Telegram Web Link
የአለማችን ሰነፍና ሃብታም የሆነችው አገር ስዊዘርላንድ አስገራሚ ነገሮች እነሆ !!

***

1️⃣. በባንክ ንግድ የከበረችው ስዊዘርላንድ ከዓለም ሰነፏ ሀብታም አገር ተብላለች። ስንፍና ሁሌም ከድህነት ጋር አይቆራኝም። ስንፍናቸውን አስመልክቶ አንኳር አንኳር ነጥቦች እነሆ፣

➡️ ሕዝቧ ገንዘብ ሞልቶ ከመትረፉ የተነሳ መሥራት አይፈልግም ፣ ልሥራ ያለም በዓመት 2 ወር ገደማ ብቻ ነው የሚሠራው።

➡️ እያንዳንዱ ስዊዝ በዓመት ቢያንስ አንድ ወር ተኩል ጉብኝትና በመዝናናት ያሳልፋል።

➡️* የእያንዳንዱ የስዊዝ ዜጋ ገቢ በዓመት ወደ 100,000 የአሜሪካን ዶላር ይገመታል፣ የኢትዮጵያ ለንፅፅር ያክል 944ዶላር ብቻ ነው።

➡️የምን ሥራ ነው፣ ተኝቼ መዋል ነው መዝናናት ነው የምፈልገው ያለ ዜጋ የስዊዝ መንግሥት በወር ወደ 262,000 የኢትዮጵያ ብር ደሞዝ ይከፍለዋል።

➡️ ገንዘብ ማውጫ መንገዱ የጨነቀው የሲዊዝ መንግሥት በየወሩ ለዜጎቹ ወደ 150,000 የኢትዮጵያ ብር ተቀማጭ ለእያንዳንዱ ስዊዝ ልመድብ ብሎ መተማመኛ ሪፈረንደም ሲጠራ 60% የሆነው ሕዝብ ምንያረግልናል ያለንንም በልተን መጨረስ አልቻልንም ብሎ የመንግሥትን ሀሳብ ውድቅ አድርጎታል።

➡️ስዊዞች የባንክ ንግድ ገንዘብ ላይ ተቀምጠው ስላደጉ የገንዘብ ጉጉት ፈፅሞ የላቸውም፣ ሰርቶ ማደግ የሚባል ነገር ጨረሶ አይታወቅም፣ እንደ አፈር ዶላር ሳይሰሩ ዝቆ መዝናናት እያለ የምን ስለስራ ማውራት ነው

እንዲቀጥል 👍

@Amazing_Fact_433
@Amazing_Fact_433
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ጭቆና ክፍዎችን ይፈጥራል !

የአዶልፍ ሂትለር ታላቅ ወንድም የአባቱ ጨካኝነትን ለማምለጥ በ13 አመቱ ነበር ከቤቱ በርሮ የጠፋው፡፡ ይህ ልጅ ከቤቱ ከሄደ በኋላ የሂትለር አባት ክፋቱን በሰባት አመቱ ለጋ ልጅ በሂትለር ላይ በእጥፍ ጨመረው፡፡ ሂትለር በአባቱ እጅ አሰቃቂ አመታትን አልፏል፡፡ ምርጫውን ተከልክሎአል፡፡ አርቲስት ለመሆን ይመኝ የነበረው ሂትለር በአባቱ አስገዳጅነት የሲቪል ሰራተኛነት አቅጣጫን እንዲከተል ተገደደ፡፡ የሂትለር ትምህርት ውጤቱ አጥጋቢ ስላልነበር የአባቱን ቁጣ እጅግ አባባሰው፡፡ የአይሁድ ዘር እንዳለበት የሚነገረው የሂትለር አባት ክፋት በሂትለር ልብ ውስጥ አይሁድን የመጥላት ዘርም እንደዘራበት ይነገራል፡፡

አባቱ ከሞተ በኋላ፣ ሂትለር በ13 አመቱ የቤት ሃላፊነትን በጫንቃው ላይ ተሸከመ፡፡ በእናቱ ሞት ምክንያት በኋላ በጉዲፈቻ ያድግ የነበረው ሂትለር ያንን ገቢ በመከልከሉ የጎዳናን ሕይወት ቀምሷል፡፡ በብዙዎች እንደሚታመነው፣ ሂትለር በልጅነቱ ያሳለፈው ስቃይ ውስጡ ከጨመረበት መራራነት እንዳልተላቀቀና በሕይወቱ ያደረጋቸው አሰቃቂ ተግባሮች የዚያ ልምምድ ተጽእኖ እንደሆኑ ይታመናል፡፡ ሂትለር ቢያንስ ለ46 ሚልየን ሰዎች መሞትና ለብዙ ንብረት መውደም ምክንያት የሆነ ሰው ነው፡፡ ሂትለር የዚህ ሁሉ ውደመት ምክንያት ከሆነ በኋላ ራሱን በራሱ አጥፍቶ እስኪሞት ድረስ ይህንን እብደቱን የሚከተሉለት ከእርሱ የባሱ እብዶች ፈጽሞ አጥቶ አያውቅም ነበር፡፡

አንዳንድ ሰዎች ምንም እንኳን በተለያዩ ለማንነት ቀውስ (Identity Crisis) አሳልፈው በሚሰጡ ልምምዶች ውስጥ አልፈው ቢያድጉም ከዚያ ሁኔታ በተሳካ መልኩ ራሳቸውን አውጥተው ለሕብረተሰቡ ጠቃሚ ዜጎች ይሆናሉ፡፡ እንደዚህ አይነት ሰዎች ብዙዎችን ወደ አንድነት፣ ወደ መከባበርና ወደ አብሮነት የሚያመጡ የመልካም ተጽእኖ ሰዎች ናቸው፡፡

አንዳንዶች ግን በመራራነት፣ በጥላቻና በአስተዳደግ ዘመናቸው በተጎነጩት የውስጥ ቂም የተቃወሰ ማንነት ይዘው ወደ አመራር ይዘልቃሉ - እንዴት አይነት ስህተት! እንደዚህ አይነት ሰዎች በውስጣቸው ያለባቸው የማንነት ቀውስ ይህ ነው ተብሎ ሊተነበይ የማይችልን ባህሪይ እንዲገልጡ ይነዳቸዋል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ የተጠናወታቸው የተቀባይነት ጥማትና የደጋፊ ፍለጋ ናፍቆት ምንም ነገር ከማድረግ እንዳይመለሱ አይኖቻቸውን አሳውሯቸዋል፡፡
ዛሬ  ሰርግ አለ ።

✔️ሙምባይ ውስጥ የሚገኘው  Jio World Convention Centre የተሰኘው ግዙፍ አዳራሽ በተጀመረው በዚህ ግዙፍ ሰርግ ላይ ለመገኘት ፡ የአለማችን ታዋቂ ሰወች ህንድ ከገቡ ጥቂት ቀናት ሆኗቸዋል ።
.....
ከደቂቃዎች በፊት የአለማችን ታዋቂው የነጻ ትግል ኮከብ ጆን ሲና በዚህ የሰርግ አዳራሽ ፡ በህንዳውያን አለባበስ አምሮበት ታይቷል ። የአለማችን ዝነኛ ቦክሰኛ ማይክ ታይሰን ከተጋባዥ ታዋቂ ሰወች ውስጥ ስሙ አለ ። ኪም ካርዳሽያን ሙምባይ ገብታለች ።
...
ከወራት በፊት ተካሂዶ በነበረው የአለማችን አስረኛው ሀብታም የአምባኒ ልጅ የሆነው አናንት እና ራዲካ ፡ ቅድመ ሰርግ ( pre- wedding ) ላይ የክብር እንግዳ የነበሩት የፌስቡክ ባለቤት ማርክ ዙከርበርግ ፡ እና ቢሊየነሩ ቢልጌትስ  ከነባለቤቱ  ፡ በአለም ዙሪያ የሚገኙ ታዋቂ ፖለቲከኞች ፡ የአለማችንን ቢዝነስ የሚዘውሩ ቢዝነስ ማኖችና ኢንደስትሪያሊስቶች. ..  ከዛሬ ጀምሮ ለሶስት ቀናት በህንድ ሙምባይ ከትመው ይቆያሉ ።
.......
የሰርግ ስነስርአቱን  ለማድመቅና በምሽቱ የሙምባይ ሰማይ ላይ ፡ እንግዶቻችን እንኳን ደህና መጣችሁ ፡ መልካም የሰርግ በአል እና የመሳሰሉ ፅሁፎችን የሚፅፉ ብርሃናማ ድሮኖች ተዘጋጅተዋል



በ Like ካሳወቃችሁኝ ግን ሌሎችም የሚደረጉትን አስገራሚ ነገሮች የማቀርብላችሁ ይሆናል


@Amazing_Fact_433
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
4-3-3 አስገራሚ እውነታዎች
Photo
ከላይ Post ካረኩላችሁ ጋር ከወራቶች  በፊት የተከናወኑትን ነገሮች  pre Wedding
Post ከፈለጋችሁ ታች ያለውን Link ተጫናችሁ አንብቡ


https://www.tg-me.com/amazing_fact_433/9170

https://www.tg-me.com/amazing_fact_433/9170
ቴሌግራም ላይ ስንት አመት ቆይታቹል😳?

ለማወቅ ይሆን ተጫኑ👉 https://www.tg-me.com/dogshouse_bot/join?startapp=0y6aR_-BTSGYuFSYENvs9w
ባቢሎን ዛሬ ላይ...

ባቢሎን ከባግዳድ በስተደቡብ 50 ማይል ርቀት ላይ በዘመናዊቷ ኢራቅ ውስጥ ትገኛለች ባቢሎን የባቢሎናውያን እና የኒዮ ባቢሎን ኢምፓየር ዋና ከተማ ነበረች። ሰፊ፣ ብዙ ህዝብ የሚኖርባት ግዙፍ ግንቦች እና በርካታ ቤተመንግስቶች እና ቤተመቅደሶች ያሏት ከተማ ነበረች። ታዋቂው ቅርሶች እና ቅርሶች የማርዱክ ቤተ መቅደስ፣ የኢሽታር በር እና የሃሙራቢ ኮድ የተጻፈባቸው ሐውልቶች ይገኙበታል። የፋርስ ወረራ ኢሊን 539 ዓክልበ፣ የኒዮ-ባቢሎን ግዛት የፋርስ ንጉሥ በሆነው በታላቁ ቂሮስ እጅ ወደቀ፣ የኦፒስ ጦርነት ተብሎ በሚታወቀው ወታደራዊ ተሳትፎ። የተመሰረተው በ2300 ዓ.ዓ አካባቢ ነው። በደቡባዊ ሜሶጶጣሚያ ጥንታዊ የአካድኛ ተናጋሪ ሕዝብ
ይሄንን ያውቃሉ ?

በኛ አለም ላይ ከሚገኙ ዛፎች መካከል እጅግ እድሜ ጠገቡ ዛፍ "Methuselah" ተብሎ የሚጠራ ሲሆን 4853 ዓመትን በዚህ አለም ላይ ኑሯል።

@Amazing_Fact_433 @Amazing_Fact_433
ዘና በሉበት 😆

@Amazing_Fact_433
- በዓለም ታሪክ ትልቁ የመሬት መንቀጥቀጥ በ2010 በሄቲ የተከሰተው አደጋ ሲሆን ለ222,570 ሰዎች ሞት፣ ለ300,000 መጎዳት እና ለ1.3 ሚሊዮን ሰዎች ከቤታቸው መፈናቀል ምክኒያት ሆኗል።

- በተጨማሪም በተፈጠረው አደጋ ምክኒያት አብዛኛው በጊዜው የታሰሩት አምልጠዋል።

@Amazing_Fact_433
አንድ ሰውዬ በኬኒያ ሀገር ለመታከም ወደ መንግስት ሆስፒታል አቅንቶ 'X-ray' ከተነሳ በኋላ ፣ በጥሩ ጤንነት ላይ ያለች በረሮ ልቡ ውስጥ እንዳለች ይነገረዋል ።

ወደ ሲንጋፖር ሄዶም መታከም እንዳለበት ይነግሩታል ።

ታማሚውም ወደ ሲንጋፖር ሄዶ ሲታይ ፣ የታየው በረሮ ልቡ ውስጥ ሳይሆን 'X-ray' ከሚያነሳው ማሽን ውስጥ የተገኘ መሆኑን ያስረዱታል ።

ብዙ ግዜ የምንያበትን ነገር ሳናፀዳ አሊያም የምንመለከትበት መስታወት ሳነነፃ የሌላውን እድፍ ለመናገር እንሮጣለን ፣ እድፉ እኛ ምንለው ነገር ሳይሆን አስተሳሰባችን ወይም የምናይበት መነፅር ነው !
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ሂትለር ተጠየቀ - "ለመሆኑ በሕይወትህ እጅግ የተናቁ የሚባሉት ሰዎች እነማን ናቸው?"

ሂትለር ሲመልስ - "የራሳቸውን ሀገር እንድወር የተባበሩኝ።"
ይህን ያውቃሉ?

በሆድ ውስጥ ያለ ህፃን በ23ኛ ሳምንቱ የእናቱን ድምፅ እንዲሁም ከውጪ የሚመጡ ድምፆችን ማዳመጥ ይችላል።

@Amazing_Fact_433
@Amazing_Fact_433
ሴት ሳያይ የሞተው ማሂያሎ ቶሎቶ

👇🏾

እ.ኤ.አ 1856 ውልደቱ ሲሆን ወላጅ እናቱ ወዲያው ነበር የሞተችው

የእናቱን ሞት ተከትሎ በግሪክ ውስጥ በሚገኝ አቶስ ተብሎ በሚጠራ ተራራማ ገዳም ውስጥ እንዲያድግ በጉዲፈቻነት ተሰጠ:: ይህ ገዳም ለሴቶች ፍፁም የተከለከለ በመሆኑ ሴቶች ዝር ብለውበት አያውቁም

በ1938 እ.ኤ.አ በ82 አመቱ ሲሞት በገዳሙ ውስጥ ልዩ የሆነ የቀብር ስነስርአት የተፈፀመለት ማሂያሎ ቶሎቶ ምናልባትም በአለም ላይ ሴት ሳያይ የሞተ ብቸኛው ሰው ተብሎ ይዘከራል

👇🏾

❤️🙌🏼
የተሻለ ኑሮን ፍለጋ. .. ሀገራቸውን ለቀው በህገወጥ መንገድ የሚጓዙትን ጋናውያንን የያዘው ሽፍን መኪና ፡ ለቀናት ሲጓዝ ከቆየ በኋላ ፡ ጭው ባለ የሰሀራ በረሀ ላይ ቆመ ።
.........
እና ስደተኞቹን የጫኑት አዘዋዋሪዎች ፡ ጋናውያኑን ከተጫኑበት ሽፍን መኪና እንዲወርዱ አዘዟቸው ።
ስደተኞቹ ስፔን ደረስን እንዴ ሲሉ ጠየቁ ፡

" አልደረሳችሁም ሆኖም ከዚህ በኋላ የምትቀጥሉት በእግራችሁ ነው "
ጋናውያኑ መከራከር አይችሉም ።
እና አንዳች የሚበላም ሆነ የሚጠጣ በማይገኝበት በረሀ ከችግርና ከሞት ጋር መፋጠጥ ግድ ሆነባችው ።
........
በዚህ መልኩ የተጣሉት ጋናውያን ስደተኞች ፡ በእግር ተጉዘው ስፔን ለመግባት ከ40-50 ዲግሪ ሴልሺየስ በሚሆነው ሞቃታማው የሰሀራ በረሀ መጓዝ ጀመሩ ።
....
ከነዚህ ስደተኞች መሀል የሚገኙት ማርያና ፊሊክስ. .. ገና ከሀገራቸው ሲነሱ ይህ ጉዞ ህይወታቸውን እንደሚቀይር አስበው ነውና ከፊት ለፊታቸውን ያለውን ሁሉ መጋፈጥ ነበረባቸው ።

ሆኖም ከሁሉም ከሁሉም የውሀ ጥሙ አቃታቸው ። በተለይ ለነዚህ ጋናውያን ጥንዶች ይህን ጉዞ ይበልጥ አስቸጋሪ ያደረገው ደግሞ ፡ የማርያ እርጉዝ መሆን ነው ።
......
በዚህ መልኩ ፡ እጅግ አስቸጋሪ በሆነ ሁኔታ ፡ ከሀይለኛው የውሀ ጥም የተነሳ የራሳቸውን ሽንት ሁሉ እየጠጡ .........አብረው ከጋና ከወጡ መሀከል ጥቂት የማይባሉ ሞተው ....... እጅግ አስቸጋሪ በሆነ የቀናት ጉዞ ውስጥ ያለፉት ማርያና ፊሊክስ እንደምንም የስፔን ድንበር ደረሱ ።
.......
ሆኖም እዛ እንደደረሱ የተቀበላቸው ፖሊስ ነበር ። ባልና ሚስቶቹ ጋናውያን የስፔንን አጥር ጥሰው መግባታቸው እንደተረጋገጠም ፡ ወደመጡበት ሀገር ወደጋና ሊመልሷቸው እየተዘጋጁ እያለ ፡ አንድ ስፔናዊ የህግ አዋቂ ቀርቦ አናገራቸው ፨
.....
" ከጋና እንደመጣችሁ አትናገሩ ፡ ጋናውያን መሆናችሁን የሚገልፅ ማንኛውንም አይነት ዶክመንት ካላችሁም ቅደዱ አጥፉና ፡ በጦርነት ከምትታመሰው ላይቤሪያ እንደመጣችሁ ተናገሩ ሲል መከራቸው ፨
........
በዚህ መልካም ሰው ምክር ምክንያት ወደጋና ከመመለስ የተረፉት ማርያና ፍሊክስ ጥገኝነት ባገኙበት ስፔን አዲስ ኑሮ ለመመስረት መጣር ጀመሩ ።
....
በዚህ መሀልም ፡ በሆድ ውስጥ ሆኖ አብሮ የስፔንን ድንበር ያቋረጠውና ፡ አሁን ላይ ሚሊየን ፓውንዶች እየተከፈለው ለአትሌቲኮ ቢልባኦ የእግር ኳስ ክለብ የሚጫወተው መጀመሪያ ልጃቸው ኢናኪ ተወለደ ።
........
ከጥቂት አመታት በኋላም ፡ በትናንትናው ምሽት ስፔን የአውሮፓን ዋንጫ እንድታነሳ የመጀመሪያውን ግብ ያገባው ኒኮ ዊሊያምስ ወደዚህ አለም መጣ ፨
.......
ለነሱና ለልጆቻቸው የተሻለ ህይወት ፍለጋ ከሞት ጋር ተጋፍጠው ፡ የሰሀራ በረሀን የተሻገሩት ማርያና ፍሊክስ ያን ሁሉ መከራና ችግር አልፈው. .. ዛሬ ከራሳቸው አልፎ ለመላው ስፔናውያን የደስታ ምንጭ ለመሆን በቅተዋል ።
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
2024/09/28 17:20:23
Back to Top
HTML Embed Code: