Telegram Web Link
መንግሥት 12 ነጥብ 57 ቢሊዮን ብር የነዳጅ ድጓማ አድርጊያለሁ አለ

መንግሥት በ2016 በጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት ለሕዝብ አገልግሎት ሰጪ ተሽከርካሪዎች 12 ነጥብ 57 ቢሊዮን ብር የነዳጅ ድጓማ ማድረጉን ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር አስታወቀ። 102 ሺህ 329 ተሽከርካሪዎች ከድጎማ ተጠቃሚነት በጊዜዊነት መታገዳቸውም ተጠቁሟል።

በትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር ብሔራዊ የታለመለት ነዳጅ ድጎማ ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ ሰልማን መሐመድ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በ2016 በጀት ዓመት ዘጠኝ ወራት ብቻ ለታለመለት የነዳጅ ድጎማ 12 ነጥብ 57 ቢሊዮን ብር ወጪ ተደርጓል።

የነዳጅ ድጎማ ከተጀመረ ጀምሮ 241 ሺህ 81 ተሽከርካሪዎች የድጎማ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የተመዘገቡ ቢሆንም፤ ጥር 1 ቀን 2016 ዓ.ም በተደረገ ኦዲት በድጎማ ማስተግበሪያ ሥርዓቱ ውስጥ የድጎማ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተመዘገበው የሚገኙት የተሽከርካሪ ቁጥር 141 ሺህ 182 ናቸው ብለዋል።
(ኢ ፕ ድ)

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር፣ በአማራ ክልል ከሚገኘው አውላላ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ 1 ሺህ የሚጠጉ ሱዳናዊያን ስደተኞች እንዲኹም ከኩመር መጠለያ ጣቢያ ከ300 እስከ 400 የሚገመቱ ስደተኞች ለቀው መውጣታቸውን መግለጡን የአገር ውስጥ ዜና ምንጮች ዘግበዋል።

ስደተኞቹ፣ ከመተማ ወደ ጎንደር በሚወስደው መንገድ ላይ እንደሚገኙ ኮሚሽኑ መግለጡን ዘገባዎቹ አመልክተዋል፡፡

ስደተኞቹ ኹለቱን መጠለያ ጣቢያዎች ለቀው ለመውጣት የተገደዱት፣ በመጠለያዎቹ የግድያ፣ ሥርቆት፣ የተደራጀ ዝርፊያና የጠለፋ ወንጀሎች በመስፋፋታቸውና የአገልግሎት ችግሮች በመባባሳቸው እንደኾነ፣ ኮሚሽኑ ከስደተኞቹ መስማቱን ጠቅሷል ተብሏል። በመተማና በባንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኩምሩክ በሚገኙ መጠለያ ጣቢያዎች ከ53 ሺህ በላይ ሱዳናዊያን ስደተኞች እንደሚገኙ የኮሚሽኑ መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት፣ የስደተኞቹን "የደኅንነት ስጋቶች" እና "የአገልግሎት አቅርቦት ችግሮች" ለመፍታት ጥረት እያደረገ መኾኑን ትናንት ባወጣው መግለጫ ያስታወቀ ሲኾን፣ በቅርቡ በአውላላ እና ኩመር መጠለያ ጣቢያዎች የተፈጠረው "ክስተት እንዳሳሰበው" መግለጡም አይዘነጋም።

@ethio_mereja_news
በአዲስ አበባ ከተማ በትላንትናው እለት ባጋጠመ የእሳት አደጋ የአንድ ሰዉ ህይወት አለፈ

በአዲስ አበባ ከተማ ግንቦት 1ቀን 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 5:17 ሰዓት ላይ በቦሌ ክፍለ-ከተማ ወረዳ 2 ጃፓን ኤንባሲ አካባቢ ባጋጠመ የእሳት አደጋ የአንድ ሰዉ ህይወት ማለፉን የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።

የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን እንደተናገሩት የእሳት አደጋዉ ያጋጠመዉ በአንድ መጋዘን ላይ ሲሆን ህይወታቸዉ ያለፈዉ ግለሰብ የመጋዘኑ የጥበቃ ሰራተኛ ናቸዉ።

የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ቦታዉ ላይ ፈጥነዉ ቢደረሱም የጥበቃ ሰራተኛዉ ህይወት አስቀድሞ ያለፈ በመሆኑ የእሳት አደጋዉ ተዛምቶ ተጨማሪ ጉዳት ሳያደርስ መቆጣጠር ችለዋል።

መጋዘኑ ለመጋዘን አገልግሎት ስራ መዋል የማይገባዉ የመኖሪያ ቤት ቢሆንም ባለንብረቶቹ ቤቱን ለመጋዘን አገልግሎት ይጠቀሙት እንደነበር ኮሚሽኑ አስታውቋል።

ማናቸዉም ዕቃዎች የሚቀሙጡባቸዉ መጋዘኖች እሳትን ሊቋቋሙ ከሚችሉ ግብዓቶች የተገነቡና ለዚሁ ዓላማ ብቻ የተገነቡ መሆን ይኖርባቸዋል ሲል ኮሚሽኑ አሳስቧል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
#ኢትዮጵያ#አሜሪካ የሚገኙ ተፈላጊዎችን ሀገሪቱ አሳልፋ በመስጠት ትብብር እንድታደርግ ጠየቀች‼️
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል፤ በአሜሪካ ተቀምጠው “የኢትዮጵያን ሰላምና ደኅንነት የሚያውኩ ተፈላጊዎችን” አሳልፎ በመስጠት በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋን ትብብር እንዲያደርጉ ጠየቁ፡፡

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከአሜሪካው የፌዴራል የምርመራ ቢሮ (ኤፍቢአይ) ጋር ያለውን ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር አምባሳደሩ የበኩላቸውን ሚና እንዲጫወቱም ኮሚሽነር ጀነራል ጥሪ ማቅረባቸውን የፌደራል ፖሊስ መረጀ አመላክቷል፡፡

ኮሚሽናር ጀነራሉ ጥያቄውን ያቀረቡት አምባሳደሩን በቢሯቸው ተቀብለው ባነጋገሩበት ወቅት ነው፡፡

አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ በበኩላቸው፤ በአሜሪካን መንግሥት የሚፈለጉ ወንጀለኞችን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አሳልፎ በመስጠት ላበረከተው አስተዋፅኦ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ሀገራቸው ለኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ተመሳሳይ ድጋፎችን እንድታደርግ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንደሚያደርጉ መናገራቸውም ተገልጿል፡፡
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ኩባንያ፣ በኢትዮጵያ "የጸጥታ ችግሮች" እና "የሞባይል ዳታ ገደቦች" ማነቆ እንደኾኑበት ሃላፊዎቹ ትናንት ናይሮቢ ውስጥ በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል።

ሃላፊዎቹ፣ በኢትዮጵያ ግጭት ባለባቸው አካባቢዎች የኩባንያው እንቅስቃሴና አገልግሎቶች የተገደቡ እንደኾኑ ገልጸዋል።

በተለይ ኩባንያው 500 የቴሌኮም ኔትዎርኮች በዘረጋበት አማራ ክልል ውስጥ፣ የሞባይል ዳታ አገልግሎት ገደብ እንደተጣለበት ሃላፊዎቹ ጠቅሰዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የኦሮሞ ህዝብ ማንነቱን ተነፍጎ፣ በቋንቋው መጠቀም አንዳይችል ተደርጎ፣ የሀገር ባለቤትነቱ ተነፍጎ በሀገሩ እንደ ሁለተኛ ዜጋ ለመቆጠር ተገዶ ቢቆይም አሁን ነጻ ወጥቷልም ብለዋል‼️

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በትናንትናው እለት በነቀምቴ ከተማ በነበራቸዉ ቆይታ “ጦርት፣ እርስ በእርስ መገዳድልና መበላላት ይብቃን” ሲሉ ጥሪ አቅርበዉ ነበር።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በትናንትናው እለት በነቀምቴ ወለጋ ስታዲየም በተዘጋጀ የድጋፍ ሰልፍ ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር ሠላም፣ አንድነትና ልማት ላይ ያተኮሩ ሐሳቦችን አንስተዋል።

በዚህም “የኦሮሞ ህዝብ ከአንድ ክፍለ ዘመን በለይ ማንነቱን ተነፍጎ፣ በቋንቋው መጠቀም አንዳይችል ተደርጎ፣ የሀገር ባለቤትነቱ ተነፍጎ በሀገሩ እንደ ሁለተኛ ዜጋ ለመቆጠር ተገዶ ቆይቷል ያሉት ጠቅላይ ሚኒትር ዐቢይ ፤ አሁን ግን በከተፈለ መሰዋእትነት “ኦሮሞ ነጻ ወጥቷል” ህዝቡ ይህንን ሊረዳ ይገባል ብለዋል።

“ለኦሮሞ ህዝብ በሙሉ በነቀምት አዋጅ ማወጅ እፈልጋለሁ” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በኦሮሚያ ምድር ውስጥ ጦርነት፣ የኦሮሞ ልጆች እርስ በእርስ በእርስ መገዳደል አንዲሁም የኦሮሞ ልጆች ተቀምጠው ስለ ችግሮቻቸው መወያየት አለመቻል ከዛሬ ጀምሮ መቆም ለአበት” ሲሉ ተናረዋል።

“በጠላት መታለል እና በጠላት አጀንዳ መከፋል ይብቃን” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ “ባህላችንን እና ማነታችንን የሚገልጸው በመወያት፣ በመደማመጥ እንዲሁም በጋራ የወሰኑትን ነገር ይዞ ወደ ስራ በመቀየር ነው” በማለት ገልጸዋል።“አብረን መወያት አቅቶን ከጠላት ጋራ መምከር አሳፋሪ ነው፤ ስለዚህ ከታሪክ ተምረን ለህዝባችን ሰላም ማምጣት አንድንችል ጦርት እና መገዳደል ይብቃ” ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።

“የኦሮሞ ህዝብ ከአንድ ከፍል ዘመን በላይ በማንም ሲገዛ እና የማንም መጫወቻ ሲሆን የቆየው አንድነት ስላጣ ነው” ብለዋል።  አዩዘሀበሻ በአልአይን ዘገባ ላይ ፤ የኦሮሞ ህዝብ በማን መጫወቻ እንደነበር እና በማን ሲገዛ እንደቆየ ጠ/ሚኒስትሩ ስለመናገራቸዉ በዘገባው አልተካተተም።

“የኦሮሞ ህዝብ በአንድንት መቆም ቢችል ኖሮ ላለፉት 50 ዓመታት የኦሮሞ ህዝብ ትግል ወደኋላ እየተመለሰ አይኖርም ነበር” ሲሉም ተናግረዋል ሲል የዜና ምንጩ ዘግቧል ።“ለልማትም፣ ለጦርነትም፣ ራስን ለመጠበቅም እንዲሁም የተለያዩ ሃሳቦችን ለማመንጨት አንድነት ያስፈልገናል” ያሉት ጠቅላይ ሚንስትሩ፤ “የኦሮሞ ህዝብ አንድንት ከማንኛመው ጊዜ እስፈላጊ የሚሆንበት ጊዜ ላይ ነን” ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በንግግራቸው ያነሱት ሶስተኛው ነጥብ ስለ ልማት ሲሆን በዚህም የለውጡ መንግስት ወደ ስልጣን ሲመጣ ሀገሪቱ ለሰራተኞቿ ደመወዘወ መከፍል የማትችልበትና የውጭ ሀገራት እዳዋ ከእቅሟ በላይ ነበር ሲሉ አስታውሰዋል።

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እንደ ምስራቅ አፍሪካ 2ኛ ነበር፤ እንደ አፍሪካም እኮኖሚያችን በጣም ወደ ኋላ የቀረ ነበር ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ “ዛሬ ግን በጦርነት እና በተለያዩ ችግሮች ውስጥ ሆነንመ ቢሆን በመስራቅ አፍሪካ 1ኛ፤ በአፍሪካ ውስጥም ከፍተኛ የኢኮኖሚ ለውጥ እየገነባን ነው” ብለዋል።

“የአፍሪካ ተምሳሌት የሚሆን ኢኮኖሚ እና ብልጽግናን የመገንባት ስራችንን የሚያቆምን ምንም ምድራዊ ኃይል የለም” ሲሉም ተናግርዋል። “ዛሬ ከነቀምት በማውጀው አዋጅ፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ መረዳት ያለበት የኦሮሞ አንድነት የማይጠበቅ ከሆነ የኢትዮጵያ አንድነት ሊጠበቅ አይችልም። ኦሮሞ ሠላም ካልሆነ ኢትዮጵያ ሠላም አይኖራትም። ኦሮሞ ታላቅ ነው።ራሱን ለውጦ አገር ይለውጣል” በማለት ተናግረዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በድጋሜ እና ቀሪ ምርጫ አንሳተፍም ሲሉ እናት ፓርቲ እና መኢአድ አስታወቁ፡፡

የዲሞክራሲያዊ ሥርዓት አንደኛዉ መገለጫ ሕዝብ በነፃ ምርጫ በመረጠዉ አካል እንዲተዳደር መቻሉ መሆኑ ነው የሚለው መግለጫው፡፡

በአገራችን ኢትዮጵያ በ6ተኛዉ ዙር አገር አቀፍ ምርጫ ወቅት ምርጫ ባልተከናወነባቸዉና ድጋሜ ምርጫ በሚደረግባቸዉ አካባቢዎች ምርጫ ለማካሄድ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እንቅስቃሴ እያደረገ እንደሆነ ይታወቃል፡፡

የተጠቀሰዉን ምርጫ አስመልክቶ አገር በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሥር ከመሆኗ እንዲሁም በተለያዩ አካባቢዎች ካለዉ የፀጥታ ሁኔታ አኳያ ምርጫ ለማካሄድ አስቻይ ኹኔታዎች እንደሌሉ በመጥቀስ አስቻይ ሁኔታዎች እስኪፈጠሩ ምርጫዉ እንዲዘገይ ቦርዱን በደብዳቤ መጠየቃችን ይታወሳል የሚለው የፓርቲዎቹ መግለጫ፡፡

ይሁን እንጂ ቦርዱ ያቀረብነዉን ጥያቄ ከግንዛቤ በማስገባት የተጠየቀዉን ማስተካከያ ማድረግ ባለመቻሉ በተጠቀሰዉ ቀሪና ድጋሜ ምርጫ የማንሳተፍ መሆናችንን ለሕዝባችን በይፋ እናደርጋለን ሲሉ ለጣብያችን በላኩት መግለጫ አስታውቀዋል፡፡

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በትግራይ ክልል የቆላ ተምቤን ወረዳ አስተዳደር፣ ከግጭት ማቆም ስምምነቱ ወዲህ ባሉት ወራት ሳይፈነዱ በቀሩ የጦር መሳሪያዎች ሳቢያ ከ100 በላይ ሰዎች እንደሞቱና አካል ጉዳተኛ እንደኾኑ መናገሩን ቢቢሲ አማርኛ ዘግቧል።

የመንግሥት እና የኤርትራ ጦር ከአካባቢው ከወጡ በኋላ፣ በወረዳው በፈንጂ እና ሌሎች በየቦታው በተጣሉ መሳሪያዎች ሳቢያ 112 ንጹሃን ዜጎች የሞትና የመቁሰል አደጋ እንደደረሰባቸው የወረዳው አስተዳደር መናገሩን ዘገባው አመልክቷል። የሞትና የመቁሰል አደጋ ከደረሰባቸው መካከል፣ በርካታ ሕጻናትና ታዳጊዎች ይገኙበታል ተብሏል።

መሬት ውስጥ የተቀበሩ ፈንጂዎችና ያልፈነዱ ተተኳሾች በትምህርት ቤቶች፣ በእርሻና በሕዝብ መሰብሰቢያ ቦታዎች፣ በመጋዘኖች እና ባጠቃላይ ጦርነት በተካሄደባቸው አካባቢዎች ተበታትነው እንደሚገኙ ተገልጧል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ህግ ማስከበሩ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት👏👏👏🏿

ዩቲዩበሮቹ በቁጥጥር ስር ዋሉ...🇪🇹👌

ለማህበረሰቡ ወግና ባህል ፍፁም ተቃራኒ የሆነ ሐሰተኛ እና አፀያፊ የፈጠራ ታሪክ እያሰራጩ ህዝብን የሚያደናግሩ ዩቲዩበሮችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

ሃሰተኛ መረጃ እና ከማህበረሰቡ መልካም ባህልና ወግ የተቃረኑ አፀያፊ የፈጠራ ታሪኮችን በማህበራዊ ሚዲያ እያሰራጩ በህዝብ ላይ ውዥንብር እና መደናገርን የሚፈጥሩ ግለሰቦች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል፡፡

ማህበራዊ ሚዲያን ለበጎ አላማ ከመጠቀም ይልቅ ገንዘብ ለማግኘት ሲሉ ብቻ ከእውነት የራቁ መሰረተ ቢስ የፈጠራ አፀያፊ ወሬዎችን እየፈበረኩ በማሰራጨት የህዝብን ደህንነት ስጋት ላይ የሚጥሉ ዩቲዩበሮችን በቁጥጥር ስር ማዋል መጀመሩን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡
በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 አማረ እና ቤተሰቦቹ በተባለ ህንፃ ላይ ቢሮ ተከራይተው የተለያዩ የዩቲዩብ ገፆችን በመክፈት የማህበረሰቡን ሥነ ልቦና የሚጎዱ የፈጠራ ታሪክ በማሰራጨት የተጠረጠሩ ስድስት ግለሰቦች በህዝብ ጥቆማ እና ፖሊስ ባደረገው ክትትል ተይዘው በየካ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ምርመራ እየተጣራ ይገኛል፡፡
በቁጥጥር ስር ከዋሉት መካከል መቅደስ መብራት መኮንን የተባለችው ግለሰብ ሮሄ፣ ልዩነት፣ ጣዕም፣ አዲስ አለም፣ ዘይቤ፣ ህይወት፣ እይታ፣ እና ዩኒት ህይወት የተባሉ የዩቲዩብ ገፆችን በመክፈት በስራ አስኪያጅነት ስትመራ የነበረች ናት ተብሏል፡፡

ብሩክ ወርቅነህ ጌታሰው የተባለ ግለሰብ ደግሞ ገፆቹን በምክትል ስራ አስኪያጅነት እና በአስተባባሪነት ሲመራ የነበረ ሲሆን ናትናኤል አበራ በቀለ፣ እየሩሳሌም አስማረ ምህረት እና ምህረት ያሲን ቲጋ የተባሉት ግለሰቦች ደግሞ በፕሮግራም አቅራቢነት እንዲሁም ናትናኤል ዮሃንስ አሸነፍ በካሜራ ባለሙያነት ሲሰሩ የነበሩ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የትዳር አጋሬ ገበያ ሄዳ አልተመለሰችም ያለውን ባል በፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋለ!

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በካፋ ዞን የገዋታ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ረዳት ኢንስፔክተር ዮሐንስ ለገሰ እንደገለፁት ከወረዳ መዳቦ ቀበሌ ተጥርጣሪው ሚያዚያ 21 ቀን 2016 ዓ.ም ወረዳው ፖሊስ ዘንድ ቀርቦ የትዳር አጋሬና የልጆቼ እናት ሚያዚያ 20 ቀን 2016 ዓ.ም ወደ ገበያ ለግብይት ሄዳ አልተመለሰችም ጉዳዩን ፖሊስ ይወቅልኝ በሚል ቀርቦ ማስመዝገቡ ነው ፡፡

እንደ ፖሊስ አዛዥ ዮሐንስ  ገለፃ ይኸው ግለሰብ ሚያዚያ 23 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 11 ሰዓት ላይ  በድጋሚ ፖሊስ ዘንድ ቀርቦ የጠፋችውን የባለቤቴን አስክሬን ጫካ ውስጥ አገኘው ብሎ ሊያመለክት በመጣበት ፖሊስ በቁጥጥር ስር አድርጎት አስክሬኑን በጥንቃቄ በማንሳት ለህክምና በመላክ መረጃና ማስረጃ ማፈላለጉን አስረድተዋል፡፡

የገዋታ ወረዳ ፖሊስ የወንጀልና ትራፊክ አደጋ የታክቲክ ምርመራ የስራ ሂደት አስተባባሪ ረዳት ኢንስፔክተር ሙሉጌታ መለሰ በበኩላቸው የወንጀል ድርጊቱን ማን ፈፀመ ለምንስ ተፈፀመ የሚለው ጥያቄ ለመመለስ የወረዳው ፖሊስ የምርመራ ቡድን ተዋቅሮ ስራውን ሲጀምር ባል ሚስቴ ጠፋች ብሎ አስመዝግቦ አስክሬኗን አገኘሁ ማለቱ  ወንጀሉን ሳይፈፅም እንዳልቀረ ከውሳኔ ደርሰው ፖሊስ የተጠርጣሪ ደሳለኝ ወርቁ ከገዋታ ወረዳ ፍርድ ቤት የብርበራ ትዕዛዝ በመያዝ በመኖሪያ ቤቱ ውስጥ በተደረገው ብርበራ ለወንጀል የተፈፀመበት የደረቀ ደም ያለበትን አንድ ጦር እና ገጀራ መገኘቱን ጠቁመዋል፡፡

መርማሪው ፖሊስ ግለሰቡ በሰጠው የእምነት ቃል እንዳረጋገጠው ሚስት ገበያ ውላ ስትመለስ ባል በወረዳው መዳቦ ቀበሌ ልዩ ስሙ ጎጀብ ወንዝ ድልድይ አከባቢ ተደብቆ መንገድ በመጠበቅ ሚያዚያ 20 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 7፡00 ሰዓት ላይ አስቀድሞ ለወንጀሉ መፈፀሚያ ባዘጋጀው ገጀራ ቀኝ እጅዋ ላይ መቶ ከሰበረ በኋላ እንዳትጮህ በለበሰችው ጥምጣም በማነቅ በያዘዉ ገጀራ ጭቅሏትዋ ላይ ሦስት ቦታ በመቁረጥ በቀኝ እና  በግራ ጎንዋ ላይ አንድ ጊዜ በመቁረጥ በቀኝ ጡትዋ ላይ  አንድ ጊዜ በመቁረጥ ከባድ ጉዳት በማድረሰ ከገደላት በኋላ የወንጀል ድርጊቱ እንዳይታወቅበት ፖሊስ ዘንድ ቀርቡ ማስመዝገቡን ፖሊስ በምርመራው ማረጋገጡን አስረድተዋል፡፡

የታክቲክ ምርመራ የስራ ሂደት አስተባባሪ ረዳት ኢንስፔክተር ሙሉጌታ መለሰ የወንጀሉ መንስኤ በተመለከተ ጠይቀናቸው ተጥርጣሪው የግል ተበዳይ እና የሁለት ልጆቹ እናት ጋር ዘወትር በመካከላቸዉ ጭቅጭቅ መኖሩን የጠቆመው ፖሊስ የግል ተበዳይ ሟች ከመጀመሪያው ባለቤቷ ጋር በትዳር ሲኖሩ ሶስት ልጆችን ከወለዱ በኃላ ማግባቱንና ሁለት ልጆችን መወለዳቸውን ገልፆ ከቀድሞ ባለቤቷ ጋር ትማግጣለች በሚል ጥርጣሬ በመነሳት ወንጀሉን መፈፀሙን ለፖሊስ የሰጠው የእምነት ቃሉን በወንጀል ስነስርዓት ቁጥር 35 እንዲያረጋግጥ መደረጉን ገልፀዋል፡፡

ፖሊስ በመጨረሻም በተጠርጣርዉ ላይ ያጣራውን የምርመራ መዝገቡ በግለሰቡ የእምነት ቃል፤በህክምና ማስረጃና ለወንጀሉ የተፈፀመበትን ጦርና ገጀራ እግዝቪት በማደራጀት ክስ እንዲመሰረትበት ለዐቃቤ ህግ እንደሚላክ ጨምረው ተናግረዋል ሲል የደቡብ ምዕራብ ፖሊስ ዘገባ ፋስት መረጃ ተመልክቷል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የወጣቶች ቢሮ፣ ዕድሜያቸው ከ15 እስከ 18 የሚኾኑ የክልሉ ታዳጊዎች ከምሥራቅና ደቡብዊ ዞኖች፣ ከሰሜን ምዕራብና ሰሜናዊ የክልሉ አካባቢዎች እንዲኹም ከመቀሌ ትምህርታቸውን እያቋረጡ በብዛት ወደ ባሕረ ሰላጤው አገራት እየተሰደዱ መኾኑን ለዋዜማ ተናግሯል።

የክልሉ ወጣቶች ማኅበር ከመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በቅርቡ ባካሄደው ጥናት፣ 81 በመቶ ያህል ወጣቶች ሥራ አጥ መኾናቸው እንደተረጋገጠ ዋዜማ ተረድታለች።

በጥናቱ ከታቀፉት ወጣቶች መካከል፣ 40 በመቶዎቹ ከክልሉ የመውጣት ወይም ከአገር የመሰደድ ፍላጎት እንዳላቸው ታውቋል ተብሏል።

@ethio_mereja_news
ዛሬ ይቺን ምድር ከፈጣሪ በታች የቀላቀለችን ፤ አለም ፊቷን ብታዞርብን እሷ ግን በደስታ ምትቀበለን ፤ ለኛ ሁሉ ነገራችን የሆነች ፤ ከአይኗ ብሌን በላይ ምትሳሳልን እናታችን ቀኗ ነው በእርግጥም ሁሉም ቀን እናታችንን ማክበር አለብን ነገርግን ዛሬ ልዩ ቀኗ ነው።

እንኳን ለእናቶች ቀን በሰላም አደረሳችሁ ፤ የእናቶቻችሁን ደስታ ያሳያችሁ ፤

መልካም ቀን!

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ጠቅላይ ሚኒስቴሩ አማራ ክልል ገብተዋል

ገዥው ብልፅግና ፓርቲ ትናንት ቅዳሜ በአማራ ክልል በገበታ ለሀገር በለማው ጎርጎራ የዘጠኝ ወራት የስራ አፈፃፀም ግምገማ ማካሄዱን ጠቅላይ ሚንስትሩ በይፋዊ የፌስቡክ ገፃቸው ላይ ገልፀዋል።

በክልሉ የተቀሰቀሰው ግጭት ዛሬም በተለያዩ አካባቢዎች ቀጥሎ ባለበት ነው የፓርቲው ከፍተኛ ሃላፊዎች ጎርጎራ የተገኙት።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
2016 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና መርሐግብር ይፋ ሆኗል፡፡

መርሐግብሩ ከትግራይ ክልል ውጪ በሁሉም ክልሎች እና በሁለቱም የከተማ አስተዳደሮች በወረቀት እና በበይነ መረብ ፈተናውን ለሚወስዱ ተፈታኞች እንደሚያገለግል የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና:—

ከሐምሌ 3-5/2016 ዓ.ም ለማኅበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች

ከሐምሌ 9-11/2016 ዓ.ም ለተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ይሰጣል።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

@sheger_press
@sheger_press
በህንድ የአእምሮ ጤና እክል ያለባት ወጣት መለኮታዊ ኃይል አላት በሚል በመመለክ ላይ ትገኛለች

በታሚል ናዱ ግዛት የሂንዱ ከተማ በሆነችው ቲሩቫናማላይ ውስር ሚስጥራዊ ኃይል አላት የተባለችው ግለሰብ የአእምሮ የጤና ችግር ላይ ብትሆንም የሕንድ ማህበረሰብን ግን እያመለካት ይገኛል።

ህንዳውያን በርከት ያሉ አምላክ እና አማልክቶች ያሏቸው ሲሆን የሂንዱ አማልክቶች ሚስጥሮች እና እውነተኛ ህይወት ላይ በርካታ አወዛጋቢ ጉዳዮች ይነሳሉ። ከነዚህ መካከል ቶፒ አማ የምትባለው ኮፍያ የምታደርገው ሴት ብዙ ጊዜ ‘ሲድዳ’ እየተባለች በቅፅል ስም ትጠራለች። ይህችው ግለሰብ አዳኛችን ናት በማለት መመለክ ላይ ትገኛለች። አማኞች ፍፁም የሆነች ብሩህ ፍጡር ናት ይሏታል። ነገር ግን ዓለማዊ አመለካከት ላላቸው ሰዎች የህክምና እርዳታ የምትፈልግ የአእምሮ እክል ያለባት ሴት ናት።

ለአማኞች የሚታየቸው በቲሩቫናማላይ ጎዳናዎች ውስጥ ስትንቀሳቀስ ማንም በማይረዳው ጥንታዊ የታሚልኛ ቋንቋ ስትናገር ሲያዩ፣ ሌሎች ደግሞ ቤት የሌላት ምስኪን ሴት ያለ አላማ ስትቅበዘበዝ እና ስታጉረመርም ትውላለች ይላሉ። ሁሉም ነገር የአመለካከት ጉዳይ በመሆኑ ልዩነቶች መስተናገዳቸው ግድ ሆኗል።ቶፒ አማ የቲሩቫናማላይ ምልክት ከመሆኗ እና ብዙ ተከታዮችን ከመሳቧ በፊት የነበራት ህይወት እንቆቅልሽ ሆኖ በመቆየቱ ለታዋቂነቷ ትልቅ አስተዋፅኦ አበርክቷል።

ሁለት ወጥ ቃላቶችን እንኳን በአንድ ላይ አሰካክታ መናገር አለመቻሏን መለኮታዊ ኃይል ቢኖራት ነው ብለው ህንዳውያኑ እንዲያስቡ አስገዷቸዋል። በህንዳውያኑ የማህበራዊ ድህረ ገፅ ተጠቃሚዎች ዘንድ ቶፒ አማ ከተማዋን እየዞረች የጠጣችውን የቡና ትራፊ የተባረከ መስዋዕት ነው በማለት ሰዎች አንስተው ሲቀምሱ ይታያል። በሌላ በኩል ይህችኑ ሴት የአዕምሮ ጤና ችግር ያለባት ፣ የቆሸሸ ልብስ የለበሰች ፣ ሰውነቷ ከመታጠብ የራቀ እና በአንዳች እክል ውስጥ እንዳለች ማስተዋል ይችላል።

አንድ የኤክስ ተጠቃሚ ባጋራው ፅሁፍ አንዳንዶች በአእምሮ ህመም እየተሰቃየች ነው ብለው የሚያስቡ እና እርዳታ ትሻለች የሚል ሰዎች ቢኖሩም ስለ እርሷ ውዳሴ የሚያቀርቡና የሚዘምሩ በርካቶች መሆናቸውን ፅፏል።ጥልቅ የሆነ መንፈሳዊ ጥበቧ ካልተገለጠልህ እሷን ማግኘት የሚችሉት የታደሉት ብቻ ናቸው ሲሉም አማኞች ይደመጣሉ።

አስደናቂው ጉዳይ የአእምሮ እክል ላይ የምትገኘው ቶፒ አማ በአብዛኛው አምላኪዎቿን ችላ ብላ የእለት ውሎዋብ ስታሳልፍ አንዳች ምስጢራዊ ኃይል እየተገለጠላት ነው ብለው የሚያስቡ አሉ። በዚህም የተነሳ በሄደችበት ቦታ ሁሉ በርካቶች ይከተሏታል።(dagu)
2024/12/26 05:33:05
Back to Top
HTML Embed Code: