Telegram Web Link
የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በተመረጡ ከተሞች በኦንላይን ለመስጠት እየተሠራ ነው

#NEWS | የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በተመረጡ ከተሞች በኦን ላይን ለመስጠት እየተሠራ መሆኑን ተገልጿል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ በአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ምክክር መድረክ ላይ ባደረጉት ንግግር የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በተመረጡ ከተሞች በኦንላይን ለመስጠት እየተሠራ መሆኑን ገልፀዋል ።

የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ሙሉ በሙሉ በኦንላይን ለመስጠት ባይቻልም በሁሉም ክልሎች በተመረጡ ከተሞች ለመስጠት እየተሠራ መሆኑን ተናግረዋል።

በዚህም በሁሉም ክልሎች ያሉ የተመረጡ ተማሪዎች በኦንላይን ፈተናቸውን የሚወስዱ ሲሆን ቀሪዎቹ ደግሞ በተለመደው አግባብ ፈተናቸውን ይወስዳሉም ብለዋል።

የሀገር አቀፍ ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር (ዶ/ር) እሸቱ ከበደ በበኩላቸው ፈተናውን በኦንላይን ለመሥጠት የሚያስችል የቅድመ ዝግጅት ሥራ እየተሠራ መሆኑን ገልፀዋል።

ተማሪዎች የሙከራ ፈተና የሚለቀቅላቸው ሲሆን ደጋግመው እንዲሞክሩና እንዲለማመዱ ይደረጋልም ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

ለዚህም እንዲረዳ የአሰልጣኞች ስልጠና በመሥጠት ተማሪዎች ተደጋጋሚ ስልጠና እንደሚሠጣቸውም ዋና ዳይሬክተሩ ገልፀዋል።

ከቀጣይ ሳምንት ጀምሮ የአሰልጣኞች ስልጠና መስጠት እንደሚጀምርም በመድረኩ ተገልጿል።

@Amazing_fact_433
@Amazing_fact_433group
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
✅️የቡልጋሪያና የቱርክ ሰወች አዲስ ልብስ ገዝተው ለዛፎች ያለብሷቸዋል ።

ለምን ቤት የሌላቸውና በጣም ደሀ የሆኑ ሰዎች እንዲለብሷቸው ። እነሱም የተቀመጠላቸውን ልብስ አመስግነው ይወስዳሉ።

ሰው ሳያይህ የሰጠኸውን ፈጣሪ ባደባባይ ይከፍልሀል ማለት ይኼ ነው


@Amazing_Fact_433
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
የጓደኛን ምክር ሳንንቅ እንስማ

የዛሬ አስራ ዘጠኝ ዓመት ገደማ የፌስቡክ መስራች ማርክ ዙከርበርግ አምስት ጓደኞቹን ሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ወደነበረችው ክፍሉ እንዲመጡ ጋበዛቸው፡፡

የግብዣው ምክንያት ደግሞ ስላሰበው የስራ ዕድል ሊያወራቸው ፈልጎ ነበር፡፡ ከተጋበዙት አምስቱ ሁለቱ ብቻ ግብዣውን አክብረው ተገኙና ሃሳቡን አድምጠው ለስራው መክፈል ያለባቸውን ሁሉ ዋጋ ለመክፈል ተስማሙ፡፡

አሁን ሁለቱም ጓደኞቹ ቢሊየነር ናቸው፡፡ ደስቲን ሞስኮቪትዝ 6.5 ፤ ኤድዋርዶ ሳቨሪን 3.4 ቢሊየን ዶላር በላይ ሀብት አፍርተዋል ፡፡
ጓደኞቻችን ስለስራ ዕድሎች ሲያወሩን ልባችንን ከፍተን ሃሳባቸውን እናድምጥ። ምክንያቱም ያ አጋጣሚ ሕይወታችን በዘላቂነት የሚቀየርበት አጋጣሚ ሊሆን ይችላልና፡፡
✅️ማዘር ትሬዛ ገና በወጣትነት ዕድሜያቸው የአስፋልቱን ዳር ይዘው ሲሄዱ አንዳች ነገር አገኙ። ቦርሳቸውን ከፍተው ጨመሩት። እንደገና ሌላ አገኙ። ቦርሳቸው ሞላ።

ከርቀት የሚያደርጉትን ሲከታተል የነበረ ፖሊስ ተጠጋቸውና ያፋጥጣቸው ጀመር። ምንድነው ያገኘሽው ?” ብሎ አፋጠጣቸው። “ ወንድሜ ተወው። ይቅርብህ። ሥራህን ብትሠራ ይሻላል ” አሉት።
ቦርሳቸውን ነጥቆ ውስጡ ያለውን ነገር ሲበረብር ጠርሙስ ሆኖ አገኘው።

የጠርሙስ ስብርባሪዎች። እነዚህን ነው ስትለቅሚ የነበረው ?” ብሎ ጠየቀ ፖሊሱ ግራ ተጋብቶ።

እማሆይም ፣ “ አዎን ወንድሜ ” አሉ። ለምን ?” ምን ሊያደርግልሽ ?” አላቸው። ይኸውልህ ፣ ይሄ መዋዕለ ሕጻናት ነው።

ሕጻናቱ ከትምህርት ቤት ሲለቀቁ የሚያደርጉትን አያውቁም። ወደ ቤታቸው ለመድረስ ሲጣደፉ እግራቸውን ቢቆርጣቸውስ ?” ስለዚህ ስብርባሪዎቹን የምጥልበት ጉድጓድ እስካገኝ ድረስ በቦርሳዬ ይዤው እዞራለሁ አሉት።
#አይገርምም ?
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from 4-3-3 ስፖርት በ ኢትዮጵያ (𝐌𝐫.Ʀᴏʙᴀ ⁷)
ከርዕስ ውጪ !

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ሆነ።

የ2016 የትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ (12ኛ ክፍል) ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ሆኗል።

የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከሐምሌ 3 እስከ ሐምሌ 5 ለማህበራዊ ሳይንስ ፤ ከሐምሌ  9 እስከ ሐምሌ 11/2016 ዓ/ም ለተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች በበይነ መረብ (Online) እና በዩኒቨርሲቲ ውስጥ በወረቀት ይሰጣል።

በወረቀት ላይ የሚፈተኑ የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ከሰኔ 30 እስከ ሐምሌ 01/2016 ዓ/ም እንዲሁም የተፈጥሮ ሳይንስ ከሐምሌ 6 እስከ 7/2016 ዓ/ም ወደ ዩኒቨርስቲ የሚገቡ ይሆናል። 

መረጃው የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ነው።

VIA ON - Tikvah Ethiopia

@Bisrat_sport_433et @Bisrat_sport_433et
ይህንን ሙሉ የሄሊኮፕተር አካላትን አንድ ላይ የሚይዘው ወሳኝ ክፍል 'Jesus nut' እያሉ ይጠሩታል። ስያሜውን ያገኘውም ድንገት ይህ እቃ ወለቀ ማለት ምንም የመትረፊያ እድል የለም አንድ ያለህ ተስፋ እሱ 👆 ስለሆነ ነው

@Amazing_fact_433
@Amazing_fact_433group
"በትንንሽ ቦታዎች ትልልቅ ሰዎች አሉ"

ማያ አንጀሉ በወጣትነቷ ያልሞከረችው ስራ የለም፦ ሴተኛ አዳሪ፣ ምግብ አብሳይ፣ የምሽት ክበብ ዳንሰኛ፣ የኦፔራ አቀንቃኝ ፣ ተዋናይት ፣ ጋዜጠኛ የመሳሰሉት . . .

እውነተኛው የነፍሷ ጥሪ ግን ደራሲነት ነበር። የሙሉ ግዜ ደራሲ ከሆነች በኋላ የሕይወት ታሪኳን የሚዳስሱ ሰባት መፅሀፍት ፅፋለች። ከነዚህ መሐል በጣም ተወዳጅነትን ያተረፈው "I know why the caged bird sings" ነው። በመፅሀፍቷ ማያ የደበቀችው የሕይወት ታሪኳ የለም። ስላሳለፈችው የሴተኛ አዳሪነት ህይወት ሁሉ በግልፅ ትናገራለች። ከዛ አዘቅት ውስጥ ለመውጣቷ ዋናው ምክንያት ስጋዋን እንጂ መንፈሷን አለመጣሏ ነበር።

ማያ የጥቁሮችን መብት ለማስከበር በ1960ዎቹ በተደረገው ትግል ከማርቲን ሉተር ኪንግ ጁኒየር እና ከማልኮም ኤክስ ጋር ሰርታለች።

የቢል ክሊንተን በአለ ሲመት ላይ በሺህ ከሚቆጠሩ ገጣሚያን መሐል ተመርጣ የግጥም ስራዋን አቅርባለች።

የጥቁር አፍሪካ አሜሪካውያን የተባበረ ድምፅ ሆናለች። ባራክ ኦባማ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ሆኖ ሲመረጥ "ከዘረኝነት እና ፆታዊ አድልዎ ክፉ ደዌ እየተፈወስን ነው" ብላለች።

ይህንን ሁሉ ያደረገችው ማያ አንጀሉ ተራ ሴተኛ አዳሪ ነበረች። ይህ መቼም ለሁላችንም ጠንካራ እና ጥልቅ መልእክት እንዳለው አምናለሁ።

@Amazing_fact_433
@Amazing_fact_433
ዶሮ ያለማቋረጥ ሲበር የታየ ረጅሙ የተመዘገበው ጊዜ 13 ሰከንድ ነው። ይህም የዶሮ በረራ በሰአቱ 301.5 ጫማ መሸፈን ችሎ ነበር።

😁የኛ ቤት ዶሮ ግን ነስርን የሚያስንቅ በረራ ታደርጋለች

@Amazing_fact_433
@Amazing_fact_433
''እያንዳንዱ ቦርሳ የራሱ ታሪክ አለው'' 💔

ይህ ጣልያን ውስጥ ላምፔዱሳ ደሴት ላይ የሚገኝ ሙዚየም ነው::
ሙዚየሙ ከአፍሪካ ተነስተው ወደ አውሮፓ ለመግባት ሜዲትራንያን ባህርን ሲያቋርጡ ውድ ሕይወታቸውን ያጡ አፍሪካውያን ቦርሳዎች የሚታዩበት ነው።

በሙዚየሙ መግቢያ ላይ እንዲህ ይላል “እያንዳንዱ ቦርሳ የራሱ ታሪክ አለው።”


@Amazing_fact_433
@Amazing_fact_433
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ጉድ እኮ ነው

በኢንዶኔዥያ በአንድ አካባቢ ያሉ ማህበረሰቦች በአመት አንድ ጊዜ የሞቱ ሰዎችን ሬሳ እያወጡ በዓል ያከብሩና ይመልሷቸዋል

@Amazing_fact_433
@Amazing_fact_433group
ብዙዎች ፊቱን ሲመለከቱ በሳቅ ይፍነከነካሉ፤ ለ30 ዓመታት ዓለምን በሳቅ አዝናንቷል። ነገር ግን ብዙዎች ትክክለኛ ህይወቱ ምን እንደሚመስል አያውቁም። ይህ የሮዋን አትኪንሰን ወይም በመድረክ ስሙ ሚስተር ቢን አጭር አስተማሪ ታሪክ ነው።

✅️እንደ ወሬ ነጋሪዎች ከአልበርት አንስታይን የሚበልጥ IQ እንዳለው የሚነገርለት ሮዋን ከኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ በኢንጂነሪንግ ማስተርስ ድግሪ የተመረቀ ነው። የሚስተር ቢን መሆን ጉዞውም የተጀመረው እዚሁ ኦክስፎርድ በሚማርበትጊዜ ነው።

በዚያን ጊዜ እንኳን ሊያስቃቸው ይቅርና በመልኩ የተነሳ የክፍሉ ተማሪዎች 'ኤሌን ፊት' እያሉ ሙድ እየያዙ ይዘባበቱ እና ያበሽቁት ነበር። በተደጋጋሚ ለትወና በሚያመለክትበት ጊዜ 'በአግባቡ ለመናገር ያዳግተው ስለነበር/ይንተባተብ ስለነበር' በተደጋጋሚ አይሆንም ይባላል። የእነሱ እምቢታ ግን ወጣቱን ወደህልሙ ከመገስገስ እና ከመሞከር ሊያቆመው አልቻለም።

ከብዙ ሙከራ በኋላ አንድ ቀን መንተባተብ አቆመ። በትክክል ማውራት ቻለ። ስለሁኔታው ሲናገር፤ "አውነቱን ለመናገር መስታውት ፊት ቆሜ ፊቴን እየቀያየርኩ አልማመድ ነበር። እራሴን ሳይሆን ገፐባህሪውን ስሆን መናገር ቀለለኝ።"

ያም ሆነ በመልኩ/በፊቱ/ የተነሳ ማንም ሊያሰራው የሚፈልግ አልነበረም። ብዙ ቢሞክርም ጥረት እንጂ ውጤት ሊያገኝ አልቻለም፤ በትወና ብቻ ሳይሆን ህይወቱም ከበደበት፤ ሁሉም ነገር ካሰበው ጋር የሚሄድ ነገር የለም።

በመጨረሻም ወደ ራድዮ ጣቢያዎች ጎራ አለ። ለአስር አመታትም ፊቱን ሲያሳይ በድምፅ ብቻ Mr bean የተባለውን ገፀባህሪ እየተጫወተ አሳደገው። በመጨረሻም ሚስተር ቢን በስሎ ከአስር ዓመት በኋላ ወደ ቴሌቭዠን በአካል መጣ።

ሚስተር ቢን መታየት ሲጀምር ሁሉም በአድናቆት መሳቅ ጀመረ...ለሮዋንም የአለም አቀፍ እውቅና እና ዝና አተረፈለት። በመጀመሪያ የተጠላበትእና የተነቀፈለት ፊቱ ለስኬቱ ቁልፍ ሆነ።

ብዙዎች እንደሚሉት ከችግሮቻችን እንደምንልቅ ችግር ነው ያልናቸው ነገሮች ወደ ስኬት ሊመሩን እንደሚገባ ያሳየ ስመጥር ሰው ሆነ።

የሚወረወርብህን ድንጋይ ሰብስበህ በሱ ቤት መስራት ወይም ዘላለም እያለቀሱ መኖር የቱ እንደሚሻል ያሳየም ሰው ነው
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
በአፍላ የፍቅር ዘመን የማይሆኑት የለም።መሮጥ-መሯሯጥ፥መምታት-መማታት፥መሳቅ-መሳሳቅ፥መብረር-ማባረር፥አረ ስንቱ!የሁለቱም ወገን ድርጊት በወጉ ለፍቅር፥ለደስታ ስለሆነ ለክፉ አሳልፎ አይሰጥም፤በመካከሉም ለቀልድ ተብሎ የሚወረወር ጠጠር አናት ፈርክሶ ሲያደማ መታየቱ ከፋ እንጅ!

የ27 ዓመቷ ዩጎዝላቪያዊት ሚላንካና የ32 ዓመቱ ጉብል ኢሊጃ ተፈቃቅረው ከተጋቡ መንፈቅ አልሞላቸውም።አቶ ባል አንዳንድ ጊዜ ድንገተኛና ያልታሰበ ድርጊት እየፈፀመ ሚስቱን ያስደነግጣል፥"ውቃቢ ያስርቃል"፤ያስቃል።በአራዳው ቋንቋ ይኮምካታል እንደ ማለት ነው።ሚስትም እንደዚሁ።

አቶ ኢሊጃ ባለቤቱን እቤት ትቶ ለስራ ይወጣና በዚያው ከአንድ ጓደኛው ቤት ይሄዳል።ሲመለስ ከዚያው ከጓደኛው ቤት የተዋሰውን ሙሉ ማስክ በማጥለቅ ወደቤቱ ያመራል።ከደጁ ደርሶ በር ሲያንኳኳ ሚስት በመስተዋቱ የታያት ባሏ ሳይሆን እጅግ አስፈሪ ልብስ የለበሰ ሰው ይሆናል።ታዲያ ባልዋ በአጋጣሚ ክፉ ቀን ሲገጥማት ራስዋን ለማዳንና ከአደጋ ለመከላከል ትችል ዘንድ የጠመንጃ አተኳኮስ አስተምሯት እንደነበር ማስክ አጥልቆ የመጣውን ሰው ስታይ  ትዝ ይላታል።

ወይዘሮ ሚላንካ ወዲያው ወደመኝታ ክፍሏ ትገባና የባሏን አውቶማቲክ ጠመንጃ ከቁምሳጥን አውጥታ የሚያብለጨለጩ ጥይቶቹን በማቃም አቀባብላ ወደበሩ ተጠጋች።በሩ ባለመስታወት ስለነበር ወይዘሮዋ ጠመንጃዋን ደግና ሰውየው ከአከባቢው እንዲሄድ ምልክት ታሳየዋለች።ያ ሞቱ የቀረበ ባል ግን ሚስቱ ላይ የቀለደ መስሎት እምቢታ በማሳየት እዚያው ይገተራል።ፊትዋን ብታኮሳትር፥እጇን ብታወራጭ ሰውየው ፍንክች ሳይል ይቀራል።

ወይዘሮ ሚላንካ የመጨረሻውን ርምጃ በመውሰድ ቃታ ስባ ተኩስ ከፈተች።የጥይት መዓት የተርከፈከፈበት ያ "ምስኪን " ባልዋ ከደጃፉ ላይ ተደፋ።ወዲያው ሟች በአንቡላንስ-ገዳይ በፖሊስ ታጀቡ። ሆስፒታል ተደርሶ የሟች ማስክ ሲገለጥ ቆማ ትመለከት የነበረችው ወይዘሮ ሚላንካ እራስዋን ይዛ እዬዬዋን ታቀልጠው ጀመር።በነገሩ ግራ የተጋቡት ፖሊሶችና ሐኪሞች ሚላንካን ዘወር አድርገው ሁኔታውን ማጣራት ሲጀምሩ ሟች ባል፥ገዳይ ደግሞ ሚስት መሆናቸውን ይረዳሉ።በሚስቱ እጅ የውሸት ሳይሆን የእውነቱን ሞት የተቀበለው ኢሊጃ በማግስቱ ሲቀበር ሴቲቱ ግን ማረፊያ ቤት ገባች።"ወንጀለኛም ሃዘንተኛም" መሆኗ ነው እንግዲ።ያለቦታው የሚሆን ቀልድ ለዚህ አበቃ።"ቀልድና.....ቤት ያጠፋል" እንዲሉ።

@Amazing_fact_433
2024/09/28 19:21:50
Back to Top
HTML Embed Code: