Telegram Web Link
#ከጨረቃ_ጋር_ተያይዞ_አላዋቂ_ወገኖቻችን_ለሚያነሱት ውዥንብር የተሰጠ መልስ፦
=========== =======
«#ጨረቃም ለሁሉም የዘመን መለኪያ ናት”፤ ለዓለም ሁሉ ምልክት ናት፤ ”በእርሷም ቀን ይለያል፤ #በጨረቃም_የበዓላት_ምልክት_ይታወቃል»። [መጽሐፈ ሲራክ 43÷6-7]

እስልምናን ለመዝለፍ ቅድሚያ ክርስትናን ጠንቅቃችሁ እወቁ።
------------------------------------------------
መፅሀፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል:–

"ህዝቤ እውቀት ከማጣቱ የተነሳ ጠፍቷል፤ አንተም እውቀትን ጠልተሃልና እኔ ካህን እንዳትሆነኝ እጠላሃለሁ" (ትንቢተ ሆሴዕ 4:6)

ትላንት ማምሻውን በዓለም ላይ የሚገኙ ከሁለት ቢሊየን በላይ ሙስሊሞች የረመዳን ወር ጾም ፍቺ ዒድ በነገው ዕለት መሆን አለመሆኑን ለማረጋገጥ ጨረቃን ሲፈልጉ እንዳመሹ ይታወቃል።

ይህን ተከትሎም ስለ እስልምና እና ክርስትና በቂ ዕውቀት የሌላቸው አንዳንድ የክርስትያን ወገኖችም ሙስሊሞች ጨረቃን በመፈለግ በዓላቸውን (ዒድ) ለማክበር በሚያደርጉት ጥረት በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ሲስቁ ሲሳለቁ ከዚያም አልፈው የጨረቃ አምላኪዎች በማለት ሲወርፉ እና ሲያሾፉ በመመልከታችን በትንሹ ይህን ለማለት ወደድን።

የጨረቃን አቆጣጠር አስመልክቶ ስለ እስልምና የተሳሳተ ግንዛቤ ላላቸው ወገኖቻችን ሁሉ እውነታውን እንዲህ በዝርዝር እናሳውቃቸዋለን።

መፅሃፍ ቅዱሳዊ መረጃ
__________
አዲስ ጨረቃ የሚለው ቃል በባይብል 28 ጊዜ ተወስቷል፤ ጥቂቶቹን ለማየት ያህል፥

ዘሁልቁ 10፥10 ደግሞ በደስታችሁ ቀን፥ በበዓላታችሁም ዘመን፥ “በአዲስ ጨረቃ” ፥ በሚቃጠል መሥዋዕታችሁና በደኅንነት መሥዋዕታችሁ ላይ መለከቶቹን ንፉ እነርሱም በአምላካችሁ ፊት ለመታሰቢያ ይሆኑላችኋል እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።

#ጨረቃም ለሁሉም የዘመን መለኪያ ናት”፤ ለዓለም ሁሉ ምልክት ናት፤ ”በእርሷም ቀን ይለያል፤ #በጨረቃም_የበዓላት_ምልክት_ይታወቃል”።
(መጽሐፈ ሲራክ 43÷6-7)

መዝሙር 81፥3 “በአዲስ ጨረቃ” ቀን በከፍተኛው በዓላችን ቀን መለከትን ንፉ፤

«#ጨረቃን_ለጊዜዎች” አደረገ ፀሐይም መግቢያውን ያውቃል።» [መዝሙረ ዳዊት 104፥19]

ቅዱስ ቁርአንም እንዲህ ይላል
_______________
ከለጋ ጨረቃዎች ይጠይቁሃል፡፡ እነርሱ ለሰዎች ጥቅም ለሐጅም ማወቂያ “ #ጊዜያቶች_ምልክቶች ” ናቸው በላቸው፡(2:189)

በሐዲስም፦

አቡ ሁረይራህ”ረ.ዐ.” እንደተረከው የአላህ መልእክተኛ(ﷺ) እንዲህ አሉ፦ “መቼም ቢሆን ለጋ ጨረቃ በረመዳን ወር ስታዩ ፆምን ጀምሩ፤ የሸዋል ለጋ ጨረቃ ስታዩ ፆማችሁን ጨርሱ፤ ሰማይ ደመናማ ሲሆንላችሁ ፆም ሰላሳ ቀን መሆኑን አጢኑ። [ኢማም ሙስሊም መጽሐፍ 6, ሐዲስ 2378]

እንግዲህ በርካቶች ይህንን ነጥብ በቅጡ ባለመገንዘብ (በተለይ ሙስሊም ያልሆኑ ክርስትያን ወገኖች) ሙስሊሞች ጨረቃ እያየን የምንፆመው እና የምንፈታው #አምላካችን_ከጨረቃ_ጋር_ባለው_ግንኙነት_ምክኒያት_ይመስላቸዋል

አንዳንዶቹም ጭራሽ #ሙስሊሞች_ጨረቃን_ያመልካሉ እስከ ማለት ይደርሳሉ። እኛ ግን ጨረቃ ታየ አልታየ እያልን ፆማችንን እና ዒዳችንን የምንወስነው ከዚህ በመነሳት እንደሆነ ማስገንዘብ እንወዳለን። እንደሚታወቀው "ረመዳን" በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ካላንደር መሠረት በአመት ውስጥ ከሚገኙት አስራ ሁለት ወራት ውስጥ የአንዱ የወር ስም ነው። "ግንቦት" እንደማለት። የሂጅራ አቆጣጠር ደግሞ ጨረቃ ላይ የተመሠረተ ቀመር (Lunar system) ነው። ስለዚህ የረመዳን ወርን ጨምሮ እስልምና የሚያውቃቸው ዓመታዊ መርሃግብሮች በሙሉ ጊዜያቸው የሚወሠነው ይህንኑ የቀን አቆጣጠር ዘዴ ተከትሎ በመሆኑ እና በዚህ ዘዴ መሠረት አንድ ወር መግባቱ የሚታወቀው የጨረቃን መውጣት ተከትሎ በመሆኑ በረመዳን (እንደተቀሩት የሂጅራ ወራት) ጨረቃን እንጠባበቃለን።

👉 ሲጠቃለል #የመጽሀፍ_ቅዱስ እና #የቁርዓን ድጋፍ ያለው የሙስሊሞች ካሌንደር #በጨረቃ ላይ መመስረቱ #ጨረቃን_ከማክበር_ወይም_ማምለክ_ጋር የሚያገናኘው ነገር የለም። በጨረቃ የዒድ በዓላት ይታወቃሉ። የፋሲካ የመስቀል የጥምቀት እና ሌሎች መሰል የክርስትና በዓላት ግን በጨረቃ ያልተለዩ መጽሀፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ በዓላት ስለመሆናቸው ምንም ጥርጥር የሌለበት ጉዳይ በመሆኑ እነዚህ ሙስሊሞችን ጨረቃ አምላኪዎች የሚሉ አላዋቂዎች ወደ ባይብላቸው መጠው እነርሱም በዓላቶቻቸውን ጨረቃን አይተው ያከብሩ ዘንድ እንጋብዛቸዋለን።

ጨረቃን ለማየት በምናደርገው ፍለጋ ምክንያት በሙስሊሞች ላይ የምትሳለቁ ወገኖቻችን ሆይ !

መጽሀፍ ቅዱሳችሁም እንደሚያረጋግጠው በጨረቃም የበዓላት ምልክት ይታወቃሉና ልክ እንደ ዒድ ሁሉ የፋሲካ በአላችሁንም በጨረቃ ለይታችሁ ማክበር ሲገባችሁ ሙስሊሙን መስደብ መዝለፋችሁ እምነታችሁ የሚያዛችሁን የማታውቁ ናችሁ ብለን በድፍረት እንድንናገር አስደፍሮናል።

መጽሐፈ ሲራክ 43÷6-7 ”ጨረቃም ለሁሉም የዘመን መለኪያ ናት”፤ ለዓለም ሁሉ ምልክት ናት፤ ”በእርሷም ቀን ይለያል፤ በጨረቃም የበዓላት ምልክት ይታወቃል”*።

ስለዚህ ጨረቃ ለምልክቶች ለዘመኖች ለዕለታት ለዓመታትም ለበዓላት መለያ እና መለኪያ እንደሆነች ባይብላችሁ ሳይቀር እየተናገረ የምትቃወሙት ለምን ይሆን ?

"ህዝቤ እውቀት ከማጣቱ የተነሳ ጠፍቷል፤አንተም እውቀትን ጠልተሃልና እኔ ካህን እንዳትሆነኝ እጠላሃለሁ" (ትንቢተ ሆሴዕ 4:6)

ድንቁርና ወይስ ለቃሉ ትዕቢት አመጽ ክህደት ?

ጨረቃን ጠብቆ ፆም መያዝ፣ መፍታትና በዓል ማክበርን ለምን ትቃወማላችሁ ? መልሱን ለእናንተው። እያልን ቅድሚያ እስልምናን ለመዝለፍ ክርስትናን ጠንቅቃችሁ እወቁ ለማለት እንወዳለን።

_______________


By 👎 Join & Share

@eslamic_center
________________________________________

💟ተወዳዳሪ
👤️ Amar hassen
Code 78

plzzz..ሼር አድርጉልኝ🙏🙏

👍 በዉድድሩ መሳተፍ ለምትፈልጉ👍
👇👇👇
Join @Diinel_Islam
Join @Diinel_Islam
👆👆👆
🔂 ሼር 🔂 ሼር 🔂 ሼር 🔂

ክፍል ➐

(የበሩ ዘበኛም ከውስጥ በኩል፦"ማን ነህ?" ይላል። እሳቸውም፦"ሙሀመድ ነኝ" ይላሉ።
ዘበኛውም፦"እንኳን ደህና መጣህ...አንተ ከመግባትህ በፊት ለማንም በሩን እንዳልከፍት ታዝዤ ነበር።

ያንተ ኡመቶችም ጀነት ከመግባታቸው በፊት ለማንም ኡመት በር እንዳልከፍት ታዝዣለሁ" ብሎ በሩን ይከፍታል።)

እንዲህ ብለን ነበር ያቆምነው አይደል?!!! እሽ አሁን የጀነት ሰዎችን እዚሁ ጀነት መግቢያ ላይ እንተዋቸው'ና ወደ.ጀሀነሞቹ ልውሰዳችሁ
ባለፈው፦"ሁሉም የሚያመልከውን አካል ይከትል" ተብሎ ሙስሊም ያልሆኑ ካሃዲያን እና አማፂያን አማልክቶቻቸውን ተከትለው ሄደዋል ብለን አልነበር!!!? እሽ እነዚያ ሰዎች የት
እንደደረሱ እንከታተላቸው። መልካም ቆይታ....
__________________
_______

ሁሉም ካሃዲ የሚያመልከውን አማልክት ተከትሎ ሲሄዱ ያልጠበቁትን ነገር ከፊታቸው ይመለከታሉ።

ጀሀነም ልትቀራመታቸው ስትምዘገዘግ በተመለከቷት ግዜ ፊቶቻቸው በድንጋጤ ይጠቁራሉ...፣ አይኖቻቸው ከፍራቻ ብዛት ወደ ሰማያዊነት መቀያየር ይጀምራሉ...፣ ሰውነቶቻቸው በፍርሀት በመራድ መነፋፋት ይጀምራል...፣ ቆዳዎቻቸው መሻከር ይጀምራል...፣ በመፅሀፎቻቸው የሰፈረላቸውን የሀፅያት ዝርዝር በተመለከቱም ግዜ፦"ዋ ጥፋቴ" እያሉ ይቆጫሉ።

በጭንቀት ትካዜ ይዋልላሉ...፣ ተስፋቸውም ይሟጠጣል...፣ ፍርሃት እራሳቸውን ከቁጥጥራቸው ውጭ ያደርጋቸዋል...፣ አንገቶቻቸውን በማቀርቀር አይኖቻቸው በማዋለል እየሰረቁ ወደሚገቡባት ጀሀነም ይመለከታሉ...።

ይህን ሲመለከቱም ለአላህ እጅ በመንሳት ጥፋተኝነታቸውን በማመን ይጮሃሉ፤ ይሁን እንጂ ያ ቀን የፍርድ ቀን ብቻ ስለሆነ ጥያቄያቸው ውድቅ ይደረጋል።

በዚህ ሁኔታ ሙጅሪሞቹ ጥፋተኝነታቸውን አምነው...፣ በእንብርክካቸው በመንፏቀቅ እና በሰማያዊው እውር አይኖቻቸው ማፍጠጥ ይጀምራሉ።

ያን ቀን ልቦቻቸው ይዋልላሉ...፤ አያስተውሉም። አፎቻቸው ይንቀጠቀጣሉ...፤መናገር ይሳናቸዋል።

ዝምድናዎች ይቆራረጣሉ...፤ ማንም ስለማንም
አያሳስበውም። ያን ቀን የውሃ ጥም እርፍት ይነሳቸዋል...፤ነገር ግን አይጠጡም።

ይራባሉ....፤ ምግብ አያገኙም። እርቃናቸውን ናቸው...፤ አይለብሱም። በዚህ ሁኔታ ላይ ሳሉ ድንገት አላህ የጀሀነም ወታደሮችን አጋዦቻቸውን...፣ ሰንሰለቶችን...፣መዶሻዎችን... ይዘው እንዲመጡ ሲጠራቸው ከጀሀነም በመውጣት ሰልፍ ይዘው የአላህን ትዕዛዝ ይጠባበቃሉ።

ይህን ትዕይንት ሙጅሪሞቹ ሲመለከቱ በቁጭት ጣቶቻቸውን መንከስ ይጀምራሉ። አይኖቻቸው እንባ ያዘንባል...፣ በእግሮቻቸው መቆም እስኪሳናቸው ድረስ ይንቀጠቀጣሉ...፤ያን ግዜ ከሁሉም ነገር ተስፋ ይቆርጣሉ።

ከዚያም አላህ ለጀሀነም ወታደሮች፦" ያዟቸው...፣ እጆቻቸውን ከአንገቶቻቸው ጋር ጠፍሯቸው...፣ ከዚያም በያዛችሁት ሰንሰለት እሰሯቸው" ይላል።

ይህን የሀያሉን ትዕዛዝ የሰሙ የጀሀነም ወታደሮችም አንዱ ሰው ላይ ለ70 ሆነው ይረባረቡበታል። እጆቻቸውን ከአንገቶቻቸው ከጠፈሩ በኋላም ወፍራሙን ሰንሰለት በአንገቶቻቸው ላይ በመጠምጠም ያንቋቸዋል።

ከዚያም ግንባሮቻቸውን በመያዝ ወደኋላ አዙረው ከእግሮቻቸው ጋር ሲያስሯቸው አጥንቶቻቸው ይሰባበራል...።

ይህ ሲፈፀምባቸው አይኖቻቸው መንሸዋረር ይጀምራል...፣ የአንገቶቻቸውም ደም ስሮች እጅጉን ይወጣጠራሉ...።

የትከሻዎቻቸውም ስጋ መቃጠል ይጀምራል...(ገና እኮ ጀሀነም አልገቡም!!!) በሰውነታቸው የተጠመጠመው የሰንሰለት ግለት አናታቸውን እና አንጎላቸውን ያንተከትከዋል...፣ የሰንሰለቱ ግለት ቆዳዎቻቸውን እየላጠ መሬት ላይ በማንጠባጠብ የውስጠኛውን የቆዳቸውን ክፍል ወደ አረንጓዴነት ይቀይረዋል።

በአንገቶቻቸው ላይ የተጠመጠመባቸው ሰንሰለት የትከሻቸውን...፣የማጅራታቸውን እና የአንገቶቻቸውን ስጋ አንጠፍጥፎ መሬት ላይ በማራገፍ...ከንፈሮቻቸውን እና የፊት ቆዳቸውን ልጦ ጥርሶቻቸውን ያንጋጥጣል...።

ከዚያም ከፍተኛ የሙቀት ሀይልን የተሸከመው ንፋስ የጀሀነምን ወላፈን ይዞ ወደ ሙጅሪሞቹ መንፈስ ሲጀምር፤ እንፋሎቱ በደም ስሮቻቸው ዘልቆ በመግባት ውስጣቸውን ያደርቀዋል።

ይቀጥላል.....

የቤተሰባችን አባል ለመሆን ከፈለጉ እና ይሄን ትእይንት እስከ መጨረሻው ክፍል ድረስ ለመከታተል ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን መቀላቀል ይችላሉ👇

http://www.tg-me.com/eslamic_center
🔂 ሼር 🔂 ሼር 🔂 ሼር 🔂

ማድረግ እንዳትረሱ!!

ክፍል ➑

ከዚያም ከፍተኛ የሙቀት ሀይልን የተሸከመው ንፋስ የጀሀነምን ወላፈን ይዞ ወደ ሙጅሪሞቹ መንፈስ ሲጀምር፤ እንፋሎቱ በደም ስሮቻቸው ዘልቆ በመግባት ውስጣቸውን ያደርቀዋል።
______________________________

በዚህ ሁኔታ ላይም ሳሉ በአላህ ትዕዛዝ የጀሀነም
ወታደሮች ለሙጅሪሞቹ ከጀሀነም የመጣ ጥቁር...፣በጣም የሚገማ...፣እጅግ ከርዳዳ...፣በጣም የጋለ እና ተራራ ላይ ቢጣል ተራራውን የሚያቀልጥ የሆነን ልብስ ያለብሷቸዋል።

ከዚያም አላህ ለወታደሮቹ፦"ወደ መዘውተሪያዎቻቸው ውሰዷቸው" በማለት ትዕዛዝ ያስተላልፋል።

የጀሀነም ወታደሮችም ከመጀመሪያው ሰንሰለት በላይ ረዥም የሆነ እና እጅግ ጠንካራ የሆነ ሰንሰለት በማምጣት\ሙጅሪሞቹን እርስ በርስ ጀርባ እና ፊት እያደረጉ በማሰር በአፍጥሞቻቸው እየጎተቷቸው በጀሀነም በር ላይ አምጥተው ያሰልፏቸዋል።

ከዚያም መላዕክት፦"ይህች በርሷ ታስተባብሉባት የነበራችሁት እሳት ናት። ይህ ፊት ትሉ እንደነበራችሁት ድግምት ነውን?ወይስ እናንተ አታዩምን? ግቧት ታገሱም ወይም አትታገሱ በናንተ ላይ እኩል ነው።

የምትመነዱት ትሰሩት የነበራችሁትን ፍዳ ብቻ ነው" ይሏቸዋል። ከጀሀነም በር ላይ በቆሙ ግዜም የጀሀነም በሮች ባጠቃላይ ይከፈታሉ...፤ ግርዶሾቿም ይገለጣሉ።

ይህን ግዜ ጀሀነም ትንተከተካለች...ወላፈኗ ቀጠናውን ያናጋዋል። ከዚያም ልክ የከዋክብትን ብዛት የሚያክል ፍንጣሬ ከወደ ጀሀነም በኩል በመውጣት በከፍተኛ ፍጥነት ወደላይ መፈናጠር ይጀምራል።

ከዚያም ይህ ፍንጣሪ ወደ ላይ:ከወጣ በኋላ ተመልሶ ጀሀነም ደጅ ላይ በቆሙት ሙጅሪሞች ራስ ላይ መዝነብ ይጀምራል።

ያን ግዜ ፀጉሮቻቸው እየነደዱ መነቃቀል ይጀምራሉ። ከዚያም ጀሀነም በዘግናኝ እና በአስፈሪ ድምፅዋ፦"የእሳት ሰዎች ኑ ወደ እኔ...!!!! የእሳት ሰዎች ኑ ወደ እኔ...!!!! በጌታዬ ልቅና እምላለሁ እኔ ነኝ ምበቀላችሁ" በማለት ትጮሃለች።

ከዚያም ቀጠል አድርጋ፦"ስለሱ ቁጣ የምቆጣ እና ለጠላቶቹ መበቀያ ያደረገኝ ጌታ ምስጋና ይገባው።

ጌታዬ ሆይ!!! በግለቴ ላይ ግለትንr ጨምርልኝ....በጉልበቴ ላይም ጉልበትን ጨምርልኝ" ትላለች።

ከዚያም ከውስጧ ሌላ መላዕክት ይወጡ'ና በጅምላ እየሰበሰቡ ሙጂሪሞችን ወደ ጀሀነም በአፍጥማቸው መወርወር ይጀምራሉ።

ከውጭ በኩል ወደ ጀሀነም ሲወረወሩ ከጀሀነም ጥልቀት የተነሳ የጀሀነምን ተራራ ሊደርሱ 70 አመት ይፈጅባቸዋል...፣ ልክ የጀሀነምን ከፍተኛ ቦታ ላይ እንደወደቁም ከግለቱ ብዛት በአንድ ግዜ 70 ቆዳ ይቀያየርላቸዋል።

ልክ እዚያ ተራራ ላይ በአፍጥማቸው ሲደፉ በመጀመሪያ ሚበሉት ዘቁም የተባለን ምግብ ነው። ዘቁም እጅግ ትኩስ ሚለበልብ ምግብ ሲሆን ምሬቱ ለመግለፅ ይከብዳል እጅጉን እሾሃማም ነው።

ይህን ምግብ አግኝተው እሱን ማኘክ ሲጀምሩም መላዕክት አጥንት ሰባሪ የሆነ ምት በመምታት ከተራራው ላይ ወደ ሸለቆው ይወረውሯቸዋል።

ከተራራው የጀሀነምን ዝቅተኛ ክፍል እስኪደርሱ ድረስ 70 አመትን ይፈጅባቸዋል።ልክ ሸለቆው ላይ እንደተደፉትም ቆዳቸው ተላልጦ አሁንም 70 ግዜ ቆዳ ይቀያየርላቸዋል።

ያች እዚያ ተራራ ላይ ያኘኳት ምግብ ጉሮሮዋቸው ላይ በመጣበቅ ወደታች መውረድም ወደ ውጭ መውጣትም እንቢ ትላቸዋለች።

ይህን ግዜ የበሏት ምግብ እና ልባቸው ጎሮሮዋቸው ላይ ይጣበቃሉ። ከዚያ ውሀ እያሉ መጮህ ሲጀምሩ ከርቀት በጀሀንም ውስጥ ምንጭ ይመለከታሉ...፤ ወደዚያች ምንጭ በመጉረፍ ለመጠጣት ሁለም እንደከብት ወደታች ይዘቀዘቃሉ።

ከምንጯ ትኩስነት ብዛት ገና ለመጠጣት ወደሷ ሲያጎነብሱ የፊቶቻቸው ቆዳ እየቀለጠ ምንጯ ውስጥ መግባት ይጀምራል።

ከዚያ ግለት እራሳቸውን ለማትረፍ ቀና በማለት ላይ ሳሉም መላዕክቶች እግሮቻቸውን በመያዝ እያዘቀዘቁ እጥንት ሰባሪ ምት በመምታት ወደ ጀሀነም ጉድጓድ ይወረውሯቸዋል ......

ይቀጥላል...

የቤተሰባችን አባል ለመሆን ከፈለጉ እና ይሄን ትእይንት እስከ መጨረሻው ክፍል ድረስ ለመከታተል ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን መቀላቀል ይችላሉ👇

http://www.tg-me.com/eslamic_center
🔂 ሼር 🔂 ሼር 🔂 ሼር 🔂

ማድረግ እንዳትረሱ!! እሺ ውዶች!!

ክፍል ➒

ከዚያ ግለት እራሳቼውን ለማትረፍ ቀና በማለት ላይ ሳሉም መላዕክቶች እግሮቻቸውን በመያዝ እያዘቀዘቁ እጥንት ሰባሪ ምት በመምታት ወደ ጀሀነም ጉድጓድ ይወረውሯቸዋል።
_____________________________________

ይህን ግዜ 140 አመት ዳግም ቁልቁል ይዘልቃሉ...።ገና ጫፉን ሳይደርሱም ነበልባሏ...፣ ግለቷ...፣ወላፈኗ ይገርፋቸዋል።እዚያች ቦታ ላይ ሲደርሱም ከግለቷ ብዛት 70 ግዜ ቆዳ ይቀያየርላቸዋል።

የላይኛው ምንጭ መጨረሻው የሚገኘው በዚህኛው ሸለቆ ውስጥ ነው'ና ይህንንም ሸለቆ ተመልክተው ለመጠጣት ሲሄዱ ውሃው እጅግ ትኩስ ነው።

ልክ ሆዳቸው ውስጥ እንደገባ ከግለቱ እና ፍላቱ ብዛት 7 ግዜ ቆዳቸው ቀልጦ ይቀያየርላቸዋል።

ከዚያም የጠጡት ፍል ውሃም የሆድ እቃቸውን እየቆራረጠ በመቀመጫዎቻቸው መውጣት ይጀምራል። የተቀራው ስጋዎቻቸውን እየቆራረጠ ይጥለዋል። አጥንቶቻቸውንም ያቀልጥባቸዋል።

ከዚያም እያንዳንዱ መላዕክት 360 ጥርስ ያለውን ግዙፍ መዶሻ ይዘው በመምጣት ፊቶቻቸውን...፣ጀርባዎቻ ቸውን...እና ጭንቅላቶቻቸውን መምታት ይጀምራሉ።

በዚያ መዶሻ እየደበደቡ ወደ ሌላ ጉድጓድ ሲገፈትሯቸው እሳት ቆዳዎቻቸው ላይ መቀጣጠል ይጀምራል...፣የእስቱ እንፋሎትም ከሰውነቶቻቸው መትነንም ይጀምራል...፣ እዥ እና ምግልም ከሰውነታቸው መፍሰስ ይጀምራል...።

ከዚያም አይኖቻቸው እየወላለቁ በጉንጮቻቸው ላይ ይንጠለጠላሉ...፣በመቀጠልም በዱንያ ይታዘዟቸው ከነበሩት ሸይጣኖችም ጋር ሁለት ሁለት እየተደረጉ ይታሰራሉ።

ከዚያም እንደታሰሩ እጅግ ጠባብ ጉድጓድ ውስጥ፦"ዋ! ጥፋቴ" እያሉ ይወተፋሉ...፣ከዚያም ዱንያ ላይ ያጠራቅሙት የነበርውን ንብረቶቻቸው በማምጣት እዚያው ጀሀነም ላይ ይግል'ና ሰውነታቸው በንብረቶቻቸው ይተኮሳል።

ቅጣቱም ይበረታባቸው ዘንድ የሰውነታቸው መጠን እጅግ ግዙፍ ይደረጋል።አንድ የጀሀነም ሰው ቁመቱ የአንድ ወር መንገድ ሲያህል የጎን ስፋቱም የአምስት ቀን መንገድ ያህላል።

ጭንቅላቶቻቸውም የዐቅረእ (ሻም የሚገኝ ዳገት) ዳገትን ያህላል።በአፎቻቸውም 32 ጥርሶች ይበቅሉላቸዋል...፤ የታችኛው ጥርሶች ከጭንቅላቶቻቸው በኩል በስተው ሲወጡ፤ የላይኛዎቹ ደግሞ ከአገጮቻቸው በስተው ይወጣሉ።

የፀጉሮቻቸው ብዛት እና ጥንካሬ ደግሞ ልክ ዋርካ ይመስላል..። ይህን ሁኔታ ረሱል (ሰዐወ) እንዲህ ሲሉ ይገልፁታል፦"ነፍሴ በእጁ በሆነችው ጌታ እምላለው አንድ የጀሀነም ሰው እጁ ከአንገቱ ተጠፍሮ ሰንሰለቱን እየጎተተ ቢመጣ እና ፍጥረታት ቢመለከቱ ድንቅ መሸሽን ይሸሹ ነበር።"

ከዚያም ይህ የጀሀነም ግለት...፣ የክፍሎቿ ጥበት እና የውስጧ እንግልት ስጋዎቻቸውን ወደ አረንጓዴነት ይቀይረዋል።

አጥንቶቻቸውም ይቀልጣል...፣ አንጎሎቻቸውም እየቀለጠ በሰውነታቸው መፍሰስ ይጀምራል...፣ ምግል እና እዥም ሰውነታቸውን ያጠምቀዋል...።

ሰውነታቸውም እጅግ በመትላት የትሎቹ ብዛት ልክ የሚዳ አህያ ይመስላሉ...፣ ለነዝያ ትሎችም ልክ የነብር አይነት ጥፍርም አላቸው...፣ በዚህ ዘግናኝ ጥፍሮቻቸው በሙጅሪሞቹ ሰውነት በመሰካት ስጋቸውን ገንጥለው ያወጣሉ።

እንደተደናበረ አውሬ እጅግ በመጮህ እየተመላለሱ መንከስም ይጀምራሉ። ከዚያም መላዕክት ይመጡ'ና በድንጋዮች እና በጠጠሮች ፊቶቻቸውን እየጎተቱ ወደ ጀሀነም ባህር ይወስዷቸዋል።

ያ ባህር ርቀቱ 70 አመት ያስኬዳል እዚያ ባህር ዘንድ እስኪደርሱም በያንዳንዱ ቀን 70,000(ሰባ ሺህ) ግዜ ቆዳቸው እየተላላጠ ይቀየራል።

ከዚያም እዚያ ባህር ዘንድ ሲደርሱም የባህሩ ወታደሮች ይቀበሏቸው'ና እግሮቻቸውን በመያዝ ወደዚያ ባህር ይወረውሯቸዋል።

የዚያን ባህር ጥልቀት ያ የፈጠረው ጌታ እንጂ ማንም አያውቀውም። በቀደምት መፃህፍትም፦"የዱንያ ባህር ባጠቃላይ ከጀሀነ ባህር ጋር ሲነፃፀር ልክ ከትልቅ ከባህር አጠገብ እንዳለች ምንጭ ናት" ተብሎ ሰፍሯል።

እኚህ ሙጅሪሞቹም ልክ ባህሩ ላይ ተወርውረው ባህሩ ሰውነቶቻቸውን ሲነካው ከማቃጠሉ የተነሳ እርስ በርስ፦"እስካሁን የተቀጣነው ቅጣት ከዚህ ጋር ሲነፃፀር ልክ እንደ ህልም ነው" ይባባላሉ።

እዚያ ባህር ውስጥ ሲገቡም አንድ ግዜ ይሰምጣሉ ትንሽ ቆይተውም ይንሳፈፋሉ።ወደ ውስጥ አንድ ግዜ ሲሰምጡ 70 ባዕ ያህል ይሰምጣሉ (እያንዳንዱ ባዕ ልክ የምስራቅ እና የምዕራብን ያህል እሩቅ ነው።)

ሞትን ቢመኙትም በፍፁም አያገኙትም። ከባህር ውስጥ ለመተንፈስ አፋቸውን አንድ ግዜ ብቅ ሲያደርጉም በዚያች ቅፅበት 70,000 (ሰባ ሺህ) መላዕክት እየተሻሙ በያዙት መዶሻ ይመቷቸዋል...፤አንዱም አይስትም።(ሩህማካ ያ አላህ)........

ይቀጥላል.........

የቤተሰባችን አባል ለመሆን ከፈለጉ እና ይሄን ትእይንት እስከ መጨረሻው ክፍል ድረስ ለመከታተል ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን መቀላቀል ይችላሉ👇

http://www.tg-me.com/eslamic_center
🔂 ሼር 🔂 ሼር 🔂 ሼር 🔂

ማድረግ እንዳትረሱ!! እሺ ውዶች!!

ክፍል ➓

በባለፈው ዳሰሳችን የጀነት ሰዎችን በር ላይ አቁመናቸው አይደል ወደ ጀሀነሞቹ የሄድነው!!? በሉ አሁን ጉዞ ወደ ጀነት...፤መቼም አንመለስም በዚህ ዙር።

ግን ጀነት በር ላይ ያሉ ሰዎች ጀነት ከመግባታቸው በፊት ጀነት ምን እንደሆነች እና ለአንድ ሰው የተዘጋጀውን ቀድመን እኛ እንግባ'ና እንይ...በሉ ኑ ሁላችሁም። ደሞ ለጉብኝት ነው ምንገባው ተፍተፍ እንዳትሉ...!!!😂

______________________

ጀነት አዕምሮ አሰላስሎ ሊገምት የማይችለው አይነት ውብ እና በአላህ እጆች የተገነባች የፈጣሪ ድንቅ የምህንድስና አሻራ ያረፈባት ምርጥ ሀገር ናት።

ጀነት የሚገባ ሰው ቁመቱ ልክ እንደ አባቱ አደም 60 ክንድ ነው።(30ሜትር) ለአንድ ሰው የተዘጋጀለት ጀነት ስፋቱ እንደየደረጃው ቢለያይም የመሀከለኛው ጀነት ስፋት ልክ የመሬትን እና የሰማይን ስፋት ያህላል።

(አስተውል ለአንድ ሰው ነው) የጀነት መሬቱ ከወርቅ የተሰራ እምነ በረድ ሲሆን...፣የአፈሯም መዓዛ እንደ ሚስክ ያውዳል...፣ብሎኬቱ ከአልማዝ እና ከወርቅ ቅልቅል የተሰራ ሆኖ የብሎኬቱ ማያያዣም ዛዕፈራን እና ሚስክ ነው።

ጀነት እንደ ግዝፈቱ እና ስፋቱም ሁላ በውስጡም ትልቅ ቤተ መንግስት አለ...፣እዚያ ቤተ መንግስት ውስጥ ሲገባ በውስጡ ሌላ 70 ቤተመንግስቶች አሉበት...፣

በያንዳንዱም ቤተመንግስት ውስጥ 70 ውብ ቤቶች ይገኛሉ...፣እዚያ ውስጥ ያሉ ቤቶች ከከበሩ ድንጋዮች እና ከአልማዝ የተሰሩ ሲሆኑ፤ የያንዳንዱ ቤት ቁመቱ ከመሬት እስከሰማይ ያህል'ና የጎኑ ስፋትም እንደዚያው ነው።

በያንዳንዱ ቤት 4000 (አራት ሺህ) መስኮቶች ይገኛሉ።እያንዳንዱ ቤት ውስጥም ከአልማዝ እና ከተለያዩ ማስዋቢያዎች የተሰሩ አልጋዎች ሲኖሩ...፤ምንጣፋቸውም ከሀር የተሰራ ነው።

ከአልጋው በስተ ቀኝ እና በስተ ግራ በኩል 400(አራት ሺህ) ከወርቅ የተሰሩ ወንበሮች አሉ።

የወንበሮቹ እግሮችም ከቀያይ አንፀባራቂ አልማዝ የተሰሩ ናቸው። በዚያ አልጋ ላይ ብቻ 70 ፍራሾች ሲገኙ የእያንዳንዱ ፍራሽ መልኩ ይለያያል፤ የትኛውም ሌላኛውን አይመስልም።

ለጀነቲቱ ባለቤት ከሀር የሆነ እና አረንጓዴ እጅግ ማራኪ ልብስ ተዘጋጅቶለታል። ለትከሻውም ከተለያዬ ከወርቅ አይነቶች እና አልማዞች የተሰራ ጌጥ ተዘጋጅቶለታል...፣ ለሰውየውም ለጭንቅላቱ ከወርቅ የተሰራ አንፀባራቂ ዘውድ ተዘጋጅቶለት፤ በዚያ ዘውድ ላይም ሰባ ማዕዘናት ይኖሩታል።

በያንዳንዱ ማዕዘን ላይ አንዲት ድንቅ ጌት ትደረጋለች...፤ ያች ድንቅ ጌጥ ምድር ላይ ብትወርድ የዱንያ ንብረት ተሰብስቦ የሷን ዋጋ አያወጣም።

ለእጁ 3 አንባሮች ይዘጋጅለታል፦
1፦ከወርቅ
2፦ከአልማዝ
3፦ከሉል

እንደዚሁም ለእግሩ እና ለእጅ ጣቶቹ የወርቅ እና የአልማዝ ቀለበት ይዘጋጅለታል።እፊትለፊቱም 10,000 (አስር ሺህ) አገልጋዮች ይሰለፋሉ....፤እነዚያ አገልጋዮች መቼም አያረጁም ሁሌም ውብ ናቸው።

(እንዲህ እያልኩ ሳወራ ለወንዶች ሙስሊሞች ብቻ እንዳይመስላችሁ ለሴቶቹም ጭምር ነው።ለንግግር ይመች ዘንድ ነው በአንድ ፆታ የተጠቀምኩት።)

በቀይ አልማዝ የተሰራ ጠረጴዛም ይዘጋጃል...፤ያ ጠረጴዛም ስፋቱ 1.6 km ሲያህል ርዝመቱም እንደዛው ነው።(የኪታቡ ነስ 1 ማይል ነው የሚለው፤ ለናንት ይመች ዘንድ በkm ቀይሬዋለሁ።)

በዚያ ጠረጴዛ ላይም 70,000 (ሰባ ሺህ) ሳህኖች ሲኖሩ...፤ ሰህኖቹም ከወርቅ እና ከአልማዝ የተሰሩ ናቸው።በያንዳንዱ ሳህንም 70 አይነት የምግብ አይነት ሲኖር የትኛውም ከየትኛውም ጣዕሙም መልኩም አይመሳሰልም።

ምናልባት ያ ሰው ከነዚህ ምግቦች እየተመገበ ሳለ ድንገት ሊጎርስ በሆነበት ሁኔታ ሌላ የተሸለ ምግብ ቢያምረው ያበእጁ የያዛት ጉርሻ በቅፅበት ወዳማረው የምግብ አይነት
ትቀየርለታለች።........

ይቀጥላል.......


የቤተሰባችን አባል ለመሆን ከፈለጉ እና ይሄን ትእይንት እስከ መጨረሻው ክፍል ድረስ ለመከታተል ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን መቀላቀል ይችላሉ👇

http://www.tg-me.com/eslamic_center
🔂 ሼር 🔂 ሼር 🔂 ሼር 🔂

ማድረግ እንዳትረሱ!! እሺ ውዶች!!

ክፍል ➊➊

ምናልባት ያ ሰው ከነዚህ ምግቦች እየተመገበ ሳለ ድንገት ሊጎርስ በሆነበት ሁኔታ ሌላ የተሸለ ምግብ ቢያምረው ያበእጁ የያዛት ጉርሻ በቅፅበት ወዳማረው የምግብ አይነት ትቀየርለታለች።
____________________________________________

እፊት ለፊቱም ካዲሞቹ በእጆቻቸው ከአልማዝ እና ከወርቅ የተሰሩ ኮባያዎችን እና ሳህኖችን ይዘው ይቆማሉ።

በነዚያ ኩባያዎች ከምር እና ውሃ አለበት።(ከምር እዛ ጣጣ የለውም፤ እዚህ ካልጠጣህ እዛ ንፁውን ትጠጣለህ። እዚጠንከር በል።)

አላህም ለሰውዬው የ40 ሰው አቅም ይሰጠው'ና ከያንዳንዱ የምግብ አይነት በሚገባ በልቶ ሲጠግብ...፤ ካዲሞቹ የፈለገውን አይነት መጠጥ ይቀዱለታል።

ያን ጠጥቶ ሲያበቃ አላህም 100,00 እጥፍ የምግብ ፍላጎት ይከፍትበታል።(40×10,000=400,000 የአራት መቶ ሺህ ሰው የመብላት አቅም ይሰጠወል)አሁንም ልክ የቅድሙን ያህል ዳግም እየጣፈጠው ይመገብ'ና ዳግም ይጠጣል።

ምግቡንም ካበቃ በኋላ ከበር በኩል ግዙፍ የሆነ የወፍ መንጋ ይገባ'ና በሰውዬው ዙሪያ እያዜሙ እንዲህ ይላሉ፦"አንተ የአላህ ወዳጅ ሆይ! እኔን ተመገበኝ፤ እኔ እኮ እንዲ እንዲ... በተባለ በጀነት ማሳ ውስጥ እንዲ...እንዲ የተባለን መጠጥ እየጠጣሁ ነው ያደግኩት" ከዚያም ሰውየውም ያማረውን እየመረጠ መብላት ይጀምራል።

ጅነት ውስጥ አራት ጅረቶች ይገኛሉ።
1፦ንፁህ ውሃ
2፦ወተት
3፦ማር
4፦ከምር(የማያሰክር)

እነዚህን መጠጦች ሰውየው ከመጠጣቱ በፊት በመረጠው መጠጥ ላይ አራት መበረዣዎች ይበረዙበታል።
1፦ዘንጀቢል (ዝንጅብል እንዳይመስላችሁ)
2፦ተስኒም
3፦ካፉር

እነዚህን መጠጦች ሲጠጡ አላህ የተለያዩ መጠጦችን እንዲጠጡ ባይወስን ኖሮ ሰውዬው በአፉ ኩባያውን ደቅኖ ይቀር ነበር፤ ከጥፍጥናው ብዛት።

ጀነት ውስጥ እጅግ በጣም ለቁጥር አዳጋች የሆነ የዛፍ ብዛት አለ።አንዷ ዛፍ የጥላዋን ስፋት 500 አመት ፈረሰ ቢጋልበው አይቆርጠውም።

ያች ዛፍ ፍሬዎቿ ከቅቤ በላይ ለስላሳ ሲሆኑ ጥፍጥናቸውም ከማር ይበልጣል።የጀነት ዛፍ ቅርንጫፉ ወደታች ያዘቀዘቀ ሲሆን ስሩ ደግሞ ወደ ላይ ነው፤ ፍሬዎቿን ለመቅጠፍ እጅግ ምቹ ናቸው።

በአንዷ ዛፍ ላይ ብቻ 70,000(ሰባ ሺህ) አይነት ፍራፍሬዎች ይበቅልባታል።እያንዳንዱ ፍራፍሬ ከሌላው በጣዕምም በመልክም ይለያያል። ሌሎች ዛፎችም ይገኛሉ።

እነዚያ ዛፎች የተለያዩ የሀር ማጌጫ ልብሶችን እና ሽቶዎችን ያበቅላሉ። ከነዚህ ዛፎች ውስጥ ደግም አንድ ግሩም እና የግዝፈትን ጫፍ የደረሰች ግዙፍ ዛፍ ትገኛለች።

ያች ዛፍ አንድ ፈረስ ጋላቢ 700 አመት ቢጋልባት ጥላዋን ማቋረጥ አይችልም። ከዛፏ ታችም ጅረት ይወርዳል። በዚያች ዛፍ እጅግ ብዙ ቅርንጫፎች አሏት...።

በያንዳንዱ ቅርንጫፍ ስር ትላልቅ ከተማዎች ይገኛሉ። የአንዱ ከተማ የጎኑም የቁመቱም ስፋት1,000 ማይል /16,000km ያህላል።

በያንዳንዱ ከተማ መሀከል ያለው ርቀትም የምስራቅን እና የምዕራብን ያህል ርቀት ነው።የሰልሰቢል ምንጭ ውሃም ከዚያች ዛፍ ውስጥ ነው የምትመነጨው።

የዚያች ዛፍ አንዲት ቅጠል ብቻ እጅግ ብዙ ህዝቦችን ማስጠለል ትችላለች። ጀነት ውስጥ ሁረልዒኖችም አሉ...።አንዲት ሁረልዒን በባህር ላይ ትንሽ ምራቋን ጠብ ብታደርግ ዱንያ ላይ ያለው ባህር ባጠቃላይ ማር ማር ይል ነበር።

የሷ አንድ ዘለላ ፀጉር ወደ ዱንያ ብቅ ቢል ኖሮ ከፀጉሯ ኑር ብዛት ፀሀይ ትደበዝዝ ነበር።የዚህች እንስት አንዲት መቅረቢው ዱንያ ላይ ቢገመት ምድር ላይ ያለው ንብረት ተሰብስቦ ዋጋውን ማውጣት አይችልም...።

ባጠቃላይ ስለሁረልዒን ተዘርዝሮ አያልቅም። ግን ደስ የሚለው ሙዕሚን ሴቶች የሁረል ዒኖች እመቤቶች ናቸው።

በአጭሩ ይህን ያህል ስለጅነት ምንነት ከዳሰስን እስቲ አሁን ደግሞ በር ላይ ያሉትን ሰዎች እናስገባቸው።.......

ይቀጥላል.........

የቤተሰባችን አባል ለመሆን ከፈለጉ እና ይሄን ትእይንት እስከ መጨረሻው ክፍል ድረስ ለመከታተል ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን መቀላቀል ይችላሉ👇

http://www.tg-me.com/eslamic_center
🔂 ሼር 🔂 ሼር 🔂 ሼር 🔂

ማድረግ እንዳትረሱ!! እሺ ውዶች!!

ክፍል ➊➋

በአጭሩ ይህን ያህል ስለጅነት ምንነት ከዳሰስን እስቲ አሁን ደግሞ በር ላይ ያሉትን ሰዎች እናስገባቸው።.......
________________________________________________

እነዚህ ቁጥር ስፍር የሌላቸው እና የቂያማ እለት እንግልት ያንቃቃቸው ሰዎች ልክ ጀነት ሲከፈት ሁሉም የወጣትነት እድሜው ላይ ይደረግ'ና ወደ ተመደበለት የጀነት ስፍራ ያለ ምንም ግፊያ ያቀናል።

ከዚያም ሁሉም ቦታ ቦታውን ከያዘ በኋላ ለሁሉም በሚሰማ መልኩ፦"የጀነት ሰዎች ሆይ!!! ቤቶቻችሁን ወዳችኋልን?" የሚል ጥሪ ከወደላይ በኩል ይመጣል።

የጀነት ሰዎችም፦"አዎን ወላሂ ጌታችን የክብር ቤት ውስጥ አስገብቶናል...፤ከሷ ቅያሪም አንፈልግም።የጌታችንንም ጉርብትና ወደናል..." ይላሉ።

ከዚያም አላህ፦"እናንተ የጀነት ሰዎች!!!" ብሎ
ይጠራቸዋል። እነሱም፦"አቤት ጌታችን ክብር ይገባህ" ይላሉ። አላህም፦"ወደዳችሁት?" ይላቸዋል።

እነሱም፦"እንዴት አንወደውም!!! ከፍጥረትህ ለማንም ያልሰጠኸውን ለኛ ሰጥተኸናል" ያላሉ። አላህም፦"ከዚህ የተሻለ ልስጣችሁ?" ይላቸዋል።

እነሱም፦"ከዚህ የተሻለ ምን አለ?" ይሉታል። አላህም፦" ውዴታዬን እናንተ ላይ አሰፍናለሁ በፍፁም በናንተ አልቆጣባችሁ" ይላቸዋል።

ከዚያም አክለው፦"ጌታችን ሆይ!!! ፊትህን ማየት እንፈልጋለን ናፍቀንሀል። የኛም ትልቁ ምንዳችን ያንተን ፊት ማየት ነው" ይላሉ።

ጀነት ውስጥ ዳሩ ሰላም የተባለች ቦታ አለች እና አላህም ለዚያች ቦታ፦"ጌጣጌጥሽን ይዘሽ ተዋቢ...፤ለባሮቼ ጉብኝት ቦታዎችሽንም አስውቢ" ይላታል። ዳሩ ሰላምም ለጌታዋ ትዕዘዝ እጅ ነስታ ትዋባለች።

ከዚያም አላህ ህዝቡን ወደ ዳሩ ሰላም እንዲጠራ አንድን መልዓክ ያዘዋል።ይህም መልዓክ ከአላህ ዘንድ በመውጣት በማራኪ እና በተረጋጋ ድምፁ፦"እናንተ የአላህ ወዳጆች የጀነት ሰዎች ሆይ!!! ኑ ጌታችሁን ዘይሩት" ብሎ ይጣራል።

ከዚያም ሁሉም በተዋቡ ዙፋኖች ሁነው በንፋስ እየተንሳፈፉ ወደ ዳሩ ሰላም ይተማሉ።በሩ ላይም ሲደርሱ፦" ከጌታችን የሆነ ሰላም በኛ ላይ ይሁን" ይላሉ።(ይህ ሰላምታቸው ነው።)

ከዚያም ይፈቀድላቸው'ና ወደ ውስጥ ይገባሉ።(ኧረ ምን ይገባሉ ብቻ ወላሂ እኛም እንገባታለን ኢንሻ አላህ) ከዚያም ከዐርሽ ታች በኩል መሲራ የተባለች ንፋስ መጥታ
ታውዳቸዋለች።

ከዚያም ወደ ውስጥ ዘልቀው ሲገቡ የጌታችንን የአላህን አርሽ ይመለከታሉ....፤አርሹ በኑር እያብለጨለጨ እና እያንፀባረቀ አሸብርቋል።

ሰዎቹም፦"ጌታችን ጥራት ይገባህ አንተ የተቀደስክ ነህ!! የመላዕክት እና የመንፈሱም ጌታ ነህ!!! ጌታችን አንተ የተባረክህ ስትሆን የላቅህም ነህ!!! ፊትህን ግለፅልን እንይህ" ይላሉ።

ይቀጥላል.........

የቤተሰባችን አባል ለመሆን ከፈለጉ እና ይሄን ትእይንት እስከ መጨረሻው ክፍል ድረስ ለመከታተል ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን መቀላቀል ይችላሉ👇

http://www.tg-me.com/eslamic_center
🔂 ሼር 🔂 ሼር 🔂 ሼር 🔂

ማድረግ እንዳትረሱ!! እሺ ውዶች!!

ክፍል ➊➌

ሰዎቹም፦"ጌታችን ጥራት ይገባህ አንተ የተቀደስክ ነህ!! የመላዕክት እና የመንፈሱም ጌታ ነህ!!! ጌታችን አንተ የተባረክህ ስትሆን የላቅህም ነህ!!! ፊትህን ግለፅልን እንይህ" ይላሉ። (እንዲህ ብለን አይደል ያቆምነው!!!)
________________________________________________

ከዚያም አላህም ከኑር(ከብርሃን) የተሰራውን ግርጆ፦"ተገለጪ!" ይላል። ግርጆዋም ትገለጣለች። አንዱ ብርሃናማ ግርጆ ሲገለጥ ቀጣዬ ግርጆ ብርሃኑ የመጀመሪያውን 70 እጥፍ ያህላል።

አንዱ ግርጆ ሲገለጥ...የብርሃኑ ድባብም አከባቢውን ሲያሸበርቅ፤ ሰዉም ኑሩን መቋቋም አቅቷቸው ሱጁድ ሲደፉ፤ 70 ግርጆዎች ይገለጣሉ።

ይህን ግዜ አላህ ብቅ ይላል።(ሱብሀነክ ያ መውላና) እነሱም ልክ አላህን እንደተመለከቱትም ለረዥም ዘመናት ሱጁድ ላይ ይደፋሉ።

ሱጁድ ላይ ሁነውም፦"አንተ የተጥራራህ ነህ፤ ምስጋና ይገባህ ጥራት ላንተ ለዘለአለም ይገባህ።

ከእሳት አድነኸን ጀነትን አስገብተኸናል....፤ምንኛ ያማረ ቤት ነው መውደድን ሁሉ ወደናል፤ አንተም ውደደን" ይላሉ።

አላህም፦"እኔም መውደድን ሁሉ ስለእናንተ ወድጃለሁ። አሁን የስራ(የአምልኮ) ግዜ አይደለም...ነገር ግን ይሄ የደስታ ቅፅበት ነው፤ የፈለጋችሁትን ጠይቁኝ እሰጣችኋለሁ....፤የፈለጋችሁትንም ተመኙ እጨምርላችኋለሁ" ይላቸዋል።

ይህን ግዜ ምንም ሳይናገሩ በውስጣቸው አላህ ይህን ኒዕማ እንዲያዘውትርላቸው ይመኛሉ። አላህም፦"የተመኛችሁትን ሁሉ እሰጣችኋለሁ፤ እንደውም በሰጠኋችሁ ያህል እጥፍ እደርብላችኋለሁ" ይላቸዋል።

ከዚያም ሰዎቹ በሱጁድ የተደፋውን ጭንቅላታቸውን ሲያነሱ የአላህ ኑር ወደ ፊቱ እንዳይመለከቱ ያንፀባርቅባቸዋል።

ይህ ትዕይንት " ﺷﺮﻗﻲ ﻗﺒﺔ ﻋﺮﺵ ﺭﺏ ﺍﻟﻌﺎﻟﻤﻴﻦ "
ይባላል። ከዚያም አላህም፦" ባሮቼ...፣ ጎረቤቶቼ...፣ምርጦቼ...፣ወዳጆቼ....ውዶቼ...፣ ፍጥረቴ ምርጦች....፣ ታዛዦቼ እንኳን ደህና መጣችሁ" ይላቸዋል።

ከአላህ አርሽ ፊትለፊት ከኑር የተሰሩ ሚንበሮች...፣ ዙፋኖች እና ምንጣፎች ይዘጋጁ'ና አላህም፦"ኑ እንደየክብራችሁ ደረጃ ተቀመጡ" ሲል ግዜ መጀመሪያ ሩሱሎች ይመጡ'ና በሚንበሮቹ ላይ ይቀመጣሉ(ሩሱል እና ነቢይ ተልዕኮዋቸው አንድ ቢሆንም ደረጃቸው ይለያያል።

የሩሱልነትን ማዕረግ እና የነቢይነት ማዕረግም አንድ ሰው ሊጎናፀፍ ይችላል።) ከዚያም ነቢያቶች ይመጡ'ና በዙፋኖቹ ላይ ይሆናሉ....፣ከዚያም ደጋግ የአላህ ባሮችም ይመጡ'ና በተዘጋጀላቸው የክብር ቦታ ይቀመጣሉ።

በመቀጠልም በፊትለፊታቸው ከኑር የሆነ እና አንፀባራቂ ማዕድ ይዘረጋላቸዋል።ከዚያም አላህ ለአገልጋዮቹ፦"ባሮቼን መግቧቸው" ይላቸዋል።

በመቀጠልም በያንዳንዱ ማዕድ 70,000(ሰባ ሺህ) ከወርቅ እና ከያቁት የተሰራ ሳህን ይደረደራል።በያንዳንዱ ሳህንም 70 የተለያየ የምግብ አይነት ይደረግበታል....።

ከዚያም አላህ፦"ብሉ ባሮቼ" ይላቸዋል።ከዚያም በደንብ በሚገባ ከበሉ በኋላ ምግቡ በጣም ጣፍጧቸው እርስበርስ፦"አሁን የበላነው ምግብ እዚያ ጀነት ውስጥ ካለው ጋር ሲነፃፀር ያ ምግብ እንደ ህልም ነው" ይባባላሉ።

ከዚያም አላህ ለአገልጋዮቹ፦"ባሮቼን አጠጧቸው" ይላቸዋል።ሁሉም ልክ መጠጡን አጣጥመው ከጠጡ በኋላ እርስበርስ፦"አሁን የጠጣነው መጠጥ ጀነት ላይ ካለው ጋር ሲነፃፃር ያኛው እንደ ህልም ነው" ይባባላሉ።

ከዚያም አላህም ለካዲሞቹ፦"ባሮቼን አብልታችኋቸዋል አጠጥታችኋቸዋል አሁን ደግም ፍራፍሬ አምጡላቸው" ብሎ ያዛቸዋል።

ከዚያም የጥፍጥናው ስሜት የእግር ጥፍር ድረስ የሚደርስን አይነት ጣፋጭ ፍራፍሬ ያቀርቡላቸው'ና እሱንም በልተው ሲያበቁ እርስበርስ፦" አሁን የበላነው ፍራፍሬ ከጀነቱ ጋር ሲነፃፀር ያኛው ልክ እንደ ህልም ነው" ይባባላሉ።

አላህም ለካዲሞቹ፦"ባሮቼን አብልታችኋቸዋል አጠጥታችኋቸዋል ፍራፍሬም መግባችኋቸዋል አሁን ደሞ ልብስ አምጡላቸው...አስውቧቸው...አስጊጧቸው" ይላቸዋል።

ይቀጥላል.....

የቤተሰባችን አባል ለመሆን ከፈለጉ እና ይሄን ትእይንት እስከ መጨረሻው ክፍል ድረስ ለመከታተል ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን መቀላቀል ይችላሉ👇

http://www.tg-me.com/eslamic_center
🔂 ሼር 🔂 ሼር 🔂 ሼር 🔂

ማድረግ እንዳትረሱ!! እሺ ውዶች!!

ክፍል ➊➍

አላህም ለካዲሞቹ፦"ባሮቼን አብልታችኋቸዋል አጠጥታችኋቸዋል ፍራፍሬም መግባችኋቸዋል አሁን ደሞ ልብስ አምጡላቸው...አስውቧቸው...አስጊጧቸው" ይላቸዋል።

ከዚያም ልብሶችን እና የክብር ጌጦችን አምጥተው ያለብሷቸዋል። ይህን ግዜ እርስበርስ፦"ይህ ልብስ ጀነት ውስጥ ካለው ጋር ሲነፃፀር ያኛው እንደ ህልም ነው" ይባባላሉ።

(በነገራችን ላይ ከቂያማ አንስቶ እስካሁን ድረስ ባሉን ዝግጅቶቻችን ላይ የተጠቀምኳቸውን ኪታቦች ያልገለፅኩላችሁ መቋጫው ላይ አሰፍረዋለሁ ብዬ ነው።)

በዚህ ሁኔታ ሙእሚኖች እጌታቸው ዘንድ እየተዝናኑ ሳለ አንዲት ቀዝቃዛ ንፋስ ከወደ አርሽ በኩል ወደነሱ መንፈስ ትጀምራለች።

መልኳ ከበረዶ በላይ የነፃ ሲሆን ቅዝቃዜዋ ማዓዛዋን ይልቅ እንዲያውድ አድርጎታል። ሁሉንም በመዓዛዋ በማከናነብ ጠረናቸውን ሙሉ በሙሉ ትቀይረዋለች።

ከዚያም ንፋሷ ፊትለፊታቸው ላይ ያለውን ማዕድ ጠራርጋ በማንሳት ቦታውን ንፁህ ታደርገዋለች። ከዚያም ዳግም አላህ፦"የፈለጋችሁትን ጠይቁኝ እሰጣችኋለሁ።

የፈለጋችሁትንም ተመኙ እውን አደርግላችኋለሁ" ይላቸዋል። ሙእሚኖቹም፦"ያ አላህ እኛ ውዴታህን እንሻለን" ይላሉሉ። አላህም፦"እኔ ስለናንተ ወድጃለሁ" ይላቸዋል።

ይህን ግዜ ዳግም በግንባራቸው ሱጁድ ይወርዱለታል። አላህም፦"ቀና በሉ ዛሬ እኮ የምንዳ ቀን ነው እንጂ የዒባዳ ቀን አይደለም" ይላቸዋል።

ይህን ግዜ የአላህ ኑር ፊታቸው ላይ እያንፀባረቀባቸው ኑር ሁነው ቀና ይላሉ። አላህ አያይዞም፦"አሁን ወደየቤቶቻችሁ ሂዱ" ይለቸዋል።

እነሱም ከአላህ ዘንድ ወደየግዛታቸው ሊሄዱ ሲወጡ የሁሉም አገልጋይ በር ላይ መጓጓዣዎቻቸውን ይዘው ይቀበሏቸዋል።ከዚያም በ 70,000(ሰባ ሺህ) ውብ ውብ አጃቢዎቻቸው ታጅበው ወደየግዛታቸው ያቀናሉ።

ሰውየው ጀነትን ሲደርስም ከፍተኛ የሆነ አቀባበል ይደረግለት'ና ልክ ወደ ውስጥ ዘልቆ ሲገባ ሚስቱ፦"ውዴ!በውበት...፣በጌጥ...፣በመዓዛ እና በብርሀን ተሸልመህ መጣህሳ...!! ዛሬ እንኳን አልላቀቅህም" ትለዋለች።

ይህን ግዜ መላዕክት፦"አዋጅ...!!!የጀነት ነዋሪያን ሆይ እስከዘለአለም በዚህ ፀጋ ተደሳቾች ናችሁ" በማለት ይጣራሉ።

ከዚያም አንድ መላዓክ በተለያዩ የክብር ልብሶች አሸብርቆ ይመጣ'ና ጀነት መግቢያ ላይ በመቆም ለዘበኛው፦"ወደ አላህ ወዳጅ ልገባ ፈልጌ ነበር ትፈቅድልኛለህ" ብሎ ሲያስፈቅደው።

ዘበኛውም፦"ወላሂ እሱን ደርሼው ማስፈቀድ እኔ አይቻለኝም። ነገር ግን ከዚህ ቀጣይ በር ላለው ዘበኛ መልዕክትህን እንዲያደርስልህ ልነግርልህ እችላለሁ" ይልና ለቀጣዩ ዘበኛ ፍቃድ እንዲጠይቅ መልዕክት ያስተላልፋል።

ቀጣዩም ዘበኛ ለሚከተለው እያስተላለፈ መልዕክቱ በሰባ ዘበኛች አማካኝነት ሲወርድ ሲዋረድ የጀነቱ ሰውዬጋ ካለው ዘበኛ ዘንድ ይደርሳል።

ዘበኛውም ለሰውዬው፦"አንተ የአላህ ወዳጅ ሆይ! የልቅና ባለቤት የሆነው የአላህ መልዕክተኛ አንተ ዘንድ ሊገባ እያስፈቀደ ነው" ይለዋል።

ከዚያም ይፈቅድለት'ና መልዓኩም ወደ ሰውዬው ዘልቆ በመግባት ሰውዬው ፊት ይቆም'ና፦"ሰላም ባንተ ላይ ይሁን አንተ የአላህ ወዳጅ...፤የልዕልና ባለቤት የሆነው አላህ ስላንተ ወዳጅ ሲሆን ሰላምታ ልኮልሃል" ይለዋል።

የሰው ልጅ ጀነት ውስጥ ሲገባ ሞት አያገኘውም እንጂ፤ ቢያገኘው ኖሮ ያን ቀን በደስታ ፈንድቶ ይሞት ነበር።
__________________
_
{እኔምለው ቆይ የጀሀነም ሰዎችን ረሳችኋቸው አይደል!!! ጀነት አልሞላ ብላለች'ና እስቲ አንድ ያህል እንቀንሳቸው'ና እናምጣቸው ረሱልም (ሰዐወ) እዚያው የሸፋዓ ቦታ እናገኛቸዋለን ተከተሉኝ።}
__________________
__
ረሱል (ሰዐወ) ጀነት ውስጥ ተቀምጠው ሳለ ጂብሪል ይመጣ'ና፦"ሙሀመድ ሆይ!!! ወንጀለኛ ኡመቶችህ ከሚቀጡበት የጀሀነም ክፍል ነው አሁን የመጣሁት ኡመቶችህም ሰላምታ ልከውልህ አክለውም <ሁኔታችን እጅጉን ከፍቷል...፤ ቦታችን እጅግ ጠቦብናል> ብለውሃል" ይላቸዋል.....

ይቀጥላል

የቤተሰባችን አባል ለመሆን ከፈለጉ እና ይሄን ትእይንት እስከ መጨረሻው ክፍል ድረስ ለመከታተል ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን መቀላቀል ይችላሉ👇

http://www.tg-me.com/eslamic_center
🔂 ሼር 🔂 ሼር 🔂 ሼር 🔂

ማድረግ እንዳትረሱ!! እሺ ውዶች!!

ክፍል ➊➎

_
ረሱል (ሰዐወ) ጀነት ውስጥ ተቀምጠው ሳለ ጂብሪል ይመጣ'ና፦"ሙሀመድ ሆይ!!! ወንጀለኛ ኡመቶችህ ከሚቀጡበት የጀሀነም ክፍል ነው አሁን የመጣሁት ኡመቶችህም ሰላምታ ልከውልህ አክለውም <ሁኔታችን እጅጉን ከፍቷል...፤ ቦታችን እጅግ ጠቦብናል> ብለውሃል" ይላቸዋል.....

ረሱል ሰዐወ ጀነትም ገብተው ሁኔታችን አያስችላቸውም'ና ብድግ ብለው አርሽ ስር በመሄድ በግንባራቸው ተደፍተው አላህን በድንቅ ውዳሴ ያወድሱታል።

አላህም፦" ሙሀመድ ሆይ! ራስህን ቀና አድርግ...፤ ጠይቅ ይሰጥሀል...፣ አማልድ ትማለዳለህ" ይላቸዋል።

እሳቸውም፦"ያ አላህ!!! ከኡመቴ ወንጀለኞቹ ጥበብህጠ(ቅጣትህ) በነሱ ላይ ተፈፃሚ ሆኖባቸዋል።እባክህ አማልደኝ" ይሉታል።

አላህም፦"ሙሀመድ ሆይ!!! ያንተን አማላጅነት ተቀብያለሁ።ወደ ጀሀነም ሂደህ ላኢላሀ ኢለላህ ያለን ሰው ሁሉ ከውስጧ አውጣ " ይላቸዋል።

እሳቸውም ጉዞ ወደ ጀሀነም ያቀናሉ።እዚያጠሲደርሱም የጀሀነም ወታደሮች አዛዥ የሆነው ማሊክ እሳቸውን ሲያይ ለክብራቸው ብድግ ብሎ ይቀበላቸውል።

እሳቸውም፦" ማሊክ ሆይ!!! ወንጀለኛ ኡመቴቼ እንዴት ናቸው?" ይሉታል።

ማሊክም፦"ምንኛ አስከፊ ሁኔታ ላይ ናቸው! ቦታቸውስ ምንኛ ጠቧቸዋል!" በማለት ያሉበትን ሁኔታ ይነግራቸዋል።

ይህን ግዜ ረሱልም ሰዐወ፦" በሩን ክፈት'ና የጀሀነምንም ክዳን አንሳ" ይሉታል።

ማሊክም በሩን ከፍቶ ልክ የጀሀነምን ክዳን ሲያነሳ ኡመት ሁሉ የረሱልን ፊት ሲመለከት፦"ያ ረሱለላህ!!! እሳት እኮ ቆዳዎቻችንን አቃጠለን..፤ጉበቶቻችንም ተቃጠሉ" እያሉ በለቅሶ'ና ጩኸት ቦታውን ይረብሻሉ።

ከዚያም በረሱል ትዕዛዝ ከጀሀነም ላ ኢላሀ ኢለላህ ያለ ሁሉ እንዲወጣ ይደረጋል። ከጀሀነም ሲወጡ ልክ የደረቀ የእሳተ ገሞራ አለት ይመስላሉ።

ከዚያም ሁሉም ከጀነት ጎን በምትገኘዋ" ﻧﻬﺮ ﺍﻟﺤﻴﻮﺍﻥ " በምትባል ውሃ ውስጥ እንዲገቡ ይደረግ'ና፤ እዚያ ውስጥ ሲገቡ የጀሀነም ምልክት ከሰውነቶቻቸው ላይ ሙሉ በሙሉ ይወገዳል።

ከዚያም ሁሉም ጀነት እንዲገቡ ሲደረግ ካፊሮችም፦"ዋ! ጥፋታችን ምን ነበር እኛም ሙስሊሞች ሁነን በነበር" እያሉ ይፀፀታሉ።

ይህን ሁኔታቸውን አላህ በቁርአን እንዲህ ሲል ይገልፀዋል።

{ ﺭُﺑّﻤَﺎ ﻳَﻮَﺩُّ ﺍﻟَّﺬِﻳﻦَ ﻛَﻔََﺮَﻭﺍْ ﻟَﻮْ ﻛَﺎﻧُﻮﺍْ ﻣُﺴْﻠِﻤِﻴﻦَ { ‏[ ﺍﻟﺤﺠﺮ :2 ]

(እነዚያ የካዱት (የትንሳኤ ቀን) ሙስሊሞች በሆኑ ኖሮ በብዛት ይመኛሉ) በመቀጠልም ነቢያቶች ሙእሚኖች መላዕክቶች በጠየቁት
መሰረት ለሁሉም የአማላጅነት እድል ይሰጠው'ና አላህም ለመላኢካዎች፦"ወደ ጀሀነም ሂዱና የአንድ ዲናርን ያህል ኸይር ነገርን ያገኛችሁበትን ሰው ሁሉ ከሷ አውጡ"ይላቸዋል።

መላዕክትም እጅግ ብዛት ያለውን ከልቅ ከጀሀነም ያወጡ'ና አላህ ዘንድ በመሄድ፦"ጌታችን ሆይ ካዘዝከን አንዱንም ሳናስቀር አውጥተናል" ይላሉ።

አላህም ለመላዕክት፦"ወደ ጀሀነም ተመለሱ'ና የዲናር ግማሽ እንኳን ከይር ያለውን ሰው ሁሉ አውጡ" ይላቸዋል። (ሙስሊሞችን ብቻ ነው)

መላዕክትም እጅግ ብዙ ከልቅ ከውስጧ ያወጡ'ና ወደ ጀነት ያስገባሉ።ከዚያም ለአላህ፦" ጌታችን ሆይ ካዘዝከን አንዱንም ሳናስቀር አውጥተናል" ይላሉ።

አላህም፦"ወደ ጀሀነም ዳግም ተመለሱና የሰናፍጭ ያህል ከይር ያለውን ሰው ከውስጧ አውጡ" ይላቸዋል።

መላዕክትም እጅግ ብዙ ከልቅ ከውስጧ ያወጡ'ና ወደ ጀነት ያስገባሉ።ከዚያም ለአላህ፦" ጌታችን ሆይ ካዘዝከን አንዱንም ሳናስቀር አውጥተናል" ይላሉ።

ከዚያም አላህ እንዲህ ይላል፦"ነቢያቶች አማልደዋል...፣ሙእሚኖችም አማልደዋል...፣መላዕክትም አማልደዋል አሁን የቀረው የ አርሀመ ራሂሚን(የአላህ) ሸፋዓ ብቻ ነው" ይላል።

በመጨረሻም ጀሀነም ውስጥ ምንም አይነት ከይር ያልሰራን ሰው ባጠቃላይ ሙስሊም በመሆኑ ብቻ ከጀሀነም ያወጣቸዋል።

ልክ ተቀጣጥሎ የጠፋ ከሰል ይመላሉ ከጀሀነም ሲወጡ። ወዲያም ወደ ጀነት በራፍ ይወሰዱ'ና እዚያ ጋ በምትገኘው ነህሩል ሀየዋን በምትባለው ውሀ ውስጥ እየተነከሩ ልክ ሉል መስለው ይወጣሉ።

ከዚያ ውሃ ውስጥ ይወጡ'ና በግንባሮቻቸውም ላይም
" ﺍﻟﺠﻬﻨّﻤﻴﻮﻥ ﻋﺘﻘﺎﺀ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﻣﻦ ﺍﻟﻨﺎﺭ "

ተብሎ ይፃፍባቸዋል።(ጀሀነማውያን የአረህማን ነፃ ወጪዎች) በመጨረሻም ጀነት ውስጥ ሁሉም ገብተው ዘለዐለማዊ ህይወታቸውን ለዘለዐለም ማጣጣም ይጀምራሉ።

#ተፈፀመ!!

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

ምንጮች
ﻣﺴﻨﺪ ﺍﻣﺎﻡ ﺃﺣﻤﺪ
ﺻﺤﻴﺢ ﺍﻟﺒﺨﺎﺭﻱ
ﺻﺤﻴﺢ ﻣﺴﻠﻢ
ﻓﺘﺢ ﺍﻟﺒﺎﺭﻱ
ﺍﻟﻐﻨﻴﺔ ﻟﻠﺸﻴﺦ ﻋﺒﺪ ﺍﻟﻘﺎﺩﺭ ﺍﻟﺠﻴﻼﻧﻲ
የመጨረሸኛውን ኪታብ" ﺍﻟﻐﻨﻴﺔ " በብዛት ተጠቅሜዋለሁ
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

በስከዛሬው ዝግጅቶቻችን ቀጠሮ እያፈረስንም ቢሆንም አብረናችሁ የነበርነው እኛ___ነበርን።

በሚቀጥለው ፕሮግራማችን እስክንገናኝ ድረስ የአላህ ጥበቃ አይለያችሁ እያልን ልንሰናበታችሁ ወደድን!!

የቤተሰባችን አባል ለመሆን ከፈለጉ እና ይሄን ትእይንት እስከ መጨረሻው ክፍል ድረስ ለመከታተል ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን መቀላቀል ይችላሉ👇

http://www.tg-me.com/eslamic_center
📺 እሁድን በነሲሓ ቲቪ

🗂 የእለተ እሁድ ፕሮግራሞች በነሲሓ ቲቪ

📌ነሲሓ ቋንቋ

🔖ኦሮምኛ ከጠዋቱ 3፡00 ጀምሮ
🔖ስልጥኛ ከጠዋቱ 4፡15 ጀምሮ
🔖ጉራግኛ ቀን ከ5፡30 ጀምሮ
🔖ትግርኛ ቀን ከ6፡45 ጀምሮ

📌ነሲሓ ለወጣቶች

🔖ሀኢያህ ሊብኒ አቢዳዉድ
🔖የሰለፎች መንገድ
🔖ምክር ለወጣቶች
🔖የተውሒድ ውበት

📌ኢስላምና ሙስሊሞች
⌚️ከ10፡00 ጀምሮ

📌የዐርብኛ ትምህርት

🔖የዐረብኛ ሰዋሰው በቀላሉ
⌚️ከ11፡00 ጀምሮ

📌ከሐዲስ ማህደር

🔖ኡምደቱል አህካም
⌚️ከ11፡45 ጀምሮ

📌ተፍሲር

🔖ቁርኣን ተፍሲር
⌚️ከምሽቱ 12፡30 ጀምሮ

📺ነሲሓ ቲቪ ኢስላማዊ እውቀት ለሁሉም
በቁርአን ላይ አላህ "እኛ" በሚለዉ ቃሉ ላይ የክርስቲያኖች ጥያቄና መልሶቻችን 1

በኡስታዝ ዋሂድ ዑመር

“በቁርኣን አላህ እኛ ሲል ወልድ ማለትም ዒሣ እና መንፈስ ቅዱስ ወክሎ ነው” የሚል ሙግት ያቀርባሉ። ይህ ውኃ አይቋጥርም

وَآتَيْنَا عِيسَى ابْنَ مَرْيَمَ الْبَيِّنَاتِ وَأَيَّدْنَاهُ بِرُوحِ الْقُدُس

2፥87 *የመርየምን ልጅ ዒሳንም ግልጽ ታምራቶችን “ሰጠነው”፤ በቅዱሱ መንፈስም “አበረታነው”*፡፡

“ሰጠነው” በሚለው የእኛነት ግስ ላይ ዒሣ ይወጣል፥ ሰጪው አላህ የሚሰጠው ዒሣ ይሆናል። በመቀጠል “አበረታነው” በሚለው የእኛነት ግስ ላይ ቅዱስ መንፈስ ይወጣል፥ አበርቺው አላህ ማበረታቻ ቅዱሱ መንፈስ ነው። ሁለቱም ከእኛነት ከወጡ አላህ ብቻውን ይቀራል፥ ስለዚህ አላህ እኛ ሲል ብቻውን ነው ማለት ነው። በተጨማሪም አላህ አንድ አምላክ ብቻ ስለሆነ ሥስት ናቸው አትበሉ በማለት ሥስትነትን ይጻረራል፦

وَلَا تَقُولُوا ثَلَاثَةٌ ۚ انتَهُوا خَيْرًا لَّكُمْ ۚ إِنَّمَا اللَّهُ إِلَـٰهٌ وَاحِد

4፥171 *«ሦስት ናቸው» አትበሉም፡፡ ተከልከሉ፤ ለእናንተ የተሻለ ይኾናልና፡፡ አላህ አንድ አምላክ ብቻ ነው*፡፡

https://www.tg-me.com/eslamic_center
በቁርአን ላይ አላህ "እኛ" በሚለዉ ቃሉ ላይ የክርስቲያኖች ጥያቄና መልሶቻችን 2

በኡስታዝ ዋሂድ ዑመር

“በቁርኣን አላህ እኛ ሲል መላእክትን ወክሎ ነው” የሚል ሙግት ያቀርባሉ። ይህም ውኃ አያነሳም!

وَإِذْ قُلْنَا لِلْمَلَائِكَةِ اسْجُدُوا لِآدَمَ

2፥34 *ለመላእክትም «ለአደም ስገዱ» “ባልን” ጊዜ አስታውስ*

“አልን” ወይም “ባልን” በሚለው የእኛነት ግስ ላይ መላእክት ይወጣሉ፥ "አልን" ባዩ አላህ የሚለውም ለመላእክት ይሆናል። መላእክት ከእኛነት ከወጡ አላህ ብቻውን ይቀራል፥ ስለዚህ አላህ እኛ ሲል ብቻውን ነው ማለት ነው።

https://www.tg-me.com/eslamic_center
#ፍጥረተ____ኣደም___(ዐ.ሰ) #ክፍል__1

1/ ከኣደም በፊት

ኣደም (ዐ.ሰ) የመጀመሪያው ፍጡር አልነበሩም። ከኣደም በፊት አላህ (ሱ.ወ) መሬትን ፈጥሮ ዘርግቷል። ሰማይን ያለ ደጋፊ ምስሶ በችሎታው ከፍ አድርጐ አንስቷታል። እንዲሁም መላእክትና አጋንንትንም ቀድመው ተፈጥረው ነበር።
መላእክት ከብርሃን የተፈጠሩ ረቂቅ ፍጡራን ሲሆን ተግባራቸውም ያለ ምንም ማመንታት ሌት ከቀን አላህን መገዛትና ማወደስ ነው። ጅኖቹም ጥሩ የአላህ ባሪያዎች ነበሩ። ወደፊት አመፀኛና ከሓዲ መሆኑን የምናውቀው ኢብሊስም ከጂኖቹ መካከል አንዱ ነው።

2/ የኣደም መፈጠርና የኢብሊስ/ሰይጣን ማመፅ

መሬት በመልካም ነገሮች የተሞላችና ከመጥፎ ነገሮች የፀዳች ነበረች። ታዲያ ይህች መሬት የሚያለማትና በውስጧም መልካምን ነገር የሚያስፋፋ ትፈልግ ነበር።
አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ በማለት ቃሉን ለመላእክት አስተላለፈ፦
إِذْ قَالَ رَبُّكَلِلْمَلَـٰٓئِكَةِ إِنِّى خَـٰلِقٌۢ بَشَرًۭا مِّن طِينٍۢ ﴿٧١﴾ فَإِذَا سَوَّيْتُهُۥ وَنَفَخْتُ فِيهِ مِن رُّوحِى فَقَعُوا۟ لَهُۥ سَـٰجِدِينَ﴿٧٢﴾
“ጌታህ «ለመላእክት እኔ ሰውን ከጭቃ ፈጣሪ ነኝ ባለ ጊዜ» (አስታውስ)፡፡
«ፍጥረቱንም ባስተካከልኩና ከመንፈሴ በነፋሁበት ጊዜ ለእርሱ ሰጋጆች ኾናችሁ ውደቁ» (አልኩ)፡፡” (ሷድ፥ 71-72)
መላእክቱም እንዲህ አሉ፦
﴿٣٠﴾...... أَتَجْعَلُ فِيهَا مَن يُفْسِدُ فِيهَا وَيَسْفِكُ ٱلدِّمَآءَ ...... ﴿
“.......በርሷ ውስጥ የሚያጠፋንና ደሞችንም የሚያፈስን ታደርጋለህን?» አሉ፡፡.......”
መላእክቱም እንዲህ ያሉበት ምክንያት አዲሱን ፍጡር በመፍራታቸው ነበር። ይህንንም ሥጋታቸውን አላህን ጠየቁ። አላህም እንዲህ በማለት መለሰላቸው፦
قَالَ إِنِّىٓ أَعْلَمُ مَا لَا تَعْلَمُونَ ﴿٣٠﴾....﴿
“.... «እኔ የማታውቁትን ነገር አውቃለሁ» አላቸው፡፡“
መላእክቱ ለጠየቁት ጥያቄ ከአላህ በኩል መልስ ከተሰጣቸው በኋላ ምንግዜም እንደሚያደርጉት የአላህ ትእዛዝ ተቀብለው ኣደም ከጭቃ እስኪፈጠር ጠበቁ። ኣደም አካላቸው ከጭቃ ተፈጥሮ መንፈስ (ሩህ) ሲነፋባቸው ተንቀሳቀሱ። አይናቸውን ወዲያና ወዲህ በመላክ አካባቢያቸውን ቃኙ። አላህም መላእክቱ ለኣደም እጅ መንሻ ሱጁድ እንዲያደርጉ አዘዘ። መላእክቱም የአላህን ትእዛዝ አክብረው ለኣደም ሱጁድ ወረዱ። ይህ ሱጁድ ኣደምን ለማምለክ ሳይሆን ሰላምታ ለማቅረብና ክብርን ለመግለፅ ነበር። ኢብሊስ ግን በኩራት መንፈስ ተወጥሮ ለኣደም ሱጁድ አላደርግም በማለት በአላህ ትእዛዝ ላይ አመፀ።
ኢብሊስ (ሰይጣን) ከመላእክቱ ጋር ይኖር ነበር። ስለዚህም ነው ለኣደም ሱጁድ ሲታዘዝ እሱም የታዘዘው። (ተፍሲር፥ አል-ቃሲም)
ነገር ግን ከመላእክቱ መካከል አልነበረም። ይልቁንም እሱ መሠረቱ ከእሳት ነው። መላእክት ግን መሠረታቸው ከብርሃን ነው። (ተፍሲር፥ አል-ቃሲም ከኢብኑል ቀይም)
አላህ (ሡ.ወ) ሁሉንም ነገር አዋቂ ከመሆኑ ጋር ሳይጧን ለኣደም ሱጁድ አላደርግም ያለበትን ምክንያት እንዲህ ሲል ጠየቀው፦
..... قَالَ مَا مَنَعَكَ أَلَّا تَسْجُدَ إِذْ أَمَرْتُكَ
“(አላህ) ባዘዝኩህ ጊዜ ከመስገድ ምን ከለከለህ? አለው፤.... “ (አል-አዕራፍ፥ 12)

ኢብሊስም ዋጋ ቢስ የሆነ ከንቱ ምክንያት በመጥቀስ እንዲህ ሲል መልስ ሰጠ።
قَالَ أَنَا۠ خَيْرٌۭ مِّنْهُ خَلَقْتَنِى مِن نَّارٍۢ وَخَلَقْتَهُۥمِن طِينٍۢ .﴿١٢﴾.
እኔ ከርሱ የበለጥኩ ነኝ፤ ከእሳት ፈጠርከኝ፤ እሱን ግን ከጭቃ ፈጠርከው አለ።
(አል-አዕራፍ፥ 12)
እርጉም የሆነው ኢብሊስ እሳት ከጭቃ የሚበልጥ መስሎት ነበር፡ በኣደም ለመኩራራት የሞከረው፤ ነገር ግን ልብ ብለን ብንመለከት ጭቃ ባህሪው የተረጋጋና ቻይ ሆኖ እናገኛዋለን። እንዲሁም ጭቃ አዝዕርትና አታክልት የሚበቅሉበትና የሚያድጉበት ቦታ ነው። እሳት ግን ባህሪው ማቃጠል፣ መቸኮልና ማጥፋት ነው።
ኢብሊስ የአላህን ጥበብ ዘንግቶ ጭቃንና እሳትን በማወዳደር ላይ ብቻ ትኩረት በመስጠት በአላህ ትእዛዝ ላይ አመፀ። አላህ ኣደምን ከጭቃ ፈጥሮ ሩህ በመንፋት አዋቂና ተንቀሳቃሽ ፍጡር የማድረጉን ጥበብ የመረዳት አቅም አላገኘም ነበር።
3/ የስሞች ተአምር
አላህ (ሱ.ወ) አዲሱን ፍጡር ኣደም የሰጠውን ልዩ ችሎታ ለመላእክት ሊገልፅላቸው ፈለገና ኣደምን የፍጡራኑን ስሞች ሁሉ አሳወቀው። መላእክቱንም የፍጡራኑን ስሞች እንዲጠቅሱ ጠየቃቸው፣ እነሱ ግን ይህን ማድረግ አልቻሉም ነበር። ምክንያቱም ከዚያ በፊት የነገራትን ስሞች አልተማሩም ነበርና ነው። ኣደም የነገራቱን ሁሉ ስሞች ለመላእክቱ ነገራቸው። በዚህን ጊዜ መጀመሪያ ኣደም ሲፈጠሩ አላህ፦
«......እኔ የማታውቁትን ነገር አውቃለሁ» አላቸው፡፡) (አል-በቀራህ፥ 30)
ያላቸውን ቃል እርግጠኝነት ተረዱና ወዲያውኑ እንዲህ በማለት አላህን አወደሱ፦

قَالُوا۟ سُبْحَـٰنَكَ لَا عِلْمَ لَنَآ إِلَّا مَا عَلَّمْتَنَآ ۖ إِنَّكَ أَنتَٱلْعَلِيمُ ٱلْحَكِيمُ ﴿٣٢﴾
«ጥራት ይገባህ፤ ከአስተማርከን ነገር በስተቀር ለኛ ዕውቀት የለንም፡፡ አንተ ዐዋቂው ጥበበኛው አንተ ብቻ ነህና» (አሉ)፡፡
(አል-በቀራህ፥ 32)

ቴሌግራም/ telegram/
https://www.tg-me.com/eslamic_center
#ፍጥረተ___ኣደም #ክፍል2

አዎ! መላእክቱ ያለምንም ማመንታት የአላህን ትእዛዝ ፈፀሙ፡ ኢብሊስ ግን የፈጣሪ አላህን ትእዛዝ በማመጹ የአላህ እርግማን ደረሰበት። በመጨረሻም ምን እንደሆነ አብረን እንመልከት።
(አላህ ከታዛዦችና እና ቅን ባሮቹ ያድርገን)

4/ ኢብሊስ ከጀንነት ሲባረር

ኢብሊስ የአላህን ትእዛዝ አምፆ በጀነት ውስጥ መቆየት አይችልም ነበር። ስለዚህም ውርደትን ተከናንቦ ጀንነትን ለቆ እንዲወጣ ከአላህ ትእዛዝ መጣበት።
قَالَ فَٱهْبِطْ مِنْهَا فَمَا يَكُونُ لَكَ أَن تَتَكَبَّرَ فِيهَا فَٱخْرُجْ إِنَّكَ مِنَ ٱلصَّـٰغِرِينَ ﴿١٣﴾
“ከርሷ (*) ውረድ፤ በርሷ ውስጥ ልትኮራ አይገባህምና ውጣም አንተ ከወራዶቹ ነህና አለው፤”
(አል-በቀራህ፥ 13)
ኢብሊስን ጌታው ከጀንነት ውጣ አንተ ወራዳና ትንሽ ነህ አለው። ይህም የሆነበት ምክንያት ለኣደም ሱጁድ አላደርግም በማለቱና በኩራት መንፈስ የአላህን ትእዛዝ በማመፅ አላህ (ሱ.ወ) ውርደት ሊያከናንበው ስለፈለገ ነው። ለአላህ የተናነሰን አላህ ከፍ ያደርገዋል፤ በአላህ ላይ የኮራን ደግሞ አላህ ዝቅ ያደርገዋል፤ ያሳንሰዋል። ይህ የተረገመና ከጀንነት የተባረረው ኢብሊስ እጣ ፈንታ ሆነ። የሚገርመው ደግሞ እርጉሙ ኢብሊስ በሠራው ወንጀል ሳያፍር ጌታውን አንድ ነገር ጠየቀ። ይህ ነገር ምን ይሆን?

5/ አቆየኝ

ኢብሊስ ከጀነት እንዲባረር የአላህ ትእዛዝ እንደተላለፈበት ሲያውቅ ወዲያውኑ እስከ ዕለተ-ትንሳኤ ድረስ በሕይወት እንዲያቆየው አላህን (ሱ.ወ) ጠየቀ። አላህም በፍቃዱና በጥበቡ እስከ ቂያማ ድረስ እንዲኖር ፈቀደለት። ይህ የአላህ ፈቃድ ነበር። አማኝ የአላህን ፍላጐት አይቃረንም። ለኢብሊስ ጥያቄ አላህ እንዲህ በማለት መልስ ሰጠው፦
“አንተ ከሚቆዩት ነህ።” (አል-አዕራፍ፥ 15)
እርጉሙ ኢብሊስ አላህ እስከ ዕለተ-ትንሳኤ እንደሚያቆየው ሲያውቅ ለኣደምና ለዝርያዎቹ ያለውን ጥላቻና በውስጡ የያዘውን ደባ ለመግለፅ ጊዜ አልፈጀበትም ነበር። እነሱን ከትክክለኛው መንገድ ለማውጣት የያዘውን እቅድ ወዲያውኑ እንዲህ ሲል ገለፀ።
“ስለአጠመምከኝም ለነርሱ በቀጥተኛው መንገድ ላይ በእርግጥ እቀመጥባቸዋለሁ አለ።” (አል-አዕራፍ፥ 16)

6/ ኢብሊስ በኣደምና ልጆቹ ላይ ሲዝት

እርጉሙ ኢብሊስ ኣደምና ልጆቹ ኃጢአትን እንዲወዱና እንዲደፋፈሩ በማድረግ አጠፋቸዋለሁ ሲል ከመጀመሪያው ዛተ፣ ሶላትን ትተው ጠማማውን መንገድ እንዲይዙ አደርጋቸዋለሁም አለ። በዚህም ዛቻው ኢብሊስ ምንጊዜም ቢሆን ተንኮል እንጂ ኸይር እንደማይሠራ ማንነቱን አጋላጠ። ነገር ግን እርግሙ ኢብሊስ ምንም ያህል ኣደምንና ልጆቹን ለማሳሳት ጥረት ቢያደርግም ደካሞችን እንጂ ጠንካራ የአላህ ባሪያዎችን ማጥመም አይቻለውም። ምክንያቱም እነሱ በኢማንና በዒባዳ የታነፁ ናቸው። ሶላታቸውን ቀጥ አድርገው ይሰግዳሉ። ቃል ኪዳናቸውንም ይጠብቃሉ፣ ዘካንም ይሰጣሉ (ያወጣሉ)። እንዲህ ያሉትን የአላህ ባሪያዎች ሰይጣን ምንም ያህል ዘዴዎችን ቢጠቀም ሊያጠማቸው አይችልም። እነሱ ጧትና ማታ ቁርአንን ስለሚያነቡና ከወንጀልም የራቁ ስለሆኑ ከሱና ከማጥሚያ ዘዴዎቹ በላይ ናቸው። ንጹህ የአላህ ባሪያዎች ስለሆኑ አላህ መኖሪያቸውን ጀንነት ያደርገዋል።
ኢብሊስን ተከትሎ ኃጢአት የሚሠራና ሶላትንና ኸይር ሥራዎችን የሚተው ሰው ግን በመጨረሻ ከኢብሊስ ጋር ወደ ገሃነም ይወርዳል። እሷም አስከፊ መኖሪያ ነች። አላህ ይጠብቀን ።

7. ኣደም (ዐ.ሰ) ወደ ጀነት

እርጉሙ ኢብሊስ ለኣደም ሱጁድ አላደርግም በማለት የአላህን ትእዛዝ በማመፁ አላህ (ሱ.ወ) ከጀንነት አባረረው። ኣደምን ደግሞ አላህ ክብር ሰጠውና ከጐኑ ባለቤቱን ሐዋን ፈጠረለት። ከዚያም ጀንነት አኖራቸው። ኣደምና ሐዋ ጀንነት ውስጥ ሲኖሩ የፈለጉትን ነገር እንዲመገቡ አላህ ፈቅዶላቸው የነበረ ሲሆን አንዲት ዛፍን ብቻ እንዳይበሉና ወደርሷም እንዳይቀርቡ አስጠንቅቋቸው ነበር። ኣደምና ሐዋ ቀጥሎ የተጠቀሰውን የአላህ ትእዛዝ አክብረው በጀነት ውስጥ ደስ የሚል ኑሮ መኖር ጀመሩ።
وَيَـٰٓـَٔادَمُ ٱسْكُنْ أَنتَ وَزَوْجُكَ ٱلْجَنَّةَ فَكُلَا مِنْ حَيْثُ شِئْتُمَا وَلَا تَقْرَبَا هَـٰذِهِ ٱلشَّجَرَةَفَتَكُونَا مِنَ ٱلظَّـٰلِمِينَ ﴿١٩﴾

“አዳምም ሆይ! አንተም ሚስትህም ከገነት ተቀመጡ፤ ከሻችሁትም ስፍራ ብሉ፤ ግን ይህችን ዛፍ አትቅረቡ፤ (ራሳቸውን) ከሚበድሉት ትሆናላችሁና (አላቸው)።”
(አል-አ’ዕራፍ፥ 19)

8/ የኢብሊስ ጉትጐታ

ኣደምና ሐ ዋን አላህ እንደወደዳቸውና እንዳከበራቸው በጀነትም እንደሚያኖራቸው ሲመለከት ኢብሊስ በቅናት ተቃጠለ፣ በዚህን ጊዜ ኣደምና ሐዋ ያሉበትን ፀጋ ለመግፈፍ ሴራውን ይሸርብ ጀመር። ለነሱ ተቆርቋር መስሎ በመቅረብ፤ አላህ ይህችን ዛፍ እንዳትበሉ ያዘዛችሁ ጉዳት ስላለው ሳይሆን እሷን ከበላችሁ ወደ መእክትነት ስለምትለወጡ ወይም በዚህ ጀነት ውስጥ ዘለዓለም ኗሪ ስለምትሆኑ ነው አላቸው። ይህን ቃሉን እውነት ለማስመሰልም በአላህ ስም ማለላቸው። ሙእሚን በአላህ ስም ሲማልለት እውነት ስለሚመስለው ኣደምና ሐዋም ኢብሊስን አመኑት ተታለሉም።

9/ ኣደምና ባለቤታቸው ሐዋ ከዛፍ ቀመሱ

ኢብሊስ ኣደምና ሐዋን በተደጋጋሚ ለነሱ ጥሩ እንደሆነ አስመስሎ ዛፉን እንዲቀምሱ ስለጐተጐታቸውና በአላህ ስም ስለማለላቸው ቃሉን አመኑና ከተከለከሉት ዛፍ በሉ። ወንጀል ላይም ወደቁ። በዚህን ግዜ ልብሳቸው ከላያቸው ላይ እየበረረ ሄዶ ርቃናቸውን ቀሩ። ኣደምና ሐዋ ሐፍረት ገላቸውን ለመሸፈን ከጀነት ቅጠል እየቆረጡ ሰውነታቸውን ማልበስ ሞከሩ። አሁን ኣደምና ሐዋ ትልቅ ስህተት ውስጥ እንደወደቁና ኢብሊስም ጥሩ መካሪ ሳይሆን ለነሱ መጥፎ አሳቢ መሆኑን አወቁ። መሃላውም የውሸት መሆኑን ተረዱ።

10/ ወቀሳና ተውበት

ኣደምና ሐዋ በሠሩት ወንጀል በጣም ተፀፅተውና አፍረው ወደ መሬት አቀረቀሩ፣ የአላህን ማስጠንቀቅያ ረስተው የኢብሊስን ምክር በመስማታቸው እጅጉን ነደሙ /ተፀፀቱ/።
ከዚያም ኣደምና ባለቤታቸው ሐዋ ጥፋታቸውን አምነው እንዲህ በማለት ከአላህ ምሕረትን ጠየቁ።

قَالَا رَبَّنَا ظَلَمْنَآ أَنفُسَنَا وَإِن لَّمْتَغْفِرْ لَنَا وَتَرْحَمْنَا لَنَكُونَنَّ مِنَ ٱلْخَـٰسِرِينَ ﴿٢٣﴾
“ጌታችን ሆይ! ነፍሶቻችንን በደልን፤ ለኛ ባትምር ባታዝንልም በእርግጥ ከከሳሪዎቹ እንሆናለን አሉ። “

(አዕራፍ፥ 23)
የአላህ እዝነት ኣደምና ሐዋን ደረሳቸው። ይቅርታም አደረገላቸው። እሱ አዛኝና ይቅር ባይ አምላክ ነውና። መጀመሪያም ኢብሊስ እንዳያሳስታቸው እንዲህ ስል አስጠንቅቋቸው ነበር።

فَقُلْنَا يَـٰٓـَٔادَمُ إِنَّهَـٰذَا عَدُوٌّ لَّكَ وَلِزَوْجِكَ فَلَا يُخْرِجَنَّكُمَا مِنَ ٱلْجَنَّةِ فَتَشْقَىٰٓ ﴿١١٧﴾
“አልንም፦ አደም ሆይ! ይህ ላንተም ለሚስትህም በእርግጥ ጠላት ነው፤ ስለዚህ ከገነት አያውጣችሁ፤ ትለፋለህና፤ “
(ጦሃ፥ 117)
ቴሌግራም/ telegram/
https://www.tg-me.com/eslamic_center
#ፍጥረተ__ኣደም__(ዐ.ሰ) #ክፍል__3

11/ ከጀነት መውጣት

አላህ (ሱ.ወ) ኣደምና ሐዋ ትእዛዙን ተላልፈው የተከለከሉትን ዛፍ በመብላት ለሠሩት ጥፋት ይቅርታ ስለጠየቁና ተውበት ስላደረጉ ምሕረት ሰጣቸው፣ ሆኖም ግን ይህ የተደረገላቸው ምሕረት ከጀነት መውጣታቸውን አላስቀረላቸውም ነበር። ከሰይጣን ጋር ወደ መሬት ወርደው አንደኛቸው የሌላቸው ጠላት ሆነው እንዲኖሩ አላህ አዘዘ። ኣደም፣ ሐዋ እንዲሁም ጠላታቸውን ኢብሊስ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል፦
قَالَ ٱهْبِطُوا۟ بَعْضُكُمْ لِبَعْضٍ عَدُوٌّۭ ۖ وَلَكُمْ فِىٱلْأَرْضِ مُسْتَقَرٌّۭ وَمَتَـٰعٌ إِلَىٰ حِينٍۢ ﴿٢٤﴾
“(አላህ)፦ ከፊላችሁ ለከፍሉ ጠላት ሲሆን ውረዱ፤ ለእናንተም በምድር ላይ እስከ ተወሰነ ጊዜ ድረስ መርጊያና መጠቀሚያ አላችሁ አላቸው።” (አል-አዕራፍ፥ 24)
ኣደምና ሐዋ ወደ ፊት ለነሱና ለዝርዮቻቸው መኖሪያና መጣቀሚያ ወደ እምትሆነው መሬት ወረዱ። ይህችን መሬት እያረሱ ያመርታሉ፣ አየሩ፣ ባህሩና የብስ ሁሉ ለነሱ መጠቀሚያ ይሆናል። ቂያማ እስከምትቆም ድረስ በመሬት ውስጥ ባሉ ሃብቶች እየተጠቀሙ ይቆያሉ።
ኣደምና ሐዋ በመሬት ላይ ሲኖሩ በነሱና በኢብሊስ እንዲሁም በልጆቻቸውና በኢብሊስ ልጆች መካከል የማያቋርጥ ጦርነት እንደሚኖር አላህ (ሱ.ወ) አሳወቃቸው። ይህ ጦርነት ኢብሊስ አባታችን ኣደምንና እናታችን ሐዋን አታሎ ወንጀል እንዲሠሩ በማድረግ ከጀነት ባስወጣቸው ጊዜ ነበር የተጀመረው። አላህ (ሱ.ወ) ኣደምና ሐዋን እንዲሁም ዝርያዎቻቸውን የኢብሊስ ሰለባ አድርጐ እንደማይተዋቸውና በእዝነት ወደ ትክክለኛው መንገድ እንደሚመራቸው ነገራቸው። ኢብሊስንም ደጋግ የኣደም ዘሮች ለሱ እንደማይሸነፉና በኢማናቸው በሶላታቸው በእርግጠኝነት እሱን እንደሚረቱት አስጠነቀቀው። በተውበቱ ፀንቶ ደግሞ ወደ ወንጀል ሳይመለስ የሚቆይ ሰው ምን ጊዜም በአላህ እዝነት ሥር እንደሚኖር ለኣደምና ሐዋ አላህ ነገራቸው።

12 ከኣደም ታሪክ የምንረዳቸው ቁምነገሮች


ለሰይጣን ጉትጐታ የማይበገር ምሉዕ የአላህ ታዛዥነት የኢስላም አስኳልና መሠረት ነው። ኣደም አላህ (ሱ.ወ) ከጭቃ የፈጠራቸው የሰው ልጅ መጀመሪያ ናቸው። ዛሬ ምድርን ሞልተው የሚገኙ የሰው ልጆች ሁሉ መሠረታቸው ኣደም ናቸው። የሰው ልጅ ስህተት ላይ ሊወድቅ ይችላል፣ ስለዚህ ምንጊዜም ወደ አላህ መመለስ አለበት። ሌላው ከታሪኩ የምንረዳው ቁምነገር አንድ ሙስሊም ጌታውን ከታዘዘና በሱም ከተመካ ከስህተት እሱው ይጠብቀዋል። ሸይጧንንም ይከላከልለታል። ስለዚህ ተውበት ማድረግና ከአላህ ምሕረትን መጠየቅ የማንኛውም ሙስሊም እለታዊ ተግባር ሊሆን ይገባል። ማንኛውም ሰው ከምቀኝነትና ኩራት መጠንቀቅ ይገባዋል። እነዚህ ባህሪያት ኣደምና ሐዋ በማሳሳት ከጀነት እንዲወጡ ያደረጋቸው የሰይጧን ባህሪያት ናቸው።
የኣደም ታሪክ በብዙ የቁርአን ምዕራፎች ውስጥ ተዘግቧል። በአል-በቀራህ ምዕራፍ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል፦

وَإِذْ قَالَ رَبُّكَ لِلْمَلَـٰٓئِكَةِ إِنِّى جَاعِلٌۭ فِىٱلْأَرْضِ خَلِيفَةًۭ ۖ قَالُوٓا۟ أَتَجْعَلُ فِيهَا مَن يُفْسِدُ فِيهَا وَيَسْفِكُ ٱلدِّمَآءَ وَنَحْنُ نُسَبِّحُ بِحَمْدِكَ وَنُقَدِّسُلَكَ ۖ قَالَ إِنِّىٓ أَعْلَمُ مَا لَا تَعْلَمُونَ ﴿٣٠﴾ وَعَلَّمَ ءَادَمَ ٱلْأَسْمَآءَ كُلَّهَا ثُمَّ عَرَضَهُمْ عَلَى ٱلْمَلَـٰٓئِكَةِ فَقَالَأَنۢبِـُٔونِى بِأَسْمَآءِ هَـٰٓؤُلَآءِ إِن كُنتُمْ صَـٰدِقِينَ ﴿٣١﴾ قَالُوا۟ سُبْحَـٰنَكَ لَا عِلْمَ لَنَآ إِلَّا مَا عَلَّمْتَنَآ ۖ إِنَّكَ أَنتَٱلْعَلِيمُ ٱلْحَكِيمُ ﴿٣٢﴾ قَالَ يَـٰٓـَٔادَمُ أَنۢبِئْهُم بِأَسْمَآئِهِمْ ۖ فَلَمَّآ أَنۢبَأَهُم بِأَسْمَآئِهِمْ قَالَ أَلَمْ أَقُل لَّكُمْ إِنِّىٓأَعْلَمُ غَيْبَ ٱلسَّمَـٰوَ ٰتِ وَٱلْأَرْضِ وَأَعْلَمُ مَا تُبْدُونَ وَمَا كُنتُمْ تَكْتُمُونَ ﴿٣٣﴾ وَإِذْ قُلْنَا لِلْمَلَـٰٓئِكَةِٱسْجُدُوا۟ لِءَادَمَ فَسَجَدُوٓا۟ إِلَّآ إِبْلِيسَ أَبَىٰ وَٱسْتَكْبَرَ وَكَانَ مِنَ ٱلْكَـٰفِرِينَ ﴿٣٤﴾ وَقُلْنَا يَـٰٓـَٔادَمُ ٱسْكُنْأَنتَ وَزَوْجُكَ ٱلْجَنَّةَ وَكُلَا مِنْهَا رَغَدًا حَيْثُ شِئْتُمَا وَلَا تَقْرَبَا هَـٰذِهِ ٱلشَّجَرَةَ فَتَكُونَا مِنَ ٱلظَّـٰلِمِينَ﴿٣٥﴾ فَأَزَلَّهُمَا ٱلشَّيْطَـٰنُ عَنْهَا فَأَخْرَجَهُمَا مِمَّا كَانَا فِيهِ ۖ وَقُلْنَا ٱهْبِطُوا۟ بَعْضُكُمْ لِبَعْضٍ عَدُوٌّۭ ۖوَلَكُمْ فِى ٱلْأَرْضِ مُسْتَقَرٌّۭ وَمَتَـٰعٌ إِلَىٰ حِينٍۢ ﴿٣٦﴾ فَتَلَقَّىٰٓ ءَادَمُ مِن رَّبِّهِۦ كَلِمَـٰتٍۢ فَتَابَ عَلَيْهِ ۚ إِنَّهُۥهُوَ ٱلتَّوَّابُ ٱلرَّحِيمُ ﴿٣٧﴾ قُلْنَا ٱهْبِطُوا۟ مِنْهَا جَمِيعًۭا ۖ فَإِمَّا يَأْتِيَنَّكُم مِّنِّى هُدًۭى فَمَن تَبِعَ هُدَاىَ فَلَاخَوْفٌ عَلَيْهِمْ وَلَا هُمْ يَحْزَنُونَ ﴿٣٨﴾
“(ሙሐመድ ሆይ) ጌታህ ለመላእክት፡- «እኔ በምድር ላይ ምትክን አድራጊ ነኝ፤» ባለ ጊዜ (የኾነውን አስታውስ፤ እነርሱም) «እኛ ከማመስገን ጋር የምናጠራህ ላንተም የምንቀድስ ስንኾን በርሷ ውስጥ የሚያጠፋንና ደሞችንም የሚያፈስን ታደርጋለህን?» አሉ፡፡ (አላህ) «እኔ የማታውቁትን ነገር አውቃለሁ» አላቸው፡፡
አደምንም ስሞችን ሁሏንም አስተማረው፡፡ ከዚያም በመላእክት ላይ (ተጠሪዎቹን) አቀረባቸው፡፡ «እውነተኞችም እንደኾናችሁ የነዚህን (ተጠሪዎች) ስሞች ንገሩኝ» አላቸው፡፡
«ጥራት ይገባህ፤ ከአስተማርከን ነገር በስተቀር ለኛ ዕውቀት የለንም፡፡ አንተ ዐዋቂው ጥበበኛው አንተ ብቻ ነህና» (አሉ)፡፡
፡-«አደም ሆይ ስሞቻቸውን ንገራቸው» አለው፡፡ ስሞቻቸውን በነገራቸውም ጊዜ «እኔ የሰማያትንና የምድርን ሩቅ ምስጢር ዐውቃለሁ፤ የምትገልጹትንና ያንንም ትደብቁት የነበራችሁትን ዐውቃለሁ አላልኳችሁምን?» አላቸው፡፡
ለመላእክትም «ለአደም ስገዱ» ባልን ጊዜ (አስታውስ) ፡፡ ሁሉም ወዲያውኑ ሰገዱ፤ ኢብሊስ (ዲያብሎስ) ብቻ ሲቀር እምቢ አለ፤ ኮራም ከከሓዲዎቹም ኾነ፡፡ «አደም ሆይ! አንተ ከነሚስትህ በገነት ተቀመጥ፤ ከርሷም በፈለጋችሁት ስፍራ በሰፊው ተመገቡ፤ ግን ይህችን ዛፍ አትቅረቡ፤ ከበደለኞች ትኾናላችሁና» አልንም፡፡
ከርሷም ሰይጣን አዳለጣቸው በውስጡም ከነበሩበት (ድሎት) አወጣቸው፡፡ «ከፊላችሁም ለከፊሉ ጠላት ሲኾን ውረዱ፤ ለናንተም በምድር ላይ እስከ ጊዜ (ሞታችሁ) ድረስ መርጊያና መጣቀሚያ አላችሁ» አልናቸው፡፡
አደምም ከጌታው ቃላትን ተቀበለ፡፡ በርሱ ላይም (ጌታው ጸጸትን በመቀበል) ተመለሰለት፤ እነሆ እርሱ ጸጸትን ተቀባይ አዛኝ ነውና፡፡

https://www.tg-me.com/eslamic_center
«ሁላችሁም ኾናችሁ ከርሷ ውረዱ፡፡ ከኔም የኾነ መመሪያ ቢመጣላችሁ ወዲያውኑ መመሪያዬን የተከተለ ሰው በነሱ ላይ ፍርሃት የለባቸውም፤ እነሱም አያዝኑም» አልናቸው፡፡
(አል-በቀራህ፥ 30-38)

ነፍሰ ገዳዩ ቃቤል

وَٱتْلُ عَلَيْهِمْ نَبَأَ ٱبْنَىْ ءَادَمَ بِٱلْحَقِّ إِذْ قَرَّبَا قُرْبَانًۭا فَتُقُبِّلَ مِنْ أَحَدِهِمَا وَلَمْ يُتَقَبَّلْ مِنَ ٱلْءَاخَرِقَالَ لَأَقْتُلَنَّكَ ۖ قَالَ إِنَّمَا يَتَقَبَّلُ ٱللَّهُ مِنَ ٱلْمُتَّقِينَ ﴿٢٧﴾
በነሱም ላይ የአደምን ሁለት ልጆች ወሬ፣ ቁርባንን ባቀረቡና (አላህ) ከአንደኛቸው ተቀብሎ ከሌላው ባልተቀበለ ጊዜ (የሆነውን) በውነት አንብብላቸው፤ በእርግጥ እገድልሀለሁ አለው፤ (ተገዳዩ) አላህ የሚቀበለው እኮ ከጥንቁቆቹ ብቻ ነው አለ።
(አል-ማኢዳህ፥ 27)
ወደ ሐበሻ ስደት-ሂጅራ

► ሁለተኛው እርምጃ ነጃሺ ማንም ሰው በርሱ ዘንድ የማይበደል ፍትሃዊ ንጉሥ መሆኑን ካረጋገጡ በኋላ ሙስሊሞች ወደ ሐበሻ እንዲሰደዱ አመላከቱዋቸው። ከነቢይነት (ኑብዋ) አምስተኛ ዓመት ላይ በረጀብ ወር የመጀመሪያው ቡድን ወደ ሐበሻ ተሰደደ። አስራ ሁለት ወንዶችና አራት ሴቶች ነበሩ። ኃላፊያቸው ዑስማን ቢን ዐፋን አልኡመዊ (ረ.ዐ) ሲሆኑ ከሳቸው ጋር ባለቤታቸው ሩቂያ ቢንት ረሱሊላህ (ሰ.ዐ.ወ) ነበሩ። ከነቢዩላህ ኢብራሂምና ከነቢዩላህ ሉጥ (ዐ.ሰ) ቀጥሎ በአላህ መንገድ ከቤተሰብ ጋር ለመሰደድ ዑስማን የመጀመሪያው ሰው ናቸው።
እነዚህ ሶሓቦች በሌሊት ጨለማ በምስጢር ወጥተው ከጂዳ በስተደቡብ ወደሚገኘው ሸዒባ ወደሚትባለው ወደብ አመሩ። የአላህ «ቀደር» ሆነና ሁለት የንግድ ጀልባዎችን አግኝተው በመሳፈር ሐበሻ ገቡ። ቁረይሾች ግን መውጣታቸውን ሲሰሙ በጣም ተቆጡ። ይዘዋቸው ወደ መካ በመመለስና መቅጣቱንና ማሳቃየቱን በመቀጠል ከአላህ ሃይማኖት ሊመልሱዋቸው ፈልገው ፤ የወጡትን ሶሓቦች ፈለጐቻቸውን በመከተል በፍጥነት ወደ ባህር አመሩ። ሙስሊሞቹ ግን ተሳፍረው አመለጡ። ቁረይሾች የባህር ጠረፍ ከደረሱ በኋላ አፍረው ተመለሱ።

በሱረቱ አል-ነጅም ላይ ሙሽሪኮች ከሙስሊሞች ጋር መስማማታቸውና ሱጁድ ማድረጋቸው
🔖ዑመር ኢብኑል ኸጣብ እና አቡ ሁረይረህ رضي الله عنهما የረመዷን ቀዳቸውን በዙል-ሒጃ 10 ቀናት ነበር የሚያወጡት።
ይህም የሆነው በዙል-ሒጃ 10 ቀናት ውስጥ የሚፆም ፆም ከሌላ ጊዜ የተሻለ አጅር (ምንዳ) የሚያስገኝ በመሆኑ ነው።ስለዚህ ቀዳእ ያለበት ሰው ከነገ ረቡዕ ጀምሮ እስከ 8ኛው ቀን ድረስ ሊፆም፣ ቀዳእ የሌለበት ሰውም በሱንና መልኩ ቀናቱን አከታትሎም ይሁን እያረፉ መጾም ተመራጭ ይሆንለታል።
ከጾም በተጨማሪም፣ ዚክር፣ቁርኣን፣ሰደቃና ልቅ ተክቢራ ማብዛት ይወደዳል።
الله أكبر الله أكبر الله أكبر لا إله إلا الله الله أكبر الله أكبر ولله الحمد.

@ዛዱል-መዓድ
2024/06/30 19:27:10
Back to Top
HTML Embed Code: