†
🌼 [ እንኳን አደረሳችሁ ! ] 🌼
▬▬▬▬▬▬ † ▬▬▬▬▬▬
❝ አንብር መስቀልዬ በዲበ መስቀል ❞
[ ግሸን ደብረ ከርቤ ማርያም ]
🕊
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡
ግሸን ደብረ ከርቤ ቅድስት ማርያም በደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት በአምባሰል ወረዳ ከደሴ ከተማ ፹፪ ኪ/ሜ ርቃ ከፍ ብሎ በሚታይ መስቀለኛ ተራራ ላይ ትገኛለች። በተለይ አቡነ ሚካኤል ጳጳስ ዘጎንደር መንፈሳዊ መናኝ በመባል የሚታወቁት ደገኛ አባት ባሠሩት ከቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ሆነው የተራራውን ተፈጥሮአዊ አቀማመጥ ሲመለከቱ አንድ ጥሩ አናጢ ከጥሩ እንጨት ባማረ ጌጥ ጠርቦ የሠራውን ግሩም የእጅ መስቀል ይመስላል።
በአቅራቢያዋም ከሚገኙ በርካታ ታሪካውያንና ጥንታውያን መካናት መካከልም ፦ ጥንታዊው የደብረ ሐይቅ አቡነ ኢየሱስ ሞዓ ገዳም ፣ የድጓ ምስክር የነበረው ደብረ እግዚአብሔር ፣ የቅኔ ትምህርት ምንጭ የሆነው ዋድላ/ደላንታ ፣ የ፲፱ ኛው ክፍለ ዘመን የሃይማኖት ውሳኔ የተደረገበት የቦሩ ሜዳ ሥላሴ ፣ የውጫሌ ውል የተፈረመበት የውጫሌ ከተማ ፣ የመቅደላ አምባ ፣ የበሽሎ ወንዝ ሸለቆና ሌሎችም ናቸው።
ግሸን ደብረ ከርቤ የሚለውን ስያሜ ከማግኘቷ በፊት በልዩ ልዩ ታሪካዊና ምሥጢራዊ ምክንያቶች ደበረ ነገሥት ፣ ደብረ ነጎድጓድ ፣ ደብረ እግዚአብሔር በሚባሉ ስሞች ትጠራ ነበር፡፡ ግሸን ደብረ ከርቤ መጀመሪያ የተመሰረተችው በዘመነ አክሱም በዐፄ ካሌብ ዘመነ መንግሥት ነበር፡፡
ዐፄ ካሌብ በየመን በሩ ክርስቲያኖች እየደረሰባቸው ከነበረው መከራ ለመታደግ ወደ ናግራን ዘምተው ድል አድርገው መንግሥት አጽንተው ሲመለሱ በዚያ ይኖሩ የነበሩ አባ ፈቃደ ክርስቶስ የሚባሉት መነኰስ አብረው ተመልሰዋል።
አባ ፈቃደ ክርስቶስም ከናግራን ሲመለሱ ሁለት ጽላቶችን ወደ ኢትዮጵያ በማምጣት የበሽሎ ወንዝን ተሻግረው ወደ ግሸን ተራራ ጫፍ ለመውጣት የአምባውን ዙሪያ ሲመለከቱ በገደሉ ላይ ንብ ሰፎ ማሩ ሲንጠባጠብ አይተው የአምላክን ስጦታ ለማድነቅ በጥንታውያን ግእዝና ዓረብኛ ቋንቋዎች ቦታውን "አምባ " "አሰል " [ አምባሰል ] ብለው ጠሩት። ትርጉሙም "የማር አምባ " ማለት ነው እስከ አሁንም አካባቢው አምባሰል እየተባለ ይጠራል።
አባ ፈቃደ ክርስቶስም ይዘዋቸው የመጡትን ሁለት ጽላቶች ወደ አምባው በማስገባት ሁለት ቤተ ክርስቲያን ሠርተው ደብሩን መሥርተዋል። ይኽንኑ ታሪክ በመከተልም ይመስላል በጉዲት ጦርነት የስደት ዘመን የአክሱሙ ንጉሥ ድል ነዓድ በዘጠነኛው ክፍለ ዘመን ከአምባሰል ባሻገር ከሐይቅ ባሕር አጠገብ ባለው ተራራ ላይ ደብረ እግዚአብሔርን መሥርቶ ኖሯል።
ከዚህም በኋላ መንግሥት ከደብረ እግዚአብሔር በመራ ተክለሃይማኖት አማካኝነት ወደ ላስታ ሲሻገር የደብረ ከርቤ ክብር በላስታ ዘመንም አልተቋረጠም፡፡ በቅዱስ ላልይበላል ዘመን እንደተፈለፈሉ የሚነገርላቸው ጅምር ዋሻዎች አሁንም በደብረ ከርቤ ግሸን ማርያም ይገኛሉ። በዚህ ዘመንም ደብረ ከርቤ የነገሥታት መናኸሪያ የሊቃውንት መገኛ የቤተ ክርስቲያን የሐዲስ ኪዳን ሥርዓት መፈጸሚያ ቅድስት ቦታ ነበረች።
በመጨረሻም በዐፄ ዘርዓ ያዕቆብ ዘመነ መንግሥት የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ መስቀል መቀመጫ ሆናለች። ፲፬፻፵፮ ዓ/ም መስከረም ፳፩ ዓፄ ዘርአ ያዕቆብ ግማደ መስቀሉንና ሌሎች ብዙ የቤተ ክርስቲያን ንዋያተ ቅድሳትን አምጥተው በግሸን ደብረ ከርቤ ማርያም አስቀመጡ፡፡
የግማደ መስቀል በረከት የእመቤታችን ምልጃና ጸሎት ከሁላችን ጋር ይሁን !
አምላካችን በኃይለ መስቀሉ ሀገራችንና ሕዝባችንን ይጠብቅልን።
† † †
🌼 🍒 🌼

[ † እንኳን ለግሼን ደብረ ከርቤ: ለብዙኃን ማርያምና ለቅዱሳኑ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † ]
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †
† 🕊 ግሼን ደብረ ከርቤ 🕊 †
† ሃገራችን ኢትዮዽያ ሃገረ እግዚአብሔር መሆኗን ታላቁ ቅዱስ መጽሐፍ ይመሰክራል:: [መዝ.፷፯ [67], አሞጽ.፱፥፯ [9:7] ሕዝቦቿም የድንግል ማርያምና የቅዱሳን አሥራት ናቸው:: የኢትዮዽያውያንን ያህል ድንግል ማርያምን የሚወድ: ለቅዱስ መስቀሉ ክብርን የሚሰጥ: ቅዱሳንንም የሚዘክር ያለ አይመስለኝም:: "እመ ብርሃንም ፈጽማ ትወደናለች:: ለዚህ ደግሞ ቅንጣት ታህል አንጠራጠርም::"
ለዓለም እስከ አሁን ድረስ የሁለቱ [የታቦተ ጽዮንና የቅዱስ ዕፀ መስቀሉ] መገኛ እንቆቅልሽ ነው:: ለእኛ ግን ሁለቱም ያሉት በቤታችን ውስጥ ነውና እንመሠክራለን:: ክብር ለቀደምት አበው ይድረሳቸውና አስፈላጊውን መንፈሳዊና ሥጋዊ ዋጋ ከፍለው ታቦተ ጽዮንን እና ቅዱስ ዕፀ መስቀሉን አምጥተውልናል::
በዚህች ዕለትም የጌታችንና የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በደብረ ከርቤ ግሼን ማረፉን አስበን በዓልን እናከብራለን:: ይኸውም ደጉ አፄ ዳዊት በሠይፈ አርዕድ የተጀመረውን ጥረት ቀጥለው: በኃይለ እግዚአብሔር አሕዛብን አስደንግጠው: እመ ብርሃንንም በጸሎት ጠየቁ::
የአምላክ እናትም ረድታቸው ቅዱስ ዕፀ መስቀሉን ከኩርዓተ ርዕሡ: ወንጌላዊ ቅዱስ ሉቃስ ከሳላት ምስለ ፍቁር ወልዳ እና ከብዙ ንዋያተ ቅዱሳት ጋር ተላከላቸው:: እርሳቸው መስከረም ፲ [10] ቀን መስቀሉን ተቀብለው: በዓሉን በተድላ አክብረው በመንገድ በ፲፻፫፻፺፮ [1396] ዓ/ም ዐርፈዋል::
አፄ ዳዊት ካረፉ በኋላ ቅዱስ መስቀሉ ለ፴ [30] ዓመታት ተቀምጧል:: አፄ ዘርዓ ያዕቆብ እስከ ነገሠበት ፲፻፬፻፳፮ [1426] ዓ/ም ድረስም ከ፮ [6] በላይ ነገሥታት አልፈዋል::
† አፄ ዘርዓ ያዕቆብ ከነገሠ ከጥቂት ዓመታት በኋላ ለቅዱስ መስቀሉ በመካነ ንግሡ ደብረ ብርሃን ቤተ ክርስቲያንን ለማነጽ ሲያስብ ጌታችን በራዕይ "አንብር መስቀልየ በዲበ መስቀል" አለው:: ከዚህ ቀን ጀምሮ ደጉ ንጉሥ የመካነ መስቀሉን ቦታ ይፈልግ ዘንድ ከሠራዊቱ ጋር ብዙ ደክሟል::
በመጨረሻም በነገሠ በ፲ [10] ዓመታት ግሼንን አምባሰል [ወሎ] ውስጥ አግኝቷት ሐሴትን አድርጓል:: ቦታዋ በሥላሴ ፈቃድ በትእምርተ መስቀል የተፈጠረች ናትና እግዚአብሔር አብ ቤተ ክርስቲያንን አንጾ መስቀሉን በብረት: በመዳብ: በናስ: በብር: በወርቅ ለብጦ: ዐፈር እንዳይነካውም አድርጐ አኑሮታል::
በቦታውም ተአምራት ተደርገዋል:: ጻድቁ ዘርዓ ያዕቆብም 'ጤፉት' የሚባል መጽሐፍን ጽፎ እዚያው አኑሮታል:: መጽሐፉ እንደሚለው በሃገራችን ያለው ግማደ መስቀሉ [የቀኝ እጁ] ብቻ ሳይሆን ሙሉው ዕፀ መስቀል ነው:: ይህ የተደረገውም መስከረም ፳፩ [21] ቀን ነው::
† 🕊 ብዙኃን ማርያም / ጉባኤ ኒቅያ 🕊 †
† ዳግመኛ ይህች ዕለት 'ብዙኃን ማርያም' ትባላለች:: በቁሙ ሲታይ ድንግል ማርያም የብዙ ቅዱሳን የጸጋ እናት መሆኗን ያመለክታል:: በምሥጢሩ ግን በዚህች ዕለት በሃገረ ኒቅያ በእመቤታችን እና በአምላክ ልጇ የሚያምኑ ፫፻፲፰ [318]ቱ ቅዱሳን ሊቃውንት መሰብሰባቸውን የሚያጠይቅ ነው::
የሊብያው ሰው አርዮስ ጌትነት ገንዘቡ የሆነ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ክዶ ሊያስክድ ሲሯሯጥ በፈቃደ እግዚአብሔር: በጻድቁ ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ ጥሪ: ፳፻፫፻፵፰ [2348] ምሑራን ከመላው ዓለም ተሰበሰቡ::
ጥሪው የተላለፈው በወርኀ ሚያዝያ ሲሆን በመንገድ ችግር ሁሉም ተጠቃለው ኒቅያ የገቡት በዚህ ቀን ነበር:: ከተሰበሰበው ብዙ ሰው መካከል የአበውን ደቀ መዛሙርት ሳንቆጥር ሃይማኖታቸው የቀና: ምግባራቸው የጸና ፫፻፲፰ [318]ቱ አበው ሊቃውንት ተገኙ::
እነዚህ አባቶች 'ሊቃውንት' ሲባሉ እንዲሁ በእውቀት ብቻ የበሰሉ እንዳይመስሉን:: 318ቱ አበው እኩሎቹ በዘመነ ሰማዕታት እጅና እግራቸውን የተቆረጡና ለሃይማኖታቸው ብዙ ዋጋ የከፈሉ ናቸው:: እኩሎቹ ደግሞ በገዳማዊ ሕይወት ያጌጡ: ፍቅረ ክርስቶስ በውስጣቸው የሚነድ: የመንፈስ ቅዱስ ቤት ናቸው:: የጉባኤውን ዜና ግን ሕዳር 9 ቀን የምንመለከት ነንና የዚያ ሰው ይበለን:: ይህች ቀን ለአባቶቻችን የሱባኤ መጀመሪያ ናት::
† 🕊 ቅዱሳን ቆዽርያኖስ እና ዮስቴና 🕊 †
† ቆዽርያኖስ ማለት አገር ያስጨነቀ የሶርያ ጠንቅ ዋይ [መተተኛ] የነበረ ሰው ነው:: ከሥራዩ ብዛት የተነሳ አጋንንትን የሚፈልገውን ያዛቸው ነበር:: በዚያ ሰሞን ታዲያ ወደ አንጾኪያ ሔዶ የለመደውን ሊሠራ አሰበ:: እንዳሰበውም ሔደ::
በአንጾኪያ ደግሞ ስም አጠራሯ የከበረ: ክርስትናዋ የሠመረ: ድንግልናዋ የተመሠከረና ደም ግባቷ ያማረ አንዲት ወጣት ነበረች:: ስሟም ዮስቴና [የሴቶች እመቤት] ትባላለች:: እንዲህ ነው ስምና ሥራ ሲገጣጠሙ::
በወቅቱ ደግሞ የእርሷ ጐረቤት የሆነ አንድ ሰው በቁንጅናዋ ተማርኮ 'ላግባሽ' ቢላት 'አይሆንም' አለችው:: ምክንያቱም እርሷ መናኝ ናትና:: በጥያቄ አልሳካልህ ቢለው በሃብት ሊያታልላት: 'እገድልሻለሁ' ብሎ ሊያስፈራራት: በሥራይ [በመስተፋቅር] ሊያጠምዳት ሞከረ:: ነገር ግን አልተሳካለትም:: ምክንያቱም ሟርት በእሥራኤል ላይ አይሠራምና:: በመጨረሻ ግን ወደ ቆዽርያኖስ ሔዶ "አንድ በለኝ" አለው:: ቆዽርያኖስም "ይሔማ በጣም ቀላል ነው" ብሎ ወዲያው አጋንንትን ጠራቸው:: "ሒዳችሁ ያችን ወጣት አምጡልኝ" ሲልም ላካቸው::
አጋንንቱ ወደ ቅድስት ዮስቴና ሲሔዱ ግን መላእክት ወርደው ቤቷን በእሳት አጥረውታል:: ተመልሰው "አልቻልንም" አሉት:: እርሱም "አንዲት ሴት ካሸነፈቻችሁማ እኔም ክርስቲያን እሆናለሁ" ብሎ አስፈራራቸው:: አጋንንቱም በማታለል አንዱ ሰይጣን እርሷን መስሎ ሌሎቹ ደግሞ አስረውት መጡ::
ቆዽርያኖስ ይህን ሲያይ ደስ ብሎት "ሠናይ ምጽአትኪ ኦ ዮስቴና እግዝእቶን ለአንስት-የሴቶች እመቤት ዮስቴና እንኳን ደህና መጣሽ" ሲል: ስሟ ገና ሲጠራ ደንግጠው አጋንንት እንደ ጢስ ተበተኑ:: "ለዛቲ ቅድስት በኀበ ጸውዑ ስማ: ከመ እንተ ጢስ ተዘርወ መስቴማ" እንዳለ መጽሐፍ::
ቆዽርያኖስም በሆነው ነገር ተገርሞ "ስሟን ሲጠሩ እንዲህ የራዱ ወደ እርሷማ እንዴት ይቀርባሉ" ብሎ ተነሳ:: መጽሐፈ ሥራዩን በሙሉ አቃጠለ:: ሃብቱንም ለነዳያን አካፍሎ ሒዶ ክርስቲያን ሆነ:: የሚገርመው ድንግል ነበርና ከብዙ ተጋድሎ በኋላ ዲቁናና ቅስናን ተሾመ::
አምላክ መርጦታልና የቅርጣግና ዻዻስ ሆኖ ተመርጦ የክርስቶስን መንጋ በትጋት ጠብቋል:: ቅድስት ዮስቴናም ገዳም አንጻ: ደናግሉን ሰብስባ ንጽሕናን ስታስተምር ኑራለች:: በመጨረሻም በዚህ ዕለት ንጉሡ ዳኬዎስ ክርስቶስን ካልካዳችሁ በሚል ብዙ አሰቃይቶ አንገታቸውን አሰይፏል::
† ቸር አምላክ በኃይለ መስቀሉ ሃገራችንን ከክፉው ሁሉ ይጠብቅልን:: የቅዱሳኑን ጸጋ ክብርም አይንሳን::
[ † መስከረም ፳፩ [ 21 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. ቅድስት ግሼን ደብረ ከርቤ
፪. ብዙኃን ማርያም
፫. "318ቱ" ቅዱሳን ሊቃውንት
፬. ቅዱስ ቆዽርያኖስ ሰማዕት
፭. ቅድስት ዮስቴና ድንግል
፮. ቅዱስ ጢባርዮስ ሐዋርያ
[ † ወርኀዊ በዓላት ]
፩. ቅድስት ድንግል እግዝእትነ ማርያም ወላዲተ አምላክ
፪. አበው ጎርጎርዮሳት
፫. አቡነ ምዕመነ ድንግል
፬. አቡነ አምደ ሥላሴ
፭. አባ አሮን ሶርያዊ
፮. አባ መርትያኖስ ጻድቅ

† " እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል:: ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል ይላል:: እንግዲህ ለእግዚአብሔር ተገዙ:: ዲያብሎስን ግን ተቃወሙ:: ከእናንተም ይሸሻል:: ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ:: ወደ እናንተም ይቀርባል::" † [ያዕ. ፬፥፮]
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖 🕊 💖
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖 🕊 💖
†
[ 🕊 ገ ድ ለ ቅ ዱ ሳ ን 🕊 ]
▬▬▬▬▬▬ † ▬▬▬▬▬▬
[ የአባታችን የቅዱስ መቃርዮስ የተጋድሎ ሕይወቱና ትምህርቱ ]
[ ክፍል አሥር ]
💛
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡
[ በምናኔ ለመኖር ከከተማ ውጭ መቀመጡና ቅስና መቀበሉ ]
❝ በመጨረሻም መቃርዮስ ወላጆቹ የተዉለትን ገንዘብ በሙሉ ለድሆችና ለጦም አዳሪዎች በመስጠት ከከተማዋ ውጪ ሄዶ መኖር ጀመረ፡፡ የሀገሩ ሰዎች ግን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ያለውን መገዛትና ፍጹም የሆነ ትሕትናውን ፣ እውነተኛነቱንና ቅድስናውን ባዩ ጊዜ በሀገራቸው ቀድሶ የሚያቆርባቸው ካህን አልነበራቸውምና ካህን ሆኖ እንዲያገለግላቸው ቅስና ይቀበል ዘንድ ወደዱ፡፡ ከዚያም ወደ ኤጲስ ቆጶሱ ሄደው መቃርዮስ ቅስና ይሾምላቸው ዘንድ መቃርዮስ ሳያውቅ በምስጢር ጠየቁት፡፡ ኤጲስ ቆጶሱም ነገሩን በወደደ ጊዜ ደስ እያላቸው ወደ መቃርዮስ በኣት በመሄድ ያለ ፈቃዱ በግድ ወደ ኤጲስ ቆጶሱ ወሰዱትና ቅስና አሾሙት፡፡ በዚያ በበኣቱ የሚያዩትና የሚመለከቱት ሁሉ በመንፈሳዊ ሕይወቱ ደስ ይሰኙበት ነበር፡፡ ሥጋውና ደሙን ይቀበሉ ዘንድም ወደ እርሱ ይሄዱ ነበር፡፡
በዚያን ጊዜ ሰይጣን ፍላጻውን ያነሳሳበት ጀመረ፡፡ እስከዚያን ጊዜ ድረስ ክፉ ሀሳብን የሚዘራ የዲያብሎስን ፈተና በልቡ መፈተን አልጀመረም ነበር፡፡ ሰይጣንም ይህ ቅዱስ በዚያ ቦታ ተቀምጦ በኋላም ለተጋድሎ በመለየት ወደ በረሃው እንዳይሄድና በረሃውን ሰማያዊ አምልኮ የሚፈጸምበትና በዚህ ምድር ለተጋድሎ በሚሆን በመንፈሳዊ ጸጋ የተከለሉ በጸሎታትና በአንብዕ እነዚህን በመሰሉ በጌታችን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም በሚፈጽሟቸው መንፈሳዊ አገልግሎቶች ምድረበዳውን አዲስ ዓለም እንዳያደርገው በመስጋት ይፈትነው ጀመር፡፡ ያን ጊዜ ከመሆኑ በፊት ሁሉን የሚያውቅና የሚመለከት ብቻውን ጥበበኛ የሆነ እግዚአብሔር የተነገረውን ያስታውስ ዘንድና ዘለዓለማዊ ሕይወትን የሚሹትን ጉባኤ እንደሚሰበስባቸው ወደ ተነገረው በረሃ ይሄድ ዘንድ በመቃርዮስ ላይ ፈተና ይመጣበት ዘንድ ሰይጣንን አሰናበተው፡፡ ❞
የአባታችን የቅዱስ መቃርዮስ ምልጃና ጸሎቱ አይለየን፡፡
ይቆየን !

🌼 [ የትሕርምት ሕይወት ! ] 🌼
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
🕊
[ " የሕግ መምህር በረከትን ይሰጣልና ! " ]
.........
" ጌታችን ሐዋርያትን ለመምህርነት ሲያዘጋጃቸው ሁል ጊዜም ቢሆን ከሕዝቡ ለይቶ ብቻቸውን የትሕርምት ሕይወትን እንዲለማመዱ ያደርጋቸው ነበር፡፡ በዚህም ጌታችን ለሐዋርያት የትሕርምት ሕይወት አንዱ የሕይወታቸው ክፍል አድርገው እንዲይዙት መሻቱን እናስተውላለን፡፡ [ሉቃ.፳፪፥፴፱]
ቅዱስ ጳውሎስም በሁሉ ክርስቶስን አብነት አድርጎ የሚኖረውን ሕይወት እኛም እንኖረው ዘንድ “እኔ ክርስቶስን እንደምመስል እኔን ምሰሉ” ብሎ አስተምሮናል። [፩ቆሮ.፲፩፥፩] እንዲሁ ሁሉም ሐዋርያት ጌታችንን መስለው የትሕርምትን ሕይወት ኖረዋል። [ማቴ.፲፥፳፯]
ስለዚህ ሐዋርያት ንጉሥ ዳዊት በመዝሙሩ “አቤቱ ፥ እርዳታው ከአንተ ዘንድ የሆነለት ፥ በልቡም የላይኛውን መንገድ የሚያስብ ሰው ምስጉን ነው:: በልቅሶ ሸለቆ ውስጥ በወሰነው ስፍራ የሕግ መምህር በረከትን ይሰጣልና፡፡ [መዝ.፹፫፥፭] እንዳለው በበአታቸው [ማለትም ብቻቸውን በጸሎት በሚተጉበት ሥፍራ] መዝሙረኛው “በለቅሶ ሸለቆ ውስጥ” ባለው ከመንፈስ ቅዱስ በኅቡዕ [በጨለማ] የሰሙትን በብርሃን ሲያስተምሩ ፤ በጆሮ የሰሙትን በሰገነት ላይ ሰብከዋል፡፡
ጌታችንም ደቀ መዛሙርቱን በተግባር ጸሎትን እንዴት መጸለይ እንዳለባቸው ካስተማራቸው በኋላ “ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸልዩ ፤ መንፈስስ ተዘጋጅታለች ሥጋ ግን ደካማ ነው” [ማቴ.፳፮፥፵፩] በማለት ለጦም ፣ ለስግደት ፣ ለጸሎት ፣ ለምንባብ እንዲሁም ለጽሙና ሕይወት ጽሙድ ከሆን መንፈስ ቅዱስ መምህር ሆኖ እንደሚመራንና እንደሚያስተምረን አስተምሮናል፡፡"
🕊
[ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ]

[ † እንኩዋን ለአበው ሰማዕታት ቅዱስ ዮልዮስና ቅዱስ ኮቶሎስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ † ]
†††
† 🕊 ቅዱስ ዮልዮስ ሰማዕት 🕊 †
ከሁሉ አስቀደሞ ስለ ሰማዕታት ዜና ሲሰማ ለዚህ ቅዱስ አንክሮ [አድናቆት]: ክብርና የጸጋ ውዳሴ ይገባዋል:: ምክንያቱም ገድለ ሰማዕታትን የጻፈልን እርሱ ነውና:: ነገር ግን መጻፍ ሲባል: ነገሮች እንዲህ እንደ እኛው ዘመን ቀላል እንዳይመስሏችሁ:: ቅዱሱ ዜና ሰማዕታትን ለማዘጋጀት ሃብቱን: ንብረቱን: ቤተሰቦቹንና ሕይወቱንም ሰውቷል::
ይህስ እንደ ምን ነው ቢሉ:- በመጨረሻው ዘመነ ሰማዕታት [በ፫ኛው መቶ ክ/ዘ] ዓለም በደመ ሰማዕታት ስትሞላ የሰማዕታቱን ዜና የሚጽፍ: ሥጋቸውን እንኩዋ የሚቀብር አልተገኘም:: "ወኃጥኡ ዘይቀብሮሙ-የሚቀብራቸውም አጡ" እንዳለ ቅዱስ ዳዊት:: [መዝ.፸፰፥፫]
እግዚአብሔር ግን ስለ ወዳጆቹ ሰማዕታት ይህንን ቅዱስ አስነሳ:: ቅዱስ ዮልዮስ በዘመኑ ደግ ክርስቲያን: ትዳርና ልጆች ያሉት: እጅግ ባለ ጸጋና ፫፻ አገልጋዮች ያሉት: ምጽዋትንም የሚወድ ሰው ነበር::
በወቅቱ ክርስቲያኖች በየመንገዱ ወድቀው መታየታቸው ዕረፍት ቢነሳው ከቤተሰቦቹ ጋር መክሮ መልካም ግን ደግሞ ከባድ ውሳኔን አስተላለፈ:: ውሳኔውንም ታጥቆ ይተገብረው ጀመር:: ነገሩ እንዲህ ነው:-
፩. የታሠሩ ክርስቲያኖችን ቁስላቸውን እያጠበ ያጐርሳቸዋል::
፪. ቀን ቀን አገልጋዮቹን አስከትሎ የሰማዕታቱን ሥጋ እየሰበሰበ: ሽቱ ቀብቶ ይገንዛቸዋል:: አንዳንዶቹን ወደ ቤተሰቦቻቸው ሲልክ ሌሎቹን ራሱ ይቀብራቸዋል::
፫. ሌሊት ሌሊት በ፫፻ው አገልጋዮቹ እየታገዘ የሰማዕታቱን ዜና: ቀለም በጥብጦ: ብራና ዳምጦ: ብዕር ቀርጾ: ሲጽፍና ሲጠርዝ ያድራል:: በተረፈችው ጥቂት ሰዓት ደግሞ ይጸልያል:: ቅዱስ ዮልዮስ በእውነት ድንቅ ሰው ነው:: በምን እንመስለዋለን! እርሱን የፈጠረውን ጌታ "ዕጹብ ዕጹብ" ብለን ከማድነቅ በቀር::
ሰማዕታቱም ስለ ደግነቱ የሚመልሱለት ቢያጡ ዝም ብለው ይመርቁት ነበር:: ምርቃናቸውም "ለሰማዕትነት ያብቃህ" የሚል ነው:: በእርግጥ ይህ ለዘመኑ ሰዎች ምርቃት ላይመስለን ይችል ይሆናል:: እርሱ ግን ይህንን ሲሰማ ሐሴትን ያደርግ: እጅም ይነሳቸው ነበር:: በዘመኑ ትልቁ ምርቃት ይሔው ነበርና::
እንዲህ: እንዲህ እያለ ዘመነ ሰማዕታት ሊፈጸም ወራት ቀሩት:: በዚህ ጊዜ ለሰማዕትነት ከመነሳሳቱ የተነሳ ጌታችንን ተማጸነ:: ጌታችንም ተገልጾለት "ሒድና ሰማዕት ሁን: ፈቅጄልሃለሁ" አለው:: እርሱም ደስ እያለው ዜና ሰማዕታቱን ለሁነኛ ሰው ሰጥቶ: ሃብት ንብረቱን ለነዳያን አካፈለ::
ቀጥሎም ቤተሰቦቹንና አገልጋዮቹን ጨምሮ ፭፻ ሰዎችን አስከትሎ ወደ ሃገረ ገምኑዲ ሔደ:: በመኮንኑ ፊት የክርስቶስን አምላክነት ቢመሰክር ፈጽመው አሰቃዩት:: በማግስቱም ወታደሮቹ ለጣዖት ካልሰገድክ ሲሉት "ቆዩማ ላሳያችሁ" ብሎ በጸሎቱ ጣዖታትን ከነ ካህናቶቻቸው ምድር ተከፍታ እንድትውጣቸው አደረገ::
በዚህ ተአምር የደነገጠው መኮንኑ አርማንዮስ ከነ ሠራዊቱ በክርስቶስ አመነ:: ክብሩንም ትቶ ቅዱስ ዮልዮስን ተከተለው:: ቀጥሎም ጉዞ ወደ ሃገረ አትሪብ ሆነ:: በዚያም ብዙ መከራን ተቀብሎ ጣዖታቱን አወደማቸው::
እዚህም የአትሪብ መኮንን ደንግጦ ከነ ሠራዊቱ አምኖ ቅዱሱን ተከተለው:: በመጨረሻ ግን ሰማዕትነት እንዳይቀርበት ስለሰጋ ቅዱስ ዮልዮስ ተአምራት ማድረጉን ተወ:: በፍጻሜውም የ፫ኛው ሃገር መኮንን ቅዱስ ዮልዮስ ከቤተሰቡና ከ፩ ሺህ ፭ መቶ ያህል ተከታዮቹ ጋር: ፪ቱን የሃገረ ገዥዎች ጨምሮ አንገታቸውን አሰይፏቸዋል:: ቅዱሱም የክብር ክብርን አግኝቷል::
† 🕊 ቅዱስ ኮቶሎስ ሰማዕት 🕊 †
ይህ ቅዱስ በቀደመ ሕይወቱ አረማዊ ሲሆን የክርስቶስን ስም ሰምቶ አያውቅም:: በ4ኛው መቶ ክ/ዘ በፋርስ [አሁን ኢራን] ሳቦር የሚባል ክፉ ንጉሥ ነግሦ ክርስቲያኖችን ያሰቃይ ነበር:: እርሱ የሚያመልከው ፀሐይና እሳት ነውና::
የዚህ ንጉሥ ልጆቹ 'ልዑል ኮቶሎስና ልዕልት አክሱ' ይባላሉ:: በቤተ መንግስት ውስጥ ስላደጉ የሚያመልኩት የአባታቸውን ጣዖት ነበር:: በፋርስ መንግስት ውስጥ ከነበሩ የጦር አለቀቆችና ሃገረ ገዥዎች አንዱ ጣጦስ ይባላል::
ይህ ሰው እጅግ ብሩህ የሆነ ክርስቲያን ነበርና ዘወትር ከንጹሕ አገልግሎቱ ተሰነካክሎ አያውቅም:: ትንሽ ቆይቶ ግን ክርስቲያን መሆኑን ሳቦር ስለ ሰማ ሠራዊት ይልክበታል:: "ሒዱና ጣጦስን መርምሩት: ክርስቲያን ከሆነና አማልክትን እንቢ ካለ በእሳት አቃጥላችሁ ግደሉት" አላቸው::
በአጋጣሚ የንጉሡ ልጅ ኮቶሎስና ጣጦስ በጣም የሚዋደዱ ባልንጀሮች ነበሩና ሊያስጥለው ወዶ ሔደ:: ኮቶሎስ ቅዱስ ጣጦስ ታስሮ በእሳት ሊቃጠል ሲል ደረሰ:: ወዲያውም ወደ እሳቱ ውስጥ ጨመሩት:: እነርሱ ፈጥኖ አመድ ይሆናል ብለው ጠብቀው ነበር:: ግን አልሆነም::
ቅዱስ ጣጦስ በእሳት መካከል ቁሞ አላቃጠለውም:: እንዲያውም በትእምርተ መስቀል ቢያማትብበት እሳቱ ብትንትን ብሎ ጠፋ:: ኮቶሎስ ተገርሞ ቅዱሱን ባልንጀራውን "ወንድሜ! ሥራይ [መተት] መቼ ተማርክ ደግሞ?" ሲል ጠየቀው::
እርሱ እስከዚያች ሰዓት ኃይለ እግዚአብሔርን አልተረዳምና:: ቅዱስ ጣጦስ ግን "ወንድሜ! አትሳሳት: እኛ ክርስቲያኖች መተትን አናውቅም:: በፈጣሪያችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ግን ሁሉን ማድረግ እንችላለን" ሲል መለሰለት::
ኮቶሎስ ተገርሞ "አሁን እኔ በክርስቶስ ባምን እንዳንተ ማድረግ እችላለሁ?" ቢለው ቅዱሱ "አዎ ትችላለህ!" አለው:: ወዲያውም "እሳት አንድዱልኝ" አለና እጣቱን በመስቀል ምልክት አስተካክሎ ወደ እሳቱ ቢያመለክት እሳቱ ፲፪ ክንድ ርቆ ተበትኖ ጠፋ::
በዚያችው ሰዓት ቅዱስ ኮቶሎሰ በክርስቶስ አመነ:: ክብሩንና የአባቱን ቤተ መንግስት አቃሎ ወደ እስር ቤት ገባ:: አባቱ ሳቦር ይህን ሲሰማ ተቆጥቶ "ምከሪው" ብሎ እህቱን አክሱን ላከበት::
ቅዱስ ኮቶሎስ ልትመክረው የመጣችውን እህቱን አሳምኖ የክርስቶስ ወታደር አደረጋት:: አስቀድሞ ቅዱስ ጣጦስ: አስከትሎም ቅድስት አክሱ ተገደሉ:: በፍጻሜው ግን ቅዱስ ኮቶሎስን እግሩን አስረው በየመንገዱ ጐተቱት:: በጐዳናም አካሉ እየተቆራረጠ አለቀ:: ክርስቲያኖች በድብቅ መጥተው የ፫ቱንም ሥጋ በክብር አኑረዋል::
አምላከ ቅዱሳን ሰማዕታትን ባጸናበት ጽናት ሁላችንም ያጽናን:: በረከታቸውንም ያብዛልን::
🕊
[ † መስከረም ፳፪ [ 22 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. ቅዱስ ዮልዮስ ሰማዕት
፪. ፲፻፭፻ [1,500] ሰማዕታት [የቅዱስ ዮልዮስ ማሕበር]
፫. ቅዱስ ኮቶሎስ ሰማዕት
፬. ቅድስት አክሱ ሰማዕት
፭. ቅዱስ ጣጦስ ሰማዕት
፮. ቅዱስ ባላን ሰማዕት
[ † ወርኀዊ በዓላት ]
፩. ቅዱስ ዑራኤል ሊቀ መላእክት
፪. ቅዱስ ሉቃስ ወንጌላዊ
፫. ቅዱስ ደቅስዮስ [የእመቤታችን ወዳጅ]
፬. አባ እንጦንስ አበ መነኮሳት
፭. አባ ዻውሊ የዋህ

" ሰውን ከአባቱ: ሴት ልጅንም ከእናቷ . . . እለያይ ዘንድ መጥቻለሁና:: ለሰውም ቤተሰዎቹ ጠላቶች ይሆኑበታል:: ከእኔ ይልቅ አባቱን ወይም እናቱን የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባውም:: ከእኔ ይልቅም ወንድ ልጁን ወይም ሴት ልጁን የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባውም:: መስቀሉን የማይዝ በሁዋላየም የማይከተለኝ ለእኔ ሊሆን አይገባውም:: " [ማቴ.፲፥፴፭]
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖 🕊 💖
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖 🕊 💖