🕊 † 🕊
[ ተዋሕዶ ፍጽምት የቅዱሳን ሃይማኖት ]
▬▬▬▬▬▬ † ▬▬▬▬▬▬
[ ❝ የእኛን መከራ ተቀበለ ! ❞ ]
🕊
❝ እርሱ ደዌያችንን ወሰደ ፤ ሕማማችንንም ተሸከመ ፤ እርሱ ስለ እኛ አዘነ ፤ ተከዘ ፤ ስለ እኛም በጥፊ በመመታት ፤ በዕሥራት ፤ በችንካር በጦር የእኛን ኃጢአት ለማስተሥረይ የቆሰለ ሆኖ አየነው ፤ በደላችንን ለማስተሥረይ ይኽን ወዶ ተቀበለ ብሎ ኢሳይያስ እንደ ተናገረ ዳግመኛም በችንካር ፤ በጦር የቈሰለው ሰው [ ሥግው ቃል ] የእኛን መከራ ተቀበለ ብሏል። [ኢሳ.፶፫፥፩-፯ ። ፶፥፭-፰]
ዳግመኛ አስታራቂያችን [ ራሱ እንደታረቀን ] እንደሆነ ፤ የእኛንም መከራ መቀበል እንዲችል ከኃጢአት በቀር በሥራ ሁሉ እንደ እኛ እንደ ተፈተነ ፥ ስለእርሱ ሲናገር ጳውሎስን እንስማው። [ዕብ.፬፥፲፬-፲፮]
ስለእኛ በታመመው ሕማም የእኛን ነፍስ የምትመስል ነባቢት ነፍስን ፡ እርሱ እንደ ተዋሐደ እናምናለን። ዳግመኛም የነፍሳችንን ሕማም በእውነት ወዶ እንደ ተቀበለ እናምናለን ፤ ይኸውም ሁከት ፤ ትካዝ ፤ የልብ ኀዘን ነው ፤ ወንጌላዊ ዮሐንስም የእርሱን ነገር ነገረን ፤ እርሱ ነፍሴ ከሥጋዬ እስከ መለየት ደርሳ አዘነች እንዳለም አስረዳ ፤ ዳግመኛም እንደ አዘነ ፡ እንደ ተከዘ በማርቆስ ወንጌል ተጽፎአል። [ማር.፲፬፥፴፬-፴፮ ። ዮሐ.፲፪፥፳፯]
በሐሰት ያይደለ በእውነት የሥጋ ሕማምን እንደታመመ በዚህ እናምናለን ፤ በገረፉት ጊዜ አልተሰማውም ፤ በሰቀሉትም ጊዜ አልደከመም ፤ በችንካርም በቸነከሩት ጊዜ ሕማም አላገኘውም ብለው ስለ እርሱ የሚናገሩትን ግን መናፍቃን እንደ መሆናቸው እኛ እናወግዛቸዋለን። ❞
[ ቅዱስ ዮሐንስ ዘኢየሩሳሌም ]
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፤ ወለወላዲቱ ድንግል ፤ ወለመስቀሉ ክቡር። አሜን።
† † †
💖 🕊 💖

†
[ 🕊 ገ ድ ለ ቅ ዱ ሳ ን 🕊 ]
▬▬▬▬▬▬ † ▬▬▬▬▬▬
[ የአባታችን የቅዱስ መቃርዮስ የተጋድሎ ሕይወቱና ትምህርቱ ]
[ ክፍል አሥራ አንድ ]
💛
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡
[ በአንዲት ወጣት ሴት መፅነስ ምክንያት እንደ ተከሰሰ ]
🕊
❝ በዚያች ሀገርም አንዲት ያላገባች ብላቴና ነበረች፡፡ እንዲሁም ከእርሷ ጋር በጣም የሚቀራረብ አንድ ጎልማሳ ነበር፡፡ የዚህ ጎልማሳ ቤተሰቦችም ይህን በተመለከቱ ጊዜ የልጅቱን ቤተሰቦች በመጠየቅ በተከበረ ጋብቻ ሥርዓት ሊያጋቧቸው አሰቡ፡፡ ነገር ግን ሁለቱም ለጋብቻ በደረሱ ጊዜ የልጁ ቤተ ሰብእ በመደህየታቸው የተነሳ የታሰበው ሠርግ ሁሉ ቀረ፡፡ ይሁን እንጂ የሚኖሩበት በአንድ አካባቢ በጉርብትና ስለ ነበር በጣም ይቀራረቡ ነበር፡፡ በመሆኑም በቤታቸው ውስጥ ሆነ ከቤታቸው ውጪ ብዙውን ጊዜ ይገናኙ ነበር፡፡
አንድ ቀን በዓል እያከበሩ ውለው በመጠጥ ምክንያት በዝሙት በመውደቃቸው ሁለቱም ድንግልናቸውን አጡ፡፡ እርሷም ፀነሰችና ቀስ በቀስ ነገሩ እየታወቀ ሲመጣ በእነርሱ ላይ እንዲህ ዓይነት የሚያሳፍር ሥራ ስለ ሠሩ እንዳይገድሏቸው ሁለቱም ወላጆቻቸውን ፈሩ፡፡ ስለዚህ አስቀድሞ ከሠሩት የዝሙት ሥራ በላይ በድጋሚ ታላቅ ኃጢአት ለመሥራት ተማከሩ፡፡ "ምን እናድርግ? ወላጆቻችን ይህን ከሰሙ ይገድሉናል" በማለት ጎልማሳውም "አባትሽ ድንግልናሽን ማን አጠፋው? ብሎ ሲጠይቅሽ መቃርዮስ የሚባለው ባሕታዊ ቄስ እርሱ ስለደፈረኝ ነው በይው" ብሎ መከራት፡፡
ፅንሷም በጣም በታወቀ ጊዜ አባቷ "ይህን አሳፋሪ ሥራ በአንቺ ላይ የሠራብሽ ማነው?" ብሎ ጠየቃት፡፡ እርሷም "አንድ ቀን መቃርስ ወደሚባለው ቄስ ሄጄ ሳለሁ በኃይል ይዞ ደፈረኝ ፤ ስለዚህ ከእርኩ ፀነስኩ" ብላ ያ ወጣት እንደ መከራት መለሰችለት፡፡ ወላጆቿና ቤተሰቦቿም ይህን በሰሙ ጊዜ ከደረሰባቸው አፍረት የተነሣ እጅግ በታላቅ ቁጣ ከብዙ ሰዎች ጋር ሆነው ወደ መቃርስ ሄደው በኃይል ከበዓቱ ይዘው አስወጡት፡፡ እርሱንም ለሞት እስኪቀርብ ድረስ አጽንተው ደበደቡት፡፡
እርሱ ግን ምን እንደ ሆነ አላወቀም ነበርና "ያለ ርኅራሄ የምትደበድቡኝ ኃጢአቴ ምንድን ናት?" እያለ ይጠይቃቸው ነበር፡፡ ከዚህ በኋላ በፍህም የጠቆሩ ገሎችን በአንገቱ ላይ በገመድ አንጠልጥለው ወዲያና ወዲህ እየጎተቱ "የልጃችንን ድንግልና ያጠፋው ይህ ነው" እያሉ እንደ እብድ በላዩ ላይ በአንድ ድምፅ ይጮኹ ጀመር፡፡
ለመቃርዮስ የእጁን ሥራ ወስዶ በመሸጥና ለመፍቅድ የሚሆነውን ነገር ገዝቶ በማምጣት የሚላላከው አንድ ምዕመን ሰው ነበር፡፡ ረድኡም በቅዱሱ ላይ በሆነው የሐሰት ነገር አዝኖና ተክዞ ፤ በደበደቡት ድብደባና በፌዛቸውና በስላቃቸው እያዘነ መቃርዮስን ይከተለው ነበር፡፡
በዚያን ጊዜ መላእክት ከሩቅ ሀገር በመጡና በሚታወቁ ደጋግ ምዕመናን ሰዎች አንጻር ተገልጠው እነዚያ ክፉ ሰዎች ከሚያደርሱበት ድብደባና ነቀፋ የተነሣ ሊሞት እንደ ቀረበ ባዩት ጊዜ የሚያሰቃዩትን ሰዎች ፦ "ይህ ተጋዳይ ምን አደረገ?" አሏቸው፡፡ እነርሱም በልጃችን ላይ የኃፍረትን ሥራ እንደ ሠራ አድርገው መልሰው ነገሯቸው፡፡ እነዚያ መላእክትም ፦ "ይህ ነገር ሐሰት ነው ፤ እኛ ይህን ሰው ከታናሽነቱ ጀምሮ እስከዚች ቀን እናውቀዋለን ፣ እርሱ የተመረጠ ጻድቅ ሰው ነውና" አሏቸው፡፡ የታሰረበትን ፈቱትና ከላዩ የታሰሩትን ገሎች ሰባብረው ጣሏቸው ፣ ከድካሙም አበረቱት፡፡ የልጅቷ አባት ግን "ፈጽሞ አይሆንም ፣ እስክትወልድ ድረስ ቀለቧን እንደሚችልና ከወለደች በኋላም ለልጁ ማሳደጊያ ገንዘብ እንደሚሰጥ ዋስ ካላቀረበ በስተቀር አንለቀውም" አለ፡፡
መቃርዮስም "ጥፋቴ ምንድን ነው? አሁን የተያዝኩበትንና የተከሰስኩበትን ነገር አላወኩትምና" አላቸው፡፡ በመጨረሻም የእጅ ሥራውን የሚሸጥለትን ረድኡን ፦ "ፍቅርን አድርግልኝ ፣ ዋስ ሁነኝ" አለው፡፡ እርሱም ዋስ ሆነው፡፡ ከዚያ በኋላ ለቀቁትና መቃርስ ወደ በአቱ ተመልሶ ገባ፡፡ ወዲያውኑ ወደ በአቱ እንደ ገባም ከዚያች ቀን ጀምሮ ራሱን ለራሱ ፦ "መቃርስ ሆይ እነሆ እንግዲህ ባለ ሚስትና ባለ ልጅ ሆነሃልና ሌሊትና ቀን መሥራት ይገባሃል" እያለ ያቺ ሴት ልጅ የምትወልድበት ጊዜ እስኪደርስ ድረስ ቅርጫቶችን እየሰራ ለዚያ ወዳጅ ለሆነውና ለሚያገለግለው ወንድም ይሰጠውና ያም ሰው ለዚያች ሐሰተኛ ልጅ እየሰጠ ኖረ፡፡
ያቺ ሴት ልጅ የምትወልድበት ቀን ሲደርስ እግዚአብሔር የዚህን ቅዱስ ንጹሕ መዝገብ ተሰውሮ እንዲቀር አልፈቀደም ፣ መቃርዮስ ቅዱስና ንጹሕ ሰው መሆኑን ፣ እግዚአብሔር እርሱን ለሚፈሩትና በእርሱ ለሚታመኑት ተስፋቸውና መመኪያቸው እርሱ ብቻ መሆኑን ለሰው ሁሉ ይገልጥ ዘንድ ወደደ እንጂ፡፡
ያቺ ልጅ ምጡ እጅግ አስጨነቃት ፤ በታላቅ ስቃይ ውስጥ ሆና እየጮኸች አራት ቀናት ያህል ቆየች፡፡ ልትወልድ ስላልቻለች ለሞት ተቃረበች፡፡ እናቷም ፦ "እንግዲህ ልትሞቺ ተቃርበሻልና ከአንቺ የሆነው ነገር ምንድን ነው? ምናልባት የተሠራ ነገር አለና ንገሪኝ" አለቻት፡፡ እርሷም "ያመነዘርኩት እገሌ ከሚባል ጎልማሳ ጋር ሲሆን በእግዚአብሔር አገልጋይ ላይ ዋሽቻለሁና በእውነት ሞት ይገባኛል" አለቻት፡፡ አባትና እናቷም ይህን በሰሙ ጊዜ ደነገጡ ፣ ለሞት እስኪደርስ ድረስ አብዝተው ስለ መቱትና ስላሰቃዩት እጅግ በጣም አዘኑ ፤ ተጸጸቱም፡፡ የአገር ሰዎችም ሁሉ ተሰበሰቡ፡፡
ያ የሚላላከው ረድኡም ያገሩ ሰዎች ወደ መቃርዮስ ሄደው ይቅር ይላቸው ዘንድ ፈጥነው ሊመጡ እንዳላቸው በሰማ ጊዜ ንጹሕነቱ በመገለጡ በብዙ ደስታ ደስ አለው ፤ አንተ የምታገለግለውና ስለ ቅድስናው ትመሰክርለት የነበርከው ሰው እንዲህ አደረገ" እያሉ ይነቅፉትና ያፌዙበት ስለ ነበር እግዚአብሔር ይህን ነውርና ኃፍረት ከፊቱ ስላራቀለት በጣም ተደሰተ፡፡
እርሱም ወደ መቃርዮስ መጣና ፦ "ያች ርግምት ሴት ኃጢአቷን እስክትናዘዝና እውነቱን እስክትናገር ድረስ ልትወልድ አልቻለችም፡፡ አሁንም ያገሩ ሰዎች ሁሉ ይቅርታ ይጠይቁህና ትእግሥትህን ያደንቁ ዘንድ ወደ አንተ ሊመጡ ነው" አለው፡፡ የአገር ሰዎችም ሁሉ ተሰበሰቡ ፣ በእርሱ ላይ የሠሩትን በደል ይቅር ይላቸው ዘንድ ወደ ቅዱስ መቃርዮስ ሄደው ለመኑት፡፡ ያን ጊዜ በበረሃ ያየውን ያንን ራእይ አስታወሰ ፤ ይቅርም አላቸው፡፡ ቀድሶ ሥጋውንና ደሙን አቀበላቸው፡፡ ❞
የአባታችን የቅዱስ መቃርዮስ ምልጃና ጸሎቱ አይለየን፡፡
ይቆየን !

[ † እንኳን ለድንግልና ሰማዕት አርሴማ ቅድስት ወዮሐንስ ወንጌላዊ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ። † ]
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †
🕊 † ቅድስት አርሴማ ድንግል † 🕊
† እናታችን ቅድስት አርሴማን በምን እንመስላታለን? እርሷ በአድማስ ላይ ተቀምጦ እንደሚያበራ እንቁ ናትና ክብሯ ብዙ ነው:: መድኃኒታችን ክርስቶስ በወንጌል እንዳለው "በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሠወር አይቻላትምና" የሰማዕቷ ሕይወት በፊታችን እንደ ብርሃን ተገልጦ ይታያል::
¤ ቅድስት አርሴማ እንደ ልጅ ወላጆቿን በመታዘዝ ደስ ያሰኘች ቡርክት ናት::
¤ ቅድስት አርሴማ ይሕ ቀረሽ የማይሏት ውብ ናት::
¤ ቅድስት አርሴማ ድንግል ናት::
¤ ቅድስት አርሴማ ባሕታዊት ጻድቅ ናት::
¤ ቅድስት አርሴማ ኃያል ሰማዕት ናት::
ይሕስ እንደ ምን ነው ቢሉ :-
አበው በትውፊት እንደ ነገሩን ከሆነ ቅዱሱ ጐርጐርዮስ የታላቋ ሰማዕት ቅድስት አርሴማ ትልቅ ወንድም ነው:: በዜና ሰማዕታት ተጽፎ እንደሚገኘው በዚያ የመከራ ዘመን ቅዱስ ጐርጐርዮስ ሦስት ኃላፊነቶች ነበሩበት :-
፩. ቅድስት አርሴማን ጨምሮ ደናግሉን ማጽናት::
፪. ትምሕርተ ቤተ ክርስቲያንን በሚገባ ማጥናት::
፫. የሚመጣውን መከራ ለመቀበል ራሱን ማዘጋጀት::
ቅዱሱ ሦስቱንም ኃላፊነቶች በሚገባ በመወጣቱ ከራሱ አልፎ ለሌሎቹ አርአያ መሆን ቻለ:: ያቺን ንጽሕት አርበኛ ቅድስት አርሴማንም አጽንቶ የደናግሉ መሪ አደረጋት:: መከራው በጣም ገፍቶ እስከ መጣበት ጊዜ ድረስ በአንድ የደናግል ገዳም ውስጥ ሆነው ይጸልዩ: ይጾሙ: ገዳማዊ ሥራንም ይሠሩ ነበር::
ለዚህም ነው ቅድስት አርሴማና ቅዱስ ጐርጐርዮስ ጻድቃን የምንላቸው:: በኋላ ግን ማሕደረ ሰይጣን ዲዮቅልጢያኖስ በመልኳ ተማርኮ ቅድስት አርሴማን ካላገባሁ በማለቱ ቅዱስ ጐርጐርዮስ ድንግሏን አርሴማን ጨምሮ ፲፳፯ ክርስቲያኖችን ይዞ ወደ አርማንያ ተሰደደ::
በአርማንያም በአንድ ገዳም ውስጥ ተደብቀው በጾምና በጸሎት ለጥቂት ጊዜ ቆዩ: ነገር ግን ረሃብ ፈጃቸው:: የሚላስ የሚቀመስ ነገር በአካባቢው ባለ መኖሩ ቅዱስ ጐርጐርዮስ ወደ ከተማ ለመውጣት ተገደደ::
በዚያም በድርጣድስ ቤተ መንግስት ውስጥ ባርነት ተቀጠረ:: በሚያገኛት ገንዘብም ወገኖቹን ይረዳ ነበር:: መከራው ግን አለቀቃቸውም:: ርጉም ዲዮቅልጢያኖስ ቅዱሳኑ ወደ አርማንያ መሔዳቸውን ስለ ሰማ ይዞ እንዲልክለት ድርጣድስን ላከው::
ድርጣድስ ግን ቅድስት አርሴማን ባያት ጊዜ ከውበቷ የተነሳ መታገስ ባለመቻሉ "ካላገባሁሽ" አላት:: ድንግሊቱ ግን "እኔ የክርስቶስ ሙሽራ ነኝ: አይሆንም" አለችው:: ሊያስፈራራት ሞከረ:: ዐይኗ እያየ ደናግሉን ጨፈጨፋቸው::
አልሳካልህ ቢለው በአደባባይ በግድ ሊያገባት ቢሞክር እጁን ጠምዝዛ በሰው ሁሉ ፊት መሬት ላይ ጣለችው:: እጅግ ስላፈረ አስገረፋት: አሰቃያት: ዐይኗንም አወጣ:: በመጨረሻም አንገቷን አስቆርጦ ከሰማዕታቱ ጋር ተራራ ላይ ጣላት::
ከነገር ሁሉ በኋላ ድርጣድስና ባለሟሎቹ ለአደን በሔዱበት ርኩስ መንፈስ ወደ አውሬነት [እሪያነት] ቀየራቸው::
የንጉሡ እንስሳ [አውሬ] መሆን በአርማንያ ታላቅ ድንጋጤን ፈጠረ:: የንጉሡ እህት ስታለቅስ በራዕይ "ለእመ ኢያዕረግምዎ ለጐርጐርዮስ አልብክሙ ድኂን - ጐርጐርዮስን ከተቀበረበት ካላወጣችሁት አትድኑም" አላቸው:: ወዲያውም ቆፍረው አወጡት::
ቅዱሱ እንደ ወጣ ዕረፍትን አልፈለገም:: ለ፲፭ ዓመታት ቀባሪ አጥቶ የተበተነውን የቅድስት አርሴማንና የሰማዕታቱን አጽም ሰብስቦ በክብር አኖረው:: ድርጣድስና ባለሟሎቹንም ወደ በርሃ ሒዶ ፈወሳቸው::
የሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ አጽም በ፲፬ኛው መቶ ክ/ዘመን ከሌሎች ሰማዕታት አጽም ጋር ወደ ሃገራችን እንደ መጣ አባቶቻችን በትውፊት ነግረውናል:: ለዚህም ይመስላል ቡርክቷ እናታችን ከሌሎች ሃገራት ለይታ ለኢትዮዽያውያን ልዩ ፍቅር ያላት:: በዋናው ገዳሟ [ወሎ / ኩላማሶ / ስባ / ውስጥ የሚገኝ ነው] ጨምሮ ስሟ በተጠራበት ሁሉ ኃይልን ታደርጋለችና::
ነገር ግን ወንድሞቼና እሕቶቼ በቅድስቷ እናታችን ስም የሚነግዱ ሥጋውያን ሰዎች በዝተዋልና እንጠንቀቅ:: የሰማዕቷ ክብር ብዙ ነውና በሕልም ላይ ብቻ አንታመን:: አባ እንጦንስ እንዳሉት "በሕልሙ የሚታመን ሰው ከንቱ ነውና::"
በዚህ ዕለት ከሰማዕቷ ጋር የመንፈስ እናቷን ቅድስት አጋታን ልናስባት ይገባናል:: ይህች እናት እመ-ምኔት ስትሆን ቅድስት አርሴማን ታስተምራት: ታጸናት: ከጐኗም ትቆምላት ነበር:: ረሃቧን: ጥሟን: ስደቷን: መከራዋንም ሁሉ አብራት ተሳትፋለች:: በፍጻሜውም አብራት ተሰይፋለች::
🕊 † ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ † 🕊
- የቤተ ክርስቲያን ምሰሶ
- ምድራዊው መልአክ
- የጌታ ወዳጅ
- የድንግል ማርያም የአደራ ልጅ
- የንጽሕና አባት
- ቁጹረ ገጽ
- የፍቅር ሐዋርያ
- የምሥጢር አዳራሽ
- የሐዋርያት ሞገሳቸው
- ነባቤ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጐድጓድ ዛሬ ይከብራል::
ምክንያቱም "ቀዳሚሁ ቃል" [ዮሐ.፩፥፩] ብሎ እንደ ንስር መጥቆ ወንጌሉን በዚህች ቀን ጽፏልና::
✞ አምላከ ቅዱሳን ለኛ ለባሮቹ የቅድስቷን ጽናት: የወንጌላዊውንም ፍቅር ያድለን:: በረከታቸውን ከማይጐድል እጁ አብዝቶ ይስጠን::
🕊
[ ✞ መስከረም ፳፱ [ 29 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. ቅድስት አርሴማ ድንግል [ሰማዕት]
፪. ቅድስት አጋታ [እመ ምኔት]
፫. "፻፲፱" ሰማዕታት [የቅድስት አርሴማ ማሕበር]
፬. ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ [ነባቤ መለኮት]
፭. ቅድስት ክርስቶስ ክብራ ኢትዮዽያዊት [በዚህ ቀን ነፍሳትን ከሲዖል ታወጣለች]
[ ✞ ወርኀዊ በዓላት ]
፩. የፈጣሪያችንና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደት
፪. ቅዱስ ዼጥሮስ ተፍጻሜተ ሰማዕት
፫. ቅዱስ ማርቆስ ዘቶርማቅ
፬. ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ኢትዮዽያዊት
፭. ቅዱስ ዘርዐ ክርስቶስ [ጻድቅና ሰማዕት]
✞ " በመጀመሪያ ቃል ነበረ:: ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ:: ቃልም እግዚአብሔር ነበረ :: ይህ በመጀመሪያው በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ:: ሁሉ በእርሱ ሆነ:: ከሆነውም አንዳች ስንኳ ያለ እርሱ አልሆነም:: በእርሱ ሕይወት ነበረች:: ሕይወትም የሰው ብርሃን ነበረች:: ብርሃንም በጨለማ ይበራል:: ጨለማም አላሸነፈውም::" ✞ [ዮሐ. ፩፥፩]
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬

Forwarded from አብሰራ ገብርኤል ለማርያም (♱ ባሕራን ♱)
🕊
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። †
† ጥቅምት ፫ [ 3 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት †
† 🕊 " ቅዱስ ጊዮርጊስ ሐዲስ " 🕊 †
† ሰማዕቱ የተወለደው በምድረ ግብጽ አሕዛብ [ተንባላት] በሰለጠኑበት የመጀመሪያው ዘመን ነበር:: በተለይ ተንባላቱ ግብፅና ሶርያን ከያዙ በኋላ ባልተጠበቀ ፍጥነት በኃይልም በሰውም ተደራጅተው ነበር:: ቅዱስ ጊዮርጊስ [ልብ በሉልኝ ሊቀ ሰማዕታት አይደለም] የተወለደው በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ ነበር::
እናቱ የተመሠከረላት ክርስቲያን ብትሆንም እንዳለመታደል አባቱ ተንባላታዊ [አሕዛብ] ነበር:: ስሙንም መዛሕዝም ይሉታል:: ሕጻኑ እንደተወለደ ያወጡለት ስም አሕዛባዊ ከመሆኑ ባለፈ በሰዓቱ መጠመቅ አልቻለም:: የወቅቱ ሕግ ከወላጆቹ አንዱ አሕዛባዊ ከሆነና አጠምቃለሁ ቢባል የሚከተለው ሰይፍ ነበር:: በዚሕ ምክንያት ሳይጠመቅ ፯ ዓመት ሞላው::
እናቱ ግን ሕጻን ቢሆንም ፍቅረ ክርስትናን ታስተምረው ነበር:: ባይጠመቅም ጸበሉን: እመነቱን ትቀባው ነበር:: ደብቃ ቅዳሴ ታሰማውም ነበር:: አንድ ቀን ግን ሕጻናት ሲቆርቡ አይቶ ካልቆረብኩ ብሎ አለቀሰ:: ምን ታድርገው? ወደ ውጪ አውጥታ ከአውሎግያ [የሰንበት በረከት] አበላችው:: "ጌታየ! ልጄን እርዳው" አለች::
ልክ በአፉ ሲቀምሳት መዓዛ መንፈስ ቅዱስ አደረበትና ፍጹም ተደሰተ:: ትንሽ ከፍ ሲል ለምን እንደማይጠመቅና እንደማይቆርብ እናቱን ጠየቃት:: "ልጄ ሆይ! ይገድሉሃል" አለችው:: ከዚህች ቀን ጀምሮ የሚጠመቅበትን ዘዴ ይፈልግ ጀመር::
አስቀድሞ ትምሕርተ ክርስትናን ተማረ:: ለአካለ መጠን ሲደርስ አፈላልጐ ጠንካራ ክርስቲያን የሆነች ሴት አገባ:: ጥቂት ጊዜ ከቆየ በኋላ ሚስቱን ስለ መጠመቅ አማከራት:: "ሌላ ሃገር ሒደህ ተጠመቅ" አለችው:: ከግብፅ ተነስቶ ሶርያ ገባ::
አባቶችን አፈላልጎ ተጠመቀ:: ቀጥሎም መንገዱን ወደ ልዳ አደረገ::
ወደ ደብሩ ተጠግቶ አባቶችን "ስም አውጡልኝ" ቢላቸው መንፈስ ቅዱስ አናግሯቸው "ጊዮርጊስ" አሉት:: እሱም ደስ እያለው: ባጭር ታጥቆ የልዳውን ቅዱስ ጊዮርጊስ ያገለግለው ገባ:: ትንሽ ቆይቶ ሁከት መንፈሳዊ ተሰማው:: ማለትም ስለ ሃይማኖቱ ደሙን ማፍሰስ ፈለገና ወደ ግብፅ ተመለሰ::
በዚያ ያሉ አሕዛብ በክርስትና ስም: ልብስና ሞገስ ሲመለከቱት ተበሳጩ:: ዕለቱኑ አሠሩት:: ሌሊት እናቱና ሚስቱ መጥተው አሉት:- "አደራ! ፍቅረ ዓለም እንዳያታልልህ:: ሰማዕት ብትሆን ላንተም ክብር: ለእኛም ሞገስ ነው" ብለውም አጽናኑት:: እንዲህ ያሉ እናትና ሚስት ማግኘትም ታላቅ እድል ነው::
ሐዲስ ጊዮርጊስም ጸና:: ከዚያች ቀን ጀምሮ ለተከታታይ ቀናት ደበደቡት: አካሉን ቆራረጡት: ደሙንም መሬት ላይ አንጠፈጠፉት:: በየመንገዱ እየጎተቱ ተሳለቁበት:: እርሱ ግን ክርስቶስን ወዷልና ሁሉን ታገሰ:: ሌሊት በሆነ ጊዜም ጌታችን ተገልጦ "ከሰማዕታት ተቆጠርህ" አለው::
በማግስቱ በአደባባይ አንገቱን በሰይፍ ቆረጡት:: ክፋታቸው የጸና ነውና ሥጋውን በእሳት አቃጠሉት:: ወደ ባሕርም ጣሉት:: እናቱ ከባሕር ስታወጣው ግን ምንም አላገኘውም ነበር:: በዚሕች ቀን እናቱና ሚስቱ በክብር ቀብረውታል::
† 🕊 " አባ ስምዖን ሊቀ ዻዻሳት " 🕊 †
በምድረ ግብጽ ተነስተው: በማርቆስ ወንጌላዊ መንበር ላይ ይቀመጡ ዘንድ ከተገባቸው ሊቃነ ዻዻሳት አንዱ እኒህ አባት ናቸው:: ከልጅነታቸው መንነው ብዙ ዘመናትን በተጋድሎ በማሳለፋቸው ሥጋዊ አካላቸው ደካማ ሆኖ ነበር::
ከገዳማዊ አገልግሎታቸው ቀጥሎም ከእርሳቸው በፊት ለነበሩ ሁለት ፓትሪያርኮች ረዳት ሆነው አገልግለዋል:: በዚህ ጊዜም ለመንጋው የሚሆኑ ተግባራትን ከመፈጸማቸው ባሻገር በጾምና በጸሎት መጋደልን አልተዉም ነበር::
ጊዜው ደርሶ በእግዚአብሔር ፈቃድ: በሕዝቡና ዻዻሳቱ ምርጫ: የእስክንድርያ ፶፩ኛ ፓትርያርክ ሲሆኑ እርሳቸው እንደ ሌሎቹ አበው 'አልፈልግም' ብለው ነበር::
ቀደም ሲል እንዳልነው አካላቸው በተጋድሎ የተቀጠቀጠ ነበርና በመንበራቸው ላይ ለብዙ ጊዜ መቆየት አልቻሉም::እግራቸውን በጠና በመታመማቸው ፈጣሪ ነፍሳቸውን እንዲቀበል ለመኑት: እርሱም ሰማቸው:: ሊቀ ዻዻሳት ሆነው በተሾሙ በ፻፷፭ ኛው ቀን [ማለትም በ፭ ወር ከ፲፭ ቀናቸው] በክብር ዐርፈው ተቀብረዋል::
† ቸሩ አምላክ ከሰማዕቱ ጽናትን: ትእግስትን: ጸጋ በረከትን ይክፈለን::
🕊
[ † ጥቅምት ፫ [ 3 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. ቅዱስ ጊዮርጊስ ሐዲስ [ሰማዕት]
፪. አባ ስምዖን ሊቀ ዻዻሳት
፫. ቅዱስ ጐርጐርዮስ ዘአርማንያ
፬. ቅድስት ታኦድራ ልዕልት
፭. ቅድስት ታኦፊላ
፮. አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
[ † ወርኀዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. በዓታ ለእግዝእትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ
፪. ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና
፫. ቅዱሳን ሊቃነ ካህናት አበው [ዘካርያስና ስምዖን]
፬. አባ ሊባኖስ ዘመጣዕ
፭. አቡነ ዜና ማርቆስ
፮. አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ዘደብረ በንኮል
፯. ቅዱስ ቄርሎስ ሊቅ [ዓምደ ሃይማኖት]
† " ስለዚሕ ወንድሞቼ ሆይ ጣዖትን ከማምለክ ሽሹ:: ልባሞች እንደመሆናችሁ እላለሁ:: በምለው ነገር እናንተ ፍረዱ:: የምንባርከው የበረከት ጽዋ ከክርስቶስ ደም ጋር ኅብረት ያለው አይደለምን? የምንቆርሰውስ እንጀራ ከክርስቶስ ሥጋ ጋር ኅብረት ያለው አይደለምን?... እኛ ብዙዎች ስንሆን አንድ ሥጋ ነን:: ሁላችን ያን አንዱን እንጀራ እንካፈላለንና:: "† [፩ቆሮ.፲፥፲፬-፲፰]

Forwarded from አብሰራ ገብርኤል ለማርያም (Dawit)
#ድንግል__ሆይ!
አንገታቸውን እንደሚያረዝሙ እንደ እብራውያን ሴቶች ልጆች በዋዛ ያደግሽ አይደለሽም ፤ #በቅድስናና #በንጽሕና #በቤተ_መቅደስ ኖርሽ እንጂ ።
#ድንግል__ሆይ!
ምድራዊ ሕብስትን የተመገብሽ አይደለም ፤ ከሰማየ ሰማያት የበሰለ #ሰማያዊ #ሕብስትን እንጂ ።
#ድንግል__ሆይ!
ምድራዊ መጠጥን የጠጣሽ አይደለም ፤ ከሰማየ ሰማያት የተቀዳ #ሰማያዊ መጠጥን እንጂ ።
(ቅዳሴ ማርያም)
🌹 #መልካም_ዕለተ_ሰንበት 🌹
አጫጭር ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
•➢ 👇 ለማግኘት // 👇
@Enatachn_mareyam
@Enatachn_mareyam
አንገታቸውን እንደሚያረዝሙ እንደ እብራውያን ሴቶች ልጆች በዋዛ ያደግሽ አይደለሽም ፤ #በቅድስናና #በንጽሕና #በቤተ_መቅደስ ኖርሽ እንጂ ።
#ድንግል__ሆይ!
ምድራዊ ሕብስትን የተመገብሽ አይደለም ፤ ከሰማየ ሰማያት የበሰለ #ሰማያዊ #ሕብስትን እንጂ ።
#ድንግል__ሆይ!
ምድራዊ መጠጥን የጠጣሽ አይደለም ፤ ከሰማየ ሰማያት የተቀዳ #ሰማያዊ መጠጥን እንጂ ።
(ቅዳሴ ማርያም)
🌹 #መልካም_ዕለተ_ሰንበት 🌹
አጫጭር ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
•➢ 👇 ለማግኘት // 👇
@Enatachn_mareyam
@Enatachn_mareyam
Forwarded from አብሰራ ገብርኤል ለማርያም (♱ ባሕራን ♱)
†
† 🕊 ክብርት ሰንበት 🕊 †
❝ የሰው ልጆች ያርፉባት ዘንድ ሰንበትን አዘጋጀ፡፡ ለጻድቃንም ለኃጥአንም ፣ ለሞቱትም በሕይወት ላሉትም ፡ የሰው ልጆች ያርፉባት ዘንድ ሰንበትን አዘጋጀ፡፡
የክርስቶስ ሰንበቱማ እርሷ ናት ፣ ለልዑልም የስሙ ማደሪያ ናት፡፡ ዛሬስ በሰማያት ያለች ተስፋችንና ሕይወታችን በዚህች በተቀደሰች ቀን ነው ፣ በርሷ በሚያርፉባት በሰንበት ቀን፡፡ ❞
[ ቅዱስ ያሬድ ]
🕊
[ መጽሐፍ እንደተናገረ በፈጣሪ እና በፍጡራን መካከል ለዕረፍት የቃል ኪዳን ማደሪያ [ ምልክት ] የሆንሽ የብርሃን ቀን ሰንበተ ሰንበታት ማርያም ሆይ በገነት ያሉ ጻድቃን በአንቺ ደስ ይላቸዋል፡፡ ኃጥአንም ከደይን በአንቺ ይወጣሉ፡፡ ]
[ አባ ጽጌ ድንግል ]