Telegram Web Link
የረመዷን ትውስታ የ5 ደቂቃ መልዕክት ስሁርና ኢፍጧር ክፍል 1
በኡስታዝ አቡ ሐይደር

Join ➤➤ www.tg-me.com/abuhyder
Click and Like ➤➤ https://www.facebook.com/Ustaz.Abuhyder
የኡስታዝ አቡ ሀይደር ትምህርቶች ስብስብ
Voice message
የረመዷን ትውስታ የ5 ደቂቃ መልዕክት እስቲግፋር በረመዷን ክፍል 2
በኡስታዝ አቡ ሐይደር

Join ➤➤ www.tg-me.com/abuhyder
Click and Like ➤➤ https://www.facebook.com/Ustaz.Abuhyder
Forwarded from .
ኢዜማ እስልምናን የኢትዮጵያ ደህንነት ስጋት አድርጎ የገለጸበት ሚስጥራዊ ሰነድ ይፋ ወጣ
====================================================
«የኢዜማን እውነተኛ ማንነት የማያውቀው ህዝብ እንዳይሸወድ መረጃውን ሼር በማድረግ ህዝቡን እናንቃ! የፓርቲው ማንነት ከቀን ወደ ቀን ይበልጥ ፍንትው እያለ መጥቷል።»
||
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) የተሰኘው የፖለቲካ ፓርቲ በዘንድሮው 6ኛው የሃገራችን ምርጫ ከሚሳተፉ የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል አንዱ ነው። በርካታ እጩዎችን በማስመዝገብ ከአሁኑ ገዢ ፓርቲ (ብልፅግና) በመቀጠል ሁለተኛ ደረጃ ይዟል።

የዚህ ፓርቲ ሊቀመንበር የሆኑት ብርሃኑ ነጋ (ዶ/ር) የርሳቸው ፓርቲ ከተመረጠ ኢስላማዊ ባንክ እንደማይፈቅድ ከአሁን በፊት የተናገሩ ሲሆን፤ ይህን እውነታ ከቀናት በፊት በድጋሜ ማረጋገጣቸው ይታወቃል።
*
ይህ በእንዲህ እንዳለ ሰሞኑን ከዚህ ፓርቲ ያፈተለከ አንድ ሚስጥራዊ መረጃ ይፋ ወጥቷል።
ኢዜማ የሃገሪቷን ወቅታዊ የደህንነት ስጋት የተነተነበት አንድ ባለ 14 ገፅ ሚስጥራዊ ሰነድ አዘጋጅቷል። ዶ/ር ብርሃኑ በዚህ ሰነዳቸው ላይ ከፓርቲያቸው ከኢዜማ እና ከመሰሎቹ በስተቀር ለሀገር ደህንነት ስጋት ብሎ ያልፈረጁት የለም።
ሰነዱ «የሃገሪቷ ወቅታዊ የደህንነት ስጋት ትንተና» ይሰኛል

[ሙሉውን 14ቱንም ገፅ በዚህ ሊንክ ብትገቡ ታገኙታላችሁ።
https://www.tg-me.com/MuradTadesse/10898]
*
በዚህ ሰነድ ላይ በርካታ አካላት የሃገራችን የደህንነት ስጋት ተብለው የተጠቀሱ ሲሆን፤ እስልምናን በተመለከተ ግን «ወቅታዊ የብሄራዊ ደህንነት ስጋቶች» በተሰኘው የሰነዱ የመጀመሪያ ክፍል ላይ «ጽንፈኝነት» በተሰኘ ዐውድ ስር ገፅ 7 እና 8 ላይ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት በአጽንኦት ተጠቅሷል።
ሰነዱ ካነሳቸው ነጥቦች መካከል፦
①) የእስልምና አክራሪነት በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች እየተስፋፋ መሆኑ፣
②) የእስልምና ኃይማኖት ተከታዮች በብዛት በሚገኙባቸው አካባቢዎች ላይ የእስልምናን አክራሪነት በወጣቱ ላይ የማስረጽ ሥራ እየተሠራ መሆኑ፣
③) በሃገሪቱ የሚነሱ የተለያዩ ቀውሶችን ከማስነሳት አልፎ እስከ ማባባስ ድረስ እየሠሩ መሆኑ፣
④) መስጅዶች የዚህ እንቅስቃሴ ዋነኛ መፍለቂ መሆናቸው፣
⑤) በተለያዩ ባለሃብቶች እንደሚደግፉና የተጠናከረ ህቡዕ አንድነት ያላቸው መሆኑን፣
⑥) ከግብፅ፣ ከሳዑዲ ዓረቢያና ከኳታር ጋር ለዚሁ አላማ ጥብቅ ግንኙነት ያላቸው መሆኑ፣
⑦) የገቢ ምንጫቸው ከውጭ የሚላክ ገንዘብ፣ ከኮንትሮባንድ ሥራ፣ ከመዓድናት ሽያጭና መንግስት በማያውቀው በሌላ መልክ ገቢ የሚያገኙ መሆኑን፣
⑧) አይኤስ፣ አል-ቃዒዳና አል-ሸባብ በኢትዮጵያ እንቅስቃሴ የጀመሩ መሆኑን፣
⑨) ሙስሊም ምሁራንና የማህበረሰብ አንቂዎች ለእምነታቸው የተቆረቆሩ በመምሰል ህዝብ ወደ ጽንፈኝነት እንዲገባ ለመሥራት አቅደው ቆርጠው የተነሱ መሆኑን፣
⑩) ነፃነትና እኩልነት ፓርቲ (ነእፓ) በጽንፈኛ ሙስሊሞች የሚሾፈር ስለሆነ እንዲታገድ… ወዘተ የሚሉ እጅግ በጣም አደገኛና መርዘኛ ሃሳቦች ተነስተዋል።

በግሌ ከዚህ ሰነድና ከዚህ በፊትም ኢዜማ ካለው አመለካከት በመነሳት፤
ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ደህንነት ከኢዜማ የበለጠ ስጋት እንደሌለ ተረድቻለሁ።
*
የሚመለከተው አካል የዚህን ፓርቲ መርዘኝነት ተረድቶ ከወዲሁ ከምርጫ ቦርድ ቢያሰናብተው መልካም ነው።
ገና ስልጣን ሳይዙ ይህን ያክል መርዘኛ ከሆኑ፤ አቅሙን ካገኙ ደግሞ ምን ሊሆኑ እንደሚችሉ ለመገመት የግድ ሩቅ አዋቂ መሆን አይጠበቅም።

*
«የፓርቲውን መርዘኝነት ሼር በማድረግ እናሳውቅ! ህዝቡ ሊነቃ ይገባል!»
||
www.tg-me.com/MuradTadesse
#ሰላቱ-ተራዊሕ "ቂያሙ–ለይል"
በአቡ ሀይደር
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኛ በሆነው፡፡
ምስጋና የዓለማት ጌታ ለሆነው ለአላህ የተገባ ነው፡፡ የአላህ ውዳሴና ሰላም የሰላም አለቃና መምህር ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ይሁን፡፡ ድልና የበላይነት ሐቅን ለማንገስና ሀሰትን ለማርከስ በደልን አጥፎቶ ፍትህን ለማስፈን ዕውቀታቸውን፣ ንብረታቸውን፣ ጉልበታቸውን፣ ጊዜያቸውንና ህይወታቸውን መስዋእት በማድረግ ለሚታገሉት ይሁን፡፡

ብዙ ጊዜ ወደ መስጂድ በመሄድ ከዒሻ ሱንነቱል-ባዕዲያ ቡኋላ የሚሰገደውን ሶላት (ቂያሙ-ለይል) ከኢማሙ ጋር አንጨርሰውም፤ መሐል ላይ እናቋርጣለን፡፡ ወይም ተራዊሕ ጨርሰን ዊትሩን ለቤት ብለን እንወጣለን፡፡፡ ይህ ተግባር የተከለከለ ባይሆንም አግባብነት የለውም፡፡ ለሊቱን ሙሉ በሶላት እንደቆመ እንዲታሰብለት የሚፈልግ አንድ ሙስሊም ከኢማሙ ጋር ሁሉንም አብሮ መጨረስ አለበት፡፡ በመሐል ያለ-ምንም አስገዳጅ ምክንያት ኳቋረጠ ቃል የተገባለትን አጅር ያጣል፡፡ ሐዲሡ የሚለው እንዲህ ነው፡-
አቢ ዘር (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደነገረን የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- "ከኢማሙ ጋር እስኪያጠናቅቅ አብሮት የቆመ(የሰገደ) ለሊቱን ሙሉ እንደሰገደ ይጻፍለታል" (ነሳኢይ 1605፣ ቲርሚዚይ 806፣ ኢብኑ ማጀህ 1327)፡፡

በዚህ ምክንያት ሁሉንም ከኢማሙ ጋር ማጠናቀቅ ይገባናል፡፡ አንዳንድ ሰዎች ደግሞ፡- በተጨማሪ ለሊት ላይ ተነስቼ ከሰሑር በፊት መስገድ ስለምፈልግ ነው ዊትሩን የተውኩት ይላሉ፡፡
አላህ ወፍቆት ለይል ላይ በድጋሚ ተነስቶ መስገድ የሚፈልግ ሰውም ተራዊሕን እስከ ዊትሩ ከኢማሙ ጋር አብሮ መስገዱ አይከለክለውም፡፡ ‹‹ከዊትር በኋላ ሶላት የለም!›› ወይም ‹‹የመጨረሻ ሶላታችሁን ዊትር አድሩጉ›› የሚለው ሐዲሥ ክልከላን ሳይሆን አለመስገዱ የተወደደ መሆኑን ለማመላከት የመጣ እንደሆነ የኢስላም ሊቃውንት ያስረዳሉ፡፡ በተጨማሪም የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) አንዳንድ ጊዜ ከዊትር በኋላ ረከዐተይን (ሁለት ረከዓህ) ይሰግዱ እንደነበር መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ ይህም የሚጠቁመው ከዊትር በኋላ ሶላት መስገድ እንደሚቻል ነው፡፡ ስለዚህ ለይልን በድጋሚ ተነስተህ የምትሰግድ ከሆነ ባለ ጥንድ ረከዓህ (ሁለት ሁለት) እያደረግህ ስገድ፡፡ በድጋሚ ግን ዊትር እንዳትሰግድ፡፡ በአንድ ለሊት ሁለት ዊትር የለምና፡፡

ሌላው በተራዊሕ ወቅት በጁዝእ የሚሰገድባቸው መስጂድ ውስጥ ከሆንክ ቁርኣን ወይም ሞባይልህ ውስጥ የጫንከውን ከፍተህ ኢማሙን ከምትከታተል ሞባይልህን አጥፍተህ ቀልብህን ሰብስበህ የኢማምህን ቂርኣት በማዳመጥ መከታተሉ ላንተ በላጭ ነው፡፡ ምክንያቱም፡-
1ኛ) ቀኝ እጅን በግራ ላይ ደርቦ በደረት ላይ አሳርፎ የማስቀመጡ ሱንና አያመልጥህምና፡፡ ቁርኣኑን ወይም ሞባይሉን ከፍተህ የምትከታተል ከሆነ ግን የግድ ቀኝ እጅህ ካረፈበት ቦታ ይነሳል፡፡
2ኛ) አላስፈላጊ እንቅስቃሴዎችን ትቆጥባለህ፡፡ ኢማሙ ጨርሶ ወደ ሩኩዕ ሲወርድ አንተ ግን፡ ሞባይልህን ወደ ኪስ ለመክተት፡ ቁርኣን ከሆነ ደግሞ መሬት ለማስቀመጥ ቦታ ፍለጋ ውስጥ ትገባለህ፡፡ ቁርአንን ደግሞ ከስሩ ምንም ነገር ሳይኖር መሬት ማስቀመጥ አይቻልም፡፡
3ኛ) በሞባይል ቁርኣን እየተከታተልክ ምንም ስልክህ ሳይለንት ቢሆንም ሰው ከደወለልህ ቁርኣኑን ሸፍኖ የደዋዩን ቁጥር ማሳየቱ አይቀርም፡፡ ስልኩን በመዝጋት ስራ ተጠምደህ አንተም አዛ ልትሆን ነው፡፡ ልብህም ከሶላቱ ወጥቶ (ኤጭ ምን አይነቱ ነው!) የሚል ስራ ውስጥ ሊገባ ነው፡፡ ታዲያ የቱ ይሻልሀል?
ሶስቱ ታላላቅ የኢስላም ሊቃውንቶች (ኢብኑ ዑሠይሚን፣ ኢብኑ ባዝ፣ አልባኒ ራሕመቱላሂ ዐለይሂም) በዚህ ጉዳይ ላይ ክልክል ነው ብለው ባያወግዙም በላጩ ግን መተዉ ነው በማለት መክረዋል፡፡
4ኛ) እኔ ከሞባይል ወይንም ዋና ቁርኣን ከፍቼ ካልተከታተልኩ እንቅልፍ ይመጣብኛል፡፡ ነሻጣዬም ይጠፋል፡፡ ድካም ድካም ይሰማኛል፡፡ ቀልቤ ከሶላት ይወጣል፡፡ ስከታተል ግን የበለጠ እጠነክራለሁ ምትሉ ካላችሁ ደግሞ፡- ታላቁ ዓሊም ሸይኽ ኢብኑ ጅብሪን (ረሒመሁላህ) ችግር የለውም መጠቀም ይችላሉ በማለት ፈትዋ ሰጥተዋል፡፡ ራሳችንን የምናውቀው እኛው ነን፡፡ በዚህ ጊዜ ግን ሰው እየደወለ አዛ እንዳያደርገን የሞባይሉን ኔትወርክ ኦፍላይን እናድርገው፡፡ ወይም call setting ውስጥ በመግባት ወደሌላ ቁጥር divert እናድርገው፡፡ ወይም ሲስተሙን ቢዚ አድርጉት፡፡
ደግሞም ‹‹ኢንና አዕጠይና ፣ ለወገብ ጤና›› እያልን በጁዝእ ከሚሰገድባቸው መስጂዶች አንራቅ፡፡ ዛሬ በዚህ ዱንያ ላይ እግሮችህ ለአላህ መቆምን ካበዙ በምትኩ ነጌ በአኼራ በቃጠሎው ቀን መቆሙ ይቀንስላቸዋልና፡፡ አላህ ይወፍቀን፡፡

ለእህቶች፡-
‹‹የአላህን ሴት ባሪያዎች ከአላህ ቤት (መስጂድ) መሄድን አትከልክሏቸው›› የሚለውን ስለ-መብታችሁ የተነገረውን ሐዲሥ ምርኩዝ አድርጋችሁ ከእህቶቻችሁ ጋር በኅብረት ለመስገድ ወደ አላህ ቤት ካቀናችሁ ቀጥሎ ያሉትን ነገራት አደራ ተጠንቀቁ፡-
1) ሒጃባችሁን ጠብቁ፡- ከቤት ስትወጡ ብቻ ሳይሆን መስጂድ ገብታችሁ እስክትሰግዱ ሰግዳችሁም ወደ ቤት እስክትመለሱ ድረስ ሒጃባችሁ ጥብቅ ይሁን፡፡ ወንዶችን የሚፈትን አይነት አለባበስ ለብሳችሁ አትውጡ፡፡ አላህን ፍሩ፡፡ ደግሞም ሽቶ ተቀብታችሁ አትውጡ፡፡ ለማነው የምትዋቡት? ውበታችሁና መዓዛችሁ ለባለቤታችሁ እና ለግላችሁ እንጂ ውጪ ላለ ሰው መሆን ስለሌለበት ከቤት ስትወጡ ተጠንቀቁ፡፡
2) ሰልፍ ማስተካከል፡- አንደኛው ችግራችሁ ነው ይባላል፡፡ (ባለቤቴ እንደነገረቺኝ)፡፡ ሶላት ላይ ተራርቃችሁ ሳይሆን ተጠጋግታችሁ እግር ለእግር ተነካክታችሁ ስገዱ፡፡ በመሐል ሸይጣን እንዳይገባባችሁ ክፍተት አትፍጠሩ፡፡ ምነው በረመዷን ታስሮ አይደል? ካላችሁም አዎ! አመጸኞቹ ታስረዋል፡፡ ሽሜዎቹ እና ደካሞቹ ግን ዕድላቸውን ይሞክራሉና ክፍተት አትፍጠሩላቸው፡፡ መስጂዱ ስላልሞላ በሚል ተበታትናችሁም አትስገዱ፡፡
3) ህጻናትን በተቻለ መጠን መስጂድ አታምጧቸው፡፡ እናንተም እህቶቻችሁም በነሱ ሰበብ አዛ እንዳትሆኑ፡፡ ማምጣቱ ግድ ከሆነና ሰውን አዛ የሚያደርጉ ከሆነም ተገንጥላችሁ ስገዱ፡፡
4) የመጣችሁበት ዓላማ ዒባዳ እስከሆነ ድረስ ሙሉ ተራዊሕን ከኢማሙ ጋር ስገዱ፡፡ አንዳንዴ ከሁለቱ ኢማሞች በድምጹ ማማር የምንወደው ኢማም ከግማሽ በኋላ ከሆነ እሱ እስኪመጣ ድረስ በማለት ገለል ብለን ቁርኣን መቅራት ወይም እንተኛና እሱ ሲጀምር ቀስቅሱኝ እንላለን፡፡ ይህ ስህተት ነው፡፡ የለሊቱን ቂያም ሙሉ አጅር ከፈለግን ሁሉንም እንስገድ፡፡ ወላሁ አዕለም፡፡
አላህ ሆይ! በረመዳን ውስጥ ካለው ኸይር ነገር የምንጠቀም አድርገን! አሚን!
Join ➤➤ www.tg-me.com/abuhyder
Click and Like ➤➤ https://www.facebook.com/Ustaz.Abuhyder
የኡስታዝ አቡ ሀይደር ትምህርቶች ስብስብ
Voice message
የረመዷን ትውስታ የ5 ደቂቃ መልዕክት "ሁሉም የሰውነት ክፍል መፆም አለበት" ክፍል 3 በኡስታዝ አቡ ሐይደር

Join ➤➤ www.tg-me.com/abuhyder
Click and Like ➤➤ https://www.facebook.com/Ustaz.Abuhyder
#ዐሽሩል_አዋኺር
በ አቡ ሀይደር
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው
የረመዷን ሀያ ለሊቶች አለፉ፡፡ አላህ ወፍቆት ኸይር የሸመተበትም ሆነ ነፍሲያው አሸንፎት ወደ ኋላ ያስቀረው ይኖራል፡፡ አሁን የቀረውን ጌዜ ግን መጠቀም የሁሉም ድርሻ ነው፡፡ አላህ ዕድሜ ሰጥቶን የምንጠቀም ያድርገን፡፡ ነቢያችን (ዐለይሂ-ሶላቱ ወስ-ሰላም) በረመዷን የመጨረሻው አስርት ቀናት ውስጥ በዒባዳ በሌላው ጊዜ ከሚበረቱት የበለጠ ይበረቱ ነበር (ሙስሊም የዘገበው)፡፡
በዚህ ለሊት ውስጥ የምትጠበቅ አንድ ለሊት አለች፡፡ እሷም ‹‹ለይለቱል-ቀድር›› ትባላለች፡፡ ይህችን ለሊት አላህ ወፍቆት ምሽቷን በዒባዳና በመልካም ተግባር ያሳለፈ የአላህ ባሪያ፡ አላህ ስራውን ከተቀበለው የሚያገኘው ትርፍ እጥፍ ድርብ ነው፡፡ እሱም፡- በሌላ ጊዜ ለአንድ ሺህ ወራት (83 ዓመት ከ4 ወር) ያህል በዒባዳ በማሳለፍ ከሚያገኘው አጅር በላይ ይሆንለታል ነው፡፡ አንዷ ለሊት 83 ዓመታትን በልጣ ተገኘች፡፡ አላሁ አክበር! አላህ ይወፍቀን፡፡
ከዛሬ ማቅሰኞ ምሽት ጀምሮ የረመዷን 21ኛ ለሊት ይጀመራል፡፡ በተከታታይ የሚመጡትን ምሽቶች በዒባዳ ለማሳለፍ እኛም ከልብ ነይተን፡ በአላህ በመታገዝ ቆርጠን እንነሳ፡፡ የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የረመዷን የመጨረሻው አስርት ቀናት ሲገባ ወገባቸውን ጠበቅ በማድረግ (በመዘጋጀት) ለሊቱን በዒባዳ ህያው ያደርጉት ነበር፣ ቤተሰቦቻቸውንም ይቀሰቅሱ ነበር (ቡኻሪና ሙስሊም)፡፡
ለይለቱል-ቀድርን ለማግኘት ከልቡ አምኖና አላህ ዘንድም የሚያገኘውን ምንዳ በማሰብ በሶላት (በዒባዳ) ላይ ያሳለፋት ሰው ያለፈው ኃጢአቱ እንደሚማርለት በሐዲሥ ተገልጾአል (ቡኻሪና ሙስሊም)፡፡
አላህ ወፍቆት ለይለቱል-ቀድርን ለማግኘት አስርቱን ቀናት በዒባዳ የሚያሳልፍ የአላህ ባሪያ ለይለቱል ቀድር በዛሬው ምሽት እንደተገኘች ሊያውቅበት የሚችልባቸው መንገዶች አሉ፡፡ ከነዚህም ውስጥ፡-
ሀ. ጸሀይ ጨረር አልባ መሆኗ፡- ኡበይ ኢብኑ ከዕብ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደነገረን ለይለቱል-ቀድር በለሊቱ ክፍል ከታየች፡ በንጋቱ ጸሀይ በምትወጣ ግዜ እንደተለመደው ጨረር አይኖራትም፡፡ ያለ ጨረር ነጣ ብላ ብቅ ትላለች፡፡ (ሙስሊም 762)፡፡
ለ. ለሊቱ ብርዳማም ሞቃትም አይሆንም፡- ሁሉም ባለበት ሃገር ላይ ባለው የአየር ንብረት ሁኔታ የሚወሰን ነው፡፡ ለይለቱል-ቀድር በምትታይበት ለሊት፡ የለሊቱ ሁኔታ ከዛ በፊት ከነበሩትና ከዛ በኋላ ከሚመጡት ቀናቶች አንጻር ሞቃታማም ሳትሆን ቀዝቃዛም ሳትሆን፡ ሰላማዊ ሆና የምታነጋ ለሊት ነች በማለት ዐብዱላህ ኢብኑ-ዐባስ (ረዲየላሁ ዐንሁማ) ከነቢያችን (ዐለይሂ-ሶላቱ ወስ-ሰላም) የሰማውን ሐዲሥ አስተላልፎልናል (ሶሒሕ ኢብኑ ኹዘይማህ 2192)፡፡
በነጋታው ይህን ምልክት አየሁ ብሎ ግን ከዒባዳ መሸሽ ትልቅ ስህተት ነው፡፡ ይልቁኑ በቀጣዮቹ ተከታታይ ቀናት ያሳለፍነውን ቀን ለይለቱል-ቀድር ታይቶበት ከሆነ አላህ እንዲቀበለን ዱዓ በማድረግ የበለጠ ልንበረታ ይገባል፡፡ በዚህ ለሊት የሚሰሩ መልካም ተግባራትን በተመለከት ለቀባሪው ማርዳት ነውና ብዙም የምለው ነገር የለኝም፡፡ በዚክር፣ በዱዓእ፣ በኢስቲግፋር፣ በቁርኣን ንባብ፣ በለይል ሶላት፣ በነቢያችን ላይ ሶላዋት በማውረድ… እንበራታ፡፡ አላህ ይወፍቀን

Join ➤➤ www.tg-me.com/abuhyder
Click and Like ➤➤ https://www.facebook.com/Ustaz.Abuhyder
ዘካተል ፊጥር ምንድን ነው ?ለማነው ሚገባው ? በኡስታዝ አቡ ሐይደር
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
መፅሀፍ ቅዱስን አፍዘሃልን?
በእጅህ ስንት ሰዎች ሰለሙ ?

ሌሎችም ጥያቄዎች

ምላሽ በኡስታዝ አቡ ሐይደር
👇👇👇👇👇
https://youtu.be/VgwAzttm4ts
https://youtu.be/VgwAzttm4ts
ከ ኡስታዝ አሕመዲን ጀበል ፔጅ የተወሰደ!!

የጎዳና ላይ ኢፍጣር ዝግጅቱ ነገ ግንቦት 03/2013 በዚያው አደባባይ ከቀኑ በ10 ጀምሮ በመንግስት ሙሉ ወጪ በጸጥታ ኃይሉ ጥበቃና አጀብ ይደረጋል።አንድ ሆነን በጋራ ከቆምን ሌሎች ጥያቄዎቻችንንም እንዲሁ እናስመልሳለን።

Sagantaan Ifxaara kaleesaa dhorkamee bakkuma sila karoorfameetti bor caamsaa 03/2013 baasii guutu mootumaadhaan Qaama nageenyyatiin kabajaan eegamaa sa'a 10 irraa kaasee ni godhama. Tokko taanee yoo waliin dhaabbannee gaaffilee keenya kaanis akkasuma ni debisiifna.
እንኳን ለ1442ኛው የዒዱል ፊጥር በዓል አላህ በሰላም አደረሳችሁ!

ዒዱኩም ሙባረክ!

ተቀበለላሁ ሚንና ወሚንኩም!
#የሸዋል ፆም ፍች (ትንሹ ዒድ)
በአቡ ሀይደር
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው
ምስጋና የዓለማት ጌታ ለሆነው ለአላህ የተገባ ነው፡፡ የአላህ ውዳሴና ሰላም፡ የሰላም አለቃና መምህር ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ ይሁን፡፡ ድልና የበላይነት ሐቅን ለማንገስና ሀሰትን ለማርከስ፡ በደልን አጥፎቶ ፍትህን ለማስፈን ዕውቀታቸውን፣ ንብረታቸውን፣ ጉልበታቸውን፣ ጊዜያቸውንና ህይወታቸውን መስዋእት በማድረግ ለሚታገሉት የአላህ ባሮች ይሁን፡፡
በተወሰኑ (ሁለት ወይም ሶስት) ብሔሮች ዘንድ ከረመዷን ዒድ (ዒዱል-ፊጥር) ማግስት ጀምሮ ለተከታታይ ስድስት ቀናት የሸዋልን ጾም ይጾሙና ሰባተኛውን ቀን እንደ ዒድ ያከብሩታል፡፡ ምክንያቱን ጠይቄ ለማወቅ እንደሞከርኩት ይህን ይመስላል፡-
የዒዱል-ፊጥር ቀን ደብዘዝ ብሎ በደንብ ሳይሞቅ የምናሳልፈው ቀኑ አንድ ቀን ስለሆነና በነጋታው ተመልሰን ወደ ሸዋል ጾም ስለምንገባ ነው፡፡ ስለዚህ ባሉት ተከታታይ ስድስት ቀናት የሸዋልን ጾም በመጾም ሁለቱንም (ረመዷንንም ሸዋልንም) እንጨርስና ከሰባተኛው ቀን ጀምሮ በደንብ ዒዱን እናከብራለን፡፡ እንበላለን እንጠጣለን፡፡ ጎረቤት፣ ጓደኛ፣ ዘመድ እንጠይቃለን፡፡ ብዙ ቀናቶች አሉንና፡፡
ከዚህ ምክንያት መረዳት እንደሚቻለው ሰዎቹ የዒዱል-ፊጥር ቀን አንድ ቀን ብቻ በመሆኑ በሰፊው ለመብላትና ለመጠጣት፣ ከዘመድ አዝማድ ጋር ለመዘያየር የማይበቃ መሆኑ ነው እንጂ የሸዋል ዒድ አለ ብለን አይደለም የሚል ነው፡፡
ማስተካከያ፡-
1ኛ/ የኢስላም ሃይማኖት እንዳስተማረን ከሁለቱ ዒዶች (ዒዱል ፊጥር እና ዒዱል አድሓ) ውጪ፡ ሙስሊሞች ሌላ ዒድ የላቸውም፡፡ የአላህ መልክተኛ ከደነገጉት ውጪ አዲስ ስርአትን መደንገግ በሃይማኖቱ ላይ መጨመር ነው፡፡ ይህ ደግሞ ቢድዐ ይባላል፡፡ የሸዋል ወር 8ኛው ቀን የሸዋል ፆም መፍቻ ዒድ ቢሆን ኖሮ፡ በዒድ ቀን መፆም ሐራም ነውና በዚህ ቀን አትፁሙ የሚል ትእዛዝ በሐዲሥ በሰፈረ ነበር፡፡ ግን የለም፡፡
2ኛ/ የሸዋል መጀመሪያ ቀን ዒዱል ፊጥር መሆኑ የታወቀ ነው፡፡ ዒድ ደግሞ የመደሰቻ፣ የመብያና የማብያ፣ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት መለዋወጫ ቀን ነው፡፡ ግን በመጀመሪያው ቀን ብቻ ነው መብላትና ማብላት፣ መዘየርና መደሰት የሚቻለው ያለው ማነው? የሸዋልን ሁለተኛና ሶስተኛ ቀናትስ መብላትና ማብላት፣ መዘያየር አይቻልም? ይቻላል፡፡ ስለዚህ ከላይ የቀረበው ምክንያት አጥጋቢ አይደለም፡፡
3ኛ/ የሸዋል ስድስት ቀናት ጾም በመጀመሪያዎቹ የሸዋል ቀናቶች ላይ ብቻ የተገደበ አይደለም፡፡ ሸዋል ሙሉ አንድ ወር 29/30 ነው፡፡ ስለዚህ ከወሩ ውስጥ የሚመቸውን ቀን መርጦ በማከታተልም ሆነ በማፈራረቅ ሸዋልን መጾም ይቻላል፡፡ እናም የደስታውን ቀን ማርዘም የሚፈልግ ከዒዱል-ፊጥር በኋላ ያለውንም ቀን መጠቀም ይቻላል፡፡ በቀሩት ቀናት ደግሞ ሸዋልን መጀመር ይቻላል፡፡
4ኛ/ ከዒዱል-ፊጥር ማግስት ጀምሮ ያሉትን ተከታታይ ስድስት ቀናት የጾመ ቤተሰብ በቀጣዩ ቀን በመብላትና ቀኑን እንደ ዒድ ቆጥሮ ሲያሳልፈው፡ ከመሐከላቸው አንድ ሰው ጾሙን ባለመጨረሱ (ቀዷእ ቢኖርበት ወይም ዘግይቶ ቢጀምር) እነሱ የሚበሉበትን ቀን ቢጾመው የቤተሰቡ አካላት ይቃወሙታልን? በዒድ ቀን እንዴት ትበላለህ ይሉታልን? አዎ! ከሆነ ምላሹ፡ ሰዎቹ ቀኑን ዒድ አድርገው ይዘውታል ማለት ነው፡፡ ይህ ደግሞ በዲነል-ኢስላም ላይ የተጨመረ ፈጠራ ‹‹ቢድዓህ›› ይባላል፡፡ አላህና መልክተኛው ከዒዱል-ፊጥር እና ከዒዱል አድሓ ውጪ የበዓል ቀን አልደነገጉልንም፡፡ የሸዋል ዒድ የሚባለው መሰረት የለውም እና እንደ-ዒድ አድርገው የሚይዙ ሰዎችን ቢድዓ መሆኑን ማስተማርና ማስገንዘብ ይጠበቅብናል፡፡
4. ሌላው ሊታወቅ የሚገባው ነገር ቢኖር፡- ከዒዱል ፊጥር ማግስት ጀምሮ በተከታታይ የሸዋልን ስድስት ቀናት የጾመ ሰው በቀጣዩ ቀን መብላት መጠጣት አይችልም ማለት አይደለም፡፡ ሰውየው ጾሙን እስካጠናቀቀ ድረስ መብላት መጠጣት ይችላል፡፡ ዋናው ነገር በቀኑ ላይ ሲበላም ሆነ ሲጠጣ ቀኑን ዒድ ነው ብሎ እንዳይመለከተውና እንደ-ዒድ አድርጎ እንዳይዘው ነው፡፡ የዒዱል-ፊጥር ቀንንም በአግባቡ ሊያከብረው ይገባል፡፡ ወላሁ አዕለም፡፡
Click and Like ➤➤
https://www.facebook.com/Ustaz.Abuhyder
Join ➤➤
www.tg-me.com/abuhyder
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
አሏህ የሚለው የአሏህ ስም አስደናቂ ትንታኔ በኡስታዝ አቡ ሐይደር
https://youtu.be/Wfjcvm9bDbY
https://youtu.be/Wfjcvm9bDbY
2024/09/28 11:17:13
Back to Top
HTML Embed Code: