Telegram Web Link
በገጠር የመሬት ሽያጭ እና ግዢ የሚያከናውኑ ሰዎችን እስከ አምስት አመት በእስር የሚያስቀጣ አዋጅ በፓርላማ ጸደቀ

የገጠር መሬትን በሸጠ ወይም በገዛ ማንኛውም ሰው ላይ እስከ አምስት ዓመት የሚደርስ ፅኑ እስራት ቅጣት የሚጥል አዋጅ በተወካዮች ምክር ቤት ጸደቀ። አዲሱ አዋጅ የግል፣ የወል ወይም የመንግስት ይዞታን በህገ ወጥ መንገድ ወርሮ ለተገኘ ሰውም ተመሳሳይ የእስራት ቅጣት ደንግጓል።

የተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ማክሰኞ ግንቦት 6፤ 2016 በነበረው መደበኛ ስብሰባው በሙሉ ድምጽ ያጸደቀው ይህ አዋጅ፤ ከ18 ዓመት በፊት የወጣውን የገጠር መሬት አስተዳደር እና አጠቃቀም አዋጅን ያሻሻለ ነው። አዲሱ አዋጅ አርሶ አደሮች፣ አርብቶ አደሮች እና ከፊል አርብቶ አደሮች በመሬት ላይ ያላቸውን መብቶች ያሻሻለ ሲሆን፤ የሴቶች እና ድጋፍ የሚሹ ሰዎችን የመሬት ተጠቃሚነት መብት ያረጋገጡ ድንጋጌዎችንም አካትቷል።

አዋጁ በረቂቅ ደረጃ ለፓርላማ ከቀረበ በኋላ ከተደረጉ ማሻሻያዎች መካከል፤ “የወንጀል ተጠያቂነት” በሚመለከተው የተጨመረው አንቀጽ ይገኝበታል። “ከመሬት ጋር ተያይዘው የሚፈጸሙ ወንጀሎች ላይ አስተማሪ እና ተመጣጣኝ ቅጣት ማስቀመጥ አስፈላጊ በመሆኑ” ምክንያት እንደተካተተ የተነገረለት ይህ ድንጋጌ፤ ከመሬት ወረራ እስከ መሬት ሽያጭ ድረስ ያሉ የህግ ጥሰቶች የሚያስከትሏቸውን ቅጣቶች ዘርዝሯል።

ማንኛውም ሰው መሬት የሸጠ ወይም የገዛ እንደሆነ፤ ከ100 ሺህ እስከ 200 ሺህ ብር ወይም ከ1 ዓመት እስከ 5 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት ወይም በሁለቱም ሊቀጣ እንደሚችል በአዲሱ ድንጋጌ ላይ ሰፍሯል። በኢፌዲሪ ሕገ መንግስት መሰረት “መሬት የማይሸጥ፣ የማይለወጥ የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የጋራ ንብረት ነው”።

ሕገ መንግስቱ የገጠርም ሆነ የከተማ መሬት የባለቤትነት መብትን የሰጠው “ለመንግስት እና ለህዝብ” ነው። ዛሬ በጸደቀው አዋጅ የግል፣ የወል ወይም የመንግስት ይዞታን በህገ ወጥ መንገድ የወረረ ማንኛውም ሰው፤ ከ1 ዓመት እስከ 5 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት አሊያም ከ30 ሺህ እስከ 100 ሺህ ብር ቅጣት ሊጣልበት እንደሚችል ተደንግጓል።

በእነዚህ ይዞታዎች ላይ ጉዳት አድርሶ የተገኘ ማንኛውም ሰው፤ ከ3 ዓመት እስከ 7 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት ወይም ከ50 ሺህ እስከ 150 ሺህ ብር እንደሚቀጣም በአዋጁ ላይ ተቀምጧል። ባልተፈቀደ ቦታ ላይ ማንኛውንም ግንባታ የሰራ ወይም እንዲሰራ የፈቀደ ሰው ደግሞ በአዲሱ አዋጅ መሰረት ከ1 ዓመት እስከ 3 ዓመት በሚደርስ እስራት አሊያም ከ25 ሺህ እስከ 50 ሺህ ብር ይቀጣል።

እነዚህ ቅጣቶች፤ ከመሬት አጠቃቀም ዕቅድ ውጪ ይዞታውን ጥቅም ላይ አውሎ የተገኘ ሰው ላይ በተመሳሳይ መልኩ ተግባራዊ የሚደረጉ ይሆናል። ሀሰተኛ የመሬት ይዞታ ማስረጃ ያቀረበ ባለይዞታ እንዲሁም ማስረጃ የሰወረ ወይም የተሳሳተ ማስረጃ የሰጠ ባለሙያ ላይ የሚጣለው እስራት ከላይ እንዳሉት የህግ ጥሰቶች ተመሳሳይ ቢሆንም የገንዘብ ቅጣቱ መነሻ ግን ወደ 20 ሺህ ብር ዝቅ ብሏል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ይሄ እብደት አሁንም አልቆመም እንዴ ? መቼ ነው እንደ ስው ምታስቡት ግን እኛ ስለ እናንተ ደከመን
ሃሰተኛ ዩቲዩበሮችን መያዙ ቀጥሏል፣ ህፃናትን አርጃለሁ በማለት ቪዲዮ የሰራችው ተያዘች።
በዩቲዩብ ሃሰተኛ ታሪኮች እውነተኛ በማስመሰል ከሰሩት መካከል ይህቺ "ገነት ግርማ" ትባላለች ሺ ህፃናትን አርጃለው ይኼኛው አንድ ሺ አንደኛዬ ነው ብላ ቪዲዮዎችን የሰራችው በውጪ ቋንቋዎችም እስኪተረጎም ያበቃችው በቅን ልቦች ከፊንፊኔ ፖሊስ ኮሚሽን ጋር በመተባበር በተሰራ ብርቱ ክትትል በቁጥጥር ስር ውላ በአሁን ሰዓት በየካ ፖሊስ መምሪያ እንደምትገኝ ታውቋል
ፖሊስ እየወስደ ያለው እርምጃ ቢዘገይም በጣም ደስ የሚያሰኝ ነው ።
https://www.tg-me.com/danny4677
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ፊንፊኔ ውስጥ የነበረ የኤርትራውያን ስር ግ ላይ የሻቢያ/ህግደፍ ደጋፊ እና የብርጌድ ንሀመዱ ደጋፊዎች እንደዚህ ሲፈላለጡ ውለዋል የምስራቅ አፍሪካ ፖለቲካ ድንቁርና ተጨምሮበት የመጠፋፊያ መንገድ ሆኗል ደሞ ለህዝብ ነው ምታገለው ይልሀል እንደዚህ ባገኘበት እየተፈላለጠ
https://www.tg-me.com/danny4677
#ብልፅግና_ፓርቲ እና #ህወሃት ግጭት የሚፈጥሩ አዝማምያዎች በጋራ ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የጋራ መግባባት ላይ መድረሳቸው ተገለጸ

በብልፅግና ፓርቲ እና በሕወሃት መካከል የተጀመረው የፓርቲ ለፓርቲ ፓለቲካዊ ውይይት ለሶስተኛ ግዜ በመቐለ ከተማ በዛሬው ዕለት በመቐለ ተካሂዷል።

ሁለቱም አካላት ለዘላቂ ሰላም መረጋገጥ በጋራ በቁርጠኝነት ለመስራት ተስማምተዋል ተብሏል። “ማናቸውንም ጉዳዮች በሰላማዊ መንገድና በውይይት እየፈቱ ለመሄድ ሁለቱም አካላት የበኩላቸውን ፓለቲካዊ ድርሻ ለመወጣትና በቁርጠኝነት ለመስራት ተስማምተዋል።

በተያያዘም የሚኖሩ የኮሙዩኒኬሽን ስራዎች የሰላም ሂደቱን የሚደግፉ እና ግጭት ቀስቃሽ ከሆኑ ንግግሮችና ይዘቶች የተቆጠቡ እንዲሆኑ መግባባት ላይ ደርሰዋል ሲል ኢፕድ ዘግቧል።

በተጨማሪም በቅርቡ በ #ራያ የተፈጠረውን የግጭት ክስተት በተመለከተም በዝርዝር ውይይት ያካሄዱት ፓርቲዎቹ “ክስተቱ መፈጠር ያልነበረበትና ከተጀመረው ዘላቂ ሰላም የማረጋገጥ ሂደት ጋር የሚቃረን እንደሆነ” መግባባት ላይ ደርሰዋል።

የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነትን ወደ መሬት ለማውረድ እየተሰሩ ላሉ ስራዎች ስኬት ምቹ ፓለቲካዊ ሁኔታ ለመፍጠር ሁለቱም ፓርቲዎች ኃላፊነታቸውን ለመወጣት፤ በቀጣይም በሌሎች አጀንዳዎች ላይ ለመወያየት ተስማምተዋል።

================

https://www.tg-me.com/danny4677
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የፋኖ ኃይሎች “ውይይትን አልቀበልም ማለታቸው ለራሳቸውም እንደማይጠቅማቸው” በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ተናገሩ። የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ተዋጊዎች “በድርድር ተስፋ ሳይቆርጡ፣ መተማመንን ለመገንባት ጥረት” እንዲያደርጉም አሳስበዋል።
https://www.tg-me.com/danny4677
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
በኢትዮጵያ ያሉ ሁሉም የታጠቁ ኃይሎች “ጊዜያዊ ሀገር አቀፍ የተኩስ ማቆም” እንዲያደርጉ የአሜሪካ አምባሳደር ጠየቁ

በኢትዮጵያ ያሉ ሁሉም የታጠቁ ኃይሎች “ጊዜያዊ ሀገር አቀፍ የተኩስ ማቆም” እንዲያደርጉ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኢርቪን ማሲንጋ ጥሪ አቀረቡ። ታጣቂዎቹ ትምህርት ቤቶች፣ የጤና ተቋማትን እና የውሃ መሰረተ ልማቶችን ኢላማ ማድረጋቸውን እንዲያቆሙም አምባሳደሩ አሳስበዋል።

በአምባሳደርነት ተሹመው ወደ ኢትዮጵያ ከመጡ ስምንት ወር የሞላቸው ማሲንጋ፤ ከእርሳቸው በፊት በነበሩ አምባሳደሮች ሲተገበር እምብዛም ያልታየውን ይፋዊ የፖሊሲ መልዕክት በዛሬው ዕለት አስደምጠዋል። አምባሳደሩ መልዕክታቸውን ለማስተላለፍ የመረጡት ታሪካዊው የአሜሪካን ግቢ፤ የንግግራቸው ማጠንጠኛ ከነበረው የሰብዓዊ መብት ጉዳይ ጋር ቁልፍ ተዛምዶ ያለው ነው።

በአሁኑ ወቅት የየመን ማህበረሰብ ትምህርት ቤት አካል የሆነው የቀድሞው የአሜሪካ ቆንስላ ግቢ፤ በጣሊያን ወረራ ወቅት የየካቲት 12 ጭፍጨፋ ሲካሄድ 750 የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን ተሸሽገውበት የነበረ ነው። ማሲንጋ በንግግራቸው ወቅቱን ሲያስታውሱ፤ “በሺህዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ያለምንም ማስረጃ እና የህግ ሂደት “ኢላማ የተደረጉበት ነበር” ብለዋል።

የአሜሪካው አምባሳደር ድሮ እና ዘንድሮን ባነጻጸረ ንግግራቸው፤ ወደ 20 ሺህ ገደማ ኢትዮጵያውያን ያለቁበት የጣሊያኑ ጭፍጨፋ ከተፈጸመ ከ87 ዓመታት በኋላ፤ በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች እና በመላው ዓለም የሚገኙ ኢትዮጵያውያን “ተመሳሳይ ፍርሃትን መጋፈጣቸውን ቀጥለዋል” ብለዋል። ሽፍታዎች፣ የታጠቁ ቡድኖች፣ አንዳንዴም የመንግስት የጸጥታ ኃይሎች፤ በህይወት የመኖር፣ የሰብዓዊ ክብርን፣ መከበርን በመሰሉ መብቶች ላይ “ያለምንም ተጠያቂነት ጥሰቶች ይፈጽማሉ” ሲሉ ማሲንጋ በንግግራቸው ወንጅለዋል።
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሁሉም ታጥቆ ህዝብ መሀል ሆኖ እየተኮስ እንዴት ሀገራችን ስላም ትሁን ታድያ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ይሄ ግለሰብ ሲሰርቅ ተይዞ ነው በህዝብ እየተደበደበ ያለው ቲክቶክ ላይ ህዝብን የሚዘርፉትን ነውረኞች ስብስቦ ለህግ የሚያቀርብ ወይም የሚቀጣ ሊኖር ይገባል
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
እነዚህ ደግመው ከአለቆቻቸው ጋር መጣላት ጀመሩ እንዴ ?
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ይቺ የሲዳማ ወጣት በመዳ ወላቡ ዩንቨርስቲ ቆይታዎ አፋን ኦሮሞ ተምራ በአፋን ኦሮሞ ኢንተርቪው ማድረግ ችላለች ቋንቋ መማር ይጠቅማል
https://www.tg-me.com/danny4677
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ኦሮምያ ላይ ከባለቤቱ በላይ በሰላም ወጥቶ በሰላም ገብቶ የሚኖር ማህበረስብ ጉራጌ ነው የፋኖ ኮፒ ሆኜ ሀገር እበጠብጣለው ማለት እንደ ፋኖ ገዳም እና ቁጥቋጦ ውስጥ ኑሮዬን እገፋለው ማለት ነው እና የኢትዮጵያ ህዝብን እና መንግስትን በጊዜ ይቅርታ ጠይቃቹ ወደ ሥራቹ ተመለሱ።
https://www.tg-me.com/danny4677
ወያኔ የኦሮሞን ህዝብ እንዴት ገሽልጦ ዘርፎ አራቁቶ መንገድ እንኳን ሳይሰራ ነው የሄደው ህዝባችን ዛሬም ስቃዩ ቀጥሏል
በ2014 እኤአ በአለም ባንክ በተዘጋጀው ፎረም ላይ በቀረበው ሪፖርት መሰረት የሻኪሶ የወርቅ ማምረቻ ከ 1997-2014 ድረስ ባሉት 16 አመታት 52 0444.71 ኪሎ ግራም ወርቅ አምርቶ 17.24 ቢሊዮን ብር እንደሸጠ ያሳያል።

ይሄ ከስር የምንመለከተው ደግሞ የሻኪሶ መንገድ ነው።
.
.
.
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የአፍሮ ስቱድዮ ባለቤት ወ/ሮ ልደት አበባው እና በጋዜጠኝነት ያየናት
ወ/ሮ ታደለች ብርሀኔ በትወና
ህፃን ናትናኤል መስፍን፣ በትወና ወጣት ካሊድ ዱጉማ ከባህልና እሴታችን ባፈነገጠ መልኩ እና በሚዘገንን አንድ በእድሜ የገፋች እናት ከ13 ዓመት በማይበልጥ ህፃን ያረገዝኩት ላንተ ሳይሆን ላባትህ ነው ስትል የሚያሳይ አፀያፊ ቪዲዮ በማሰራት በሚድያ ሲያስተላልፉ የነበሩት የዩትዩብ ባለቤቶች በዛሬው እለት ፊንፍኔ ከተማ ላይ በቁጥጥር ስር ውለዋል።
ፖሊስ የጀሙረውን አኩሪ ተግባር ይቀጥልበት
https://www.tg-me.com/danny4677
እንዴት አይነት አውሬ ተፈልፍሎ ነው የተለቀቀብን ???

ይቺ ምስኪን ተደፈረች መደፈሯን እና ፍትህ ማጣቷን ስትናገር ፣ ደግመው አፈነው ወስደው ደፈሯት ።

የሲዳማ ክልል መንግሥት ወንጀለኞችን የገቡበት ገብቶ አይቀር ቅጣት ማሳየት አለበት

.
.
.
.
ፊንፊኔ እና ፊንፊኔ ዙርያ ያላቹ ኦሮሞዎች ተደራጁ ማህበራትን አደራጁ ሥሩ ንግድ ውስጥ ግቡ በሞያ እና በክህሎታቹ ተደራጅታቹ ሥሩ የመጪው የወራጁ የበይ ተመልካች አትሁኑ በግልህ ብትሮጥ ምታመጣው የለም በመደራጀት እንጂ ፊንፊኔ የእናንተው ናት ሥሩባት ኑሩባት።
2024/09/25 00:23:09
Back to Top
HTML Embed Code: