Telegram Web Link
ይህ የሆነው በዚሁ በሀገራችን ጎፋ ዞን ፣ በጌንዞ ጎፋ ወረዳ ፣ ኬንቾ ሻቾ ቀበሌ ላይ ነው።

በዕለተ ሰኞ ከረፋዱ 4:00 አንስቶ ባጋጠመው የመሬት መንሸራተት ናዳ ሳቢያ ከ229 በላይ ወገኖች ህይወታቸው እንዳለፈ ተረጋግጧል።

ከ50 በላይ ህፃናትን ህይወት የቀጠፈው አደጋ ብዙዎችን ማስገረሙን ተያይዞታል ፤ በዚሁ ሀገራችን ኢትዮጵያ መሆኑ ይበልጥ ጭንቀትን ይፈጥራል።

ቁጥሩ ከዚህ በላይ ሊያሻቅብ እንደሚችል እየተጠቆመ ይገኛል። በሰው ሀይል ቁፋሮ እየተደረገ ሲሆን ማሽን እንዳይገባ ቦታው ተደፋት ስለመሆኑ ተገልጿል።

በአከባቢው ለሚገኙ ወገኖቻችን መፅናናቱን እየተመኘን ህይወታቸውን ላጡ ነፍሳቸው ይማር እንላለን።

🕯🕊

@Amazing_Fact_433
@Amazing_Fact_433
እንግሊዛዊው ማይክል ካሮል ህይወትን ለማሸነፍ ፡ የሚረዳውን ስራ ሲፈልግ ፡ ሲወጣ ፡ ሲወርድ ቆየ ። ግን ለሱ የሚሆን ስራ የለም ።
ለሱ የሚሆን ስራ ያለው አንድ ቦታ ብቻ ነው ። የእንግሊዝ መዘጋጃ ቤት ።
እና የሎንዶን ከተማ ፡ መዘጋጃ ቤት. . የፅዳት ሰራተኞች እንደሚፈልግ ያወጣውን ክፍት የስራ ቦታ አይቶ ሄዶ ተመዘገበ ።
ከቀናት በኋላም ተቀጠረ ።

ማይክል ይህንን ስራ በመስራት ላይ እያለ ፡ አንድ ቀን ካገኛት ገንዘብ ላይ ቆጥቦ ሎተሪ ቆረጠ ።
ፈጣሪ በ19 አመትህ የለንደን ከተማ ፅዳት ሰራተኛ ሆነህ አትቅር ሲለው ፡ የቆረጠው ሎተሪ ደርሶት. .. የ18 .4 ሚሊዮን ዶላር አሸናፊ ሆነ ።

ማይክል ካሮል ፡ ከፅዳት ሰራተኝነት ፡ በአንድ ጊዜ ሚሊየነር ሆነ ። ህይወት ሳቀችለት ።
ቤት ገዛ ፡ መኪኖች ኖሩት ።

ከዚያን እለት ጀምሮም ፡ ስራ የሚባል ነገር አለርጂኩ ሆነ ።

ጠዋት ይነሳል ፡ ሲጠጣ ይውላል ፡ ከብዙ ሴቶች ጋር መዋል ፡ ድራግ መጠቀም ጀመረ ።
አኗኗሩ ቅጥ አጣ ።

በተለያዩ ወንጀሎች እየተከሰሰ ፡ ፍርድ ቤት መቅረብ ስራው ሆነ ። በዚህም ከሰላሳ ያላነሱ ጊዜያት በተለያዩ ትናንሽ ወንጀሎች ተከሶ ፍርድ ቤት እየቀረበ. .. ፡ በገንዘብ እና በቀላል እስር ይቀጣ ነበር ።

ማይክል የአልኮል ሱሰኝነቱ ከመብዛቱ የተነሳ በቀን ፡ ሁለት ጠርሙስ ቮድካ ይጠጣ ነበር ።
............
በአንድ ወቅት የለንደን ከተማ ፅዳት ሰራተኛ ሆኖ ድህነትን እንዳላጣጣማት ያሳለፈውን መጥፎ ጊዜ ረስቶ ፡ 24/7 ገንዘቡን መርጨቱን ቀጠለበት ።
.....
በዚህ ሁኔታ ጥቂት አመታት ካለፉና ፡ በእጁ የነበረው ገንዘብ እንዳልነበር ሆኖ ፡ ቤት ፡ መኪና ፡ ንብረቱን ሁሉ ከሸጠ በኋላ ማይክል ስራ መስራት እንዳለበት አሰበ ። ለአመታት ስራ የሚባል ነገር ትቶ መኖሩ ቆጨው ።
እና አንድ ቀን ጠዋት ተነስቶ ወደ አንድ ቢሮ ሄዶ አንኳኳ
......
ሃላፊው እንዲገባ ፈቀዱለት
እንዴት ኖት አላቸው ።
ሰውየው ምቾት የለወጠውን ማይክልን በቶሎ ማስታወስ አልቻሉም ።

እርግጥ ነው ጊዜው ስለቆየ ረስተውኝ ይሆናል ። እኔ ማይክል ካሮል እባላለሁ ። ከአመታት በፊት እናንተ ጋር እሰራ ነበር ።

ሰውየው አላስታወሱትም ።

ምን ነበር የምትሰራው ብለው ጠየቁት
ፅዳት ሰራተኛ ነበርኩ
ሰውየው ትዝ አላቸው ፡ ጥቂት ካወሩት በኋላ እና አሁን ምን ልርዳህ አሉት
የበፊት ስራዬን ፡ ለመጀመር ማለት . .. የከተማ ፅዳት ሰራተኛ ፡ ከፈለጋችሁ ................
.........

ሰውየው ማይክልን ቀጠሩት ።
..........

እና አሁን በለንደን ጎዳና ላይ ፡ አንድ ወፍራም ሰውዬ. .. የፅዳት ስራ ሲሰራ ካያችሁት ፡ ያ ሰው ፡ በአንድ ወቅት ሚሊየነር የነበረውና ፡ ህይወት የሰጠችውን እድል ሊጠቀምበት ባለመቻሉ ፡ ተመልሶ ፅዳት ሰራተኛ የሆነው ማይክል ካሮል እንደሆነ እወቁ ።
........
የተሰጠንን እድል በአግባቡ እንጠቀምበት


........
Dragonflies የተባሉት የነፍሳት ዝርያዎች 6 እግሮች ቢኖሯቸውም ሰውነታቸውን መሸከም ስለማይችሉ መራመድ ይከብዳቸዋል። እግራቸውን ለመራመድ ሳይሆን ለሌሎች ተግባሮች (ለምሳሌ ምግብ ለመያዝ) ይጠቀሙበታል

@Amazing_fact_433
በጎፋ ዞን ባጋጠመው የመሬት ናዳ አደጋ ምክንያት ብዙሃንን ለሞት ዳርጓል።

ለነዚህ ደጋግ ህዝቦች ብዙዎች ለመድረስ የባንክ ሂሳብ ቁጥር ይፋ ተደርጓል።

የጎፋ ዞን የአደጋ ጊዜ ዝግጁነት እና ምላሽ ፈንድ - 1000511561276

* አንዳንድ ሀሰተኛ የባንክ ሂሳብ ቁጥሮች እየተሰራጩ ስለሆነ በመጠንቀቅ ይህንን ይጠቀሙ!

በድጋሚ ለአከባቢው ማህበረሰብ መፅናናት እንመኛለን።

@Amazing_Fact_433
🔘የኦሎምፒክ ጨዋታዎች አርማ አምስት የተጠላለፉ ባለብዙ ቀለም ቀለበቶችን ያቀፈ ነው !

ሰማያዊው ቀለበት አዉሮፓን ይወክላል ፣ ቢጫው ቀለበት እስያን ይወክላል ፣ ጥቁር ቀለበት አፍሪካን ይወክላል ፣ አረንጓዴው ቀለበት አውስትራሊያ ይወክላል ፣ ቀይ ቀለበት ደግሞ አሜሪካን ይወክላል።

@Amazing_Fact_433 @Amazing_Fact_433
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🔗የአለማችን ዉዱ ሞተርሳይክል 🏍

የአለማችን ዉዱ ሞተር በምስሉ ላይ እንደምትመለከቱት ማርከስ ሊሚትድ ይሰኛል። ዋጋዉም 11 ሚሊየን ዶላር ያስወጣል።💵

@Amazing_Fact_433 @Amazing_Fact_433
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ይህንን ያውቃሉ?

በእግርኳስ ሊግ ቀዳሚ የሆነችው አውሮፓዊቷ ሀገር እንግሊዝ የቆዳ ስፋቷ 130,310 Km² ቢሆንም በሀገሪቷ ውስጥ 2127 ደረጃቸውን የጠበቁ የእግርኳስ መጫወቻ ስታድየሞች አሏት።

በተቃራኒው ደግሞ የሀገራችን የቆዳ ስፋት 1,112,000 Km² ቢሆንም አንድም ጥራቱን የጠበቀ ስታድየም የለንም። ብሄራዊ ቡድናችንም ጨዋታ የሚያደርገው ከሀገር ውጪ ተሰዶ እንደሆነ አይዘነጋም።

የሀገራችን አጠቃላይ የቆዳ ስፋት ከእንግሊዝ ጋር ሲነፃፀር በ8.53 እጥፍ የበለጠ ነው።

ይህ በእንዲህ እያለ ሀገራችን የ2029 የአፍሪካ ዋንጫ የማዘጋጀት ፍላጎት እንዳላት ተሰምቷል።

...? 🙄


@Amazing_Fact_433 @Amazing_Fact_433
☞︎ በአውስትራሊያ ሰዎች አምፖሉ ራሳቸው እንዲቀይሩ አይፈቀድላቸውም።በዚህም የተነሳ የኤሌክትሪክ ሠራተኛን የማነጋገር ግዴታ አለባቸው።
☞︎ ይህንን ህግ ተግባሯዊ የማያደርጉ ከሆነ በመኖሪያ ቤት ከሆነ ከ$10 ዶላር ጀምሮ ተግባራዊ ሲሆን ሰዎች በሚበዙበት ቦታ ከሆነ እስከ $50 ዶላር ይሆናል።

@Amazing_Fact_433 @Amazing_Fact_433
የተረሳው እንቁ የሀገራችን ልጅ አቡበከር ናስር

500 ❤️ REACT ከሆነ የአቡኪ አጭር የህይወት ታሪክ እናቀርባለን።

@Amazing_Fact_433
@Amazing_Fact_433
I LOVE YOU ሬስቶራንት ።
.........
ጃደን ስሚዝ ፡ ከአመታት በፊት በተሰራው ካራቴ ኪድ ፊልም ላይ ሲሰራ የምታውቁት ታዳጊ ሲሆን ፡ የታዋቂው የሆሊውድ አክተር የዊል ስሚዝ ልጅ ነው ።

እና ይሄ ታዳጊ ዛሬ አድጎ ቁምነገር መስራት ጀምሯል ። ጃደን ስሚዝ ምንም እንኳን የሀብታም ልጅ እና እሱም ገና በልጅነቱ ብራም ሆኖ ቢያድግም ። ሲወጣ ሲገባ የሚያያቸው የሎስ አንጀለስ ምስኪን ቤት አልባዎች ጉዳይ ያሳስበው ነበር ።
እና ለነዚህ ቤት አልባ ወገኖቹ ያለውን ፍቅር ለመግለፅ I LOVE YOU የሚል ሬስቶራንት ከፍቷል ።
...........
እና ልክ የምሳ ሰአት ሲደርስ በመግብ የታጨቀው ተንቀሳቃሽ ሬስቶራንት ፡ ቤት አልባና ችግርተኛ ሰወች በብዛት ወደሚኖሩበት የሎስ አንጀለስ አንድ ጎዳና ላይ ሄዶ ፡ ወንበሮችን አዘጋጅቶ እንግዶቹን መጠበቅ ይጀምራል ።
እና መብላት ፈልገው ግን ገንዘብ ለሌላቸው ሁሉ ጥራት ያላቸው ምግቦችንና ፡ የታሸገ ውሀ የያዙ ፡ በላያቸውም ላይ እወዳችኋለሁ የሚል፡ፅሁፍ በተጻፈባቸው የወረቀት ባጎች እያደረገ ይሰጣል ።

ጃደን ስሚዝ በዚህ የጀመረውን ምስኪኖችን የመመገብ ስራ አስፋፍቶት አሁን ላይ ቋሚ ሬስቶራንቶች ተከፍተው አገልግሎቱን እየሰጡ ነው ። ጃደን ይህን ሀሳብ ሲጀምር ዋና እቅዱ ቤት አልባዎችን እና ችግረኞችን ለመመገብ ስለሆነ ፡ ለነሱ ምንም አያስከፍልም ፡ ነገር ግን ምግቡን ወዶት ለመመገብ የመጣ መክፈል የሚችል ሰው ግን ፡ የምግቡን እጥፍ ዋጋ መክፈል ይጠበቅበታል ።
........

በጥቁር ታዋቂ ሰወች ላይ የሚደረገው የተቀነባበረ ስም ማጥፋትና ፡ የጥላቻ ሰለባ የሆነው ጃደን ስሚዝ. .የተቸገሩ ሰወች. . .ምግብ ብቻ ሳይሆን ውዴታና ፍቅርን ማግኘት አለባቸው ብሎ ስለሚያምን. .. እሱ በከፈታቸው በነዚህ ተንቀሳቃሽና ቋሚ ምግብ ቤቶች እያንዳንዱ ችግረኛ ለመመገብ ሲመጣ. .. ከምግቡ ጋር አንድ ቃል ይነገረዋል ። I LOVE YOU የሚል ።

..............
በህይወት መኖሩን ለማረጋገጥ ተማሪዎችን ከነ መምህራቸው ያገተው ሰው

ባቡራም ብሂል የተባለው ህንዳዊ የ40 ዓመት ጎልማሳ ራጃስታን በተሰኘችው ግዛት የሚኖር ሰው ነው፡፡

የግዛቲቱ አስተዳዳሪዎች ይህንን ሰው መሞቱን የሚያትት ማስረጃ ለቤተሰቦቹ ይልካሉ፡፡ በህይወት እያለ መሞቱን የሚያስረዳ ማስረጃ የደረሰው ይህ ሰው አለመሞቱን ለማሳየት ወደ ተቋሞ ቢሄድም የሚሰማው ያጣል፡፡

መንግስት ለግለሰቡ የሞት ማስረጃ ከሰጠ በኋላ ንብረቶቹ ወደ ሌላ ሰው ሊያስተላልፍ እንደሚችል የሰጋው ባቡራም በህይወት መኖሩን ለማሳየት መላ ይዘይዳል፡፡

ይህ ግለሰብም ባሳለፍነው ሳምንት ቢላዋ እና ቤንዚን ነዳጅ በመያዝ ባቅራቢያው ወዳለ አንደኛ ትምህርት ቤት ያመራል፡፡
ትምህርት ቤቱ ውስጥ ከገባ በኋላም በትምህርት ለይ ወደ ነበሩ አንድ ክፍል ድንገት በመግባት ተማሪዎቹን ከነ መምህራኑ ያግታል፡፡

ተማሪዎች ከነ መምህራቸው ባልታወቀ ሰው መታገታቸውን ጥቆማ የደረሳቸው ፖሊሶችም ወደ ስፍራው ያመራሉ፡፡
በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋለው ይህ በህይወት የለም የተባለው በመጨረሻም ድርጊቱን የፈጸመው አለመሞቱን ለማሳየት በሚል እንደሆነ ይናገራል፡፡

በመጨረሻም ሞቷል በሚል በስህተት ተመዝግቦ የነበረው ሰው በህይወት መኖሩን አረጋግጧል ሲል ኦዲቲ ሴንትራል ዘግቧል፡፡፡፡
ይሁንና ግለሰቡ ለፈጸመው ወንጀል መቀጣቱ እንደማይቀር በፖሊስ ተነግሮታል ተብሏል፡፡

©Alain
©wasulife

https://www.tg-me.com/amazing_fact_433
የልደት ቀንዎን በዓለም ላይ ካሉ ቢያንስ ዘጠኝ ሚሊዮን ሰዎች ጋር እንደሚጋሩ ያውቃሉ?

ይህም ማለት በየዕለቱ ልደታቸውን የሚያከብሩ ዘጠኝ ሚሊዮን የሚቅጠሩ ሰዎች አሉ።

ይህም በቀን ውስጥ ከአለም አጠቃላይ ህዝብ 0.001131% በአማካይ ልደቱን ያከብራል።

[Sendòist]

@Amazing_Fact_433 @Amazing_Fact_433
የአፍሪካ አንደኛ ደረጃ ላይ የምትገኘው የእግርኳስ ብሄራዊ ቡድን ማነው?
Anonymous Quiz
35%
ሴኔጋል
19%
ግብፅ
39%
ሞሮኮ
7%
ኮትዲቯር
በአለማችን ላይ ምንም ወንዝ የሌላት ብቸኛዋ ሀገር ማን ናት?
Anonymous Quiz
11%
ኤርትራ
66%
ሳዑዲ ዓረቢያ
15%
ኳታር
8%
ሰሜን ኮርያ
2024/09/28 21:33:51
Back to Top
HTML Embed Code: