Telegram Web Link
ጎሮ አካባቢ በተከሰተ የእሳት አደጋ 13 የንግድ ሱቆችና በጋራዥ ዉስጥ የነበሩ አምስት ተሽከርካሪዎች ሙሉ በሙሉ ወደሙ


ግንቦት 3 ቀን 2016 ዓ.ም ሌሊት 6:50 በለሚ ኩራ ክፍለ-ከተማ ወረዳ 9 ጎሮ ገብርዔል ቤተክርስቲያን አጠገብ የተነሳዉ የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ከባድ ጉዳት ማድረሱን የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።

በእሳት አደጋዉ በቤተክርስቲን ዙሪያ ያሉ 13 የንግድ ሱቆችና በጋራዥ ዉስጥ የነበሩ አምስት ተሽከርካሪዎች ሙሉ ሙሉ የወደሙ እና በጋራዡ ላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል።

የእሳት አደጋዉን ለመቆጣጠር 12 የአደጋ መቆጣጠር ተሽከርካሪዎች 66 የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች የተሰማሩ ሲሆን የእሳት አደጋዉን ለመቆጣጠርም 4 :10 ሰዓት መፍጀቱን የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።

የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች እሳቱን ለመቆጣጠር ባደረጉት ርብርብ እሳቱ ወደ-ቤተክርስቲያኒቱ እንዳይዛመት ማድረግ የቻሉ ሲሆን በጋራዡ የነበሩ ቁጥራቸዉ 15 የሆኑ ተሽከርካሪዎችንም ማዳን ችለዋል።በአደጋዉ በሰዉ ላይ ምንም ጉዳት አልመድረሱን አቶ ንጋቱ ጨምረው ለብስራት ተናግረዋል።

በጋራዡ ውስጥ የነበሩ ተሽከርካሪዎች የያዙት ነዳጅና ሌሎች ፈሳሽ ተቀጣጣዮች እንዲሁም ንግድ ሱቆቹ እሳትን ሊቋቋሙ ከማይችሉ ቆርቆሮና መሰል ግብዓቶች መገንባታቸዉ  ለእሳቱ መባባስ አስተዋጾኦ ማድረጉን አቶ ንጋቱ ተናግረዋል።

የተሽከርካሪ ጥገና አገልግሎት የሚሰጡ ጋራዦች ደረጃቸዉን በጠበቁ ግብዓቶች የተገነቡና ከንግድ ሱቆች ከመኖሪያ አካባቢዎች  የራቁ መሆን እንዳለበት ኮሚሽኑ አስጠንቅቋል።

የአደጋውን መንስኤ ፖሊስ እያጣራ መሆኑን ብስራት ለማወቅ ችሏል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ባህር ዳር

በአማራ ክልል ርዕሰመዲና በበባህር ዳር ከተማ በአባይ ወንዝ ላይ የተገነባው ድልድይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተገኙበት በዚህ ሰዓት የምረቃ ስነስርዓቱ እየተከናወነ ነው።

ድልድዩ 380 ሜ ገደማ ርዝመት እና ወደ ጎን 43 ሜ ርዝመት ያለው ሲሆን ድልድዩ ከሚሰጠው የትራንስፖርት አገልግሎት ባሻገር ለባህርዳር ከተማ ተጨማሪ ውበትን ያጎናፀፈ ሆኗል።

@ethio_mereja_news
በኢትዮጵያ ላይ የአውሮፓ ኅብረት ያሳለፈውን ውሳኔ ካልቀየረ መንግሥት ተመጣጣኝ ዕርምጃ እንደሚወስድ አስታወቀ

የአውሮፓ ኅብረት ምክር ቤት ከሳምንት በፊት ለኢትዮጵያውያን የሚደረገውን የቪዛ አሰጣጥ ሒደት ለማጥበቅ ያሳለፈውን ውሳኔ ካልቀየረ፣ መንግሥት ተመጣጣኝ ውሳኔ እንደሚያስተላልፍ አስታወቀ፡፡

የአውሮፓ ኅብረት በቪዛ ጉዳይ በቅርቡ ያሳለፈውን ውሳኔ እንዲሽር ኢትዮጵያ እንደምትፈልግ ጠቅሰው፣ ይህ ካልሆነ ግን ከውሳኔው ጋር የሚጣጣም የራሷን ተመጣጣኝ ዕርምጃ ትወስዳለች ያሉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ ነብዩ ተድላ ናቸው፡፡

ቃል አቀባዩ በሳምንታዊ መግለጫቸው የአውሮፓ ኅብረት በኢትዮጵያ ላይ ያሳለፈው የቪዛ ውሳኔ ትክክል እንዳልሆነ በመግለጽ፣ ኢትዮጵያ ለኅብረቱ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቱን በጠበቀ መንገድ ማሳወቋን አስረድተዋል፡፡

ኅብረቱ ወደ አውሮፓ የገቡ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ወደ አገራቸው በመመለሱ ረገድ ለኢትዮጵያ መንግሥት ተደጋጋሚ ጥያቄዎች ቢያቀርብም፣ ባለሥልጣናት ተገቢውን ምላሽ ባለመስጠታቸው በኢትዮጵያውያን ላይ የቪዛ አሰጣጥ አሠራሩን ማጥበቁን በማስታወቅ ነበር ውሳኔውን ያስተላለፈው፡፡

በአውሮፓ ኅብረት በተለይም ‹‹ሸንገን ቪዛ›› ውስጥ በሚገኙ አገሮች ጥገኝነት የጠየቁ ኢትዮጵያውያን ጉዳያቸው የመኖሪያ ፈቃድ የማያሰጥ ሆኖ ሲገኝ፣ ጉዳዩ በፍርድ ቤት ታይቶ ወደ አገራቸው መመለስ አለባቸው የሚባሉትን ኢትዮጵያ እንድትወስድ በመጠየቁ ምክንያት ውሳኔው መተላለፉን ቃል አቀባዩ ተናግረዋል፡፡

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የኢትዮጲያ ፕሬስ ድርጅት የትግራይ ትምህርት ቤቶች ሁኔታ በማስመልከት ያጋራው መረጃ ሚዛናዊ አይደለም ሲሉ የትግራይ ትምህርት ቢሮ  ኃላፊ ዶ/ር ኪሮስ ጉዕሽ ተናገሩ

ኃላፊው በይፋዊ የፌስቡክ ገፃቸው ባጋሩት መልዕክትም "የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ተማሪዎቻችን በረሃብ ምክንያት ከትምህርት ገበታ እያቋረጡ ፤ ጦርነቱ የፈጠረው ተፅዕኖ መምህራኖቻችን መቋቋም አልቻሉም፤ 552 ትምህርት ቤቶች በወራሪዎች ተይዞብናል እዛው ያሉ ልጆቻችንም ለአምስት ዓመታት ከትምህርት ገበታ ርቀዋል፤ የተፈናቀሉ ወገኖቻችን በትምህርት ቤት ስለተጠለሉ የመማር ማስተማሩ ሥራ  ፈተና ሆኖብናል፤ በጦርነቱ ምክንያት የነበሩን ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ ወድመዋል፤ በአጠቃላይ ጦርነቱ የትምህርት ስርዓቱ፣ የሰው ሃይላችን እና ትምህርት ቤቶቻችን ሙሉ በሙሉ ወድምው ትምህርት ማስጀመር ተቸግረናል እና እርዱን ብለን መግለጫ ስንሰጥ ተማፅኖቻችን ወደ ህዝብ እንዲድርስ ኣልተባብረም " ብለዋል።

አያይዘውም "አሁን በቅርቡ ከሚያዝያ 2015 እስከ ሚያዝያ 2016 የተሰሩ በጣም ውስን ስራዎች መረጃ ስናወጣ ስኬት የመሰለው ይህ ድርጅት መረጃውን ወስዶ ኣሰራጭቶ ስላአጋጠሙን ችግሮች ምንም ሳይገልፅ አልፏል" ብለዋል።

ኃላፊው አክለውም የተዘረዙት ነጥቦች ለፕሬስ ድርጁቱ ስኬት መስለው የታዩትም በዋነኝነት  ከዓለም ኣቀፍ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች፣ በትግራይ ማህበረሰብ እና ከዓለም ባንክ በተገኘ ድጋፍ የተሰሩ ናቸው ያሉ ሲሆን አሁንም ቢሆን ድርጅቱ የህዝብ ከሆነ እንደአገር በሁሉም አቅጣጫ ያሉን ችግሮች በእኩል እንዲያይና የሚያስተላልፈው ዜናው ሚዛናዊ ሆኖ ሊሰራ ይገባል ሲሉ ተደምጠዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ፣ በአማራ ክልል ነፍጥ ያነሱ ታጣቂ ኃይሎች ወደ ሰላማዊ ሕይወት እንዲመለሱ ትናንት በባሕርዳር ተገኝተው በአዲሱ የአባይ ድልድይ ምረቃ ላይ ባደረጉት ንግግር ጥሪ አቅርበዋል።

ዐቢይ በዚኹ ንግግራቸው፣ "በማይገባ ነገር መገዳደል ይብቃ” የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል።

ጠቅላይ ሚንስትሩ፣ ታጣቂ ኃይሎች ወደ ሰላም ተመልሰው ከክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ ጋር ከሠሩ፣ ፌደራል መንግሥቱም የራሱን ትብብር ለማድረግ ዝግጁ እንደኾነ ገልጸዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
Update

ከሐዋሳ ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ የነበረዉ አዉሮፕላን ዉስጥ ታይቷል የተባለዉ ጭስ በዉስጡ ያለዉ ዘይት በመቃጠሉ የተነሳ መሆኑ ተገለፀ!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሰሞኑ በአዉሮፕላኑ ላይ የተከሰተው ጉዳይን አስመለክቶ እንዳስታወቀው ከእሳት ወይም ከሌላ ነገር ጋር የተያያዘ ሳይሆን አዉሮፕላን ዉስጥ ያለዉ ዘይት ተቃጥሎ ነዉ በወቅቱ የተከሰተው ጭስ ሊፈጠር የቻለዉ ይህም አልፎ አልፎ የሚያጋጥም ችግር ነዉ ብሏል።

የአየር መንገዱ ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰዉ በተለይ ለካፒታል እንደተናገሩት " በአዉሮፕላኑ ዉስጥ ያለዉ ዘይት መጋጠሉ እና ከእርሱ ጋር ተያይዞ የተፈጠረ ጭስ ነዉ ይህ ደግሞ የተለመደ ነዉ ብለዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ቁጥር ET154 ሚያዝያ 29፣ 2016 ከሀዋሳ ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ እያለ በአውሮፕላን ውስጥ ጭስ መታየቱን አስታዉቆ እንደነበር ይታወቃል። via Capital

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በእነ አቶ ዮሐንስ ቧያሌው መዝገብ፤ የቃሊቲ ማረሚያ ቤት ኃላፊ ለፍርድ ቤት ማብራሪያ እንዲሰጡ ታዘዙ‼️

በእነ አቶ ዮሐንስ ቧያሌው መዝገብ የእስረኞችን አያያዝ በተመለከተ የቃሊቲ ማረሚያ ቤት ኃላፊ ፍርድ ቤት ቀርበው ማብራሪያ እንዲሰጡ በፍርድ ቤት ታዘዘ።

አቶ ክርስቲያን ታደለ “ለቀናት” ምግብ አለመመገባቸውን ለፍርድ ቤቱ ዛሬ በዋለው ችሎት ገልጸዋል። ምግብ ያልተመገቡት፤ በማረሚያ ቤቱ “ #አማራ ተከሳሾች ስለሆናችሁ እንደሌሎቹ ተከሳሾች አትስተናገዱም” በሚል የቤተሰብ ጥየቃ ሰዓት ላይ ለውጥ በመደረጉ መሆኑን ለችሎቱ አስረድተዋል።

ዶ/ር ካሳ ተሻገርም በተመሳሳይ፤ “ የቀጠሮ እስረኞች ሆነን እያለ ነገር ግን ከፍርደኞች ጋር እንድንታሰር አድርጎናል” ሲሉ አቤቱታቸውን ለችሎቱ በቃል መግለጻቸውን ጠበቃቸው ሄኖክ አክሊሉ ለቢቢሲ ገልጸዋል።

ዶ/ር ካሳ “መንግሥት አላግባብ በተለያየ ሚዲያ ከሰራው ዘገባ ጋር በተገናኘ ፍርደኞች እኛ ላይ ዛቻ እና ማስፈራራት አድርሰውብናል” ማለታቸውን ሄኖክ ጠቅሰዋል።

በተከሳሾቹ የቀረቡ ሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን በተመለከተ የ #ኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን መርምሮ አጣርቶ ውጤቱን ለፍርድ ቤቱ እንዲያሳውቅ ችሎት ትዕዛዝ ሰጥቷል።

ከዚህ በተጨማሪም ተከሳሾች “ማረሚያ ቤቱ ከማንነታችን ጋር በተያያዘ በምሳ ሰዓት ብቻ እንድንጠየቅ ተደረግን” በሚል ላቀረቡት አቤቱታ ማረሚያ ቤቱ ምላሽ እንዲሰጥ እና የቃሊቲ ማረሚያ ቤት ኃላፊ በአካል ቀርበው እንዲያስረዱ መታዘዙንም ጠበቃ ሄኖክ አስረድተዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ  አስተዳደር በራያ ወረዳዎች መሠረታዊ የሕዝብ አገልግሎቶችን ለማስጀመር ከፌደራል መንግሥቱ ጋር እየተወያየ እንደኾነ ለዋዜማ ተናግሯል።

በአካባቢዎቹ የመንግሥት ተቋማት እንደተዘጉና መደበኛ እንቅስቃሴዎች ባብዛኛው መስተጓጎላቸውን ዋዜማ ከነዋሪዎች አረጋግጣለች።

ከአካባቢው የተፈናቀለ ነዋሪ የለም ሲሉ ያስተባበሉት የደቡብ ትግራይ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሃፍቱ ኪሮስ፣ በፈረሱት አስተዳደራዊ መዋቅሮች ውስጥ ይሠሩ የነበሩ አመራሮችና ሠራተኞች ግን ተፈናቅለው ሊኾን ይችላል ብለዋል።

የተባበሩት መንግሥት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ቢሮ ግን፣ በቅርቡ በትግራይ ኃይሎችና በአማራ ታጣቂዎች መካከል በተፈጠረው ግጭት ሳቢያ ከራያ አከባቢዎች ከ36 ሺህ በላይ ሰዎች መፈናቀላቸውን አስታውቆ ነበር።

ዋና አስተዳዳሪው፣ ከጦርነቱ በፊት በመንግሥታዊ መዋቅሮች ተመድበው ይሠሩ የነበሩ ሠራተኞች ወደ ሥራ እንዲመለሱ እየተደረገ መኾኑን ገልጸዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በትምህርት ተቋማት በሚቀጠለው 2017 ዓ.ም ምንም አይነት አዳዲስ ፕሮጀክቶች እንደማይኖሩ ተገለጸ‼️
በሚቀጠለው ዓመት 2017 ዓ.ም ምንም አይነት አዳዲስ ፕሮጀክቶች እንደማይኖሩ የገንዘብ ሚኒስቴር ዴኤታ ዶ/ር ኢዮብ ተካልኝ አስታወቁ።

ሚኒስትር ዴኤታው ይህንን ያስታወቁት የትምህርት ሚኒስቴርና የ22 ዩኒቨርሲቲዎች የ2017 በጀት ዕቅዳቸው በተገመገመበት ወቅት ነው።

የትምህርት ሚኒስቴር፣ የሚኒስቴሩ ሁለት ተጠሪ ተቀማት፣ የ8 የምርምርና የ14 የአፕላይድ ዩኒቨርስቲዎች የ2017 በጀት እቅድ በገንዘብ ሚኒስቴር በተካሄደ የበጀት ስሚ መርሀ ግብር ተገምግሟል።

የበጀት ስሚ መርሀ ግብሩን የመሩት የገንዘብ ሚኒስትር ክቡር አቶ አህመድ ሽዴ እንደገለጹት የበጀት ዝግጅቱ ዋና ትኩረት የሀገሪቱን ሀብትና የመንግስትን በጀት በእቅድ ለተያዘለት አላማ ብቻ በአግባቡና በቁጠባ መጠቀም መሁኑን ጠቁመው አስፈጻሚ መስሪያ ቤቶችና የስራ ሀላፊዎችም በጀትን በአግባቡ ጥቅም ላይ እንዲውል የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡

ሚኒስቴር መሰሪያ ቤቱ እና ከፍተኛ የትምህርት ተቋማቱ የበጀት እቅዳቸውን በተቀመጠላቸው የበጀት ጣሪያ መሰረት አስተካክለው በጠቂት ቀናት ውስጥ ለገንዘብ ሚኒስቴር እንዲያቀርቡ መጠየቃቸውን ከገንዘብ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያሳያል።(አዲስ ሰታንዳርድ)

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
NewsUpdate‼️

በአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሐመር በኢትዮጵያ ወቅታዊ የጸጥታና ፖለቲካዊ ኹኔታ ዙሪያ ከኦነግ ሊቀመንበር ዳውድ ኢብሳ እና ከኦፌኮ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ጋር ትናንት አሜሪካ ኢምባሲ ውስጥ ተወያይተዋል።

ኦነግ፣ ሐመር እና ዳውድ "ሰፋ ያለ ውይይት" ማድረጋቸውንና ዳውድ ኦነግ ለዓመታት ያለፈባቸውን አስቸጋሪ የፖለቲካ ኹኔታዎች ለሐመር እንዳብራሩላቸው ገልጧል።

ዳውድ የአገሪቱን ችግሮች ለመቅረፍ፣ ለዓመታት ከሕግ ውጭ የታሠሩ የኦነግ አመራሮችን "ባስቸኳይና ያለምንም ቅድመ ኹኔታ" መፍታት፣ “የተዘጉ የኦነግ ጽሕፈት ቤቶች መክፈት" እና "በመላው አገሪቱ ታስረው የሚገኙ የፖለቲካ እስረኞችን ኹሉ መፍታት" እንደሚያስፈልግ ሃሳብ ማቅረባቸውን ግንባሩ ጠውሷል።

ሐመር በበኩላቸው፣ በኢትዮጵያ ግጭቶች በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ አሜሪካ ጥረት እንደምታደርግ ለዳውድ ነግረዋቸዋል ተብሏል። [ዋዜማ]

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
መንግሥት የመንግሥት ሠራተኞች ቅጥርና ምደባ የአገሪቱን ብሄረሰቦች ብዝኀነትና የጾታና የአካል ጉዳተኞችን ተዋጽዖ የጠበቀ እንዲኾን የሚያስገድድ ረቂቅ አዋጅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርቧል።

ምክር ቤቱ፣ በረቂቅ አዋጁ ላይ ትናንት ተወያይቷል። ረቂቅ አዋጁ፣ በመንግሥት ሠራተኞች ደሞዝ ጭማሪ፣ ደሞዝ እርከን፣ ክፍያና ጥቅማጥቅሞች ላይ ማሻሻያ እንዳደረገም ተገልጧል።

የአነሳ ብሄረሰቦችና የማኅበረሰብ ክፍሎች በመንግሥት መስሪያ ቤቶች በቅጥር፣ ምደባ፣ ዝውውር፣ በሥራ ደረጃ እድገት፣ በትምህርትና ሥልጠና ረገድ ተጨማሪ መንግሥታዊ ድጋፍ እንዲደረግላቸውም ረቂቅ አዋጁ ይደነግጋል። ምክር ቤቱ፣ ረቂቅ አዋጁን ጉዳዩ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ መርቶታል።

@ethio_mereja_news
በሰሜን ሸዋ ዞን በሁለት ወረዳዎች በተመሳሳይ ቀን በደረሰ የድሮን ጥቃት የበርካታ ሰላማዊ ሠዎች ሕይወት አለፈ!!

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ቀወት ወረዳ ተሬ ቀበሌ ጉሎ በተባለ ትምህርት ቤት እና ሞላሌ ወረዳ እሁድ ግንቦት 4፤ 2016 ዓ.ም. በደረሰ የድሮን ጥቃት ከአስር በላይ ሠላማዊ ሰዎች መገደላቸውንና መቁሰላቸውን ተገለጸ።

ከቀወት ወረዳ ዋና መቀመጫ ሸዋሮቢት በግምት 20 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በሚገኘው የጉሎ (ጎጥ) አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከቀኑ 7፡30 ገደማ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት አራት ሠዎች ሲገደሉ አምስት ሠዎች ደግሞ መቁሰላቸውን የዐይን እማኞችና የተጎጂ ቤተሰቦችን ዋቢ በማድረግ ቢቢሲ ዘግቧል።

ዶይቼ ቬለ የዜና ወኪል በቀዎት ወረዳ እና ሞላሌ ወረዳዎች በዕለቱ ተፈጸመ በተባለ የሰውአልባ ድሮን ጥቃት 14 ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸውን እና በርካቶች መቁሰላቸውን ዘግቧል።

በትምህርት ቤቱ የተፈጸመው የድሮን ጥቃት መምህራንና የአካባቢው ማሕበረሰብ የወላጅ መምህራን ህብረት (ወመህ) ስብሰባ ላይ በነበሩበት ቅጽበት መሆኑን ለቢቢሲ የተናገሩ አንድ የስብሰባው ተካፋይ፤ በጥቃቱ እሳቸውም ጭንቅላታቸው ላይ እንደቆሰሉ ገልጸዋል።

ከሟቾቹ ውስጥ ሁለቱ የስብሰባው ተሳታፊዎች ሲሆኑ፤ ሁለቱ ደግሞ የት/ቤቱ ዙሪያ ላይ የነበሩ ሠላማዊ ሠዎች እንደሆኑ ቢቢሲ ያነጋገራቸው ሌላ የአይን እማኝ ተናግረዋል።

የፍንዳታ ድምጽ ሰምተው ወደ አካባቢው በፍጥነት እንዳመሩ የተናገሩ አንድ የዐይን እማኝ እንደደረሱ አስከሬን ማየታቸውን ጠቅሰው፤ የአራት ሠዎች ሕይወት ማለፉንና በርካታ ሠዎች መቁሰላቸውን ተናግረዋል።

ተመሳሳይ ዞን በሞላሌ ወረዳ መዘዞ ተብላ በምትጠራው ከተማ አጠገብ በተጣለ ሌላው የድሮን ጥቃት ሶስት የፋኖ አባላት እና በመጠጥ ሽያጭ ላይ የተሰማራች አንድ ሴት ጨምሮ አራት ያልታጠቁ ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸውን ዶይቸ ቼለ ዘግቧል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ለተለያዩ አምባሳደሮች ሹመት ሰጡ

የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ዛሬ ለተለያዩ አምባሳደሮች ሹመት ሰጥተዋል።

የፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት እንዳስታወቀው ፕሬዝደንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ለተለያዩ አምባሳደሮች ሹመት ሰጥተዋል።

በዚህ መሰረትም ፦

1. አምባሳደር ፍስሐ ሻውል ገብሬ
2. አምባሳደር እሸቴ ጥላሁን ወልደየስ
3. አምባሳደር ለገሰ ገረመው ሃይሌ
4. አምባሳደር ደሊል ከድር ቡሽራ
5. አቶ እስክንድር ይርጋ አስፋው
6. አቶ ልዑልሰገድ ታደሰ አበበ
7. ወይዘሮ ናርዶስ አያሌው በላይ
8. አቶ ብሩክ መኮንን ደምሴ
9. አቶ ቴዎድሮስ ግርማ አበበ
10. አቶ መኩሪያ ጌታቸው ወርቁ ን
በባለ ሙሉ ስልጣን አምባሳደርነት

እንዲሁም፦

1 አቶ በትረ መንግስቱ ብርሃኑ
2 አቶ ዮሃንስ ፈንታ ወልደጊዮርጊስ
3 አቶ ኃይለሥላሴ ሱባ ገብሩ
4 አቶ ንጉስ ከበደ ካሳው
5 አቶ ዘሪሁን አበበ ይግዛው
6 አቶ ተሾመ ሹንዴ ሀሚጦ
7 አቶ ሌሊሳ ብርሃኑ ገለታ
8 አቶ ደረጀ በየነ ደምሴ
9 አቶ ሰብስቤ ባዴ አድባብ
10 አቶ ነብዩ ተድላ ነጋሽ
11 አቶ አንተነህ አለሙ ሰንበቴ
12 ወይዘሪት ለምለም ፍስሃ ምናለ
13 አቶ አንዋር ሙክታር መሀመድ
14 አቶ አብርሃም መንግስቱ ገመቹ ን በአምባሳደርነት የሾሙ መሆኑን የፕሬዝዳንት ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።

Via:ኢትዮ ኤፍ ኤም

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በደቡብ ኢትዮጵያ እና የኦሮሚያ ክልሎች አዋሳኝ ዳግም በተነሣ ግጭት ሦስት ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ‼️

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን ጎርካ ወረዳ እና በኦሮሚያ ክልል የምዕራብ ጉጂ ዞን ሱሮ ባርጉዳ እና ገላና ወረዳዎች አዋሳኝ አካባቢዎች፣ በታጠቁ ሰዎች መካከል ውጊያ እየተካሔደ መኾኑን ነዋሪዎች አስታወቁ፡፡

በምዕራብ ጉጂ ዞን የገላና ወረዳ አስተዳደር ሰላም እና ጸጥታ አስተዳደር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኢያሱ ጂኦ፣ ግጭቱ ትላንት ማክሰኞ መቀስቀሱንና አንድ አርብቶ አደር ሲገደል ሌላ አንድ መቁሰሉን አረጋግጠዋል፡፡

የኮሬ ዞን ሰላም እና ጸጥታ መምሪያ ኃላፊ አቶ ተፈራ ቦንዶራ በበኩላቸው፣ ከጃሎ እና ከሻፉለ ቀበሌዎች፣ ሁለት ሰዎች ሲገደሉ አንድ ሰው መቁሰሉን ተናግረዋል፡፡ በርካታ ሰብልም በገጀራ ቆራርጠው አበላሽተዋል ሲል አንድ የአዩዘሀበሻ ቤተሰብ ከላይ ያለውን ምስል አያይዞ ገልጿል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በኢትዮጵያ ጊዜያዊ አገር አቀፍ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረግ ዩናይትድ ስቴትስ ጠየቀች!

በኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ኧርቪን ጄ.ማሲንጋ፣  ረቡዕ፣ ግንቦት 7 ቀን 2016 ዓ.ም.፣ አገራቸው በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ያላትን ፖሊሲ የሚያንጸባርቅ ንግግር አድርገዋል፡፡

አምባሳደሩ፣ በአዲስ አበባ በሚገኘው የአሜሪካ ግቢ ባደረጉት ንግግር፣ በኢትዮጵያ በትጥቅ ግጭት ውስጥ የገቡ አካላት፣ ግጭት አቁመው በንግግር ሰላምን እንዲያሰፍኑና የሰብአዊ መብቶችን እንዲያከብሩ አሳስበዋል፡፡

የታጠቁ ቡድኖች፣ ፖለቲካዊ ዓላማዎቻቸውን በዐመፅ ለማሳካት እየገፉ መኾናቸውንና መንግሥትም ይህን ለመከላከል የሚወስዳቸው ርምጃዎች፣ በፖለቲካ ምኅዳሩ ላይ የማይካድ ተጽእኖ ያለው መኾኑን የተናገሩት አምባሳደር ማሲንጋ፣ ውይይትን ወደ ጎን ያለው ይህ አካሔድ የመብት ጥሰቶችም እንዲቀጥሉ ማድረጉን ገልጸዋል፡፡

በመላ አገሪቱ “ሰላማዊ ዜጎች፣ በተለያዩ ኀይሎች ከሕግ ውጭ ግድያ፣ የዘፈቀደ እስራት፣ አስገዳጅ ስወራ፣ ከግጭት ጋራ የተያያዘ ጾታዊ ጥቃት እና ሌሎችም ጥቃቶች እየተፈጸሙባቸው መኾኑን የሚገልጹ ዘገባዎችን ስናይ እጅግ አዝነናል፤” ሲሉም ተናግረዋል፡፡

በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሱት የፋኖ ታጣቂ ቡድኖች፣ ፊታቸውን ወደ ድርድር እንዲያዞሩ አምባሳደሩ ሲጠይቁ፤ ህወሓት፣ በኀይል ወሰን ለማስመለስ ከሚደረግ እንቅስቃሴ እንዲቆጠብና የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊትም የሰላም ውይይትን እንዲቀጥል አሳስበዋል፡፡

በአፍሪካ ቀንድ የዩናይትድ ስቴትስ ልዩ መልዕከክተኛ አምባሳደር ማይክ ሐመር፣ ልዩ ልዩ የሲቪክ ተቋማት እና የፖለቲካ ፓርቲዎች መሪዎች እና ተወካዮች በተገኙበት አምባሳደሩ ባደረጉት የፖሊሲ ንግግር፣ ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በውስጣዊ ግጭቶች እየታመሰች እንደምትገኝ አስታውሰዋል፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥትም፣ የአገሪቱን ችግሮች በኀይል ለመፍታት ከሚያደርገው ጥረት እንዲቆጠብ የጠየቁት አምባሳደሩ፣ በእስር ላይ የሚገኙ ቁልፍ የፖለቲካ ሰዎችን መፍታቱ ጠቃሚ እንደኾነም

አስገንዝበዋል። ያን ተፈጻሚ ማድረግም፣ ኢትዮጵያውያን የሚፈልጉትን የፖለቲካ ውይይት ሊያግዝ እንደሚችል ነው የተናገሩት።

አምባሳደር ማሲንጋ፣ ጊዜያዊ አገር አቀፍ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲፈጸምም ጠይቀዋል፡፡

ሁሉም የታጠቁ ተዋናዮች፣ በመላ አገሪቱ ዐዲስ የሕዝብ መፈናቀልን ጨምሮ ለሰዎች ሥቃይ ምክንያት ከመኾን መገታት እንዳለባቸው ያነሡት አምባሳደሩ፣ ትምህርት ቤቶችን፣ የጤና ተቋማትንና የውኃ መሠረተ ልማቶችን ዒላማ ማድረግ እንዲቆም፣ የተሟላና ያልተገደበ ሰብአዊ አቅርቦት እንዲኖርም ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ይህም እንደ መነሻ፣ ጊዜያዊ አገር አቀፍ የተኩስ አቁምን እንደሚጨምር አመልክተዋል፡፡

ግጭት የኢትዮጵያውያንን ሥቃይ ከማባባስ ያለፈ መፍትሔ የሌለው በመኾኑ፣ ውይይት ትኩረት እንዲደረግበት ያሳሰቡት አምባሳደሩ፣ ምንም እንኳን ፍጹም ሊኾን ባይችልም፣ ኹሉም ወገኖች የአገራዊ ምክክሩን ዕድል ሊጠቀሙበት እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

Via VoA

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
2024/11/05 23:12:12
Back to Top
HTML Embed Code: