🕊
[ † እንኳን ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጥንተ በዓለ ሆሳዕና በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † ]
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †
🕊 † ጥንተ በዓለ ሆሳዕና † 🕊
† "ጥንተ በዓል" ማለት በዓሉ : ተአምሩ [የማዳን ሥራው] የተፈፀመበት የመጀመሪያው ቀን ማለት ነው:: በዚህም መሠረት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ከሆሳዕና ጀምሮ እስከ ዸራቅሊጦስ ድረስ ያሉ ዐበይት በዓላትን ሁለት ጊዜ ታከብራለች::
፩ኛው. "ጥንተ በዓል" ሲሆን
፪ኛው. ደግሞ "የቀመር በዓል" ይሠኛል::
መሠረቱ የቅዱሳን ሐዋርያት ቀኖና እና የአባታችን የድሜጥሮስ መንፈሳዊ ቀመር ነው::
ስለሆነም ዓለም ከተፈጠረ በአምስት ሺህ አምሥት መቶ ሠላሳ አራት [5,534] ዓመት : የዛሬ አንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ ሰባ አራት [1,974] ዓመት : ልክ በዛሬዋ ቀን [መጋቢት ፳፪] (22) ስም አጠራሩ ከፍ ከፍ ይበልና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በፍጹም ትሕትና በአህያዋና በውርንጫዋ ጀርባ ላይ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም [ ቤተ መቅደስ ] ገብቷል::
ታላቅ የምስጋና መስዋዕትም ከመላዕክት : ከሐዋርያት : ከሕጻናት : ከአረጋውያን : ከፀሐይ : ከጨረቃ : ከከዋክብት : ከቢታንያ ድንጋዮች . . . በአጠቃላይ ከፈጠረው ፍጥረት ሁሉ ቀርቦለታል:: ጌትነቱንም በገሃድ ገልጧል::
† ከበዓሉ በረከት ይክፈለን:: እኛንም ለጣዕመ ምስጋናው የተዘጋጀን ያድርገን::
🕊
[ † መጋቢት ፳፪ [ 22 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. ቅዱሳን ሐዋርያት : ንጹሐን አርድእትና ቅዱሳት አንስት [የጌታችን ፻፳ [120] ቤተሰቦች]
፪. ቅዱስ ቄርሎስ መንፈሳዊ [የቅድስት ሃገር ኢየሩሳሌም ዻዻስ የነበረ : ንጽሕናው የተመሠከረለት አባት ሲሆን በ፫፻፹፩ [381] ዓ/ም በቁስጥንጥንያ ከተሠበሠቡ ፻፶ [150] ቅዱሳን ሊቃውንት አንዱ ነው:: ብዙ ድርሳናትንም ጽፏል::]
[ † ወርኀዊ በዓላት ]
፩. ቅዱስ ዑራኤል ሊቀ መላእክት
፪. ቅዱስ ሉቃስ ወንጌላዊ
፫. ቅዱስ ደቅስዮስ [የእመቤታችን ወዳጅ
፬. አባ እንጦንዮስ [አበ መነኮሳት]
፭. አባ ዻውሊ የዋህ
† " አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ እጅግ ደስ ይበልሽ:: አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ እልል በዪ:: እነሆ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው:: ትሑትም ሆኖ በአህያም: በአህያይቱ ግልገል በውርንጫይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል::" † [ዘካ.፱፥፱] (9:9)
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖 🕊 💖

እግዚአብሔር በደዌው አልጋ ሳለ ይረዳዋል መኝታውን ሁሉ በበሽታው ጊዜ ያነጥፍለታል እኔስ አቤቱ ማረኝ
#መፃጉዕ
#የአብይ_ፃም_አራተኛ_ሳምንት
በዚህ ሰንበት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ድውያንን መፈወሱ እውራንን ማብራቱ ሽባን መተርተሩ ለምፃሞችን ማንፃቱን የምናስብበት ነው በተለይም በአንድ ሰንበት የ38 ዓመት ታማሚን(መፃጉዕ) በቃሉ መፈወሱን የምናሰብበት ሳምንት ነው፡፡
#የሚሠበከው_ምስባክ
እግዚአብሔር ይረድኦ ውስተ አራተ
ሕማሙ ወይመይጥ ሎቱ ኩሎ ምስባቤሁ
እምደዌሁ አንሰ እቤ እግዚኦ ተሰሃለኒ መዝ 40:3
#የሚነበበው_ወንጌል ፡-ዮሐንስ 5 (John)÷1
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ድውያንን የፈወስ እኛንም ከአጥያት ደዌ ይፈውስን እንዲሁም
ከፌታችን የተደቀነብንን ድዌ ያርቅልን አሜን !!!
#መልካም_ዕለተ_ሰንበት🙏
አጫጭር ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
•➢ 👇 ለማግኘት // 👇
@Enatachn_mareyam

[ † እንኳን ለታላቁ ነቢይና ጻድቅ ቅዱስ ዳንኤል ዓመታዊ በዓለ ዕረፍት በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። † ]
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †
🕊 † ቅዱስ ዳንኤል † 🕊
† ነቢይ ማለት በቁሙ ኃላፍያትን [አልፎ የተሠወረውን ምሥጢር]: መጻዕያትን [ለወደ ፊት የሚሆነውን] የሚያውቅ ሰው ማለት ነው:: ሃብተ ትንቢት የእግዚአብሔር የባሕርይ ገንዘቡ ሲሆን እርሱ ለወደደው በጸጋ ይሰጠዋል:: እነዚህም ከጌታ ሃብተ ትንቢት የተሰጣቸው አባቶችና እናቶች "ቅዱሳን ነቢያት" በመባል ይታወቃሉ::
ዘመነ ነቢያት ተብሎ የሚታወቀው ብሉይ ኪዳን ቢሆንም እስከ ምጽዓት ድረስ ጸጋውን እግዚአብሔር ለፈቀደላቸው አይነሳቸውም:: በሐዋርያት መካከልም ቅዱስ አጋቦስን የመሰሉ ነቢያት ነበሩ:: [ሐዋ.፲፩፥፳፯] (11:27) ቅዱሳን ነቢያት ከእግዚአብሔር እየተላኩ ሰውን ከፈጣሪው እንዲታረቅ ይመክራሉ: ይገስጻሉ::
ከበጐ ሃይማኖታቸውና ንጽሕናቸው የተነሳም እግዚአብሔርን በተለያየ አርአያና አምሳል አይተውታል::
"እስመ በአንጽሖ መንፈስ ርዕይዎ ነቢያት ለእግዚአብሔር: ወተናጸሩ ገጸ በገጽ" እንዳለ አባ ሕርያቆስ:: [ቅዳሴ ማርያም]
የብዙ ነቢያት ፍጻሜአቸው መከራን መቀበል ነው:: እውነትን ስለ ተናገሩ: አንዳንዶቹም በእሳት: አንዳንዶቹም በሰይፍ: አንዳንዶቹም በመጋዝ ተፈትነዋል:: ሌሎቹ ለአናብስት ሲጣሉ ቀሪዎቹ ደግሞ በድንጋይ ተወግረዋል::
ስለዚህም መከራቸው ለቤተ ክርስቲያን መሠረት ተብለዋል:: ጌታም ለደቀ መዛሙርቱ "ሌሎች ደከሙ: እናንተ በድካማቸው ገባችሁ" ብሎ የነቢያቱን መከራ ተናግሯል:: [ዮሐ.፬፥፴፮] (4:36)
ነቢያት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስና እና ድንግል እናቱን ለማየት ብዙ ጥረዋል: ሽተዋልም:: "ብዙ ነቢያትና ጻድቃን እናንተ የምታዩትን ሊያዩ ሹ" እንዳለ ጌታ በወንጌል:: [ማቴ.፲፫፥፲፮] (13:16) [፩ጴጥ.፩፥፲] (1:10) ዛሬ ግን በሰማያት ጸጋ በዝቶላቸው: ክብር ተሰጥቷቸው ሐሴትን ያደርጋሉ::
† ቅዱሳን ነቢያት በዋነኝነት አሥራ አምስቱ አበው ነቢያት: አራቱ ዐበይት ነቢያት: አሥራ ሁለቱ ደቂቀ ነቢያትና ካልአን ነቢያት ተብለው በአራት ይከፈላሉ::
† "አሥራ አምስቱ አበው ነቢያት" ማለት ፦
† ቅዱስ አዳም አባታችን
† ሴት
† ሔኖስ
† ቃይናን
† መላልኤል
† ያሬድ
† ኄኖክ
† ማቱሳላ
† ላሜሕ
† ኖኅ
† አብርሃም
† ይስሐቅ
† ያዕቆብ
† ሙሴና
† ሳሙኤል ናቸው::
† " አራቱ ዐበይት ነቢያት " ፦
† ቅዱስ ኢሳይያስ ልዑለ ቃል
† ቅዱስ ኤርምያስ
† ቅዱስ ሕዝቅኤልና
† ቅዱስ ዳንኤል ናቸው::
† " አሥራ ሁለቱ ደቂቀ ነቢያት " ፦
† ቅዱስ ሆሴዕ
† አሞጽ
† ሚክያስ
† ዮናስ
† ናሆም
† አብድዩ
† ሶፎንያስ
† ሐጌ
† ኢዩኤል
† ዕንባቆም
† ዘካርያስና
† ሚልክያስ ናቸው::
† " ካልአን ነቢያት " ደግሞ :-
† እነ ኢያሱ
† ሶምሶን
† ዮፍታሔ
† ጌዴዎን
† ዳዊት
† ሰሎሞን
† ኤልያስና
† ኤልሳዕ ሌሎችም ናቸው::
† ነቢያት በከተማም ይከፈላሉ::
† የይሁዳ ኢየሩሳሌም :
† የሰማርያ [ እሥራኤል ] ና
† የባቢሎን [ በምርኮ ጊዜ ] ተብለው ይጠራሉ::
† በዘመን አከፋፈል ደግሞ :-
† ከአዳም እስከ ዮሴፍ [የዘመነ አበው ነቢያት]:
† ከሊቀ ነቢያት ሙሴ እስከ ነቢዩ ሳሙኤል [የዘመነ መሳፍንት ነቢያት]
† ከቅዱስ ዳዊት እስከ ዘሩባቤል ያሉት [የዘመነ ነገሥት ነቢያት]:
† ከዘሩባቤል ዕረፍት እስከ መጥምቁ ዮሐንስ ያሉት ደግሞ [የዘመነ ካህናት ነቢያት] ይባላሉ::
ስለ ቅዱሳን ነቢያት በጥቂቱ ይህንን ካልን ወደ ዕለቱ በዓል እንመለስ::
ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳንኤል ቅድመ ልደተ ክርስቶስ በ፮፻ [600] ዓመታት አካባቢ ከይሁዳ ነገሥታት ዘር ተወለደ:: ገና በሕፃንነቱ ናቡከደነጾር ኢየሩሳሌምን አቃጥሎ : ሕዝቡን ማርኮ ወደ ባቢሎን ሲያወርዳቸው አብሮ ወርዷል::
ከሕፃንነቱ ጀምሮ በአምላኩ ፍቅር የታሠረ : ከሦስቱ ጓደኞቹ [አናንያ : አዛርያና ሚሳኤል] ጋር ጾምና ጸሎትን ያዘወትር ነበር:: በዘመኑ እንደርሱ ያለ መተርጉመ-ሕልም አልተገኘምና ለወገኖቹ ሞገሳቸው ነበር::
ኃይለኛውን ንጉሥ ናቡከደነጾርን ጨምሮ የባቢሎንና ፋርስ ነገሥታት ያከብሩት : ይወዱትም ነበር::
ቅዱስ ዳንኤል በጥበብና በሃይማኖት የአሕዛብን አማልክት ድል ነስቷል:: አሕዛብ በተንኮል ወደ አናብስት ጉድጓድ ውስጥ ቢያስጥሉት እግዚአብሔር የአናብስቱን አፍ ዘግቷል:: ዕንባቆምንም አምጥቶ መግቦታል::
ቅዱስ ዳንኤል የብሉይ ኪዳኑ "አቡቀለምሲስ" ይባላል:: ስለ ጌታችን የማዳን ሥራና ስለ ዳግም ምጽዐቱ በግልጥ ተናግሯል:: ሐረገ ትንቢቱም ፲፪ [12] ምዕራፍ ነው:: የዘመኑ አይሁድ ክርስቶስ ገና አልተወለደም ለማለት ዳንኤልን ጠልተውታል::
ታላቁ ነቢይና ጻድቅ ቅዱስ ዳንኤል እስራኤል ወደ ሃገራቸው ሲመለሱ አብሯቸው አልመጣም:: ከ70 ዓመታት በላይ በጸጋ ትንቢት ኑሮ እዛው ባቢሎን ውስጥ አርፏል::
† ፈጣሪ ከበረከቱ ለሁላችን ያድለን::
† በዚህች ቀን ክፉዎች አይሁድ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ይገድሉ ዘንድ በቤተ ቀያፋ መከሩ::
† እርሱ ቸሩ አምላክ ከክፉ መካሪዎች ይሠውረን::
🕊
[ † መጋቢት ፳፫ [ 23 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩.ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳንኤል [የስሙ ትርጓሜ- እግዚአብሔር ፈራጅ ነው ማለት ነው::
[ † ወርኀዊ በዓላት ]
፩. ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት
፪. ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕታት
፫. ቅዱስ ሰሎሞን ንጉሠ እስራኤል
፬. አባ ጢሞቴዎስ ገዳማዊ
፭. አባ ሳሙኤል
፮. አባ ስምዖን
፯. አባ ገብርኤል
† " የዚያን ጊዜም ንጉሡ አዘዘ:: ዳንኤልንም አምጥተው በአንበሶች ጉድጓድ ጣሉት . . . ድንጋይም አምጥተው በጉድጓዱ አፍ ላይ ገጠሙት . . . በነጋውም ንጉሡ ማልዶ ተነሳ . . . ወደ ዳንኤል በቀረበ ጊዜ በኀዘን ቃል ጠራው . . . ዳንኤልም ንጉሡን . . . በፊቱ ቅንነት ተገኝቶብኛልና . . . አምላኬ መልዐኩን ልኮ የአንበሶቹን አፍ ዘጋ:: አንዳችም አልጐዱኝም አለው . . . ዳንኤልም ከጉድጓድ ወጣ:: በአምላኩም ታምኖ ነበርና አንዳች ጉዳት አልተገኘበትም::" † [ዳን.፮፥፲፮-፳፫]

† እንኳን ለጻድቁ አባታችን ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ዓመታዊ በዓለ ፅንሰት በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። †
🕊 💖 🕊
ሰዳዴ ጽልመት አባታችን ቅዱስ ተክለሐይማኖት
"...ከበዐቱ ሳይወጣ ሌሊትና ቀን ቆመ። አልተቀመጠም ወደ ግራና ወደ ቀኝም አልተንቀሳቀሰም። ውኃም ቅጠልም ቢሆን ከቅዳሜና ከእሑድ በቀር በዚያ ወራት ምንም ምን አልቀመሰም። እህል ግን ከመነኰሰ ጀምሮ እስከ ዕለተ ሞቱ ድረስ አልቀመሰም። ፀሓይንም ጨረቃንም ከዋክብትን በጋና ክረምትንም ቡቃያና አበባንም ፍሬውንም አላየም። ዓይኖች ሳሉት እንደ ዕውር ጆሮዎች ሳሉት እንደ ደንቆሮ የሚናገር የተከናወነ አንደበት እያለው እንደ ዲዳ ሆነ። ከምስጋና በቀር ምንም ምን አይናገርም። ሌሊትና ቀንም እግዚአብሔርን አመሰገነ። ዓለምንም እንደ ትቢያና እንደ ጉድፍ ቆጠረው ከክርስቶስ ጋር እንደተሰቀለ ሆነ ልቡናውም ዘወትር ወደ ዓየር የተመሰጠ ነበር።
እንዲህ ባለም ገድል ብዙ ዘመን [፳፪ [22] ዓመታት] ኖረ። ቁመትንም ካበዛ ወዲህ አንዲቱ የእግሩ አገዳ ተሰበረች ደቀ መዛሙርቱ አንሥተው አክብረው በሰበን ጠቅልለው ከመንበሩ እግር በታች ቀበሯት። ከዚህም ባንዲት እግሩ ሰባት ዓመት ቆመ። ከነዚህም አራቱን ዓመት ውሃው አልጠጣም"።
[ ገድለ ተክለ ሃይማኖት ]
🕊 💖 🕊
የኢቲሳ አንበሳ ፥ የኢትዮጵያ ብርሃን ፥ ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ሐራሴ ወንጌል ፥ የጣኦታት ጠላት ፥ ጣኦታትን የሰባበሩ ፥ የአምላካቸውን ስም ያስከበሩ ፥ ሐዲስ ሐዋርያ በረከታቸው ይደርብን ምልጃ ጸሎታቸው አይለየን፡፡

†
💖 [ የትሕርምት ሕይወት ! ] 💖
🕊 💖 🕊
🍒
[ " ተጋድሎአችሁን እስከ መጨረሻ ለመፈጸም ትጉ ! ... " ]
🕊 💖 🕊
" ተወዳጆች ሆይ ! እናንተ በእግዚአብሔር ጸጋ ክርስቲያን የሆናችሁ አይደላችሁምን ?
ስለዚህ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሕግጋትን ጠብቁ፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ ፦ “ እግዚአብሔር ለሰው ፊት እንዳያደላ ፥ ነገር ግን በአሕዛብ ሁሉ እርሱን የሚፈራና ጽድቅን የሚያደርግ በእርሱ የተወደደ እንደ ሆነ በእውነት አስተዋልሁ” [የሐዋ.፲፥፴፬] ብሎ የተናገረውን ቃል ልብ በሉ፡፡
ስለዚህ ክርስቲያን በመሆናችን ብቻ እንዳንታበይ እንጠንቀቅ፡፡ ይልቁኑ እርሱን በመፍራት የትሕርምትን ሕይወት ገንዘባችን አድርገን ልንመላለስ ይገባናል፡፡
እኛ በጽድቅ ሕይወት የምንደክመው መሠረት ለመጣል ብቻ አይደለም፡፡ ሕንፃውን ለመጨረስ ነው እንጂ፡፡ ሕንፃን የሚገነባ ሰው ድካሙ ሕንፃው እስኪጠናቀቅ ድረስ ነው፡፡ ያለበለዚያ መድኅን ዓለም ክርስቶስ ፦ “ከእናንተ ግንብ ሊሠራ የሚወድ ለመደምደሚያ የሚበቃ ያለው እንደ ሆነ አስቀድሞ ተቀምጦ ኪሳራውን የማይቈጥር ማን ነው? ያለዚያ መሠረቱን ቢመሠርት ፥ ሊደመድመውም ቢያቅተው ፥ ያዩት ሁሉ ይህ ሰው ሊሠራ ጀምሮ ሊደመድመው አቃተው ብለው ሊዘብቱበት ይጀምራሉ።” [ሉቃ.፲፬፥፳፰-፴] ብሎ እንዳስተማረው ይሆንብናል፡፡
የምደራዊ ወታደር የጦርነት ቆይታው አጭር ነው፡፡ ነገር ግን የአንድ ተሐራሚ ተጋድሎ እስከ ዕድሜ ፍጻሜው ነው፡፡ እንዲህም ስለሆነ ተጋድሎን በፍጹም ጽናት ትጋትና ትዕግሥት ሊጀመር ይገባናል፡፡
ተወዳጆች ሆይ ! አንበሳን መግደል ካሻችሁ እናንተን አግኝቶ እንደ ሸክላ ዕቃ እንዳይሰብራችሁ አድፍጣችሁ ትጠብቁታላችሁ እንጂ ፊት ለፊት አትጋፈጡትም፡፡ እንዲሁ ባሕር ውስጥ ብትሰጥሙ ደረቅ ምድር እስከታገኙ ድረስ ነፍሳችሁን ለማዳን ትጥራላችሁ እንጂ በውኃ ውስጥ ሰጥሞ ለመሞት እጅ አትሰጡም፡፡
እጅ ከሰጣችሁ ግን በውኃ ውስጥ እንደተጣለ ድንጋይ ሰጥማችሁ ትቀራላችሁ፡፡ ስለዚህ ወንድሞቼ ሆይ ! ጠላት ዲያብሎስ ድል እንዳይነሣችሁና በእናንተ ላይ እንዳይሰለጥን እንዲሁም ከድል አክሊል ይልቅ ውርደትን እንዳትለብሱ ተጋድሎአችሁን እስከ መጨረሻ ለመፈጸም ትጉ፡፡"
🕊
[ ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ]

💛
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
🕊 ዐቢይ ጾም [ ጾመ እግዚእ ] 🕊
▷ " ከ ጨ ለ ማ መ ው ጣ ት ! "
[ 💖 በብፁዕ አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ 💖 ]
[ 🕊 ]
----------------------------------------------------
" መብራትንም አብርተው ከዕንቅብ በታች አይደለም እንጂ በመቅረዙ ላይ ያኖሩታል በቤት ላሉት ሁሉም ያበራል።
መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ።" [ ማቴ.፭፥፲፭ ]
" ሁላችሁ የብርሃን ልጆች የቀንም ልጆች ናችሁና። እኛ ከሌሊት ወይም ከጨለማ አይደለንም"
[ ፩ ተሰሎ.፭፥፭ ]