Telegram Web Link
Audio
📚አዲስ ትምሕርት 📚 ሸህሩ ረመዷን🌙
"የረመዷን ወር ክብር" ክፍል 1

🎙 አዘጋጅ⇊
በኡስታዝ አቡ ሀይደር

Mp3 ዳውሎድ ለማድረግ
https://bit.ly/3tWT8Wo

Join ➤➤ www.tg-me.com/abuhyder
Click and Like ➤➤ https://www.facebook.com/Ustaz.Abuhyder
📚አዲስ ትምሕርት 📚
"ኪታብ ኡሱሉል_ኢማን" ክፍል 16

🎙 አዘጋጅ⇊
በኡስታዝ አቡ ሀይደር

Mp3 ዳውሎድ ለማድረግ
https://bit.ly/31Ingc7

Join ➤➤ www.tg-me.com/abuhyder
Click and Like ➤➤ https://www.facebook.com/Ustaz.Abuhyder
📚አዲስ ትምሕርት 📚
"ኪታብ ኡሱሉል_ኢማን" ክፍል 17

🎙 አዘጋጅ⇊
በኡስታዝ አቡ ሀይደር

Mp3 ዳውሎድ ለማድረግ
https://bit.ly/2QUOgTy

Join ➤➤ www.tg-me.com/abuhyder
Click and Like ➤➤ https://www.facebook.com/Ustaz.Abuhyder
📚አዲስ ትምሕርት 📚
"ኪታብ ኡሱሉል_ኢማን" ክፍል 18

🎙 አዘጋጅ⇊
በኡስታዝ አቡ ሀይደር

Mp3 ዳውሎድ ለማድረግ
https://bit.ly/3cKAZp6

Join ➤➤ www.tg-me.com/abuhyder
Click and Like ➤➤ https://www.facebook.com/Ustaz.Abuhyder
ሰኞን መፆም ይቻላልን?

ነገ ዕለተ ሰኞ የሻዕባን 30ኛው ቀን፣ የውሙ ሸክ "የጥርጣሬ ቀን" በመባል ይታወቃል። የረመዷንን ቀዷ ያልጨረሰ ሰው ወይም ሰኞና ሐሙስን መፆም ያስለመደ ሰው ነገን መፆም ቢፈልግ መፆም ይችላል።

لقول النبي صلى الله عليه وسلم: (لا تَقَدَّمُوا رَمَضَانَ بِصَوْمِ يَوْمٍ وَلا يَوْمَيْنِ إِلا رَجُلٌ كَانَ يَصُومُ صَوْمًا فَلْيَصُمْهُ). رواه البخاري (1914) ومسلم (1082)

ነቢዩ ሙሐመድ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ይላሉ:–

"ከዛ በፊት ይፆም ለነበረ ሰው ካልሆነ በቀር: ረመዷንን በአንድ ወይም በሁለት ቀን ቀደም ብላችሁ በፆም አትጀምሩት" (ቡኻሪና ሙስሊም)

ኢማሙ ነወዊይ "አል መጅሙዕ 6/399"

ሸይኽ ሷሊሕ አል ሙነጂድ "https://islamqa.info/ar/answers/26860/%D9%85%D8%A7-%D8%AD%D9%83%D9%85-%D8%B5%D9%8A%D8%A7%D9%85-%D9%8A%D9%88%D9%85-%D8%A7%D9%84%D8%B4%D9%83-%D8%A8%D9%86%D9%8A%D8%A9-%D8%A7%D9%84%D9%82%D8%B6%D8%A7%D8%A1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በረመዷን ወር በሐላባ፣ በሀድያና በከንባታ የሚገኙ ምስኪኖችን ለማስፈጠርና ወሩን ደስተኛ ኾነው እንዲያሳልፉ በኸይር ሥራ መተባበር የምትፈልጉ ሁሉ በነዚህ አካውንት የነየታችሁትን ያህል ማስገባት ትችላላችሁ!

SADIK MOHAMMED AHMED
COMMERCIAL BANK OF ETHIOPIA
1000317507589
0911 10 32 31

SADIK MOHAMMED AHMED
0871170135101
ወጋገን ባንክ
ስልክ 0911103231

SDIK MOHAMMED AHMED
1011300008645
ኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ
0911103231

ከነዚህ ውጭ በሌላ አካውንት እንዳታስገቡ!
የኡስታዝ አቡ ሀይደር ትምህርቶች ስብስብ
Voice message
📚አዲስ ትምሕርት 📚
"ኪታብ ኡሱሉል_ኢማን" ክፍል 19

🎙 አዘጋጅ⇊
በኡስታዝ አቡ ሀይደር

Mp3 ዳውሎድ ለማድረግ


Join ➤➤ www.tg-me.com/abuhyder
Click and Like ➤➤ https://www.facebook.com/Ustaz.Abuhyder
የኡስታዝ አቡ ሀይደር ትምህርቶች ስብስብ
Voice message
Audio
📚አዲስ ትምሕርት
"ኪታብ ኡሱሉል_ኢማን" ክፍል 20

🎙 አዘጋጅ⇊
በኡስታዝ አቡ ሀይደር

Mp3 ዳውሎድ ለማድረግ


Join ➤➤ www.tg-me.com/abuhyder
Click and Like ➤➤ https://www.facebook.com/Ustaz.Abuhyder
እንኳን ለ 1442ኛው የረመዷን ወር ፆም አላህ በሰላምና በጤና አደረሳችሁ!!

ጌታ አላህ ወሩን የተባረከ፣ የዒባዳ ወቅት ያድርግላችሁ። በተለይ በተለይ ዱዓእ ላይ እንበርታ። በኡምማው ላይ ክፋትና ተንኮልን ያሰቡ ጠላቶች: በራሳቸው ላይ እንዲገለበጥ አላህን አጥብቀን እንለምነው።

ረመዷን ሙባረክ
ለረመን ሰይጣናት ከታሰሩ ሰዎች ለምን አልሰለሙም?

በአቡ ሀይደር

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው
ክብርና ምስጋና ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ የተገባ ይሁን (አል-ፋቲሓ 2)፡፡ የአላህ ሰላምና ውዳሴ የሰው ዘር ታላቅ መሪ ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ (አል-አሕዛብ 56) ለመላው የአላህ መልክተኞች (አል-ሷፍፋት 181) የሐቅንም መንገድ በተከተለ ሁሉ ላይ ይሁን (ጣሀ 47)፡፡

አንዱ ክርስቲያን ነው ይህን ጥያቄ ያቀረበው፡፡ እናንተ ሙስሊሞች እንደምትሉት በረመዷን ወር ሰይጣናት የሚታሰሩ ከሆነ፡ አሁን የሚያሳስተን የለምና፡ ለምን እኛ ክርስቲያኖች ሙስሊም አልሆንም ታዲያ? የሚል፡፡ ለዚህ ጥያቄም መጠነኛ ምላሹ እንዲህ ይቀርባል፡-

ጥቅላዊ ምላሽ፡-

ወገናችን! ሰዎችን ኹሉ ያከፈረው (ከሀዲ ያደረገው) ሸይጧን ነው ማን አለህ ቀድሞውኑ? እንደዛ ተብሎ ቢሆን ኖሮ፡ በታሰረ ጊዜ የከፈሩት በጠቅላላ ለምን ተመልሰው አልሰለሙም? የሚል ጤናማ ጥያቄ ማቅረቡ ተገቢ ይኾን ነበር፡፡ ግን ባልተባለ ነገር ላይ ቆሞ ጥያቄ ማቅረብ ትልቅ የአስተሳሰብ መዛባት ነው፡፡ ሸይጧን ለሰዎች ክህደትና አመጽ ጎትጓች በመሆኑ፡ የጥፋት ሰበብ ተደርጎ ይወሰዳል እንጂ፡ በሰዎች ልብ ላይ ተሹሞ፡ በልባቸውና በእምነት መካከል ጣልቃ በመግባት እንዳያምኑ ይጋርዳል አልተባለም፡፡ ይህን የማድረግ ስልጣንም አልተሰጠውም፡፡ እሱ ወደ ኃጢአት ይጣራል እንጂ፡ ኃጢአቱን የሚፈጽመው ሰውየው እራሱ ነው፡፡ ስለሆነም ስለ ሥራው ይጠየቃል፡፡ አንተም በሸይጧን መታሰር ሰበብ እኔ ለምን አልሰለምኩም ታዲያ? ላልከው፡ እውን ለመስለምና አላህን ብቻ ለማምለክ እራስህን አዘጋጅተህ ነበርን? ከሸይጧን የከፋውን ጠላትህንስ (ነፍሲያህን) መከተል አቁመህ ነበርን? በማለት ልንጠይቅህ እንወዳለን፡፡ እስኪ አንተም ውስጥህን መርምረውና የዚያኔ መልሱን ታገኘዋለህ፡፡

ዝርዝር ምላሽ፡-

1ኛ/ ከሁሉ በፊት ሊታወቅ የሚገባው ጉዳይ ቢኖር፡- ለማመንም ሆነ ለመካድ ሰበቡ ሰውየው እራሱ መሆኑን ነው፡፡ በእምነትና በክህደት ጉዳይ ላይ አንዱን በመምረጥ ቁርጥ ውሳኔ ለማድረግ የኛ ፈቃድ ሚናውን ይጫወታል፡፡ ሸይጣን ይህንን ውሳኔአችንን ለማስቀየር ወይንም ለመቀልበስ ምንም ስልጣን አልተሰጠውም፡፡ የሱ ድርሻው መጎትጎትና በኃጢአት ባሕር ላይ ዋኝተን እንድንቀር፡ በተውበት (ንሰሀ) ወደ አላህ መንገድ እንዳንመለስ፡ መጥፎውን ጥሩ በማስመሰል የማታለያ መንገዶችን መጠቀም ነው እንጂ፡ በፍጹም ሰው ከልቡ ወስኖ ለመስራት ያቀደውን ነገር (ጥሩም ሆነ መጥፎ) ለማገድና ለመቀየር የሚያስችል ስልጣን አልተሰጠውም! የለውምም፡፡

ያ ቢሆን ኖሮ፡ ስለኛ ኃጢአት የሚጠየቀው እሱ በኾነ ነበር፡፡ ስለዚህ አንተም ሙስሊም ያልኾንከው በተሰጠህ ነጻ-ፈቃድ የአላህን መንገድ ለመከተል ባለመምረጥህ ሰበብ እንጂ፡ ባንተ ፍላጎትና ፈቃድ ላይ ሸይጧን ተሸሞብህ ከልክሎህ አይደለም፡፡ ያ በመኾኑም የሸይጧን መታሰርም ሆነ መፈታት ባንተ ውሳኔ ላይ ምንም የሚያመጣው ለውጥ የለም፡፡ እሱ ከእውነት መንገድ ሰዎችን ለማገድ ከመጎትጎትና ወደ ጥፋት መንገድ ከመጥራት ውጭ ሌላ አቅም አልተሰጠውምና፡፡ የአላህ ቃል በትንሳኤው ዕለት (የውሙል ቂያም) በሸይጧንና በተከታዮቹ መካከል ስለሚደረገው የቃላት ምልልስ እንዲህ ይነግረናል፡-

" وَقَالَ الشَّيْطَانُ لَمَّا قُضِيَ الْأَمْرُ إِنَّ اللَّهَ وَعَدَكُمْ وَعْدَ الْحَقِّ وَوَعَدْتُكُمْ فَأَخْلَفْتُكُمْ وَمَا كَانَ لِيَ عَلَيْكُمْ مِنْ سُلْطَانٍ إِلَّا أَنْ دَعَوْتُكُمْ فَاسْتَجَبْتُمْ لِي فَلَا تَلُومُونِي وَلُومُوا أَنْفُسَكُمْ مَا أَنَا بِمُصْرِخِكُمْ وَمَا أَنْتُمْ بِمُصْرِخِيَّ إِنِّي كَفَرْتُ بِمَا أَشْرَكْتُمُونِ مِنْ قَبْلُ إِنَّ الظَّالِمِينَ لَهُمْ عَذَابٌ أَلِيمٌ " سورة إبراهيم 22
"ነገሩም በተፈጸመ ጊዜ፣ ሰይጣን ይላቸዋል፦ አላህ እውነተኛውን ቃል ኪዳን ገባላችሁ፤ ቃል ኪዳንም ገባሁላችሁ፤ አፈረስኩባችሁም፣ ለኔም በናንተ ላይ ምንም ሥልጣን አልነበረኝም ግን ጠራኋችሁ፤ ለኔም ታዘዛችሁ ስለዚህ አትውቀሱኝ፤ ነፍሶቻችሁንም ውቀሱ እኔ የምረዳችሁ አይደለሁም፤ እናንተም የምትረዱኝ አይደላችሁም፤ እኔ ከአሁን በፊት ለአላህ ተጋሪ በአደረጋችሁት ነገር ካድኩ፤ በዳዮቹ ለነርሱ በእርግጥ አሳማሚ ቅጣት አልላቸው።" (ሱረቱ ኢብራሂም 14፡22)፡፡

ይህ አንቀጽ የሚያስረዳው፡- አላህ በባሮቹ መካከል ፍትሐዊ ዳኝነትን በመዳኘት፡ የጀነቱም ወደ ጀነት፣ የጀሀነሙም ወደ ጀሀነም እንዲገባ ፍርድንና ውሳኔን ባስተላለፈ ወቅት፡ ሸይጧንም ለከሀዲያን፡- አላህ መቀስቀስና ከሞት መነሳት፡ ከዛም በእኔ ዘንድ ቆማችሁ መዳኘትና፡ ለሥራችሁ ተገቢ የኾነን ክፍያ እከፍላችኋለሁ በማለት፡ በነቢያቱ አንደበትና በመለኮታዊ መጽሐፍቱ አማካኝነት እውነተኛ ቃል ኪዳንን ገብቶላችሁ ነበር፡፡ እኔ ደግሞ፡ ሞቶ መቀስቀስ የሚባል ነገር የለም፡፡ ጀነት እና ጀሀነም የሚባለውን ዓለምም ማንም ሄዶ ያየው የለም፡ ስለዚህ በዚህቹ ምድራዊ ህይወታችሁ እንዳሻችሁ ሁኑ፡ ምንም አትሆኑም አይዟችሁ! በማለት የሀሰት ቃልን ገብቼላችሁ አፈረስኩ፡፡ ቢሆንም እናንተ እኔን መውቀስ አትችሉም!፡፡ ምክንያቱም እኔ ስጠራችሁ እሺ ብላችሁ የታዘዛችሁኝ እናንተው ናችሁ እንጂ፡ እኔ እናንተን ለማስገደድ ስልጣን አልነበረኝምና፡፡ ያ በመሆኑም የገዛ ነፍሳችሁን ውቀሱ እንጂ፡ እኔን አትውቀሱ! አሁን እኔ እናንተን የምረዳችሁ፡ ወይም እናንተ እኔን የምትረዱ አይደላችሁምና፡ በምድራዊ ህይወታችሁ ከአላህ ሌላ በማምለክ ባጋራችሁበት ነገር ሁሉ ክጃለሁ አላውቃችሁም! እንደሚላቸው ነው፡፡

እኛም የአላህን ቃል ተከትለን የምንለው፡- ሰዎች ኢስላምን እንዳይቀበሉ ሸይጧን ጉትጎታ ከማቅረብ ውጭ ሌላ ሚና የለውም፡፡ ኃይሉን ተጠቅሞ ማስቆምም አይችልም ነው፡፡ ደግሞም የሸይጧን ተንኮሉ ደካማ ነውና፡ በአላህ ኃይልና እገዛ ኃይሉንና ተንኮሉን መና ማስቀረት ይቻላል፡፡ የአላህ ቃል እንዲህ ይላል፡-

" الَّذِينَ آمَنُوا يُقَاتِلُونَ فِي سَبِيلِ اللَّهِ وَالَّذِينَ كَفَرُوا يُقَاتِلُونَ فِي سَبِيلِ الطَّاغُوتِ فَقَاتِلُوا أَوْلِيَاءَ الشَّيْطَانِ إِنَّ كَيْدَ الشَّيْطَانِ كَانَ ضَعِيفًا " سورة النساء 76
"እነዚያ ያመኑት ሰዎች፣ በአላህ መንገድ ይጋደላሉ፤ እነዛ የካዱትም በጣዖት መንገድ ይጋደላሉ፤ የሰይጣንንም ጭፍሮች ተጋደሉ። የሰይጣን ተንኮል ደካማ ነውና።" (ሱረቱ-ኒሳእ 4፡76)፡፡

2ኛ/ ሰው ነጻ ፈቃድ ያለው ፍጡር ነው፡፡ እንደ ሮቦት በተሞላው ነገር ብቻ የሚንቀሳቀስ ግኡዝ ፍጥረት አይደለም፡፡ ነጻ ፈቃድም ስላለው ከአምላኩ ዘንድ፡- ይህንን አድርግ! ይህንን ደግሞ አትቅረብ! የሚል መለኮታዊ ትእዛዝን በኃላፊነት ተቀብሏል፡፡ በኃላፊቱም ልክ፡ ነገ በጌታው ዘንድ ይጠየቃል፡፡ ግዳጁን በአግባቡ ተወጥቶ እንደኾን የጌታውን እዝነት ጀነትን ይጎናጸፋል፡፡ ግዳጁን ችላ ብሎ የሸይጧንን መስመር ተከትሎ እንደኾን የጌታውን የቁጣው መገለጫ የኾነውን ጀሀነም እሳትን ይገባል፡፡
እንግዲያውስ ሸይጧን በሰው ነጻ ፈቃድ ላይ ጣልቃ በመግባት፡ ሰዎችን ከመልካም ሥራ በማገድ እንቅፋት መሆን ከቻለ፡ የኛ ነጻ ፈቃድ ትርጉሙ ምኑ ላይ ነው? አንድ አባት በጠዋቱ ማልዶ ይነሳና ልጁን፡- ከሰአት ለምሳ ቤት እስክመለስ ድረስ ከገበያ ወጥተህ እነዚህን ነገራት ገዝተህ ጠብቀኝ! በማለት ትእዛዝ ይሰጠውና፡ ልጁን ከበሩ ማገር ጋር እንዳይንቀሳቀስ ጥፍር አድርጎ አስሮት ወደ ስራው ይኼዳል፡፡ ይህ አባት ከሰዓት ላይ ለምሳ ወደቤቱ ሲመለስ፡ ልጁን እዛው የታሰረበት በሩ ላይ ያገኘውና፡ የላክሁህን እቃ ለምን አላመጣህም? በማለት ይቀጣዋል፡፡ አሁን የዚህ አባት እርምጃ ትክክለኛ ነበር! ብሎ የሚያስብ ሰው ይኖራልን? በፍፁም የለም! ከተባለ ደግሞ፡- እንግዲያውስ አባት ለልጁ ከሚያዝነው በላይ፡ ለባሮቹ የሚራራው አምላክስ፡ የሱን ትእዛዛት እንዳናከብር ሰይጣን በኃይሉ እንቅፋት ሲሆንብን፡ እያየና እየሰማ በዝምታ በማለፍ፡ ከዚያም የቂያም ቀን፡ ለምን ትእዛዜን አላከበራችሁም በማለት ይቀጣናል ብሎ ማሰብስ እንዴት ይቻላል?

ለምን ሰው የገዛ ነፍሱን ድክመት በሸይጧን ጉትጎታ ያሳብባል? አላህም እኮ ነጻ ፈቃድ የሰጠን፡ አመስጋኝ ሆነን የእምነትን መንገድ እንድንከተል፡ ወይንም ከሀዲ ሆነን የጥመትን መንገድ በመከተል በፈቃዳችን እንድንወስን ነው፡፡ የአላህ ቃል ሲናገር እንዲህ ይላል፡-

" إِنَّا خَلَقْنَا الْإِنْسَانَ مِنْ نُطْفَةٍ أَمْشَاجٍ نَبْتَلِيهِ فَجَعَلْنَاهُ سَمِيعًا بَصِيرًا (2) إِنَّا هَدَيْنَاهُ السَّبِيلَ إِمَّا شَاكِرًا وَإِمَّا كَفُورًا " سورة الإنسان 3-2
"እኛ ሰዉን፥ (በሕግ ግዳጅ) የምንሞክረዉ ስንሆን፥ ቅልቅሎች ከሆኑ የፍትወት ጠብታ ፈጠርነዉ፤ ሰሚ ተመልካችም አደረግነዉ። እኛ፥ ወይ አመስጋኝ ወይም ከሐዲ ሲሆን መንገዱን መራነዉ፤ (ገለጽንለት)።" (ሱረቱል ኢንሳን 76፡2-3)፡፡

3ኛ/ ሌላው ወገናችን ያልተረዳው ነጥብ፡ ሸይጧናት ይታሰራሉ ሲባል፡ ሁሉንም አለመሆኑን ነው፡፡ በነቢያዊ ትምሕርቱ ላይ እንደተብራራው፡ እነዚህ በረመዷን ወር የሚታሰሩት ሸይጧናት እጅግ አመጸኞቹን አስቸጋሪዎቹን እንደሆነ ነው፡፡ ቀጣዩ ሐዲሥም ይህን እውነት እንዲህ ይገልጸዋል፡-

عن أبي هريرة رضي الله عنه قال : قال رسول الله صلى الله عليه وسلم: ( إِذَا كَانَ أَوَّلُ لَيْلَةٍ من شَهْرِ رَمَضَانَ صُفِّدَتِ الشَّيَاطِينُ وَمَرَدَةُ الْجِنِّ ، وَغُلِّقَتْ أَبْوَابُ النَّارِ فلم يُفْتَحْ منها بَابٌ ، وَفُتِّحَتْ أَبْوَابُ الْجَنَّةِ فلم يُغْلَقْ منها بَابٌ ...) الحديث ، رواه الترمذي (682) ، وابن ماجه (1642) ، وحسَّنه الألباني في " صحيح الجامع " (759).
ከአቢ ሁረይራህ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- "የረመዷን ወር የመጀመሪያው ለሊት ሲገባ፡ ሸይጧናትና አመጸኛ ጂንኒዎች ይታሰራሉ፡፡ የጀሀነም በሮች አንድም ሳይቀር ይከረቸማሉ፡፡ የጀነት በሮች አንድም ሳይቀር ይከፈታሉ…" (ቲርሚዚይ 682፣ ኢብኑ ማጀህ 1642፣ አልባኒይ ሶሒሑል ጃሚዕ 759)፡፡)

ከዚህ ሐዲሥ በመነሳት፡ በረመዷን የሚታሰሩት፡ ለሰዎች አስቸጋሪና አመጸኛ የሆኑ ሸይጧናት መሆናቸውን መረዳት እንችላለን፡፡ አቅመ ደካማዎቹና ሽሜዎቹ ደግሞ የጉትጎታ ሥራቸውን ይቀጥላሉ ማለት ነው፡፡ ወላሁ አዕለም፡፡

4ኛ/ በተጨማሪም ይህ ወገናችን የሳተው ነገር፡ ሰዎቹን ከአላህ መንገድ ለማደናቀፍ ያላሰለሰ ጥረት የሚያደርገው ከጂንኒ ወገን የኾነው ሸይጧንን ብቻ አድርጎ መሳሉ ነው፡፡ የገዛ ነፍሲያችንም (ስሜት) እጅግ አደገኛ ጠላት ነው፡፡ ሰው የሸይጧንን ጉትጎታ ማሸነፍ የሚችለው፡ በነፍሲያው ላይ ድልን ከተቀዳጀ በኋላ ነው፡፡ ነፍሲያችን ትእዛዝን አትወድም፡፡ ስሜትንና ዝንባሌን እንድንከተል ትመክረናለች፡፡ ከአላህ መንገድና እሱን ከማምለክ ታዘናጋናለች፡፡ ስለዚህ የሸይጧን ጉትጎታ ብቻ ሳይሆን የገዛ ነፍሲያችንም ከኛው ጋር ትግል ውስጥ መሆኗን ማወቅ አለብህ፡፡ አንተንም ለመስለም የሚከለክልህ ይህ የነፍሲያህ እምቢተኝነት መሆኑን አስተውለሀልን?

5ኛ/ በመጨረሻም ለዚህ ወገናችን የምናስተላልፈው መልእክት፡ ሂዳያ (ቅኑን ጎዳና ማግኘት) የአላህ ተውፊቅ (መልካሙን ዕድል እንድታገኝ መግጠም) እንጂ፡ የገዛ ሥራችን ውጤት አይደለም፡፡ እኛ መሆን የምንችለው ነገር ቢኖር ሰበብ መሆን ብቻ ነው፡፡ ውጤቱ ግን ከአላህ ዘንድ ብቻ የሚሰጥ ነው፡፡ ስለዚህ ዕድሜህን ሙሉ ከአላህ መንገድ ወጥተህ፡ የነፍሲያህና የሸይጧን መጫወቻ ለመሆን ፈቅደህ ስታበቃ፡ ሸይጧን ነው ከመንገድ ያስወጣኝ ማለት አያዋጣም፡፡ ቅድሚያ ነፍሲያህንና ሸይጧንን ታግለህ በአላህ መንገድ ለመታገል ከወሰንክ አላህም ቅኑን ጎዳና እንደሚመራህ በመግለጽ ቃልን ገብቷልና፡ አንተም ለማመን እራስህን አዘጋጅ፡ ሸይጧን ስለታሰረ የሚሰልም፡ ስለተፈታ ደግሞ የሚክድ ሰው የለምና፡፡ የአላህ ቃል እንዲህ ይላል፡-

" وَالَّذِينَ جَاهَدُوا فِينَا لَنَهْدِيَنَّهُمْ سُبُلَنَا وَإِنَّ اللَّهَ لَمَعَ الْمُحْسِنِينَ " سورة العنكبوت 69
"እነዚያም በኛ መንገድ የታገሉ መንገዳችንን በእርግጥ እንመራቸዋለን፤ አላህም በእርግጥ ክበጎ ሠሪዎች ጋር ነው።" (ሱረቱል ዐንከቡት 29፡69)፡፡

Click and Like ➤➤
https://www.facebook.com/Ustaz.Abuhyder
2024/11/16 11:19:15
Back to Top
HTML Embed Code: