Telegram Web Link
እኛ የምንሰራው ስራ በጠቅላላ አስቀድሞ የታወቀ፣ የተጻፈና የተወሰነ ከሆነ ለምን እንለፋለን ታዲያ? ደግሞስ የኛ ነጻ-ፈቃድ ትርጉሙ ምኑ ላይ ነው? በመጨረሻው ቀንስ ጌታችን ለምን ይተሳሰበናል?

ለእነዚናህ ጥያቄዎች አጥጋቢ መልስ ከፈለጉ በትእግስት ሙሉዉን ያንብቡ!

ክፍል አንድ

ምስጋና የዓለማት ጌታ ለሆነው ለአላህ የተገባ ነው፡፡ የአላህ ውዳሴና ሰላም የሰላም አለቃና መምህር ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ ይሁን፡፡ ድልና የበላይነት ሐቅን ለማንገስና ሀሰትን ለማርከስ በደልን አጥፎቶ ፍትህን ለማስፈን ዕውቀታቸውን፣ ንብረታቸውን፣ ጉልበታቸውን፣ ጊዜያቸውንና ህይወታቸውን መስዋእት በማድረግ ለሚታገሉት ይሁን፡፡ በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው

አንድም ትክክለኛውን የቀዷ ወል-ቀደር ጽንሰ-ሀሳብ ባለመገንዘብ አልያም ራስ ግራ ተጋብቶ ሌላውንም ግራ ለማጋባት በተደጋጋሚ የሚነሳ ጥያቄ አልለ፡፡ እሱም፡- እኛ የምንሰራው ስራ በጠቅላላ አስቀድሞ የታወቀ፣ የተጻፈና የተወሰነ ከሆነ ለምን እንለፋለን ታዲያ? ደግሞስ የኛ ነጻ-ፈቃድ ትርጉሙ ምኑ ላይ ነው? በመጨረሻው ቀንስ ጌታችን ለምን ይተሳሰበናል? የሚል ነው፡፡ ለነዚህ ጥያቄዎች በአላህ ፈቃድ የቻልኩትን ያህል ምላሹን ለማብራራት እሞክራለሁ ኢንሻአላህ፡-

1ኛ) ቀጥታ መደ መልሱ ገብተን ዝርዝር ነጥቡን ከማየታችን በፊት እነዚህን ነጥቦች ከልብ እናስተውላቸው፡-

ሀ/ ስንናገር የፈለግነውን ቃላት በምንችለው ቋንቋ መርጠን ሀሳባችንን እንገልጻለን፡፡ ምላሳችን ሰውን መመረቅና ዱዓእ ማድረግ እንደሚችለው ሁሉ መራገምና መሳደብም ይችላል፡፡ ማንኛችንም ብንሆን በንግግር ወቅት የሆነ የማናውቀው ውጪያዊ ኃይል መናገር የማንፈልገውን ነገር እንድንናገር እንዳስገደደንና ላያችን ላይ እንደተጫነብን አይሰማንም፡፡ ለመልካሙም ሆነ ለመጥፎው ንግግር ተናጋሪው እኛው መሆናችንን ውስጣችን ያምናል፡፡

ለ/ መስሚያችን ሲፈጠር የመስማት ባህሪ ተሰጥቶት ነው የተፈጠረው፡፡ ምን እንሰማለን? የሚለው ግን በኛ ምርጫ ላይ የተመረኮዘ ነው የሚሆነው፡፡ የቁርኣን ጣቢያዎችን ከፍተን የአላህን ቃል የሰማንበት ጆሮ የሙዚቃ ጣቢያ ብንከፍትለት ይህንን እንኳ አልሰማም ብሎ ራሱን አይደፍንም። የወንድሞችንና የእህቶችን ምክርና ዳዕዋ ለመስማት ያዘጋጀነው ጆሮአችን በዛው መልኩ ሐሜትንና አለ ተባለ ወሬን በደንብ መስማት ይችላል፡፡ የአየር ሞገድ የሚያመጣው ተባራሪ ድምጽ ጆሮአችን ካልገባ በቀር ከዛ ውጪ ማንኛውንም ነገር ለመስማት ያለ ፍላጎታችን የተገደድንበት ምንም አይነት ሁኔታ የለም፡፡

ሐ/ አይናችን አላህ ተመልካች አድርጎ ፈጥሮታል፡፡ ማየት መቻሉ ተፈጥሮአዊ ባህሪው እንጂ የኛ ነጻ ፈቃድ ውጤት አይደለም፡፡ እንግዲያውስ በዚህ አይን ምን ታይበታለህ? የሚለው ነገር በኛ ምርጫ ላይ የተመረኮዘ ነው፡፡ ይህን አይናችንን ሰበር አድርገን የቀኝ መንገዳችንን ይዘን መጓዝ እንደምንችለው ሁሉ፤ ቀና በማድረግም ያልተፈቀደልን እይታ ላይ ማተኮርና ማፍጠጥ እንችላለን፡፡ አፍሪካ ቲቪ ላይ ያረፈው አይናችን ቃና ቲቪ ላይ (ውስጤ አይደለም) ለማረፍም የሚያግደው የለም (የአላህ ተውፊቅ የገጠመው ሲቀር)፡፡ ለምን አየህ? ተብለን ብንወቀስ እኔ ምን ላድርግ? አይኔ እኮ ነው! ብለን ማመካኘት እንችላለንን? ወይንስ ማየት ያልፈለግነውን ነገር የመጀመሪያው የአይን ግጭት ካልሆነ በስተቀር ከዛ በኋላ ያለውን በግድ እንድናይ ተደርገን ነው ማለት እንችላለንን? በፍጹም!

መ/ ልቦናችን ማሰብና ማሰላሰል እንዲችል ሆኖ የተዘጋጀ አንድ የሰውነት ዋነኛ ብልት ነው፡፡ በሱ ሰበብ ለሰዎች የሚጠቅምን ነገር ለማምጣት መልካምን ማሰብ፣ ጥሩን መመኘት፣ ሰዎችን መውደድና ማፍቀር እንችልበታለን፡፡ በዛው ተቃራኒ ክፋትን ማሰብ፣ ምቀኝነትን፣ ጥላቻን ማስተማርና በልብ ቦታ እንዲይዝ ማድረግ እንችላለን፡፡ ማንም ሰው ተገዶ የማይወደውን አካል በልቡ እንዲወደው፣ መልካም ያሰበለትን ክፉ እንዲሆንበት አልተደረገም፡፡ ይህ የነጻ ፈቃድና የልምድ ውጤት ነው፡፡

ሠ/ እጃችን በተፈጥሮው መያዝ የሚችል አንድ አካል ነው፡፡ በዚህ እጃችን ከኪሳችን ገብተን ሳንቲም በማውጣት ለአላህ ብለን ሶደቃ እንደምናደርገው ሁሉ ከሰው ኪስና ቦርሳ በመግባት ለስሜታችን ስንል መስረቅና መዝረፍ እንችልበታለን፡፡ በዚሁ እጃችን አደጋን ሰበብ ሁነን መከላከል እንደምንችለው ሁሉ በተቃራኒውም ሰበብ በመሆን በሰው ላይ አደጋ ልናደርስ እንችላለን፡፡ ግን በኛ እጅ ማንም ሰው ሊገለገልበትና ሊጠቀምበት አይችልም፡፡ ያ አይነት ስሜትም ተሰምቶንም አያውቅም፡፡ ይህንን የምትቃወሙ ካላችሁ ደግሞ፡- እኔም ፖስት ያደረግሁት፣ እናንተም ላይክና ሼር ያደረጋችሁትና እንዲሁም ኮመንት የሰጣችሁት በገዛ እጃችን አልነበረም ማለት ነውን?

ረ/ እግራችንን ጌታ አላህ መንቀሳቀስና መራመድ እንዲችል አድርጎ ነው የፈጠረው፡፡ ታዲያ በዚሁ እግር የአላህ ቤት በመጓዝ ለውዱ አምላካችን እንደምንቆምለት (እንደምንሰግድለት) ሁሉ ሲኒማ ቤት በመሄድም ለነፍሲያችን ቋሚ ተሰላፊ እንሆናለን፡፡ ቀበሌ ሄዶ ወረፋ በመያዝም ለስጋዊ ህይወታችን ቀለብን እንሸምትበታለን፡፡ በኛ እግር ወደ መስጂድም ሆነ ወደ ሲኒማ ወይም ወደ ቀበሌ የተራመደ የለም፡፡ ምናልባት እንደ መኪና የእግር ኪራይ ተጀምሮ ከሆነ እንጂ (ለፈገግታ)፡፡

ሰ/ ኢራዳህ (ፈቃድና ፍላጎት) የሚባለውም ነገር ከኛው ጋር አብሮ የተፈጠረ ነው፡፡ ወደ ሆቴል እንደገባን ምግብ እሲኪመጣ አንጠብቅም፡፡ ቅድሚያ ሜኑ (ቃኢማህ) እንመለከታለን፡፡ ለምን? ተብለን ብንጠየቅ የምፈልገውን ምግብ ለመምረጥ ነዋ! የሚል ይሆናል ምላሻችን፡፡ ሞባይል መሸጫ ገብተን መጀመሪያ ረድፍ ላይ የተቀመጠውን ሞባይል ገዝተን አንወጣም፡፡ ምክንያቱም፡- ጥሩና ለዋጋ ተስማሚ የሆነውን ሞባይል መምረጥ ስላለብን ነዋ! እንላለን፡፡ ልብስ ቤት ገብተን ማንኛውንም ጨርቅ አንስተን አንለብስም፡፡ ከሰውነታችን ጋር በውበትም ሆነ በልክ አብሮ የሚሄደውን እንመርጣለን (ለዚህ ሴቶች ትልቅ ምስክር ናቸው)፡፡

ታዲያ ከዚህ በኋላ እውን እኛ ነጻ-ፈቃድ የሌለን የአላህ ፍጡሮች ነን ማለት እንችላለን? እፍረት አይዘንምን? የፈለግነውን ነገር መርጠን መናገር፣ መስማትና ማየት ከቻልን ለምንፈልገው ሰው የፈለግነውን መጠን መስጠት ከቻልን፣ ወደፈለግነው ቦታ መሄድ ከቻልን ለምንድነው በቀዷ ወል-ቀደር የምናሳብበው? "ሐያእ ማድረግ ከኢማን ነው!" በማለት ነቢያችን (ዐለይሂ-ሶላቱ ወስ-ሰላም) አልመከሩንምን? ኧረ እንፈር ሼም ነው፡፡

ጌታችን አላህስ በነዚህ በሰጠን ኒዕማ ‹ጸጋ› ምን ሰራችሁበት ብሎ እኛን ቢጠይቀን አግባብነት የለውምን? በማዳም ቤት ለሰበርሽው ብርጭቆና በካውያ ላበላሸሽው ከንዱራ የጥፋተኝነት ስሜት ከተሰማሽ እንዴት በአላህ መሬት ላይ ለፈጸምሺው ኃጢአት የጸጸት ስሜት አይሰማሽም? ኃጢአቱ የቀደር ውጤት እንጂ ያንቺ ፈቃድ የታከለበት ካልሆነ የማዳም ንብረቶች ሲበላሹም የቀደር ውጤት ነው እንጂ የኔ ስህተት አይደለም ብለሽ ለመብትሽ ተካረከሪያ! (ልብ ሲኖርሽ አይደል!)

" ثُمَّ لَتُسْأَلُنَّ يَوْمَئِذٍ عَنِ النَّعِيمِ " سورة التكاثر 8
"ከዚያም ከድሎታችሁ ሁሉ፣ በዚያ ቀን ትጠየቃላችሁ።" (ሱረቱ-ተካሡር 102፡8)፡፡

2ኛ/ አሁን ደግሞ ወደ ጥያቄው እንመለስና፡- ሁሉም ነገር ቀድሞ የተጻፈና የተወሰነ ከሆነ ለምን እንለፋለን ታዲያ? የሚለውን እንየው፡-

ሀ/ የምንለፋውና የምንሰራው፡- ጌታችን አላህ ስሩ ብሎ ስላዘዘን ነው፡፡ አላህ የኛ ጌታ ነው፡
፡ እኛ ደግሞ የርሱ ባሮች ነን፡፡ ጌታ በባሪያው ላይ ሙሉ ስልጣን አለው፡፡ ባሪያ ግን ነጻነቱ የጌታውን ፈቃድ መፈጸም እንጂ ከጌታው ትእዛዝ ወጥቶ የራሱን ነጻነት በራሱ ማወጅ አይደለም፡፡ እኛ የአላህ ጥገኞች ነን፡፡ እኛነታችን እራሱ የአላህ ነው፡፡ የኔ የምንለው ማንነት የለንም፡፡ ካልነበርንበት ዓለም በችሎታው አስገኘን፡፡ ከዛም ቀጥሎ በህይወት መኖር እስከፈቀደልን ጊዜ ድረስ ሲሳያችንንም ኃላፊነቱን ወስዶ ይቀልበናል፡፡ በመጨረሻም የሰጠንን ህይወት ሩሓችንን ከውስጣችን በማውጣት ይገድለናል፡፡ ቀጥሎም ሬሳችን በክብር ከአፈር በታች እንዲቀበር ያደርጋል፡፡ ከዛም እሱ በፈለገው ቀን በቀንዱ (በጥሩንባው) መልአኩን እንዲነፋ በማዘዝ ዳግም ይቀሰቅሰናል፡፡ በመቀስቀስም በፊቱ አቁሞ ለፍርድ ይተሳሰበናል፡፡ እንደ ስራችን መጠንም በፍትሐዊነቱ ዋጋችንን ይከፍለናል፡፡

" قُتِلَ الْإِنْسَانُ مَا أَكْفَرَهُ * مِنْ أَيِّ شَيْءٍ خَلَقَهُ * مِنْ نُطْفَةٍ خَلَقَهُ فَقَدَّرَهُ * ثُمَّ السَّبِيلَ يَسَّرَهُ * ثُمَّ أَمَاتَهُ فَأَقْبَرَهُ * ثُمَّ إِذَا شَاءَ أَنْشَرَهُ * كَلَّا لَمَّا يَقْضِ مَا أَمَرَهُ * فَلْيَنْظُرِ الْإِنْسَانُ إِلَى طَعَامِهِ * أَنَّا صَبَبْنَا الْمَاءَ صَبًّا * ثُمَّ شَقَقْنَا الْأَرْضَ شَقًّا * فَأَنْبَتْنَا فِيهَا حَبًّا * وَعِنَبًا وَقَضْبًا * وَزَيْتُونًا وَنَخْلًا * وَحَدَائِقَ غُلْبًا * وَفَاكِهَةً وَأَبًّا * مَتَاعًا لَكُمْ وَلِأَنْعَامِكُمْ " سورة عبس 32-17
"ሰው ተረገመ፤ ምን ከሐዲ አደረገው? (ጌታው) ከምን ነገር ፈጠረው?( አያስብምን?) ከፍትወት ጠብታ ፈጠረው መጠነውም። ከዚያም (መውጫ) መንገዱን አገራው። ከዚያም ገደለው፤ እንዲቀበርም አደረገው፤ ከዚያም (ማንሳቱን) በሻ ጊዜ ያስነሳዋል። በውነት ያንን (ጌታው) ያዘዘውን ገና አልፈጸመም። ሰውም ወደ ምግቡ ይመልከት፤ እኛ ውሃን ማንቧቧትን ያንቧቧን መሆናችንን፤ ከዚያም ምድርን (በደካማ ቡቃያ) መሰንጠቅን የሰነጠቅን፤ በውስጧም እኽልን ያበቀልን፤ ወይንንም፤ እርጥብ ሳርንም፤ የዘይት ወይራንም ዘንባባንም፤ ጭፍቆች አትክልቶችንም፤ ፍራፍሬንም ገለባንም፤ (ያበቀልን መሆናችንን ይመልከት)። ለናንተም ለእንሰሶቻችሁም መጠቀሚያ ይሆን ዘንድ (ይህን ሰራን)።" (ሱረቱ ዐበሰ 80፡17-32)፡፡
እናም የዚህን ጌታ ትእዛዝ ያልፈጸምን የማንን ትእዛዝ እንፈጽም? አዎ! የምንለፋው የምንሰራው፡- አምላካችን አላህ እኔ ያዘዝኳችሁን ነገር ስሩ ብሎ ስላዘዘን ነው፡፡

" وَقَضَى رَبُّكَ أَلَّا تَعْبُدُوا إِلَّا إِيَّاهُ وَبِالْوَالِدَيْنِ إِحْسَانًا إِمَّا يَبْلُغَنَّ عِنْدَكَ الْكِبَرَ أَحَدُهُمَا أَوْ كِلَاهُمَا فَلَا تَقُلْ لَهُمَا أُفٍّ وَلَا تَنْهَرْهُمَا وَقُلْ لَهُمَا قَوْلًا كَرِيمًا * وَاخْفِضْ لَهُمَا جَنَاحَ الذُّلِّ مِنَ الرَّحْمَةِ وَقُلْ رَبِّ ارْحَمْهُمَا كَمَا رَبَّيَانِي صَغِيرًا " سورة الإسراء 24-23
"ጌታህም (እንዲህ ሲል) አዘዘ፦ እርሱን እንጂ ሌላን አትገዙ፤ በወላጆቻችሁም መልካምን ሥሩ፤ በአንተ ዘንድ ሆነው አንዳቸው ወይም ሁለታቸው እርጅናን ቢደርሱ ፎህ አትበላቸው፤ አትገላምጣቸውም፤ ለነርሱም መልካምን ቃል ተናገራቸው። ለሁለቱም ከእዝነትህ የመዋረድን ክንፍ ዝቅ አድርግላቸው፤ ጌታዬ ሆይ በሕጻንነቴ (በርኅራኄ) እንዳሳደጉኝ፣ እዘንላቸውም በል።" (ሱረቱል ኢስራእ 17፡23-24)፡፡

ለ/ የምንለፋውና የምንሰራው ስራችን አላህ ዘንድ በራሕመቱ ሰበብ ተቀባይነትን ካገኘ የልፋታችንን ዋጋ ለመቀበል ነው፡፡ እሱም፡- የአላህን መለኮታዊ ፊት ለማየት፣ የጀነትን ዘላለማዊ ህይወት ለማግኘት፣ የነቢያችንን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የጀነት ጉርብትናን ለማግኘትና ከምንፈራው የጀሀነም እሳት ለመጠበቅ ነው፡፡
አላህ ትእዛዙን ያከበሩ ምእመናን ባሮቹን ጀነትን ሊሸልማቸው ቃል ገብቷልና፡-

"وَالَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ سَنُدْخِلُهُمْ جَنَّاتٍ تَجْرِي مِنْ تَحْتِهَا الْأَنْهَارُ خَالِدِينَ فِيهَا أَبَدًا وَعْدَ اللَّهِ حَقًّا وَمَنْ أَصْدَقُ مِنَ اللَّهِ قِيلًا " سورة النساء 122
"እነዚያም ያመኑና በጎ ስራዎችን የሠሩ፣ በስራቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች ዘላለም በውስጣቸው ዘውታሪዎች ሲሆኑ እናገባዋቸዋለን፤ አላህ እውነተኛን ተስፋ ሰጣቸው። በንገገርም ከአላህ ይበልጥ እውነተኛ ማን ነው?" (ሱረቱ-ኒሳእ 4፡122)፡፡
" وَعَدَ اللَّهُ الْمُؤْمِنِينَ وَالْمُؤْمِنَاتِ جَنَّاتٍ تَجْرِي مِنْ تَحْتِهَا الْأَنْهَارُ خَالِدِينَ فِيهَا وَمَسَاكِنَ طَيِّبَةً فِي جَنَّاتِ عَدْنٍ وَرِضْوَانٌ مِنَ اللَّهِ أَكْبَرُ ذَلِكَ هُوَ الْفَوْزُ الْعَظِيمُ " سورة التوبة 72
"አላህ ምእምናንንና ምእምናትን ከስሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶችም ዉስጥ መልካም መኖሪያ ቤቶችን ቃል ገብቶላቸዋል፤ ከአላህም የሆነዉ ዉዴታ ከሁሉ የበለጠ ነው፤ ይህ እርሱ ታላቅ ዕድል ነው።" (ሱረቱ-ተውባህ 9፡72)፡፡

3ኛ/ አሁን የሚነሳው ጥያቄ ደግሞ፡- እንግዲያውስ እኛም ነጻ ፈቃድና ምርጫ ያለን ፍጡሮች ከሆንን፣ ፈቃዳችንን ተጠቅመን የፈለግነውን ነገር መስራት ከቻልንና በስራችን ልክ ደሞዛችንንም ከፍትሐዊው አምላክ ከአላህ ዘንድ የምንቀበል ከሆነ ነገራት ሁሉ አስቀድሞ ተወስነው አልቀዋል፡፡ ሁሉ ነገር ተጽፎ ተጠናቆአል ማለት ምንድነው ታዲያ? እኛስ ይህን የተወሰነውን ነገር ጥሰን መውጣት እንችላለንን? ይህ የተወሰነው ነገርስ ከኛ ጋር ያለው ግኑኝነት ምንድነው? የሚለው ነው፡፡
የዚህን ጥቄ ምላሽ ከነ-ማብራሪያው በክፍል ሁለት ፕሮግራማችን ላይ አቀርበዋለሁ ኢንሻአላህ፡፡ አላህ እውነቱን እውነት አድርጎ ይግለጽልን፡፡ እንከተለውም ዘንድ እርዳታው አይለየን፡፡ ሀሰትን ሀሰት መሆኑን ለይቶ ይግለጽልን፡፡ እንርቀውም ዘንድ ጥበቃው አይለየን፡፡ወአኺሩ ዳዕዋና ዐኒል-ሐምዱ ሊላሂ ረቢል ዓለሚን፡፡
ይሄን ፅሁፍ ማንበብ 100 መፅሐፍት እንደማንበብ ነው!

★★★★★

✍️በወጣትነት ሁሉም ነገር ትክክል ነው ከሚል መመሪያ ውጣ ፤ ሁሉንም ካላየሁ አላምንም አትበል ። ሰምቶ ማመን ፣ ከተጎዱት መማር አስተዋይነት መሆኑን አትርሳ ። የሰማንያ ዓመት ዕውቀትን ለመገብየት ግድ ሰማንያ ዓመት መኖር የለብህም ። ሰማንያ ዓመት ከኖሩት በትሕትና መጠየቅ ይገባሃል ።
:
✍️ምክርን ብትሰማ በነጻ ትማራለህ ። ምክርን አልሰማ ብትል ግን በዋጋ እንደምትማር እወቀው ። በዋጋ መማር ግን አድካሚ ደግሞም የሚያስመርር ነው ። ብልህ ከሆንህ በሰው ከደረሰው ትማራለህ ፣ ሞኝ ከሆንህ ግን በራስህ ሲደርስ ትማራለህ ።
:
✍️የታየህን አሳይ ፣ ያልታየህን አጥራው ። በደንብ ያልተረዳኸውን አታስተምረው። ያልቀመስከውን ለሰው አትጋብዝ ። የሰማኸውን ሁሉ አትመን ። ያየኸውን ሁሉ ስጡኝ ፣ የተናገርከውን ሁሉ ፈፅሙ አትበል ። የሰጠኽውን እርሳ እንጂ አታውራ። ፍፃሜውን ሳታይ ምስጋና አታብዛ ። ቀኑ ሳይመሽ ቀኑ ጥሩ ነው አትበል ።
:
✍️ዓይንህ የፊቱን ቢያይ ልብህ የኋላውን ያስብ ። ነገ ላይ እንድትደርስ የትናንቱን አትርሳ ። የምትሄድበት እናዳይጠፋህ የመጣህበትን አትዘንጋ ።
:
✍️የአባቶችህን መልካም ሥራ አብነት አድርግ ። ካሳለፉት ሕይወት ተማር እንጂ አወዳሽና ወቃሽ አትሁን ። ሌሎች መሆን ያለባቸውን ስታውቅ አንተ መሆን ያለብህ እንዳይጠፋህ ተጠንቀቅ ። ደግሞም አንተም በታሪክ ፊት መሆንህን እወቀው ።
:
✍️ክፋት አይሙቅህ ፣ መልካም ነገርም ብርድ ብርድ አይበልህ ። ለክፋት አቅም ካለህ ለበጎ ነገርም አቅም አለህና ተግባርህ የምርጫ ውጤት ነውና አስብበት ።
:
✍️ገንዘብ የሚመልሰው የገንዘብን ጥያቄ ብቻ ነውና ሁሉንም ነገር ገንዘብ ያስገኝልኛል ብለህ አታስብ ። ላለው አትሩጥ ፣ ምጽዋትህና ተግባርህ በአቅምህ መጠን ይሁን እንጂ ከአቅምህ አትነስ ። ድሃም ሆነህ ተበድረህ ስጦታ አትስጥ ። በጣም ካልቸገረህ ለቅንጦት አትበደር ። ያንተን ድርሻ ከጨረስህ ያልተጨረሰ የሌሎችን ድርሻ ፈፅምላቸው ።
:
✍️ለሀብታም አትሳቅ ፣ የደሀ ጉልበት አይለፍብህ ፣ ያለ ሰው ሰው አልሆንክምና ሰው አትጥላ ፣ የወጣህበትን መሰላል አትገፍትር ፣ ለመውረድም ያስፈልግሃልና ፣ ያየኽውን ሴት ሁሉ የመውደድ ጠባይህ ካለቀቀህ ትዳር አትያዝ ፣ ካልጋበዙህ በቀር አማካሪ አትሁን ፣ ባልጠሩህ ሥፍራ አቤት አትበል ፣ ካልሾሙህ መሪ አትሁን ፣ ጉድለት በሌለበት ቦታ ጊዜህን አታባክን ፣ የሰው ፊት ጥገኛ ሁነህ ሲስቁልህ የምትስቅ ሲቆጡህ የምታለቅስ አትሁን ፣ ነገርህን በልክ ፣ ቃልህን በጣዕም ፣ ድምፅህን በዝግታ ፈፅመው ።
:
✍️እውር እንዳይሉህ ያልታየኽን አያለሁ አትበል ። ጨካኝ እንዳይሉህ ያልተሰማህን ጩኸት እሰማለሁ አትበል ። ንፉግ እንዳይሉህ ያለ አቅምህ እረዳለሁ አትበል ። ነገር አይገባውም እንዳይሉህ ያልገባህን እንደገባህ አድርገህ አትለፍ ። አንድ በጎ ዕውቀት ሳትጨብጥ የዋልክበትን ቀን እንደ ኖርክበት አትቁጠረው ፣ ስለዚህ መፅሐፍትን አንብብ ፣ አዋቂዎችን ጠይቅ ፣ ሁሉን ሳትንቅ ስማ ።
:
✍️ሥልጣን ሲሰጥህ መሪ እንጂ አለቃ አትሁን ፤ ከፊት እየቀደምህ አስከትል እንጂ ከኋላ ሆነህ አትቅደም ።
:
✍️በዓላማ ኑር ፤ እንቅፋቶች የሚያጸኑህ እንጂ ተግባርህን የሚያስተውህ አይሁኑ ። ሕይወት ትምህርት ቤት መሆኑና ባለማወቅ ብዙ ትህምርቶች እንዳያመልጡህ ተጠንቀቅ ።
:
✍️የመከራ ቀን ወዳጆችህን አትርሳ ፤ የዛሬ ሰው ብቻ አትሁን ፤ የትላንቱንም አስብ ፤ አንገት የተፈጠረው ዞሮ ለማየት ነውና ።
:
✍️ዓለም ዋዣቂ ናት ። ከፍና ዝቅ ስትል አትደናገጥ ፤ ፀሐይ ዝናብን ተከትላ ትፈነጥቃለች ። ከመከፋትም በኋላ ትልቅ መፅናናት ይሆናል ። ከሌሊት በኋላም ሌሊት አይመጣም ። ከሀዘን በኋላ ደስታ ይሆናልና በርታ!
:
✍️መነቀፍን አትፍራ ፤ ነቀፋህን ግን አጥራው ፤ ስለ ሀሰት ሳይሆን ስለ እውነት ተገፋ ፤ ሌሎችን ውደድ ፍቅር ስጦታ እንጂ ብድር አይደለምና አልወደዱኝም ብለህ በአበዳሪዎች አንቀጽ አትካሰስ ፤ የገባህን አድርግ የዚህ ዓለም ሰው ሲወድህም ሲጠላህም ባለማወቅ ነው ። ብዙዎች ስለወደዱህ ይወድሃል ፤ ብዙዎች ስለጠሉህ ይጠላሃል ።
:
✍️ሁልጊዜ የበላዮችህን አትመልከት ፤ የበታቾችህንም ተመልከት ። ለድምፅ አልባዎች ጩህላቸው ፣ ለተጠቁት ተሟገትላቸው ። እውነት እውነት በማለትህ የምታጣው ሀሰተኛ ወዳጅህን ብቻ ነው ። እውነት እውነት በማለትህ የምታተርፈው ግን እውነተኛ ወዳጅን ነው ።
:
✍️ደጋፊዎች ተከታዮች አይደሉም ። ሰዎች ስለደገፉህም የያዝኩት እውነት ነው ብለህ መንቻካ አትሁን ፤ ምናልባት ዛሬ የሚጮሁልህ ዛሬን ሊረሱብህ ሊሆን ይችላልና ። ሲያለቅሱልህም ቃልህ ማርኳቸው ሳይሆን የሞተ ዘመዳቸው ትዝ ብሏቸው ሊሆን ይችላልና አለቀሱ ብለህ ንግግርህን ድንበር አታሳጣው ። እውነትንም በደጋፊ ብዛት እንዳትመዝናት ተጠንቀቅ ።
:
✍️ለእውነታ እንጂ ለይሉኝታ አትኑር ፤ ያን ስልህ የምትኖርበት ሕዝብና ባሕል ከእውነት ጋር እስካልተጋጨ መጋፋት የለብህም። ሠዎች የሚቀበሉህ ባሕላቸውን ስታውቅና ስታከብርላቸው ነው ።
:
✍️ልጅነት የለሰለሰ መሬት ፣ ወጣትነት የአዝመራ ዘመን ፣ ሽምግልና ደግሞ የአጨዳ ዘመን መሆኑን አስተውል ። በሽምግልናህ የምታጭደው የወጣትነትህን አዝመራ ነውና ዛሬ ለምትዘራው ተጠንቀቅ ።
:
✍️የሰዎችን ያለማወቅ አግዝ ፤ ዕውቀትህ ባላወቁት ላይ እንድትኮራና እንድትፈርድ አያድርግህ የአዋቂ ኩሩ ቁጥሩ ካላዋቂዎች ነውና ማወቅ ባለዕዳነት እንዳይሆን አላዋቂዎችን እርዳቸው !!

✍️ሁሉን ወሬ ላውራ አትበል ፣ የደበቁህን ምስጢር አታውጣጣ ፣ የሰማኽውን ወሬና የተገለጠልህን ምስጢር ምን መፍትሔ ሰጠኸውና ? ያየህውን ሥራ ሁሉ እሰራለሁ የሰማኸውን ትምህርት ሁሉ እማራለሁ አትበል ። ይህ የተሰወረው የቅንዓት ጠባይ ነውና ሁሉን ልያዝ ማለትም ዝንጉ አድረጎ እንዳያስቀርህ ሁሉም ውስጥ ልኑር አትበል ።

✍️ቆንጆዎች ቁንጅናቸው ሁሉን የሚተካ እየመሰላቸው ከዕውቀትና ከትሕትና ይርቃሉ ። ሁሉንም ሰው በመልካቸው የሚማርኩት ስለሚመስላቸው ኩሩና ተንኮለኞች ይሆናሉ ። አንተ ግን ቆንጆ ወዳጅን እንጂ ቆንጆ ቁመናን አትሻ ፤ ቆንጆ ትዳርን እንጂ ቆንጆ ሴትን አትመኝ ፤ የላይ ነገር ከንቱና ኀላፊ ነውና በሚፈርስ አካል ፣ ኑሮ በሚለውጠው መልክ አትደለል።

✍️እወድሃለሁ ብለህ የምትናገረውን ቃል ውለታ አታድርገው ፣ መውደድህን የምትናገረው እንወድሃለን እንዲሉህ አይሁን ፣ ሠላም ያለው አፍቃሪ የራሱን ፍቅር ያለ ምክንያት መፈፀም የሚችል ብቻ እንደሆነ እወቅ ። መወደድህን ለመስማት አትጠብቅ ።

✍️ ዛሬ የመዝራት ዘመንህ ነገ መከርህ ነውና በእምነት እውነትን ዝራ ፤ በምታውቀው ቦታ ላይ አገልጋይ በማታውቀው መልካም ተግባር ላይ ደጀን ሁን ፤ በቦታህ መምህር ያለቦታህ ተማሪ ሁን ፤ ክብሩ እንዳይቀንስብህ ከዕቃ ትምክህት ፣ ከዕውቀት ሙግት ራቅ ።

✍️ቂም አፍን የሚያመር ፣ ልብን የሚያነቅዝ ፣ ተግባርን የሚያልፈሰፍስ ነውና ለበደለህ ሰው ቅያሜህን ግለጥለት ፤ ቂመኝነት በክፉ መሸነፍ እንጂ ጀግንነት አይምሰልህ ።

✍️ከህሊናህና ከመንፈሳዊ አማካሪህ ሳትመክር ምንም ነገር አትወስን ፤ አጥርተህ ሳትሰማ ቃል አትግባ ። መከራ ካልደረሰ በቀር ባል በሌለበት ቤት ውስጥ ከሚስቲቱ ጋር ብቻህን አትቀመጥ ።
:
✍️የሚበልጥህ ልኩራብህ እንዳይልህ ፣ ያነሰህ ልድረስብህ ብሎ እንዳያጠፋህ የሀብትህን ልክ እንዳታወራ ፤ በገዛ አፍህ ባንዱ ትከብራለህ ባንዱ ትቀላለህና።
✍️በጣም በማክበርህ እንዳታመልከው ፤ በጣም በመናቅህ እንዳታዋርደው ሠው እንዳንተ መሆኑን እወቀው ።

✍️የእኔ መናገር ምን ይለውጣል? ብለህም ስህተትን አትለፍ ፤ የእኔ አስተዋፅኦ ምን ይጠቅማል ? ብለህም ስጦታህን አትጠፍ ።

✍️መልካም ቃል ከስጦታ ይበልጣልና መልካም ቃል ተናገር ፤ ማንኛውም ስጦታ ከልመና ወንበር አያስነሣም ። የተስፋ ቃል ግን እንደሚያስነሣ አውቀህ ለሰዎች የተስፋ ቃል ስጣቸው ።

✍️ትምህርት ለዕውቀት ያዘጋጃል እንጂ ዕውቀትን አይጨርስም ። ዕውቀትህን የምትይዝበትን ሥነ-ሥርዓት ግን ያሳይሃል ። አእምሮህን ለማረቅ ትምህርት ፣ ሰውነትህን ለመግዛት ትዕግስት ፣ ከማንም ጋር ለመኖር ሥነ-ሥርዓት ያስፈልግሃል ። ለህሊናህ እረፍት ግን እምነት ያሻሃል ። ተከታይ ለማበጀት ደግሞ ግልጽ መሆንና ታማኝነት ግድ ይልሃል ።

✍️ አንተው እውነትን ጠልተሃት ዘመኑ እውነትን ጠልቷል አትበል ። ዘመን እኔና አንተ ነን ፤ በራሱ ክፉና ደግ የሆነ ዘመን የለም።

✍️መልካም ምክር ብትሰማ ሕይወት ቀላል ይሆንልሃል ። ትክክለኛም ውሳኔ መልካም ምክር ከመቀበል ይገኛልና!

ምንጭ፡ ከዚሁ ከፌስ ቡክ መንደር የተገኘ
የነቢዩ ሙሐመድ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የሕይወት ታሪክ
ወደ ሐበሻ ስደተ-ሂጅራ
ከነብይነት (ኑቡዋ) አምስተኛው ዓመት ላይ በረጃብ ወር የመጀመሪያው ቡድን ወደ ሐበሻ ተሰደደ። አሥራ ሁለት ወንዶችና አራት ሴቶች ነበሩ። ኃላፊያቸው ዑስማን ቢን ዐፋን አልኡመዊ (ረ.ዐ) ሲሆኑ፥ ከሳቸው ጋር ባለቤታቸው ሩቂያ ቢንት ሙሐመድ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ነበሩ። ከነቢዩላሂ ኢብራሂምና ከነቢዩላህ ሉጥ (ዐ.ሰ) በኋላ ቀጥሎ በአላህ መንገድ ከቤተሰብ ጋር ለመሰደድ ዑስማን የመጀመሪያው ሰው ናቸው።
#አላህን__መፍራት

አላህ እንዲህ ብሏል፦

(وَإِيَّـٰىَ فَٱرْهَبُونِ ﴿٤٠﴾)
"እኔንም ብቻ ፍሩ።" (አል_በቀራህ፡ 12)

#ሐዲሥ 50/397

የእውነተኞች ሁሉ እውነተኛ የሆኑት የአላህ መልዕክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ሲሉ ነግረውናል በማለት ኢብኑ መስዑድ (ረ.ዐ) አስተላልፈዋል ፦ "ከእናንተ አንዳችሁ የሚፈጠርበት ነገር ከእናቱ ሆድ ውስጥ ለአርባ ቀናት (የዘር) ፈሳሽ ሆኖ ይቆያል። ከዚያም ለተመሳሳይ ጊዜ የረጋ ደም ይሆናል። ከዚያም ለተመሳሳይ ጊዜ የተላመጠ ሥጋ ይሆናል። ከዚያም መላኢካ ተልኮ ነፍስ ይዘራበታል። (መላኢካ) አራት ነገሮች ይታዘዛል። ሲሳዩን፣ የሚሞትበትን ወቅት፣ ሥራውንና እድለቢስ (ሸቂይ) ወይም እድለኛ (ሰዒድ) መሆኑን (እንዲጽፍ)። ከርሱ ውጭ ሌላ አምላክ በሌላው (አምላክ) እምላለሁ! ከእናንተ አንዳችሁ በርሱና በጀነት መካከል አንድ ክንድ ያክል ርቀት እስኪቀረው ድረስ የጀነት ሰዎችን ሥራ ሲሠራ ይቆያል። (ትንሽ ሲቀረው) የተጻፈበት ይቀድመውና የእሳት ሰዎችን ሥራ በመሥራት እሳት ይገባል። ከእናንተ አንዳችሁ የእሳት ሰዎችን ሥራ ሲሠራ ይቆይና (ሊገባበት) አንዲት ክንድ ሲቀረው የተጻፈው ቀድሞት የጀነት ሰዎችን ሥራ በመሥራት ጀነት ይገባል።" (ቡኻሪና ሙስሊም)

ከሐዲሡ የምንማራቸው ቁምነገሮች

1/ በቀዷ ቀደር _መልካምም ሆነ ክፉ_ ሁሉም ነገር ከአላህ እንደሆነ ማመን ያሻል።
2/ ሐዲሡ ወደ መልካም ሥራ ሰዎች እንዲሽቀዳደሙና በርሱው እንዲዘወትሩ ያነሳሳል።
3/ የሰዎች ስኬታማነት የሚለካው በፍጻሜያቸው ነው። እናም በተሠሩት መልካም ሥራ መኮፈስ መዝናናት የሚቻልበት ሁኔታ የለም።
4/ አንድ መልካም ሥራ የሠራ ሰው ንጹሕ እንደሆነ ሊያቆየው ይገባል። በክፉ ሥራ ሊበክለው አይገባም።
5/ ሁሌም በአላህ መታገዝ፣ ፍጻሜ እንዲያምር አላህን መጠየቅ፥ ክፉ ፍጻሜን መፍራትና ከርሱ በአላህ መጠበቅ ያስፈልጋል።
وَاسْتَعِينُوا بِالصَّبْرِ وَالصَّلَاةِ ۚ وَإِنَّهَا لَكَبِيرَةٌ إِلَّا عَلَى الْخَاشِعِينَ

(አል-በቀራህ - 45)
በመታገስና በሶላትም ተረዱ፡፡ እርሷም (ሶላት) በፈሪዎች ላይ እንጅ በሌላው ላይ በእርግጥ ከባድ ናት፡፡
#አላህን__መፍራት 7

#ሐዲሥ 50/403

የአላህ መልዕክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ተከታዩን ሲናገሩ ሰምቻለሁ በማለት ሚቅዳድ (ረ.ዐ) አስተላልፈዋል፦ "በትንሳኤ ቀን ፀሐይ የአንድ 'ሚል' ርቀት ያህል ወደ ሰዎች ትቀርባለች፡፡"

ሐዲሡን ከሚቅዳድ ያስተላለፉት ሱለይም ኢብኑ ዓሚር (ረ.ዐ)፦ "በአላህ እምላለሁ፥ (መልዕክተኛው) ሚል ሲሉ በምድር ላይ ያለውን (የታወቀ) ርቀት ይሁን ወይም የዓይን መኳያ (የሚመጥን) አልገባኝም" ብለዋል።
መልዕክተኛው (ﷺ) ንግግራቸውን በመቀጠል እንዲህ አሉ፦ "ሰዎች እንደየሥራቸው በላብ ይዋጣሉ። እስከ ቁርጭምጭምቶቹ የሚዋጥ አለ። እስከ ጉልበቶቹ የሚዋጥ አለ። እስከ ጎሮሮው ድረስ የሚዋጥም አለ።" ካሉ በኋላ በእጃቸው አፋቸውን እያመለከቱ ፦ "ላቡ (አፉ ድረስ ደርሶ) እንደልጓም የሚለጉመውም አለ" አሉ። (ሙስሊም ዘግበውታል)

ከሐዲሡ የምንማራቸው ቁምነገሮች

1/ የሰው ልጆች ከመጭው ዓለም የሚያገኛቸው ጭንቀትና ድንጋጤ እንደየሥራቸው ይለያያል።
2/ ሐዲሡ ወደ መልካም ሥራ ይገፋፋል። ከክፉ ሥራም ያስጠነቅቃል።
#አላህን__መፍራት 8

#ሐዲሥ 50/404

አቡ ሁረይራ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ "የሰው ልጅ በዕለተ ቂያማ ላባቸው ወደ ምድር ውስጥ ሰባ ክንድ ያህል እስክጠልቅ ድረስ በላብ ይጠመቃሉ። (ከፍታው) ጆሮዎቻቸው ድረስ ደርሶም (አፋቸውን) ይለጉማቸዋል።" (ቡኻሪና ሙስሊም)

ከሐዲሡ የምንማረው ቁምነገር

፨ የዕለተ ትንሳኤን አስደንጋጭነት ባሕሪ ማሳየትና ከእኩይ ተግባር ማስጠንቀቅ የዚህና መሰል ሐዲሦች አቢይ ዓላማ ነው።
#አላህን__መፍራት 9

#ሐዲሥ 50/405

አቡ ሁረይራ (ረ.ዐ) እንዲህ ሲሉ አስተላልፈዋል፦ ከአላህ መልክተኛ (ﷺ) ጋር እያለን "ጓ" የሚል ድምጽ ሰሙ። "ይህ ምን እንደሆነ ታውቃላችሁን?" በማለት ጠየቁን። "አላህና መልክተኛው ያውቃሉ" አልናቸው። "ይህ የዛሬ ሰባ ዓመታት እሳት ውስጥ የተጣለ ድንጋይ (ድምጽ) ነው። (ድንጋዩ) እስካሁን ድረስ ወደታች ሲያሽቆለቁል ኖሮ አሁን ገና ከጀሃነም ሥር መድረሱ ነው። እናም ጓ የምል ድምጽ ሰማችሁ" አሉ። (ሙስሊም ዘግበውታል)

፨ ከሐዲሡ የምንማረው ቁምነገር

1/ ሐዲሡ የጀሃነምን ጥልቀት ያሳያል። ይህም በርሷ የመቀጣትን አስከፊነት ያመለክታል። አላህን ወደ መፍራት የሚመራ መልዕክት ነው።
2/ ለሰሐቦች የተሰጠ ተአምር (ከራማ) ከሐዲሡ ውስጥ ተመልክቷል። የተምር ዛፍ ቁራጭ ሲያለቅስ እንደ ሰሙት ሁሉ ጀሃነም ሥር ላይ የወደቀን ድንጋይ ጓጓታ መስማት ቻሉ።
3/ አንድ ሰው የማያውቀው ነገር ሲገጥመው "አላህና መልዕክተኛው ያውቃሉ" ማለቱ የተወደደ ነው።
4/ አስተማሪ ስለ አንድ ነገር ከማስተማሩ በፊት የተማሪዎችን ትኩረትና ስሜት መሳብ መቻሉ ብልህነት ነው።
#አላህን__መፍራት_10

#ሐዲሥ 50/406

ዐዲይ ኢብኑ ሐቲም (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፦ ""ከእናንተ ውስጥ ጌታው ያለ አስተርጓሚ የማያናግረው ማንም የለም። (በዚያ ወቅት ሰውየው) ወደቀኙ ሲመለከት ካስቀደመው (ሥራ) ውጭ ምንም ነገር አይታየውም። ወደ ግራው ሴመለከት ካስቀደመው (ሥራው) ውጭ ምንም ነገር አይታየውም። ወደ ፊት ሲመለከትም ከፊት ለፊቱ ከእሳት ውጭ ምንም ነገር አያይም። በክፋይ ተምርም ቢሆን ከእሳት ተጠበቁ።" (ቡኻሪና ሙስሊም)

፨ ከሐዲሡ የምንማራቸው ቁምነገሮች

1/ ሐዲሡ ለምጽዋት ያነሳሳል። ጥቂት ነገርም ቢሆን መመጽወት ተገቢ ነው። መልካም ሥራ አይናቅም።
2/ በመልካም ሥራ መበረታታትና ከክፉ ሥራ መከልከል ያስፈልጋል። በመጭው ዓለም ከአላህ ፊት ሲቆሙ ከሐፍረት ለመዳን።
3/ አላህ በመጭው ዓለም ለባሮቹ ይቀርባል። በመካከላቸው ምንም ዓይነት ማዕከል (ዋሲጣ) ወይም አስተርጓሚ አይኖርም። ስለዚህም ሙእሚን ከርሱ ትእዛዝ ከማፈንገጥ መጠንቀቅ ይኖርበታል። እርሱው መስካሪ እርሱው ዳኛ ነውና።
4/ የሰው ልጅ በመጭው ዓለም ከመልካም ሥራው ውጭ ሌላ ምንም የሚጠቅመው ነገር የለም። ዘመድ፣ ገንዘብና ሥልጣን አይፈይደውም። ክብርና ዝና አይጠቅመውም።
#አላህን__መፍራት_12

#ሐዲሥ 50/408

አቡ በርዛህ ነድላት ኢብኑ ዑበይድ አል አስለሚይ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ "በመጭው ዓለም ማንም ሰው ዕድሜውን እንዴት እንዳሳለፈው፣ በዕውቀቱ ምን እንደሠራ፣ ገንዘቡንም ከየት እንዳገኘውና ለምን ተግባር እንዳዋለው፣ ጉልበቱንና አቅሙን ለምን ተግባር እንዳዋለው ሳይጠየቅ እግሩ አትንቀሳቀስም።' (ቲርሚዚ ዘግበውታል። ሐሰኑን ሶሒሕ ብለውታል)

፨ ከሐዲሡ የምንማራቸው ቁምነገሮች

1/ እድሜን አላህ በሚወደው ተግባር ላይ ለማለፍ መጣር።
2/ በኢኽላስ (በቅንነት) ለመሥራት መታተር።
3/ ገንዘብን ከሐላል ምንጭ ብቻ ማግኘትና ለመልካም ተግባራት ብቻ ማዋል።
4/ አካልን አላህ ከከለከለው ተግባር መጠበቅና አላህን ለመገዛት ግልጋሎት ማዋል።
5/ አንድ ሰው ጠቃሚ የሆነ ትምህርት መማር አለበት፡፡ በዚህ ዕውቀቱ ሊሠራበትና ሌሎችንም ሊጠቅም ይገባል። ይህም ለአላህ መሆኑ የግድ ነው።
6/ እያንዳንዱ ሰው በመጭው ዓለም በሥራው ይጠየቃል።
#አላህን__መፍራት_13

#ሐዲሥ 50/409

አቡ ሁረይራ (ረ.ዐ) እንዲህ ሲሉ አስተላልፈዋል። "የአላህ መልዕክተኛ (ﷺ) ፦ "(ምድር) የዚያን ቀን ወሬዋን ታወራለች፡፡" የሚለውን አንቀጽ ሲያነቡ ፦ "ወሬዋ ምን እንደሆነ ታውቃላችሁን?" በማለት ጠየቁ። "አላህና መልዕክተኛው ያውቃሉ" አሏቸው (ባልደረቦቻቸው)። "ወሬዋ እያንዳንዱ ሴት ወይም ወንድ ከጀርባዋ የሠራውን ማውራቷ ነው። በዚህ ቀን ይህን ይህን ሠርተሃል ትላለች። ወሬዋ ይህ ነው" አሉ። (ቲርሚዚ ዘግበውታል። ሐሰኑን ሶሒሕ ብለውታል።)

፨ ከሐዲሡ የምንማራቸው ቁምነገሮች

1/ ለመልካም ሥራ መነሳሳትና ከኃጢአት መራቅ እንደሚገባ።
2/ አላህ ምድርን ማናገር መቻሉ የወሰን የለሽ ችሎታው አካል ነው።
#አላህን__መፍራት_14

#ሐዲሥ 50/410

አቡ ሰዒድ ኹድሪ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ (ﷺ) እንዲህ አሉ፦ "የቀንዱ ባለቤት ቀንዱን ከአፉ አስገብቶ፥ (የምጽአት ጥሪ) ትእዛዝ ሲሰጠው ለመንፋት፥ ትእዛዝ በመጠባበቅ ላይ እያለ እንዴት ደስታ ይሰማኛል ? ይህ የመልዕክተኛው (ﷺ) አባባል ለባልደረቦቻቸው እጅግ ከበዳቸው። እርሳቸውም፦ "አላህ በቂያችን ነው። በርሱ መመካት ምን ያምር፥ በሉ" አሏቸው። (ቲርሚዚ ዘግበውታል። ሐሰን ነው ብለዋል)

ከሐዲሡ የምንማራቸው ቁምነገሮች

1/ የቀንዱ ባለቤት የምጽአት ቀን (ቂያማ) መድረሱን የሚያመለክት ጡሩንባ የሚነፋው መላኢካ ነው። በቀንድ እንደሚነፋ በቁርኣን ተገልጿል።
2/ ሐዲሡ የቂያማን ቀን መፍራትን ያስተምራል።
3/ ወደ አላህ መጠጋት፣ የርሱን እገዛ መጠየቅ፣ ለመልካም ተግባር መሽቀዳደም እንደሚገባም ይገልጻል።
4/ የአላህ መልዕክተኛ (ﷺ) ቂያማ በኡመታቸው (በሕዝባቸው) ላይ እንዳይከሰት የነበራቸውን ሥጋት ያሳያል። እኩይ በሆኑ የሰው ዓይነቶች ላይ እንደሚከሰት ቢያውቁም።
ቴሌግራም/ telegram/
https://www.tg-me.com/eslamic_center
#ጅኖች በምን መልኩ ወደ ሰውነታችን እንደሚገቡ ያውቃሉ?
1 :- #ተዘዋዋሪ :- ልክፍት ፣ስንቆጣ ፣ስንጨነቅ ፣የሚጠጋ ጅን ሲሆን አዑዙ ቢላህ ብለን ወይንም ውዱእ ብናደርግ ይሸሻል ።
2 :- #ጊዜአዊ:- ልክፍትበአንድ ቀን ፣ በሳምንት ወይም በወር አንድ ጊዜ የሚመጣ ሲሆን በጠዋት እና በማታ ዚክርና ሱረተል በቀራህ በማዘውተር እንዳይመለስ ማድረግ ይቻላል ።
3 : - #ቋሚ ፦ ልክፍት ከሰውነታችን አንድ አካል ላይ የሚቀመጥ ሲሆን ራስ ~ ሆድ ~ ማህፀን ~ ኣንዳንድ ጊዜም ሙሉ ሰውነታችንን ሊቆጣጠር ይችላል። በሩቅያ ሸርዕያ ይባረራል።
4: - #ውጫዊ ፦ ልክፍት እንስሳ መስለው የሚተናኮሉ ጀኖች ሲሆኑ እንቅልፍ ላይ በመምጣት ማነቅ ፣ ማፈን ፣ ሙሉ
አካላችንን እንዳይንቀሳቀስ ይጫኑናል : ውዱእ አድርጎ መተኛት አያተል ኩርሲይ እና ሌሎች መጠበቂያዎችን ቁርአኖች ቀርተን መተኛት ትልቁ መፍትሄ ነው።
5 :- #ተሸጋጋሪ፦ ልክፍት ከሰው ወደ ሰው የሚሸጋገሩ አስቸጋሪ ና ከባድ ጅኖች ሲሆኑ በተለይ ቤተሰብ ውስጥ በውርስ ይተላለፉል ። እነዚህም በሩቅያ ሸርዕያ ይባረራሉ።

በሲህር እና በጂን የሚመጡ በሽታዎች ዉስጥ በጥቂቱ ፡
የሚጥል በሽታ፤ ድብርት፤ ያለምንም ምክኒያት መስጋት፤ የእንቅልፍ እጦት፤ ከባድ የሆነ የመርሳት ችግር፤ ተደጋጋሚ እና ከባድ የሆነ ራሰ ምታት እና የጨጋራ በሽታ፤ ተከታታይ የሆነ ትኩሳት፤ ከባድ የሆነ የሰዉነት ድካም፤ ከተለመደው ዉጭ የሆነ ከባድ ቁጣ፤ ሳያስቡት መዉደቅ፤ የደም ስሮች መድረቅ፤
በእጅ እና በእግር ላይ መደንዘዝ እና ህመም መሰማት፤ የሳንባ ቁስለት፤ የእተነፋፈስ ችግር፤ ከባድ የሆነ ግሳት፤ ቶሎቶሎ ሽንት መሽናት፤ ሆድ በአየር መሞላት፤ አንዳንዴም ለብዙ ጊዜያት ሽንት አለመሽናት፤ እንግዳ የሆነ የቆዳ በሽታ፤ብዙዉን ጊዜ በምሽት በታፋ አካባቢ ማሳከክ፤ በድንገት ለመጥፎ ሱሶች (እንደ አልኮል መጠጥ፤ ሲጋራ፤ ዝሙት እና ለመሳሰሉት ) ፍላጎት ማሳየት፤ እጢ፤ ካንሰር፤ በሴቶች ተከታታይ የሆነ የፅንስ መጨናገፍ፤ ብዙ ደም መፍሰስ፤ በወር አበባ ጊዜ የጀርባ እና የሆድ ህመም፤ በወንዶች ላይ ስንፈተ ወሲብ፤ እና የመሳሰሉት ናቸዉ፡፡
እንዳጠቃላይ፤ በህክምና የማይድኑ ጊዜን ሰአት ለይተዉ የሚመጡ የጤና እክሎች በጂን በሲህር ወይም በቡዳ የሚመጡ እንደሆነ ልናዉቅ ይገባል፡፡
አያቱ ሩቂያህ
አያቱ ሩቂያህ ከቁርአን የተዉጣጡ አጫጭር ሱራዎች እና የቁርአን አያቶች (ምዕራፎች) ናቸዉ፡፡ አያቱ ሩቂያ ከሲህር ፣ ከቡዳ ፣ ከጂን እንዲሁም ከሌሎች ነገሮች ለመጠበቂያ እንዲሁም ለማፍሰጃ የሚቀሩ የቁርአን አያቶች ናቸዉ፡፡
አያቱ ሩቂያ ሰላሳ ሶስቱ የቁርአን አያቶች በመባል የሚታዎቁ ሰሆን እነሱም እንደሚከተሉት ናቸዉ፡-
ሱረቱ ፋቲሀ ፡ ምዕራፍ ከ 1–7
ሱረቱ በቀራህ ፡ ምዕራፍ ከ 1-5፣ 163፣ 255-257 እና 284-286
ሱረቱ ኢምራን ፡ ምዕራፍ 18፣ 26 እና 27
ሱረቱ አዕራፍ ፡ ምዕራፍ 54-56
ሱራቱ ኢስራ ፡ ምዕራፍ 110 እና 111
ሱረቱ ሙዕሚኑን ፡ ምእራፍ 115-118
ሱረቱ ሷፋት ፡ ምዕራፍ 1-11
ሱረቱ ረህማን ፡ ምዕራፍ 33-40
ሱረቱ ሀሽር ፡ ምዕራፍ 21-24
ሱረቱ ጂን ፡ ምዕራፍ 1-4
ሱረቱ ካፊሩን ፡ ምዕራፍ 1-6
ሱረቱ ኢኽላስ ፡ ምዕራፍ 1-4
ሱረቱ ፈለቅ ፡ ምዕራፍ 1-5
ሱረቱ ናስ ፡ ምዕራፍ 1-6
አላህ ሆይ! ከምቀኛ ከቅናተኛና ከክፉ ሰሪ መሰሪ ባንተ እንጠበቃለን። አላሁመ አሚን
«በዚህች ዓለም ላይ የሚኖር ሰው የኢማንን ጥፍጥና ካላገኘ፤
ከታላላቅ ዓለማዊ ቅጣቶች ውስጥ ዋናው አግኝቶታል።»
📮የቁርኣን ምክር 1⃣

💥(„...ከሰዎች ውስጥም ብዙዎች ያለ እውቀትና ማስረጃ በዝንባሌ፣ በስሜትና በግምት ብቻ ሰዎችን ያጠማሉ፤ ጌታህ ወሰን አላፊዎች እነማን እንደሆኑ ያውቃል። <እርሱም ወሰን አላፊዎችን አይወድም>„)
ከአል-አንዓም አንቀጽ 119 የተወሰደ።

💥ወሰን ከማለፍም ይሁን፣ ከወሰን አላፊዎችና በግምትና በስሜት ከሚነዱ ሰዎች እንድንጠነቀቅ ቁርኣን ይመክረናል!

💥በስሜት ከመመራትና ጠሞ ከማጥመም አላህ ይጠብቀን።
📮የቁርኣን ምክር 2⃣

💥(„...ሰዎችን ሊያጠም ያለ እውቀት አላህ ላይ ውሸትን ከሚቀጥፍ ሰው የበለጠ በዳይ ማን አለ?! አላህ በደለኛ ሰዎችን ቀናውን መንገድ አይመራቸውም።„)
ከሱረቱል-አንዓም አንቀጽ 144 የተወሰደ።

💥ውሸትን በራሱ እንድንጠነቀቅና ይበልጥ ደግሞ ያለ በቂና ትክክለኛ እውቀት ዲን ላይ በመናገር (ሐላል..ሐራም በማለት) አላህና መልእክተኛው ላይ መዋሸትና መቅጠፍን እንድንርቅ ቁርኣን አጥብቆ ይመክረናል!

መመለስ አሻፈረኝ ብለን ያለ እውቀት እየተመራንና እየመራን ከቀጠልን ከራሳችን አልፎ ሰዎችንም መበደላችን አይቀርም።
አላህ ደግሞ በደለኛን በዱኒያ ወደ ሐቅ ጎዳና፣ በኣኺረህ ደግሞ ወደ ጀነት መንገድ አይመራውም!
ስለዚህ አላህ ቀናውን መንገድ እንዲመራንና እንዲያስተካክለን ቀድመን እኛ እሱ ከከለከለን ነገሮች መከልከል ይገባናል።

💥ከበደልና አላህ ላይም ይሁን ሰዎች ላይ ከመዋሸት አላህ እራሱ ይጠብቀን!።
📮የቁርኣን ምክር 3⃣

💥ሙእሚኖች ጀነት ሲገቡ፤ („...የጀነትን መንገድና ጀነት ለመግባትም ያበቃንን መልካም ስራ ለመስራት ለመራን ጌታችን አላህ ምስጋናና ውዳሴ ይገባው!
አላህ ባይመራን ኖሮ አንመራም ነበር፣ የጌታችን መልእክተኞችም እውነትን ይዘው ነበር ወደኛ የመጡት።„ ይላሉ! "ይህች ትሰሩት በነበረው መልካም ስራችሁ ምክንያት የታደላችኋት/ በምሪት የተሰጠቻችሁ ጀነት ናት" ይባላሉ።)
ከሱረቱል-አዕራፍ አንቀጽ 43 የተወሰደ መልእክት።

💥ጀነት የሚገባው -በአላህ ፍቃድ- በስራ እንደሆነና ለውዷ ጀነት ውድ ጊዜአችንን በመስጠት የተለያዩ መልካም ስራዎችን በብዛት መስራት እንዳለብንና በስራችን ከመደነቅ ታቅበን ለመልካም ስራዎች ሁሉ ያበቃንና የመራንን አላህን ማመስገን እንደሚገባን ቁርኣን ይመክረናል።

💥የዱኒያ ባለስልጣን አንድን ሰው ቢወደው ወይም ቢያደንቀው ነገ ትቶት የሚሞትን ወይም የሚፈርስን ምድራዊ ቤት ነው የሚሰጠው!
አላህ ግን ባሪያውን ሲወደው መሞትና መሰደድ የሌለባትንና መቼም የማትፈርሰዋን ጀነት ነው የሚያድለው!።

ذَٰلِكَ فَضْلُ اللَّهِ يُؤْتِيهِ مَنْ يَشَاءُ ۚ وَاللَّهُ وَاسِعٌ عَلِيمٌ.

نسأل الله من فضله!
2024/06/28 11:09:03
Back to Top
HTML Embed Code: