#Alert
ግብጽ፣ ኤርትራን ከሕወሓት ጋር ለማስታረቅ በምትችልበት ኹኔታ ዙሪያ ከኤርትራ ጋር እየመከረች መኾኗን የኢምሬቶች ጋዜጣ ናሽናል ዘግቧል። ኤርትራ እና ግብጽ የወታደራዊ ትብብርና የመረጃ ልውውጥ ለማድረግ አማራጮችን እየፈተሹ እንደኾነም ዘገባው ጠቅሷል። ሁለቱ አገራት ለመፈራረም ያስቡት ስምምነት፣ በቀይ ባሕር አካባቢ የመርከቦችን ደኅንነት ለማረጋገጥ ርምጃዎችን መውሰድን ያካትታል ተብሏል። የግብጽ ደኅንነት ሚንስትር ጀኔራል ከማል አባስና ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ባድር አብደላቲ ሰሞኑን አሥመራ ውስጥ ከፕሬዝዳንት ኢሳያስ ጋር መወያየታቸው ይታወሳል። [ዋዜማ]