Telegram Web Link
🔴ሰሜን ዕዝ በአንድ ሌሊት 7ሺ ሰራዊት በተኛበት ተረሽኗል ።

@amarawiyan
“በአንዳንድ ቦታዎች ላይ የይገባኛል ጥያቄ የሚነሳባቸው እና አከራካሪ የሆነ ቦታዎች፤ ዳግም የሰው ልጆችን ህይወት ሳይነጥቁ፤ በሰላም፣ በድርድር እና በሀገሪቱ ህገ መንግስት መሰረት ብቻ ምላሽ እንዲያገኙ በሁለቱም ወገኖች ከመተማመን ተደርሷል፡፡

ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ

@amarawiyan

የህወሓት እና የብልግና አመራሮች አዲስአበባ ውስኪ እየራጩ ነው !
አርበኛ ዘመነ ካሴ ከዚህ በላይ መታሰር አለበት የሚል እምነት የለኝም። የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት አመራሮች ከግለሰባዊ ስሜት በመውጣት በመንግስታዊ ትክሻ እና ኃላፊነት የዘመነን ጉዳይ ትመለከቱት ዘንድ እጠይቃለሁ። chrstian tadele
ህወሓት በማይጨው ጦርነት መክፈቱ ተሰምቷል ።

ለሰዓታት ቆሞ የነበረው ውጊያ በህወሓት በኩል ተጀምሯል ።

@amarawiyan
ህውሃት ስምምነቱን ጥሶ አዲስ ጦርነት ከፈተ።

ህውሃት ከትናንት በስቲያ ምሽት ለሰራዊቱ ኮረምን ተቆጣጥረናል በማለት ተናግሯል።

ትናንት ከቀኑ 5:00—10:00 ማይጨውንና አካባቢውን እንድሁም መስዋት የተባለች ከተማን ከመከላከያው ነፃ ለማድረግ 8 ጊዜ የውጊያ ሙከራ አድርጎ ከሽፎበታል።

ትናንት ከሰዓት በኋላ በተደመሰሰበት ምትክ በርካታ ቁጥር ያለው ኃይል ወደ ማይጨው አስጠግቷል።ህውሃትን ማመን ቀብሮ ነው።

ምንጭ :-Wasu Mohammed

@amarawiyan
በሰላም ስምምነቱ የተበሳጩ የሕወሐት ደጋፊዎች በሲያትል በመኪናቸው መንገድ ዘግተዋል።

በንፁሐን ደም የተጨማለቁ አውሬዎች የደም ጥማታቸውን ያረኩ አይመስሉም !

@amarawiyan
ዘላለማዊ ክብር ለሰማዕታት ! ለሀገር ለአማራ ህዝብ የተከፈለ መካሻ ማወራረጃ የሌለው መስዋዕትነት !
የኢትዮጵያ እና የህወሓት ጦር መሪዎች በናይሮቢ ተገናኙ።

@amarawiyan
የወሰዱት ንብረት እንጅ ማንነቴን መቀየር አልቻሉም! ጎልማሳው አርሶ አደር ሰይድ ሁሴን

በበቀል ተፀንሶ በክፋት ተወልዶ ያደገው የአውሬው መንጋ!

ታጣቂው አሸባሪ የትግራይ ወራሪ ቡድን ከሁለት አመት በላይ ቆይታ ባደረገበት ዋጃ ከተማ ላይ ጫፍ የወጣ አማራ ጠልነቱን አረጋግጦ አልፏል።

የትውልድ ቦታው በጀግኖቹና በአይበገሬዎቹ ወርቄ ላይ የሆነውና ነዋሪነቱን በዋጃ ከተማ ያደረገው አርሶ አደር ሰይድ ሁሴን ከመጠላያ ቤትና ንብረት እሰከ ተሽከርካሪ በአረመኔዎቹ የጠላት ስብስቦች ተጠቂ ሆኗል።

ለዘመናት የማንነትን ጥያቄ ሲያነሳ የነበረው የራያ አላማጣ ፣ ባላ፣ ጨርጨር፣ ዋጃና ጥሙጋ ህዝብ በአፋኞች ስር ሆኖ በግዞት ተቆልፎ በርካታ የስቆቃ ጊዜ አሳልፏል።

ይህ በፎቶው የምትመለከቱት ጎልማሳ አርሶ አደር ሰይድ ሆሴን ኑሮን ለማሻሻል በአረብ አገር ከባለቤቱ ጋር በስደት እያለ ሰርቶ ያጠራቀመውን በወጃ ከተማ ትዳር መስርቶ የሚኖር ታታሪ አርሶ አደር ነው።

አንተ የእኛን ሰራዊት ተዋግተው የጨረሷቸው ወርቄዎች ናቸው ያንተም ትውልድ ቦታ ከዚያው ነው በማለት ቤቱን በከባድ መሰሪያ በመምታትና በማፍረስ፣ 30 ኩንታል ጤፍ፣ 40 ኩንታል ማሽላ፣ 115 ግራም ወርቅ፣ የወንድሙን የቤት መኪና የውስጥ እቃ እና ሙሉ የቤት ቁሳቁስና በጥሬ ገንዘብ ከ 98 ሽህ ብር በላይ በመዝረፍ ዛሬ ላይ ቤተሰቡን ይዞ በባዶው እንዲንገላታ ሆኗል።

እነኝህ የክፋት ጥግ ቀለባቸው የሆኑ አሸባሪዎች የወሰዱት ንብረት እንጅ ማንነቴን አልቀሙኝም ከጀግናው የወገን ጥምር ጦር ጎን በመሆን ተፋልሜ ዛሬ ላይ የሰላም አየር መግኜቴ ኩራት ይሰማኛል ብሎናል ጀግናው ተዋጊም አራሽም አርሶ አደር ሰይድ ሁሴን

©ራያ ኮሙኒኬሽን

@amarawiyan
የፌዴራል መንግስት እና የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በኦሮሚያ ክልል በተደጋጋሚ በንፁሃን ላይ እየደረሱ ያሉ ጥቃቶችን በአስቸኳይ ያስቁሙ ሲል የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ኢሰመጉ) ጥሪ አደረገ።

የፌዴራል መንግስት እና የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በኦሮሚያ ክልል በተደጋጋሚ በንፁሃን ላይ እየደረሱ ያሉ ጥቃቶችን በአስቸኳይ ያስቁሙ ሲል የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ኢሰመጉ) ጥሪ አደረገ።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች ማንነትን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች መፍትሔ እንዲያገኙ:_

1) በግንቦት 15 ቀን 2014 ዓ.ም፣
2) ግንቦት 20 ቀን 2014 ዓ.ም፣
3) ግንቦት 28 ቀን 2014 ዓ.ም፣
4) ሰኔ 14 ቀን 2014 ዓ.ም፣
5) ሰኔ 27 ቀን 2014 ዓ.ም፣
6) ሰኔ 29 ቀን 2014 ዓ.ም፣
7) ጳጕሜ 4 ቀን 2014 ዓ.ም፣
8) መስከረም 15 ቀን 2015 ዓ.ም፤
9) መስከረም 20 ቀን 2005 ዓ.ም፣
10) መስከረም 25 ቀን 2015 ዓ.ም እንዲሁም
11) ጥቅምት 24 ቀን 2015 ዓ.ም በተከታታይ ጋዜጣዊ መግለጫዎችን በማውጣት የሚመለከታቸው አካላት መፍትሄ እንዲሰጡት ሲያሳስብ መቆየቱን አውስቷል።

ይሁን እንጅ ችግሩ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ ዜጎች ለከፍተኛ የሰው ህይወት መጥፋት፣ ለአካል ጉዳት፣ ለንብረት ዝርፊያና መውደም፣ ለእገታና መፈናቀል እየተዳረጉ ይገኛሉ ብሏል፡፡

1) በኦሮሚያ ከልል ምስራቅ ወለጋ ዞን ከሳሲጋ ወረዳ በቅርብ ርቀት ላይ በምትገኝ ጽጌ ከተማ በጥቅምት ዐ8 እና 09 ቀን 205 ዓ.ም የታጠቁ ቡድኖች ባደረሱት ጥቃት ሞት፣ የአካል ጉዳት እና ንብረት ውድመት መድረሱን

2) በተመሳሳይ ጥቅምት 19 ቀን 205 ዓ.ም ከጊዳ አያና ወደ ነቀምት በሚወስደው መንገድ ላይ በህዝብ ትራንስፖርት ሲጓዙ በነበሩ ተማሪዎች ላይ በተፈጸመ ጥቃት በአሁን ሰዓት ቁጥራቸው ያልታወቁ ሰዎች መሞታቸውን እና የአካል ጉዳት መድረሱን ኢሰመጉ ካሰባሰባቸው መረጃዎች ለመረዳት ችሏል፡፡

ከጥቅምት 2 ቀን 205 ዓ.ም ጀምሮ ከነቀምት ወደ ምዕራብ ወለጋ፣ ቄለም ወለጋ እና አሶሳ የሚወስደው መንገድ በተለያዩ ቦታዎች በሸኔ ታጣቂ ቡድን መዘጋቱን እንዲሁም

የተዘጉ መንገዶችን እና በታጣቂ ቡድኑ የተያዙ አካባቢዎችን ለማስለቀቅ በታጣቂ ቡድኑ እና በመንግስት የጸጥታ አካላት መካከል በሚደረግ የተኩስ ልውውጥ ንጹሀን ሰዎች ላይ ሞት እና የአካል ጉዳት እየደረሰ መሆኑን ኢሰመጉ ካሰባሰባቸው መረጃዎች ለመረዳት መቻሉን ጠቅሷል፡፡
በተጨማሪም ከዓመታት በፊት ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው የነበሩና አንጻራዊ ሰላም አለ ብለው ወደ መኖሪያቸው በተመለሱ የጊዳ አያና ወረዳ ፊት በቆ ቀበሌ ነዋሪዎች ላይ በተደጋጋሚ ጊዜ በታጠቁ ቡድኖች ዘረፋ እየተፈጸመባቸው መሆኑንም ገልጧል።

3) በኦሮሚያ ከልል ምስራቅ አርሲ ዞን ጀጁ ወረዳ ሑሩታ ዶሬ ቀበሌ ጥቅምት 27 ቀን 2015 ዓ/ም በሸኔ ታጣቂዎች በተከፈተ ጥቃት 4 ሰዎች ህይወታቸው ሲያልፍ የአካል ጉዳት የደረሰባቸውም እንዳሉና የቀበሌው ነዋሪዎች አሁንም በከፍተኛ ስጋት ላይ እንደሚገኙ፣

4) በተመሳሳይ በጀጁ ወረዳ አምሻራ ቀበሌ ጥቅምት 27 ቀን 2015 ዓ.ም ምሽት ላይ 8 ሰዎች በሸኔ መገደላቸውን እንዲሁም

5) በኦሮሚያ ክልል በምስራቅ አርሲ ዞን ጀጁ ወረዳ፣ አዲስ ህይወት፣ መንበረ ህይወት፣ ተስፋ ህይወት፣ መርቲ እና አጫሞ ቀበሌዎች የሚኖሩ _ የአካባቢው ነዋሪዎች በታጣቂ ቡድኑ ተከበው በከፍተኛ ችግር ውስጥ መሆናቸውን፣

6) በተጨማሪም ጥቅምት 27 ቀን 2015 ዓ.ም በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን ሳሲጋ ወረዳ በሚገኝ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ 5 የቤተክርስቲያን አገልጋዮች በአሰቃቂ ሁኔታ ማንነታቸው ባልታወቀ ታጣቂ ቡድኖች መገደላቸውን ኢሰመጉ ካሰባሰባቸው መረጃዎች ለመረዳት መቻሉን ጠቅሷል፡፡

7) በምዕራብ ሸዋ ዞን አማያ ወረዳ ቡርቃ ቀበሌ ጥቅምት 24 ቀን 2015 ዓ.ም የሸኔ ታጣቂዎች በእርሻ ስራ የሚተዳደሩ 4 ሰዎችን አግተው ከወሰዷቸው በኋላ እያንዳንዳቸው ሶስት መቶ ሺህ ብር (300.000) ካመጡ ከእገታው እንደሚለቀቁ ተገልጾላቸው የታጋቾች ቤተሰቦችም ገንዘቡን አሰባስበው ሲሄዱ የታገቱት ሰዎች በሸኔ ታጣቂ ቡድን በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለው ወሊሶ ፖሊስ ጣቢያ አስከሬናቸው እንደተገኘና ጥቅምት 28 ቀን 2015 ዓ.ም አስከሬናቸው ዘመዶቻቸው ወደሚገኙበት ተወስዶ የቀብር ስነ ስርዓታቸው መፈጸሙን ኢሰመጉ ለማወቅ ችሏል፡፡

8) በሌላ በኩል በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን ጥቅምት 27 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 2 ሰዓት ጀምሮ የሸኔ ታጣቂዎች ነቀምቴ ከተማ በመግባት ንጹሃን

ሰዎች ላይ ግድያ፣ የአካል ጉዳት፣ የንብረት ዝርፊያና ሰዎችንም አግተው በመውሰድ አካባቢውን ለቀው መውጣታቸውን ኢሰመጉ ካሰባሰባቸው መረጃዎች

ለመረዳት ችሏል፡፡

9) ጥቅምት 28 ቀን 2005 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ወደ ሀዋሳ በሚወስደው የፍጥነት መንገድ ላይ ወደ መቂ ከተማ አካባቢ ታጣቂዎች በመንገዱ ሲጓዙ በነበሩ መኪናዎች ላይ ተኩስ በመክፈት ጥቃት እንደፈጸሙ እና በዚሀም ጥቃት የሰዎች ህይወት ማለፉን፣ አካል ጉዳት መድረሱን እና በመንገዱ ሲጓጓዚ የነበሩ አንዳንድ መኪናዎቸ መቃጠላቸውን ኢሰመጉ ካሰባሰባቸው መረጃዎች ለመረዳት ችሏል፡፡

10) በተጨማሪም በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን ጊሚቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ በአብዛኛው የአማራ ብሔር ተወላጆች ከሚኖሩበት አካባቢ ከ800 በላይ አባወራዎችን የሸኔ ታጣቂ ቡድን ወደ አካባቢው መጠጋቱን እና ከቦ መያዙን ተከትሎ መንግስት በፌደራል ፖሊስ በማጀብ ወደ ሌላ የጸጥታ ሁኔታው ወደሚሻልበት ቦታ ይዞአቸው መሄዱን ኢሰመጉ መረጃ መሰብሰቡን ገልጧል።

በመጨረሻም ኢሰመጉ ከላይ በተዘረዘሩት ጉዳዮች ላይ የአካባቢዎቹ የደህንነት ሁኔታ ምቹ ሲሆን ሰፋ ያለ የምርመራ ስራን በመስራት ዝርዝር ዘገባን እንደሚያዘጋጅ ገልጧል፡፡

@amarawiyan
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፣ ፋና ብሮድካስቲንግ ዜናውን አጥፍተውታል።

@amarawiyan
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የፈፀመውን ክህደት በዝርዝር ተመልከቱ !

https://youtu.be/S3du6y8mLqQ
2024/11/16 06:37:11
Back to Top
HTML Embed Code: