#ቅድስት፤ #ሁለተኛው_የዐቢይ_ጾም_ሳምንት
‹‹ ሰንበትየ ቅድስት›› የሚልና ይህን የመሰለ የሰንበትን ቅድስና የሚያዘክር ምስጋና የሚቀርብበት ሳምንት ነው፡፡
የዚህቸ የሰንበት ክብር እጅግ ልዩ ነው ከዳግም ምጽዓት በኃላ ጸንታ የሚትቆየው ብቻኛዋ ዕለት ይህች ሰንበት ነች
‹‹ እምኵሉ ዕለት ሰንበት አክበረ
ወእምኵሉን አንስት ማርያምሃ አፍቀረ ››
ከዕለታት ሁሉ ሰንበትን አከበረ ከሴቶች ሁሉ ደግሞ #ማርያምን_አፈቀረ መረጠ ‹‹ቅዱስ ያሬድ ››
#መልካም_ዕለተ_ሰንበት🙏
አጫጭር ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
•➢ 👇 ለማግኘት // 👇
@Enatachn_mareyam

🕊 💖 🕊
[ የዐቢይ ጾም ሁለተኛ ሳምንት ]
💖
[ 🕊 ቅድስት 🕊 ]
ቅድስት ማለት የከበረች የተለየችና የተመሰገነች ማለት ነው ፤ ይኸውም በባሕርዩ ቅዱስ የሆነው ጌታ ጾምን ቀድሶ የጀመረባት ዕለት በመሆኑ ሊቁ ቅዱስ ያሬድ ይህ ሳምንት ቅድስት የሚል ሥያሜ ሰጥቶታል::
ይህ ሳምንት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ስለ እግዚአብሔር የባሕርይ ቅድስና እንዲሁም ቅዱስ እግዚአብሔር ስለቀደሳቸው ቅዱሳን አካላት [ ጾም ቅድስት ፣ ሰንበት ቅድስት ፣ ቤተ ክርስቲያን ቅድስት ወዘተ እያለች ] የምታስተምርበት ሳምንት ነው።
ሰው ሁሉ በቅድስና መንገድ በመመላለስ የክብሩ ባለቤት የመንግሥቱ ወራሽ እንዲሆን እግዚአብሔር " እኔ ቅዱስ ነኝና እናንተም ቅዱሳን ሁኑ " በማለት ስለማስተማሩ ስፊ ትምህርት ይሰጥበታል።
እግዚአብሔርን ማየትና የእግዚአብሔር የሆነውን ሥርዓት መከተል ስለሚያስችል ዕለት ዕለት መልካም በማድረግ ቤተ መቅደስ ተብሎ የተነገረለትን ሰውነታችንን በንጽሕና በመጠበቅ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ዕቃ ሆነን መቅረብ እንደሚገባን ይዘከርበታል።
እግዚአብሔር አምላካችን ቅዱስ ነው እያልን በልባችን አምነን በአፋችን መስክረን በተግባር ግን ከቅድስና ርቀን እንዳንኖር እግዚአብሔር እንደቀደሰንና ልጅነትን እንደሰጠን በማመን በተቀደሰ ሁኔታ መኖር ይገባናል።

[ ቅድስና ምንድነው ? ]
ቅድስና ማለት ቀደስ ባረከ ፤ ለየ ፤ አከበረ ፤ አመሰገነ ፤ አነጻ ፤ ሰውነቱን ከርኩሰት ልቡን ከትዕቢት አራቀ ከሚለው ከግዕዝ ሥርወ ግሥ የተገኘ ኀይለ ቃል ሲሆን ቅድስና ማለት መለየት ፤ መክበር ፤ መመስገን ፣ መንጻትና መጽናት ማለት ነው፡፡
ሰውም ሆነ ሌላውም ነገር ቅዱስ የሚሆነው የእግዚአብሔር ስለሚሆን ብቻ ነው ፤ ሰው ሃይማኖት ይዞ በሥነ ምግባር እየተቀደሰ ሊሄድ ይችላል ፤ [ ዮሐ ፲፯ ፥ ፲፯ ] ዳግመኛ የሰው ልጅ ከመንፈስ ቅዱስ ሲወለድ የቅድስና ሥራ ይጀምራል ፤ በሕይወቱ ደግሞ ቅድስናውን እያሳደገ ይሄዳል ፤ በዕለተ ምጽአት ቅድስናው ፍጹም ይሆናል። [ ፩ኛ ቆሮ.፲፭ ፡ ፶፩ ፣ ፩ኛ ተሰ.፬ ፥ ፬ ]
ቅድስና በአማኝ ሕይወት ውስጥ የሚያድገው በእግዚአብሔር ኀይል ነው ፤ ነቢዩ ሕዝቅኤል " መቅደሴ ለዘለዓለም በመካከላቸው በሆነ ጊዜ እኔ እስራኤልን የምቀድሰው እግዚአብሔር እንደሆንኩ አሕዛብ ያውቃሉ::" በማለት ተናግሯል:: [ ሕዝ ፴፯ ፥ ፳፰ ]
የሰው ልጅ ለእግዚአብሔር አገልግሎት የተለየ በመሆኑ በፍጹም ኀይሉ በፍጹም ነፍሱ በፍጹም ልቡ እግዚአብሔርን መውደድ አለበት:: ቅድስናውና ፍቅሩ ደግሞ ትእዛዙን በመጠበቅ ይገለጣል። [ማር.፲፪ : ፴፫ ፣ ዮሐ.፲፬፥፳፩ ፣ ፊል.፪፥፲፪ ፣ ፩ኛዮሐ.፭፥፳፫ ፣ ዘሌዋ.፲፱፥፪ ፣ ፩ኛ ጴጥ.፩፥፲፭ ]

† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬
[ ቤተክርስቲያንን እንወቅ ]
[ ክፍል - ፳፪ - ]
[ ን ዋ ያ ተ ቅ ድ ሳ ት ! ]
🕊
ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን። "ቤተክርስቲያንን እንወቅ" በተሰኘው ሳምንታዊ መርሐ-ግብር ባለፈው ሳምንት ሥርዓተ አምልኮት በሚለው ዓብይ ርዕስ ሥር ሥርዓተ ቅዳሴ በመጽሐፍ ቅዱስ የሚለውን ተመልክተን ነበረ። ንዋያተ ቅድሳት የተመለከተው የዛሬው መርሐ-ግብር እነሆ !
[ 🕊 ን ዋ ያ ተ ቅ ድ ሳ ት 🕊 ]
ቤተክርስቲያናችን በእግዚአብሔር የተወደደውን አገልግሎቷን ስትፈጽም እግዚአብሔር ለባህርዩ ቆሻሻ ነገር አይስማማውምና እንደ አቤል ለተወደደው መስዋዕቷ ማቅረቢያ ለአገልገሎቷም ማስፈጸሚያ ይሆኑ ዘንድ ንዋያተ ቅድሳቷን እንደየ ሥርዓቱ አዘጋጅታለች፡፡ እግዚአብሔር ቢፈቅድ የተወሰኑትን እንመልከት፡፡
፩. [ ታቦት / ark / ] ፦
ማለት ማደሪያ ማለት ነው ማደሪያነቱም ለልዑል እግዚአብሔር ነው፡፡ ጌታ ሙሴን ሸምሸርሸጢን ከሚባል ከማይነቅዝ እንጨት ርዝመቱን 125 ቁመቱን 75 ወርዱን 75 ሳ.ሜ አድርገህ ታቦትን ቅረጽ በውስጥና በውጭ በወርቅ ለብጠው ፣ ሁለቱን ኪሩቤል እንደሚናተፉ አውራ ዶሮዎች አስመስለህ ቅረጽበት ብሎ አዝዞት እንዳለው አድርጎ ሠርቶታል በአገልግሎት ረገድም የጽላቱ ማኖሪያና እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር የመኖሩ ምልክት ነበር። [ ዘጸ 25 ፥ 1-22 ፣ 40፥20 ]
እስራኤል ታቦትን ያከብሩ ጌታም በርሱአድሮ ብዙ ተአምራትን ያድርግላቸው ነበር። [ ኢያሱ 3፥6 ] [ ሳሙ 4፥6 ] ዛሬም በቤተ መቅደስ መሥዋዕተ ወንጌል የጌታ ሥጋና ደሙ ይፈተትበታል፡፡
ምሳሌነቱም ፦ ታቦት የእመቤታችን ፣ ጽላት የጌታ ፣አንድም ታቦት የእመቤታችን ፣ ጽላት የትስብዕት /የሥጋ/ ቃሉ የአካላዊ ቃል ምሳሌ ነው፡፡ አንድም ታቦት የጌታ ፣ የማይነቅዝ እንጨት የእመቤታችን ምሳሌ ፤ ከማይነቅዝ እንጨት መሠራቱ ጌታ በኃጢአት ከማትለወጥ ከእመቤታችን ለመወለዱ ምሳሌ ነው፡፡
፪. [ ጽላት /Tablet of the law/ ] ፦
ጽላት ማለት ሰሌዳ አንድም መጸለያ ማለት ነው የመጀመሪያዋ ጽላት በግብር አምላካዊ የተገኘች 2 ክፍሎች ያሏትና 10ሩ ትእዛዛት የተጻፈባት ሙሴ በደብረ ሲና ከጌታ የተቀበላት ኋላም እስራኤል ለጣኦት ሲሰግዱ አይቶ ቢደነግጥ ከእጁ ወድቃ የተሰበረችው የዕንቁ ጽላት ናት። [ ዘጸ 32፣15-20 ]
ሁለተኛዋ ሙሴ በፊተኛዋ አምሳል መሠረት በግብር አምላካዊ 10ሩ ትዕዛዛት የተጻፈባት በቤተ መቅደስ በታቦቱ ላይ ሆና ኃይል ታደርግ የነበረችና /ዘጸ 34፣1-28/ በንጉሥ ሰሎሞን ዘመን ወደ ሀገራችን መጥታ በአክሱም ጹዮን እንደተቀመጠች የሚነገርላት የዕብነበረድ ጽላት ናት፡፡ ምሳሌነቷ ከላይ ተገልጿል ጸሎተ ቅዳሴው ታቦቱንና ጽላቱን አንድ አድርጎ ታቦት እያለ ይጠራዋል፡፡
፫. [ መንበር / Throne / ] ፦
ከወርቅ ፣ ከብር ፣ ከብረት ወይም ከእንጨት ይሠራል አገልግሎቱም ከቤተ መቅደስ ታቦት /ጽላት/ ይቀመጥበታል። ጸሎት ይጸለይበታል ፤ መሠዋዕት ይሠዋበታል ፤ በመንበሩ ላይ በመደበኛነት የሚቀመጡ ንዋያተ ቅድሳት ታቦት /ጽላትና/ ሥዕለ ማርያም ምስለ ፍቁር ወልዳ ሲሆኑ በቅዳሴ ጊዜ ሥጋውን ደሙን ለመፈተት የምንገለገልባቸው ጻሕል ፣ ጽዋዕ ፣ ማኀፈዳት ፣ ዕረፈ መስቀል ፣ መስቀል ፣ ዕጣን ይቀመጡበታል፡፡
መንበሩን የሚዳስሱና የሚያገለግሉበት ቀሳውስቱ ናቸው ዲያቆናት ግን ከበውት ይቆማሉ፡፡
ምሳሌነቱም ፦ መንበር የእመቤታችን ፣ ታቦት /ጽላት / የጌታ ፣ አንድም መንበር የመንበረ ጸባዖት ፣ ታቦት /ጽላት/ የሰማያዊ ንጉሥ የጌታ ፣ ልዑካን የሠራዊተ መላእክት ምሳሌ ነው፡፡
[ በቀጣይ ብንኖር ታቦት በሐዲስ ኪዳን ያለውን ትርጓሜና አገልግሎት በሰፊው የሚቀርብ ይሆናል። ]
[ ይቆየን ]
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፥ ወለወላዲቱ ድንግል ፥ ወለመስቀሉ ክቡር፡፡
† † †
💖 🕊 💖

[ † እንኳን ለሐዋርያው ቅዱስ ኩትን ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † ]
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †
🕊 † ሐዋርያው ቅዱስ ኩትን † 🕊
† ቅዱስ ኩትን በዘመነ ሐዋርያት የነበረ : ከአሕዛብ ወደ ክርስትና በቅዱስ ዻውሎስ አማካኝነት የተመለሰ : ከቅዱሳን ሐዋርያት እግር ሥር ቁጭ ብሎ ይማር ዘንድ የታደለ : በፍፁም ድንግልናው የተመሰገነ ሐዋርያዊ አባት ነው::
ይህ ቅዱስ ሚስት ነበረችው:: ግን በትዳር ውስጥ ሆኖ ድንግልናን መጠበቅ እንደሚቻል ያሳየ የሐዲስ ኪዳን ሰው ነው:: ቅዱስ ኩትን በንጽሕናው : በአገልግሎቱና በጣዕመ ስብከቱ በሐዋርያትና ምዕመናንም ተወዳጅ ነበር:: ለብዙ ዘመናት በወንጌል አገልግሎት ኑሮ በዚሕች ቀን በመልካም ሽምግልና አርፏል::
† ፈጣሪ ከበረከቱ ያድለን::
🕊
[ † መጋቢት ፱ [ 9 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
1. ቅዱስ ኩትን ሐዋርያ
2. ቅዱስ እንድርያኖስ ሰማዕት
3. ቅዱስ አውሳብዮስ ሰማዕት
4. ፳፻ [2,000] ሰማዕታት [የአባ ኖብ ማሕበር]
[ † ወርሐዊ በዓላት ]
፩. አባ በርሱማ ሶርያዊ [ለሶርያ መነኮሳት ኁሉ አባት]
፪. አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ]ኢትዮዽያዊ]
፫. ፫፻፲፰ [318ቱ] ቅዱሳን ሊቃውንት [ርቱዐነ ሃይማኖት ዘኒቅያ]
፬. የብሔረ ብፁዐን ጻድቃን
፭. አባ መልከ ጼዴቅ ዘሚዳ [ኢትዮዽያዊ]
፮. ቅዱስ ዞሲማስ ጻድቅ [ዓለመ ብፁዐንን ያየ አባት]
† " . . . ስለ ድንግልናው ያፈረ ሰው ቢኖር የወደደውን ያድርግ:: ቢያገባም ኃጢአት የለበትም:: ሳይናወጥ በልቡ የጸና ግን ግድ የለበትም:: የወደደውን እንዲያደርግ ተፈቅዶለታል:: ድንግልናውንም በልቡ ይጠብቅ ዘንድ ቢጸና መልካም አደረገ:: እንዲሁም ድንግልን ያገባ መልካም አደረገ:: ያላገባም የተሻለ አደረገ:: " † [ ፩ቆሮ.፯፥፴፮-፴፰ ] ( 7:36-38 )
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
† † †
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

👉 ሰዋች ታናሽነትህን እና ትሕትናህን አይተው እንዲያከብሩህ እንጂ፣
ለራስህ ክብር ሰጥተህ፣
ሌሎች ላይ በመጫን እንዲያከብሩክ አትፈልግ።
'ማክበር' ከልብ የሚፈልቅ ስሜት እንጂ፣ ተገድዶ የሚመጣ ባለ መኾኑ፣
ሰዎች እንዲያከብሩህ አታስገድዳቸው።
👉 አንድ ሰው እንዲታዘዝህ ልታስገድደው ትችል ይሆናል፤
እንዲያከብርህ ግን ማስገደድ ፈጽሞ አይቻልም።
ኹለቱንም አስገድዶ ማስፈጸም ደግሞ አምባገንነት ነው።
👉 ሰዎችን ስትቀርብ ቀላል እንጂ ኃይለኛ ነፋስ አትኹን፤
ብዙዎች 'ኃይል' መለያቸው ስለ ኾነ 'ማዕበል' ሆነው መቅረብ ይወዳሉ።
በቀላል ነፋስ የተመሰሉት 'ትሑታን' እና 'ታጋሾች' ግን የሚለዩት፣ ራሳቸውን ዝቅ በማድረጋቸው ነው፤
ከሰዎች ጋር ስትቀርብም ደግሞ 'ራስኽን በመውደድ' አይኹን።
'በወንድሞች መዋደድ፥ ርስ በርሳችኊ ተዋደዱ" ተብሏል።
ይኽም ያለ ማቆላመጥ ከልብህ በትሕትና ይሁን"

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን †
[ † እንኳን ለቅዱስ ዕፀ መስቀል ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † ]
† መጋቢት ፲ [ 10 ] †
🕊 † ቅዱስ ዕፀ መስቀል † 🕊
ለስም አጠራሩ ጌትነት ይሁንና ቸር አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ለማዳን ከሰማያዊ ክብሩ ወደ ምድር ወርዶ: በማሕጸነ ማርያም እግዝእት በኪነ ጥበቡ ተጸንሶ: በኅቱም ድንግልና ተወልዶ: በፈቃዱ መከራ መስቀልን ተቀብሎ: ከግራ ቁመት: ከገሃነመ እሳት: ከሰይጣን ባርነት: ከኃጢአት ቁራኝነትም አድኖናል::
"እምእቶነ እሳት ዘይነድድ አንገፈነ" እንዳለ ሊቁ::
ምንም መስቀል በብሉይ የወንጀለኞች መቅጫ ሆኖ ቢቆይም እግዚአብሔር ለዓለም መዳኛነት የመረጠው ነውና ሕብረ ትንቢቶች ሲነገሩለት: በብዙ ሕብረ አምሳልም ሲመሰል ኑሯል:: ከተፈጥሯችን ጀምሮ ዓለም ራሷ አርአያ ትዕምርተ መስቀል ናት::
እግዚአብሔር ለቃየን እንዳይገድሉት ከሰጠው ምልክት [ዘፍ.፬፥፲፭] (4:15) ጀምሮ ይስሐቅ ሊሰዋ የተሸከመው እንጨት[ዘፍ.፳፪፥፮] (22:6): ቅዱስ ያዕቆብ ያያት የወርቅ መሰላል [ዘፍ.፳፰፥፲፪] (28:12): ያዕቆብ የዮሴፍን ልጆች የባረከበት መንገድ[ዘፍ.፵፰፥፲፬] (48:14): ባሕረ ኤርትራን የከፈለችው የሙሴ በትር [ዘጸ.፲፬፥፲፭] (14:15): የናሱ ዕባብ የተሰቀለበት እንጨት [ዘኁ.፳፩፥፰] (21:8) ጨምሮ በርካታ ምሳሌዎች ለቅዱስ መስቀሉ መኖራቸውን መተርጉማን ተናግረዋል::
ቅዱስ ዳዊትን የመሰሉ ነቢያት ደግሞ "ለሚፈሩሕ ከቀስት ያመልጡ ዘንድ ምልክትን ሰጠሃቸው" እያሉ መስቀሉን ከርቀት ተመልክተዋል:: [መዝ.፶፱፥፬] (59:4)
በሐዲስ ኪዳን ግን ምሳሌው ገሃድ ሆኖ: ጌታ በዕፀ መስቀል ላይ ተሰቅሎ ሥጋውን ቆረሰበት: ደሙን አፈሰሰበት: ዓለምንም አዳነበት:: ስለዚህም "መስቀል ብርሃን ለኩሉ ዓለም: መሠረተ ቤተ ክርስቲያን" ተብሎ የሚመሰገን ሆኗል::
+ቅዱስ ያሬድ ሊቁ አክሎ "መስቀል መልዕልተ ኩሉ ነገር: ያድኅነነ እምጸር" ብሎ ጠላትን ማሳፈሪያ መሆኑን ይነግረናል:: ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ዻውሎስም ስለ መስቀሉ አምልቶ አጉልቶ አስተምሯል:: መመኪያችን ነውና:: [፩ቆሮ.፩፥፲፰] (1:18), ]ገላ.፮፥፲፬] (6:14)
አንዳንዶቹ እኛን 'የተሰቀለውን ትታቹሃል' ይሉናል::
የተሰቀለውማ የጌቶች ጌታ: የነገሥታት ንጉሥ: የአማልክት አምላክ: ሁሉ በእጁ የተያዘ: ኢየሱስ ክርስቶስ ነውና ከኦርቶዶክስ በላይ የሚያመልክ በወዴት አለና::
ነገር ግን መስቀሉን ንቆ የተሰቀለውን ማክበር አይቻልምና እኛ ለመስቀሉ የጸጋ ስግደትን እንሰግዳለን : እናመሰግነዋለን: እናከብረዋለን: ቤዛ: ጽንዕ: መድኃኒት: ኃይል እያልንም እንጠራዋለን:: አባቶቻችን በመስቀሉ ምርኩዝነት ማዕበለ ኃጢአትን: ባሕረ እሳትን ተሻግረዋል::
በመስቀሉ ቢመኩ አጋንንትን ድል ነስተዋል:: ጠላትንም አሳፍረዋል:: እኛም በመስቀሉ አምነን ከብረን: ገነን እንኖራለን:: ተጠቅመንበታልና ከራሳችን ሕይወት በላይ ምስክርን አንፈልግም::
🕊 † በዓለ መስቀል † 🕊
በዚች እለት የክብር ባለቤት ጌታችን አምላካችንና መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት መስቀል የተገለጠበትና የተገኘበት ነው ። የዚህም የከበረ ዕፀ መስቀል መገለጡና መገኘቱ ሁለት ጊዜ ሆኗል።መጀመሪያ የፃድቁ ንጉስ የቆስጠንጢኖስ እናት በሆነች በንግስት ህሌኒ እጅ ነው።
"እርሷ ለእግዚአብሄር ተስላ ነበርና ልጇ ቆስጠንጢኖስ ወደ ክርስቲያን ሀይማኖት ቢገባ ወደ ኢየሩሳሌም ሄዳ መስቀሉን እስከ አገኘችው ድረስ ልትፈልግው በኢየሩሳሌም ያሉ ቅዱሳት መካናትንና አብያተ ክርስቲያናትን ልታንፃቸው ነው። ከዚህ በኃላ ልጇ አምኖ የክርስትና ጥምቀትን በተጠበቀ ጊዜ እሌኒ ቅድስት ወደ ኢየሩሳሌም ሄደች ከእረሷ ጋርም ብዙ ሰራዊት ነበር ደርሳም ስለ ከበረ መስቀል መረመረች የሚያስረዳት አላገኘችም የአይሁድ ወገን የሆነ አንድ ሽማግሌ ሰው አስራ በርሀብና በጥማት አሰቃየችው ።
በተጨነቀም ጊዜ ለንግስት እሌኒ የጉልጎታን ኮረብታ አስጠርጊ ብሎ ነገራት እርሷም ይጠርጉ ዘንድ አይሁድን አዘዘቻቸው። ቤቱን የሚጠርግ ሰው ሁሉ ጥራጊውን በውስጡ የከበረ መስቀል በአለበት በጌታችን መቃብር ላይ እንዲጥል አይሁድ አስቀድመው አዝዘው ነበርና ንግስት እሌኒ እስከ ደረሰችበት ጊዜ ከሁለት መቶ አመት በላይ ጥራጊያቸውን ሲጥሉበት ኖሩ ኮረብታም ሆነ።
አይሁድም በጠረጉ ጊዜ ሶስት መስቀሎች ተገለጡ የክብር ባለቤት ክርስቶስ የተሰቀለበት የትኛው እንደሆነ አላወቁም። የሞተ ሰውም አግኝተው አመጡ ። አንዱንም መስቀል አምጥተው በሞተው ሰው ላይ አኖሩት አልተነሳም ደግሞ ሌላውን መስቀል አምጥተው በሙቱ ላይ አኖሩ አሁንም አልተነሳም ከዚህም በኃላ ሶስተኛውን መስቀል አምጥተው በሙቱ ላይ አደረጉት ያንጊዜ የሞተው ሰው ተነሳ እሌኒም የክርስቶስ መስቀል እንደሆነ አውቃ ሰገደችለት የክርስቲያንም ወገኖች ሁሉ ሰገዱለት።
ለልጅዋ የላከችው ይህ መስቀል ነው የሚል በሌላ መፅሀፍ ይገኛል የቀረው ግን ግንዱ በውስጡ ተተክሎበት የነበረው ከእርሱም እኩሌታውን ከቅንዋቱ ጋራ ወደ ልጅዋ የላከችው ነው። ከዚህም በኃላ ስራአታቸውና የህንፃቸው ነገር በመስከረም ወር በአስራ ሰባት ተፅፎ የሚገኝ አብያተ ክርስቲያናትንና የከበሩ ቦታዎችን አነፀች።
ሁለተኛው በሮሙ ንጉስ በህርቃል ዘመን የሆነው ሲሆን የፋርስ ሰዎች በግብፅ አገር ሳሉ ወደ አገራቸው ሊመለሱ ወደዱ። ከሹማምንቶቻቸው አንዱ የጦር መኰንን ተነጥሎ ወደ ኢየሩሳሌም አልፎ ደረሰ ወደ ከበረ መስቀል ቤተ ክርስቲያንም ገባ። መስቀሉም በላዮ በተተከለበት ግንድ ፊት ታላቅ ብርሀን ሲበራ አይቶ ሊያነሳው እጁን ዘረጋ። እሳትም ወጥታ እጁን አቃጠለችው።
ከክርስቲያን በቀር ማንም ሊነካው እንደማይችል የመስቀልን የክብሩን ነገር ሰዎች ነገሩት። ሁለት ዲያቆናትንም ይዞ የከበረ መስቀልን እንዲሸከሙ አዘዛቸወወ ከኢየሩሳሌምም ብዙ ሰዎችን
ማርኮ ወደ አገሩ ተመለሰ።
የፋርስ ሰዎች ኢየሩሳሌምን እንዳጠፏት ብዙዎች ሰዎችንም እነድ ማረኩና የከበረ የክርስቶስንም መስቀሉን እንደ ወስዱየሮም ንጉስ ህርቃል በሰማ ጊዜ እጅግ አዘነ። ስለርሱም እንዲፆሙ ምእመናንን አዝዞ ወደፋርስ ዘምቶ ወጋቸው ብዙዎችንም ገደላቸው የከበረ እፀ መስቀልንም እየፈለገ በሀገራቸው ሁሉ ዞረ ግን አላገኘውም።
ያ ዲያቆናቱና መስቀሉን የወሰደ መኰንን ከቦታዎች በቤቱ አነፃር ባለ በአንድ ቦታ ላይ ወስዷቸው ጥልቅ ጉድጓድእንዲቆፍሩ አዝዞ በዚያ የከበረ መስቀልን አስቀበረ እነዚያንም ዲያቆናት ገደላቸው።
ነገር ግን ያ መኰንን የማረካት የካህናት ወገን የሆነች በእርሱ ቤት የምትኖር አንዲት ብላቴና ነበረች። እርሷም የከበረ መስቀልን ሲያስቀብርና ሁለቱን ዲያቆናት ሲገድላቸው በቤቱ ውስጥ ሁና በመስኮት ትመለከት ነበር ወደ ንጉስ ሕርቃልም ሂዳ መኰንኑ ያደረገውን ሁሉ ነገረችው።
ይህንንም ንጉስ ሰምቶ እጅግ ደስ አለው ያቺ ብላቴናም መራችው ከእርሱም ጋራ ብዙ ሰራዊት ሆኖ ኤጲስቆጶሳትና ካህናትም ነበሩ ።ወደ ቦታውም እስከምታደርሳቸው ያቺን ልጅ ተከተሏት ቅፍረውም የከበረ እፀ መስቀልን አገኙት ከአዘቅቱም አወጡት ንጉሱና ሰራዊቱም ሰገዱለት።

በልብሰ መንግስቱም አጐናፀፈው ታላቀወ ክብርንም አከበረው እጅግም ደስ አለው ከሰራዊቱ ጋር። የዚህም መስቀል ሁለተኛ የተገለጠበትና የተገኘበት በዚች ቀን በመጋቢት አስር ነው። ከዚህ በኃላ ንጉሱ የከበረ እፀ መስቀልን ተሸክሞ ወደ ቁስጥንጥንያ ከተማ ወሰደው።
መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ካረገ ከዓመታት በሁዋላ አይሁድ በአንድ ነገር ተቸገሩ:: የክርስቶስን ሐዋርያት እያሳደዱ ቢገድሉም ከመስቀሉና ሥጋ ክርስቶስ አርፎበት ከነበረው ጐልጐታ ላይ የሚደረገውን ተአምር ግን መግታት አልተቻላቸውም::
መቼም ለተንኮል አያርፉምና ቅዱስ መስቀሉን ሽፍቶቹ ከተሰቀሉባቸው ጋር ደርበው አርቀው ቀበሩት:: አካባቢው የጉድፍ መጣያ እንዲሆንም አዋጅ ነገሩ:: ለክፋት ሲሆን ተባባሪው ብዙ ነውና ለ፫፻ [300] ዓመታት ያህል ቆሻሻ ቢጥሉበት
ተራራ ሆነ::
ከዚህ ሁሉ ነገር በሁዋላ እናታችን ቅድስት እሌኒ [ሔለና] በመንፈስ ቅዱስ አነሳሽነት: በቅዱስ ኪራኮስ መሪነት: በቅዱስ ሚካኤል ረዳትነት ደመራ አስደምራ: እጣን አጢሳ መካነ መስቀሉን አገኘች::
መስከረም ፲፯ [17] ቀን የተጀመረው ቁፋሮ መጋቢት ፲ [10] ቀን ተጠናቆ: ንጹሕ መስቀሉ ወጥቶ ብርሃን በርቷል: ሙታን ተነስተዋል:: ከ፲ [10] ዓመት በሁዋላም የመስቀሉ ቤተ መቅደስ
ታንጾ መስከረም ፲፯ [17] ቀን ተቀድሷል::
ይህ ቅዱስ ዕፀ መስቀልም በደጉ አፄ ዳዊት ዘመን ወደ ሃገራችን መጥቶ: በጻድቁ አፄ ዘርዓ ያዕቆብ አማካኝነት በደብረ ከርቤ [ግሸን ማርያም] ተለብጦ ተቀምጧል::
አምላከ ቅዱሳን በኃይለ መስቀሉ: በሞገሰ መስቀሉ ይጠብቀን:: ከበረከቱ አሳትፎ በዓሉን የሰላም ያድርግልን::
🕊
[ † መጋቢት ፲ [10] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. ቅዱስ ዕፀ መስቀል
፪. ቅድስት ዕሌኒ ንግሥት
፫. ቅዱስ ኪራኮስ አረጋዊ
፬. ቅዱስ መቃርስ ዘኢየሩሳሌም
[ † ወርሐዊ በዓላት ]
፩. ቅዱስ ናትናኤል ሐዋርያ
፪. ቅዱስ ኒቆላዎስ ዘሃገረ ሜራ
፫. ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ ጻድቅ ንጉሥ
፬. አቡነ መልክዐ ክርስቶስ
፭. ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ [ወልደ እልፍዮስ]
" የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት : ለእኛ ለምንድን ግን የእግዚአብሔር ኃይል ነውና . . . መቼም አይሁድ ምልክትን ይለምናሉ:: የግሪክ ሰዎችም ጥበብን ይሻሉ:: እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን:: " [፩ቆሮ.፩፥፲፰-፳፫] (1:18-23)