🕊
[ † እንኳን ለሰማዕቱ ቅዱስ ሰለፍኮስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † ]
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †
🕊 † ሰማዕቱ ሰለፍኮስ † 🕊
† ቅዱስ ሰለፍኮስ በዘመነ ሰማዕታት የነበረ ክርስቲያን ወጣት ነው:: በወቅቱ ያ የጭንቅና የመከራ ዘመን ከመምጣቱ በፊት በተቀደሰ ጋብቻ ለመኖር አስጠራጦኒቃ የምትባል ደግ የሆነች ክርስቲያናዊት ወጣት አጭቶ ነበር::
በዕጮኝነት ዘመናቸው ጾምን: ጸሎትንና ንጽሕናን በመምረጣቸው ያየ ሁሉ ያደንቃቸው ነበር::
ታዲያ የሠርጋቸው ቀን እየቀረበ ሲመጣ ያ የመከራ ዘመን [ዘመነ ሰማዕታት] ጀመረ::
ሁለቱ ንጹሐን ወጣት ክርስቲያኖች ተመካከሩና ወሰኑ:: በምክራቸውም መሠረት ሁለቱም ከነ ድንግልናቸው ሰማዕትነትን ለመቀበል ተዘጋጁ:: በዚች ዕለትም ስለ ቀናች ሃይማኖትና ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፍቅር ከብዙ ስቃይ በሁዋላ በከሃዲው ንጉሥ ትዕዛዝ ቅዱስ ሰለፍኮስ በሰማዕትነት አልፏል::
† ከቅዱሱ ሰማዕት በረከት አምላከ ቅዱሳን ያድለን::
🕊
[ † መጋቢት ፲፭ [ 15 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. ቅዱስ ሰለፍኮስ ሰማዕት
፪. እናታችን ቅድስት ሣራ ጻድቅት [ግብፃዊት]
፫. አባ ሕልያስ ሰማዕት
፬. ቅዱስ ጊዮርጊስ ሐዲስ
[ † ወርሐዊ በዓላት ]
፩. ቅዱስ ቂርቆስና እናቱ ኢየሉጣ
፪. ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ አፈ በረከት
፫. ቅዱስ ሚናስ ግብፃዊ
፬. ቅድስት እንባ መሪና
፭. ቅድስት ክርስጢና
† " ሰው ሁሉ እንደ እኔ ሊሆን እወዳለሁና:: ነገር ግን እያንዳንዱ ከእግዚአብሔር ለራሱ የጸጋ ስጦታ አለው:: አንዱ እንደዚህ ሁለተኛውም እንደዚያ:: ላላገቡና ለመበለቶች ግን እላለሁ:: እንደ እኔ ቢኖሩ ለእነርሱ መልካም ነው:: ነገር ግን በምኞት ከመቃጠል መጋባት ይሻላልና ራሳቸውን መግዛት ባይችሉ ያግቡ::" † [፩ቆሮ.፯፥፯] [7:7]
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
† † †
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
💖 🕊 💖

[ † እንኳን ለጻድቁ ሊቀ ጳጳሳት አባ ሚካኤል ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † ]
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †
🕊 † አባ ሚካኤል ሊቀ ጳጳሳት † 🕊
† አባ ሚካኤል በትውልዳቸው ግብጻዊ ሲሆኑ ገና በሕፃንነታቸው ገዳማዊ ሕይወትን መርጠው ለዓመታት በተጋድሎ ገዳመ አስቄጥስ ውስጥ ኑረዋል:: በዘመኑ ግብጽ ሊቀ ጳጳሷ አርፎባት ነበርና በሱባዔ እያሉ "አባ ሚካኤልን ሹሙት" የሚል ቃል ከሰማይ ሰምተው "እንሹምህ" አሉት:: "እንቢ" ቢላቸው ግድ ብለው አስረው ሹመውታል::
አባ ሚካኤል በመንበረ ማርቆስ ላይ እረኝነት [ጵጵስና] ተሹሞ ጭንቅ ጭንቅ መከራዎችን ተቀብሏል:: በወቅቱ የነበረው የግብጽ ከሊፋ [አባቶቻችን ክፉ ሰው ማለት ነው ይላሉ] አባ ሚካኤልን አሥሮ በሕዝቡ ፊት ይደበድባቸው ነበር::
ከመከራው ብዛት የተነሳ በርካቶቹ ተገደሉ: ከ ፳ ሺህ [20,000] በላይ ምዕመናን ሃይማኖታቸውን ካዱ::
ይህንን የሰሙት የወቅቱ የኢትዮጵያ ንጉሥ በመንፈሳዊ ቅንዐት ፻ሺህ [100,000] ፈረሰኛ: ፻ሺህ [100,000] በበቅሎ: ፻ሺህ [100,000] ሠራዊት በግመል ጭነው ወደ ግብጽ ወርደው ከሊፋውን አስጨንቀው የግብጽን ክርስቲያኖች ከመከራ ታድገዋል::
አባ ሚካኤልም ከእሥር ከተፈቱ በኋላ የካዱ ምዕመናንን ለመመለስ ብዙ ደክመዋል:: ተሳክቶላቸውማል:: ጻድቁ ሊቀ ጳጳሳት ከዓመታት ተጋድሎ በኋላ በዚህች ቀን አርፈዋል::
† ፈጣሪ ከበረከታቸው አይንሳን::
🕊
[ † መጋቢት ፲፮ [ 16 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. ቅዱስ አባ ሚካኤል ሊቀ ጳጳሳት
[ † ወርኀዊ በዓላት ]
፩. ኪዳነ ምሕረት [የሰባቱ ኪዳናት ማሕተም
፪. ቅድስት ኤልሳቤጥ [የመጥምቁ ዮሐንስ እናት]
፫. ቅዱስ ገብረ ማርያም ጻድቅ ንጉሠ ኢትዮጵያ [የቅዱስ ላሊበላ ወንድም]
፬. ቅዱስ አኖሬዎስ ንጉሥ ጻድቅ
፭. አባ አቡናፍር ገዳማዊ
፮. አባ ዮሐንስ ወንጌሉ ዘወርቅ
፯. አባ ዳንኤል ጻድቅ
† " በድካም : አብዝቼ በመገረፍ : አብዝቼ በመታሠር : አትርፌ በመሞት ብዙ ጊዜ ሆንሁ:: በድካምና በጥረት : ብዙ ጊዜም እንቅልፍ በማጣት : በራብና በጥም : ብዙ ጊዜም በመጦም : በብርድና በራቁትነት ነበርሁ . . . የቀረውን ነገር ሳልቆጥር ዕለት ዕለት የሚከብድብኝ የአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ አሳብ ነው::" † [፪ቆሮ. ፲፩፥፳፫-፳፰]

[ † በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! † ]
🕊 † አልዓዛር ሐዋርያ † 🕊
† ቅዱስ አልዓዛር በሃገረ ቢታንያ ከእህቶቹ ማርያና ማርታ ጋር ይኖር ነበር:: ሦስቱም ድንግልናቸውን ጠብቅው ጌታችንን ያገለግሉት ነበርና አልዓዛርን ከ ፸፪ [ 72 ] ቱ አርድእት ማርያና ማርታን ደግሞ ከ፴፮ [ 36 ] ቱ ቅዱሳት አንስት ቆጥሯቸዋል::
በወንጌል ጌታችን ይወዳቸው እንደነበር ተገልጧል:: [ዮሐ.፲፩፥፫] [11:3] ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲወድ የሚያበላልጥ ሆኖ አይደለም:: ይልቁኑ በምሥጢር እነርሱ ተወዳጅ የሚያደርጋቸውን ሥራ ይሠሩ እንደነበር ሲነግረን ነው እንጂ::
ቅዱስ መጽሐፍ እንደ ነገረን ጌታችን በነ አልዓዛር ቤት በእንግድነት ይስተናገድ ነበር:: [ዮሐ.፲፪፥፩] [12:1] በመጨረሻዋ ምሴተ ሐሙስም ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ለሐዋርያቱ ያቀበላቸው በእነዚህ ቅዱሳን ቤት ውስጥ ነው::
ቅዱስ አልዓዛር በጽኑዕ ታሞ በዚሕች ቀን አርፏል:: ቅዱሳት እህቶቹ ማርያና ማርታ ከታላቅ ለቅሶ ጋር ዕለቱኑ ቀብረውታል:: [ዮሐ.፲፩] [11]
† ቸር ጌታችን ክርስቶስ ከ4 ቀናት በሁዋላ ሊያስነሳው ይመጣልና ከበረከቱ ይክፈለን:: [ይቆየን]
🕊
[ † መጋቢት ፲፯ [ 17 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. ቅዱስ አልዓዛር ጻድቅ ሐዋርያ
፪. ቅዱስ ቴዎቅሪጦስ አናጉንስጢስ [ሰማዕት]
፫. ቅዱስ ተላስስ ሰማዕት
፬. ቅዱስ ዮሴፍ ኤዺስ ቆዾስ
፭. ቅዱስ ጊዮርጊስ መስተጋድል
[ † ወርኀዊ በዓላት ]
፩. ቅዱስ እስጢፋኖስ ሊቀ ዲያቆናት [ ቀዳሜ ሰማዕት ]
፪. ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ [ ወልደ ዘብዴዎስ ]
፫. ቅዱስ ኤዺፋንዮስ ዘቆዽሮስ
፬. ቅዱሳን አበው መክሲሞስና ዱማቴዎስ
፭. አባ ገሪማ ዘመደራ
፮. አባ ዸላሞን ፈላሢ
፯. አባ ለትጹን የዋህ
† " ጌታ ኢየሱስም :- ' ትንሳኤና ሕይወት እኔ ነኝ:: የሚያምንብኝ ቢሞት እንኩዋ ሕያው ይሆናል:: የሚያምንብኝም ሁሉ ለዘለዓለም አይሞትም:: ይህን ታምኛለሽን?' አላት:: እርስዋም [ማርታ] :- 'አዎን ጌታ ሆይ: አንተ ወደ ዓለም የሚመጣው ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆንህ እኔ አምናለሁ::' አለችው::"† [ዮሐ.፲፩፥፳፭-፳፯] (11:25-27)

[ † እንኳን ለቅዱስ ኤስድሮስ ሰማዕት ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † ]
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †
🕊 † ቅዱስ ኤስድሮስ † 🕊
† ሰማዕትነት በክርስትና ለሃይማኖት የሚከፈል የመጨረሻው ዋጋ [መስዋዕትነት] ነው:: ሰው ለፈጣሪው ሰውነቱን ሊያስገዛ: ሃብት ንብረቱን ሊሰጥ ይችላል:: ከስጦታ በላይ ታላቅ ስጦታ ግን ራስን አሳልፎ መስጠት ነው::
ራስን መስጠት በትዳርም ሆነ በምናኔ ውስጥ ይቻላል:: የመጨረሻ ደረጃው ግን ሰማዕትነት ነው::
"አማን መነኑ ሰማዕት ጣዕማ ለዝ ዓለም:: ወተዓገሡ ሞተ መሪረ በእንተ መንግስተ ሰማያት::" እንዳለው ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ
ሰማዕትነት ማለት መራራውን ሞት ስለ ፍቅረ እግዚአብሔር ሲሉ መታገስ ነው::
እርሱ ቅሉ መድኃኒታችን ክርስቶስ የሰማይና የምድር ጌታ ሲሆን ኃፍረተ መስቀልን ታግሦ ሙቶልን የለ!
በዓለም ያሉ ብዙ እምነቶች ስለ መግደል በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ያስተምራሉ:: ክርስትና ግን መሞትን እንጂ መግደልን የሚመለከት ሕግ የለውም::
እርሱ ባለቤቱ "ጠላቶቻችሁን ውደዱ:: የሚረግሟችሁን መርቁ:: ስለሚያሳድዷችሁ ጸልዩ::" ብሎናልና:: [ማቴ.፭፥፵፬] (5:44) ነገር ግን ዕለት ዕለት ራሳችንን በሃይማኖትና በምግባር ካልኮተኮትነው ክርስትና በአንድ ጀምበር ፍጹም የሚኮንበት እምነት አይደለምና በፈተና መውደቅ ይመጣል::
በተለይ የዘመኑ ክርስቲያን ወጣቶች ልናስተውል ይገባናል:: የቀደሙ ወጣት ሰማዕታት ዜና የሚነገረን እንድንጸና ነውና::
ቤተ ክርስቲያናችን ኢትዮዽያዊውን የጐንደር ዘመን ሊቅ ጨምሮ በዚህ ስም የምትዘክራቸው አያሌ ቅዱሳንና ሊቃውንት አሏት::
ዛሬ የምናከብረው ሰማዕቱ ቅዱስ ኤስድሮስ በዘመነ ሰማዕታት የነበረ: ቅዱስ ፃና የሚባል ደግ ጉዋደኛ የነበረው: ሁለቱንም እናቶቻቸው እንደሚገባ ያሳደጉዋቸው የ፫ (3) ኛው መቶ ክ/ዘመን ክርስቲያኖች ነበሩ::
በወጣትነት ዘመናቸው በድንግልና: ቅዱስ ፃና የሠራዊት አለቃ: ቅዱስ ኤስድሮስ ደግሞ የልብስ ዝግጅት ባለሙያ ነበሩ:: ከሚያገኙት ገቢ ለዕለት ጉርስ ብቻ እያስቀሩ ለነዳያን ይመጸውቱ ነበር::
በመከራ ዘመን [ዘመነ-ሰማዕታት] ቅዱሳኑ ያላቸውን ሁሉ ለነዳያን አካፍለው በክርስቶስ ስም መሞትን መርጠዋል::
በዚህች ቀንም አስቀድሞ ቅዱስ ኤስድሮስ አንገቱን ተሰይፎ የክብርን አክሊል ተቀዳጅቷል::
† ፈጣሪ ከሰማዕቱ ክብር ያድለን::
🕊
[ † መጋቢት ፲፰ [ 18 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. ቅዱስ ኤስድሮስ ሰማዕት
[ † ወርሐዊ በዓላት ]
፩. ቅዱስ ፊልዾስ ሐዋርያ
፪. አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ሰባኬ ሃይማኖት [ረባን]
፫. አቡነ አኖሬዎስ ዘደብረ ጽጋጋ
፬. ማር ያዕቆብ ግብፃዊ
† " የጭንቀት ቀን ሳይመጣ በጉብዝናህ ወራት ፈጣሪህን አስብ:: ደስ አያሰኙም የምትላቸውም ዓመታት ሳይደርሱ: ፀሐይ: ጨረቃና ከዋክብትም ሳይጨልሙ . . . አፈርም ወደ ነበረበት ምድር ሳይመለስ: ነፍስም ወደ ሰጠው ወደ እግዚአብሔር ሳይመለስ ፈጣሪህን አስብ::
ሰባኪው:- "ከንቱ: ከንቱ: ሁሉ ከንቱ ነው" ይላል::" † [መክ.፲፪፥፩-፱] (12:1-9)
† " ዳሩ ግን የነገር ሁሉ መጨረሻ ቀርቦአል:: እንግዲህ እንደ ባለ አእምሮ አስቡ:: ትጸልዩም ዘንድ በመጠን ኑሩ:: ፍቅር የኃጢአትን ብዛት ይሸፍናልና ከሁሉ በፊት እርስ በርሳችሁ አጥብቃችሁ ተዋደዱ::" † [፩ዼጥ.፬፥፯] (4:7)

[ † እንኳን ለቅዱሳኑ የአስከናፍር ቤተሰብ ዓመታዊ በዓለ ዕረፍት በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † ]
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †
🕊 † ቅዱስ አስከናፍር † 🕊
† ከብዙ መቶ ዓመታት በፊት አስከናፍር የሚባል ደግ ክርስቲያን ማርታ የምትባል በሃይማኖትና ምግባር የምትመስለውን ሴት አግብቶ ይኖር ነበር:: እንደ ሕጉና ሥርዓቱ በሥጋ ወደሙ ተወሥነው እንግዳ ቢቀበሉ: ነዳያንን ቢያበሉ እግዚአብሔር ጸሎታቸውን ሰምቶ አርቃድዮስና ዮሐንስ የሚባሉ ልጆችን ሰጣቸው::
አስከናፍርና ማርታ ልጆቻቸውን ጥበብ መንፈሳዊን [ቃለ እግዚአብሔርን] አስቀድመው አስተምረው : ሥጋዊ ጥበብን እዲማሩላቸው ቢልኩዋቸው መንገድ ላይ መርከብ ተሰብሮባቸው ብዙዎቹ ሲሞቱ ወንድማማቾች ግን የመርከብ ስባሪ ወደተለያየ ቦታ አድርሷቸዋል::
አርቃድዮስና ዮሐንስ "ወደ ዓለም አንመለስም" ብለው መነኑ:: ወላጆቻቸው የሆነውን ሰምተው በጭንቅ ሃዘንና ለቅሶ ለብዙ ጊዜ ኑረዋል:: ከዘመናት በሁዋላ ግን የልጆቻቸውን መኖር በራዕይ የተረዱት አስከናፍርና ማርታ ሃብት ንብረታቸውን ለነዳያን አካፍለው ወደ በርሃ መንነው ሔደዋል::
ጥበበኛ እግዚአብሔር አራቱንም አገናኝቷቸው ለብዙ ዓመታት በአንድ ገዳም ውስጥ ተጋድለዋል:: በዚሕች ዕለትም አራቱም ወደ ሰማያዊው ሠርግ ተጠርተዋል::
† ቸር አምላክ ከቅዱሱ ቤተሰብ በረከት ይክፈለን::
🕊
[ † መጋቢት ፲፱ [19] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. ቅዱስ አስከናፍር : ሚስቱ ማርታ : ልጆቹ አርቃድዮስና ዮሐንስ
፪. ቅዱስ አርስጥቦሎስ ሐዋርያ [ከ፸፪ [72]ቱ አርድእት-የቅዱስ ዻውሎስ ደቀ መዝሙር]
፫. ሰባቱ ቅዱሳን ሰማዕታት [ከተለያየ ቦታ ተሰብስበው በክርስቶስ ስም የሞቱ)]
[ † ወርሐዊ በዓላት ]
፩. ቅዱስ ገብርኤል ሊቀ መላእክት
፪. ቅዱስ ኤስድሮስ ሰማዕት
፫. አቡነ ዓቢየ እግዚእ ጻድቅ
፬. አቡነ ስነ ኢየሱስ
፭. አቡነ ዮሴፍ ብርሃነ ዓለም
† " እንግዲህ ወንዶች በሥፍራ ሁሉ አለ ቁጣና አለ ክፉ አሳብ የተቀደሱትን እጆች እያነሱ እንዲጸልዩ እፈቅዳለሁ:: እንዲሁም ደግሞ ሴቶች በሚገባ ልብስ ከእፍረትና ራሳቸውን ከመግዛት ጋር ሰውነታቸውን ይሸልሙ:: እግዚአብሔርን እንፈራለን ለሚሉት ሴቶች እንደሚገባ መልካም በማድረግ እንጂ በሽሩባና በወርቅ: ወይም በዕንቁ: ወይም ዋጋው እጅግ በከበረ ልብስ አይሸለሙ::" † [፩ጢሞ.፪፥፰] (2:8)

[ † እንኩዋን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አልዓዛርን ከሞት ላስነሳበት ደግ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ † ]
🕊 † ሐዋርያ ቅዱስ አልዓዛር † 🕊
ከቀናት በፊት ጻድቅና ሐዋርያ ቅዱስ አልዓዛር አረፈ ብለን ነበር:: ለስም አጠራሩ ስግደት: ክብር: ጌትነት ይድረሰውና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ አልዓዛር ባረፈ በአራተኛው ቀን ወደ ቢታንያ ደረሰ::
ማርታ ቀድማ ወጥታ ከእንባ ጋር ተቀበለችው::
"አዳም ወዴት ነህ" ያለ [ዘፍ.፫፥፲] (3:10) የአዳም ፈጣሪ "አልዓዛርን ወዴት ቀበራችሁት" አለ:: ቸርነቱ: ባሕርዩ ያራራዋልና ማርያም ስታለቅስ ባያት ጊዜ አብሮ አለቀሰ::
ከዚያም በባሕርይ ስልጣኑ "አልዓዛር! አልዓዛር!" ብሎ አልዓዛርን አስነሳው:: ይሕች ተአምርም በአይሁድ ዘንድ ግርምት ሆነች:: ለጌታም የሞት ምክንያት አደረጉዋት:: ቅድስት ቤተ ክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱስን መሠረት አድርጋ እንዲህ ታስተምራለች:: [ዮሐ.፲፩፥፩] (11:1-ፍጻሜው)
ቅዱስ አልዓዛር ጌታችን ካስነሳው በሁዋላ በበዓለ ሃምሳ መንፈስ ቅዱስን ተቀብሎ [ቁጥሩ ከ ፸፪ቱ (72ቱ) አርድእት ነውና] : ለ ፵ [40] ዓመታት ወንጌልን አስተምሮ : በ፸፬ [74] ዓ/ም አካባቢ ቆዽሮስ ውስጥ አርፏል::
የጌታችን ቸርነቱ : የአልዓዛር በረከቱ ይድረሰን::
🕊
[ † መጋቢት ፳ [20] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. ቅዱስ አልዓዛር ጻድቅ ሐዋርያ [የጌታ ወዳጅ]
፪. ቅድስትና ብጽዕት ሰማዕት አስጠራጦኒቃ [ከታላላቅ ሰማዕታት አንዱዋ]
፫. ቅዱሳን ሰማዕታት [የቅ/አስጠራጦኒቃ ማሕበር]
፬. እናታችን ቅድስት ጽጌ-ሥላሴ [ኢትዮዽያዊት]
፭. ቅዱስ አስቃራን ሰማዕት
፮. አባ ሚካኤል ሊቀ ዻዻሳት
[ † ወርኀዊ በዓላት ]
፩. ቅዱስ ቴዎድሮስ ሊቀ ሠራዊት [ሰማዕት]
፪. ቅዱስ ዮሐንስ ሐፂር
፫. ቅዱስ አክሎግ ቀሲስ
፬. ቅዱስ አፄ ካሌብ ጻድቅ (ንጉሠ ኢትዮዽያ)
፭. አባ አሞንዮስ ዘሃገረ ቶና
፮. ቅድስት ሳድዥ የዋሒት
" ጌታ ኢየሱስም 'ብታምኚስ የእግዚአብሔርን ክብር እንድታዪ አልነገርሁሽምን?' አላት . . . ይሕንም ብሎ በታላቅ ድምጽ 'አልዓዛር ሆይ ወደ ውጭ ና' ብሎ ጮኸ:: የሞተውም እጆቹና እግሮቹ በመግነዝ እንደ ተገነዙ ወጣ:: ፊቱም በጨርቅ እንደ ተጠመጠመ ነበረ:: ጌታ ኢየሱስም 'ፍቱትና ይሂድ ተውት' አላቸው:: " [ዮሐ.፲፩፥፵] (11:40-44)
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬