕ እስከ 1 ሚሊዮን ብር እጅ መንሻ ክፍያ እንደሚጠየቅ ዋዜማ ካነጋገረቻቸው የተለያዩ ምንጮች ሰምታለች።

በተለይም በከተማይቱ፣ ትልቅ ሀብት የሚያንቀሳቅሱና ከፍተኛ የገቢ ምንጭ ያላቸው ናቸው በሚባሉ አድባራትና ገዳማት አሥተዳዳሪ፣ ጸሐፊ፣ ሂሳብ ሹም ሆኖ ለመቀጠር ከ 3 መቶ ሺሕ እስከ 1 ሚሊዮን ብር እጅ መንሻ (ጉቦ) እንዲከፍሉ እንደሚጠየቁ ነግረውናል።

ጉዳዩን በቅርበት የሚያውቁና ከጉዳዩ ጋር ትሰሰር ያላቸው ምንጮች እንዳሉት፣ ሥራ ፈላጊዎች በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የቤተክርስቲያኒቱን ትምህርት ከ 5 እስከ 15 ዓመታት ያህል ተምረው ሥራ ፍለጋ ወደ አዲስ አበባ በሚመጡበት ወቅት እንደየሥራ ዘርፉ ክፍያ ካልከፈሉ ቅጥር የማይታሰብ ነው።

አሁን ላይ በቤተክርስቲያኒቱ ያለው የቅጥር ሁኔታ በሕግና በስርዓት ማስታወቂያ ወጥቶ ሰዎች አመልክተውና ተወዳደረው ሳይሆን ገንዘብ የመክፈል አቅም ያላው የሚቀጠርበትና ሥራ የሚያገኙበት እንደሆነ እነዚሁ ምንጮች ለዋዜማ ገልጸዋል።

ዋዜማ ካነጋገረቻቸው በርካታ ሥራ ፈላጊዎች መካከል አንዱ እንዳሉት አቋቋም፣ ድጓ እና ቅኔ የተሰኙትን የቤተክርስቲያኒቱን ትምህርት አጠናቀውና አስመስክረው ሥራ ፍለጋ በከተማይቱ ውስጥ ባሉ በርካታ አቢያተ ክርስቲያናት ቢያመለክቱም “እጅ መንሻ ክፍያ ካልፈጸምክ ቅጥር የለም” መባላቸውን ተናግረዋል።

ሥራ ፈላጊው የመጡት ከአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ደብረ ብርሃን ከተማ እንደሆነ የተናገሩ ሲሆን፣በዚያ አካባቢ ባሉ ገዳማትና አድባራት ተዘዋውረው አስፈላጊውን የቤተክርስቲያኒቱን ትምህርት መማራቸውን አስረድተዋል።

ሆኖም ሥራ ፍለጋ ወደ አዲስ አበባ ሲመጡ ነገሩ እንዳሰቡት እንዳልሆነላቸውና ሥራ ለመቀጠር 3 መቶ ሺሕ ብር ክፍያ መጠየቃቸውን ይገልጻሉ። በተለይም ከተማይቱ ውስጥ ባሉ ታላላቅ አድባራትና ገዳማት ለመቀጠር የሚጠየቀው የገንዘብ መጠን ደግሞ ለሰሚው ግራ የሚያጋባ ነው ሲሉ ትዝብታቸውን አጋርተዋል።

ተቀጣሪን ከቀጣሪ የሚያገናኙ ደላላዎች የጉዳዩ ዋና ተዋናዮች ሲሆኑ ሥራ ፈላጊዎቹን ካሉበት ፈልገው በሀገረ ስብከት ውስጥ ከሚሰሩ ሰዎች ጋር በቀጥታ የሚያገናኟቸው ሲሆን፣ ደላሎቹም ከሚገኘው ገንዘብ ላይ ድርሻ እንዳላቸው አስረድተዋል።

በዚሁ ጉዳይ ላይ ዋዜማ ያነጋገረቻቸው ስሜ አይጠቀስ ያሉ አንድ ግለሰብ እንደተናገሩት በአዲስ አበባ ውስጥ ባለ አንድ ትልቅ ደብር በመሪጌታነት የሥራ መደብ የተቀጠሩት ከሁለት ዓመታተ በፊት መሆኑን ያስረዳሉ።

በዚያ ወቅትም አጠቃላይ የቅጥሩን ሂደት ለመጨረስ 350 ሺሕ ብር በየደረጃው ላሉ የቤተክርስቲያኒቱ አመራሮች እጅ መንሻ ክፍያ መፈጸማቸውን ለዋዜማ ተናግረዋል።

እሳቸው እንደሚሉት ይህ ጉዳይ አሁን የጀመረ ሳይሆን የሰነበተና ቀስ በቀስ ስር እየሰደደ መጥቶ አሁን ላይ ሕጋዊ እስኪመስል ድረስ በግልጽ የሚከናወን የአደባባይ ምስጢር ነው ።

እጅግ ከባድ የሚባለውን የቤተክርስቲያኒቱን ትምህርት ለበርካታ ዓመታት የተማሩና እውቀቱ ያላቸው ሰዎች የተጠየቁትን ክፍያ መፈጸም ባለመቻላቸው በአዲስ አበባ ከተማ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ያሉ በርካቶች ናቸው ።

ከእነዚህ መካከል በከተማይቱ አደባባዮች ላይ ሎተሪ የሚያዞሩ፣ በጥበቃ ሥራ የሚተዳዳሩ፣የቀን ሥራ የሚሰሩ በየአቢያተክርስቲያናቱ ደጅ እየጠኑ ያሉ ሰዎች ቁጥራቸው ብዙ ነው።

ይህን ጉዳይ ከሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ጀምሮ፣የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ፣የየመምሪያው የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም በየደረጃው ያሉ ሰዎች የሚያውቁትና ተደጋጋሚ አቤቱታ የቀረበበት ነው ሲሉ ጉቦ ተጠይቀናል ያሉት ግለሰቦች አስረድተውናል።

ሆኖም ግን ይህን ችግር ለመፍታትና እንደዚህ አይነት አሰራር ለማስቆም አንዳችም ጥረት ሲደረግ ተመልክተው እንደማያውቁ ያስረዳሉ።

ዋዜማ ያነጋገረቻቸው አንድ ሌላ ግለሰብ ደግሞ በስብከተ ወንጌል የሥራ ዘርፍ ለመቀጠር አመልክተው 4 መቶ ሺሕ ብር ክፍያ መጠየቃቸውን አውስተዋል።

ሆኖም ይህን ያህል ገንዘብ የመክፈል አቅሙ ስለሌላቸው እንደተውት ገልጸዋል።

ዋዜማ በጉዳዩ ላይ የአዲስ አበባ አገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ የሆኑትን ሊቀ ማእምራን የማነ ዘመንፈስቅዱስን ጠይቃለች።

“ከሠራተኛ ቅጥር ጋር ተያይዞ እንደዚህ አይነት ችግሮች የሉም ማለት አይቻልም” ብለዋል ዋና ሥራ አስኪያጁ።

ሥራ አስኪያጁ አክለውም የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በዚህ ሰዓት ሙሉ ለሙሉ የሠራተኛ ቅጥር መፈጸም አቁሟል ሲሉ አክለዋል።

ከዚሁ ችግር ጋር ተያይዞ፣ እሳቸውን ጨምሮ ከጠቅላይ ቤተ ክህነት እንዲሁም ከአዲስ አበባ አገር ስብከት የተወጣጡ አባላትን ያካተተ ኮሚቴ መቋቋሙን ለዋዜማ ገልጸዋል።

ችግሩን ለመቅረፍም ከዚህ በኋላ አድባራት ራሳቸው ማስታወቂያ አውጥተው ሰራተኞችን አወዳድረው ቅጥር እንዲፈጽሙ ለማድረግ የሚያስችል አሰራር እንዲፈጠር ውይይት እየተደረገ ነው ብለዋል።

ከሥራ ቅጥር ጋር ተያይዞ ቅሬታ ከሚያነሱ ሰዎች ጋርም የሚመለከታቸው የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት፣ ውይይት መካሄዱን ሊቀ ማእምራን የማነ ገልጸዋል።

በሌላ በኩል የቤተ ክርስቲያኒቱን ትምህርት የተማሩ በሙሉ አዲስ አበባ ውስጥ ባሉ አድባራትና ገዳማት ሥራ ለመቀጠር ከተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች ወደ ከተማይቱ በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚፈልሱ ጠቁመዋል።

ይህ ደግሞ አሁን ለሚነሳው ችግር እንዲጋለጡ ትልቁን ሚና እንደሚጫወት ሥራ አስኪያጁ አብራርተዋል።

በተጨማሪም ሥራ አስኪያጁ ከሦስት ወራት በፊት ከቤተክርስቲያኒቱ ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፣ የአዲስ አበባን አገረ ስብከት ከዚህ ቀደም በተለያዩ ጊዜያት በሥራ አስኪያጅነት የመምራት እድል እንደነበራቸው ተናግረዋል።

በዚህ ወቅት ወደዚሁ ኃላፊነት ድጋሚ ሲመጡ ተቋሙ በብዙ መልኩ ተዳክሞና የተለያዩ የአሰራር ችግሮች አጋጥመውት እንዳስተዋሉ አንስተዋል።

ከነዚህም መካከል በአገረ ስብከቱ አላስፈላጊ የሆነ የሠራተኛ ቅጥር ተከናውኖ መታዘባቸውን ጠቁመዋል።

እሳቸው ወደ አገረ ስብከቱ በሥራ አስኪያጅነት ሲመጡ፣ ከ 1 መቶ በላይ ፣በአለቅነት፣ በሂሳብ ሹምና በፀሀፊነት ጭምር የተመደቡ ትርፍ ሰራተኞች ደሞዝ ይከፈላቸው እንደነበር ገልጸዋል።

ሥራ አስኪያጁ እንዳሉት “የአዲስ አበባ አገረ ስብከት የታወከ፣ጩኽት የበዛበትና መረጋጋት የተሳነው ነው”

“ወደ ኃላፊነት ስመጣ እንደ ተቋም ፈርሶ ነው ያገኘሁት” ሲሉ ተደምጠዋል።

Via ዋዜማ

@ethio_mereja_news
ሰበር‼️

የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ አባላት እና ፕሬዘዳንቱ ላይ ሕጋዊ እና አስተዳደራዊ እርምጃ እንዲወሰድባቸው ተጠየቀ‼️

👉 በቀረበው ሰነድ ዶክተር አሸብርን ጨምሮ የሥራ አስፈጻሚው ቦርድ አባላት የፈጸሟቸውን በደሎች በዝርዝር ተመልክቷል

👉አቤቱታው ከፍተኛ የሆነ የፋይናንስ ጥሰትና ምዝበራ መካሄዱን ይገልጻል

👉 ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረ ሥላሴ ያለ እሱ ፍቃድና ዕውቅና እየተቃወመ በግድ ምክትል እንዳደረጉት ተጠቅሷል።

👉 ረ/ኮሚሽነር አትሌት ደራርቱ ቱሉ ያለ ምርጫ ለቦርዱ አመራርነት እንድታልፍ መደረጉም ተያይዟል።

በኢትዮጵያ ተመዝግበው ያሉ ሕጋዊ የስፖርት ፌዴሬሽኖች በሕጋዊ ወኪል ጠበቆቻቸው አማካኝነት፤ በኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝዳንት እና ስራ አስፈጻሚ ቦርድ አባላት ላይ አስዳደራዊ እርምጃ እንዲወስድ የሚጠይቅ ሰነድ በዛሬው ዕለት ለኢፌዴሪ ባህልና ስፖርት ሚንስቴር አስገብተዋል።

አቤቱታ አቅራቢ ፌዴሬሽኖቹ በሰነዳቸው ላይ ካቀረቧቸው ምክንያቶች መሐል፦

👉ግንቦት 16 ቀን 2016 ዓ/ም ኮሚቴው ከፌዴሬሽኖቹ እውቅና ውጪ በድብቅ ጥሪ ተደርጎ በድብቅ የተፈጸመ ስብሰባ ማካሄዱን ይገልጻል።

👉አቤቱታ አቅራቢ ፌዴሬሽኖች ባልተጠሩበት፤ ሰኔ 4 ቀን 2016 ዓ/ም በተደረገ ሕገወጥ የኦሎምፒክ ኮሚቴ የሥራ አስፈጻሚ ቦርድ አባላት ምርጫ፤ ኮሚቴ ለሚፈልጋቸው ጥቂት አባላት ብቻ ጥሪ በማድረግ፤ መተዳደሪያ ደንቡ የማይፈቅድላቸውን በድምፅም ሆና ያለ ድምፅ የጠቅላላ ጉባኤው አባል ያልሆኑ ግለሰቦችን የምርጫ አስፈጻሚ ኮሚቴ አድርገዋቸዋል።

👉 ከዶክተር አሸብር ወልደ ጊዮርጊስ ጋር የጥቅም ግንኙነት አላቸው ያሏቸውን የኢትዮጵያ ቅርጫት ኳስ ፌዴሬሽን ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር ጥበቡ ቸኮልን ኮሚቴው አስመራጭ በማድረግ ሕግ ተላልፏል ሲል በአቤቱታው ላይ ያስነብባል።

👉አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረ ሥላሴ ዕውቅና እና ፍቃድ ድርጊቱን እየተቃወመ በሕገ ወጥ ምርጫው ላይ ምክትል ፕሬዝዳንት እንዲሆን ተደርርጓል የሚል አቤቱታም ይገኝበታል።

👉የሥራ አስፈጻሚ ቦርድ አባላት በጠቅላላ ጉባኤው ምርጫና አብላጫ ድምፅ እንደሚመረጡ መተዳደሪያ ደንቡ የሚደነግግ ቢሆንም ረ/ኮሚሽነር አትሌት ደራርቱ ቱሉ ያለ ምርጫ እንድታልፍ መደረጉን በሰንዱ ተብራርቷል።

👉ለኮሚቴው ከረጂ ተቋማት የተሰበሰበ ከ300,000,000.00 (ከሦስት መቶ ሚልየን ብር) በላይ ምን ላይ እንደዋለ በኦዲት ሪፖርት እንደማያውቁት አቤቱታ አቅራቢዎቹ በሰነዱ ላይ ገልጸው በተጨማሪም ከስፖንሰር አድራጊዎች የተገኙ በውጭ ምንዛሪ ገቢ የተደረጉ ገንዘቦች ምን ላይ እንደዋሉ የሙያሳይ ግልጽ የኦዲት ሪፖርት አለመደረጉን አቤቱታ አቅራቢዎቹ ጨምረው ዘርዝረዋል።

👉ሰነዱ የአትሌት ገዘኸኝ አበራንም ጉዳይም አያይዞታል።

👉 በአትሌቶች አመራረጥ ላይ ተደርጓል ስለተባለው አድሏዊ አሠራርም ተካቷል።

👉ለአገር ክብር ምልክት ከሆኑ አትሌቶች ይልቅ የአመራሮቹ ዘመድ አዝማዶች አገር ወክለው እንዲሄዱ መደረጉም ተነሥቷል።

👉 ሰነዱ የሥራ አስፈጻሚው ቦርድ አባላት የቅርብ ዘመዶች በኮሚቴው ያለ አግባብ ቅጥር እንዲፈጸምላቸው በማድረግ ምንም ዓይነት ሥራ ሳይፈጽሙ ገንዘብ በመመዝበር በርካታ የፋይናንስ ጥሰት መደረጉን ጨምሮ ይገልጻል።

እነዚህን እና ሌሎችንም አቤቱታዎች ያቀረቡት ፌዴሬሽኖች

👉ኮሚቴው አሻሻልኩት ያለው መተዳደሪያ ደንብ እንዲታገድ፤

👉ሰኔ 4 ተደረገ የተባለው ሕገ ወጥ ምርጫ እንዳልተደረገ ተደርጎ ቀሪ እንዲደረግላቸው፤

👉የተፈጸሙት ተግባራት ከባድ የሆነ የዲሲፕሊን ጥፋት ውጤት በመኾናቸው ቦርዱ ከኃላፊነት ታግዶ እንዲቆይ

👉 በገለልተኛ ኦዲተር ምርመራ እንዲደረግ፤ በመጠየቅ

👉ሚንስቴር መሥሪያ ቤቱ አስተዳደራዊ ርምጃ እንዲወሰድላቸው አቤቱታ አቅራቢዎቹ ጠይቀዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በአገልግሎት ታሪፍ ላይ በየሦስት ወሩ የ10 በመቶ ጭማሪ ለማድረግ መዘጋጀቱን የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል። የታሪፍ ጭማሪው የኢትዮጵያ መንግሥት ከአለም ባንክ ጋር ከተፈራረመው ስምምነቶች አንዱ እንደሆነም ተጠቁሟል፡፡

በማሻሻያው መሠረት በመጀመሪያው ዓመት ብቻ በየሶስት ወሩ ደንበኞች ለኤሌክትሪክ አገልግሎት የሚከፍሉት ታሪፍ ቢያንስ በ10 በመቶ ይጨምራል። አለም ባንክ ይፋ ባደረገው ሰነድ የኢትዮጵያ መንግሥት የአራት ዓመታት የኤሌክትሪክ ታሪፍ ማሻሻያ ማጽደቁን አመላክቷል።
የኢትዮጲያ መንግስት በቀጣይም ውሃ፣ቴሌኮምና መሰል አገልግሎቶች ላይ ተመሳይ ማሻሺያዎችን ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ተገደሉ‼️

በአርሲ አንድ ካህንን ጨምሮ አጠቃላይ 6 የሚደርሱ ሰዎች በታጣቂዎች መገደላቸው ተገለፀ‼️

በአርሲ ሀገረ ስብከት አሰኮ ወረዳ ጢዮ ቀበሌ ጠለታ ጨፋ ከተማ የጠለታ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ካህንን ጨምሮ 6 ኦርቶዶክሳውያን በኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች መገደላቸው ታውቋል።

ግድያው የተፈጸመው ከነሐሴ 7 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ሲሆን ከሞቱት በተጨማሪም 3 ሰዎች ከባድ ጥቃት ደርሶባቸው በህክምና ላይ እንደሚገኙ ከአካባቢው የሚወጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ።

በታጣቂዎቹ የተገደሉትን ሰዎች አስከሬናቸውን ለማንሳትና ለመቅበር አስቸጋሪ በመሆኑ ከቤተክርስቲያኑ ራቅ ወዳለ ቦታ በመውሰድ የቀብር ሥርዓቱን ለመፈፀም ተገደዋል።

በተለያየ መንገድ ቤተ ክርስቲያንን ሲረዱ የነበሩ ኦርቶዶክሳውያን ተለይተው ሀብት ንብረታቸው መቃጠሉንና የአካባቢው ምእመናንም ቤታቸውን ትተው በዱር በስጋት ውስጥ ናቸው ብለዋል፡፡

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የማራቶን አሰልጣኙ ገመዶ ደደፎ መታሰሩ ታወቀ

(መሠረት ሚድያ)- የኢትዮጵያ የማራቶን ቡድንን በፓሪስ ኦሎምፒክ መርቶ ውጤት ያመጣው አሰልጣኝ ገመዶ ደደፎ ዛሬ ጠዋት የሲቪል ልብስ በለበሱ የፀጥታ አካላት በቁጥጥር ስር መዋሉን መሠረት ሚድያ ሰምቷል።

ከውድድሩ በሗላ የሁለት ሚልዮን ብር ሽልማቱን አልቀበልም ያለው አሰልጣኙ የብዙዎች መነጋገርያ ሆኖ ነበር። እስሩ ከዚህ ጋር የተያያዘ መሆኑን ብዙዎች እየገመቱ ያሉ ቢሆንም በይፋ የተባለ ነገር የለም።

መሠረት ሚድያ የአሰልጣኝ ደደፎን ስልክ ደጋግሞ የሞከረ ቢሆንም እስካሁኑ ሰዓት ድረስ ማግኘት አልቻለም።

በዚህ ዙርያ ተጨማሪ መረጃ እንደደረሰን እናቀርባለን።

መሠረት ሚድያ!

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
Update‼️

ለጥያቄ ትፈለጋለህ ተብሎ ጠዋት የተወሰደው አሰልጣኝ ገመዶ ደደፎ አሁን ከመሸ ወደ ቤት መመለሱ ተነግሯል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ሁሉም ትግራዋይ ወዴት እያመራን ነው ? ሲል ራሱን በራሱ በመጠየቅ የመፍትሄ ሃሳብ መስጠት ይገባዋል ሲሉ አቶ ጌታቸው ረዳ አሳሰቡ

በመቐለ ከተማ ዓለም አቀፍ የትግራይ ሙሁራን ማህበር (GSTS) ለ3 ቀናት ያዘጋጀው ትግራይ ክልል መልሶ በማቋቋም ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ ዛሬ መካሄድ ጀምሯል።

በውይይት መድረኩ መክፈቻ ንግግር ያደረጉት አቶ ጌታቸው ረዳ" ሁሉም ትግራዋይ ወዴት እያመራን ነው ? ብሎ ራሱን በራሱ በመጠየቅና በመመለስ የመፍትሄ ሃሳብ መስጠት ይገባዋል " ብለዋል።

" ያለውን መድረክ በመገንዘብ የመፍትሄ ሃሳብ በማስቀመጥ የበኩሉን ሃላፊነት መወጣት አለበት " ሲሉም ተናግረዋል።

" የሙሁራኑ ውይይት ማንኛውም ፓለቲካዊ ልዩነት ይኑር ችላ መባል እና መታለፍ የሌለባቸውን በመያዝ እንዲጠሩ መስራት ይጠበቅበታል " ሲሉ አስገዝበዋል።

ለ3 ቀናት ይቆያል በተባለው የውይይት መድረክ በርካታ ጥናታዊ ፅሁፎች ይቀርባሉ ፣ ውይይትም ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።

ከመላው ኢትዮጵያ ጨምሮ ፥ ከአፍሪካ ፣ አሜሪካ ፣ አወሮፓና ልሎች የዓለም ክፍሎች የተጋበዙ የትግራይ ሙሁራን በውይይት መድረኩ በመሳተፍ ላይ እንደሚገኙ ተሰምቷል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የወደብ አማራጮችን ለማስፋት ከጎረቤት ሀገራት ጋር በቅንጅት እየተሰራ ነው - ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር

የወደብ አማራጮችን ለማስፋት ከጎረቤት ሀገራት ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ ባርኦ ሀሰን ከፋናቢሲ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገራት ጋር ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ዲፕሎማሲ ንግግሮች ማድረግ መቀጠሏን ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገራት ጋር ያላትን ትብብር ማጠናከሯ መሰረተ ልማትን በመዘርጋት ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ፈተናዎችን በጋራ ለማሸነፍ ያግዛል ብለዋል፡፡ ከጎረቤት ሀገራት ጋር ሰጥቶ የመቀበል መርህ አዎንታዊ ምላሽ እየተገኘበት መሆኑንም አንስተዋል ሚኒስትር ዴኤታው፡፡

በተጨማሪም ወደቦች ላይ የሚስተዋለው ችግርን ለመቅረፍ ከጅቡቲ ጋር የጋራ ትብብር ባለስልጣን ለመመስረት ሂደቱ መጠናቀቁን ጠቅሰዋል፡የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብዩ ተድላ ይህንኑ ያረጋገጠ ሲሆን ኢትዮጵያ በህጋዊ እና በሰላማዊ መንገድ አስተማማኝ የባሕር በር ለማግኘት የምታደርገውን ዲፕሎማሲያዊ ጥረት አጠናክራ ትቀጥላለች ብሏል።

በተለይም ኢትዮጵያ ከሶማሊያ ፌደራል መንግሥት ጋር የተፈጠሩ ልዩነቶች እስኪፈቱ ድርስ ዲፕሎማሲያዊ ጥረቷን እንደምትገፋበትም አምባሳደር ነብዩ ገልጸዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ስለ ባህርዳር‼️

በአማራ ክልል ርዕሰመዲና ባህርዳር ከተማ ዛሬ ነሀሴ 10 በተለይ ከሰዓት በኋላ ጀምሮ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ተስተጓጉሏል፣የንግድ ቤቶች ተዘጋግተው ተመልክተናል ብለዋል።

የክልሉ የፀጥታ ቢሮ ሀላፊ አቶ ደሳለኝ ጣሰው ጉዳዩን አስመልክቶ ከሰዓት በፊት መግለጫ የሰጡ ሲሆን "ባህርዳር ላይ ምንም አይፈጠርም፣ የፀጥታ መዋቅሩ በአስተማማኝ ደረጃ ላይ ይገኛል" ሲሉ ተደምጠዋል።

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን በበኩሉ ባህርዳር ላይ ምንም የተፈጠረ የፀጥታ ችግር የለም፣ ህዝቡ ተረጋግቶ የተለመደ የዕለት ከእለት ተግባሩን እንዳያከናውን ጥሪ አቅርቧል።

የከተማዋ ነዋሪዎች እንደሚሉት ትናንት ጀምሮ የፋኖ ሀይሎች ወደ በባህርዳር ከተማ እንገባለን፣ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ እንዲቆም ጥሪ አድርገዋል በሚል ለመዝጋት እንደተገደዱ ገልፀውልኛል።

የከተማዋ አንድ ነዋሪ "ምሳ አዝዤ ATM ደርሼ ስመለስ ሹሮ ቤቱ ተዘግቶ አገኘሁት ሲል ገልፆልኛል። መሰራታዊ የመንግሥት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አገልገሎት መስጠት አቁመዋል ብለዋል። ሰሞኑን ከፍተኛ የሆነ የቦንብ ፍንዳታ ይሰሙ እንደነበር ጠቁመዋል።

ውጊያ አለ ወይ
እስካሁን ምንም አይነት ተኩስ አልሰማንም፣አብዛኛው በስጋት ምክንያት ነው የዘጉት ያሉ ሲሆን ህዝቡም በቤት ውስጥ ለመቀመጥ ተገዷል፣ ግራ ገብቶናል" ሲሉ የባህርዳር ነዋሪዎች አስተያየታቸውን ለአዩዘበሀሻ ሰጥተዋል።
ይህ መረጃ እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ ያለው መረጃ ይህ ነው።(ayu)

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
<<ተሳትፎ ነው ላልነው ይቅርታ እንጠይቃለን።ኦሎምፒክ ግን ተሳትፎ ነው።>> ዶ/ር አሸብር

የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ የፓሪስን ኦሎምፒክ አስመልክቶ ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ለእነ ዶ/ር አሸብር ከጋዜጠኞቹ የቀረቡት ጥያቄዎች ሲጠቃለሉ... "ይቅርታ ጠይቃችሁ ስልጣን ልቀቁ?" የሚል ነበር።

ዶክተር አሸብር የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት አሸብር ወ/ጊዮርጊስ (ዶክተር) ከሰጧቸው ምላሾች መሐከል ...

📌 ተሳትፎ ነው ላልነው ይቅርታ እንጠይቃለን ።ኦሎምፒክ ግን ተሳትፎ ነው።

📌 ከIOC ከመቶ ሺህ ዶላር በታች ነው የተሰጠን።

📌 የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ያካሄደው  ምርጫ ትክክለኛ ነው።

📌 የቀረበብን ክስ ሰምተናል ግን አንደነግጥም።

📌 አትሌቶችን ጥሩ ሆቴል አስቀምጠናል። ሆቴል ውስጥ ደግሞ አስረን አላስቀምጥናቸውም።

📌 የቦክስ ተወዳዳሪው በኦሎምፒክ ያልተሳተፈው ፓስፓርት ስለሌውና ስደተኞች መጠለያ ስለሆነ ነው።

📌 አትሌት ገዛኸኝ አበራ ሶስት ጉዞዎችን ሰርዞ በአራተኛው ጉዞ ነው ፓሪስ የመጣው። ያቀረበው ክስ ውሸት ነው። ዋሽቷል።

📌 አትሌት ፍሬህይወት ከፓሪስ የቀረችው በዶፒንግ ምክንያት ነው። ተገቢውን ምርመራ አድርጋ ውጤቷን ማሳወቅ አልተቻለም።

📌 የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ የጣሰው ምንም አይነት ደንብ የለም።

📌 የፌዝ ሪፖርት አላቀረብንም። የፌዝ ሪፖርት አቀረባችሁ በመባሉ ስሜታችን አይነካም።

ሥልጣን አልለቀም!

📌 እንደ ኃይሌ ገ/ሥላሴ ሰልፍ ሳይ አልሮጥም። ኃይሌ በሰልፍ ወረደ በሰልፍ ሊመለስ ይፈልጋል ።

📌 የሚያግደን ምንም ኃይል የለም።

📌 ደሀ ስለሆንን አነስተኛ ልዑክ ይዘን የሄደነው የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ልዑክ ነው።

📌 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ፌዴሬሽንን ያፈረሰው ኃይሌ ገ/ሥላሴ ነው።

📌 ለኃይሌ ስንል የሽግግር መንግስት እናቋቋም እንዴ? ...እኔ ከዚህ ጋ ብነሳ ኃይሌ በፍጹም እዚህች አይደርሳትም።

📌 “ ከሀላፊነት በመውረድ እና በመውጣት የሚመጣ ለውጥ የለም እግር ኳሱን ምሩ ብዬ ጥዬ ወጥቼ የመጣ ለውጥ የለም።  
 
📌 ጉዳፍ ፀጋይን ለማግባባት ሞክረን ነበር ፣ ነገር ግን አቋሟ ጥሩ ስለነበር በሦስቱም ርቀቶች እወዳደራለሁ ስላለች ትተናታል።" 
 
📌 እኔ ከኃላፊነት ብለቅ እንኳ ኃይሌ ገብረ ሥላሴ የሚገባበት መንገድ የለም።  
 
📌 ወደ ኢትዮጵያ ስትመጣ ሰላማዊ ሰልፍ ይጠብቅሃል ተብዬ ነበር ፣ ሰላማዊ ሰልፍ የዲሞክራሲ መገለጫ ነው ፣ እንደ ኃይሌ ሰልፍ ሳይ አሮጥም።  
 
📌የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ከማንም በላይ ጉልበት አለው ፣ ጉባኤው ጠንካራ ነው።  
 
📌 ሕግ ላይ አጥብቀን ስለምንሰራ ብዙ ጊዜ አልሸነፍም ! 

📌 የኔ ሸልማት የኢትዮጵያ ህዝብ ፍቅር ነው!

ጋዜጣዊ መግለጫ ተጠቃሏል።

በዚህ ጋዜጣዊ መግለጫ ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ  ምክንያቱ ባልተገለጸበት ሁኔታ  አልተገኘችም።

“ በህዝቡ ከኃላፊነት እንዲለቁ እየተጠየቁ ነው ፣ በባንዲራው ስም ይልቀቁ!" ተብለው የተጠየቁት ዶ/ር አሸብር “ ከኃላፊነት አለቅም “ ሲሉ አጭር ምላሽ ሰጥተዋል።
Via Befekadu Abay

@sheger_press
@sheger_press
ህወሃት የእነ ጌታቸው ረዳ ቡድን በህወሓት ስም እንዳይቀሳቀስ አግጃለሁ ብሏል‼️

በህወሃት ሊቀመንበር ደብረፅዮን ቡድን ዛሬ ባወጣም መግለጫ በ14ኛ ያልተሳተፉ የህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ አባላት ማለትም የነ ጌታቸው ረዳ  ቡድን፥  ከዛሬ ጀምሮ በየትኛውም መድረክ በህወሓት ስም እንዳይቀሳቀሱ ማገዱን ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
2024/10/01 17:38:33
Back to Top
HTML Embed Code: