Telegram Web Link
የልጁን ጾታ ለማወቅ በሚል የሚስቱን ሆድ ለመቅደድ የሞከረው ሰው የእድሜ ልክ እስር ተፈረደበት

የአምስት ሴት ልጆች አባት የሆነው አባወራው ወንድ ልጅ የመውለድ ከፍተኛ ጉጉት ነበረው ተብሏል

ከሚስቱ ጋር በተፈጠረ ግጭት ምክንያት ሊወለድ አንድ ወር የቀረው ወንድ ልጅ በደረሰበት ጉዳት ህይወቱ አልፏል

ፓና ላል በህንዷ ኡታር ፕራዲሽ የሚኖር ሲሆን ላለፉት 22 ዓመታት አኒታ ከተሰኘች ሚስቱ ጋር ይኖር ነበር፡፡

ሁለቱ ባለትዳሮች አምስት ሴት ልጆችን ያፈሩ ቢሆንም አባትየው ወንድ ልጅ ባለመውለዱ ሚስቱን ተጠያቂ ያደርግ እንደነበር ተገልጿል፡፡

ስድስተኛ ልጃቸውን ሊወልዱ ትንሽ ቀናት የቀራቸው እነዚህ ባለትዳሮች በተለይም አባትየው የልጃቸውን ጾታ አጥብቆ ማወቅ ይፈልግ ነበር፡፡

የባልና ሚስት የቅርብ ቤተሰቦች ጉዳዩን በእርጋታ እንዲፈቱት ቢወተውቱም ጥንዶቹ ችግራቸውን መፍታት እንዳልቻሉ ተጠቅሷል፡፡

የልጁን ጾታ ለማወቅ እስኪወለድ የመጠበቅ ትዕግስት ያጣው ይህ አባትም የሚስቱን ሆድ ለመቅደድ ሲሞክር ሚስትየው ሮጣ ታመልጣለች፡፡

በመኖሪያ ቤታቸው አቅራቢያ ወደ ሚሰራው ወንድሟ በመሄድ ላይ እያለች ህመም በርትቶባት ስትጮህ የሰማው ወንድሟም ወደ ሆስፒታል እንደወሰዳት እና ህይወቷ እንደተረፈ ኢንዲያን ቱዴይ ዘግቧል፡፡

እንደ ዘገባው ከሆነ እናትየው በተደረገላት ህክምና ህይወቷ ቢተርፍም በማህጸኗ የነበረው ወንድ ልጇ ህይወቱ አልፏል ተብሏል፡፡

አባትየው በፖሊስ ቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ በሰጠው ቃል እኛ በንብረት ተጣልተን አለመግባባት ተፈጠረ እንጂ ጉዳቱን አልፈጸምኩም ቢልም የአካባቢው ፍርድ ቤት የእድሜ ልክ እስር ውሳኔ እንደተወሰነበት ተገልጿል፡፡

በ2020 የተፈጸመው ይህ ወንጀል ክርክር እና ማጣራት ከተደረገ በኋላ ከሰሞኑ እልባት አግኝቷል፡፡(አል-ዐይን)

@ethio_mereja_news
በሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሂደት ላይ የሙስሊሞች ውክልና አነስተኛ ነው ሲል የኢትዮጵያ እስልማና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ቅሬታውን አሰማ፡፡

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ከኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ቀጥሎ አጀንዳ ያስገባ ተቋም መሆኑ ተሰምቷል፡፡

ከኢትዮ ኤፍ ኤም ጋር ቆይታ የነበራቸው የምክር ቤቱ የሙስሊሞች ምክክር ፅ/ቤት ሀላፊ የሆኑት ሀጂ ኑረዲን ጀማል አጀንዳውን ለኮሚሽኑ ስናስገባ ኮሚሽኑ በደስታ እንደተቀበላቸውና ጥሩ ግንኙነት እንዳላቸው ተናግዋል፡፡

ይሁን እንጂ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ህዝበ ሙስሊም ቁጥር ያማከለ ውክልና በኮሚሽኑ ውስጥ አለመኖሩ ቅሬታ እንደተሰማቸው ገልፀዋል፡፡

"ከመጀመሪያውም ቅሬታችን ማህበረሰብ ነው የተደራጀው የሚል ሀሳብ ኮሚሽኑ ቢኖረውም በተወከሉ የማህበረሰብ ክፍሎች ውስጥ ሀይማኖትን አላማከለም" የሚለው ቅሬታ እንደተሰማው የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት አንስቷል፡፡

"በሀገሪቱ ውስጥ በአሁን ሰዓት ካሉት ማህበራት ሁሉ ቀድሞ ሀይማኖት ነበር ይህንን ስራ ቀድሞ ከወረዳ ጀምሮ ሳይወክል በክልል ደረጃ መደረጉ ትክክል አይደልም" ሲሉ ያስረዳሉ፡፡

"ሙስሊሞች ካልተሳተፉ የሙስሊሙን ጥያቄ ማን ሊያነሳው ይችላል?" የሚሉት ሀጂ ኑረዲን ከኮሚሽኑ ጋር ጥሩ ግንኙነት ቢኖራቸውም የተሳትፎው ጉዳይ እንዲፈታ እንደሚፈልጉ ተናግረዋል፡፡የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ከሀገራዊ ምክከር ኮሚሽኑ ጋር በዚህ ዙሪያ ምክክር ያደረገ ቢሆንም መፍትሄ አለመኑሩን ለማወቅ ችለናል፡፡

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ባለ 9 አጅንዳ 47 ጥያቄዎች ማስገባቱ የተገለፀ ሲሆን፣
ከአጀንዳዎቹ መካከልም በሀገሪቱ ለረጅም ግዜ የቆየው የገዢ እና ተገዢ ትርክት መቆም አለበት ኢትዮጵያን የገነቧት ሁሉም ኢትዮጵያውያን ናቸው ስለዚህ የሁሉ ተሳትፎ ጎልቶ ይቅረብ፣ሙስሊሙ ኢትዮጵያዊ መሆኑ በግልፅ ምክክሩ ሊፈታው የሚገባ ነው የሚልም ተካቶበታል፡፡

ሌላው የሀገር ጀግኖች ላይ እና በትምህርት መማሪያዎች ላይ ያለው የሙስሊሙ ሚና መካተት አለበት የሚልና በተለይም ከህዝብ ቆጠራ ጋር ተያይዞ ሙስሊሙ ሁል ግዜ 33 በመቶ ብቻ ነው የሚለው በትክክል ተቆጥሮ ትክክለኛ ቁጥሩ ሊቀመጥ ይገባል የሚሉ አጀንዳዎች እንደተካከቱበት ተሰምቷል፡፡

Via Ethio FM

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ምርጫ ቦርድ፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በእስር ላይ በሚገኙ ሰባት የኦነግ አመራሮች ዙሪያ ማጣራት አድርጎ ከኾነ እንዲያሳውቀው በደብዳቤ መጠየቁን ቢቢሲ አማርኛ ዘግቧል።

ቦርዱ በታሳሪዎቹ የፓርቲው አመራሮች ሕይወት ላይ የሚያሰጋ ነገር ስለመኖሩ ፓርቲው አቤቱታ እንዳቀረበለት በደብዳቤው ላይ መግለጡን ዘገባው አመልክቷል።

ቦርዱ በጉዳዩ ላይ ያደረገው ክትትል ፍሬ አለማፍራቱን ጠቅሷል ተብሏል። ኦነግ፣ አብዲ ረጋሳን ጨምሮ ሰባቱ አመራሮቹ ለሦስት ዓመታት ታስረው የሚገኙት ፍርድ ቤት በነጻ እንዲለቀቁ ከወሰነላቸው በኋላ መኾኑን በተደጋጋሚ ገልጧል።

ተቃዋሚ ፖለቲከኞቹ ታስረው የሚገኙት ኦሮሚያ ክልል ውስጥ ሲኾን፣ መንግሥት ከአንድ እስር ቤት ወደ ሌላ እስር ቤት በማዘዋወር አድራሻቸውን ሲያጠፋ ቆይቷል በማለት ዓለማቀፍ የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች ይከሳሉ።

@sheger_press
@sheger_press
የትግራይ ኃይሎች 'በአላማጣ ከተማ ትምህርት ቤቶች ውስጥ መስፈራቸውን' ነዋሪዎች ተናገሩ‼️

ከሳምንት በፊት የትግራይ ጊዚያው አስተዳደር ፕሬዚደንት አቶ ጌታቸው ረዳ ታጣቂዎቻችን ከራያ አስወጥተናል ማለታቸው ይታወሳል።

የትግራይ ኃይሎች 'በአላማጣ ከተማ መታየታቸውን እና በትምህርት ቤቶች ውስጥ መስፈራቸውን' ነዋሪዎች እና በአማራ ክልል የተሾሙት የአላማጣ ከተማ ከንቲባ ገለፁ።

በትግራይ ክልል በኩል የተሾሙት የከተማዋ ከንቲባ በበኩላቸው ክሱ “ፈጽሞ ሐሰት ነው፤ ከአካባቢው የወጣ እንጂ የገባ መደበኛ ሠራዊት የለም” ሲሉ አስተባብለዋል።
ቢቢሲ ያነጋገራቸው ሦስት የአላማጣ ከተማ ነዋሪዎች ካለፈው ሳምንት ሰኞ ወዲህ የትግራይ ኃይሎች እንቅስቃሴ በከተማዋ እንደሚታይ ተናግረዋል። 

አንድ የከተማው ነዋሪ ታጣቂዎቹ በከተማዋ “ኮከብ ጽባሕ ትምህርት ቤት፣ ምሥራቅ ትምህርት ቤት እና ከሐይቅ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጀርባ ባሉ ሦስት ትምህርት ቤቶች ላይ የቡድን መሣሪያ ጭምር ይዘው ነው የገቡት” ብለዋል።

አክለውም “ኋላ ላይ ግን የመከላከያ ሠራዊት ሁሉንም አጠቃለው መብራት የሚባለው ትምህርት ቤት አድርገዋቸዋል” በማለት አሁን ስላለው ሁኔታ ገልጸዋል።

ነዋሪው ጨምረውም “በአየር ማረፊያ አዲስ ዓለም የሚባል ትምህርት ቤት ትምህርት ቆሞ የህወሓት ታጣቂዎች እየኖሩበት ነው” ብለዋል።

በአማራ ክልል የተሾሙት የአላማጣ ከተማ ከንቲባ አቶ ኃይሉ አበራ በከተማዋ ሁለት ትምህርት ቤቶች ላይ ታጣቂዎች ሰፍረው እንደሚገኙ ገልጸዋል።

በትግራይ ክልል የተሾሙት የአላማጣ ከተማ ከንቲባ አቶ ዝናቡ ደስታ ግን በፕሪቶሪያው ስምምነት መሠረት አወዛጋቢ ከሆኑ ቦታዎች የትግራይ ሠራዊት ሙሉ በሙሉ መውጣቱን ገልጸው፤ አንደ አዲስ የገባ ሠራዊት አለመኖሩን ተናግረዋል።

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳዳር ፕሬዝደንት አቶ ጌታቸው ረዳ ባለፈው ሳምንት ማብቂያ ላይ በኤክስ ገጻቸው ባጋሩት ጽሑፍ፣ ተፈናቃዮችን ለመመለስ ሲባል በአላማጣ ከተማ አቅራቢያ ከሚገኙ ገርጃሌ እና በቅሎ ማነቂያ አካባቢዎች የትግራይ ኃይሎች እንዲወጡ መደረጉን ገልጸዋል።(BBC)

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
አቡነ ሉቃስ በተከሰሱበት የቅስቀሳ ወንጀል በ6 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ተወሰነ

አቡነ ሉቃስ በተከሰሱበት የቅስቀሳ ወንጀል ጥፋተኛ በተባሉበት ድንጋጌ በሥድስት ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ተወሰነ።

የቅጣት ውሳኔውን የወሰነው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ ሕገ-መንግሥታዊና በሕገ-መንግሥት ሥርዓት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀል ጉዳዮች የሚመለከተው ችሎት ነው።

የፍትሕ ሚኒስቴር የተደራጁና ድንበር ተሻጋሪ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጀነራል ዐቃቤ ሕግ በአቡነ ሉቃስ ላይ ከሦስት ወራት በፊት÷ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ሕግ አንቀጽ 247 (ሐ) እና አንቀጽ 258 (ሀ) ሥር እና የወንጀል ሕግ አንቀጽ 251 (ሐ) የተመላከተውን ድንጋጌ ተላልፈዋል የሚሉ ሁለት ክሶች ማቅረቡ ይታወሳል፡፡

ተከሳሹ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተ-ክርስቲያን የቅዱስ ሲኖዶስ አባል እና የምሥራቅ አውስትራሊያ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ፣ በጠቅላይ ቤተክኅነት የገዳማት መምሪያ የበላይ ኃላፊ ሊቀ-ጳጳስ ሆነው በማገልገል ላይ እያሉ ስለ ሰላም እና አንድነት የመስበክ ሐይማኖታዊ ግዴታቸውን በመተው ታኅሣስ 19 ቀን 2016 ዓ.ም በአሜሪካ ቴክሳስ እና አካባቢው በሚገኝ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተ-ክርስቲያን ሐመረ ብርሃን ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ ቤተ-ክርስቲያን ታቦት ወጥቶ በቆመበት ዐውደ-ምኅረት ላይ የአመፅ ቅስቀሳ ማድረጋቸውን የክስ ዝርዝሩ ያስረዳል፡፡

የዐቃቤ ሕግን ማስረጃ የተመለከተው ፍርድ ቤትም የተከሰሱባቸው ክሶች በአንቀጽ 247 (ሐ) ሥር ተጠቃልሎ የጥፋተኝነት ፍርድ ማስተላለፉ ይታወቃል፡፡

በመሆኑም ዐቃቤ ሕግ ካቀረባቸው ሦስት የቅጣት ማክበጃ አስተያየቶች መካከል ፍርድ ቤቱ አንዱን የቅጣት ማክበጃ አስተያየት በመያዝ እና ተከሳሹም የቀደመ የወንጀል ሪከርድ የሌለባቸው መሆኑን መነሻ በማድረግ አንድ የቅጣት ማቅለያ ተይዞላቸው ዛሬ በዋለው ችሎት የቅጣት ውሳኔ ተሰጥቷል።

በዚህም መሰረት ፍርድ ቤቱ በእርከን 23 ሥር በሥድስት ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጡ በሌሉበት ውሳኔ ሰጥቷል፡፡ (በታሪክ አዱኛ)

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ወሳኝ ጥቆማ እንዳያመልጣቹ‼️

ቴሌግራም ብቻ በመጠቀም ምንም ብር ሳታወጡ ገቢ የምታገኙበት መንገድ እያመቻቸን እንገኛለን።

አሁንኑ በዚ ቻናል ይቀላቀሉ👇👇
Join us 👉 https://www.tg-me.com/sheger_crypto
የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዚደንት አቶ ጌታቸው ረዳ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ዛሬ ያሳልፈው ውሳኔ "ትክክለኛ" እርምጃ ነው አሉ‼️ 

የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህ.ወ.ሓ.ት) የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባሉ ጌታቸው ረዳ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የዛሬው ውሳኔ ወደ ትክክለኛው አቅጣጫ የተደረገ አንድ እርምጃ ነው አሉ።

ጌታቸው ረዳ በይፋዊ የኤክስ ገፁ እንዳሰፈረው፤ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔ ይፋ የተደረገበትን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መግለጫ በማያያዝ "የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔ ሰላምን ለማጠናከር ወደ ትክክለኛው አቅጣጫ አንድ እርምጃ የተራመደ ነው" በማለት ገልጸዋል።

@sheger_press
@sheger_press
የአማራና የኦሮሚያ ክልሎች በሚዋሰኑበት የሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ አካባቢ የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ተደጋጋሚ ጥቃት እያደረሱባቸውና በርካቶች እየተፈናቀሉ እንደኾነ ነዋሪዎች ለዋዜማ ሪፖርተር ተናግረዋል።

በተለይ ሰረርኩላ እና ቱቲን የመሳሰሉ ቀበሌዎች ነዋሪዎች፣ የትምህርትና ጤና አገልግሎቶችን ማግኘት እንዳልቻሉ ተናግረዋል።

ነዋሪዎች ጥቃቱን የሚያደርሱባቸው፣ ከአማራ ክልል ተሻግረው የሚመጡ የፋኖ ታጣቂዎች እንደኾኑ ዋዜማ ሰምታለች።

ግንቦት 14 ቀን፣ እነዚሁ  “የደራ ማንነት አስመላሽ ኃይል” የሚል ስያሜ ይዘው የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች በሰረርኩላ፣ ቱቲ፣ ብርጄ፣ ሰንቀሌ እና አባዶን በተባሉ ቀበሌዎች በተመሳሳይ ሰዓት በፈጸሙት ጥቃት፣ በሰው ሕይወትና ንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሳቸውን የዐይን እማኞች ተናግረዋል።

የፋኖ እና የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ታጣቂዎች ሰላማዊ ሰዎችን አፍኖ በመውሰድ ገንዘብ እንደሚጠይቁም ነዋሪዎቹ ገልጸዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በ1 ቢሊዮን ብር የተገነባው የራሱ ቢራ መጥመቂያ ያለው ሆቴል በቢሾፍቱ

አቶ አማኑኤል ሳይፈርት ይባላሉ፣ በአውሮፓ ጀርመን 22 አመት ኖሯል። መንግስት ለዲያስፖራው ባመቻቸው የኢንቨስትመንት እድል ተጠቅመው ወደ ሀገራቸው በመምጣት አቶ አማኑኤል በኮንስትራክሽን ሴክተሩ ላይ ከሰሩ በኋላ በሆቴሉ ዘርፍ ላይ ክፍተት በመመልከት የቱሪዝም ማዕከል በሆነችው በቢሾፍቱ ከተማ ሆቴል ለመክፈት እንቅስቃሴ ጀመሩ፣ እንቅስቃሴው ተሳክቶ ከ12 አመት ግንባታ በኋላ ተጠናቆ ለቢሾፍቱ ከተማ ተጨማሪ ድምቀት ሆኖ ሳይፈርት ሆቴል ተከፍቶ ስራ ጀምሯል።

ሳይፈርት ሆቴል የተለያየ ደረጃ ያላቸው 100 የመኝታ ክፍሎች ያሉት ሲሆን ለውጪ ሀገር ዜጎች ከ40 እስከ 100 ዶላር ክፍያ ይጠይቅባቸዋል፣ ለኢትዮጵያዊያን ክፍያው ከውጪ ሀገር ዜጎች እንደሚለይ ተነግሯል።

1900 ካሬ ላይ ያረፈው ሆቴሉ 9 የስብሰባ አዳራሾች፣ ስፓ፣ ጂም፣ ዋና ገንዳ እንዲሁም የራሱ የቢራ መጥመቂያ እንዳለው አቶ አማኑኤል ተናግሯል።

ሆቴሉን ገንብቶ ለማጠናቀቅ ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ የጨረሰ ሲሆን ለ250 ዜጎች ቋሚ የስራ እድል ፈጥሯል።(FastMereja)

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በኢትዮጵያ፣ በግጭቶችና ጦርነት ከደረሰው ጉዳት መልሶ ለማገገም 44 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልግ የኢትዮጵያ ፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ከሌሎች የምርምር ተቋማት ጋር በመተባበር ባደረገው አዲስ ጥናት ማመልከቱን ሪፖርተር ዘግቧል።

አገሪቱ በግጭቶችና ጦርነቶች ባለፉት ጥቂት ዓመታት ከአጠቃላይ ምርቷ 7 ነጥብ 5 በመቶ የሚኾነውን እንዳጣች ጥናቱ ማረጋገጡን ዘገባው ጠቅሷል።

ኢትዮጵያ ጦርነትና ግጭቶች ካደረሱባት ጉዳት ለማገገም፣ የሰሜኑ ጦርነት ካለቀበት ጊዜ ጀምሮ አምስት ዓመታት ሊወስድባት እንደሚችልም ጥናቱ መግለጡን ዘገባው ጠቅሷል።

ገንዘብ ሚንስቴር ባለፈው ዓመት ባካሄደው ጥናት፣ ለመልሶ ግንባታ 29 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልግ አስታውቆ ነበር።

አዲሱ ጥናት በአማራና ኦሮሚያ ክልሎች ባለፉት ኹለት ዓመታት በተከሰቱ ግጭቶች የደረሱ ጉዳቶችን አያክትትም ተብሏል።

@sheger_press
@sheger_press
ጥቆማ‼️

Hamster‼️

Guys ይህ ትልቅ ብር ማግኛ ኤርድሮፕ ነው እየተባለ ይገኛል

በርግጠኝነት እንገራቹ ይህ List መሆኑ አይቀሬ ነው ።

አሁንኑ በመጀመር ታፕ ታፕ አድርጉ

ያልጀመራቹ ጊዜው ሳይረፍድ  አሁንኑ በዚ ሊንክ ጀምሩት👇

ለመጀመር👇👇
https://www.tg-me.com/hamster_kombat_bot/start?startapp=kentId769729488


አጨዋወቱን ለከበዳቹ ዝርዝሩን በዚ ቻናል ያገኙታል👇👇
https://www.tg-me.com/sheger_crypto
አቶ የሽዋስ አሰፋ መታሰራቸው ተሰምቷል‼️

በአንድ ወቅት ሰማያዊ ፓርቲን አፍርሰው ወደ ኢዜማ ሲቀላቀሉ "ከትንንሽ ፓርቲ መሪነት ይልቅ የትልቅ ፓርቲ አባል መሆን ይሻላል" በሚል ንግግራቸው ስማቸው ጎልቶ የሚነሳው የሽዋስ አሰፋ ትናንት ግንቦት 23 ቀን 2016 ዓ.ም ምሽት አንድ ሰዓት ካዛንቺስ አካባቢ ከሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው በፖሊስ ተይዘው እንደተወሰዱ ከቤተሰቦቻቸው ተሰምቷል።

አሁን ላይ ሦስተኛ ፖሊስ ጣቢያ እንዲመገኙ ለማወቅ ተችሏል።ለእስር ያበቃቸው ጉዳይ በግልፅ አልታወቀም።

@ethio_mereja_news
ጥቆማ‼️

Online ስራ መስራት ከፈለጉ ሸገር Crypto ቻናልንን ይቀላቀሉ።

በርግጠኝነት ይወዱታል👇

JOin 👉 https://www.tg-me.com/sheger_crypto
አመራሩ ተገደሉ‼️

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የኤፍራታና ግድም ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ የነበሩት አቶ አልብስ አደፍራሽ በቀን 24/9/2016 ዓ.ም ከለሊቱ 6:00 ሰዓት አካባቢ በቤታቸው እያሉ በተተኮሰባቸው ጥይት ህይወታቸው ማለፉን ከወረዳው ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘሁት መረጃ ያመላክታል(አዩዘበሀሻ)።
ነፍስ ይማር

@sheger_press
@sheger_press
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ እና ፕሬዝደንት ኢሳያስ በደቡብ ኮሪያ ዋና ከተማ ሴኡል ይገኛሉ‼️

ሁለቱ መሪዎች በደቡብ ኮሪያ የአፍሪካ  የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ደቡብ ኮሪያ ሴኡል ይገኛሉ።

ኢሳያስ አፈውርቂ ትናንት ወደ ሴኡል ያቀኑ ሲሆን ጠ/ሚ አብይ አህመድ ዛሬ ጠዋት ደቡብ ኮሪያ ሴኡል መድረሳቸው ታውቋል። በደቡብ ኮሪያ የሚካሄደው የአፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ነገ ይጀመራል።

@ethio_mereja_news
" በሃይማኖት ጉዳዮች ረቂቅ አዋጅ " ላይ የመጨረሻ የግብዓት ማሰባሰቢያ መድረክ ላይ ረቂቁ ከባለፈው መጠነኛ ማሻሻያዎች ተደርጎበት መቅረቡን ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል።

በመጀመሪያው ረቂቅ አዋጅ ያልነበረና የመንግሥትንና የክልሎችን ግዴታና ኃላፊነት በመዘርዘር የተቀመጠው ክፍል አንዱ ነው።

በዚህ ክፍል ላይ መንግሥት በሃይማኖት አስተምህሮና የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ መግባት እንደማይችል ተደንግጓል፡፡

በተጨማሪ ማንኛውም የሃይማኖት ተቋም ከውጭ አገር የሚላክለትን የገንዘብ ዕርዳታ፣ ስጦታ ወይም ሌሎች የገንዘብ ድጋፎችን በሕግ ሥልጣን ለተሰጠው አካል ማሳወቅ እንደሚኖርበት ተደንግጎ የነበረው የረቂቅ አዋጁ ክፍል ከተሻሻለው ረቂቅ እንዲወጣ ተደርጓል፡፡

ነገር ግን ማንኛውም የሃይማኖት ተቋም ፦

የሃይማኖት ተቋሙን ኦዲት ሪፖርት ለሰላም ሚኒስቴር እንዲያቀርብ፣

የበጀት ዓመቱ በተጠናቀቀ #በ3_ወራት የፋይናንስ እንቅስቃሴውን በገለልተኛ ኦዲተር ማስመርመር እንደሚኖርበት የተቀመጠው የረቂቁ ክፍል በተሻሻለው ላይ #ተካቷል፡፡

ሌላኛው ተሻሽሎ የቀረበው የረቂቅ ክፍል አለባበስን እና የተማሪዎች አመጋገብን ጨምሮ በማንኛውም የትምህርት ተቋም ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚደረግ ሃይማኖታዊ ተግባር የመንግሥትና ሃይማኖት መለያየት መርህንና የሃይማኖት ነፃነትንም በጠበቀ መንገድ መከናወን አለበት የሚለው ነው፡፡


የግብዓት ማሰባሰቢያ መድረኩ የመጨረሻ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ከዚህ ቀደም በመንግሥት እና በሃይማኖት መካከል ያለው ልዩነት ምን ድረስ እንደሆነ ሳይታወቅ ቆይቷል ብለዋል።

አዋጁን ማዘጋጀትም ያስፈለገው ይህን ጉዳይ በግልጽ ለማስቀመጥ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

(Reporter Newspaper)

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በምስራቅ ሃረርጌ ዞን ከእድሜ እኩያው ጋር በተፈጠረ ፀብ የግድያ ወንጀል የፈፀመዉ ተከሳሽ በፅኑ እስራት ተቀጣ

በምስራቅ ሀረርጌ ዞን በደኖ ወረዳ ጎሮ ቀበሌ ውስጥ ከእድሜ እኩያው ጋር በተፈጠረ ፀብ ቅራኔ ውስጥ ገብቶ የተጣላውን ልጅ አባት በመግደል የተከሰሰ ግለሰብ በፅኑ እስራት መቀጣቱን የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አስታውቋል ።

የምስራቅ ሀረርጌ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የኮሚኒኬሽን ጽህፈት ቤት ሃላፊ አ/ቶ  ሳሊም ሙክታር ለብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን እንደተናገሩት ተከሳሽ አልኸዲን ሃማዝ የእድሜ እኩያውን ወላጅ አባት ላይ የግድያ ወንጀል መፈፀሙን ገልፀዋል ።ተከሰሹ ግንቦት 8 ቀን 2015 ዓ.ም ከምሽቱ 4 ሰዓት ላይ የተጣላውን የእድሜ እኩያውን ለማጥቃት ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲሄድ በማጣቱ በያዘው ስለታማ መሣሪያ አ/ቶ ሙሃመድ አብዱልመጅድ ጭንቅላታቸውን በመምታት ከፍተኛ ጥቃት አድርሶባቸዋል ።

ተከሳሹ በወቅቱ ጉዳቱን በማድረስ ተሰውሮ የነበረ ሲሆን ጉዳት የደረሰባቸው አ/ቶ ሙሃመድ በአካባቢው ማህበረሰብ ትብብር ህክምና ቢያገኙም ህይወታቸው ማለፉ ተጠቁሟል ። ፖሊስ በበኩሉ ተጠርጣሪውን ክትትል በማድረግ በቁጥጥር ስር አውሎ የምርመራ መዝገቡን በሰውና በህክምና ማስረጃ በማጠናከር ለዓቃቤ ህግ ይልካል ።

ዓቃቤ ህግም የደረሰውን የምርመራ መዝገብ ተንተርሶ በተከሳሹ ላይ ክስ መስርቶበታል ። ዓቃቤ ህግ የመሠረተውን ክስ ሲመለከት የቆየው የምስራቅ ሀረርጌ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተከሳሽን ጥፋተኛ ሲል ብይን ሰጥቷል ። 

ፍርድ ቤቱ ግንቦት 21 ቀን 2016 ዓ.ም በዋለው የወንጀል ችሎት ተከሳሹን ያስተምራል ሌሎችም ያስጠነቅቃል በማለት ተከሳሽ አልኸዲን ሃማዝ በ15 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ውሳኔ አስተላልፏል ።

@ethio_mereja_news
ጥቆማ‼️

Hamster‼️

Guys ይህ ትልቅ ብር ማግኛ ኤርድሮፕ ነው እየተባለ ይገኛል

በርግጠኝነት እንገራቹ ይህ List መሆኑ አይቀሬ ነው ።

አሁንኑ በመጀመር ታፕ ታፕ አድርጉ

ያልጀመራቹ ጊዜው ሳይረፍድ  አሁንኑ በዚ ሊንክ ጀምሩት👇

ለመጀመር👇👇
https://www.tg-me.com/hamsTer_kombat_bot/start?startapp=kentId1204288009


አጨዋወቱን ለከበዳቹ ዝርዝሩን በዚ ቻናል ያገኙታል👇👇
https://www.tg-me.com/sheger_crypto
2024/12/28 02:54:28
Back to Top
HTML Embed Code: