🕊
[ † እንኳን ለነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ኤርምያስ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † ]
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †
🕊 † ቅዱስ ኤርምያስ † 🕊
† ታላቁ ነቢይ ቅዱስ ኤርምያስ ከዐበይት ነቢያት አንዱ ሲሆን ቅድመ ልደተ ክርስቶስ በ፮፻ [600] አካባቢ የነበረ ነቢይ ነው:: አባቱ ኬልቅዩ ይባላል:: ከካኅናተ እስራኤል አንዱ ነበር::
እግዚአብሔር ኤርምያስን የጠራው ገና በሕጻንነቱ ነበር:: "ከእናትህ ማሕጸን ሳትወጣ መርጬሃለሁ: ቀድሼሃለሁ" ሲልም በገሃድ መስክሮለታል:: [ኤር.፩፥፭]
ከቅዱሳን ነቢያት እንደ ኤርምያስ የተሰቃየና ያለቀሰ የለም:: ከ፯ [70] ዘመናት በላይ ስለ ወገኖቹ አልቅሷልና:: ሊቃውንት "ነቢየ ብካይ" [ባለ እንባው ነቢይ] ይሉታል::
ዘመኑ ዘመነ ኃጢአት [ዘመነ ዐጸባ] ነበር:: እሥራኤላውያን ከመሪዎቻቸው ከነ ሴዴቅያስ ጋር በክፋት ተባብረውም ነበርና ኤርምያስን አልሰሙትም:: ይልቁኑ ክፉ ቦታ ውስጥ አስረው አሰቃዩት:: እግዚአብሔር ግን በኢትዮዽያዊው አቤሜሌክ አማካኝነት ከመከራው አዳነው::
የተሰበከላቸውን የንስሃ ጥሪ አልሰሙምና ስልምናሦር የሚባል የአሕዛብ ንጉሥ መጥቶ አሥሩን ነገድ ማርኮ አሦር [ነነዌ] አወረዳቸው:: በሁዋላ ደግሞ በኃይለኝነቱ የታወቀው የባቢሎን ንጉሥ ይማርካቸው ዘንድ ወደ ሁለቱ ነገድ ኢየሩሳሌም ደረሰ:: ኤርምያስ ወደ ከተማዋ ዳር ወጥቶ ስለ ኢየሩሳሌምና ስለ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አለቀሰ::
ከቤተ መቅደስ ንዋያት እኩሉን ለምድር አደራ ሰጣትና ሸሸገችው:: ነቢዩ የተናገረው አይቀርምና ንጉሡ ናቡከደነጾር እኩሉን ገድሎ: እኩሉንም ማርኮ: ኢየሩሳሌምን አቃጥሎ: የአሕዛብ መዘባበቻ አድርጐ ባቢሎን አወረዳቸው::
ቅዱስ ኤርምያስን ግን ትሩፋን [ከመከራው የተረፉት] ይዘውት ወደ ግብፅ ወረዱ እንጂ አልተማረከም::
በዚያም ተአምራትን አድርጐ አራዊትን አጥፍቷቸዋል:: ትንሽ ቆይቶ ግን እውነተኛ አባት: ነቢይ: መምሕርም ነውና ወደ ሕዝቡ [ወደ ባቢሎን] ወረደ:: በዚያም ትንቢትን እየተናገረ: ሕዝቡን ከ፸ [70] ዓመታት በሁዋላ ወደ ሐገራቸው እንደሚመለሱ እያስተማራቸው በባቢሎን ቆይቷል:: ያለ በደሉም በመከራቸው ተካፋይ ሆኗል::
ሰባው ዘመን ሲፈጸም እግዚአብሔር እንደ ቃል ኪዳኑ በኤርምያስ መሪነት እሥራኤል ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ:: አሁንም ግን ክፋታቸውን ይተው ዘንድ ፈቃደኞች አልነበሩምና ኤርምያስ ገሠጻቸው::
በዚህ ተበሳጭተው ሊወግሩት ሲሉ ጸጋ በዝቶለት: ምስጢርም ሰፍቶለት ስለ ነገረ ሥጋዌ [ስለ ክርስቶስ የማዳን ሥራ] አምልቶና አጉልቶ ትንቢት ተናገረ:: አንዴ ልቡናቸው ታውሮ ኤርምያስ ነው ብለው ድንጋዩን በድንጋይ ሲወግሩት ውለዋል:: ዘግይቶ ግን ኤርምያስ ራሱን ገለጠላቸው:: ስለ እነርሱ ሲል ፸ [70] ዘመን ያለቀሰውንና ምትክ የሌለውን አባታቸውን ወግረው ገደሉት::
ታላቁ ነቢይ ቅዱስ ኤርምያስ ፶፪ [52] ምዕራፎች ያሉት ሐረገ ትንቢት ተናግሯል / ጽፏል:: ዜና ሕይወቱ ከራሱ የትንቢት መጽሐፍ በተጨማሪ በተረፈ ኤርምያስ: በመጽሐፈ ባሮክ: በገድለ ኤርምያስ: በዜና ብጹዐን: በመጽሐፈ ስንክሳርም ተጽፏል::
በዚህች ዕለት ንጉሡ ሴዴቅያስ ቅዱስ ኤርምያስን አስሮት እያለ ኢትዮዽያዊው ቅዱስ አቤሜሌክ ያስፈታበት [ከረግረግ ያወጣበት] ይታሰባል::
† ቸር እግዚአብሔር በኤርምያስ ምልጃ ሃገራችንን ከጥፋት: ሕዝቦቿን ከስደትና ከመቅሰፍት ይሰውርልን::
🕊
[ † ሚያዝያ ፲፪ [12] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. አቡነ ሳሙኤል ዘቆየጻ [ኢትዮዽያዊ]
፪. ቅዱስ ኤርምያስ ነቢይ
፫. ቅዱስ አቤሜሌክ ኢትዮዽያዊ
፬. ቅዱስ ባሮክ
፭. ቅዱስ እለእስክንድሮስ ዘኢየሩሳሌም
[ † ወርሐዊ በዓላት ]
፩. ቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላዕክት
፪. ቅዱስ ማቴዎስ ሐዋርያ
፫. ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ
፬. ቅዱስ ቴዎድሮስ ምሥራቃዊ [ሰማዕት]
፭. ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ
፮. አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ
፯. ቅዱስ ድሜጥሮስ
† " ኢየሩሳሌም ሆይ ነቢያትን የምትገድል: ወደ እርሷ የተላኩትንም የምትወግር: ዶሮ ጫጩቶቿን ከክንፎቿ በታች እንደምትሰበስብ ልጆችሽን እሰበስብ ዘንድ ስንት ጊዜ ወደድሁ! አልወደዳችሁምም:: እነሆ ቤታችሁ የተፈታ ሆኖ ይቀርላቹሃል:: እላችሁአለሁና: በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው እስክትሉ ድረስ እንግዲህ ወዲህ አታዩኝም:: " † [ማቴ.፳፫፥፴፯-፴፱]
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖 🕊 💖

†
💖 [ ቅ ዱ ስ ሚ ካ ኤ ል ! ] 💖
🕊 💖 🕊
" ከሚካኤል በቀር ማንም የሚያጸናኝ የለም። "
[ ዳን.፲፥፳፩ ]
🕊
"የተጨነቀውን የተጨቆነውን ነፃ የምታወጣው ሚካኤል ሆይ ፦ ሰላም ላንተ ይሁን ፡ ሠራተኛው ሠርቶ እንዲበላ ውሎ እንዲገባ የምትጠብቀው ሚካኤል ሆይ ሰላም ላንተ ይሁን፡፡
ችግረኛውን ለመርዳት ከልዑል ዘንድ የምትላክ ሚካኤል ሆይ ሰላም ላንተ ይሁን አዳኝነትህን በማመን የለመነህን በክንፈ ረድኤትህ የምትሠውረው ሚካኤል ሆይ ሰላም ላንተ ይሁን፡፡
በኀዘን በትካዜ ላይ ወድቆ የሚፍገመገመውን የሚንፈራገጠውን ፈጥነህ ደርሰህ ደግፈህ የምታጽናናው ሚካኤል ሆይ ፤ አንገትህን ዘንበል ቀለስ አድርገህ በፈጣሪ ፊት ሰግደህ እኛ ባሮቹን በቸርነቱ ይጎበኘን ዘንድ የማናዊት እጁን ዘርግቶ ይባርከን ዘንድ ለምን አማልድ ለዘላለሙ አሜን፡፡"
[መልክአ ሚካኤል]
ኦ ሚካኤል ! ኦ ሚካኤል ! ኦ መተንብል !
ካህነ አርያም ትሰመይ ቢጸ ሱራፌል ፥
ዘም ርዑሳን ርዑስ ፥ ወዘም ልዑላን ልዑል
ጊዜ ጸዋይኩከ ቅረበኒ በምህረት ወሳህል !

የመላእክት አለቃ #ቅዱስ_ሚካኤል_አባቴ🙏🙏
#ሚካኤል_ሆይ ችግሬን አቅልልኝ ጭንቀቴን አስወግድልኝ ምክርን ትለግሰኝ ጥበብንም ታስተምረኝ ዘንድ አባት እዳደረግኩክ አንተም ልጅ አድርገኝ
#ሚካኤል_ሆይ ብስጭትና ፈና ደርሰውብኝ ወደአንተ በማመለክትበት ጊዜ ወዳጅ ለወዳጁ ለችግሩ እደሚደርስለት ወዳጅህን ለመርዳት ተፋጠን አንጂ የቸርነትህን በር አትዝጋብኝ።
ሁልጊዜ በፈጣሪ ፊት የምትቆም የአምላክ ቧለሟል #ቅዱስ_ሚካኤል ሆይ እኔን ባርያህን በጸሎት ከማሰብ አትርሳኝ ወዳጅ ወዳጁን ይረሳ ዘንድ አይቻለውም
አንተ ግን ደግ ነክና ሀዘኔን በደስታ ለውጠክ ከአምላኬ ጋር አስታርቀኝ🙏
#_ሰናይ__ቀን🙏
ለመቀላቀል 👇👇👇👇
@Enatachn_mareyam

[ † እንኳን ለጻድቃንና ሰማዕታት አባ ኢያሱና አባ ዮሴፍ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † ]
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †
🕊 † አባ ኢያሱና አባ ዮሴፍ † 🕊
† እነዚህ ፪ ቅዱሳን የደብረ ኮራሳኑ ጻድቅና ኮከብ የቅዱስ ሜልዮስ ደቀ መዛሙርት ናቸው:: የቅዱስ ሜልዮስ ነገርስ እንደ ምን ነው ቢሉ :-
ቅዱስ ሜልዮስ ልጅነቱን በመንፈሳዊ ትምሕርት ያሳለፈ: በጉብዝናው ወራት ፈጣሪውን ያሰበ ደግ ክርስቲያን ነው:: ይሕችን ዓለም ከነ ክፋቷ ንቆ ኮራሳት ወደሚባል በርሃ ሔዶ በተራራውና በደኑ ውስጥ በጾምና በጸሎት: በትሕርምትም ለበርካታ ዓመታት ተጋድሏል::
በነዚህ የብሕትውና ዘመናቱ ልብሱን ፀሐይና ብርድ ቆራርጦ ስለ ጨረሳቸው ፈጣሪው ጸጉርን አልብሶታል:: የአባ ሜልዮስ ጸጉሩ እስከ እግሩ: ጽሕሙ እስከ ጉልበቱ ነበር::
እድሜው ገፍቶ ሲያረጅ እንዲያገለግሉት እግዚአብሔር ሁለት ወጣት ምስጉን ክርስቲያኖችን ላከለት:: እነርሱም አባ ኢያሱና አባ ዮሴፍ ይባላሉ:: ሁለቱ ቅዱሳን አምላካቸውን እግዚአብሔርንና አባታቸው ቅዱስ ሜልዮስን በፍጹም ቅንነት አገልግለዋል::
ከቆይታ በሁዋላ ግን በአካባቢው የነበሩ ጣዖት አምላኪዎች አራዊት እናጠምዳለን ብለው በዘረጉት መረብ ቅዱስ ሜልዮስን ያዙት:: ክርስቲያን መሆኑን ሲያውቁ "ለፀሐይ ስገድ" ብለው ደበደቡት::
ደቀ መዛሙርቱ ተሯሩጠው መጥተው አባታቸውን በመከራ መሰሉት:: ክርስቶስን አንክድም ስላሉ ሁለቱንም በሰይፍ አንገታቸውን መቷቸው:: ቅዱስ ሜልዮስን ግን ለ፲፭ ቀናት ካሰቃዩት በሁዋላ በቀስት በተደጋጋሚ ወግተው ገድለውታል:: ጻድቅና ሰማዕት ቅዱስ ሜልዮስ ብዙ ተአምራትን አድርጉዋል::
ገዳዮች ግን ወደ ሃገራቸው ሲመለሱ የሜዳ አህያ ሊያድኑ የወረወሩትን ቀስት የእግዚአብሔር መልአክ ወደነርሱ መልሶባቸው ልብ ልባቸውን ተወግተው ሙተዋል::
† ይህች ቀን ቅዱሳን አባ ኢያሱና አባ ዮሴፍ ሰማዕትነትን የተቀበሉባት ናት::
† ቸር አምላክ ከቅዱሱ ሜልዮስና ከደቀ መዛሙርቱ በረከትን ያካፍለን::
🕊
[ † ሚያዝያ ፲፫ [ 13 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. ቅድስት ዲዮኒስ ዲያቆናዊት [የሐዋርያት ተከታይ የነበረች]
፪. አባ ኢያሱና አባ ዮሴፍ [ሰማዕታት]
፫. ቅዱስ መናድሌዎስ
፬. አባ አኮላቲሞስ
[ † ወርኀዊ በዓላት ]
፩. እግዚአብሔር አብ
፪. ቅዱስ ሩፋኤል ሊቀ መላዕክት
፫. ፺፱ኙ "99ኙ" ነገደ መላዕክት
፬. ቅዱስ አስከናፍር
፭. ፲፫ቱ "13ቱ" ግኁሳን አባቶች
፮. ቅዱስ አርሳንዮስ ጠቢብ ገዳማዊ
፯. አቡነ ዘርዐ ቡሩክ
† " ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ: ወይስ ጭንቀት: ወይስ ስደት: ወይስ ራብ: ወይስ ራቁትነት: ወይስ ፍርሃት: ወይስ ሰይፍ ነውን? 'ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ እንገደላለን:: እንደሚታረዱ በጐች ተቈጠርን' ተብሎ እንደ ተጻፈ ነው:: በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን::" † [ሮሜ.፰፥፴፭-፴፰]

[ 🕊 የዐቢይ ጾም ሰባተኛ ሳምንት 🕊 ]
† [ ኒቆዲሞስ ] †
🕊 💖 🕊
ይህ የዐቢይ ጾም ሰባተኛው ሰንበት ስያሜ ነው፡፡ ይህም ዕለት ኒቆዲሞስ የተባለው የአይሁድ መምህር በሌሊት ወደ ጌታው ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ እየመጣ ይማር እንደነበረ ይታሰብበታል። በዚም ዕለት የኒቆዲሞስን ታሪክ የሚያስታውስ መዝሙር ይዘመርበታል፡፡
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፤ ምሁረ ኦሪት ኒቆዲሞስን በመንፈቀ ሌሊት ስለ ምሥጢረ ጥምቀት ያስተማረበት ዕለት ነው።
[ ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ ! ]
'' እውነት እውነት እልሃለሁ ፥ ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይ አይችልም አለው። ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም። ከሥጋ የተወለደ ሥጋ ነው፥ ከመንፈስም የተወለደ መንፈስ ነው። " [ ዮሐ.፫፥፫-፮ ]
† 🕊 ክብርት ሰንበት 🕊 †
💖

† [ መምህር ሆይ ! ] †
🕊 💖 🕊
መሆንህን አውቆ እውነተኛ
ገሰገሰ ወዳንተ በሌሊት ሳይተኛ
ቅዱስ ቃልህንም ሲሰማ ፈወሰው
የታወረ ኅሊናውን አብርቶ አቀናው
ጥያቄውን እንዲያቀርብ አበረታታኸው
ስለ ዳግም ውልደትም አስተማርከው።
" እውነት እውነት እልሀለሁ " ስትለው
ዳግመኛ ያልተወለደ ሰው …
የእግዚአብሔርን መንግሥት ለማየት አይቻለው "
ምሥጢሩ ባይገባው
" ከሥጋ የተወለደ ሥጋ ነው፡፡
ከመንፈስ የተወለደ መንፈስ ነው "
ብለህ አስረዳኸው፡፡
" ይህ ሊሆን እንዴት ይቻላል ? " ብሎ ኒቆዲሞስ ቢጠይቅህ
" አንተ የእስራኤል መምህራቸው ነህ ፤
ነገር ግን እንዴት ይህን አታውቅም ? ....
ከሰማይ ከወረደው የሰው ልጅ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ የለም ፤ …
የሰው ልጅ እንዲሁ ይሰቀል ዘንድ አለው፡፡ "
ብለህ አስተማርከው፡፡
አሁንስ ገባው ፤ እውነቱንም አውቆ ጌታውን
ዘመናት አልፈው ሲደርስ ጠብቆ ተራውን
ቢኖርም ተብሎ መምህር ፣ በሌላ ሕግ ተደብቆ
ያለ አንተ ሲኖር ከአይሁድ ተደባልቆ
አሁን ግን ሰጠኸው የእውነት ሕይወት
በመስቀል ላይ ገልጸህ ፍጹም አፍቅሮት
ክብርንም አገኘ በአንተ ስቅለት
ገንዞ እንዲቀብርህ በዓርብ ዕለት !