Telegram Web Link
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ጉድ ተመልከቱ😂
የጊዮርጊስ የፈረሱ ኮቴ ተገኝቷል🙈🙈

ሰዎች ሊታለሉ ይችላሉ ፡ነገር ግን በዚህ ደረጃ ሲሆን ግን ያሳዝናል ጊዮርጊስ ኢትዮጵያ ኖሯል እንዴ?
ተስፋቢሱ ፋኖ በቋራ ኮዘራና እንኮይ ውሃ በሚገኙ የቅማንት ህዝብ ላይ ከትናንት ጀምሮ ጦርነት የከፈተ ሲሆን በርካታ ንፁሃን ዜጎች ተጎድተዋል አሁንም ፀረ ህዝቡ ፋኖ በሰላማዊና ንፁሃን የቅማንት ተወላጆች ላይ የጥፋት ዘመቻውን አጠናክሮ ቀጥሏል። የሚመለከተው የፊዴራል ፀጥታና መከላከያ ሰራዊት በተጠቀሰው ቦታ ሰላማዊና ንፁሃን ዜጎችን በማንነታቸው ተለይተው በፋኖ እየደረሰባቸው የሚገኘው የሽብር ተግባር እንዲከላከል እናሳስባለን።

ፋኖ አሁን ላይ የደረሰበትን ትልቅ ኪሳራና ሽንፈት እንዲሁም ያለበትን የትጥቅና ተተኳሽ ችግር ለመቅረፍ ምዕራብ ጎንደር ዞን ከሱዳን አዋሳኝ ድንበር ላይ የግጭት ቀጠና ለማድረግ አዲስ የሽብር እስትራቴጂ አቅዶ ብሄር ተኮር ግጭትን ለማስነሳት ከትናንት ጀምሮ ግጭት እንዲነሳ አድርጓል ።
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
አክቲቪስቶቻችን ወጥረው እየሰሩ ነው
የሃረርጌ ኦሮሞ በጣም ጎበዝ እና ሥራ ወዳድ ሲሆን በኦሮምያ ዋና ከተማ ፊንፊኔ በመግባት በተለያዩ ንግዶች ውስጥ እየተሰማራ ለከተማዋ ብዙ አስተዋፆ እያደረገ ይገኛል እንደ አለመታደል ሆኖ ያለው መንግሥት ኦሮሞን ሳይሆን ሌሎቹን ለማስደሰት ከኦሮሞ ነጥቆ ለሌሎች ለመስጠት እና ቅዱስ ለመባል የሚስራ በመሆኑ ምክንያት የኦሮሞ ህዝብ ተገፍቶ ከወጣበት ከፊንፊኔ ተሙልሶ እንዳይገባ ከነ ብርሃኑ ነጋ ቡድን ጋር ዛሬም በህዝባችን ላይ ሸፍጥ እየተሰራ ይገኛል አሁንም ቢሆን በንግድ ሥራ ላይ ለተሰማሩ ኦሮሞዎች የንግድ ቢቦታዎች እና የብድር አገልግሎት ሊመቻችላቸው ይገባል በደሙ ሥልጣን ላይ ያወጣቹሁን ማህበረሰብ ባትገፉት ጥሩ ነው።
የብሔር ብሔረሰቦች “ብዙሃነት እና አካታችነት” ስርዓት፤ በመንግስት መስሪያ ቤቶች ተግባራዊ እንዲደረግ የሚደነግግ አዋጅ ለፓርላማ ቀረበ

ማንኛውም የመንግስት መስሪያ ቤት “ኢትዮጵያን የሚመስል የሰራተኞች ስብጥር መኖሩን የሚያረጋግጥ”፣ “የብሔር ብሔረሰቦችን ብዙሃነት እና አካታችነት” ያገናዘበ ስርዓት ተግባራዊ ማድረግ እንዳለበት የሚደነግግ የአዋጅ ረቂቅ ለፓርላማ ቀረበ። በመንግስት መስሪያ ቤት ውስጥ የሚፈጸም የሰራተኛ ስምሪት፤ የብሔር ብሔረሰቦችን እና ህዝቦችን “ሚዛናዊ ተጽዕኖ” ለማሳደግ በሚያስችል መልኩ መፈጸም እንዳለበትም የአዋጅ ረቂቁ ያዝዛል።

እነዚህን ድንጋጌዎች ያካተተው አዲሱ የህግ ማዕቀፍ፤ በ2010 ዓ.ም. የጸደቀውን እና እስካሁን በስራ ላይ የቆየውን “የፌደራል መንግስት ሰራተኞች አዋጅ” የሚተካ ነው። በአስራ ሰባት ክፍሎች እና በ160 አንቀጾች የተዋቀረው ይህ የአዋጅ ረቂቅ፤ የደመወዝ ጭማሪ፣ የደመወዝ እርከን፣ የመንግስት ሰራተኞች ክፍያ እና ጥቅም ጥቅም፣ የማትጊያ ወይም ማበረታቻ ስርዓት፣ የሰራተኞች ብቃት ምዘና እና ማረጋገጫ፣ የስልጠና አሰጣጥ እና ስራ ስምሪትን የተመለከቱ ድንጋጌዎች በዝርዝር የቀረቡበት ነው።

በነባሩ አዋጅ ያልተካተቱ “ነጻ ገለልተኛ ስርዓት መገንባት”፣ “ሁሉ አቀፍ ብዝሃነት፣ አካታችነት እና ተጨማሪ የድጋፍ እርምጃ አፈጻጸምን” የተመለከቱ ድንጋጌዎችንም አዲሱ የአዋጅ ረቂቅ በውስጡ ይዟል። የአዋጅ ረቂቁ ዛሬ ማክሰኞ ግንቦት 6፤ 2016 በተካሄደው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ላይ በቀረበበት ወቅት፤ አዲሱ የህግ ማዕቀፉ እንዲዘጋጅ ካስፈለገበት ምክንያቶች ውስጥ የ“ህብረ ብሔራዊነትን” ጉዳይ አንዱ መሆኑን በፓርላማ የመንግስት ተጠሪው አቶ ተስፋዬ በልጅጌ ተናግረዋል።

የአዋጅ ረቂቁ ይህንን ጉዳይ በዳሰሰበት ክፍሉ፤ “በማንኛውም የመንግስት መስሪያ ቤት ኢትዮጵያን የሚመስል የመንግስት ሰራተኞች ስብጥር መኖሩን በማረጋገጥ፤ የብሔር ብሔረሰቦችን፣ የአካል ጉዳተኞች፣ የጾታ ተዋጽኦ የመሳሰሉትን ብዙሀነት እና አካታችነትን ያገናዘበ የመንግስት አገልግሎት እና አስተዳደር ስርዓት ተግባራዊ መደረግ አለበት” ሲል ደንግጓል። የመንግስት መስሪያ ቤቶች “ብቃት እና ውድድርን መሰረት በማድረግ” የሰራተኞች ስብጥር እንዲኖር የሚያስችሉ ዕቅዶችን መተግበር እንዲሁም የክትትልና የቁጥጥር ስርዓት መዘርጋት እንዳለባቸውም በአዋጅ ረቂቁ ላይ ሰፍሯል።

* * ዝርዝር ዘገባውን ለማንበብ ይህን ሊንክ ይጫኑ፦ https://ethiopiainsider.com/2024/13041/
በገጠር የመሬት ሽያጭ እና ግዢ የሚያከናውኑ ሰዎችን እስከ አምስት አመት በእስር የሚያስቀጣ አዋጅ በፓርላማ ጸደቀ

የገጠር መሬትን በሸጠ ወይም በገዛ ማንኛውም ሰው ላይ እስከ አምስት ዓመት የሚደርስ ፅኑ እስራት ቅጣት የሚጥል አዋጅ በተወካዮች ምክር ቤት ጸደቀ። አዲሱ አዋጅ የግል፣ የወል ወይም የመንግስት ይዞታን በህገ ወጥ መንገድ ወርሮ ለተገኘ ሰውም ተመሳሳይ የእስራት ቅጣት ደንግጓል።

የተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ማክሰኞ ግንቦት 6፤ 2016 በነበረው መደበኛ ስብሰባው በሙሉ ድምጽ ያጸደቀው ይህ አዋጅ፤ ከ18 ዓመት በፊት የወጣውን የገጠር መሬት አስተዳደር እና አጠቃቀም አዋጅን ያሻሻለ ነው። አዲሱ አዋጅ አርሶ አደሮች፣ አርብቶ አደሮች እና ከፊል አርብቶ አደሮች በመሬት ላይ ያላቸውን መብቶች ያሻሻለ ሲሆን፤ የሴቶች እና ድጋፍ የሚሹ ሰዎችን የመሬት ተጠቃሚነት መብት ያረጋገጡ ድንጋጌዎችንም አካትቷል።

አዋጁ በረቂቅ ደረጃ ለፓርላማ ከቀረበ በኋላ ከተደረጉ ማሻሻያዎች መካከል፤ “የወንጀል ተጠያቂነት” በሚመለከተው የተጨመረው አንቀጽ ይገኝበታል። “ከመሬት ጋር ተያይዘው የሚፈጸሙ ወንጀሎች ላይ አስተማሪ እና ተመጣጣኝ ቅጣት ማስቀመጥ አስፈላጊ በመሆኑ” ምክንያት እንደተካተተ የተነገረለት ይህ ድንጋጌ፤ ከመሬት ወረራ እስከ መሬት ሽያጭ ድረስ ያሉ የህግ ጥሰቶች የሚያስከትሏቸውን ቅጣቶች ዘርዝሯል።

ማንኛውም ሰው መሬት የሸጠ ወይም የገዛ እንደሆነ፤ ከ100 ሺህ እስከ 200 ሺህ ብር ወይም ከ1 ዓመት እስከ 5 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት ወይም በሁለቱም ሊቀጣ እንደሚችል በአዲሱ ድንጋጌ ላይ ሰፍሯል። በኢፌዲሪ ሕገ መንግስት መሰረት “መሬት የማይሸጥ፣ የማይለወጥ የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የጋራ ንብረት ነው”።

ሕገ መንግስቱ የገጠርም ሆነ የከተማ መሬት የባለቤትነት መብትን የሰጠው “ለመንግስት እና ለህዝብ” ነው። ዛሬ በጸደቀው አዋጅ የግል፣ የወል ወይም የመንግስት ይዞታን በህገ ወጥ መንገድ የወረረ ማንኛውም ሰው፤ ከ1 ዓመት እስከ 5 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት አሊያም ከ30 ሺህ እስከ 100 ሺህ ብር ቅጣት ሊጣልበት እንደሚችል ተደንግጓል።

በእነዚህ ይዞታዎች ላይ ጉዳት አድርሶ የተገኘ ማንኛውም ሰው፤ ከ3 ዓመት እስከ 7 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት ወይም ከ50 ሺህ እስከ 150 ሺህ ብር እንደሚቀጣም በአዋጁ ላይ ተቀምጧል። ባልተፈቀደ ቦታ ላይ ማንኛውንም ግንባታ የሰራ ወይም እንዲሰራ የፈቀደ ሰው ደግሞ በአዲሱ አዋጅ መሰረት ከ1 ዓመት እስከ 3 ዓመት በሚደርስ እስራት አሊያም ከ25 ሺህ እስከ 50 ሺህ ብር ይቀጣል።

እነዚህ ቅጣቶች፤ ከመሬት አጠቃቀም ዕቅድ ውጪ ይዞታውን ጥቅም ላይ አውሎ የተገኘ ሰው ላይ በተመሳሳይ መልኩ ተግባራዊ የሚደረጉ ይሆናል። ሀሰተኛ የመሬት ይዞታ ማስረጃ ያቀረበ ባለይዞታ እንዲሁም ማስረጃ የሰወረ ወይም የተሳሳተ ማስረጃ የሰጠ ባለሙያ ላይ የሚጣለው እስራት ከላይ እንዳሉት የህግ ጥሰቶች ተመሳሳይ ቢሆንም የገንዘብ ቅጣቱ መነሻ ግን ወደ 20 ሺህ ብር ዝቅ ብሏል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ይሄ እብደት አሁንም አልቆመም እንዴ ? መቼ ነው እንደ ስው ምታስቡት ግን እኛ ስለ እናንተ ደከመን
ሃሰተኛ ዩቲዩበሮችን መያዙ ቀጥሏል፣ ህፃናትን አርጃለሁ በማለት ቪዲዮ የሰራችው ተያዘች።
በዩቲዩብ ሃሰተኛ ታሪኮች እውነተኛ በማስመሰል ከሰሩት መካከል ይህቺ "ገነት ግርማ" ትባላለች ሺ ህፃናትን አርጃለው ይኼኛው አንድ ሺ አንደኛዬ ነው ብላ ቪዲዮዎችን የሰራችው በውጪ ቋንቋዎችም እስኪተረጎም ያበቃችው በቅን ልቦች ከፊንፊኔ ፖሊስ ኮሚሽን ጋር በመተባበር በተሰራ ብርቱ ክትትል በቁጥጥር ስር ውላ በአሁን ሰዓት በየካ ፖሊስ መምሪያ እንደምትገኝ ታውቋል
ፖሊስ እየወስደ ያለው እርምጃ ቢዘገይም በጣም ደስ የሚያሰኝ ነው ።
https://www.tg-me.com/danny4677
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ፊንፊኔ ውስጥ የነበረ የኤርትራውያን ስር ግ ላይ የሻቢያ/ህግደፍ ደጋፊ እና የብርጌድ ንሀመዱ ደጋፊዎች እንደዚህ ሲፈላለጡ ውለዋል የምስራቅ አፍሪካ ፖለቲካ ድንቁርና ተጨምሮበት የመጠፋፊያ መንገድ ሆኗል ደሞ ለህዝብ ነው ምታገለው ይልሀል እንደዚህ ባገኘበት እየተፈላለጠ
https://www.tg-me.com/danny4677
#ብልፅግና_ፓርቲ እና #ህወሃት ግጭት የሚፈጥሩ አዝማምያዎች በጋራ ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የጋራ መግባባት ላይ መድረሳቸው ተገለጸ

በብልፅግና ፓርቲ እና በሕወሃት መካከል የተጀመረው የፓርቲ ለፓርቲ ፓለቲካዊ ውይይት ለሶስተኛ ግዜ በመቐለ ከተማ በዛሬው ዕለት በመቐለ ተካሂዷል።

ሁለቱም አካላት ለዘላቂ ሰላም መረጋገጥ በጋራ በቁርጠኝነት ለመስራት ተስማምተዋል ተብሏል። “ማናቸውንም ጉዳዮች በሰላማዊ መንገድና በውይይት እየፈቱ ለመሄድ ሁለቱም አካላት የበኩላቸውን ፓለቲካዊ ድርሻ ለመወጣትና በቁርጠኝነት ለመስራት ተስማምተዋል።

በተያያዘም የሚኖሩ የኮሙዩኒኬሽን ስራዎች የሰላም ሂደቱን የሚደግፉ እና ግጭት ቀስቃሽ ከሆኑ ንግግሮችና ይዘቶች የተቆጠቡ እንዲሆኑ መግባባት ላይ ደርሰዋል ሲል ኢፕድ ዘግቧል።

በተጨማሪም በቅርቡ በ #ራያ የተፈጠረውን የግጭት ክስተት በተመለከተም በዝርዝር ውይይት ያካሄዱት ፓርቲዎቹ “ክስተቱ መፈጠር ያልነበረበትና ከተጀመረው ዘላቂ ሰላም የማረጋገጥ ሂደት ጋር የሚቃረን እንደሆነ” መግባባት ላይ ደርሰዋል።

የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነትን ወደ መሬት ለማውረድ እየተሰሩ ላሉ ስራዎች ስኬት ምቹ ፓለቲካዊ ሁኔታ ለመፍጠር ሁለቱም ፓርቲዎች ኃላፊነታቸውን ለመወጣት፤ በቀጣይም በሌሎች አጀንዳዎች ላይ ለመወያየት ተስማምተዋል።

================

https://www.tg-me.com/danny4677
2024/06/26 03:19:44
Back to Top
HTML Embed Code: