Telegram Web Link
"እባካችሁ ወጣቶች አትቀመጡ፣ስራ ለመፍጠር ሞክሩ፣እኛ ነፃ ስልጠናና ሌሎች እገዛዎችን እናደርጋለን"EDI

ኢዲአይ ከሰሞኑ ከወዳጆቼ ጋር ለትውውቅና አጭር ስልጠና ጋብዞንን ነበር። በቅድሚ ትውልድን ወደ ስራ ፈጣሪነት ለማስገባት የተቋቋመ በመሆኑ ለተቋሙ የስራ ኃላፊዎች ትልቅ አክብሮት አለኝ።

የኢትዮጵያ ኢንተርፕርነርሺፕ ኢንስትቲዩት(EDI) ይባላል።ከፊል-ራስ-ገዝ የምርምር አስተሳሰብ በኢኮኖሚ ጥናት እና የፖሊሲ ትንተና ፣ ምርምር እና ፖሊሲ ማጠናቀር ፣ አቅም መፍጠር፣ የእውቀት ሽግግር እንዲካሄድ በስራ ፈጠራ ላይ የሚያሰለጥን እና የሚያማክር ተቋም ነው።

በኢትዮጵያ የሚዲያ ኢንድስትሪ ውስጥ ለሚመጣው አዲስ የኢንተርፕርኒያል ሚዲያ አስተሳሰብ የድርሻውን ለመወጣት ነበር ያሰባሰበን።የሚዲያ አንቀሳቃሾቹ በኢኮሲስተም ውስጥ ዋና ተዋናይ መሆን እንዲችሉ ባላቸው ላይ ጥሩ ግንዛቤን ያስጨበጠ ቆይታ ነበር።
"እባካችሁ ወጣቶች አትቀመጡ፣ስራ ለመፍጠር ሞክሩ፣እኛ ነፃ ስልጠናና ሌሎች እገዛዎችን እናደርጋለን" ከተቋሚ የስራ ሃላፊዎች በተደጋጋሚ ሲነገር የነበረ ሃሳብ ነው።የEDI ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሀሰንን ጨምሮ አሰልጣኞችና አስተባባሪዎች እነ ዳኒ ትውልድ ላይ እየሰራችሁት ያለው መልካም ስራ ለሌሎችም ምሳሌ ነውና በርቱልን።(wasumohammed)

@ethio_mereja_news
መረጃ‼️

እስክንድር ነጋ ከመንግስት ሰዎች የሰላም ድርድር ሂደት መጀመሩ ታውቋል

እስክንድር ነጋ የፋኖ ታጣቂዎችን ወክሎ ከመንግስት ድርድር መጀመሩ ተገልጿል። በ3ኛ ወገን አመቻችነት እስክንድር ነጋ ከመንግስት ሰዎች ጋር ቀጥተኛ ያልሆነ የድርድር ሂደት መጀመሩ ተጠቁሟል።

መንግስት ከእስክንድር ጋር እያደረገ ያለው ድርድር የሚሳከ ከሆነ ከእስክንድር ቡድን ጋር ከሸዋ የሻለቃ መከታው ቡድን፣ ከወሎ የምሬ ወዳጆ እና የኮ/ል ፈንታሁን ቡድኖች፣ ከጎጃም የማስረሻ ሰጤ እና የማንችሎት ቡድኖች፤ ከጎንደር በሻለቃ ሀብተ ወልድ የሚመራ ቡድን ወደ በድርድርሩ እንዲሳቱፉ ጥረት እየተደረገ ይገኛል።

ከሰላም ውጪ ሌላ አማራጭ መንገድ የለም! ሰላም ለኢትዮጵያ(natnael)

@ethio_mereja_news
ጎንደር

ሚያዚያ 4/2016 ዓም ከረፋዱ 5:00 አካባቢ ቦሌ ሚሊኒየም አዳራሽ ጀርባ ከፀጥታ አካላት ጋር በነበረ የተኩስ ልውውጥ ህይወታቸው ያለፈው 2 የፋኖ አባላት ዛሬ በጎንደር ቤተሰቦች አስከሬናቸውን ሳያገኙ ፍትሃትና ባህላዊ የሽኝት ሥነ ሥርዓት አካሂደዋል።።

ናሁሰናይ አንዳርጌ እና አቤኔዘር ጋሻው በተኩስ ልውውጥ ከተገደሉ በኃላ ወላጆቻቸው ወደ አዲስ አበባ በመምጣት አስከሬናቸውን አግኝተው ቀብር ለመፈጸም ፌደራል ፖሊስ ፣ አዲስ አበባ ፖሊስ ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት ድረስ ጥያቄ ቢያቀርቡም ምላሽ ሳያገኙ 2 ወር ለሚጠጋ ጊዜ መጠበቃቸውን እና በመጨረሻም ተስፋ መቁረጣቸውን ተናግረዋል።

ዛሬ ግንቦት 26 ቀን 2016 ዓ.ም. ጎንደር ውስጥ የናሁሰናይ አንዳርጌ አስከሬኑ በሌለበት በባህላዊ መንገድ በቤተሰብና በወዳጆች ፍትሃቱና የሽኝት ሥነ ሥርዓቱ በአባ ጃሌ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ተፈጽሟል።

አንድ የቤተሰብ አባል ደግሞ " ለቀስተኛው ካለ አስከሬን በተካሄደው የስንብት ሥነ ሥርዓት ላይ ለመታደም ወደ ቤተ-ክርስቲያን እያመራ ሳለ የመንግሥት ፀጥታ ኃይሎች የናሁሰናይ ፎቶ እና ስም ያለበትን 2 ባነር በኃይል ተቀብለዋል። ከዚህ ውጭ ምንም የተፈጠረ ነገር የለም " ብለዋል።

የአቤኔዘር ጋሻው የሽኝት በተመሳሳይ ቤተሰቡ አስከሬኑ ባላገኘበት ሁኔታ ቀደም ብሎ መከናወኑን የቤተሰቡ አባላት ገልጸዋል ሲል ቢቢሲ አማርኛ አስነብቧል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሪያል ማድሪድ ደጋፊዎችን በማጓጓዝ የታሪክ አካል በመሆናችን ተደስተናል አለ

"ዓለምን በአንድ ቋንቋ የሚያግባባው እግር ኳስ ከነገሰበት የአውሮፓ ክለቦች ሻምፒዮና መንደር ተገኝተናል። ትልቁን ዋንጫ ለ15ኛ ጊዜ በማሸነፍ ድልን የተጎናጸፈው የሪያል ማድሪድ ክለብ ደጋፊዎች ምርጫ በመሆን ደጋፊዎቹን ከማድሪድ ወደ እግር ኳሱ ድግስ እንግሊዝ ምድር በማጓጓዝ የዚህ ታሪክ አካል በመሆናችን ደስ ይለናል።
"የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሀገር ውስጥ እና በዓለም እየሰጠ ከሚገኘው መደበኛ የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት በተጨማሪ የቻርተር በረራዎችን በመስጠት ተመራጭ አየር መንገድ መሆኑን በማስመስከር ላይ ይገኛል።" ሲል የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታውቋል።
ethiopianairlines

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
መንግስት ከ 2 ሚሊዮን በላይ አሽከርካሪዎችን በተለያዩ ምክኒያቶች ቀጥቶ ከ 1.1 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ አገኘ

የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር የ 9 ወራት የስራ የስራ እና እቅድ አፈጻጸሙን ባቀረበበት በዛሬው ም/ቤት ጉባዔ ላይ በወራቱ 2 ሚሊዮን 17 ሺህ 930 አሽከርካሪዎች በተለያዩ ምክንያቶች መቀጣታቸውን የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስትሩ ዶ/ር አለሙ ስሜ ተናግረዋል።

ሚኒስትሩ በሪፖርታቸዉ ከተቀጡ አሽከርካሪዎች 1 ቢሊዮን 129 ሚሊዮን 544 ሺህ 187 ብር መንግስት ገቢ አግኝቷል ማለታቸውን ብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ሰምቷል።

በወራቱ በሀገር አቀፍ ደረጃም በድግግሞሽ 9 ሚሊዮን 854 ሺህ 902 ተሽከርካሪዎች ላይ የቴክኒክ ቁጥጥር መደረጉንም ገልጸዋል። በተጨማሪም ከ 103 ሺህ በላይ በሆኑት አሽከርካሪዎች ላይም ድንገተኛ የአልኮል ፍተሻ ተደርጓል ብለዋል።

በተጨማሪም ባልታወቁ እና የሶስተኛ ወገን በሌላቸዉ አሽከርካሪዎች በደረሱ የትራፊክ አደጋዎች ለተጎዱ ሰዎች ሙሉ በሙሉ የካሳ ክፍያ ማግኘታቸውንም የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስትሩ ዶ/ር አለሙ ስሜ መናገራቸውን ብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ሰምቷል።

@ethio_mereja_news
በአዲስ አበባ ከተማ የአከራይ እና ተከራይ ህጋዊ ውል ምዝገባ ሰኔ 1 ቀን 2016 ዓ.ም እንደሚጀመር የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ አስታውቋል።

የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ መጽደቁ ይታወቃል፡፡

በዚህም አስተዳደሩ አዋጁን በመመሪያ በማስደገፍ ወደ ስራ ለማስገባት ዝግጅቶቹን ማጠናቀቁ ተገልጿል።

ከሰኔ 1 እስከ 30 ቀን 2016 ዓ.ም በከተማዋ ውስጥ የሚገኙ የግል ቤት አከራዮች ከተከራዮቻቸው ጋር ህጋዊ ሰነዶቻቸውን ይዘው በመቅረብ ምዝገባ ማድረግ ይችላሉ ተብሏል።

ቤት አከራዮች ፦

➡️ ህጋዊ የምዝገባ ውል ለመፈጸም ወደ ወረዳ ጽ/ቤቶች በሚሄዱበት ወቅት ቤቱ የራሳቸው ስለመሆኑ ወይንም ህጋዊ ተወካይ መሆናቸውን የሚገልጽ ሰነድ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል።

ተከራዮች ፦

➡️ ማንነታቸውን የሚገልጽ መታወቂያ ወይም ሌላ ህጋዊ ማንነታቸውን የሚያረጋግጥ ሰነድ ይዘው መቅረብ አለባቸው።

በስራ ሰዓት መመዘግብ የማይችሉ አከራይና ተከራዮች ቅዳሜና እሁድ እንዲሁም በስራ ቀን ማታ ከ12 ሰዓት በኋላ ህጋዊ የውል ምዝገባውን መፈጸም ይችላሉ።

Source: tikvahethiopia

@ethio_mereja_news
አዲስ አበባ😭

በፌስቡክ ስሙ አቤነዘር ይባላል በትክክለኛ ስሙ አቤል ሲሆን ሰሞኑን አዲስ አበባ በ22 አካባቢ በመኪና ታገዘ ዝርፊያ ሰለባ ሆኖ ነበር። ሞባይሉ ነጥቀው ሲሮጡ እሱም ሲከተል በመኪና ገጭተው ጥለውት አመለጡ።በሀኪም ሲረዳ ቆይቶ ህይወቱ አለፈ።ያሳዝናል።ሞባይል ነጥቀውና በትንሽ ገንዘብ ሞባይል የሚሸጡ እንዲሁም በየአካባቢው የተሰሩቁ ሞባይል የሚገዙ የሌባ ተባባሪዎችን ለህግ ማቅረብ ይገባል።ለአቤል ቤተሰብ መፅናናቱን ይስጥል።(wasumohammed)

@sheger_press
ኢሰመኮ፣ በአማራ ክልል ታውጆ ከነበረው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጋር በተያያዘ መንግሥት አስሮ ያቆያቸውን ሰዎች የመልቀቁን ሂደት እንዲቀጥል ዛሬ ባወጣው አጭር መግለጫ አሳስቧል።

ኢሰመኮ፣ "ወደ መደበኛው የሕግ አተገባበር ሂደት መመለስ"፣ በአዋጁ በአንዳንድ የክልል አካባቢዎች ተጣሉ "የእንቅስቃሴ ገደቦች እንዲነሱ" እና "ማኅበረሰባዊ አገልግሎቶች" ወደነበሩበት እንዲመለሱ ጠይቋል።

ኢሰመኮ ይህንኑ ጥሪውን ያስተላለፈው፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባለፈው ጥር 24 ለአራት ወራት ያራዘመው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የቆይታ ጊዜ ግንቦት 24 ቀን መጠናቀቁን ተከትሎ ነው።

@ethio_mereja_news
ተወዳጁ ተዋናይ አማኑኤል ሐብታሙ ከ42 ቀናት እስር በኋላ ዛሬ ዳይሬክተሩን ዳግማዊ ፈይሳ ጨምሮ ከ20 ተጠርጣሪዎች ጋር ፍርድ ቤት ቀርቧል

"በቡድን በመደራጀት ወጣቶችን መልምሎ በማሰማራት፣ ገንዘብ ለሽብር ቡድኑ ሎጂስቲክስ መግዣ ለማዋል... ሕገ-መንግስቱን እና ሕገ-መንግታዊ ስርዓቱን በኃይል በትጥቅ ትግል ለመቀየር ሲንቀሳቀሱ በመገኘታቸው ተጠርጥረው".... የሚሉ መዘርዝሮችን የያዘ የጊዜ ቀጥሮ ማመልከቻ ፖሊስ ለፍርድ ቤቱ አቅርቧል።

ተዋናይ አማኑኤል እስራኤል አገር "እብደት በሕብረት" የተሰኘ ቴአትሩን ለማሳየት አውሮፕላን ሊሳፈር ሲል ሚያዝያ 15 ቀን 2016 ዓ/ም ከአዲስ አበባ ኤርፖርት በፖሊሶች ተይዞ ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ተወስዶ መታሰሩ ይታወሳል።

አማኑኤል ከታሰረ ከ42 ቀናት በኋላ በዛሬው ዕለት ግንቦት 28 ቀን 2016 ዓ/ም ፖሊስ ፍርድ ቤት አቅርቦት የነበረ ሲሆን ፍርድ ቤቱ ፖሊስ የጠየቀውን ተጨማሪ ጊዜ ቀጠሮ በመፍቀድ ለሰኔ 11 ቀን ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

ተዋናይ አማኑኤል በተጨማሪም በቅርቡ በፖሊስ ተይዞ ለእስር የበቃው የ"እብደት በሕብረት" ቴአትር አዘጋጅ አንጋፋው ከያኒ ዳግማዊ ፈይሳን ጨምሮ ሌሎች 20 ሰዎችን በአንድ መዝገብ ለፌደራል መደበኛ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ጊዜ ቀጠሮ ወንጀል ችሎት ቀርበዋል።

ጠበቆች ተወክለው በመቅረብ የዋስትና መብታቸው ከዚህ ሁሉ የእስር ቀናት በኃላ እንኩዋን ሊፈቀድላቸው የሚገባ መሆኑንና እስሩም አግባብነት የሌለው መሆኑ አንስተው ተከራክረዋል። ሕገ መንግስታዊ እና ስነ ስርአታዊ የሕግ ድንጋጌዎች ተጠቅሶ ሰፊ ክርክር ከተደረገ በኋላ ችሎቱ ሁሉንም ተጠርጣሪዎች ለሰኔ 11 ቀን 2016 ዓ/ም ተለዋጭ ቀጠሮ እንደተሰጣቸው ማረጋገጥ ችያለሁ።
ወልድያ‼️

በወልዲያ ከተማ የመንግሥት ኃላፊዎች ላይ ያነጣጠሩ ሦስት የቦምብ ጥቃቶች መፈጸማቸው ተነገረ!!

በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ወልዲያ ከተማ በዚህ ሳምንት ብቻ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችን እና ተቋምን ዒላማ ያደረጉ ሦስት የቦምብ ጥቃቶች መፈጸማቸውን ነዋሪዎች ተናገሩ።

በዞኑ አስተዳደር ጽህፈት ቤት እና በመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች መኖሪያ ቤት ላይ እንደተፈጸሙ በተነገረው ጥቃቶች የሰዎች ሕይወት እንዳላለፈ ተገልጿል። የመጀመሪያው ጥቃት የሰሜን ወሎ ዞን ብልጽግና ጽ/ቤት ኃላፊ ሙጋድ በተባለ ሰፈር ተከራይተው በሚኖርበት ቤት ላይ እንደተፈጸመባቸው የተናገሩት ነዋሪዎች፤ በጥቃቱ ንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል ብለዋል። ግንቦት 25/2016 ዓ.ም. እሁድ ምሽት ላይ ተፈጸመ በተባለው ጥቃት የገዢው ፓርቲ ኃላፊ ላይም ሆነ በቤተሰባቸው ላይ ጉዳት እንዳልደረሰ ሁለት ነዋሪዎች ሰዎች ተናግረዋል።

ሌላ የአካባቢው ነዋሪ ግን በጥቃቱ የብልጽግና ጽህፈት ቤት ኃላፊው ሳይጎዱ አልቀረም ያሉ ሲሆን፤ ጥቃቱን ተከትሎ በአካባቢው የነዋሪዎች እንቅስቃሴ ታግዶ እንደነበር ገልጸዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ቅዱስ ሲኖዶስ ምን ወሰነ ?

ግብረ ሰዶማዊነትና የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ ፦

➡️ በሕገ ተፈጥሮም ሆነ በሰው ልጅ የሰብዓዊ አኗኗር ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው፣

➡️ ፈጣሬ ዓለማት እግዚአብሔር መለኮታዊ ፈቃዱ በተገለጠባቸው ቅዱሳት መጻሕፍት ፈጽሞ #የተከለከለ

➡️ በቀኖናተ ቤተ ክርስቲያን፣ በፍትሕ መንፈሳዊና በፍትሐ ብሔር ድንጋጌዎች፣ በሥነ ልቦና ደንቦች የተወገዘ፣

➡️ ሥነ አእምሮዊ ሚዛንን የሚያዛባ፣

➡️ ግለሰባዊ ማንነትን፣ ቤተሰባዊ ሕይወትን፣ ማኅበራዊ ትሥሥርን የሚጎዳ ተግባር በመሆኑ ቅዱስ ሲኖዶስ አጥብቆ #እንደሚያወግዝ ገልጿል።

#የተመሳሳይ_ጾታ_ጋብቻ እና #የግብረ_ሰዶማዊነትን ኃጢአት በተመለከተ የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን አቋም በሚገልጽ መልኩ ራሱን ችሎ ዓለም አቀፋዊ ይዘቱን ባገናዘበ ሁኔታ ዝርዝር መግለጫ እንዲሰጥ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል።

(tikvahethiopia)

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በአማራ ክልል በጦርነት ምክንያት 2 ነጥብ 6 ሚሊየን ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ርቀዋል ተባለ

የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ በያዝነው አመት ብቻ በጦርነት ምክንያት 2 ነጥብ 6 ሚሊየን ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጭ መሆናቸውን አስታውቋል።

ቢሮው በአመቱ 6 ነጥብ 2 ሚሊየን ተማሪዎችን መዝግቦ ለማስተማር አቅዶ የነበረ ቢሆንም ወደ ትምህርት ገበታ መምጣት የቻሉት 58 በመቶ ብቻ የሚሆኑት ናቸው ብሏል።

በዚህም 2 ነጥብ 6 ሚሊየን የሚደርሱ ተማሪዎች በሰላም እጦት የተነሳ ትምህርታቸው ላይ መገኘት አለመቻላቸውን ነው የገለጸው።

በክልሉ ጦርነት መከሰቱ በትምህርት ቤቶች እና የመማሪያ መገልገያ ቁሳቁሶች ላይ ጉዳት ማስከተሉንም የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ጌታቸው ቢያዝን ተናግረዋል።

ምስራቅ፣ ምዕራብ፣ ሰሜን ጎጃም፣ ደቡብ ጎንደር በከፊል በጦርነቱ የትምህርት መሰረተ ልማቶች ጉዳት መድረሱን ከቢሮው ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል።

ለመሰረተ ልማት ጥገና በቂ ፋይናንስ አለመኖር፣ አንዳንድ አካባቢዎች የተከሰተው ድርቅ እና ጎርፍ በክልሉ የትምህርት እንቅስቃሴ ላይ ሌላኛው ተፅእኖ የፈጠረ ጉዳይ መሆኑን አቶ ጌታቸው አንስተዋል።

በቅርቡ በጦርነት ሳቢያ ምን ያህል ትምህርት ቤቶች ጉዳት እንደደረሰባቸው እና በትምህርት ስርአቱ ላይ ያመጣውን ተጽእኖ የተጠና ጥናት ይፋ ይደረጋል ብለዋል (አራዳ ኤፍኤም)

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
Hamster‼️

በዚ ቻናል ያስተዋወቅንላቹ ስለ ሀምስተር ኤርድሮፕ ወሳኝ አዲስ መረጃ ተሰምቷል።

በዚኛው ቻናላችን በዝርዝር
ለቀነዋል ያንብቡት👇👇
https://www.tg-me.com/sheger_crypto
2024/09/30 05:14:47
Back to Top
HTML Embed Code: