Telegram Web Link
ቃል የተገባው ትልቅ የዒድ መስገጃ ቦታ የዛሬ ሳምንት ረቡዕ ርክክቡ ይፈጸማል

ለህዝበ ሙስሊሙ ኢስላማዊ ማዕከል በመሆን አገልግሎት እዲሰጥ ታስቦ የዛሬ ዓመት በጠቅላይ ሚኒስትሩ ቃል የተገባው ትልቅ የመስገጃ ቦታ የዛሬ ሳምንት ረቡዕ እንደሚፈጸም የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት አስታውቋል፡፡

የአዲስ አበበ ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ከአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ከክቡር ሐጂ ሱልጣን አማን ጋር በዛሬው ዕለት በስልክ ባዳረጉት ውይይት መሰረት ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት የክብር ዶክተር ሙፍቲ ሀጂ ዑመር ኢድርስ ጋር በመነጋገር ቀኑ መወሰኑን ነው ምክር ቤቱ የገለጸው::
አላህ ለይለተል ቀድርን ይወፍቀን።


የመጣብንን በላእም ያንሳልን።
አሰላሙ ዐለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱሁ ያ ጀምዓ ዛሬ ረመዳን 21ኛ ሌሊት ነው ። ይህ ሌሊት ምናልባት ለይለተል ቀድር ሊሆን ስለሚችል በዱዓእ ፣ በዒባዳ እና ያቅማችን ያህል ሰደቃን ለመስጠት በመነየት እናሳልፍ ። አላህ ኸይር ሥራ ላይ ያግዘን፤ ተቀባይነት ያለውን ዱዓና ዒባዳ ይወፍቀን ፣ ኻቲማችንን ያማረ ያድርግልን። ከወረርሽኙም ይጠብቀን ። በወረሽኙ የሞቱብንን ሻሂድነትን ይወፍቃቸው ፣ ጀነተል ፍርዶስም ይወፍቃቸው ፣ ወረርሽኙም ያንሳልን አሚን ፣ ቀሪ ሕይወታችን ላይ በረካ ያድርግልን ወንጀላችን አፉ ይበለን ፣ ክፉ ነገራችንን ያስወግድልን ፣ ኸይሩን ሁሉ ይወፍቀን አሚን ያላህ
ለይለቱል ቀድር

#ጥያቄ፡ ያለሁበት ለሊት ለይለቱል ቀድር መሆኑን እንዴት ማወቅ እችላለሁ? ይህን የተከበረ ለሊት እንዴትስ ላሳልፍ? ሶላት በመስገድ ወይስ ቁርአን በመቅራት?
——————––––————————–
#መልስ፡ ቢስሚላሂ ረህማኒ ረሒም

ለይለቱል ቀድርን (የውሳኔዋን ለሊት) ህያው ማድረግ እንደሚወደድ የሚጠቁሙ ብዙ ሐዲሶች ተዘግበዋል። የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ይላሉ፡-

”من قام رمضان إيمانًا واحتسابًا غفر له ما تقدم من ذنبه “ ”ومن قام ليلة القدر إيمانًا واحتسابًا غفر له ما تقدم من ذنبه“

“(የአላህን ቃልኪዳን) እያመነና (ምንዳውን) እየተሳሰበ በረመዳን ለሊት የቆመ (የሰገደበት) ሰው ያሳለፈውን ወንጀል በሙሉ ይማራል።” “(የአላህን ቃልኪዳን) እያመነና (ምንዳውን) እየተሳሰበ ለይለቱል ቀድርን የቆመ (የሰገደበት) ሰው ያሳለፈውን ወንጀል በሙሉ ይማራል።” (ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)

ለይለቱል ቀድር የተባረከ ለሊት ነው። አላህ ወህይ (ራእይ) ለማውረድ መርጦታል። አላህ እንዲህ ይላል፡-

حم * وَالْكِتَابِ الْمُبِينِ * إِنَّا أَنزَلْنَاهُ فِي لَيْلَةٍ مُّبَارَكَةٍ إِنَّا كُنَّا مُنذِرِينَ

“ሐ.መ (ሓ ሚም)፡፡ አብራሪ በኾነው መጽሐፍ እንምላለን፡፡ እኛ (ቁርኣኑን) በተባረከች ሌሊት ውስጥ አወረድነው፡፡ እኛ አስፈራሪዎች ነበርንና፡፡” (አድ-ዱኻን 44፣ 1-3)

አላህ በዚህ አንቀፅ ውስጥ በመፅሀፉ (በቁርአን) ይምላል። በተባረከ ለሊት እንዳወረደውም ይናገራል። ይች ለሊትም ለይለቱል ቀድር ናት።

ለይለቱል ቀድር የተለያዩ ምልክቶች አሏት። በርሷ ውስጥ ሙስሊሞች የሚጠመዱባቸው የተለያዩ ሥራዎችም አሉ። በዚያ ቀን የሚሠሩ አምልኮዎችም ሌላ ጊዜ ከሚሠሩት ይበልጥ የላቀ ክብርና ደረጃ ያስገኛሉ።

ከለይለቱል ቀድር ምልክቶች መሀል የተወሰኑትን እንጥቀስ። ኢማም ኢብኑ ተይሚያህ ፈታዋ አል-ኩብራ ላይ እንዲህ ይላሉ፡-

“ለይለቱል ቀድር ከረመዳን የመጨረሻው አስር ቀናት ላይ የሚከሠት አንድ ለሊት እንደሆነ ከነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ተነግሯል። ‘ከረመዷን ወር የመጨረሻዎቹ አስር ቀናት ውስጥ ነው ያለችው።’ ብለዋል፤ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ)። በአስሩ የረመዷን ወር የመጨረሻ ቀናት በነጠላ የሚቆጠሩት ቀናት ላይ እንደሆነችም የሚጠቁሙ ሐዲሶችም እንዲሁ ተዘግበዋል። ነጠላነት ግን ካለፉት የረመዳን ቀናት ወይም ከሚቀሩት የረመዳን ቀናት አንፃር ሊታይ ይችላል። ስለዚህ ካለፈው አንፃር ካየነው ሀያ አንደኛው፣ ሀያ ሦስተኛው፣ ሀያ አምስተኛው፣ ሀያ ሠባተኛው እና ሀያ ዘጠነኛው ቀን ይበልጥ ለይለቱል ቀድር ሊሆኑ እንሚችሉ ይጠረጠራሉ። እነዚህ ብዙዎች የሚጠብቁበት አቆጣጠር ነው። ይሁንና የቀሩትን የረመዷን ቀናት በማሰብ ልንቆጥርም እንችላለን። ምክንያቱም ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ይላሉ፡-

لتاسعة تبقى لسابعة تبقى لخامسة تبقى لثالثة تبقى

“እርሷ በሚቀሩት ሰባት፣ አምስት፣ ሦስት… ቀናት ውስጥ ትሆናለች።”

በዚህ መሠረት ወሩ ሠላሳ ቀን ከሆነ ከታች ወደ ላይ ሲቆጠር ጥንድ ቀናት የሚሆኑት ለሊቶች ከላይ ወደ ታች ሲቆጠር ለይለቱል ቀድር ሊሆኑ ይችላሉ። ማለትም ሀያ ሁለተኛው ለሊት ዘጠኝ ቀናት የሚቀሩት ለሊት ሊሆን ቻለ። ስለዚህ ሀያ አራተኛው ቀን ደግሞ ሰባት ቀናት የሚቀሩት ለሊት ሆነ… እያልን ልንሄድ ነው። ታላቁ ሶሐባ አቡ ሰዒድ አልኹድሪይ (ረ.ዐ)- በሶሒሕ እንደተዘገበው- ያለፈውን ሐዲስ በዚህ መልኩ ተረድተውታል።

በዚሁ መሠረት ወሩ በሀያ ዘጠኝ ካበቃ ደግሞ ሒሳቡ ከዚህ በፊት ከተጠቆሙት ቀናት ጋር ተመሳሳይ ቀናት ላይ ለይለቱል ቀድርን ልንጠብቅ ነው ማለት ነው። ስለዚህ ሙስሊም ሁሉ የመጨረሻዎቹ አስር ቀናት ውስጥ ለይለቱል ቀድርን በሙሉ ንቃት መጠበቅ ይገባል። የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) “አስሩ የመጨረሻ ቀናት ላይ በንቃት ጠብቋት!” ብለዋል። በተለይም የመጨረሻዎቹ ሰባት ቀናት ላይ መጠበቁ በጣም ይጠነክራል። በተለየ ሁኔታ ደግሞ ሀያ ሰባተኛው ለሊት እንደሆነች ኡበይ ኢብኑ ከዕብ (ረ.ዐ) ይነግሩናል። ‘እንዴት አወቁ?’ ተብለው ቢጠየቁ ‘ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) በነገሩን ምልክት ነዋ። የእርሷ (የለይለቱል ቀድር) ንጋት ላይ ፀሀይ ልብስ እንደሚታጠብበት ሳፋ (ጠሽት) ንፁህና ደካማ ሆና ትወጣለች። ሲሉ መልእክተኛው ነግረውናል።’

ኡበይ ኢብኑ ከዕብ ከነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ይዘው የነገሩን ይህ ምልክት የታወቀ የለይለቱል ቀድር ምልክት ነው። ለሊቷ መሀለኛ የአየር ሁኔታ ያላትና ብርሀን ያላት መሆኗ ሌሎች ምልክቶች ናቸው። በእርግጥም አላህ ለአንዳንድ ሠዎች በመናም (በህልም) ሊያሳውቃቸውና ብርሀኗን ሊያሳያቸው ይችላል። ይህ ለይለቱል ቀድር ነው ብሎ የሚነግራቸው ሠው ሊልክባቸው ወይም ልቡን ከፍቶለት እውነት ለይለቱል ቀድር መሆኗን የሚለይበት ነገር ልቡ ውስጥ ሊጥልበት ይችላል።” የኢብኑ ተይሚያህ ንግግር እዚህ ላይ አበቃ።

በእለቱ የሙስሊሞች ሥራ ምን መሆን አለበት?

ለሊቱ የተባረከ ለሊት ነው። ከአንድ ሺህ ወራት በላይ ዋጋ ያለው ለሊትም ነው። አላህ -ልክ ጁምዓ ውስጥ ያለችውን፣ ዱዓ ተቀባይነት የሚያገኝባትን ውድ ሰዓት እና ታላቁን ስሙን (ኢስሙል አዕዘምን) እንደደበቀ ሁሉ- ለይለቱል ቀድርንም ደብቋታል። የመደበቃቸው ምስጢርም ሠዎች እነሱን ለማግኘት እንዲጥሩ ለማድረግ ነው። በእርግጥ ለይለቱል ቀድር መች እንደሆነ በውል ባይታወቅም አስሩ የመጨረሻ ቀናት ውስጥ መሆኑን አሳልፈናል። ስለዚህ እርሷን ለማግኘት አስሩን የመጨረሻ ቀናት ለሊቶች በሙሉ በዚክር፣ በዱዓ፣ ቁርአን በመቅራት፣ ሶላት በመስገድ… ማሳለፍ ያስፈልጋል።

የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) አስሩ የመጨረሻ የረመዳን ቀናት ውስጥ -ከምንም ጊዜው በላይ- ለዒባዳ ይጠነክራሉ። ቁርኣን ያነባሉ። ሶላት ያበዛሉ። ዱዓ ላይ ይጠነክራሉ። ቡኻሪ እና ሙስሊም አዒሻን (ረ.ዐ) ዋቢ በማድረግ እንደዘገቡት:-

أن النبي صلى الله عليه وسلم كان إذا دخل العشر الأواخر أحيا الليل وأيقظ أهله وشد المئزر

“የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) አስሩ የረመዳን የመጨረሻ ቀናት በሚገቡ ጊዜ ለሊቱን ህያው ያደርጋሉ። ቤተሰቦቻቸውን ያነቃሉ። ሽርጣቸውን ያጠብቃሉ።”(ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)

በአህመድና በሙስሊም ዘገባ:-

كان يجتهد في العشر الأواخر ما لا يجتهد في غيرها

“መልእክተኛው (ሰ.ዐ.ወ) በሌላ ጊዜ ከሚያደርጉት አምልኮ በላቀ ሁኔታ በእነዚህ አስር ቀናት ውስጥ ያደርጋሉ።” (አህመድና ሙስሊም ዘግበውታል)

ለይለቱል ቀድርን እንድንጠብቅ የአላህ ነብይ (ሰ.ዐ.ወ) ብዙ ጊዜ ቅስቀሳዎችን አድርገዋል። ከሰዪዲና አቡሁረይራህ እንደተዘገበው የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- “(የአላህን ቃልኪዳን) እያመነና (ምንዳውን) እየተሳሰበ ለይለቱል ቀድርን የቆመ (የሰገደበት) ሰው ያሳለፈውን ወንጀል በሙሉ ይማራል።” ስለዚህ ይህ ሐዲስ ለሊቱን በሶላት ማሳለፍ እንሚወደድ እያስተማረ ነው።

ያን ቀን ዱዓ እንድናደርግ የሚቀሰቅሱ ሐዲሶችንም እናገኛለን። ቲርሚዚ አዒሻን (ረ.ዐ) ዋቢ አድርገው ባስተላለፉት ሐዲስ

قلت: يا رسول الله، أرأيت إن علمت أي ليلة ليلة القدر ما أقول فيها؟ قال: قولي: اللهم إنك عفو تحب العفو فاعف عني

“የአላህ መልእክተኛን (ሰ.ዐ.ወ) ለይለቱል ቀድርን ካወኩኝ
Forwarded from Hik promo
ጌዜዎን በምን ማሳለፍ ይፈልጋሉ ከታች ምርጥ ምርጥ ቻናሎች ለናንተው ተስማሜ ናቸው
""""""🎁 ረመዷን 🎁"""""""""

ነብያችን (ሰ ዐ ወ) በ3 🎁 ነገሮች ያልተጠቀመ ሰው ከአላህ ራህመት የወጣ ሰው ነው ብለዋል!!!
1 "ረመዷን መቶ ራሱን ወደ ኸይር ስራ ያልመለሰ ሰው::
2 "የኔ ስም ሲነሳ ሶለዋት የማያወርድ ሰው::
3 "እናትና አባቱ በህይወት እያሉ ያልተጠቀመባቸው ሰው ናቸው ብለዋል:: ሰለዚህ ይህ ታላቅ እንግዳ ብዙ ኸይሮችን ይዞልን እየመጣ ነው አኛስ በዚህ በተባረከ ወር አጅር ለመሰብሰብ ምን ያክል ዝግጁ ነን?? ""በዚህ ተላቅ እንግዳ መምጣት ምክንያት,,,,,
1 ሾይጧን ይታሰራል
2 የጀሀነም በሮች ይዘጋጋሉ
3 የጀነት በሮች ይከፉፈታሉ:: ይሉናል ረሱል )ሰዐወ( ::
በዘህ በረመዷን ወር:,
1 "በመጀመሪያዎቹ 10 ቀናት አላህ ለባሮቹ ራህመት
የሚያወርድበት ነው::
2 "በመካከለኛዎቹ 10 "ቀናት አላህ ባሮቹን የሚምርበት ነው::
3 "በመጨረሻዎቹ 10 ቀናት ደግሞ አላህ ባሮቹን ከጀሀነም እሳት ነፃ የሚያወጣበት ነው:: ይሉናል ነብይና ሙሀመድ (ሰዐወ) ያ አላህ እውነትም በዘህ ወር
ያልተጠቀመ ከአላህ እዝነት የወጣ ነወ አላህ ይጠብቀን
እና:: እናም እህት ወንድሞቸ የ11 ወር ወንጀል ተጠራርጎ
ገደል በሚገባበት በዘህ ታላቅ ወር ሁላችንም ለዒባዳ
መነሳሳት ለኸይር ስራ መሽቀዳደም ይኖርብናል በዘህ ወር አላህ ጋ ያለንን ግንኙነት ካላስተካከልን መቸም አናስተካክልም:: አላህ በዚህ ታላቅ ወር ከሚጠቀሙት ያድርገን:: አሚን
ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ተናገሩ"አንድ ሰው በሞተ ጊዜ ዘመዶቹ በቀብር ሥነስርአቱ ላይ ሲጨናነቁ አንድ እጅግ ያማረ ቆንጆ ሰው በጭንቅላቱ በኩል ይቆማል።ጀናዛውም እንደተከፈነ ያ ሰው በከፈኑ እና በሞተው ሰው ደረት መሀል ይሆናል።ከቀብር ሥነስርአቱም በህዋላ ቀባሪ ቤተሰቦቹ ወደ ቤት ሲመለሱ ሁለት ሙንከር እና ነኪር የተባሉ ምላኢኮች ወደ ቀብሩ በመምጣት ጀናዛውንና ያንን ቆንጆ ሰው በመለያየት ያንን የሞተውን ሰው በእምነቱ ጉዳይ ብቻውን በጥያቄ ሊያፋጡት ይሞክራሉ ። ሆኖም ያ ቆንጆ ሰው ይናገራል "ይህ ሰው አጋሬም ጋደኛዬም ነው ብቻውንም ልተወው አልችልም። እናንተ እንድትጠይቁት ከተመደባቹ ስራችሁን መሥራት ትችላላቹ እኔ ግን ወደ ጀነት መግባቱን ሳላረጋግጥ ትቼው እልሄድም"። ከዝያም ወደ ሞተው አጋሩ በመዞር እንዲህ ይለዋል "እኔ አንዳንዴ ድምፅህን ከፍ አርገህ ሌላ ጊዜ ደግሞ ቀስ ብለህ ስታነበኝ የነበርኩት ቁርአን ነኝ ምንም አትጨነቅ፤ ከሙንከርና ነኪር ጥያቄና መልስ በኃላ ምንም ጭንቀት አይኖርብህም"፤ጥያቄና መልሱም ካለቀ በኃላ ያ ቆንጆ ሰው አል ማሉል አላ በተባሉ የጀነት መላኢኮች የተዘጋጀ በመልካም ሽታ የሚያውድ እና ከ ሀር በተሰራ ልብስ የተዘጋጀ አልጋ ያዘጋጅለታል።
2. ረሰል(ሶ.ዐ.ወ) እንደተናገሩት በቂያማ ቀን በአላህ ሱ.ወ ፊት ስንቆም ከቁርአን የበለጠ ለኛ ሚከራከርልን አይኖርም ከነብይያትም ከ መላኢኮችም በበለጠ።
3. እባክዎን ይህን መልእክት የቻሉትን ያህል ያስተላልፉ። ረሱል (ሶ.ዐ.ወ) እውቀትን ከኔ ለሌላው አስተላልፉ አንድም አረፍተ ነገር ብትሆን እንኩዋን ብለዋል።
4. ይህ መልእክት 🗣በ አላህ ፍቃድ በቀጣይ 7 ቀናት ቢያንስ 5 ሚልዬን👥 ሰዎች እንዲዳረስ ዱአ እያደረግን ነው።

☕️ እባክዎን ይህን መልእክት ለ ቤተሰብዎ😍😘 ለዘመድዎትና ላሚያውቅዋቸው ሁሉ በማስተላለፍ
/ ♻️ሼር♻️ / ከተትረፈረፈው የአላህ ምንዳ ተጠቃሚ ይሁኑ 🙏
🍋 እርስዎ ቁርአንን ሲይዙ ሰይጣን ራሱን ያመዋል።
🍋 ሲከፍቱት ይወድቃል።
🍋 እያነበቡት ሲያይ ራሱን ይስታል።
🍋 "ይህንን መልእክት ሊያስተላልፉ ሲያስቡ ላማዳከምና ለማስነፍ ይሞክራል"።

😍 እኔ አሸነፍኩት ምክንያቱም ለእርስዎ መላክ ችያለሁ። እርሶስ??? ምን ይጠብቃሉ ♻️ ሼር ያርጉት ለምታቁት ሙስሊም 👳‍♂ወንድሞቻችንና 🧕እህቶቻችን .......
-------------------🌀------------------------🌀
«ዱኒያ»
«የሰው ልጅ አንዳንዴ አላህ"ﷻ"በሐብት፣ በመልካም ሚስት፣ በልጆች ሲያጣቅመውና በጤንነት ሲያቀማጥለው የጸጋን በሮች ሁሉ በከፈተለት ጊዜ ልክ አሏህ እንደወደደው አድርጎ ያስባል።

فَأَمَّا ٱلۡإِنسَٰنُ إِذَا مَا ٱبۡتَلَىٰهُ رَبُّهُۥ فَأَكۡرَمَهُۥ وَنَعَّمَهُۥ فَيَقُولُ رَبِّيٓ أَكۡرَمَنِ
ሰውማ ጌታው በሞከረው ጊዜ፣ ባከበረውና ባጣቀመውም (ጊዜ) «ጌታዬ አከበረኝ (አበለጠኝ)» ይላል፡፡ (89/15)

«ሌላኛው ሰው ደግሞ ቤት፣ መኪና፣ ሀብት፣ሚስት ስለሌለው ብትኖርም ሀዘን ስትሆንበት፣ ልጆቹ አመጸኞች ሲሆኑበት ልክ አላህ እንደጠላው አድርጎ ያስባል።

وَأَمَّآ إِذَا مَا ٱبۡتَلَىٰهُ فَقَدَرَ عَلَيۡهِ رِزۡقَهُۥ فَيَقُولُ رَبِّيٓ أَهَٰنَنِ
በሞከረውና በእርሱ ላይ ሲሳዩን ባጠበበ ጊዜማ «ጌታዬ አሳነሰኝ» ይላል፡፡ (89/ 16)

« እውነታው ግን እነዚህ አይነት የሰው ልጆ አስተሳሰብና ለአላህ ውዴታ መመዘኛ የሰጡት ትርጉም ትክክል አይደለም። ለዚህም አላህ"ﷻ" ቀጥሎ { كَلَّا } ሲል ሁለቱንም የተዛባ አስተሳሰብ ውድቅ ደረገው። {"كَلَّا") በዐረብኛ ቋንቋ ከፊቷ የነበረን የተዛባ አስተሳሰብ ውድቅ አድራጊ ቃል ናት።

"ማለትም ከላይ በመጣው ዐውድ መልእክቷ «እናንተ ሰዎች ሆይ! እናንተ እንደምታስቡት አይደለም። የሀብትና ጸጋ ስፋት መስጠቱ የአላህ ውዴታን አይገልጽም። የሀብት ጥበትና የተጨናነቃ ሀያት የአሏህን አለመውደድ አይገልጽም። አላህ"ﷻ" ዱንያን ለሚወደውም፣ለማይወደውም፣ ለሙእሚንም፣ ለካፊርም፣ ይሠጠዋል» ማለቷ ነው።

«የአላህ መልክተኛ"ﷺ" እንዲህ ብለዋል፦ «ዱኒያ ከአላህ ዘንድ የትንኝ ክንፍ ያክል ሚዛን ቢኖራት ኖሮ ካፊር አንዲትን ጉንጭ ውሃ ከእርሷ አይጎነጭም ነበር»። (ቲርሚዚይ፥ 2320)

«የዱኒያ ነገር እንደዚህ ከሆነ፦ አንድ ሰው አላህ ጸጋ በረከቱን ቢከፍትለት፡በጤና ፣ በሀብት፣ በልጆች ቢንደላቀቅ በእርግጥ የአላህ (ፈድል) ችሮታ ነው። ግን ይህ ሰው ሙጅሪም ሁኖ ጌታውን እያመጸ አላህ"ﷻ" ጸጋና በረከት የሰጠኝ ስለወደደኝ ነው ብሎ ካሰበ መልሱ "ከልላ" ነው።

«ሰዎች በኩፍር ላይ ሁነው የወንጀልን አይነት ሁሉ እየፈጸሙ አላህ በሀብትና በንግሥና ምስራቁንም ምዕራቡንም እንዲገዙ ሲፈቅድ በዚህ ጸጋ ብቻ አላህ ስለወደዳቸው መስሎ የሚታያቸው ይህንንም ጸጋ ለውዴታው ማስረጃ ሊያደርጉ ይችላሉ። መልሱ ግን አሁንም «አይደለም» ነው።

«ይህ አይነት እውነታ በተጨባጭ ታሪክ ተፈጽሞ አልፏል።
«ቃሩን»፦ አመጸኛ ከኃዲ ነው አላህ አይወደውም። ግን የሀብቱ ካዝና መክፈቻ ቁልፎች ብቻ በብዙ በግመሎች ይጫን ነበር። ግን አላህ እስከ ንብረቱ ወደ ምድር አሰጠመው።

«ለነብዩ ሱለይማን(ዐሰ)»፦ አላህ ንግሥናንና ሀብትን ሰጥቷቸዋል ግን ይወዳቸዋል ምርጥ የአሏህ ባሪያ ታላቅ ነብይ ነበሩ።

«ለፈርዖን»፦ አላህ ንግሥና ሀብትን ጸጋዎቹን ለግሶታል። ጸጋው ከአቅሙ በላይ ሁኖበት «እኔ ሃያሉ አምላክ» ነኝ ብሎ እስኪናገር ድረስ በጸጋ አቀማጥሎታል። ግን አይወደውም በክፉ ቅጣት ይዞታል።

«ዱንያ የአሏህን ውዴታ መለኪያ መስፈርት በፍጹም ልትሆን አትችልም። ምክንያቱም የትንኝ ክንፍ ያክል እንኳ ሚዛን የላትምና። አላህ"ﷻ" እንዲወደው የፈለገ፦ ሙእሚን መሆን፣ የእርሱን ትእዛዝ ይጠብቃል፣ መልካምን ይሠራል፣ ለሠዎች ያዝናል፣ ሁሌ ለኽይር ስራ ሁሉ ተሽቀዳዳሚ ይሆናል።

«በጎ ሥራንም ሥሩ፤ አላህ በጎ ሠሪዎችን ይወዳልና፡፡ (2/195)
«አላህ (ከኃጢኣት) ተመላሾችን ይወዳል፤ ተጥራሪዎችንም ይወዳል በላቸው፡፡ (2/222)

«በቃል ኪዳኑ የሞላና የተጠነቀቀ ሰው አላህ ጥንቁቆችን ይወዳል፡፡ (3/76)
«አላህም ትዕግስተኞችን ይወዳል፡፡ (3/146)
«አላህ በርሱ ላይ ተመኪዎችን ይወዳልና፡፡ (3/159)
«አላህ በትክክል ፈራጆችን ይወዳልና፡፡ (5/42)

«በነገሩ ሁሉ አስተካክሉም፡፡ አላህ አስተካካዮችን ይወዳልና፡፡ (49/9)
«አላህ እነዚያን እነርሱ ልክ እንደ ተናሰ ግንብ የተሰለፉ ኾነው በመንገዱ (በሃይማኖቱ) የሚጋደሉትን ይወዳል፡፡ (61/4)

የአላህን ሐቅ ጠብቀው እሱ ከወደዳቸው ባሮቹ ያድርገን።
❐.በቴሌ ግራም፦ https://www.tg-me.com/eslamic_center
★የኢማን ድክመት★
★★★★★★★★
የኢማን ድክመት በሙስሊሞች መካከል እጅጉኑ የተስፋፋ እና የተበተነ በሽታ ነው፣ የዚህ በሽታ ተፅኖ ወይም የበሽያው ክፋት ታማሚዎች ላይ በግልፅ እየታየ ይገኛል፣ ይህ የኢማን መድከም በሽታ የሙሲባ ሁሉ መነሻ መሰረት የበላእ ሁሉ ምክናየት ነው።
አመፅ ላይ መውደቅ የኢማን ትልቁ ድክመት ነው፣ ወንጀሎችን መዳፈር በብዙሃኖች ዘንድ እንደ ወንጀል ሳይሆን እንደ ተለምዶ እስኪታይ ድረስ ሲደጋገምና ሲፈፀም ይታያል፣ ይባስ ብሎ ወንጀል ፈፃሚዎቹ በመፀፀት ፋንታ ሲፎክሩበት እያየን ነው። ሰውየው ለመጀመሪያ ግዜ ወንጀልን ሲፈፅም እያፀየፈው ሲሰራ እንዳልነበር እየተላመደው እና ልቡ በወንጀል እየተሸፈነ ሲመጣ ወንጀሏ አይኑ ላይ እያነሰችና ቦታ የማይሰጣት ቀላል ነገር ሆና ትታየዋለች በዚህም በኩል ጥፋቱ እየተስፋፋ ጌታውን መዳፈሩ እየጨመረ ይሄዳል።

ﺣﺪﻳﺚ ﺃﺑﻲ ﻫﺮﻳﺮﺓ  ﻗﺎﻝ : ﺳﻤﻌﺖ ﺭﺳﻮﻝ
ﺍﻟﻠﻪ ﷺ ﻳﻘﻮﻝ : ‏« ﻛﻞ ﺃﻣﺘﻲ ﻣﻌﺎﻓﻰ ﺇﻻ
ﺍﻟﻤﺠﺎﻫﺮﻳﻦ، ﻭﺇﻥ ﻣﻦ ﺍﻟﻤﺠﺎﻫﺮﺓ ﺃﻥ ﻳﻌﻤﻞ
ﺍﻟﺮﺟﻞ ﺑﺎﻟﻠﻴﻞ ﻋﻤﻼ، ﺛﻢ ﻳﺼﺒﺢ ﻭﻗﺪ ﺳﺘﺮﻩ ﺍﻟﻠﻪ
ﻋﻠﻴﻪ ﻓﻴﻘﻮﻝ : ﻳﺎ ﻓﻼﻥ، ﻋﻤﻠﺖ ﺍﻟﺒﺎﺭﺣﺔ ﻛﺬﺍ
ﻭﻛﺬﺍ، ﻭﻗﺪ ﺑﺎﺕ ﻳﺴﺘﺮﻩ ﺭﺑﻪ، ﻭﻳﺼﺒﺢ ﻳﻜﺸﻒ
ﺳﺘﺮ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻨﻪ‏» ، ﻣﺘﻔﻖ ﻋﻠﻴﻪ
አቡ ሁረይራህ ባስተላለፉት ሀዲስ የአሏህ መልእክተኛ ﷺ: «ኡማዬ ሁሉም ይማርለታል ይቅር ይባላል ወንጀላቸውን ለሰው የሚያወሩት ሙጃሂሮች ሲቀሩ ፣ ወንጀሉን ይፋ ከማውጣት ይመደባል አንድ ሰው ለሊት ወንጅሎ ወንጀሉን አሏህ ሸፍኖለት አድሮ ሳለ አንተ እከሌ እኔኮ ዛሬ ለሊት እንድህ እንድህ ሳደርግ አደርኩኝ ብሎ ማለቱ ፣ ጌታው ደብቆለት ሰትሮለት አድሮ እሱ የአሏህን የሽፋን ግርዶ ከራሱ ላይ ይገላልጠዋል።» አሉ
ቡኻሪ (6069) ሙስሊም (2990) ዘግበውታል

قال الله ( ثُمَّ قَسَتْ قُلُوبُكُم مِّن بَعْدِ ذَٰلِكَ فَهِيَ كَالْحِجَارَةِ أَوْ أَشَدُّ قَسْوَةً ۚ )
البقرة (74)

ጌታችን አሏህ እንድህ አለ፦ {ከዛም በኋላ ልቦቻቸው ፣ እንደ ድንጋይ ኧረ ከዛም በላይ ደረቀች።} አል በቀረህ (74)

ወንድሞቼና እህቶቼ ልቡ በወንጀል የደረቀ ሰው ምክር አይጠቀረመውም።

( إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَذِكْرَىٰ لِمَن كَانَ لَهُ قَلْبٌ)
ق (37)

አሏህ እንድህ አለ፦ {በዚህ ተግሳፅ አለ የሚያስተነትንበት ጥሩ ልቦና ላለው።} ቃፍ (37)

ሰዎች ዒባዳ ላይ መዘናጋታቸው ፣ ለዒባዳ ትኩረት አለመስጠታቸው ፣ ሶላታቸውን እህል እንደሚለቅም ዶሮ መተክተካቸው ይህ የኢማን ድክመት ነው ብዙዎች ሶላት ሲሰግዱ በልቡ ዱንያን ይዞራል የአሏህ መልእክተኛ ﷺ: ቲርሚዚ (3479) አቡ ሁረይራን ዋቢ በማድረግ በዘገቡት ሀዲስ «እናንተ ዱዓችሁ መልስ እንደሚያገኝ እርግጠኛ የሆናችሁ ስትሆኑ አሏህን ለምኑት ፣ እወቁ አሏህ ከዘነጋ ልብ ዱዓእን እንደማይቀበል።»

ከጥፋታችን በመውጣት አሏህን ምህረት በመጠየቅ ከበሽታው ልንላቀቅ ተገቢ ነው።
https://www.tg-me.com/eslamic_center
👉🌲#ነብዩሏህ_ሷሊህ_ዐለይሂ_ሰላም🌲

🌈ክፍል 1⃣

ሳሊህ ዐ ሰ በነቢይነት ከመመረጣቸው በፊት ህዝቡ ዘንድ በምልካም ስነ
ምግባራቸው የሚታወቁ፣ከከበርቴ ቤተሰብ የተወለዱ፣ከዚያም አልፎ ሰዎች
ለፍርድ ሚያስቸግር ክርክር ሲገጥማቸው እሳቸው ጋር የሚሄዱ ምርጥ የአላህ
ባርያ ናቸው።
ወደፊት ሀገሪቷን በንግስና ያስተዳድሯታል ተብሎም ይገመት ነበር።
በንዲህ አይነት ሁኔታ ላይ ሳለ ሳሊህ ዐ ሰ የጌታቸውን ተልዕኮ እንደተቀበሉ
በትኩስነቱ፦" ወገኖቼ ሆይ! አላህን ተገዙ፡፡ ከእርሱ ሌላ ለእናንተ ምንም
አምላክ የላችሁም፡፡ ከዓድም በኋላ ምትኮች ባደረጋችሁና በምድሪቱም ላይ
ባስቀመጣችሁ ጊዜ አስታውሱ፡፡ ከሜዳዎቿ (ሸክላ) ሕንጻዎችን ትገነባላችሁ፡፡
ከተራራዎችም ቤቶችን ትጠርባላችሁ፡፡ ስለዚህ የአላህን ጸጋዎች አስታውሱ፡፡
በምድርም ውስጥ አጥፊዎች ኾናችሁ አታበላሹ" በማለት ጥሪውን አስተጋባ።
ይህን በሰሙ ግዜ ትዕቢታቸው አናታቸው ላይ ወጣ...ኩራታቸው
ገነፈለ...የከተማይቱ መሳፍንትም፦"አንተ ሳሊህ! ቆይ አንተ ከኛ በምን ተሽለህ
ነው አላህ መልዕክተኛ አድርጎ ሊመርጥህ የቻለው? ይልቁኑ አማልክቶቻችን
በመጥፎ አይን ሳያዩህ አልቀሩም'ና አብደሀል" አሉት።
ከዚያም እንደተለመደው ሳሊህ(ዐ ሰ) የድሆች እና ምስኪኖች ተከታይ
ይበራከቱለት ጀመር።ይሁን እንጂ በለፀጋዎች እና ጉልበተኞቹ ዝም ማለትን
አልመረጡም'ና ምእመናኑ ዘንድ በመሄድ፦"እናንተ ባመናችሁት ነገር እኛ
ክደናል" በማለት ይሳለቁባቸው ነበር።
ከዛላችሁ እነዚህ አመፀኛ ህዝቦች አንደ ቀን የሳሊህን ዐ ሰ ጥሪ ለማስቆም
እና ተከታዮቹን ከሱ ለማራቅ ምን ማድረግ እንዳለባቸው ሊመካከሩ አንድ ቦታ
ተሰበሰቡ።
ብዙ ከመከሩ በኋላ በመጨረሻም ሳሊህን (ዐ ሰ) ያለ ተከታይ ብቻውን
ለማስቀረት አንድ መፍትሄ አገኙ።
እሱም፦"ሳሊህን የሚከተል ከአማልክቱ በኩል የማይድንን በሽታ
ይይዘዋል።ከሳሊህም የሚርቅ ከነዚህ ነገሮች የተጠበቀ ይሆናል" በማለት
ከተማይቷን ቀወጧት።
ነገር ግን ትክክለኛይቱ የዳዕዋ ጥሪ መንገዷን ይዛ ቀጥላለች።በዚህ ሁኔታ ላይ
ሳሉ አንድ ቀን ሳሊህ ዐ ሰ ጥሪያቸውን በህዝብ ፊት ሲያደርሱ ህዝቡም፦"አንተ
ሳሊህ እውን አንተ ነቢይ ከሆንክ ማረጋገጫ ይሆነን ዘንድ እስቲ ተዐምር
አምጣልን" አሉት።
የከተማይቱ ሹማምንት እና የተከበሩ ሰዎች በቦታው ነበሩ።የማይችለውን ነገር
በመጠየቅ እንዳደናገሩት በማሰብ የማላገጥን ሳቅ ይስቁበትም ጀመር።(ወላሂ
ነቢያቶች አላህ ምንዳቸውን ከፍ ያድርግላቸው።በገዛ ሀገራቸው ይሳቀቃሉ)
ከመሳፍንቱ መሀክል አንዱ ቆመ'ና፦"አንተ ሳሊህ ተዐምር ማሳየት እችላለሁ
የምትል ከሆነ የተዐምሩን አይነት እኛ ነን ምንመርጠው ያንተ ስራ እኛ
የመረጥነውን ተዐምር መተግበር ብቻ ነው" አሉት
እኛ እያየን ከዚህ ተራራ ውስጥ በግዝፈቷ አቻ የሌላት የአስር ወር እርጉዝ
የሆነች፣መልኳም ቀይ የሆነ፣ከግዝፈቷ የተነሳ የከተማይቱ ይዝብ እና እንስሳት
የሚጠጡትን ውሀ በአንዴው መጠጣት የምትችል ትልቅ ግመል
አውጣልን"አሉት።
ነቢዩላህ ሳሊህም (ዐ ሰ) ህዝቡ ሁሉ ተዐምሩን አይተው በማመን ከጀሀነም
ይድኑ ዘንድ የከተማይቱ ሰው ሁሉ እንዲሰበሰብ አዘዙ'ና ሁሉም ተሰበሰቡ።
ከዚያም ሳሊህ (ዐ ሰ) ለጌታቸው ሱጁድ በመውረድ ጌታቸውን ይማፀኑ
ጀመር።አላህም የሱን መልዕክተኞች በህዝባቸው ፊት አያሳፍራቸውም'ና
ተራራው በጣም መንቀጥቀጥ ጀመረ።
ህዝቡ ሁሉ አይኑን ተራራው ላይ ተክሏል።ካሁን አሁን ምን ሊከሰት ነው
በማለት እርስ በርስ ይተያያሉ።
በዚህ ሁኔታ ላይ ሳሉ ተራራው ከፍተኛ ጩኸት ካስተጋባ በኋላ በጣም
በመሰንጠቅ ከመሀከሉ ህዝቡ በጠየቀው መልኩ ትልቅ እና እርጉዝ ቀይ
ግመል ወጣች።
ይህን ባዩ ግዜ አይኖቻቸው ፈጠጠ፣ አንደበታቸው ደረቀ፣ምላሶቻቸው ተሳሰሩ።
ሳሊህም ዐ ሰ፦"ህዝቦቼ ሆይ! ይህች ግመል የአላህ ተዐምር
ናት።ታይዋታላችሁ፤ ትዳስሷታላችሁም እናንተ ዘንድም ትኖራለች።
ባስቀመጣችሁት መስፈርት መሰረት ትልቅ እና እርጉዝ ሴት ግመል እንደመሆኗ
መጠን ካሁን በኋላ ውሀችሁንም ለጋራ ነው ምትጠጡት።
አንድ ቀን ግመሊቱ ስትጠጣ ቀጣይ ቀን እናንተ ትጠጣላችሁ። ምክንያቱም
መጀመርያ ያስቀመጣችሁት መስፈርት ይህ ነው'ና።
ነገር ግን ይህችን ግመል አንዳችሁ በመጥፎ ከተተናኮላችኋት የአላህ ፈጣኑ
ቅጣት ይወርድባችኋል" በማለት አስረዳቸው።
ከዚያም ህዝቡ ለሳሊህ ዐ ሰ ያለው አመለካከት 100% ተቀየረ።ሁሉም
ከማንም በላይ ሳሊህን ያከብር ጀመረ።ብዙ ሺህ ሰውም የሳሊህ ተከታይ ሆነ።
ይህ ያሳሰባቸው የከተማይቱ ሹማምንት አንድ ቀን ተሰብስበው ምን ማድረግ
እንዳለባቸው ሲወያዩ ውለው በመጨረሻም ግመሊቱን በመግደል ተስማሙ።
ይህ የተወሰነውም በአንድ መጠጥ ቤት ውስጥ ሆነው ነበር።አጋጣሚ እዛው
መጠጥ ቤት ሳሉ የመጠጥ ጥማቸው ሳይቋረጥም ከመጠጡ ቤት ጓዳ
"መጠጥ አልቋል" የሚል መርዶ ደረሳቸው።
ሹመንቱም፦"ለምንድነው በርከት አድርጋችሁ ማትሰሩት" ብለው ሲጮሁባቸው
የመጠጥ ቤቱ ባለቤት፦"ዛሬ ውሀ የግመሊቱ ተራ ስለሆነ ውሀ የለም'ና ብዙ
መስራት አልቻንም" ብላ መለሰችላቸው።
ከመሀከላቸውም አንድ ቀዳር ኢብን ሳሊፍ ኢብን ጁንደዕ የተባለ አመፀኛ
ከመሰል ጓደኛው ጋር ተነሳ'ና ግመሏን ሊገድል ጉዞ ጀመረ።በጉዞ ላይ ሳሉም
ሌላ ሰባት ሰዎችን መንገድ ላይ በመቀላቀል ዘጠኝ ሁነው ግመሏ ውሀ
የምትጠጣበት ስፍራ ደረሱ።....
www.tg-me.com/eslamic_center
👌*ዘካቱልፊጥር ምንድን ነው?*
ዘካቱልፊጥር የረመዳን ፆም መገባደጃ ላይ የሚሠጥ ሶደቃ (ምፅዋት) ነው። በነፍስ ወከፍ እያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው። “ሰደቀቱል-ፊጥር”፣ “ሰደቀቱ ረመዳን” እና “ዘካቱል-በደን” ተብሎም ይጠራል- ዘካቱልፊጥር።

*መች ተደነገገ? አስፈላጊነቱስ?*

ዘካቱልፊጥር ከሒጅራ በኋላ ሁለተኛው አመት ላይ ተደነገገ። እንደ አብዝሀ ዑለሞች እምነት ዘካቱልፊጥር ግዴታ (ዋጂብ) ነው። ጥቂቶች የጠበቀ ሱና (ሱና ሙአከዳ) እንጂ ግዴታ አይደለም የሚል አቋም አላቸው። ግዴታ ለመሆኑ የሚቀርቡ መረጃዎች በርካታ ናቸው። ከነርሱ መሀል ጥቂቶቹን እናንሳ። በቅድሚያ ከቁርአን፡-

وَالَّذِينَ فِي أَمْوَالِهِمْ حَقٌّ مَّعْلُومٌ

لِّلسَّائِلِ وَالْمَحْرُومِ

“እነዚያም በገንዘቦቻቸው ላይ የታወቀ መብት ያለባቸው የኾኑት። ለለማኝ ከልመና ለሚከለከልም (መብት ያለባቸው የኾኑት)።” (አል-መዓሪጅ 70፤ 24-25)

ከሐዲስ ደግሞ ይኸኛውን እንይ፡- ከዐብዱላህ ኢብኑ ዐባስ እንደተዘገበው

فَرَضَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم زَكَاةَ الْفِطْرِ؛ طُهْرَةً لِلصَّائِمِ مِنَ اللَّغْوِ وَالرَّفَثِ، وَطُعْمَةً لِلْمَسَاكِينِ، مَنْ أَدَّاهَا قَبْلَ الصَّلاةِ فَهِيَ زَكَاةٌ مَقْبُولَةٌ، وَمَنْ أَدَّاهَا بَعْدَ الصَّلاةِ فَهِيَ صَدَقَةٌ مِنَ الصَّدَقَاتِ

“ዘካቱልፊጥር ፆመኛ ከአልባሌ ንግግርና ከረፈስ (የወሲብ ወሬዎች) እንዲፀዳበትና ለድሆች ምግብ እንዲሆን የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ.) ደንግገውታል። ከሰላት በፊት የሠጠ ሰው ተቀባይነት አለው። ከሰላት በኋላ የሠጠ ሰው ግን እንደማንኛውም ሰደቃ ትሆንለታለች።” (አቡ ዳዉድና ኢብኑ ማጃህ ዘግበውታል፤ ሃኪም ሀዲሱን በቡኻሪ መስፈርት ሶሂህ ብለውታል)

የፊጥር ዘካ የፆመኞችን ፆም ይጠግናል። በሠላሳው የፆም ቀናት ወቅት ከተናገራቸው መጥፎ ንግግሮች፣ ከአጓጉል ቀልዶች ማበሻ በመሆን ፆሙን እንደማሟያና መጠገኛ ሆኖ ፅዱ እና ንፁህ ያደርገዋል። ከዚህም ሌላ ዘካተልፊጥር በውስጡ ከፍተኛ የሆነ ማህበራዊ ጥቅም ይዟል። ድሆችና ችግረኞች በተባረከው የዒድ ቀን ለልመና እንዳይሠማሩና የሰውን እጅ ከማየት ተብቃቅተው ተደስተው እንዲውሉ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደርጋል።
*
*ማን ላይ ነው ግዴታ የሚሆነው? ምን ያህል ነው መጠኑ?**

ከኢብኑ ዑመር (ረ.ዐ) እንደተዘገበው፡-

فَرَضَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم زَكَاةَ الْفِطْرِ صَاعًا مِنْ تَمْرٍ أَوْ صَاعًا مِنْ شَعِيرٍ، عَلَى الْعَبْدِ وَالْحُرِّ، وَالذَّكَرِ وَالأُنْثَى، وَالصَّغِيرِ وَالْكَبِيرِ، مِنْ الْمُسْلِمِينَ، وَأَمَرَ بِهَا أَنْ تُؤَدَّى قَبْلَ خُرُوجِ النَّاسِ إِلَى الصَّلاةِ

“የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ.) -ባሪያና ጨዋን፣ ወንድና ሴትን፣ ህፃንና አዋቂን ሳይለዩ- ዘካቱል-ፊጥርን በማንኛውም ሙስሊም ላይ ግዴታ አድርገዋል። ዘካው የሚሠጠው አንድ ቁና ተምር ወይም አንድ ቁና ገብስ ነው ። ቁና ወይም አንድ ሷዕ ግምቱ 2.25 ኪ.ግ. (ሁለት ኪሎ ግራም ከሩብ) ተብሏል። ሰዎች ለሰላት ወደ መስገጃ ቦታ ከመውጣታቸው በፊት ዘካው እንዲሰጥም አዘዋል።” (ቡኻሪና ሙስሊም)

*ዘካተልፊጥር የሚሠጠው መች ነው?*

ከዐብዱላህ ኢብኑ ዐባስ የተዘገበው ሀዲስ እንዲህ ይላል፡-

فَرَضَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم زَكَاةَ الْفِطْرِ؛ طُهْرَةً لِلصَّائِمِ مِنَ اللَّغْوِ وَالرَّفَثِ، وَطُعْمَةً لِلْمَسَاكِينِ، مَنْ أَدَّاهَا قَبْلَ الصَّلاةِ فَهِيَ زَكَاةٌ مَقْبُولَةٌ، وَمَنْ أَدَّاهَا بَعْدَ الصَّلاةِ فَهِيَ صَدَقَةٌ مِنَ الصَّدَقَاتِ

“ዘካቱልፊጥርን ፆመኛ ከአልባሌ ንግግርና ከረፈስ (የወሲብ ወሬዎች) እንዲፀዳበትና ለድሆች ምግብ እንዲሆን የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ.) ደንግገውታል። ከሰላት በፊት የሠጠ ሰው ተቀባይነት አለው። ከሰላት በኋላ የሠጠ ሰው ግን እንደማንኛውም ሰደቃ ይሆንለታል።” (አቡ ዳዉድና ኢብኑ ማጃህ ዘግበውታል፤ ሃኪም ሀዲሱን በቡኻሪ መስፈርት ሶሂህ ብለውታል)

*ዘካችንን ለማን እንስጥ?*

ፉቀሃዎች ዘካቱልፊጥር የሚሠጠው የገንዘብ ዘካ (ዘካቱል-ማል) ለሚሠጣቸው ሠዎች ነው ብለው ያምናሉ። አላህም በቁርአን ውስጥ የነርሱን ማንነት ጠቅሷል። አላህ እንዲህ ይላል፡-

إِنَّمَا الصَّدَقَاتُ لِلْفُقَرَاءِ وَالْمَسَاكِينِ وَالْعَامِلِينَ عَلَيْهَا وَالْمُؤَلَّفَةِ قُلُوبُهُمْ وَفِي الرِّقَابِ وَالْغَارِمِينَ وَفِي سَبِيلِ اللَّهِ وَابْنِ السَّبِيلِ ۖ فَرِيضَةً مِّنَ اللَّهِ ۗ وَاللَّهُ عَلِيمٌ حَكِيمٌ

“ግዴታ ምጽዋቶች (የሚከፈሉት) ለድኾች፣ ለምስኪኖችም፣ በርሷም ላይ ለሚሠሩ ሠራተኞች፣ ልቦቻቸውም (በእስልምና) ለሚለማመዱት፣ ጫንቃዎችንም (በባርነት ተገዢዎችን) ነጻ በማውጣት፣ በባለ ዕዳዎችም፣ በአላህ መንገድም በሚሠሩ፣ በመንገደኛም ብቻ ነው። ከአላህ የተደነገገች ግዴታ ናት። አላህም ዐዋቂ ጥበበኛ ነው።” (አት-ተውባ 9፤ 60)

እንደ ኢማሙ ማሊክ እና ኢማም ኢብኑ ተይሚያ አመለካከት ደግሞ ዘካቱልፊጥርን ለድሆችና ለሚስኪኖች ብቻ መስጠት ይቻላል።“ለሚስኪኖች ምግብ ናት” የሚለው ነብያዊ ንግግር የዚህን አመለካከት መሠረት አደላድሏልና እኛም ድሆችና ሚስኪኖችን ብቻ ለይቶ መሥጠት ይቻላል ብለን እምናለን።

*ዘካቱልፊጥር የት ይሠጥ?*
በላጩና የተሻለው ዘካን ዘካ አውጪው የኖረበትና የፆመበት ሀገር ላይ መስጠት ነው። ጉዞ ላይ በመሆኑ ረመዳንን ያለ ሀገሩ የፆመ እንደሆነ የፆመበት ቦታ ላይ መስጠት ይገባዋል (እንደ ሻፊዒያና ሐንበሊያ መዝሀብ ዑለሞች አመለካከት)። ይህን አመለካከት የሚመሠርቱት ዘካቱልፊጥር ከፆመኛው አካል ጋር እንጂ ከገንዘቡ ጋር የማይያዝ የዘካ አይነት መሆኑን በማመላከት ነው።
የዒድ ሥርዓትና ድንጋጌዎች
----------❀❀❀❀❀----------

የዒድ አስፈላጊነት
----------❀❀❀❀❀----------

ክፋል1

ዒድ ማለት “ዓውድ” ከሚለው የዓረብኛ ቃል የተያዘ ሲሆን መመላለስ
ማለት ነው። ዒድም በየአመቱ ስለሚመላለስ ይህን ስያሜ አግኝቷል።
የዓረብኛ ቋንቋ ማንኛውንም የደስታ ቀን ዒድ (በዓል) ብሎ ይጠራል። በስድ
ጥቅም ላይ ሲውል ግን ኢስላማዊ ትርጓሜው ሁለቱን የኢስላም በዓላት
ብቻ ይጠቁማል።
የሙስሊሞች በዓላት ሁለቱ ዒዶች -ዒድ አልፊጥር እና ዒድ አልአድሃ-
ናቸው።
ከአነስ (ረ.ዐ) እንደተዘገበው
ﻗَﺪِﻡَ ﺭَﺳُﻮﻝُ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﺻَﻠَّﻰ ﺍﻟﻠَّﻪُ ﻋَﻠَﻴْﻪِ ﻭَﺳَﻠَّﻢَ ﺍﻟْﻤَﺪِﻳﻨَﺔَ ﻭَﻟَﻬُﻢْ ﻳَﻮْﻣَﺎﻥِ ﻳَﻠْﻌَﺒُﻮﻥَ ﻓِﻴﻬِﻤَﺎ
ﻓَﻘَﺎﻝَ ﻣَﺎ ﻫَﺬَﺍﻥِ ﺍﻟْﻴَﻮْﻣَﺎﻥِ ﻗَﺎﻟُﻮﺍ ﻛُﻨَّﺎ ﻧَﻠْﻌَﺐُ ﻓِﻴﻬِﻤَﺎ ﻓِﻲ ﺍﻟْﺠَﺎﻫِﻠِﻴَّﺔِ ﻓَﻘَﺎﻝَ ﺭَﺳُﻮﻝُ ﺍﻟﻠَّﻪِ
ﺻَﻠَّﻰ ﺍﻟﻠَّﻪُ ﻋَﻠَﻴْﻪِ ﻭَﺳَﻠَّﻢَ ﺇِﻥَّ ﺍﻟﻠَّﻪَ ﻗَﺪْ ﺃَﺑْﺪَﻟَﻜُﻢْ ﺑِﻬِﻤَﺎ ﺧَﻴْﺮًﺍ ﻣِﻨْﻬُﻤَﺎ ﻳَﻮْﻡَ ﺍﻟْﺄَﺿْﺤَﻰ
ﻭَﻳَﻮْﻡَ ﺍﻟْﻔِﻄْﺮ
“የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) መዲና ሲገቡ የመዲና ሠዎች
የሚደሰቱባቸው ሁለት በዓላት እንዳሏቸው አወቁ። እርሳቸውም እነዚህ
ሁለቱ ቀናት ምንድናቸው በማለት ጠየቁ። ሰዎችም ከእስልምና በፊት
በጃሂሊያ ጊዜ እንጫወትባቸው የነበሩ በዓላት ናቸው አሏቸው። የአላህ
መልእክተኛም (ሰ.ዐ.ወ) ‘አላህ ከነርሱ የተሻሉ ሁለት ዒዶችን
ሠጥቷችኋል። ዒዱልፊጥር እና ዒድ አልአድሃን።’ አሏቸው።” (አቡ ዳውድ
ዘግበውታል)
ዒዱል-ፊጥር የሸዋል ወር የመጀመሪያው ቀን ላይ የሚከበር የሙስሊሞች
የመጀመሪያው በዓል ነው። ከዚያም ወርሀ ዙልሒጅጃ ላይ ሁለተኛው ዒድ -
ዒዱል-አድሓ- አለ። ዒዱል-ፊጥር ሙስሊሞች ከረመዳን ፆም በኋላ
ለመጀመሪያ ጊዜ የሚያፈጥሩበት ወይም ፆማቸውን የሚገድፉበት ቀን ላይ
የሚውል በዓል ነው። ለዚህ ነው ዒዱል-ፊጥር የሚባለው።
ዒድ ሰዎች ከህይወት ጭንቅና ሀሳብ እረፍት እንዲያደርጉ፣ በሙስሊሞች
መሀል እዝነትንና ፍቅርን ለማስፈን፣ የአላህን ፀጋዎች ለማመስገን…
የታለመ በዓል ነው።
የኢስላም ዒድ ከሌሎች የኃይማኖት በዓላት ይለያል። ኢስላም ውስጥ ዒድ
ግዴታ ከሆኑ አምልኮዎች ጋር ተሳስሯል። የዒድ ደስታ ያን ቀን ከሚፈፀሙ
አምልኮዎች ጋር ይተሳሰራል። ግዴታ የሆነባቸውን ፆም የፆሙ ሰዎች
ፆማቸው ሲጠናቀቅ ሊደሰቱ ይገባል። ምክንያቱም ግዴታ የሆነባቸውን
የአምልኮ ስርዓት ለማጠናቀቅ አላህ ገጥሟቸዋል። ሐጅ ያደረጉ ሠዎች
ሐጃቸውን ሲያጠናቅቁ ሊደሰቱ ይገባል። ምክንያቱም ግዴታ የሆነባቸውን
ሐጅ ፈፅመዋል። ስለዚህ ኢስላም ውስጥ -ዒድ- እንደ የዒባዳ (የአምለኮ)
ምልክት ይታያል። ስለዚህ ከሌሎች በዓላት ይለያል።
ቁርአን በኩራትና በአናኒያ የተወጠረ ደስታን ከልክሏል። የአላህ ፍጡሮች
ላይ የበላይነትን ለማሳየት የሚደረግ ደስታ መግለጫን አውግዟል።
ስለቃሩን በተናገረ ጊዜ አላህ እንዲህ ብሏል፡-
ﺇِﺫْ ﻗَﺎﻝَ ﻟَﻪُ ﻗَﻮْﻣُﻪُ ﻟَﺎ ﺗَﻔْﺮَﺡْۖ ﺇِﻥَّ ﺍﻟﻠَّﻪَ ﻟَﺎ ﻳُﺤِﺐُّ
ﺍﻟْﻔَﺮِﺣِﻴﻦَ
“ወገኖቹ ለእርሱ አትኩራ፤ አላህ ኩራተኞችን አይወድምና ባሉት ጊዜ
(አስታውስ)።” (አል-ቀሰስ 28፤ 76)
እንዲህ አይነቱን ደስታ አላህ አይወደውም። ምክንያቱም በሰውየውና
በማህበረሰቡ መሀል ፍቅር እንዳይኖር ያደርጋል። ጥላቻን ያሰፍናል። በሌላ
ቦታ ላይ ደግሞ አላህ በእዝነቱና በችሮታው እንድንደሰት አዞናል። ከአላህ
እዝነት መገለጫዎችና ከችሮታዎቹ ማሳያዎች መሀል ለታላላቅ የአምልኮ
ሥርዓት መገጠማችን እና እንድንታዘዘው መፍቀዱ ነው።
ዒድ ኢስላም ውስጥ ለደስታ ብቻ አልተደነገገም። የበጎ ስራ ፍላጎቶችን
ለማጎልበትም ጭምር ተወጥኗል እንጂ። በጎ ስራ ከዒድ ውጭ የግል
ልማድ ሊሆን ይችላል። በዒድ ጊዜ ግን የማህበረሰብ ጉዳይ ይሆናል።

ክፋል2 ይቀጥላል ........
⁩✿‏͜͡ ͜͡ ͜͡ ͜͡ ͜͡ ͜͡ ͜͜͜͜͜͡͡͡͡ ͜͡ ͜͜͜͜͡͡͡ ͜͜͜͜͡͡͡ ͜͡ ͜͡ ͜͡ ❀❀ ͜͡ ͜͡ ͜͡ ͜͡ ͜͜͜͜͜͡͡͡ ͜͡ ͜͜͜͡͡ ͜͜͜͜͡͡͡͡ ͜͡ ͜͡ ͜͡ ͜͡ ͜͡ ͜͡ ͜͡✿‏
@eslamic_center
⁩✿‏͜͡ ͜͡ ͜͡ ͜͡ ͜͡ ͜͡ ͜͜͜͜͜͡͡͡͡ ͜͡ ͜͜͜͜͡͡͡ ͜͜͜͜͡͡͡ ͜͡ ͜͡ ͜͡ ❀❀ ͜͡ ͜͡ ͜͡ ͜͡ ͜͜͜͜͜͡͡͡ ͜͡ ͜͜͜͡͡ ͜͜͜͜͡͡͡͡ ͜͡ ͜͡
የዒድ ቀንን እና ዘካተ-ል-ፊጥርን የተመለከቱ ነጥቦች
===================================
#Share_Share_Share
《መልዕክቱ ወቅታዊ ስለሆነ ለሌሎችም ብታሰራጩት መልካም ነው።》
||

①) ብይኑ፦
========
የዒድ ሶላትን መስገድ ልክ እንደ ዋጅብ ጥብቅ ሱን'ና ነው።

②) ወቅቱ፦
========
ጸሐይ ከወጣች የአንድ ስንዝር ከፍታ ወቅት ጀምሮ ጸሐይ ዘንበል እስከምትል ድረስ ነው።
በላጩ ወቅት ግን፤ የዒደ-ል-አዽሓ ሶላት ከሆነ በአል-አዽሓ ወቅት መጀመሪያ ላይ ይሰገዳል፤ ሰዎች ለኡዹሕያ እርድ እንዲመቻቸው!
የዒደ-ል-ፊጥር ሶላት ከሆነ ደግሞ ቢዘገይ ይመረጣል፤ ሰዎች ዘካተ-ል-ፊጥርን ለማውጣት እንዲመቻቸው!
ነቢዩ (ሶለል'ሏሁ ዐለይሂ ወሰል'ለም) የዒደ-ል-ፊጥርን ሶላት ጸሐይ ሁለት ስንዝሮችን ያክል ከፍ ስትል ይሰግዱ ነበር፤ የዒደ-ል-አዽሓን ሶላት ደግሞ ጸሐይ አንድ ስንዝር ያክል ከፍ ስትል ይሰግዱ ነበር።
[ዙበይድ "ኢቲሓፉ ሳደቱ-ል-ሙተቂን: 3/392" ላይ አስፍረውታል።
ሓፊዝ ኢብኑ ሐጀር በ"አል-ተልኺስ" ላይ፣ ሸውካኒ በ"ኒይለ-ል-አውጧር" ላይ ዘግበውታል።]

③) በዕለቱ የሚያስፈልጉ አደቦች፦
======================
1) መታጠብ፣ ሽቶ መቀባት፣ ያገኙትን ውድና አዲስ ልብስ መልበስ።
[ሓኪም: 4/230፣ በዳኢዑ-ል-መነን: 484]
*
2) ወደ ሶላት ከመሄድ በፊት መመገብ። በተምር ማፍጠር! የተምሮቹ ቁጥር ኢ–ተጋማሽ ቢሆንና ከሦስት ተምሮች ባያንስ ይመረጣል። ተምሮቹን ነጣጥሎ መመገብም መልካም ነው። ተምር ከሌለ በሌላ በተገኘ ምግብ ማፍጠር ይወደዳል።
[ቲርሚዚይና ኢብኑል ቂጧን]
*
3) የዒድ ሌሊት ጀምሮ ተክቢራ ማለት።
√ ዒደ-ል-ፊጥር ከሆነ ኢማሙ ወደ ሶላት እስኪወጣ ድረስ ይቆያል።
ዒደ-ል-አዽሓ ከሆነ ደግሞ እስከ አያመ-ተሽሪቅ መጨረሻ ድረስ ይቆያል።
የተክቢራ ቃሉ «አላሁ አክበር፣ አላሁ አክበር፤ ላ ኢላሃ ኢለ-ል'ሏህ– አላሁ አክበር፣ አላሁ አክበር፤ ወሊላሂ-ል-ሐምድ!» የሚለው ነው።

*
4) ወደ መስገጃ ቦታ ሲወጡ በአንድ መንገድ መሄድና ሲመለሱ በሌላ መንገድ መመለስ።
[ቡኻሪይ: 2/29፣ አቡ ዳውድም ኢብኑ ዑመርን ጠቅሰው ተመሳሳይ መልዕክት አስተላልፈዋል።]
*
5) ዝናብና መሰል አስቸጋሪ ነገሮች ከሌሉ ሜዳ ላይ መስገድ።
*
6) የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት መለዋወጥ!
ይሄውም አንዱ ከሌላው ጋር ሲገናኝ «ተቀበለ-ል'ሏሁ ሚና ወሚንኩም» መባባል!
[በይሀቂይ በ"ሱነኑ-ል-ኩብራ: 3/319"፣ ኢብኑ ሐጀር በ"ፈትሑ-ል-ባሪ: 3/422" ላይ አስፍረውታል።]
*
7) ሰፋ ያለ ምግብ፣ መጠጥና የተፈቀደ ቀልድና ጫዎታ ይቻላል።
ኢ–ሸሪዓዊ የሆነ ቀልድና ጭፈራ ግን በጥብቅ የተከለከለ ነው።
[አሕመድ: 3/460፣ ዐብዱ-ር-ረዛቅ በሙስነፉ: 15566፣ ፈትሑ-ል-ባሪ: 3/422፣ ቡኻሪይ: 2/21]

④) የአሰጋገድ ሁኔታ፦
===============
ሰዎች ወደ መስገጃ ቦታቸው ተክቢራ እያሉ ይወጣሉ።
ጸሐይ የተወሰኑ ሜትሮችን ከፍ ስትል ኢማሙ ሊያሰግድ ይነሳል።
አዛንም ሆነ ኢቃመህ የለም።
[ቡኻሪይና አቡ ዳውድ ዘግበውታል።]
የሚሰገደው ሁለት ረከዓዎች ብቻ ነው።
√ በመጀመሪያው ረከዓ ላይ ተክቢረተ-ል-ኢሕራምን ጨምሮ ሰባት ጊዜ «አላሁ አክበር» ይባላል።
√ በሁለተኛው ረከዓ ላይ ከሱጁድ ሲነሱ ከሚደረገው ተክቢራ ውጭ አምስት ጊዜ «አላሁ አክበር» ይባላል።
[ቡኻሪይና አቡ ዳውድ ዘግበውታል።]
*
መጀመሪያ ኢማሙ «አላሁ አክበር» ሲል ተከታዮቹም ተከትለው ይላሉ።
ኢማሙ በመጀመሪያው ረከዓህ ከፋቲሓ ቀጥሎ «ቃፍ»ን ይቀራል። በሁለተኛው ረከዓህ ደግሞ «አል-ቀመር»ን ይቀራል።
ወይም በመጀመሪያው ረከዓህ «አል-አዕላ»ን፣ በሁለተኛው ረከዓህ ደግሞ «አል-ጛሺያህ»ን ወይም «አሽ-ሸምስ»ን ይቀራል።
[ሙስሊም]
የሚቀራው ድምፅ በማውጣት «ጀህር» ነው።
ኢማሙ ሶላቱን ካጠናቀቀ በኋላ ለኹጥባ (ሰዎችን ለመምከር) ይነሳል።
የዒደ-ል-ፊጥር ሶላት ከሆነ ስለ ዘካተ-ል-ፊጥርና ህግጋቷ ትኩረት አድርጎ ይመክራል። የዒደ-ል-አዽሓ ሶላት ከሆነ ደግሞ ስለ ኡዹሕያና ብይኑ ይበልጥ አተኩሮ ይመክራል።
በኹጥባው መሀል አልፎ አልፎ ተክቢራ ይላል።
[ቡኻሪይና ሙስሊም]
*
ከዒድ ሶላት በፊትም ሆነ በኋላ የሚሰገድ ሶላት የለም።
[ሰባቱ የሐዲሥ ሊቃውንት ዘግበውታል።]
ወደ ቤታቸው ሲመለሱ ግን ሁለት ረከዓዎችን ነቢዩ ይሰግዱ ነበር።
[ኢብኑ ማጃህ ሶሒሕ ብለውታል።]
*
የዒድ ሶላት ያመለጠው ሰው ግን አራት ረከዓህ አድርጎ ይሰግዳል።
ተሸሁድ እንኳ ቢሆን ከኢማሙ አንዳች ነገር ያገኘ ሰው ግን፤ ሁለት ረከዓህ ነው የሚሰግደው።
በዒድ ቀን መጾም አይቻልም፤ በጥብቅ የተከለከለ ነው። በስህተት የጾመ ሰው ግን ወንጀል የለበትም።
የዒድ ሶላት ቀኑን ባለማዎቅ ስላለፈ ውድቅ አይደረግም። በቀጣዩ ቀን መከናወን ይችላል።
ልጃ ገረዶችና የወር አበባ ላይ ያሉ እንስቶችም ጭምር ይወጣሉ። ሶላት ባይሰግዱም ዳር ላይ ድባቡን እያዩና እየተደሰቱ የሚተላለፈውን መልዕክት እያዳመጡ ይቀመጣሉ።
[ቡኻሪይና ሙስሊም]
ወደ ሶላት ሲወጡ በእግር መጓዝ ሱንና ነው።
[ቲርሚዚይ]
*
ዘካተ-ልፊጥር (ሶደቀተ-ል-ፊጥር) የሚሰጠው የዒድ ሶላት ከመሰገዱ በፊት ነው። ይህ በላጩና ለተፈለገበት አላማ እንዲውል የሚያደርግም ነው። በሁሉም የረመዳን ቀናት ማውጣት ይቻላል።
√ የሚወጣውም በአንድ ሰው አንድ ቁና (አራት እፍኞች) ወይም ከ2.5 እስከ 3 ኪሎ ግራም ነው። አንዳንዶች ደግሞ አንድ ቁና (ሷዕ) 2.156 ኪሎ ግራም ነው ብለዋል።
√ የእህሉ አይነት ከተምር፣ ከገብስ፣ ከስንዴ፣ ከዘቢብ፣ ከእርጎና መሰል የአካባቢው ማኅበረሰብ በብዛት ከሚመገበው የምግብ አይነት ይሆናል።
√ በሴትም በወንድም፣ በትንሽም በትልቅም፣ በባሪያም በጨዋም ላይ ግድ ነው።
የአንድ ቀን ቀለቡን ችሎ የሚተርፈው ያለው ሰው መጠኑ እንኳ ባይሞላ ያንኑ ማውጣት አለበት።
የሚሰጠው ለሚስኪኖች ነው። አላማውም የጾመኛን ጾም መጠገንና በዚህ በዒድ ቀን ድሆችን ከልመናና እንግልት ማብቃቃት ነው።
√ በጥሬ ገንዘብ ማውጣት ይቻላል።
ሙዓዝ ኢብኑ ጀበል፣ ዑመር ኢብኑ ዐብደ-ል-ዓዚዝ፣ አቡ ሐኒፋ፣ ማሊክ፣ ቡኻሪይ፣ ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚይ'ያህ እና ሌሎችም ይህን ሃሳብ ይደግፋሉ።
ሻፊዒይና አሕመድ እንዲሁም ከዘመናችን ዑለማዎች ውስጥ ኢብኑ ዑሠይሚንና ሌሎችም ግን ይቃወማሉ።
ከኺላፍ ለመውጣት ይህን መተግበሩ የተሻለ ነው።
አላሁ አዕለም።
[ዝርዝር ሃሳቦችን «ነሳኢይ: 5/48፣ አቡ ዳውድ: 1609፣ ሱነኑል ኩብራ: 4/175፣ ቡኻሪይ: 73 እና 76 ፥ ኪታቡ ዘካህ ላይ፣ ሙስሊም: 17 እና 19 ፥ ኪታቡ ዘካህ ላይ እና ሌሎችም ድርሳናት ላይ መመልከት ይቻላል።]

《መልዕክቱ ወቅታዊ ስለሆነ ለሌሎችም ብታሰራጩት መልካም ነው።》

ማሳሰቢያ፦
========
በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት፤ የዘንድሮው የዒደ-ል-ፊጥር ሶላት በቤተ ውስጥ ነው የሚሰገደው።
=========
ረመዳን 30, 1441 ዓ.ሂ
ግንቦት 15, 2012 E.C
May 23, 2020 G.C
||
የቴሌግራም ቻነሌን በመቀላቀል በቀላሉ የምለቃቸውን መረጃዎች ማግኘት ትችላላችሁ።
Join:
www.tg-me.com/eslamic_center
ዒድ ሙባረክ
==========
ለመላው ሙስሊሞች «ዒደኩም ሙባረክ»።
እንኳን ለ1441 ዓ.ሂ የዒደ-ል-ፊጥር በዓል በሰላም አደረሰን።

አላህ መልካም ሥራቸውን ከተቀበላቸው ባሮቹ ያድርገን።
የመጣብንን በላእ ያንሳልን።

«ተቀለል'ሏሁ ሚን'ና ወሚንኩም»

ዒዳችን የሰላምና የጤና እንዲሆንልን ተመኘሁ።
የወደፊት ዘመናችን የሰላምና የእድገት፣ የዲልና የጽድቅ ይሁንልን።

=========
www.tg-me.com/eslamic_center
☞ አምስት ጥቆማዎች፤ የሸዋልን ፆም ለጀመሩ እህቶች

الحمد لله والصلاة والسلام على رسول الله وعلى آله وصحبه، أما بعـد:

ከሸዋል ፆም ጋር በተያያዘ ብዙ እህቶች ከሚጠይቋቸው ጥያቄዎች በመነሳት አምስት ጥቆማዎች ይኖሩኛል፤

1) ቀዳ ያለባት ሴት ከቀዳና ከሸዋል ሱና የትኛውን ታስቀድም?

☞ በሀይድ ወይም በወሊድ ደም ምክኒያት ረመዳንን አሟልታ ያልፆመች ሴት፤ ከሸዋል ስድስት ቀናት መፆምን አስመለክቶ በሀዲስ የተጠቀሰውን የአንድ አመት ፆም ምንዳ ለማግኘት አጅሩን እንደሚያገኝ ቃል የተገባለት ረመዳንን ካሟላ በኋላ የፆመው ሰው ስለሆነ፤ ቅድሚያ ረመዳንን መፆም ግድ ስለሚል በተቻላት መጠን ከሸዋል ሱና በፊት የረመዳንን ቀዷ ለማጠናቀቅ መሞከር ይኖርባታል።

📚 የሳውዲ ቋሚ የፈትዋ ኮሚቴ ይህንን በማስመልከት እንዲህ ብሏል፤ ¹ «ከረመዳን የተወሰኑ ቀናት ያሉበት ሰው በቅድሚያ እነሱን ሊፆምና ከዛ በኃላ ከሸዋል ወር ስድስት ቀናትን ሊፆም ይገባል፤ ምክኒያቱም ረመዳንን አስከትሎ ከሸዋል ስድስት ቀን ሊፆም የሚችለው ረመዳንን አሟልቶ ከፆመ ነው።» ፈታወለጅናህ 10/392

ይህንን መተግበር ሴቶች ያለባችውን ቀዷ በጊዜ መክፈል ይችሉ ዘንድ ያበረታቸዋል።

2) የረመዳንን ወር በሙሉ ካልፆመችስ?

📚 ሸይኽ ኡሰይሚን እንደገለፁት²
በወሊድ ወይም በተለያዩ በሽታዎች ምክኒያት ረመዳንን ሙሉዉን መፆም ያልቻለች ሴት ሸዋልን ቀዳ በማውጣት ከጨረሰችና ስድስቱን የሱና ቀናት መፆም የምትችልበት ጊዜ ሸዋል ውስጥ ካላገኘች የዘገየችው ከአቅም በላይ በሆነ ምክኒያት (ደሩራ) ስለሆነ ቀጣዩ የዙልቂእዳ ወር ከገባ በኃላም ቢሆን በሸዋል ሱና ነይታ ፆሟን ብታሟላው ኢን ሻ አላህ አጅሩን ታገኛለች። ይህንን መልእክት ያዘለውን የሸይኽ ኡሰይሚን ፈትዋ በመጅሙኡል ፈታዋ 20/19 ያገኙታል

3) ቀዳና የሸዋል ሱናን በአንድ ኒያ መፆም፦

📚 ሸይኽ ኢብኑ ባዝ ረሂመሁላህ (ኑሩን አለደርብ)² የጥያቄና መልስ ፕሮግራም ላይ ተጠይቀው ሲያብራሩ እንዲህ ብለዋል፤ «የስድስቱን ቀናት ፆም ከፈለገች በቅድሚያ ቀዳ አውጥታ በመቀጠል ሱናውን ፆም ትፁም። በሸዋል ወር ቀዳ አውጥታ ስድስቱን ቀናትም ከፆመች ትልቅ ኸይር ነው። የስድስቱን የሸዋል ቀናት ፆም ከቀዳ ጋር በአንድ ኒያ ብትፆም ግን የስድስቱን ቀናት አጅር ታገኛለች ብዬ አላስብም። የሸዋል ፆም የሚፆመው በተገደበ ጊዜ ሲሆን እራሱን የቻለ ኒያ ይፈልጋል።»

ስለዚህም ሁለቱን በአንድ ላይ መፆም ሳይሆን ቅድሚያ ረመዳንን አሟልቶ ሱናውን ፆም መጀመር ተገቢ ነው።

4) የሸዋል ወር ሳያልቅ የመጀመሪያዎቹ ስድስት ቀናት ቢያልፉስ?

☞ ብዙ ሴቶች የሸዋል ፆም የሚባለው ወሩ እንደገባ ያሉት ስድስት ቀናት ብቻ ይመስሏቸዋል። ይህ ስህተት ነው። በሀዲሱ የተጠቀሰው ምንዳ ከሸዋል ወር ስድስት ቀናት የፆመን ሰው ሁሉ ይመለከታል። ይህ ደግሞ መጀመሪያም መጨረሻም በመካከልም ሊሆን ይችላል።

5) የሸዋልን ፆም አከታትሎ መፆም፦
☞ ሸዋል እንደገባ ብዙ ሰዎች አከታትለው በመፆም ይጨርሳሉ። ይህም ስንፍናን ለማስወገድና በረመዳን ያካበቱትን የመፆም ብቃት ላለማጣት ከማሰብ ነው። ነገር ግን በተቃራኒው ሰኞና ሀሙስ እንዲሁም አያመልቢድ በመፆም ሱና ፆም የመፆምን ልምድ ማዳበርም መልካም ነው። አንዳንድ ሴቶች አከታትለው መፆማቸው ግዴታ ስለሚመስላቸው ከመፆም ይሳነፋሉ። ይህ ሊታረም የሚገባው ግንዛቤ ነው።

አላህ ፆማችንን ይቀበለን ዘንድ እማፀነዋለሁ!

አቡጁነይድ ሸዋል 4/10/1436

————// ————
¹ (...والذي ينبغي لمن كان علي شيء من أيام رمضان أن يصومها أولا ثم يصوم ستة أيام من شوال ؛ لأنه لا يتحقق له اتباع صيام رمضان لست من شوال إلا إذا كان قد أكمل صيامه . وبالله التوفيق وصلى الله على نبينا محمد وآله وصحبه وسلم ) فتاوى الجنة الدائمة 10/392

² سئل الشيخ ابن عثيمين رحمه الله تعالى عما إذا كان على المرأة دين من رمضان فهل يجوز أن تقدم الست على الدين أم الدين على الست ؟
فأجاب بقوله : "إذا كان على المرأة قضاء من رمضان فإنها لا تصوم الستة أيام من شوال إلا بعد القضاء ، ذلك لأن النبي صلى الله عليه وسلم يقول : ( من صام رمضان ثم أتبعه ستا من شوال ) ومن عليها قضاء من رمضان لم تكن صامت رمضان فلا يحصل لها ثواب الأيام الست إلا بعد أن تنتهي من القضاء ، فلو فرض أن القضاء استوعب جميع شوال ، مثل أن تكون امرأة نفساء ولم تصم يوما من رمضان ، ثم شرعت في قضاء الصوم في شوال ولم تنته إلا بعد دخول شهر ذي القعدة فإنها تصوم الأيام الستة ، ويكون لها أجر من صامها في شوال ، لأن تأخيرها هنا للضرورة وهو ( أي صيامها للست في شوال) متعذر، فصار لها الأجر" انتهى مجموع الفتاوى 20/19

³ سئل الشيخ ابن باز رحمه الله
هل يجوز للمرأة الجمع بين صيام ستة أيام من شوال وقضاء ما عليها من رمضان في هذه الأيام الستة بنية القضاء والأجر معاً، أم لا بد من القضاء أولاً ثم صيام ستة أيام من شوال؟
نعم، تبدأ بالقضاء، ثم تصوم الست إذا أرادت، الست نافلة، فإذا قضت في شوال ما عليها ثم صامت الست من شوال فهذا خير عظيم، وأما أن تصوم الست بنية القضاء والست فلا يظهر لنا أنه يحصل لها بذلك أجر الست، الست تحتاج إلى نية خاصة في أيام مخصوصة.

https://www.tg-me.com/eslamic_center
"በአላህ" ይህን ፅሑፍ አንብበህ / አንብበሽ ሼር ሳታደርግ / ሳታደርጊ እንዳታልፍ / እንዳታልፊ !!

Part ➊

ነፍስ ያለው ነገር ሁሉ የሙታንን መንደር ተቀላቅሎ አለም በሚያስፈራ ሁኔታ በጭርታ ተውጣለች።

ፍጥረተ አለሙ ባዶ ሁኗል...።መላዕክት....፣
ሰዎች...፣ጂኖች...፣እንስሳዎች...ሁሉም ሙተው አላህ ብቻውን ቀርቷል።

ያ ቀን የአላህ ቁጣው እጅጉን አይሏል...።ያ ቀን
ለተፀፃቾች በሩ የሚዘጋበት ቀን ነው...።ያ ቀን ሚስጥሮች ሁሉ ይፋ የሚወጡበት ቀን ነው...።

አዎ!!! ያ ቀን መላዕክት በፍርሃት የሚንበረከኩበት ቀን ነው....ያ ቀን የውመል ቂያማ ነው።

ፍጥረተ አለም በደረቅ ጭርታ ተውጦ ሳለ አላህ ኢስራፊል የተባለውን መልዓክ በመቀስቀስ የመሰብሰብያ ጡሩንባውን እንዲነፋ ያዘዋል።

መልዓኩም ለትዕዛዙ እጅ በመንሳት ለእለቱ የተዘጋጀውን ጡሩንባ በከፍተኛ የድምፅ ሀይል ሲነፋ ነፍስ ያለው ነገር ሁሉ ከሙታን መንደር መትመም ይጀምራሉ።

ሰዎች...፣ጂኖች...፣መላዕክት...እንስሳት እና ሌሎችም ፍጥረታት የጡሩንባውን ድምፅ ሲሰሙ ሁሉም በያሉበት ይባንናሉ።

የሰው ልጆችም በዚህ አስፈሪ ድምፅ በመበርገግ ከአደም ጀምሮ እስከ መጨረሻው ትውልድ ያለው ሁሉ ከሰውነቱ አፈር እያራገፈ ከቀብሩ መነሳት ይጀምራል።

ሁሉም እርቃኑን ነው...። ጫማ የለም...፣ልብስ
የለም...፣ሁሉም አልተገረዘም ልክ እንደተወለደ ሆኖ ከቀብሩ እየወጣ መሰብሰብ ይጀምራል።

ትዕይንቱ እጅጉን ያስፈራል...፣ሰዎች በከፍተኛ ግራ መጋባት ውስጥ ናቸው...፣ሁሉም ደንግጧል...፣ለዘላለም ከተጋደመበት ለምን እንደተቀሰቀሰ አያውቅም...፣ድንጋጤው ይሄን ለማስተንተን ፋታ አይሰጥም።

ሁኔታው ለሁም ያስደነግጣል...፣ማንም ስለማንም ማሰብም ሆነ መጨነቅ አይፈልግም ሁሉም እራሱን ማዳን ነው ሚፈልገው...።

በዚህ ሁኔታ ሁሉም ፍጥረታት ከሞታቸው ከተቀሰቀሱ በኋላ ወደ አረዱል መህሸር (የመሰብሰቢያይቱ ምድር) ሁሉም ይተማል።

ያች ምድር እኛ ምናውቃት ምድር አይደለችም። ያች ምድር ለሂሳብ ብቻ የተፈጠረች ምድር ናት...።

ምንም አይነት ወንጀል በላይዋ አልተፈፀመባትም...፣ዚና አልተሰራባትም...፣ደም አልፈሰሰባትም...በቃ ንፁህ ምድር
ናት።

ፍጥረታት ወዴት መሄድ እንዳለባቸው እና ወዴት እየሄዱ እንደሆነ ሳያውቁ ብቻ ወደዚያች ምድር በጅምላ ይነዳሉ...።

ከፊሉ ሰው እየጋለበ ወደዚያች ምድር ያቀናል። ሌላው በፍጥነት እየተራመደ ይሄዳል...፣ የተቀሩትም በፊቶቻቸው እየተንከባለሉ በግዳቸው ይሄዷታል። ብቻ ሁሉም እንደየስራው ጥራት የአካሄዱም ሁኔታ ይለያያል።

ያን ቀን ማንም ማንንም ሊያናግር አይችልም...፤ብቻ ሁሉም ከራሱ ጋር ያወራል <ይህች ምድር እኛ ምናውቃት ናት ወይስ ሌላ ናት...!!! አይ እሷ እንኳን አይደለችም።

እሷ ብትሆንማ የታሉ ወንዞቿ...?! የታሉ ጋራ ሸንተረሯ...?! የታሉ ሸለቆዎቿ...?!> በማለት እያሰላሰሉ ወደ መሰብሰብያው ያቀናሉ።

ሁሉም በማያውቋት ምድር ላይ ሁነው ዙሪያቸውን በመመልከት በፍራቻ እና በግርምት መሃል ሲዋልሉ ድንገት ከወደ ላይ በኩል በሚያስፈራ ሁኔታ ሰማዩ ይሰነጠቃል።

ሁሉም ድንብርብሩ ይወጣል...፣የሰማዩ መሰንጠቅ ያስከተለው ከፍተኛ እና እስፈሪ ድምፅ ሁሉንም ወደ ላይ ቀና ብለው እንዲመለከቱ ያስገድዳቸዋል።

አሁን የሁሉም አይን ተሰንጣቂው ሰማይ ላይ ፈጧል...፤ ሰማዩ እየተሰነጣጠቀ መላዕክቱን እየተሸከመ ይወርዳል...።

ይህ ሁኔታ ለሰው ልጆች ጉልበት አብረክራኪ ፍርሃትን ይፈጥርባቸዋል።በዚህም በመደናገጥ ሰዎች ለመላዕክት፦"እናንተ መሃል ጌታችን አለ እንዴ..!?" በማለት ይጠይቃሉ።

መላዕክቱም በመንቀጥቀጥ፦"ጌታችን ጥራት
ይገባው...!!! እኛ መሃል የለም። ነገር ግን ይመጣል" ይላሉ።.......

ቀጣዩን ክፍል ለማንበብ👇

۩○◙◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩
Join እና ሼር በማድረግ ኢስላማዊ ዕውቀትን ያሰራጩ Click and Join ➤➤ http://www.tg-me.com/eslamic_center
"እንደተለመደው ሼር ማድረጉ እንዳይረሳ እሺ ውዶች" part ➌ 03 : 00 ሰዓት ላይ ይዘንላችሁ እንቀርባለን! መልካም ንባብ!

Part ➋

መላዕክቱም በመንቀጥቀጥ፦"ጌታችን ጥራት
ይገባው...!!! እኛ መሃል የለም። ነገር ግን ይመጣል" ይላሉ።

በዚህ መሃል ሰዎች በዝምታ እና በድንጋጤ ተውጠው ሳለ የዐረሽ ተሸካሚ መላዕክት የፍጥረተ አለሙን ጭርታ በተስቢህ እና በታህሊል(በዚክር) እያደመቁ መውረድ
ይጀምራሉ።

ሁሉም መላዕክት በሰልፍ ሁነው ቦታ ቦታቸውን ከያዙ በኋላ አላህ በፈለገበት ዙፋኑን ያስቀምጣል።ከዚያም ከነ ንግስናው እና ከነ ልቅናው ወደ ፍርዱ ቦታ ይወርዳል።

ያን ግዜ ሁሉም በፍርሃት ይዋጣል መላዕክት...፣ሰዎች... ፣ጂኖች...ሁሉም ፍርሃት ድንበሩን ያልፍባቸዋል...ማንም ምንም አይተነፍስም አካባቢው ምንም እንኳን በብዙ ፍጥረታት ቢሞላም አላህ ሲወርድ ጭርርር ይላል።

ከዚያም አላህ፦"እናንተ የሰው ልጆች እና ጅኖች ሆይ!!! ከተፈጠራችሁበት እለት አንስቶ እስከዚህች ቀን ድረስ እኔ እናንተን ሳዳምጥ እና ስራዎቻችሁንም ስመለከት ቆይቻለሁ...።

ዛሬ እኔን በፅሞና አድምጡኝ። እነሆ የስራችሁ ውጤት የተመዘገበበት መዝገብ በያንዳንዳችሁ ላይ ይነበብላችኋል...።

በዚያ መዝገብ መልካም ነገርን ያገኘ አላህን ያመስግን...፤ ነገር ግን መጥፎ ነገርን ያገኘ ነፍሱን እንጂ ሌላ ማንንም መውቀስ አይችልም" በማለት የስብስቡን መክፈቻ ተናግሮ ፍጥረቱን በፍርሃት ይውጣል።

ይሄን ሲሰሙ ሁሉም ይደነግጣሉ...፣በድንጋጤ እንባ ከምንጩ ይደርቃል...፣ ሰዉ ሁሉ ልክ እንደ ሰካራም ይዋልላል...። የአላህ ቁጣ ያሸበራቸው መላዕክትም ሰልፋቸውን ይዘው ሚሆነውን በፍራቻ ይጠባበቃሉ።

መላዕክቱ የሰው ልጆችን ዙሪያ በመክበብ መሄጃ መምለጫ ያሳጣሉ...።

ፀሀይ ከሁሉም ሰው ጭንቅላት በስንዝር ርቀት ላይ ትገኛለች...ቃጠሎዋ,አይሏል...የፀሀይዋ ንዳድ ብዛት ሰው አናቱ እንደፈላ ውሀ ይንተከተክ ጀምሯል...ሰው የገዛ ላቡ እንደ ወንዝ ያሰምጠው ይዞታል...፣ ግማሹ እስከ ቁርጭምጭሚቱ...፣ከፊሉ እስከ ጉልበቱ...፣ ከፊሉ እስከወገቡ...፣ ሌላው እስከ አንገቱ.....ብቻ አከባቢው በሰዎች ላብ አስፈሪ ማዕበልን ፈጥሯል።

ምንም ጥላ ሚባል ነገር የለም...ቦታው እልልልም ያለ በረሀ እና ለጥ ያለ ሜዳ ነው...። ሰው በዚህ አንተክታኪ የፀሃይ ንዳድ ውስጥ ሳለ ከወደ አላህ በኩል አንድ ጥሪ ይመጣል...።

ያን ጥሪ ረሱል የኔ ጣፋጭ (ሰዐወ) ሲገልፁት ያምርባቸዋል'ና አንድ አፍታ ከሳቸው ጋር ልተዋችሁ፦" ጥላ ሚባል ነገር በማይኖርበት ቀን አላህ 7 ሰዎችን በራሱ ጥላ ስር ያስጠልላቸዋል።

1፦ፍትሃዊ መሪ (ሁሉም በየዘርፉ መሪ ነው)
2፦አላህን በማምለክ ያደገ ወጣት
3፦ዘውትር በመስጅዶች ላይ ልቡ የተንጠለጠለ ሰው
4፦ሁለት ለአላህ ብለው የተዋደዱ እና(ከተለያዩም) ለሱ ብለው የሚለያዩ ሰዎች
5፦ባለ ፀጋ እና ቆንጆ ሴት ለሀራም ስትጠራው አላህን እፈራለሁ ያለ ሰው
6፦በቀኙ ሲመፀውት ከግራው የሚደብቅ(ሙክሊስ)
7፦ብቻውን አላህን አስታውሶ የሚያለቅስ ሰው" ያን ቀን እኚህ 7 አይነት ሰዎች ከዚያ ሀሩር ይድናሉ።

(እስቲ አንድ ግዜ ወደላይ ከፍ በሉ'ና ሰባቱንም አይነት ሰዎች ዳግም አንብቧቸው። ከዚያ ከሰባቱ በአንዱ እንኳን መኖር አለመኖራችሁን ቼክ አድርጉ።)

በዚህ ሁኔታ ነው እንግዲህ አላህ፦"ለኔ ልቅና ብለው የተዋደዱ የታሉ...?! ዛሬ ጥላ በሌለበት ቀን ጥላዬ ስር አስጠልላቸዋለሁ" ብሎ ከፍጥረታት መካከል የሚጣራው።

(በዚያ ቀን ምስካሪዎቼ ሁኑ እኔም ለአላህ ብዬ ሁላችሁንም እወዳችኋለሁ።) አሁን ሁሉም ቦታ ቦታውን ይዟል...።

ጥላ ቃል የተገባለትም ከንዳዱ ተርፎ በአርሽ ጥላ ስር ተጠልሏል...፤ሌላው የፀሀይቱን እማይቻል ሀሩር በፀጋ ተቀብሎ አናቱን እያንተከተከ ትርምሱ መላ ቅጡን አሳጥቶታል...፤ ሁሉም ሂሳብ ሚደረግበትን ሰዐት እየተጠባበቀ ነው።

በዚህ ሁኔታ ነው እንግዲህ 50,000(ሀምሳ ሺህ) አመት ህዝቡ የሚተራመሰው። (እስቲ ከንባቡ ቆም ብላችሁ 50,000 አመትን በምናባችሁ ከዚያ ሁሉ ትርምስ ጋር ሳሉት።
.
.
.
.
.
.
.
.
.
አይከብድም??? ያ ረበል ዒዛ!!!)

ህዝቡ እያለቀሰ...፣እየጮኸ እና እየተተራመሰ ይህ 50,000 አመት ተጠናቅቆ ካለቀ በኀላ ሰው መላ ፍለጋ እሪይ ማለት ይጀምራል።

በመጨረሻም አንድ ውሳኔ ላይ በመድረስ ሰው ሁሉ አባታቸው አደም ዘንድ በመሄድ ሂሳብ እንዲጀመር እና ከዚህ መከራ......

ይቀጥላል...

የቤተሰባችን አባል ለመሆን ከፈለጉ እና ይሄን ትእይንት እስከ መጨረሻው ክፍል ድረስ ለመከታተል ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን መቀላቀል ይችላሉ👇

http://www.tg-me.com/eslamic_center
እንደተለመደው ይችንም ሼር በማድረግ ማንበብ ለሚፈልጉ እህት ወንድሞቻችን በተን በተን እናድርግላቸው!! ሼር አደራረጋችው ታይቶ "ክፍል" ➍ ይቀጥላል

part ➌

በመጨረሻም አንድ ውሳኔ ላይ በመድረስ ሰዉ ሁሉ አባታቸው አደም ዘንድ በመሄድ ሂሳብ እንዲጀመር እና ከዚህ መከራ ይገላገሉ ዘንድ አላህን እንዲያማልድ እንዲህ በማለት ይጠይቁታል

፦"አደም ሆይ! አንተ የሰው ልጆች ሁሉ አባት ነህ...፣አላህም በእጁ ነው የፈጠረህ...፣ ከራሱ መንፈስም ነው ባንተ የነፋብህ...፣ከዚያም መላዕክትን ላንተ ክብር እንዲያጎበድዱ አዞልሃል።

ታዲያ አትመለከትም እንዴ የደረሰብንን መከራ እና እንግልት!!! እባክህ ጌታህ ዘንድ በመሄድ አማልደን ሂሳብ ያድርግልን'ና ይገላግለን" ይህን ግዜ አደምም፦"ጌታዬ ከዚህ በፊት ተቆጥቶ የማያውቀውን'ና ካሁን በኋላም የማይቆጣውን አይነት ቁጣ ዛሬ ተቆጥቷል።

ከዚህ በፊት እኔም የከለከለኝን በለስ በልቼ አስቆጥቼዋለሁ'ና ላማልዳችሁ አልችልም። ይልቁኑ ሌላ ሰው ጋር ሂዱ...ኑህ ጋ ሂዱ ነፍሴ ነፍሴ..." በማለት ለራሱ መውጫ ቀዳዳ እንዳጣ ይነግራቸዋል።

ከዚያም ህዝቡ ባጠቃላይ ወደ ኑህ ይተም'ማል ለኑህም፦" ኑህ ሆይ!!! አንተ የመጀመሪያው ረሱል ነህ...።አላህም አመስጋኝ ባሪያ ብሎህ ሰይሞሀል...።

ታዲያ አትመለከትም እንዴ የደረሰብንን መከራ እና እንግልት!!! እባክህ ጌታህ ዘንድ በመሄድ አማልደን ሂሳብ ያድርግልን'ና ይገላግለን" ይሉታል።

ኑህም ዐሰ፦ ጌታዬ ከዚህ በፊት ተቆጥቶ የማያውቀውን'ና ካሁን በኋላም የማይቆጣውን አይነት ቁጣ ዛሬ.ተቆጥቷል።

እነሆ እኔ አንድ ሙስተጃብ ዱዓእ ነበረችኝ በሷም ህዝቤ ላይ ዱዓእ አድርጌ አስጠፍቼያቸዋለሁ።ወደ ኢብራሂም ዐሰ ሂዱ ነፍሴ...ነፍሴ....!!!" ብሎ ይሰናበታቸዋል።

አሁንም ወደ ኢብራሂም ዐሰ ይሄዱ'ና፦"አንተ የአላህ ነብይ አንተ በምድር የአላህ ውድ ሆይ!!! ታዲያ አትመለከትም እንዴ የደረሰብንን መከራ እና እንግልት!!!

እባክህ ጌታህ ዘንድ በመሄድ አማልደን ሂሳብ ያድርግልን'ና ይገላግለን" ይሉታል።

ኢብራሂምም ዐሰ፦" ጌታዬ ከዚህ በፊት ተቆጥቶ የማያውቀውን'ና ካሁን በኋላም የማይቆጣውን አይነት ቁጣ ዛሬ ተቆጥቷል።

እኔም በህይወቴ አንዲት ውሸት ዋሽቻለሁ'ና....ነፍሴ....ነፍሴ...!!! ወደ ሙሳ ዐሰ ሂዱ" ይላቸዋል።

የፀሃዩ ሀሩር ያቀለጠው...፣መሄጃ የጠፋበት'ና እንግልት ያጎሳቆለው ህዝብም ሂድ ወደተባለበት በመሄድ አሁን ሙሳ ዐሰ ጋ ደርሷል።

ሙሳን ዐሰ ሲያገኙትም፦"ሙሳ ሆይ!!! አንተ የአላህ መልዕክተኛ ነህ። አላህም አንተን በማነጋገር ልዩ አድርጎሃል...። ታዲያ አትመለከትም እንዴ የደረሰብንን መከራ እና እንግልት!!! እባክህ ጌታህ ዘንድ በመሄድ አማልደን ሂሳብ ያድርግልን'ና ይገላግለን" ይሉታል።

ሙሳም፦" ጌታዬ ከዚህ በፊት ተቆጥቶ የማያውቀውን'ና ካሁን በኋላም የማይቆጣውን አይነት ቁጣ ዛሬ ተቆጥቷል።

እኔም ከዚህ በፊት ልገድላት የማትገባን ነፍስ ገድያለሁ'ና ነፍሴ...ነፍሴ... ወደ ዒሳ ዐሰ ሂዱ" ይላቸዋል። ህዝቡም ወደ ዒሳ ዐሰ ዘንድ በመሄድ፦"ዒሳ ሆይ!!! አንተ የአላህ መልዕክተኛ ነህ ወደ መርየም በተነፋው መንፈስም ያለ አባት እንድትወለድ አድርጎሃል።

ታዲያ አትመለከትም እንዴ የደረሰብንን መከራ እና እንግልት!!! እባክህ ጌታህ ዘንድ በመሄድ አማልደን ሂሳብ ያድርግልን'ና ይገላግለን" ይሉታል።

ዒሳም ዐሰ፦" ጌታዬ ከዚህ በፊት ተቆጥቶ የማያውቀውን'ና ካሁን በኋላም የማይቆጣውን አይነት ቁጣ ዛሬ ተቆጥቷል....ነፍሲ...ነፍሲ...ወደ ሙሀመድ ሂዱ!!!" በማለት ለራሱ መውጫ ቀዳዳ ይፈልጋል።

በመጨረሻም የሰው ዘር ባጠቃላህ ወደ ውዱ ሙሀመድ.... ወደ አዛኙ ሙሀመድ...ወደ አስተዋዩ ሙሀመድ...ወደ ክቡሩ መሀመድ ይተማሉ።

(የሁሉም ነቢይ ኡመት ተሰብስቦ ወደተለያዩ ነቢያት ዘንድ ሄዶ ሄዶ... መላ ሲያጣ ረሱል (ሰዐወ) ዘንድ ሲመጣ ምን ተሰማችሁ...!!! ሆድ ይፍጀው።)

ከዚያም ፍጥረቱ ባጠቃላይ ሙሀመድ ዘንድ በመምጣት፦"አንተ ሙሀመድ ሆይ!!! አንተ የነቢያት መደምደሚያ ነህ...፣አንተ መጪውም ያለፈውንም ወንጀልህን አላህ ይቅር ብሎሃል።

ታዲያ አትመለከትም እንዴ የደረሰብንን መከራ እና እንግልት!!! እባክህ ጌታህ ዘንድ በመሄድ አማልደን ሂሳብ ያድርግልን'ና ይገላግለን" ይሏቸዋል።.... #ይቀጥላል

ላልሰማው በማዳረስ ኢስላማዊ ግዳታችንን እንወጣ!!!!

የቤተሰባችን አባል ለመሆን ከፈለጉ እና ይሄን ትእይንት እስከ መጨረሻው ክፍል ድረስ ለመከታተል ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን መቀላቀል ይችላሉ👇

http://www.tg-me.com/eslamic_center
🔂 ሼር 🔂 ሼር 🔂 ሼር 🔂

ክፍል ➎ እንደተለመደው ልክ 3:00 ሰዓት ላይ ይዘንላችው እንቀርባለን እስከዛው ሼር በማድረግ ይጠብቁን

ክፍል ➍

ከዚያም ፍጥረቱ ባጠቃላይ ሙሀመድ ዘንድ በመምጣት፦"አንተ ሙሀመድ ሆይ!!! አንተ የነቢያት መደምደሚያ ነህ...፣አንተ መጪውም ያለፈውንም ወንጀልህን አላህ ይቅር ብሎሃል።

ታዲያ አትመለከትም እንዴ የደረሰብንን መከራ እና እንግልት!!! እባክህ ጌታህ ዘንድ በመሄድ ° አማልደን ሂሳብ ያድርግልን'ና ይገላግለን" ይሏቸዋል።

ይህን ግዜ ረሱልም (ሰዐወ)፦"አና ለሃ...!!! አና ለሃ...!!! (ለዚህች ቀን ምልጃ እኔ የተገባሁ ነኝ)" በማለት የፍጥረቱን ተስፋ ያለመልማሉ።

በመቀጠልም የክብር ባለቤት እና የፍቅር ተምሳሌት የሆኑትም ነብይ አላህ ዘንድ በመሄድ ከዙፋኑ ስር በግንባራቸው ተደፍተው አላህ በሚያመነጭላቸው ለየት ባለ ውዳሴ አዛኙን አላህን ማወደስ ይጀምራሉ።

በአላህም ትዕዛዝ አንድ መልዐክ ይመጣ'ና በግንባራቸው የተደፉትን ነብይ እጃቸውን ይዞ ቀና ያደርጋቸዋል።ቀና ሲሉም አላህ ከማወቁም ጋር፦"ሙሀመድ ሆይ!! ምን ፈልገህ ነው?" ይላቸዋል።

ረሱልም (ሰዐወ)፦"ያ ረቢ ለዚህ ቀን ምልጃን ቃል ገብተህልኛል'ና በህዝቡ ላይ አማልደኝ።ሂሳቡንም ተሳሰባቸው" ይሉታል።

ይህን ካሉ በኋላ ወደ ቦታቸው በመመለስ እሳቸውም ከህዝቡ ይቀላቀላሉ።የአላህ ምላሹ አልታወቀም....፣ ፍጥረት ባጠቃላይ ፍርሃት ናላውን አዙሮታል.....፣ሁሉም ራሱን ብቻ ሚያድንበትን መንገድ ነው ሚፈልገው።

ህዝቡ የመጨረሻ የተስፋቸው ማረፊያ ያደረጉትን ነብይ ምላሽ በመጠባበቅ ላይ ሳሉ ድንገት ከወደ ሰማይ በኩል ድምፅ መሰማት ይጀምራል።

ይህን ግዜ ሁሉም በድንጋጤ ወደ ላይ ቀና ብሎ ሲመለከት አላህ ከደመና በሆነ ጥላ ሲወርድ ይመለከታሉ።ያን ቀን የሱን አርሽ ስምንት ተሸካሚ መላዕክትም ይዘው ይወርዳሉ።

(ሱብሃነከ ያ ረብ) እነዚያ መላዕክት እጅግ ግዙፍ ከመሆናቸው ብዛት እግራቸው ያለው እታች ሰባተኛ መሬት ሲሆን ወገባቸው ሰማይ ጋ ይደርሳል።

ትከሻቸው ደግሞም ዐርሹ ረህማን ያለበት ነው።
በዚህ ግዝፈታቸው አርሽን ተሸክመው በሚያምር ውዳሴ እና ቅዳሴ የፍጥረተ አለሙን ጭርታ እየደመሰሱ እንዲህ እያሉ ይወርዳሉ፦

"የልቅና እና የጉልበት ባለቤት የሆነው አላህ ጥራት ይገባው። የንግስ'ና እና የፍጥረተ አለሙ ግዛት በእጁ የሆነው አላህ ጥራት ይገባው።
ያ ለማይሞተው እና ህያው ለሆነው አላህ ጥራት
ይገባው።

ያ ፍጥረትን የሚያስሞት እና ለራሱ ከመሞት የተጥራራው ጌታ ጥራት ይገባው። እሱ የተጥራራ ነው...፣እሱ ቅዱስ ነው...። የላቀው እና የመላዕክት እንዲሁም የመንፈስ(የጂብሪል) ጌታ የሆነው አላህ ጥራት ይገባው።

ያ የላቀው፤ ፍጥረትን የሚያስሞት እና ለራሱ ከመሞት የተጥራራው ጌታ ጥራት ይገባው" ይህ ውዳሴ በራሱ የቀኑን አስፈሪነት ያመለክታል።

ከዚያም አላህ ጀሀነምን በ70,000(ሰባ ሺህ) ልጓም አስጠፍሮ በማሳሰር እና በያንዳንዱ ልጓም 70,000 መላዕክትን እያስጎተተ እንድትመጣ ያደርጋታል።

(አስቡት ምን ያህል ጉልበት ቢኖራት ነው ለጀሃነም 70,000×70.000= 4,900,000,000(አራት ቢልየን ዘጠኝ መቶ ሚልየን) መላዕክት ሚጎትቷት!!!! ኢላሃና ሩህማክ)

ጀሀነም በዚህ ሁኔታ ተጠፍራ ስትመጣ ፍጥረቱን ባየች ግዜ ለአላህ ቁጣ በማገዝ እሷም ከፍተኛ የጩኸት ድምፅ ታሰማለች...፣ልጓሟን ከያዙት መላዕክቶች ልታፈተልክም ትቃረባለች።

ያን ግዜ ነፍስ ያለው ነገር መላዕክት... ሰው... ጂኑ ሳይቀር በእንብርክኩ ይወድቃል። ያን ሰዐት ጀሀነም ብትለቀቅ ሙዕሚኑንም ካፊሩንም ጠራርጋ ታስገባ ነበር.... ከዚያም ሂሳብ ይጀመራል...።

የስው ልጆች እና ጋኔኖች ሲቀሩ በፍጥረታት ባጠቃላይ ሂሳብ ይደረጋል። በእንስሳት...በአውሬዎች...ቀንድ ያላት ቀንድ አልባዋን የወገቻት ሳይቀር ሂሳብ በማድረግ እንድትበቀላት ይደረጋል።


የቤተሰባችን አባል ለመሆን ከፈለጉ እና ይሄን ትእይንት እስከ መጨረሻው ክፍል ድረስ ለመከታተል ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን መቀላቀል ይችላሉ👇

http://www.tg-me.com/eslamic_center
🔂 ሼር 🔂 ሼር 🔂 ሼር 🔂

ክፍል ➎

የስው ልጆች እና ጋኔኖች ሲቀሩ በፍጥረታት ባጠቃላይ ሂሳብ ይደረጋል። በእንስሳት...በአውሬዎች...ቀንድ ያላት ቀንድ አልባዋን የወገቻት ሳይቀር ሂሳብ በማድረግ እንድትበቀላት ይደረጋል።

በመጨረሻም እነዚህ ሂሳብ የተደረገላቸው ፍጥረታት ባጠቃላይ አንዲት (አፈር ሁኑ) በምትለው የአላህ ቃል ሁሉም በቅፅበት አፈር ሆነው ይጠፋሉ።

ያን ግዜ ከሃዲያን፦"ምነው እኛም አፈር የመሆንን እድል አግኝተን አፈር በመሆን ይሄን ጭንቅ በተገላገልን" በማለት ከንቱ ምኞትን ይመኛሉ።

ከዚያም ሁኔታው ባህሪውን በመቀየር የሰዎች እና የጋኔኖች ሂሳብ ይጀመራል።መጀመሪያ ሂሳብ የሚደረገው በደም ዙሪያ ነው።

ሁሉም ገዳይ የተገዳይን ጭንቅላት ተሸክሞ ይመጣል።በዚህ ሁኔታ በፊሰቢሊላህ ምክንያት ነፍስ የገደሉ ሙጃሂዶችም የተገዳዮችን ራስ ይዘው አላህ ዘንድ ሲቀርቡ ተገዳይም አላህን፦"ጌታዬ ሆይ! ይህ እኔን ለምንድነው የገደለኝ?" በማለት ይጠይቃል።

አላህም ከማወቁ ጋር፦ለምንድነው የገደልከው?" በማለት ገዳዩን(ሙጃሂድ) ይጠይቀዋል። ገዳይ (ሙጃሂድም)፦"ጌታዬ ሆይ! ልቅና ላንተ ይሆን ዘንድ ነው የገደልኩት" በማለት ይመልስለታል።

አላህም፦"እውነት ተናግረሃል" በማለት የሙጃሂዱን ፊት ልክ እንደፀሀይ ብርሃን ኑር በማልበስ መላዕክትን ወደ ጀነት እንዲወስዱት ያዛቸዋል።

ከዚያም ሌላ ገዳዮች'ና ተገዳዮችም(በሌላ ጉዳይ የተገዳደሉ) የተገዳዮችን ራስ በመሸከም መምጣት ይጀምራሉ።

ተገዳዮችም፦"ጌታዬ ሆይ! ይህ እኔን ለምንድነው
የገደለኝ?" በማለት ይጠይቃል። አላህም ከማወቁ ጋር፦ለምንድነው የገደልከው?" በማለት ገዳዩን ይጠይቀዋል።

ገዳይም፦"ጌታዬ ሆይ! ልቅና ለኔ ይሆን ዘንድ ነው የገደልኩት" በማለት ይመልስለታል። አላህም፦"ከስረሃል" ይለዋል።

ከዚያም ምድር ላይ ያለ ተገዳይ ሁሉ ገዳዩን እንዲበቀል በማድረግ ሌላ ሌላ ሀቆችም በአላህ ፍትሀዊነት ወደ ቦታቸው እንዲመለሱ ይደረጋል።

ይህ ከተጠናቀቀ በኋላ ከወደ አላህ በኩል፦"አዋጅ...!!! ሁሉም ፍጥረት ይገዛው ወደ ነበርው አማልክት ይከትል" የሚል ጥሪ ይመጣል።

ከዚያም አንዱ መልዓክ በአላህ ትዕዛዝ የዑዘይርን ምስል ይላበስ'ና በፍጥረቱ ፊት ሲቆም አይሁድ የተባለ ፍጥረት ባጠቃላይ እሱን ተከትሎ ይጎርፋል።

አንዱም መልዓክ የዒሳን (ዐሰ) ምስል በመላበስ ፍጥረቱ ፊት ሲቆም ክርስቲያን የተባለ ፍጥረት ባጠቃላይ ይህን መልዓክ እየተከተል መጉረፍ ይጀምራል።

በዚህ ሁኔታ የሁሉም ሀይማኖት ተከታዮች ጌታ ብለው የያዙት ነገር እየተመሰለላቸው ያን ነገር እየተከተሉ ሁሉም ይጎርፉ'ና ሙስሊሞች እና ሙናፊቆች ይቀራሉ።

ሁሉም ፊጥረት አማልክቱን ተከትሎ ከተመመ በኋላ አላህ ( እራሱ ብቻ በሚያውቀው'ና በፈለገው አይነት ሁኔታ) ሙስሊሞች እና ሙናፊቆች ያሉበት ቦታ በመምጣት፦" እናንተ ሰዎች ሆይ! ትገዟቸው ወደ ነበሩት አማልክት አትሄዱምን?!!" ይላቸዋል።

እነሱም፦"በአላህ እንምላለን...በአላህ እንምላለን እኛ ከአላህ ሌላ ጌታ የለንም።ከሱ ሌላም ተገዝተን አናውቅም" በማለት ይመልሳሉ።

አላህም ልቅናውን እና እሱነቱን በሚያውቁ ሁኔታ ከታፋው ጥቂት ይገልጥላቸዋል።ሙዕሚኖች ይህን በተመለከቱ ግዜ ለጌታቸው ክብር በአገጮቻቸው በመደፋት ሱጁድ ያደርጋሉ።

ሙናፊቆቹም አላህ ወገቦቻቸውን በማድረቅ ለሱጁድ ጎንበስ እንዳይሉ ያደርጋቸዋል(አላህ ይጠብቀን) ከዚያም ሲራጥ ይዘረጋል።

ሲራጥ በጀሀነም ላይ የተዘረጋ ረጅም ድልድይ ሲሆን፤ ድልድዩ እንደ ሰይፍ የሰላ ነው...፣ከታቹ ጀሀነም ትንተከተካለች...የጀሀነም አውሬዎች ከሲራጥ የሚወድቁ ሰዎችን ለመቀራመት ከድልድዩ ታች ይተራመሳሉ።

ሲራጥ ማለት ሙዕሚኖች ብቻ የሚያልፉበት ድልድይ ሲሆን ከሙእሚኖችም ተደናቅፎ በመውደቅ የጀሀነም አውሬዎች ሰለባ የሚሆኑ አሉ።

በዚያ ድልድይ ላይ ሁሉም የአስተላለፉ ሁኔታ እንደየኢማኑ ጥንካሬ ይለያያል።አንዳንዱ በአይን እርግብታ ድልድዩን ሲሻገር...ከፊሉ በመብረቅ ፍጥነት ያህል ይሻገረዋል።

ሌላው እንደ ብርቱ ጋላቢ ፍጥነት ሲሻገረው...ከፊሉም እንደ እግረኛ ተራምዶ ድልድዩን ያቋርጠዋል። ይቀጥላል....



የቤተሰባችን አባል ለመሆን ከፈለጉ እና ይሄን ትእይንት እስከ መጨረሻው ክፍል ድረስ ለመከታተል ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን መቀላቀል ይችላሉ👇

http://www.tg-me.com/eslamic_center
🔂 ሼር 🔂 ሼር 🔂 ሼር 🔂

ክፍል ➏


የተቀሩት የሙዕሚኖች ክፍል ደግሞ በእንብርክካቸው ሲንፏቀቁ ተከታዮቹም ከጀሀነም ወላፈን ጥቂት እየገረፋቸው ድልድዩን ይሻገሩታል።

(ይህ ሲሆን ረሱል ሰዐወ ድልድዩ ጫፍ ላይ ሆነው ኡመታቸውን እያዩ፦"ጌታዬ ሆይ ሰላም አውርድ...ጌታዬ ሆይ ሰላም አውርድ" ይላሉ።)

የተቀሩት ከድልድዩ እየተደናቀፉ በአፍጥማቸው በመውደቅ የጀሀነም ሰለባ ይሆናሉ።
______________
_

(እዚህች ጋ አንዱን አቁመን አንዱን ተከትለን ልንሄድ ግድ ይለናል።የጀሃነሙን ነገር እና ስለጀሀነም ሰዎች ያለውን ጉዳይ ለግዜው ያዝ እናድርገው እና ሲራጡን(ድልድዩን) ከተሻገሩት ሰዎች ጋር አብረን እንከተል።

ከዚያ ወደ ጀሀነሞቹ ጋር እንሄዳለን። ሙዱ ከተመቸን እዚው ጀነት ላይ እንቀራለን ክክክክ...
______________
__

አሁን ሙዕሚኑ ከሙናፊቁ ተለይቷል...።ሁሉም የሲራጥን ድልድይ ተሻግረው ጉዞ ወደ ፊት ቀጥለዋል።

የፍጥረቱ ብዛት ከቁጥር ጣሪያ የናረ ነው...፣የሁሉም ነቢያት ኡመቶች አሉ ሲራጥን ተሻግረው የጀነት ደጃፎች ላይ ደርሰዋል።

ነገር ግን የጀነት በሮች ባጠቃላይ ዝግ ናቸው።ይህ የሲራጥን የጭንቅ ድልድይ በስንት መከራ የተሻገረ እና እፎይ ጀነት ልገባ ነው ብሎ ተስፋ ያደረገ ህዝብ ሁሉ የጀነት በር መዘጋቱን ሲያይ አላህን ለማናገር በመፍራት ዳግም አማላጅ ፍለጋ ይጀምራሉ።

እንደተለመደው ግዜ ሁላ አደም ጋ በመሄድ ጀነት እንዲያስከፍት ይጠይቁታል።አደምም ይፈራል...።

ኑህ ጋ ይሄዳሉ...፤ኑህም አይሞክርም...። ኢብራሂም ጋርም ይሄዳሉ። እሱም ፍራቻውን ይገልፅላቸዋል...።ሙሳ ዘንድም ሲሄዱ እንደማይደፍር ይነግራቸዋል። ዒሳ ዘንድ ሲሄዱም፦"በፍፁም እኔ አልችልም ባይሆን ሙሀመድ ዘንድ ሂዱ" ይላል።

(ያ ረሱሉላህ መቼስ እርሶን አላህ አይመልሶትም።) (በነገራችን ላይ ረሱል (ሰዐወ) 3 አይነት ሸፋዓ ነው ያላቸው፦

1፦ለመላው ፍጥረት ሂሳብ እንዲደረግ
2፦ለጀነት መክፈቻ እና
3፦ለኡመቶቻቸው....)

አሁን ሁሉም በሙሉ ተስፋ ሙሀመድ ዘንድ ይጎርፋሉ ከዚያም ጀነትን እንዲያስከፍቱላቸው ይጠይቃሉም። ሀቢቡና'ም (ሰዐወ) የጀነት በር ላይ በመቆም ማንኳኳት ይጀምራሉ።

የበሩ ዘበኛም ከውስጥ በኩል፦"ማን ነህ?" ይላል። እሳቸውም፦"ሙሀመድ ነኝ" ይላሉ። ዘበኛውም፦"እንኳን ደህና መጣህ...አንተ ከመግባትህ በፊት ለማንም በሩን እንዳልከፍት ታዝዤ ነበር።

ያንተ ኡመቶችም ጀነት ከመግባታቸው በፊት ለማንም ኡመት በር እንዳልከፍት ታዝዣለሁ" ብሎ በሩን ይከፍታል። #ይቀጥላል

የቤተሰባችን አባል ለመሆን ከፈለጉ እና ይሄን ትእይንት እስከ መጨረሻው ክፍል ድረስ ለመከታተል ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን መቀላቀል ይችላሉ👇

http://www.tg-me.com/eslamic_center
2024/10/01 06:08:10
Back to Top
HTML Embed Code: