Telegram Web Link
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
እነዚህ የሀገር ጠላት የሀገር ሸክሞች ናቸው
ሩዋንዳ 800 ቸርች እና መስጊዶች በከፍተኛ ድምፅ ብክለት ምክንያት ዘግታለች

Rwanda Closed 8000 Churches for noise pollution and exploitation‼️

Since the Rwandan government enacted a new Noise Pollution law in 2018, it has closed at least 8,000 churches and 100 mosques.
In 2018, Rwanda enacted new laws regulating churches, religious organizations, and pastors to regulate noise pollution.

rema.gov.rw/fileadmin/user
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የተቀለደበት ህዝብ እና ሀገር
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሌላውን ካስተማራቹ እናንተ ለምን ከሌላው ብሄር በተለየ ደንቆሮ ለምን ሆናቹ ነው የኛ ጥያቄ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Clan leaders from Somalia's regions of Jubaland, Hiraan, Shebelle, and Baykol have voiced strong opposition to President Hassan Sheikh’s recent military cooperation agreement with Egypt
ዜና፡ በ #ኦሮሚያ ክልል እየተካሄደ ያለው ግጭት እንዲቋጭ የሰሜን ሸዋ ዞን ህዝብ በሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ አቀረበ

በኦሮሚያ ክልል በኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት እና በፌዴራል መንግስት መካከል እየተካሄደ ያለው ግጭት በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ እና ሰላም እንዲሰፍን በሺዎች የሚቆጠሩ ግለሰቦች ነሐሴ 19 ቀን 2016 በሰሜን ሻዋ ዞን በሱሉልታ እና ጭንጮ ከተሞች ባካሄዱት ሰልፎች ጠየቁ።

ሰልፎቹ አባ ገዳዎች፣ ሃደ ሲንቄ፣ የሃይማኖት መሪዎች፣ አስተማሪዎች፣ ሽማግሌዎች፣ ልጆች እና ሴቶች ጨምሮ የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች አንድ ላይ በመሰባሰብ ተካሄደዋል።

የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ሰልፎቹን አስመልክቶ በማህበራዊ ሚዲያ ባወጣው መግለጫ “ገዢው ፓርቲ የተወሰኑ ሰዎችን በማነሳሳት የሰሜን ሸዋ ህዝብ የሰላም ጥሪ እያቀረበ ነው በማለት ላይ ነው” ብሏል።

ያንብቡ፦
ሰላም ማምጣት ምርጫ ሳይሆን ግዴታ ነው ዛሬ በተማፅኖ ስላም ስጠኝ ብሎ የሚለምንህ አንተ የካድሬ ቤተስብ ብለህ የምትስድበው አበቃ ያለ ቀን ሁሉም ነገር ያበቃል ።
#NoMoreWar
ኦቦ ሸመልስ አብዲሳ ለዲያስፖራ ኦሮሞ ለእሬቻ ሀገሩ እንዲገባ እየተሰሩ ያሉ ልማቶችን እንዲታይ ጥሪ አደረገ !!

ከዲያስፖራው ጋር ጥሩ ግኑኝነት መፍጠር ለህዝባችን ስላም ወሳኝ ነው
<<ነፃነቱም...መበልፀጉም ይለፈን>>
◾️
ብዙ አይነት የሕዝብ ሰቆቃ አንብበናል። ስለ ብዙ ግፍ ሰምተናል። ስላለፉት ዘመናት በደሎች ፅፈናል። ጮኸናል። ጭቆናን አውግዘናል። ግን የባሰው መጣ...

ያለፉት ጭቆናዎች አርሶ እንደይበላ አልከለከሉትም። ቄዬውን በእሳት አላጋዩም። የመንቀሳቀስ ነፃነቱን አልነፈጉም። ወላድ ላይ መንገድ አልዘጉም። በእገታ አለንገላቱም። ከሁሉ በላይ በሕይወት የመኖር መብቱን አልገፈፉም።

በሰላሌ ምድር ባለፉት ጥቂት ዓመታት የማይሆን ሆኖዋል። አርሶ መብላት፣ ነግዶ መግባት፣ ት/ቤት ሄዶ መማር፣ ደግሶ መዳር፣ አልቅሶ መቅበር...ቅንጦት ሆኖዋል። እንኳን ነፃነት ሊያገኝ የነበረውንም አጥተዋል።መታገት፣ መገደል፣ መዘረፍ፣ መረገጥ...የየዕለት ሕይወቱ አካል ከሆኑ ሰነባብተዋል። ሰቆቃ...እልቂት....ብቻ!
◾️
አሁን ዴሞክራሲ፣ የፖለቲካ ነፃነት፣ ልማት፣ መንገድ፣ ድልድይ..ገለመሌ ለዚህ ሕዝብ የቅንጦት እቃዎች ናቸው። ተፈጥሮ ከፍጥረት ስትቃረን፣ የደም ፅዋው፣ የግፍ ጎተራው ሞልቶ ሲፈስ ልጆቹን እንደ በሬ ጠምዶ አደባባይ ወጣ። መልዕክቱ ግልፅ ነው። ነፃነታችሁ በአፍንጫዬ ይውጣ፣ ብልፅግናችሁም ይለፈኝ እያለ ነው። ጥያቄው አንድ እና አንድ ነው...
<<ሰላሜን ብቻ መልሱልኝ>>
◾️
ችግሩ ዛሬም ሕዝቡን አትሰሙትም...!

Via ጥላዬ ያሚ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በጎ ዜና ከሱማሌ ክልል
ትጉህ የሆነው የሶማሌ ሕዝብ ኢትዮጵያችንን ለመቀለብ ቆርጦ ተነስቷል። ሩዝ በሸበሌ ተመርቶ እየተሰበሰበ ነው።
የኤርትራ መንግስት ተቃዋሚ የሆነው የቀይ ባህር አፋር ዴሞክራሲያዊ ድርጅት በኢትዮጵያ ባካሄደው ስብሰባው የኤርትራውን መሪ ከስልጣን ለማንሳት ቁርጠኛ መሆኑን ገለፀ

Read more: www.tg-me.com/meseretmedia/2
በጎ ዜና አፋር ክልል

አፋር ክልል ከፍተኛ የሙዝ ምርት በማምረት ለትግራይ ክልል እና ለመሀል ሀገር መላክ ጀምሯል
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የግብጽ የጦር አውሮፕላኖች ወደ ሞቃዲሾ መሣሪያ ጭነው መጡ።

ዛሬ ከሰዓት በኋላ ሁለት የግብጽ የጦር አውሮፕላኖች (አንቶኖቮች) ወደ ሞቃዲሾ አደን አዴ አለም አቀፍ ኤርፖርት መጥተዋል። የመጡ ሲሆን

የጦር አውሮፕላኖቹ ክላሽ እና ስናይፐር የመሳሰሉ የጦር መሳሪያዎችን እንደዚሁም ተተኳሾችን ጭነው እንደመጡ መረጃዎች አመልክተዋል። የመጡት የጦር መሳሪያዎች በ7 የጭነት ተሽከርካሪዎች ተጭነው ወደ መከላከያ ሚኒስቴር መወሰዳቸውን የመረጃ ምንጮች ገልጸዋል።

12 የሚደርሱ የግብጽ የጦር መኮንኖች መሳሪያውን ይዘው የመጡ ሲሆን ምናልባትም ለሶማሊያ ወታደሮች ስልጠና ለመስጠት ሊቆዩ ይችላሉ የሚል ጥርጣሬ አለ።
አንዳንድ ምንጮች በገለጹት መሰረት አውሮፕላኖቹ ከላይ ከተገለጹት የጦር መሳሪያዎች በተጨማሪ የግንኙነት መሳሪያዎችንም ጭነው መጥተዋል።

በቀጣዮቹም ቀናት ተመሳሳይ በረራዎች እንደሚኖሩ፣ ወደ ሂራን ክልል ብለደወይን ከተማ እንደሚጓዙ መረጃዎች አመላክተዋል።

አብዛኞቹ የሶማሊያ ግዛቶች የግብጽን ጦር መግባት ገብነት እየተቃወሙ ናቸው።
ኦሮምያ ውስጥ የሁለት ወንድማማቾች ደም አፋሳሽ ጦርነት ቆሞ በድርድር መፍታት አለበት የምለው በመሀል ምስኪኑ ንፁሀን እያለቀ እየተፈናቀለ ስለሆነ ነው ከታች ያለውን የአዲስ ማለዳ ዜና አንብቡት !!


በኦሮሚያ ክልል ግጭት በተቀሰቀሰባቸው አካባቢዎች 1 ነጥብ 3 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች ተፈናቅለዋል ተባለ

በኦሮሚያ ክልል ግጭት በተቀሰቀሰባቸው አካባቢዎች 1 ነጥብ 3 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች መፈናቀላቸውን ሴንተር ፎር ዴቭሎፕመንት ኤንድ ካፓሲቲ ቢዩልዲንግ (CDCB) አስታወቀ።

ድርጅቱ በክልሉ ስላለው ኹኔታ አስመልክቶ ባወጣው ሪፖርት፤ “በክልሉ እየተካሄደ ያለው ግጭት ካስተለው መፈናቀል በተጨማሪ፤ የሰው ሕይወት ጠፍቷል፣ ንብረት ወድሟል እንዲሁም የልማት እንቅስቃሴዎች ተቀዛቅዘዋል” ያለ ሲሆን፤ የሕዝቡም ማህበራዊ ትስስር መሸርሸሩን ጠቁሟል፡፡

ድርጅቱ አደረኩት ባለው ጥናት መሰረት በአሁኑ ወቅት በኦሮሚያ ክልል 1 ሚሊየን 292 ሺሕ 323 ሰዎች ተፈናቅለዋል ያለ ሲሆን፤ ከእነዚህ ውስጥ 374 ሺሕ 400 ወይንም 29 በመቶ የሚሆኑት ብቻ በመጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ ድጋፍ እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ገልጿል፡፡

የተቀሩት 71 በመቶ የሚሆኑት ተፈናቃዮች ደግሞ በማህበረሰቡ ውስጥ ተበታትነው እንደሚገኙ አስታውቋል፡፡

ድርጅቱ በዩኤስኤይዲ ትብብር ባዘጋጀው በዚህ ሪፖርት፤ በተለይም በምስራቅ ወለጋ እና ምዕራብ ወለጋ ያለው ኹኔታ እጅግ አሳሳቢ መሆኑን የተገለጸ ሲሆን፤ ከአጠቃላይ ተፈናቃዮች ውስጥ  859 ሺሕ ወይንም 66 በመቶ የሚሆኑት ከኹለት ዞኖች ብቻ የተፈናቀሉ መሆናቸው ተመላክቷል፡፡

በተጨማሪም በክልሉ ያለው ግጭት በትምህርት ላይ ያመጣውን ተፅዕኖ በዝርዝር ያስቀመጠው ሪፖርቱ፤ በክልሉ 739  ትምህርት ቤቶች መዘጋታቸውን እንዲሁም ከ210 ሺሕ በላይ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው ውጪ መሆናቸውን ገልጿል።

1 ሺሕ 117 መምህራንና የትምህርት ባለሙያዎች ከሥራቸው ገበታቸው ውጪ መሆናቸውንም ጨምሮ አመላክቷል፡፡

በተጨማሪም ድርጅቱ ከክልሉ ጤና ቢሮ አገኘሁት ባለው መረጃ መሰረት፤ ግጭት በተቀሰተባቸው አካባቢዎች የሚገኙ 208 ጤና ተቋማት ሙሉ በሙሉ፣ እንዲሁም 788 የሚሆኑት ደግሞ በከፊል መውደማቸው መገለጹን አዲስ ማለዳ ከሪፖርቱ ተመልክታለች፡፡

በዚህም 10 አምቡላንሶች መዘረፋቸውን፣ 45 የሚሆኑት መቃጠላቸውን እንዲሁም 25 ደግሞ ከአገልግሎት ውጭ መሆናቸው የተነገረ ሲሆን፤ በተጨማሪም 2 ሞተር ሳይክሎች መዘረፋቸውን፣ 5 የሚሆኑት ከአገልግሎት ውጭ መሆናቸውን እንዲሁም፤ 80 የሚሆኑት ደግሞ መቃጠላቸውን ገልጿል፡፡

“በምዕራብ ኦሮሚያ ወረዳዎች እና መካከለኛው አካባቢዎች በመንግሥት እና በክልሉ በሚንቀሳቀሰው የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ታጣቂዎች መካከል የሚስተዋለው ግጭት፤ እንዲሁም በተለይ በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን በፋኖ ታጣቂ ቡድን የሚደረሰው ጥቃት ውድመት አድርሷል” ሲልም ሪፖርቱ ገልጿል።

በተጨማሪም “ግጭት በተቀሰቀሰባቸው አካባቢዎች ማህበራዊ ደንቦች ተሽረዋል፣ ማህበራዊ ተቋማት ወድመዋል፤ ጭካኔ እና ሕገወጥነት የተለመደ ሆኗል።” ያለው ሪፖርቱ፤ "ለዚህም በጥቅምት ወር 2015 በምዕራብ ወለጋ ዞን ሳሲጋ ወረዳ በገሎ ቀበሌ በመካነ ኢየሱስ ቤተ ክርሰቲያን ውስጥ፤ፐለአምልኮ በተሰበሰቡ ሰዎች ላይ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት የ14 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ማረጋገጫ ነው።" ሲል ገልጿል።

ሴንተር ፎር ዴቭሎፕመንት ኤንድ ካፓሲቲ ቢዩልዲንግ (CDCB) በሪፖርቱ በክልሉ የሚስተዋሉት ግጭቶች በተለይ ሴቶች እና ሕጻናትን ለአደጋ የጣሉ መሆናቸውን የገለጸ ሲሆን፤ ቤተሰቦቻቸውን በድንገት የሚያጡ ሕጻናት ቁጥር እየጨመረ መሆኑን አስታውቋል። በተጨማሪም ባለቤቶቻቸው የሞቱባቸው ሴቶች ለዝርፊያ፣ ለአስገድዶ መድፈ እና ለተለያዩ አካላዊ ጥቃቶች እየተጋለጡ መሆኑን ጠቁሟል፡፡

ስለሆነም በክልሉ የወደሙ መሰረተ ልማቶቸ እንዲስሩ ለአርሶ አደሮች ድጋፍ ማድረግ ያስፈልጋል ያለው ድርጅቱ፤ በተዋጊዎች መካከል በአስቸኳይ ሰላም እንዲወርድም በሪፖርቱ ጠይቋል።

ለደረሰውም ውድመት ከክልሉ፣ ከፌደራል መንግሥቱና ከግብ-ሰናይ ተቋማት አስቸኳይ እርዳታ እንደሚያስፈልግ አሳስቧል።

#NoMoreWar
2024/09/22 21:24:19
Back to Top
HTML Embed Code: