Telegram Web Link
Kygo & Selena Gomez - It Ain't Me (Audio)
Kygo & Selena Gomez - It Ain't Me

ይህን መሰል ዘፈን ከፈለጉ የዘፈን ቻናላችንን ይቀላቀሉ 👍
በኬንያ ይህ አትክልተኛ ተቀጥሮ ከሚሰራበት ቤት 3ት እህትማማቾችን አስረግዙዋል።

@Amazing_fact_433
@Amazing_fact_433
ጋደም ብላቹ ፊልም የሚታይበት ሲኒማ ቤት መኖሩን ታውቁ ይሆን?!

በ ታይላንድ ሀገር የሚገኝው ይህ ሲኒማ ቤት ለእያንዳንዱ ተመልካች አልጋ አለ ብርድልብስ እና አንሶላ አለ። ትራስ አለ። ከዚያማ ዘና ብለህ ፊልምህን መኮምኮም ነው።

ሌላው ደግሞ Drive-in Theatre ነው። ይኼ ደሞ ከመኪናህ ሳትወርድ ፊልም የምታይበት ዘዴ ነው። ትልቅ ስክሪን አለ። መኪና ማቆሚያ ሰፊ ፓርኪንግ ስፔስ አለ። መኪናህን አቁመህ እዛው ተቀምጠህ ፊልምህን ማየት ነው።

@Amazing_fact_433
@Amazing_fact_433
በሶማሊ በአንድ ወቅት አጥፍቶ ለመጥፋት ያሰበ አሸባሪ ቦምብ ይዞ አውሮፕላን ውስጥ ገብቶ የነበረ ሲሆን ከበረራው ከደቂቃዎች በኋላ ቦሞቡ በፈለገው መንገድ ባለመፈንዳቱ በአውሮፕላኑ አንድ አቅጣጫ ብቻ ቀዳዳ ፈጥሮ በከፍተኛ ፍጥነት ሰውየው ሳያስበው ተወገደ። የሞተው ብቸኛው ስው እሱ ነበር

@Amazing_fact_433
@Amazing_fact_433group
እውነተኛ ፍቅር!

የታመመ ባሏን በጀርባዋ የተሸከመችው ድንቅ ሴት፦ የ32 ዓመቷ ሂባ የ3 ልጆች እናት ናት ከ6 ዓመታት፤ በፊት ባሏ በተደራረበበት በሽታ እግሮቹ መንቃሳቀስ ይሳናቸዋል። በየቀኑ ሆስፒታል መሄድና ህክምናውን መከታተል ነበረበት።

ታዲያ ይህች ድንቅ ሴት 'ፍታኝ' አላለችም ወይም 'ጥላው' አልሄደችም። 'አብሽር! እኔ አለውልህ' ብላ በሴት አቅሟ ባሏን ጀርባዋ ላይ አዝላ በየቀኑ ወደ ሆስፒታል ታመላልሳለች።

"በኔ እንዳታፍር! 'ልፍታሽ' ብያት፤ ነበር። እሷ ግን አልተቀበለችኝም። ሚስቴ ለኔ ልዩ ሴት ናት። እናቴ በሆዷ 9 ወር ሚስቴ ደሞ ለ6 ዓመት በጀርባዋ ተሽክማኛለች።" ይላል።

እሷም በበኩሏ "እስክሞት ድረስ እሸከመዋለሁ።" ትላለች ።

ይህን መሰል ወረት የለሽ፤ ንፁህ ፍቅር ያድለን
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
በሃገር ዴንማርክ እንዳሻዎ ለልጆ ስም ማውጣት አትችሉም! መንግስት ለህዝቡ ካቀረበው 7,000 ስሞች ውጭ ለልጃቹ ስም ማውጣት አትችሉም! 🇩🇰🇩🇰

7,000 የወንድም የሴትም አንድ ላይ ተደምሮ ነው!


@Amazing_Fact_433
@Amazing_Fact_433
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
በቻይና አንድ የ86 ዓመት አዛውንት የ81 ዓመት አዛውንት የመጀመሪያ ፍቅራኛቸውን አግብተዋል

 ከ60 ዓመታት በፊት ፍቅረኛሞች ነበሩ ።  በመጨረሻም የትዳር ጓደኞቻቸው ሲሞቱ ሰሞኑ መጋባታቸውን  የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

@Amazing_Fact_433
@Amazing_Fact_433
የጭንቅ ቀን ሰው! ፓትርያሪክ ሺኖዳ በእሸቴ አሰፋ
ክህደት እና ፀፀት ፣ጥፋት እና ምህረት ሃዋርያው ፔጥሮስ መቆያ በእሸቴ አሰፋ

@Amazing_Fact_433
@Amazing_Fact_433
እንኳን ለ እየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በዓል በሰላም አደረሳችሁ መልካም በዓል ።

@Films_433 @Films_433
በአዲስአበባ ከተማ፥ በቀበና ወንዝ ለይ ከፍ ያለ የመስታወት ድልድል ሊሰራ መሆኑ ተነግሯል 🎢

@Amazing_Fact_433
Suresh Raina ማለት በክሪኬት ስፖርት ክሬዚ ለሆኑት ህንዳውያን ፡ እንደ ድንቅ የሚታይ ፡ እጅግ ዝነኛና ፡ በኑሮውም ሚሊየነር የሆነ ታዋቂ ሰው ነው ።
በቅርቡም ከክሪኬቱ አለም አረፍ ብሎ በታዋቂው NDTV የስፖርት ተንታኝ በመሆን ለስሜቱ ይሰራል ።
....
እና ትናንት ወደ አንድ ቦታ እየሄደ እያለ በመሀል መኪናውን አቁሞ የሰፈር ጉሊት ውስጥ ብርቱካንና አትክልቶች ሲገዛ በአድናቂዎቹ ካሜራ ውስጥ ገብቷል ።
......
የማይደበዝዝ ዝና ያለው Suresh Raina ከፈለገ የሚፈልገውን አትክልትና ፍራፍሬ ፡ አደለም በመኪና ፡ በሄሊኮፕተር አስልኮ የመጠቀም ብቃት ያለው ሰው ነው ።
ሆኖም ከአንድ በሰፈር ውስጥ ካለች ጉልት ነጋዴ እቃ ሲገዛ አንድም ፀሀይ ላይ ተቀምጣ ፡ አላፊ አግዳሚው ይገዛኝ ይሆን በሚል ስሜት የምትቃኘውን ጉልት ነጋዴ ሴት ለማበረታታት ሲሆን. .. በሌላ በኩልም ፡ ታች ካለው ህብረተሰብ ጋር ትሁት ሆኖ ለመመሳሰል ነው ። down to earth ፐርሰናሊቲ ።
....


@Amazing_Fact_433
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ይሄን ፎቶ ተመልከት እና ፁህፉን አንብበው

በአማዞን ቤት ፡ እያንዳንዱ መፅሀፍ ሲሸጥ ደወል ይደወል ነበር ።
🔔

ጄፍ ቤዞስ ፡ እ.ኤ.አ. በ 1995 ላይ በትንሽ ጋራጅ ውስጥ አማዞንን የመሰረተ ጊዜ ፡ የሚጠቀሙበት ሰርቨር ብዙ የኤሌትሪክ ሀይል ስለሚፈልግ ፡ በስራ ሰአት ሚስቱ የፀጉር ማድረቂያ መጠቀም ፡ ወይም በቫኪዩም ክሊነር ቤት ማፅዳት አትችልም ነበር ።
....
ከዛም ይህን ድርጅት ከመሰረቱ ከቀናት በኋላ ቢዝነሱን ሰፋ አድርገው ሀያ የሚሆኑ ሰራተኖችን ቀጥረው ፡ በዌብሳይታቸው ገብቶ መፅሀፍ የሚገዛ ሰው መጠበቅ ጀመሩ ።
እና በዛን ወቅት ወደ አማዞን ዌብሳይት የሆነ ሰው ገብቶ አንድ መፅሀፍ ሲታዘዝ ፡ በአማዞን ቤት ደስታ ይሆናል ።

አስገራሚው ነገር አማዞን ሽያጭ በጀመረባቸው በነዚህ ሳምንታት ፡ አንድ መፅሀፍ ሲታዘዝ ፡ ደወል ይደወላል 🔔 ይሄኔ የአማዞን ሰራተኞች የሆነ ሰው በኦንላይን መፅሀፍ እንደገዛቸው ያውቃሉ ፡ እና ፡ ይህን ከአማዞን መፅሀፍ ያዘዘው ሰው ስም ለማየት ኮምፒውተሩን ይከባሉ ።
......
ማለትም በቀን ውስጥ አስር ጊዜ ሽያጭ ከፈፀሙ ፡ አስር ጊዜ ደወል ይደወል ነበር ማለት ነው ። ሆኖም አማዞን ብዙም ሳይቆይ ከሚጠበቀው በላይ ብዙ ትእዛዞች መቀበል በመጀመሩ አንድ መፅሀፍ ሲሸጥ ደወል መደወል ያቆመው በሳምንታት ውስጥ ነው ።
....
ዛሬስ. .....
ያ. .. አንድ መፅሀፍ ሲሸጥ ደወል ይደውል የነበረው አማዞን በአንድ ቀን ከስድስት ሚሊዮን በላይ የተለያዩ እቃዎችን ይሸጣል ። እንደድሮው ቢሆን በቀን ውስጥ ስድስት ሚሊየን ጊዜ ደወል ይደወል ነበር ማለት ነው ።
....
እያንዳንዱን ስኬቱን ደወል በመደወል ያበስር የነበረው አማዞን ፡ አንድ መፅሀፍ ሲሸጥ በደስታ ያጨበጭብ የነበረው አማዞን ፡ ዛሬ ላይ ከ1,525,000 በላይ ጊዜያዊና ቋሚ ሰራተኞችን ቀጥሮ ያሰራል ።

እንደምንም በቆጠባት አስር ሺህ ዶላር ቢዝነስ የጀመረው ጄፍ ቤዞፍ አሁን 197 ቢሊየን ዶላር ሀብት በስሙ አስመዝግቧል ።
......
ነገ በተሻለ ጉልበት ለመንቀሳቀስ ሀይል ይሆነን ዘንድ በያንዳንዱ ትናንሽ ስኬት ፡ እንደጄፍ ቤዞስ በደስታ ደወላችንን እናንሳ
🔔
........
ፎቶ ፡ የአሁኑ ቢሊየነር ጄፍ ቤዞፍ አማዞንን በመሰረተበት ወቅት
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
2024/09/28 21:31:56
Back to Top
HTML Embed Code: