Telegram Web Link
"ነገ ተቋማት ዝግ ሆነው ይውላሉ"

የመንግስት ኮሚኒኬሽን ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉ "አዲሱ የበዓላት ሕግ ገና አልጸደቀም፤ ስለዚህ ዝግ ነው" ብለዋል።

የኮሙኒኬሽን ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ከበደ ደሲሳ <<በካላንደር ላይ የተለወጠ ነገር ስለመኖሩ እርግጠኛ አይደለሁም።ካላንደር ይዘጋዋል።ካላንደር እንደሚዘጋው ነው የምናውቀው ለምን እንዳወዛገበ አይገባኝም ። መስሪያ ቤቶች በራሳቸው ውሳኔ ሥራዎችን ሊያቅዱ ይችላሉ። ከሠራተኞቻቸው ጋር ተስማምተው>> ሲሉ አስረድተዋል።

ሁለቱም የስራ ኃላፊዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ከሰጡት ቃል የተወሰደ ነው።

@ethio_mereja_news
ጥቆማ‼️

Hamster‼️

Guys ይህ ትልቅ ብር ማግኛ ኤርድሮፕ ነው እየተባለ ይገኛል
ምንም ብር ስለማታወጡበት ብትሞክሩት አይከፋም ባይ ነን

ያልጀመራቹ ጊዜው ሳይረፍድ አሁንኑ በዚ ሊንክ ጀምሩት👇

ለመጀመር👇👇
https://www.tg-me.com/hamster_kombat_bot/start?startapp=kentId769729488


አጨዋወቱን ለከበዳቹ ዝርዝሩን በዚ ቻናል ያገኙታል👇👇
https://www.tg-me.com/sheger_crypto
ፍርድ ቤቱ የዋስትና ጥያቄውን በድጋሚ ውድቅ አደረገ

የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ቤተክህነት ጽሕፈት ቤት ሥራ አስኪያጅ የኾኑት ቀሲስ በላይ መኮንንና ግብረ አበሮቻቸው ማረሚያ ቤት ኾነው ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ ወስኗል፡፡

ፍርድ ቤቱ ትናንት ሰኞ ብይኑን የሰጠው፣ ተከሳሾቹ የተከሰሱበት ከባድ የሙስና ወንጀል ከ10 ዓመት በላይ የእስር ቅጣት ሊያስጥል እንደሚችል በመግለጽ ነው።
ከምዝበራ መኩራው ጋር በተያያዘ የተከሰሱት
1ኛ. ቀሲስ በላይ መኮንን፣
2ኛ. በግብርና ኢንቨስትመንት ላይ የተሰማራው እያሱ እንዳለ ወ/መስቀል፣
3ኛ. በኮሚሽን ስራ ላይ የተሰማራው በረከት ሙላቱ ጃፋር፣
4ኛ. አለምገና ሳሙኤል ዲንሳ
5ኛ. የኒሞና ንግድ ስራ ኃላ/የተ/የግል ማህበር ስራ አስኪያጅ አበራ መርጋ ተስፋዬ ናቸው።

ከ1ኛ እስከ 3ኛ ያሉ ተከሳሾች ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበው ነበር።

ያቀረቡት የዋስትና ጥያቄም ውድቅ ተደርጎ በማረፊያ ቤት እንዲቆዩ ታይዟል።

ፍርድ ቤቱ፣ የተከሳሾች ጠበቆች ያቀረቡትን የዋስትና ጥያቄም በድጋሚ ውድቅ አድርጓል። ኾኖም ፍርድ ቤቱ የቀሲስ በላይን የጤና ኹኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት እስከ ቀጣዩ ተለዋጭ ቀጠሮ ግንቦት 29 ድረስ በፌደራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ እንዲቆዩ አዟል።

ቀሲስ በላይ ባለፈው ሚያዝያ በቁጥጥር ሥር የዋሉት፣ በአፍሪካ ኅብረት ግቢ ውስጥ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ ሐሰተኛ ሰነዶችን በመጠቀም፣ ከኅብረቱ የባንክ ሒሳብ  ከስድስት ሚሊዮን ዶላር በላይ ወደ ሌላ የባንክ ሒሳብ ለማዛወር ሙከራ አድርገዋል ተብለው ነበር።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
አሜሪካ ለግንቦት 20 እንኳን አደረሳችሁ አለች

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ግንቦት 20ን አስመልክቶ በዛሬው ዕለት“መልካም ምኞታቸውን" ለኢትዮጵያ ገልፀዋል።
ግንቦት 20 ቀን 1983 በኢህአዴግ ጥላ ስር የታጠቁ ሃይሎች ጥምረት ከ17 አመት የትጥቅ ትግል በኋላ የደረግ አገዛዝ እንዲወድቅ የተረገበት ዕለት ነው። በዚህም በሀገራችን በተለይ በእህአዴግ የስልጣን ዘመን በድምቀት ከሚከበሩ በዓላት አንዱ ግንቦት 20 ነበር። ግንቦት 20 ዛሬ ላይ ላለንበት የብሄር ፖለቲካ የቀውስ ምንጭ ነው የሚሉም አሉ።
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሆኑት ብሊንከን ግንቦት 20ን አስመልክቶ የሚከተለውን ብለዋል👇
"በኢትዮጵያውያ እና በአሜሪካ መካከል ያለውን ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር እንሰራለን።
ዩናይትድ ስቴትስ ለኢትዮጵያ ሰላምን በውይይት ለማምጣት፣የጋራ ኢኮኖሚያዊ ደህንነትን ለማረጋገጥ እና እንደ የአየር ንብረት ለውጥ እና ጤና ያሉ ዓለም አቀፍ ጉዳዮችን በትብብር ለመፍታት የሚደረገውን ጥረት እንደምትደግፍ ቃል ገብተዋል።
"ኢትዮጵያ አሁን የገጠሟትን ፈተናዎች ለማሸነፍ እና ለወደፊት ብሩህ ተስፋን ሰንቃ እያደረገች ያለውን ጉዞ እና ጥረት የአሜሪካ ህዝብ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጎን ይቆማል"ሲሉ በመግለጫቸው ላይ ማንሳታቸውን አዩዘሀበሻ ተመልክቷል።

@ethio_mereja_news
መንግስታት የተቀያየሩበትና ስልጣን የያዙበት ቀን እንደ ሕዝባዊ በዓል ሊቆጠር እንደማይገባ ተገለጸ

መንግስታት ከስልጣን የወረዱበትም ይሁን ወደ ስልጣን የመጡበትን ቀን ህዝባዊ በዓል ሁኖ ሊከበር እንደማይገባ መናኸሪያ ሬዲዮ ያነጋገራቸው የታሪክ ባለሙያ ተናግረዋል፡፡

ግንቦት 20 ለአመታት በህዝባዊ በዓላት ዉስጥ ሳይካተት በህግ ሳይጸድቅ ሲከበር የቆየ ቢሆንም የህዝብ በአል ሊደረግ እንደማይችልና ኢህአዴግ የደርግ መንግስትን ገልብጦ ስልጣን የያዘበት ወይንም ማዕከላዊ መንግስትን የተቆጣጠረበት እለት ሆኖ በየአመቱ ስራ እና ትምህርት ዝግ ሆኖ ሲከበር መቆየቱ አግባብነት እንዳልነበረው የታሪክ ባለሙያው አቶ ደረጄ ተክሌ ተናግረዋል፡፡

ግንቦት 20 ለአመታት ሲከበር የቆየበት መንገድ ህጋዊ መሰረት የሌለዉ መሆኑን የሚናገሩት ባለሙያው በዓሉ በልማድ በህዝብ በዓላት ዝርዝር ዉስጥ ቢገባም በምክር ቤት ጸድቆ እንዲከበር ያልተወሰነና የጥቂት ሰዎች መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ከአንደኛው የመንግስት ስርዓት ወደ ሌላኛው ሽግግር ሲደረግ ስህተቶች ሊደገሙ እንደማይገባና ልዩነቶችን ያጠበበ ሊሆን እንደሚገባ የሚናገሩት ደግሞ ሌላኛው የታሪክ ባለሙያ አቶ በላይ ስጦታው ናቸው፡፡

የታሪክ ቅብብሎሽ በትኩረት ካልተጠና ሃገራዊ ማንነቶች እየጠፉና እየተሸረሸሩ እንደሚያልፉ የሚናገሩት ባለሙያው ከአንዱ ወደ ሌላኛው የመንግስት ስርዓት ሽግግር ሲደረግ በመሪው እና ተመሪው መካከል ያለው መተማመን እንዳይጠፋ ነው በትኩረት መሰራ ያለበት ብለዋል፡፡

መንግስታት ስልጣን የተቆጣጠሩበትን ቀን ከመዘከር ይልቅ ካለፈው ስርዓት በቅብብሎሽ ሊማሩትና ሊያስቀጥሉት የሚገባ የስራ ባህል ሊኖራቸው እንደሚገባ ባለሙያዎቹ አመላክተዋል።

መናኸሪያ ሬዲዮ
@ethio_mereja_news
ጥቆማ‼️

Hamster‼️

Guys ይህ ትልቅ ብር ማግኛ ኤርድሮፕ ነው እየተባለ ይገኛል
ምንም ብር ስለማታወጡበት ብትሞክሩት አይከፋም ባይ ነን

ያልጀመራቹ ጊዜው ሳይረፍድ  አሁንኑ በዚ ሊንክ ጀምሩት👇

ለመጀመር👇👇
https://www.tg-me.com/hamster_kombat_bot/start?startapp=kentId769729488


አጨዋወቱን ለከበዳቹ ዝርዝሩን በዚ ቻናል ያገኙታል👇👇
https://www.tg-me.com/sheger_crypto
ትናንት ምሽት በኤርትራ መንግሥት ደጋፊዎች እና ተቃዋሚዎች መካከል በእስራኤሏ ቴላቪቭ ከተማ በተፈጠረ የቡድን ጠብ አንድ ሰው እንደተገደለ የእስራኤል ዜና ምንጮች ዘግበዋል።

በብጥብጡ አምስት ሰዎች እንደቆሰሉና ከእነዚህ ውስጥ ሦስቱ ከባድ ጉዳት እንደደረሰባቸው ዘገባዎቹ አመልክተዋል። 20 ያህል ኤርትራዊያን ደሞ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ውለዋል ተብሏል።

ብጥብጡ የተፈጠረው፣ የመንግሥት ተቃዋሚዎች የመንግሥት ደጋፊዎች ስብሰባ ወደሚያደርጉበት አዳራሽ ሂደው ተቃውሞ ባሰሙበት ወቅት እንደኾነ ተገልጧል።

@ethio_mereja_news
ባለሃብቱ አብነት ገብረመስቀል ዓቃቤ ሕግ የመሠረተባቸው ክስ ተቋርጦ ከስምንት ወራት እስር በኋላ ትናንት ከቀትር በኋላ ከእስር መፈታታቸውን ዋዜማ ተረድታለች።

የጸረ-ሙስና ዓቃቤ ሕጎች በአብነትና ሌሎች አራት ግለሰቦች ላይ የመሠረቱትን የሙስና ክስ ያቋረጡት፣ አብነት ከባድ የጤና እክል ስላጋጠማቸው እንደኾነ ታውቋል።

ዓቃቤ ሕግ አብነትና ግብረ አበሮቻቸው አዲስ አበባ ወሎ ሠፈር አካባቢ የሚገኝ ቦሌ ታዎርስ በሊዝ የያዘውን 1 ሺህ 972 ስኩዌር ሜትር መሬት በተጭበረበረ መንገድ ለሌላ ግለሰብ አስተላልፈዋል፤ ሕጋዊ ያልኾነ ገንዘብን ሕጋዊ አስመስለው አቅርበዋል በማለት ነበር ክስ የመሠረተባቸው።

አብነት በመሬቱ ላይ የ40 በመቶ ድርሻ የነበራቸው ሲኾን፣ ሼክ መሃመድ አል አሙዲን ደሞ የ60 በመቶ ድርሻ ነበራቸው።

@ethio_mereja_news
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ)፣ በአማራና ኦሮሚያ ክልሎች በግጭት ተሳታፊ የኾኑ ኹሉም አካላት ያለምንም ቅድመ ኹኔታ ተኩስ አቁም እንዲደረጉ ዛሬ ባወጣው ሪፖርት ጠይቋል።

ኢሰመኮ፣ የግጭት ተሳታፊ አካላት በማናቸውም የግጭት ሂደት ዓለማቀፍ የሰብዓዊ መብቶችና የሰብዓዊነት ሕጎች ጥሰትን ከመፈጸም እንዲቆጠቡ፣ ተጠያቂነትን እንዲያረጋግጡ፣ በሲቪሎች ሕይወት፣ አካል እና ንብረት ላይ ጥቃት ከማድረስ እንዲቆጠቡም ጥሪ አድርጓል።

ኮሚሽኑ፣ መንግሥት በኦሮሚያ እና አማራ ክልሎች በትጥቅ ግጭቶቹ ዓለማቀፍ የሰብዓዊ መብቶችና የሰብዓዊነት ሕጎችን በጣሱ አካላት ላይ የወንጀል ምርመራና የክስ ሂደት እንዲጀመር እና ከግጭቶቹ ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ሥር ውለው እስካሁን ክስ ያልተመሠረተባቸው ግለሰቦችንም እንዲለቅ አሳስቧል። 

ኢሰመኮ፣ ከሕግ ውጭ ግድያ፣ የሲቪል ሰዎች ሞት፣ የአካል ጉዳት፣  የዘፈቀደ፣ የጅምላ እና የተራዘመ እሥራት፣ አስገድዶ መሰወር እንዲሁም እገታ አሳሳቢነታቸው እንደቀጠለ መኾኑን ገልጧል።

ኢሰመኮ ይህን ጥሪ ያቀረበው፣ በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች ከግጭቶች ጋር በተያያዘ እንዲኹም በሌሎች ክልሎች በቅርብ ወራት ውስጥ የመንግሥት ኃይሎች፣ ታጣቂ ቡድኖችና ሌሎች ማንነታቸው ያልታወቁ ኃይሎች በሲቪሎች ላይ የፈጸሟቸውን ግድያዎችና ያደረሷቸውን አካላዊ ጉዳቶች አስመልክቶ ባወጣው ሰፊ ሪፖርት ነው።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
We call to our Investors!
Just one step: From purchasing NFTs to creating and co-founding the bank of the future: TLVD Trusty Bank!
Closed listing by founders from May 9, 2024!
Open sale of NFTs on the DeFi marketplace OpenSea begins on June 10, 2024!
UNION IS STRENGTH!
+372 5837 7377
https://tlvd.uk
https://opensea.io/collection/tlvd
https://www.tg-me.com/nftttbank
በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች በግጭት ዐውድ ውስጥና ውጭ የሚፈጸሙ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች አሳሳቢነትና ሥጋቶችን በተመለከተ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ሪፖርት አውጥቷል።

በሪፖርቱ ፦

- ከሕግ ውጭ ግድያ (በድሮን ጨምሮ) ፣ የሲቪል ሰዎች ሞት፣ የአካል ጉዳት፣ የንብረት ውድመትና ዘረፋ፤
- የዘፈቀደ፣ ሕገወጥ፣ የጅምላና የተራዘመ እስራትና የተፋጠነ ፍትሕ እጦት፤
- እገታ
- አስገድዶ መሰወር እና ያሉበት ቦታ ሳይታወቅ አስሮ ማቆየት
- የሀገር ውስጥ መፈናቀል ... ተዳሰዋል።

° በጸጥታ መደፍረስ፣
° ከመንግሥት አካላት ተገቢውን ምላሽና ትብብር በወቅቱ ባለማግኘት
° በሌሎች ምክንያቶች ምርመራቸውና ክትትላቸው የዘገዩና የተጓተቱ በርካታ ጉዳዮችን መኖራቸው ተገልጿል።

እነዚህን ጉዳዮች በመርመርና ክትትል በማድረግ በተገቢው ጊዜ ይፋ የሚያደርግ ይሆናል ተብሏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከኮሚሽኑ የተላከለትን ዝርዝር ሪፖርት ከላይ አያይዟል፤ በጥሞና ያንብቡት።

ኢሰመኮ በግጭት ዐውድ ውስጥ እና ከዐውድ ውጭ የሚፈጸሙ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችንና ሥጋቶችን በአስቸኳይ ማቆም ይገባል ብሏል።

የአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎችን ጨምሮ ሁሉንም የትጥቅ ግጭቶች በውይይት በመፍታት ዘላቂ ሰላምና የሰብአዊ መብቶች መከበርን ማረጋገጥ እንደሚገባም አስገንዝቧል። (#EHRC)
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል፣ ፕሮጀክቶች በሚገነባባቸው አካባቢዎች ከካሳ ይገባኛል ጥያቄ ጋር በተያያዘ ከ11 ቢሊዮን ብር በላይ በክርክር፣ በቅሬታና በአቤቱታ ላይ እንደሚገኝ አስታውቋል።

ኩባንያው የተጋነኑ የካሳ ጥያቄዎች የገጠሙት፣ ከውሃ፣ ከንፋስ፣ ከደረቅ ቆሻሻና ከከርሰ ምድር እንፋሎት የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶቹ ጋር በተያያዘ እንደኾነ ገልጧል።

የተጋነኑ የካሳ ጥያቄዎች ፕሮጀክቶችን በጊዜ እንዳያጠናቅቅ እንቅፋት እንደኾኑበትና የበጀት ጫና ውስጥ እንዳስገቡትም ኩባንያው ተገልጧል። ኩባንያው ከካሳ ክፍያ ጋር በተያያዘ ከ340 ሚሊዮን ብር በላይ በፍርድ ቤት ታግዶብኛል ብሏል።

ኩባንያው ይህን ያለው፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለሕዝብ ጥቅም መሬት የሚለቀቅበትን፣ ካሳ የሚከፈልበትንና ተነሺዎች የሚቋቋሙበትን ኹኔታ በሚወስነው የተሻሻለ ረቂቅ አዋጅ ላይ በተወያየበት ወቅት ነው።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
መንግስት በአማራ ክልል የጣለውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲያነሳ ተጠየቀ‼️

የመብቶች እና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል (ካርድ) በኢትዮጵያ እንደ አዲስ እየተባባሱ የመጡት የሲቪክ ምህዳሩን የሚያጣብቡ ድርጊቶች እንዳሳሰቡት አስታውቋል።

የፌደራል መንግሥት ከአንድ ዓመት በፊት የክልል ልዩ ሀይሎችን “መልሼ አደራጃለሁ” የሚል ውሳኔ ማሳለፉን ተከትሎ ነበር በአማራ ክልል ግጭት የተከሰተው።

ግጭቱ በመንግስት የጸጥታ ሀይሎች እና የፋኖ ታጣቂዎች መካከል የተካሄደ ሲሆን ግጭቱ ተባብሶ መቀጠሉን ተከትሎ በአማራ ክልል ለስድስት ወራት የሚዘልቅ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታወጁ ይታወሳል።

ከሐምሌ 28 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ የታወጀው ይህ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለተጨማሪ አራት ወራት የተራዘመ ሲሆን ይህ አዋጅ ሊጠናቀቅ አንድ ሳምንት ብቻ ቀርቶታል።

ይኼውም የጸጥታ እና ደህንነት አካላት የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ምርመራ የሚሠሩ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶችን እያዋከቡ ከመሆኑንም ባሻገር በቲያትር እና ጥበብ መልኩ የሚቀርቡ ሥራዎችን በማገድ እንዲሁም የቲያትር ባለምያዎቹን ለእስር የመዳረግ እርምጃዎች በተደጋጋሚ እየተስተዋሉ እንደሚገኙ ካርድ ገልጿል።

በዚህም “ካርድ እነዚህ አደገኛ እና ሕገ መንግስታዊ መብቶችን የሚጋፋ ድርጊቶች ተቀባይነት የላቸውም” ብሎ እንደሚያምንም አመላክቷል።

ስለሆነም መንግስት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን እንዲያነሳ፣ ሐቀኛ የተጠያቂነት ስርዓት እንዲዘረጋ እንዲሁም የሲቪክ ምህዳሩን እንዲያከብርና እንዲጠብቅ ጥሪውን አቅርቧል።

@ethio_mereja_news
ድሮኖቹ የሚያስወነጭፏቸው ሮኬቶች የእያንዳንዳቸው ዋጋ ከ60,000 እስከ 100,000 ዶላር አንደሚገመት ይነገራል፣ ቱርክ ሰራሽ ድሮኖቹ ደግሞ 5 ሚልዮን ዶላር ወይም 280 ሚልዮን ብር ገደማ ይሸጣሉ።

ይህም ማለት እያንዳንዱ ድሮን ታጥቆ የሚሰማራው የአንዱ ሮኬት ዋጋ ብቻ በትንሹ 3.5 ሚሊዮን ብር ገደማ ይገመታል፣ ለአንድ በረራ የሚጫኑት ሁለቱ ከሰባት ሚልዮን ብር በላይ ማለት ነው።

ባለፉት ሶስታ አመታት በትግራይ፣ በኦሮሚያ እና አሁን ደግሞ በአማራ ክልል እየተደረጉ ባሉ ጦርነቶች በሰው ህይወት እና ንብረት ላይ ከተከሰተው ውድመት በተጨማሪ ጦርነቱ በድሃ ሃገራችን ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል።

- በሀገሪቱ 33 ፐርሰንት የሚሆኑት ልጆች (ከሶስት ልጅ አንዱ) ከትምህርት ገበታ ውጭ ናቸው

- በደቡብ ክልል የመንግስት ስራተኞች ደሞዝ ከተከፈላቸው ከአንድ አመት በላይ ሆኗቸዋል፣ በአንዳንድ ቦታዎች ሲብስባቸው ሰልፍ የወጡ አሉ

- ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን  መመገብ አቅቶአቸዋል

- የሀገሪቷ የውጭ ንግድ ገቢ በ30 በመቶ መቀነሱን መንግሥት በቅርቡ አስታውቋል

ለእነዚህ እና ለአያሌ ውስብስብ ችግሮች ምክንያቱ በሀገሪቱ እየተካሄደ ያለው ጦርነት ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ በሀገሪቱ ውስጥ እየተካሄዱ ያሉ ጦርነቶች መቆም አለባቸው በሚለው ላይ መስማማት አለበት፣ ያለበለዛ ትውልድ እየጠፋ እና ሀገሪቱ እየወደመች መቀጠሏ አይቀርም።

ይህን እውነት ጆሮ ያለው ይስማ!

Kesis Temesgen

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ቤተክርስቲያኗ የውስጥ ፈተናዎቼ በዝተውብኛል አለች

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የውስጥ ፈተናዎቼ በዝተውብኛል ብላለች፡፡ ቤተክርስቲያኗ ይህንን ያለችው ዛሬ በተጀመረው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ላይ ነው፡፡

የጉባኤውን መጀመር አስመልክቶ ብፁዕ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት እንደተናገሩት በአሁኑ ጊዜ በከባድ ፈተና ውስጥ እያለፈች ትገኛለች ብለዋል፡፡

ቤተክርስቲያኗ የውጭው ፈተና ባይቀርላትም ከሱ በላይ ግን በውስጧ የሚነሡ ፈተናዎች ተልእኮዋን በአግባቡ እንዳትወጣ ዕንቅፋት ሆነውባታል ሲሉም ተናግረዋል፡፡

ከጥንት ጀምሮ የነበረ፣ በእግዚአብሔር ቃል የተቃኘ መንፈሳዊ ባህሏ ተዘንግቶአል፤ በምትኩም ፍቅረ ሢመትና ፍቅረ ንዋይ ነግሦአል፤ መለያየትና መነቃቀፍ እየሰፉ መጥተዋልም ብለዋል፡፡

ሃይማኖታችንንና ባህላችንን የማይወክሉ ኃይለ ቃላት፣ ኃላፊነት በጎደለው አገላለጽ እየተሰነዘሩ በጎቻችንን አስበርግገዋል፤ ድርጊቶቹ በበጎቻችን ዘንድ የነበረንን ተሰሚነትና ተደማጭነት ሊቀንሱብን እየተንደረደሩ ናቸው ሲሉ ገልጸዋል፡፡

Via EOTC

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ጥቆማ‼️

Online ስራ መስራት ከፈለጉ ሸገር Crypto ቻናልንን ይቀላቀሉ።

በርግጠኝነት ይወዱታል👇

JOin 👉 https://www.tg-me.com/sheger_crypto
በ2016 በጀት ዓመት ከአማራ ክልል 71 ቢሊዮን ብር ግብር ለመሰብሰብ ቢታቀድም፣ መሰብሰብ የተቻለው 33 ቢሊዮን ብር መሆኑን  ትናንት የአሜሪካ ድምፅ ዘግቧል።

ለገቢው መቀነስ በክልሉ የተከሰተው ግጭት ትልቁን ድርሻ ወስዷል።

@ethio_mereja_news
በሜትር ታክሲ አሽከርካሪ ከመደፈር እንደተረፈች ድምፃዊት ትዕግስት ኃይሉ (እግቱ) ገለፀች።

ትላንትና በከተማችን የሚሰራ የሜትር ታክሲ ሹፌር ሊደፍረኝ ነበረ ያለችው ድምፃዊቷ ከቤት ስወጣ ያደረሰኝን ሹፌር አመሻለሁ ሲለኝ ፕሮግራሜን ስጨርስ ቤቴን ስለሚያውቀውም መጀመሪያ በሰላም ስላደረሰኝም ወደ ቤት እንዲመልሰኝ ደወልኩለት ትንሽ ቢያረፍድም መጣ ስትል የተፈጠረውን አብራርታለች።

ቤት ልደርስ ትንሽ ሲቀረኝ መኪናውን አቁሞ ሲታገለኝ እወጋሻለሁ ብሎ ሲያስፈራራኝ፣ አምልጬ ወደ ቤት ገብቻለሁ። ሲታገለኝ ልብሴ ስለተቀደደ ኪሴ ውስጥ የነበረ ገንዘብ ሙሉበሙሉ መኪና ውስጥ ወድቆብኛል ብላለች።

ትማሩበታላችሁ፣ የእኔን ስህተት ተዘናግታችሁ አትደግሙትም ብዬ አምናለሁ ስትል እግቱ የደረሰባትን ገልፃለች።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ጥቆማ‼️

Online ስራ መስራት ከፈለጉ ሸገር Crypto ቻናልንን ይቀላቀሉ።

በርግጠኝነት ይወዱታል👇

JOin 👉 https://www.tg-me.com/sheger_crypto
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ፣ በኢትዮጵያ በሚያዝያ እና ግንቦት ወራት መጀመሪያ የጣለው ዝናብ ባስከተለው ጎርፍ ከ590 ሺህ በላይ ሕዝብ ጉዳት እንደደረሰበትና ከ95 ሺህ በላይ ሕዝብ እንደተፈናቀለ አዲስ ባወጣው ሪፖርት አስታውቋል።

ከባድ ዝናብና ጎርፍ የተከሰተው፣ በአማራ፣ አፋር፣ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ፣ ኦሮሚያ፣ ሲዳማ፣ ሶማሊ፣ ደቡብ ኢትዮጵያ እና ትግራይ ክልሎች እንደሆነ የቢሮው ሪፖርት አመልክቷል። ዝናቡ በበርካታ መኖሪያ ቤቶች፣ መሠረተ ልማቶችና በሰብል ማሳዎች ላይ ጉዳት ማድረሱንም ሪፖርቱ ጠቅሷል።

ባኹኑ ወቅት ከጎርፉ በተጨማሪ፣ በተለያዩ ክልሎች 93 ወረዳዎች በኮሌራ በሽታ እንደተጠቁ የገለጠው ሪፖርቱ፣ በሽታው ከተከሰተባቸው ወረዳዎች መካከል 30ዎቹ በኦሮሚያ፣ 24ቱ በሶማሌ እና 12ቱ በአፋር እንደሚገኙ ተገልጧል።

ግጭት እና አዲስ የሰዎች መፈናቀል ባለበት ሰሜናዊ አማራ ክልል ውስጥ ኮሌራ በሽታ እንደገና ማገርሸቱም አሳሳቢ እንደኾነ ቢሮው አስታውቋል።

በተመሳሳይ የወባ በሽታ በኹሉም የአገሪቱ ክልሎች በ1 ሺህ 397 ወረዳዎች በስፋት ተከስቷል ተብሏል።

@ethio_mereja_news
2024/11/18 04:59:29
Back to Top
HTML Embed Code: