Telegram Web Link
ንግግሩ የበዛ ሰው ስህተቱ ይበዛል መሣሣቱ የበዛ ሰው ደግሞ
ሐያኡ ያንሣል ሐያኡ ያነሰም
ለአሏህ ያለው ፍራቻ ይቀንሳል
ለአሏህ ፍራቻው የቀነሠ ደግሞ
ቀልቡ ሞቷል ማለት ነው!

ኡመር ረዲየሏሁ ዐንሁ!

#መልካም_ኸሚስ😍
💚💚💚💚💚🌹🌹🌷🌹🌹
💚❤️ የኸሚስ ጀባታ

💚❤️አንዳንድ ሶሃቦች የረሱላችንን ፊት ሲመለከቱ
በድጋሚ የራሳቸው ፊት ይፋጠጡ ነበር
🎈ኮለል ያለው ባህር የማይደፈርሰው
🎈 አባቱን አደምን ከስደት መለሰው ተብሎ የለ

💚❤️ሰይዲና ኢብን አባስ ረሱልን ሲወስፉ ደግሞ እንዲህ ይላሉ
🎈 ما رأيت رسول الله مع الشمس والقمر إلا وكان أنور من الشمس وأضوء من القمر
🎈ረሱልን ከፀሃይ እና ጨረቃ ጋር አላየኋቸውም
🎈ኑራቸው ከፀሃይ ልቆ የበራ
🎈ወገግታቸው ከጨረቃ የበለጠ ቢሆኑ እንጂ
🎈ያ ቀመረል መካ ሲራጄ ሙኒሬ
🎈 ሲሩል ካኢናቲ ሚስጥረ ብዕሬ
💚❤️ ሰዎች ሰይድ በራእ ዘንድ መጥተው፡ በራእ ሆይ የረሱል ፊት እንዴት ዐይነት ነበር ! ልክ እንደ ሰይፍ አብረቅራቂ ነበርን ብለው ሲጠይቋቸውሳ?
🎈 لا بل مثل القمر 🌘
አይደለም ፊታቸው እንደ ጨረቃ ቦግ ያለ ነበር

💚❤️ጀማልሁ ሸንተረር ጀማልሁ ተራራ
💚❤️ወስፍሁ አላልቅ አለኝ ምነው ኸይረል ወራ

🗯ሐቢቤዋ የሰይዲና ዩሱፍን መልከመልካምነት ለሶሃቦች ሲገልጡላቸው
🎈أعطي يوسف شطر الحسن
🎈ዪሱፍ የውበትን ግማሽ ተሰጥቷል

💚❤️የገባው ገብቶታል ያልገባው የሰይድ ዩሱፍ ፊት አምሮታል
💚❤️ውበት ማለት እራሳቸው ሐቢብ ናቸው፡
❤️💚ዩሱፍም የሐቢብ ግማሽ ደረሳቸው
🎈በሰይዲና ዩሱፍ ቁንጅና ወይዛዝርቶች እጃቸውን በስለት ሸረከቱ
💚❤️ በረሱል ውበት የዘይኑን ለቅሶ ልድረስ ያለች ሚስኪን እናት ጉበቷ ፈነዳ
💚❤️ አቅል የሌላት ግመል ያን ውበት ካላየው ሳር ቅጠሉ ይቅርብኝ ቀለብ በቃኝ ብላ እራሷን በረሃብ ገደለች
💚❤️ዘላኑ አህያ አደብ ገዛሁ ነብዬ ብሎ እሽክር ሁኖ ኖሮ ሲሞቱበት ቅስሙ ተሰባብሮ በውበቱ የናፍቆት ሃራራ እራሱን ገደል ውስጥ ገፍትሮ ተሰቃይቶ ሞተ

🔆 ፀሐይም አለችው
💚❤️እኔ አንተ ላይ ጨረሬን ልኬ ጥላህን ላነጥፍ አልችልምና አንተው ብርሃንህን ላክልኝ!

💚❤️ጎንትሎ ጀምሎ ኸላልቆት ረባሁ
💚❤️ሙሂብ ሊያሳብድ ነው ኸረ ምን ጉድነሁ


🙏ሸጋ ኸሚስ
صلو عليه💚
@abubekersidik
Forwarded from Warida islamic tube
#ጤነኞች__ሆይ____!!
#አልሀምዱ_ሊላህ_ልንል_አይገባምን??
<========================>
ስንቶች አሉ በየቤታቸው የአልጋ ቁራኛ ሆነው አመታትን ያስቆጠሩ፤
ስንቶች አሉ ዛሬ ጤነኛ ነገ በሽተኛ እየሆኑ አብረው ከመጓዝ ወደ ኋላ የቀሩ፤
ስንቶች አሉ ለሰው ለማስረዳት ከሚከብድ ህመም ውስጥ ሆነው ብቻቸውን የሚያንጎራጉሩ፤
እና ለአንተ ለጤነኛው አልሀምዱ ሊላህ ማለት ያንስሀልን!!??
<============================>

#የጤናህ_ፀጋ__!!
<=============>
የጤንነት ፀጋ ጥቅሙ እሚታወቀው፡
ህመምህ በርትቶ ውስጥህን ሲጨንቀው፡
የበሽታህን ጥግ ሰው ሲል አልረዳህ ፡
ሁሉም በሀሳቡ በግምት ሲነዳህ፡
የሚመስለኝ ብሎ ሀሳብ ሲመነዳህ፡
<=====================>
መላ ቅጡ ጠፍቶህ ሲበረታ ዕህታህ፡
በፅኑ ስትያዝ ሲፀና በሽታህ፡
አይንህ እንባ ቋጥሮ ዱብ ሲል ዘለላው፡
ተስፋ እየጨለመ ሲጠፋብህ መላው፡
<==========\\==========>
ወዳጂም ጓደኛ ከጎንህ ስታጣ፡
የቻለውም መጥቶ ደባብሶህ ሲወጣ፡
በህመም ስትሟቅቅ በዕሳት ስትቀጣ፡
<=====================>
የምትወደው ሁሉ ጣፋጩ ሲመርህ፡
አላምጦ መዋጡ በጣም ሲያስቸግርህ፡
አሁን ሰላም ሆነህ ፈጥነህ ስትተኛ፡
ጤና የነበርከው ሲሉህ በሽተኛ፡
<===================>
ወዳጂ ጓደኞችህ ከፊትህ ሲያለቅሱ፡
ላንተ በመጨነቅ አንዴ ሲቀመጡ ድጋሜ ሲነሱ፡
የጤንነት ፀጋ ያኔ ትዝ ይልሀል፡
ድርጊቶችህ ሁሉ ያኔ ይሰሙሀል፡
<~~~~~~~~\\~~~~~~>
ተሽሎኛል ብለህ ሀረካ ስትጀምር፡
ድጋሜ ስትተኛ ስትታመም የምር፡
ከጥፍር እስከ ፀጉርህ በሽታ ሲፍቅህ፡
ድጋሜ ሰው መሆን ጤና ሲናፍቅህ፡
<~~~~~~~~~~~~~~~~>
በህይወት እያለህ ሁሉም ሰው ሲረሳህ፡
ወዳጅ ዘመድ ሲሸሽ ሲጠፋ እሚያነሳህ፡
መናገር ስታቆም ምላስህ ሲታሰር፡
በነጋ በመሸ ህመም ስትበሰር፡
<==================>
በህመም ላይ ሆነህ፤
ሲፈራረቅብህ ክረምትና በጋ፡
ያኔ ነው ምታውቀው፤
የመኖርን ትርጉም ያብሮነትን ዋጋ፡
ያኔ ትረዳለህ፤
የሰውነትን ልክ የጤናህን ፀጋ፡
<=======\\=========>

الحمد ليلاه
Join us👉 @WaridaIslamicTube
★አስገራሚ፣የእናት፣ታሪክ★
አንዲት ባልቴት ታሪኳን እንዲህ ስትል ትተርካለች...–»………»
ሶስት 3 ወንድ ልጆች ነበሩኝ ታዲያ ሁሉም ትዳር የያዙ ነብሩ፣
★ከእለታት አንድ ቀን ከልጆቼ ቤት ማድር ፈለኩና ትልቁን ልጄን
ወደ ቤትክ መጥተክ ውሰደኝ አልኩት እሱም በጧት መጥቶ ወደ
ቤቱ ወሰደኝ አደርኩ ጧት ላይ ለሱቢሂ ሶላት ውዱ ማድረጊያ
ሚስቱ ውሃ እንድታመጣልኝ አዘዝኳት አመጣችልኝና ውዱ
አድርጌ ሰገድኩና ቀረውን ውሃ ከተኛሁበት ፍራሽ ላይ ደፋሁት
ከዛም ትንሽ ቆይታ ሻይ ይዛልኝ ስትመጣ ሌሊት ላይ ከፍራሹ
ሼንቴን መቆጣጠር አቅቶኝ እንደደፋሁትና እንድታፀዳው ጠየኳት።
ከዛም ይህን ስትሰማ የመጀመሪያው ልጄ ሚስት ንዴቷን መቋቋም አልቻለችም ብዙ ትዘልፈኝ ጀመር ይባስ ብሎም
አንሶላውን እንዳጥብና እንዳፀዳ ነገረች ድጋሜ እንዳይለመደኝም በከባዱ አስጠነቀቀችኝ እኔም ንዴቴንና ሀዘኔን
ተቋቁሜ ልጄ ይሄ አሁን ያየሽው ባህሪ የትልቅ ሰዎች ባህሪ ነው
እኔ ደግሞ እንደምታይኝ አርጂቻለው ራሴን መቋቋም አልችልም
ብዬ አልኳት ከዛም ወጥቼ ወደ መካከለኛው ልጄ ቤት ሄድኩኝ፣
★ከትልቁ ልጄ ቤት ያደረኩትን ከመካከለኛውም ልጄ ቤት ለውዱ
ማድረጊያ የተሰጠኝን ቀሪውን ውሃ ከተኛሁበት ፍራሽ ላይ
ደፋሁትና የሆነውን ለልጄ ሚስት ነገርኳት እሷም በጣም
ተናደደች ሰደበችኝ እንደ መጀመሪያዋ ሚስት እንዳደርግ አዘዘችኝ።
እኔም ያለችኝን ሁሉ ፈፅሜ ወደ መጨረሻው ትንሹ ልጄ ቤት
አመራሁኝ!!
★ከሁለቱ ልጆቼ ቤት ያደረኩትን ከመጨረሻው ልጄ ቤት አደረኩት ከዛም የመጨረሻው ልጄ ሚስት ሻይ ይዛልኝ
ስትመጣ የሆነውን ሁሉ ነገርኳት" እሷም ፈገግ እያለች አያስቡ
እናቴ አብሸሩ ይሄ እኮ በማንኛውም ሰው ላይ የሚመጣ ነገር ነው እርጅና ነው አያስቡ እኔ አፀዳዋለው አለችና ማፅዳት
ጀመረች። እኔም ንግግሯና ምግባሯ ስላስደሰተኝ የመጨረሻውን
ልጄን ሚስት እጇን ይዤ ልጄ ሆይ እኔ በእርግጥ የእጅሽን ልክ
አላቀውም ስጦታ ልገዛልሽ ፈልጌ ነው እናም በምልክት ልክሽን
አሳውቂኝ አልኳት እሷም አሳወቀችኝ ያለኝን ብር ሁሉ አውጥቼ
ወደ ወርቅ ቤት አመራሁና በያዝኩት ብር ሁሉ ለመጨረሻው
ልጄ ሚስት ወርቅ ስጦታ ገዛሁበት የገዛሁትን ስጦታ ይዤ ወዴት
መጨረሻው ልጄ ቤት አመራሁና ስደርስ የመጀመሪያው ልጄ
ሚስቱና እሱ የመካከለኛው ልጄ ሚስቱና እሱ እንዲመጡ
አዘዝኩ እነሱም መጡ ያን ያደርኩት አውቄና ለፈተና መሆኑንና
ፈተናውን ያለፈችው የመጨረሻው ልጄ ሚስት እንደሆነችና
የያዝኩት ወርቅ ሁሉ ለእሷ እንደሆነ ነግሬ አይናቸው እያየ
ለመጨረሻው ልጄ ሚስት ሰጠዃትና ከዚክ በዃላ ቀሪውን
እድሜዬን ልትካድመኝ የምትችለው እሷ ብቻ እንደሆነችና ከእሷ ጋር የለችኝን ቀሪ ዕድሜ ከመረሻው ልጄ ቤት እንዲሆን እንደምፈልግ ነገርኳቸው።
የመጀመሪያው ልጄ ሚስትና የመካከለኛው ልጄ ሚስት በሰሩት
ስራ እጅግ ሃፍረት ተሰማቸው አዘኑ
ﻫَﻞْ ﺟَﺰَﺍﺀُ ﺍﻟْﺈِﺣْﺴَﺎﻥِ ﺇِﻟَّﺎ ﺍﻟْﺈِﺣْﺴَﺎﻥُ
የበጎ ሥራ ዋጋ በጎ እንጅ ሌላ ነውን?
ሱረት አል ረህማን 55:60
በመጨረሻም_ልብ_የምትሉኝ_ከሆነ
በጎነት_ለራስ_ነው_ ﻗﺺ _ ﺍﻟﺪﻧﻴﺔ ከሚለው_የአረበኛ_ፔጅ_
በ—»★ፈርሀን_ኑር_የተተረጎመ"
ከወላጆቻችን ሀዘን"አላህ ይጠብቀን!!
/አሚን!!/
ሼር በማድረግ ያዳርሱ

@abubekersidik
@abubekersidik
Forwarded from Warida islamic tube
ስለ አባይ መገደብ #ሸህ_ሁሴን_ጅብሪል የተናገሩት ትንቢት በከፊል እነሆ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇

አባይን ሊያግድ ነው ተባለ በይፋ
ውሃው እንዳይባክን ከንቱ እንዳይደፋ
አረብ ደነገጠ ቂያማ እንደተደፋ
ያለፊት መሪዎች ነበሩ ከርፋፋ
ዝም ብለው እያዩ ምንም እንዳልጠፋ
በደሉ በዛና ረዝሞ ታጠፋ
ስምንተኛው መሪ ጀግና ነው ቀልጣፋ
ማነንም ሳይፈራ ጊዜም ሳያጠፋ
አባይን ለማገድ ፎከረ ደነፋ
ከፊቱ የሚቆም ጀግና ወንድ ጠፋ
ደግሞ ተናገረ አዋጁን በይፋ
ከተናገረው ቃል ትንሽ ልወስፋ
እናት አገራችን ቁማ ተሰልፋ
ሰዎች እየዋኙ አትጠጣም ጨልፋ
አረቦችን ፈርተህ አንገትክን አትድፋ
ግብፅ ብትፎክር ተቆጥታ አኩርፋ
ጦርነት ብትከፍት ባሩድ ቢከረፋ
እንገጥማታለን በዱላም ባካፋ
እንኳን ዘመናዊ መሳሪያ ሳይጠፋ
ሰው ላገሩ ምነው ቢደክም ቢለፋ
ቢሞትስ ምን አለ ሂወቱ ብትጠፋ
ኩራት አይደለም ወይ ለልጅ ልጆች ተስፋ
አባይም ይታገድ በአገር ውስጥ ይስፋፋ
ሌላ ጣና ይበጅ ውሃው ይንሰራፋ
ይሄነን ሲናገር ወሬ ተጧጧፈ
ህዝቡም ተደሰተ አብሮ ተሰለፈ
አንዳንድ ሰው ሲቀር ሃሳበ ወልካፋ
ነገር እንደ ጋቢ ለብሶ የሚያስፋፋ
ምን ኸይር ብትሰራ አደፍራሽ አይጠፋ
በውሆቿ ብቻ ምንም ሳትለፋ
መልሳ ሃበሻ ልትሆን ነው አንጋፋ
ኃላ ከመነደም ዋሽቶ ከማፈር
ሳያረጋግጡ ከመደናገር
ሰው እያዋረዱ ስሙን ከመስበር
ሰው እንዴት ይናቃል መልኩ ቢጠቁር
ችግር ያስከትላል አስከፊ ነገር
ህዝብ ይከፋፍላል መጥፎ ነው ላገር
የቱኛው ነው ባሪያው የትኛው ነው ሁር
የዘጠኝ ወር ልጅ ነው ሁሉም ሲፈጠር
በአላህ ስራ ገብተን አንከራከር
በዚህ የተነሳ በዚሁ ነገር
አየሁት ሱዳንን ህዝቡ ሲማረር
ብደፍራችሁ እዳ ዝም ብል ችግር
ዋሪዳው መጣና አለኝ ተናገር
እንግሊዝ ሱዳንን ከለቀቀ ሃገር
ይዘገያል እንጅ ኃላ አለ ነገር
እንግሊዞች ወጥተው ሳይውሉ ሳያድር
በሱዳን ውስጥ ውሰወጡን ጀመረ ሽብር
ለምን ይሆን ሱዳን የማይጠረጥር
እንግሊዝ ነካክቶት ምን ሊሆን አገር
አማሪካ ተብሎ ስሙ ቢቀየር
ያው እንግሊዙ አይደል ነገር የሚጭር
ሱዳን አጁ ረጥቦ ቢታይበት ኸይር
ነጮች አተኮሩ በሱዳን ሃገር
ጠይሙን ተው አርገው ዞሩ ወደ ጥቁር
የሱዳን ኗሪ ህዝብ ጠይምና ጥቁር
ጠይሙ ገዥ ነው ተገዡ ጥቁር
ጥቁሩስ ለመግዛት አያውቅም ነበረ
ከብት ያረባ ነበር ተሰማርቶ ዱር
ነጮች አተኮሩ በሱዳን አገር
ጠይሞችን ትተው ዞሩ ወደ ጥቁር
ሃብቱን ለመቀማት ዘርፈው ለመዞር
ሱዳንን ሊከፍሏት ሁለት ሶስት ሃገር
ሱዳን መላውጠፍቶ እራሱ እንዲዞር
ሱዳን ተቀየረች በአንድ ቀን ጀምበር
በሃበሻ ሲስቁ መጣ በጅ አዙር
ማነው በሃበሻ ላይ ያልሰራ ነውር
ሁሉም በሚችለው ሲታገል ነበር
እውነቱን ካወራን ስንነጋገር
ሱማሌ ሱዳን ሶስተኛ ምስር
ተንኮል ያስባሉ በሃበሻ ላይ ሸር
እንድትከፋፈል የሃበሻ ምድር
ምን በድላ ይሆን ይች ደሃ ሃገር
ለኛ የተመኙት ለነሱም አይቀር
እኛም ዱዓ አድርገናል በምንችለው ቀድር
የሃበሻ ጠላት እንዲመነጠር
አላህ ኸይሩን አይቶ ሰሚዑል በሲር
በወሬማ ቢሆን ሰው ማጭበርበር
አረብ በዓለም ላይ የለውም ወደር
ሲያሰቃይ ኑሯል ነቢን ሲያስቸግር
ሃበሻ ተንቃ ታይታ እንደ መንደር
አረቦች በሷ ላይ ይስቁ ነበር
ወንጭፌን አምጡልኝ ዲንጋ ልወርውር
በየቤቱ ዙራ የምትቆረቁር
በድፍን ሃበሻ ወሬ ምታበስር
አባይ መታገዱ መሆኑ የምር
ዳንኪራ እንዲመታ ህዝቡ እንዲጨፍር
መቸም ደስ ያለው ሰው አያውቅም ነውር
ምኑ ያስገርማል ተነስቶስ ቢበር
ወድቀህ በደስታ እንዳትሰበር
ከመሄድህ በፊት ከእውነቱ አገር
የሃበሻ ሰዎች ስሙኝ ስናገር
በአንድ ላይ ተስማምተን ስንተባበር
ክንዳችን ሲጠና ስንጠነክር
መተንፈስ ይቻላል ደፍሮ መናገር
አለም ተገረመ ከዳር እስከዳር
ወሬው ተናፈሰ ታየ እንደታምር
አረብ ሲተራመስ ሲደነጋገር
ግበፅ ውሃው ቀንሶ ጠምቶት ቆሽቱ ሲያር
ያን ጊዜ ነው አረብ ሃበሻን ሚያከብር
እውነቱን አውጥቶ ሃቅ የሚናገር
የኛ እንደሆን አባይ የሚመሰክር
ግብፅም ድምጿ ጠፋ እንዲያ ስትፎክር
መጠንቀቅ ጥሩ ነው አደጋ እንዳትፈጥር
ነቃ ብለህ ጠብቅ ከተማም ገጠር
ዝም ብለህ እንዳትሞት ሳትንፈራፈር
አይዞህ የሃገር ልጅ አይበልህ ቅር
ንግግሬም ባይጥም ስናገር ባያምር
አየሁት ውሃችን ሲሸጥ ብዙ ብር
እስኪያቅተን ድረስ ገንዘቡን መቁጠር
ያውም ተለምነን ወድቀው ጫማ ስር
ተሸጠ ነው ያልኩህ አይደለም ብድር
ይዘገያል እንጅ ታዘበኝ ቢቀር
ጅምሩ ጥሩ ነው ሃቲማው ይመር።

Join us👉 @WaridaIsamicTube
18 الكهف
الشيخ سعود الشريم
⤴️⤴️⤴️
📖 سورة الكهف
📖 ሱረቱል ከህፍ

በቃሪዕ ስኡድ ሹረይም


قال رسول الله ﷺ
'' من قرأ سورة الكهف في يوم الجمعة أضء له من النور مابين الجمعتين


قــال رسول الله ﷺ

‏أكثروا من الصلاة عليّ ليلة الجمعة و ⁧

#يــوم_الجمعة ⁩ فإن صلاتكم معروضة

عليّ حديث صحيح .. ‏ﷺ 🌿

🌹🌹🌹ﷺﷺﷺ🌹
🌹🌹🌹ﷺﷺﷺ🌹
👉 ሰይዳችንን ለማየት የፈለገ ማን ነው?

አቢሁረይራ ባስተላለፉት ሀዲድ ሰይዳችን ﷺ እንዲህ ብለዋል።
እኔን በመናሙ ማየት የፈለገ ኸሚስ ማታ ላይ ከመተኛቱ በፊት 2ረከአ
ይስገድ በየአንዳንዱ ረከአ ላይ ፋቲሀን አየተልኩርሲይ እና15ጊዜ
ሱረተል ኢኽላስ ቁልሁወሏሁ አሀድን ይቅራ.በሁለተኛውም ረከአ ልክ
እንዲሁ ያርግ ከዛም በሰላቱ መጨረሻ ላይ 1000ጊዜ አላሁመሰሊ
አላሙሀመድ ነብይል ኡሚይ ይበል.
የሚቀጥለው ሳምንት ጁመአ አይመጣም እኔን በህልሙ ያየኝ ቢሆን
እንጂ.በሁለቱ ጁመአዎች መካከል ባሉት ቀናት ማለት ነው.
ከመፋቲሁል ፈረጅ ኪታብ የተወሰደ
ሁላችንም ለመስራት እንሞክር ውዶቼ መቼም ሰይዳችንን ﷺ ለማየት
እንኳን ይሄንን ነፍሳችሁን ስጡ ብንባል መርሀባ ነው ምንለው የታወቀ
ነው.
ግን ይሄ ስራ ሚሰራው ከመሀባ ጋር ነው ምን አልባት አንድ ጊዜ
ሞክረን ካላየናቸው አይ በቃ አላየኅቸውም ብለን መተው የለብንም
በየሳምንቱ መሞከር አለብን ውዶቼ
ይሄን ሰርተህ ራሱ ባታያቸው ይሄ ስራህ ሰይዳችን ﷺ ጋ ይቀርባል
ባንተም በጣም ይደሰቱበሀል
ከዛም ከሙሂባች መዝገብ ትፃፋለህ ይሄን ሰርተን ባናያቸውም እንኳን
እሳቸውን ማስደሰታችን ከሙሂቦች መዝገብ መፃፋችን ይሄ በጣም
ትልቅ እድል ነው.
አላሁመ ወፊቅና ሩእየተ ሸሪፍ ፊልመናም ያረብ ያአላህ
አላሁመሰሊ አላሰይዲና ሙሀመዲን ሰላተን ቱመቲኡና ቢሩእየቲህ
መልካም ጁሙአ
Join us👉 @WaridaIslamicTube
ይህንን ድንቅ ታሪክ ያውቁ ኖሯል ???
┈┈•••✿❒ ❒✿•••┈┈
አላህ ( ሱ.ወ) ጅብሪል (ዐ.ሰ) ምን በፈጠረ ግዜ አሳምሮ ነበር
የፈጠረው::
600 ክንፎችን የቸረው ሲሆን የአንዱ ክንፍ
ርዝመት ከፀሐይ መውጫ እስክ ፀሐይ መግቢያ
ይደርሳል።
ጅብሪልም ይህን በተመለከተ ግዜ እንዲህ አለ ፡እንደኔ አሣምረክ
የፈጠርከው አለን ? ብሎ አላህን(ሡ.ወ)ን ጠየቀው
አላህም (ሡ.ወ) የለም አለው ።
ጅብሪልም በጣም በመደሠት 2 ረካዐ ሀረመ ለያንዳንዱ ረካዐ 20
ሺ ዐመት ፈጀበት ።
እንደጨረሠም አላህ(ሡ.ወ) ም የሚገባኝን መገዛት ተገዝተኸኛል
እንዳንተ የሚገዛኝም የለም ነገር ግን በመጨረሻው ዘመን አካባቢ
ነብይ ይመጣል እኔ ዘንድ ውድ የሆነ ሙሐመድ(ሰ.ዐ.ወ) የሚባል
፡የሡ ዑመቶች ደካሞች ወንጀለኞች ናቸው፡፡
2 ረካዐ ይሠግዳሉ በመሠላቸትም ጭምር በአጭር ደቂቃ ከብዙ
ሀሣብ ጭንቅ ጭምር ጋር ይሰግዳሉ።
ነገር ግን በልቅናዬ በክብሬ ይሁንብኝ
የነሡ ሠላት እኔ ዘንድ ተወዳጅ ነች ።
ካንተ ሠላት የነሡ
ሠላት እኔ ዘንድ ተወዳጅ የሆነችው እነሡ በኔ ትዕዛዝ ነው
የሚሰግዱት አንተ ግን በሠጠሁህ ኒዕማ ተደሥተህ በፍላጎትህ
ነው ።
ጅብሪልም ለዚህ ኢባዳቸው ምን አዘጋጀህላቸው ? ሢልው
ጀነቱል መዕዋ አለው
ጅብሪልም ለማየት ፍቃድ ጠየቀ አላህ (ሡ.ወ)ም ፈቀደለት
በሙሉ ክንፎቹ መብረር ጀመረ።
1ክንፉ ሢዘረጋ 3 ሺ ዐመት ይቆርጣል እጥፍ ሢሆን እንደዛው።
በዚህ ሁኔታ 300 ዐመት በረረ ያም ሆኖ ደከመው አረፍ ብሎ
ስጁድ አድርጎ አላህ ሆይ ግማሿን ደረስኩ ወይስ ሩቧን ወይስ
ሲሶዋን ?? ብሎ ጠየቀ
አላህ(ሠ.ወ) ም 3000 ዐመት ብትበር የሠጠሁክን ያክል ሀይል
የሠጠሁክን ያክል ክንፍ እጥፍ ብሠጥህ አሁን የበረርከውን ያክል
ብትበር የሙሐመድን (ሠ.ዐ.ወ) ዑመት የሠጠሁትን ስጦታ አንድ
አስረኛውን አትደርስም !!!! አላሁ አክበር አላህ(ሡ.ወ) ምን ያክል
ስጦታ አዘጋጀልን ለ 2 ረካዐ ሡብሀነ አላህ።ትክክለኛ ሠጋጆች
አላህ ያድርገን።
አሚን
•════••• •••════

@abubekersidik
Forwarded from Warida islamic tube
# ዳንዩ ሳኒ (አብዋ ኢማሙ)
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
አብዋ አሚሙ ወደ ሰማይ ቀጥ ብለው አያቁም አይተው
አያቁም.ከዛም አንድ ጊዜ አብዋ ሰገዱና ወደ ሰማይ መልከት ቢሉ
ጭልም አለ አሉ. ምን ጉድ ነው አሉ አብዋ አሁን ሰግደን አልነበር እንዴ
ምነው ጨለመሳ ሲሉ. እነሸህ አንቱ ቀጥ ስላልኩ እኮ ነው እስቲ
ጎንበስ በሉ አሏቸው.ከዛም ጎንበስ ያሉ ጊዜ ፀሀይቷ መጀመሪያ
እንደነበረችው ሆነች ወጣች።ለዛም ነው ሲመድኅቸው እንዲህ ነበር
ሚሉት.
የተለየ ነበር ጌታውን ሲፈራ
አንድ ቀን ቀጥ ቢል ወደ ሰማይ ጋራ
ፀሀይቱ ጠፋች ግንባሩን አክብራ። 😍
መደድ ያሸይኹል አክበር ዳንዩ ሳኒ አመደነላሁ ሚን መደዲሂም
ወስቂና ሚንሸራቢሂም ቢሲሪል አስራሪል #ፋቲሀ

Join us👉 @WaridaIslamicTube
#ሐጅና_የዑምራ_ክፍል_1 🕋
بـسـم الـلـه الـرحـمـن الـرحـيـم الحمد لله رب العالمين وصلى الله على سيدنا محمد وعلى ءاله وصحبه وسلم
قال الله سبحانه تعالى { #وأتـمـو_الـحـج_والـعـمـرة_لـلَّـه} (سورة البقرة/196)
ትርጉም፦ " ሐጅና ዑምራን ለአሏህ ብላችሁ አሟልታችሁ ስሩ።"
ቡኻሪይና ሙስሊም ከኢብኑ ዑመር ረዲየሏሁ ዐንሁ) ነቢያችን እንዲህ አሉ በማለት ዘግበዋል፦
"بني الإسلام على خمس شهادة أن لا إله إلا الله وأن محمد رسول الله، وإقام الصلاة، وإيتاء الزكاة، وحج البيت، وصوم رمضان."
ትርጉም፦እስልምና የተገነባው በአምስት ነገራቶች ነው። (እነሱም) ከአሏህ ሌላ በእውነት የሚገዙት ነገር እንደሌለ፣ ሙሐመድ የአሏህ መልእክተኛ መሆናቸውን መመስከር፣ ሶላት መስገድ፣ ዘካ መስጠት፣ ሐጅ ማድረግና፣ የረመዷንን ወር መፆም (ናቸው)።"
ታላቁ ዓሊም ዐብዱሏህ አል–ሐዳድ አል–ሐድረሚይ ተቀዳሚው ፈቂህ በመባል የሚታወቁት እንዲህ አሉ፦
"من تكلف الحج شوقا إلى بيت الله وحرصا على إقامة الفريضة إيمانه أكمل وثوابه أعظم وأجزل، لكن بشرط أن لا يضيع بسببه شيأ من الفرائض، وإلا كان ءاثما واقعا في الحرج كمن بنى قصرا وهدم مصرا".
"ካዕባን ለማየት በመናፈቅ፣ ግዴታን ለመፈፀም በመጓጓት የሐጅን ወጭ ችሎ የተጓዘ ኢማኑ የተሟላ ነው። ምንዳውም ትልቅና ብዙ ነው። ነገር ግን በዚህ ድርጊት ምክንያት ግዴታዎችን አላማጓደል መስፈርት ነው አለበለዚያ ወንጀል ላይ የወደቀ ይሆንና፤ ቤተ መንግስት ገንብቶ ከተማን እንዳወደመ ይሆናል።"
አሏህ ሶላትና ዘካት የሌላቸውን ልዩ ነገር ለሐጅ አድርጎለታል። ይኸውም ትላልቅና ትናንሽ ወንጀሎችን ያስምራል።ተወዳጁና ተናፋቂዉ ነቢይዐለይሂ ሶላቱ ወሰላም እንዲህ ይላሉ፦
"من حج فلم يرفث ولم يفسق خرج من ذنوبه كيوم ولدته أمه" رواه البخاري.
ትርጉም፦ ያለ ግብረ ስጋ ግንኙነትና ያለ ከባድ ወንጀል ሐጅ ያደረገ፤ ልክ እናቱ እንደወለደችው ቀን ከወንጀሉ ነፃ ይሆናል።ቡኻሪ ዘግበውታል።
#ሐጅ_በሚችል_ሰው_ላይ_ግዴታ_መሆኑን_ዑለማኦች በጋራ የተስማሙበት ጉዳይ ነው፡፡ለዚህም ግዴታነቱን የካደ ለእስልምና አዲስ ወይም ዑለማኦች ካሉበት ርቆ ያደገ ካልሆነ በስተቀር ከእስልምና ይወጣል። ነገር ግን ግዴታ መሆኑን እያመነ ፤ ሐጅ ማድረግ እየቻለ የተወ ወንጀለኛ ነው እንጂ አይከፍርም። በዑምራ ጉዳይ ግን ዑለማኦች ይለያያሉ። እንደ ኢማሙ አል–ሻፊዒይ ያሉ አንዳንድ ዓሊሞች ዑምራ ግዴታ ነው ሲሉ፤ አንዳንዶቹ ደግሞ ሱና ነው እንጂ ግዴታ አይደለም ብለዋል።
#ኢንሻ'_አሏህ_ክፍል ሁለት ይቀጥላል...


┏━ 💗 ━━━━ 💗━┓
@abubekersidik
┗━ 💗 ━━━━ 💓━┛
🌹️ያማረ⇨የሰመረ
🌺ማራኪ⇨አርኪ
🌺የሰከነ⇨የሰፈነ
🌺ፏፏ ⇨ያለ
🌺ደስ⇨የሚል
🌺ጁሙዓ⇨ይሁንላቹ
#መልካም_ጁመዓ

@abubekersidik
ሱረቱል ካፍ ቃሪ ራሽደ አል ፋሲይ
﷽ { የጁምዓ ቀን ሱናዎች }
1 ገላን መታጠብ
2 ሽቶ መቀባት (ለወንድ)
3 ጥርስ መፍቂያ መጠቀም
4 የክት ልብስ መልበስ ለወንድ (ነጭ ልብስ)
5 በጊዜ ወደ መስጂድ መሄድ
6 በእግር ወደ መስጂድ መሄድ
7 መስጂድ ውስጥ የሰዎችን ትከሻ አለመረማመድ
8 ኹጥባ እየተደረገም ቢሆን ተህየቱ መስጂድ መስገድ
9 ኹጥባ ወደ ሚያደርገው ኢመም መዞር እና ኢማሙን እያዩ ኹንባን ማዳመጥ
10 ኹጥባ በሚደረግበት ወቅት ፀጥታን መላበስ
11 ሰደቃ ማብዛት
12 ከሀሙስ ማታ እስከ ጁምዓ ዐስር ድረስ ሱረቱል ካፍ መቅራት
13 ዱዓ ማድረግ
14 የአላህ መልክተኛ(ሠ.ዐ.ወ) ላይ ሰለዋት ማብዛት
@abubekersidik
@abubekersidik
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ለበይክ አላሁመ ለበይክ...!🤲 መልካም ጁምዐ

JOIN👉 @abubekersidik 💚🤎
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አሳዛኙ እውነታ

በአለም ላይ ያሉ ሙስሊሞች በሙሉ በእድሜ ልክ አንዴ እንኳ ምነው በአጋጠመኝ ብለው የሚመኙት፣ አሏሁ ተዓላ ወንጀሎችን በሙሉ የሚምርበትስራ እንዲሁም ሶፋ እና መርዋ ፣ ሀጀሩል አስወድ እና ሩክኑል የማንይ፣ ሚና እና ሙዝደሊፋ፣ ዐረፋ እና ከዕባ ፣ ዘምዘም እና የነብዩ ሙሐመድ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም የትውልድ ስፍራ...ሌሎችም እጅግ ብዙ የተባረኩ ቦታዎች የሚዘየርበት ከእስልምና መሰረቶች ውስጥ አንዱ የሀጅ ስነ ስርአት በበሽታ ምክንያት ተዘግቶ ሙስሊም ሁሉ ተከፍቶ አዝኖ ለአውሮፓ ሀገራት የእግር ኳስ ጨዋታ በአንድ ስቴድየም ከ50,000 ሰው በላይ መሰብሰብ ተፈቅዶለት ሲታይ ነብዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም በይሀቂይ በዘገቡት ሀዲስ: "حُجُّوا قَبْلَ أَنْ لَا تَحُجُّو" ያሉት ንግግር እውን መሆኑን እንረዳለን። የሀዲሱ ትርጉምም ሀጅ ማረግ የማትችሉበት ጊዜ ከመምጣቱ በፊት ሀጅ አድርጉ ማለት ነው።

***********************************
-------------------------------------------------------------

@abubekersidik 💚
#የሐጅና_የዑምራህ_አድራጊ_ህግጋቶች_ክፍል_2🕋
 بسم الله الرحمٰن الرحيم الحمد لله رب العالمين والصلاة والسلام على رسول الله
አምልኮታዊ ተግባሮች ትክክል ሆነው ተቀባይነት የሚያገኙት ሸሪዓ ጋር በሚስማማ መልኩ ስንተገብራቸው እንደሆነ ለማንም ግልፅ ነው። ይህ ደግሞ ሊረጋገጥ የሚችለው በእውቀት ብቻ ነው። ለዚህም ነው ከነቢያችን ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም በተዘገበልን መሰረት አንድ ሰው ሐጁና የተቀሩት አምልኮታዊ ተግባሮቹ ተቀባይነት እንዲኖረው ከእውቀት ባለቤቶች መማር አለበት የምንለው። ምክንያቱም ካለማወቅ ጋር የሚደረግ አምልኮት (ዒባዳ) አድራጊውን አያድነውም። ይህ ነው ከታላላቅ ዑለማኦች በተዋረድ የደረሰን። ለዚህም ስንል ከዚህ በመቀጠል የሐጅና ዑምራን እንዲሁም የአሏህ መልእክተኛ ረሱሉን ዚያራ ማድረግ ሸሪዓን በሚስማማ መልኩ እንዴት እንደሚከናወን ህግጋቱን እናቀርባለን
🕋 #ለሐጅ_ግዴታነት ቅድመ ሁኔታዎች፡ሸ የሐጅ ግዴታነት ቅድመ ሁኔታዎች የሚከተሉት ናቸው፦
➊, #ሙስሊም_መሆን
➋, #ለአካለ_መጠን_መድረስ
➌, #ነፃነት (ባሪያ አለመሆን)
➍ , #ሐጅ_ለማድረግ_የሚያስችል አቅም ወይም ችሎታ፡፡ሴት ልጅ ከእርሷ ጋር የሚሄድ መሕረም# (እንደ ወንድም) ወይም ባል ወይም ታማኝ ሴቶች ካላገኘች በእርሷ ላይ ሐጅ ግዴታ አይሆንባትም። ግዴታ ለሆነው ሐጅ ብቻዋን መሄድ ትችላለች። ነገር ግን ሱና ለሆነው ሐጅና የነቢያችንና የሌሎችን የደጋግ ሷሊሖችን ቀብር ለመዘየር ብቻዋን መሄድ አትችልም።
#የሐጅ_ማእዘኖች_ግዴታዎችና_ሱናዎች፦ ለሐጅ ስነ–ስርአት ማእዘኖች(አርካኖች)ግዴታዎች(ዋጂቦች) እና ሱናዎች አሉት። ማእዘኖች(አርካኖች) ሲባል ካለነሱ ሐጁ ሊፈፀም የማይችል ከመሆኑም በላይ በእርድ አይካሱም።ግዴታዎች(ዋጂቦች)# ሲባል ደግሞ ካለነሱ ሐጁ ከወንጀል ጋር ሊፈፀም ይችላል። በእርድም የሚካሱ ናቸው። ሱናዎች ደግሞ ካለነሱ ሐጁ ያለ ወንጀል ሊፈፀም ይችላል(ማለትም የሐጅ ሱናዎችን ቢተው ወንጀለኛ አይሆንም)። ነገር ግን ምንዳው ያመልጠዋል።
#የሐጅና_ዑምራ_አፈፃፀም፦የሐጅ ሩክኖች (ማእዘኖች) 6 ናቸው፦
➊ ኢሕራም ማድረግ (የሐጅ ኒያን ማድረግ/ መነየት)
➋ ዐረፋ ተራራ ላይ መቆም(መገኘት)
➌, ጠዋፍ ማድረግ (ካዕባን ሰባት ጊዜ መዞር)
➍, ሰዕይ ማድረግ #በሶፋና በመርዋ መሐል ሰባት ጊዜ መመላለስ)
➎ ፀጉርን መላጨት ወይም ማሳጠር
➏, ሩክኖቹን ወይም ማእዘኖቹን ቅደም ተከተል መጠበቅ ነው(ማለትም ከኢሕራም ይጀምራል ከዛ ዐረፋ ተራራ መቆም,,,,, በቅደም ተከተል ማድረግ ነው)።
⇛አንደኛው የሐጅ ማእዘን ኢሕራም ማድረግ የሐጅ ኒያ ማድረግ ነው፦ ኢሕራም ማለት በሐጅ ስራ ውስጥ ለመግባት ኒያ ማድረግ ማለት ነው። ሐጅ ማድረግ የፈለገ ከየትኛውም አገር ቢሆን ሚቃቱን ከመሻገሩ በፊት በልቡ ኒያ ያደርጋል። #ሚቃት_ማለት_ነቢያችን_ሐጅ_ለሚያደርጉ_ሰዎች_ኢሕራም ሳያደርጉ እንዳይሻገሩ(ኢሕራም እንዲያደርጉበት) የወሰኑላቸው ቦታዎች ናቸው። እነዚህም ሚቃቶች አምስት ናቸው፦
➊, #አባር_ዐሊ፦ ከመዲና በኩል ለሚመጡ የሐጅ ተጓዦች። የሚገኘውም ወደ መካ በሚወስደው መንገድ ከመዲና 15 k.m ርቆ ነው። ይህ ሚቃት በመዲና በኩል አድርገው በየብስ ለሚጓዙ ለሻም አገር ሰዎች ነው።
➋, #ዛቱ_ዒርቅ፦ ከዒራቅ በኩል ለሚመጡ የሐጅ ተጓዦች ነው።
➌, #ቀርኑ_አስ__ሰዓሊብ፦ ከከፍተኛማ ሒጃዝ በኩል ለሚመጡ ለሐጅ ተጓዦች ነው።
➍, #የለምለም ( #አለምለም)፦ ከየመን በኩል ለሚመጡ ለሐጅ ተጓዦች ነው(ከኢትዮጵያ የሚሄዱ ሰዎች የሚነይቱበት ቦታ እዚህ ነው)።
➎, #ጁሕፋህ፦ ለሻም ለግብጽና ለምእራብ ዐረብ አገራት ሰዎች ነው። እናም የሐጅ ተጓዥ ከነዚህ ሚቃቶች አንዱን ከመሻገሩ በፊት በልቡ ኒያ ማድረግ አለበት። #ከሐበሻ_ለሚመጡ_የሐጅ_ተጓዦች_አብዘሀኛውን_ጊዜ_በአየር የሚያልፉት በየመን በኩል ስለሆነ #የለምለም ከመሻገራቸው በፊት ኒያ ማድረግ አለባቸው። በሌላ ቦታ ለሚጓዙ የሐጅ ተጓዦች
በሚያልፉበት ሚቃት ኒያ ያደርጋሉ። በአየር የሚጓዙ የሐጅ ተጓዦች ኢሕራም(ኒያ) የሚያደርጉት በአገራቸው ወይም አውሮፕላን ላይ ሚቃቱን ከመሻገራቸው በፊት ነው።
#አሏሁ_ተዓላ_ሐጅ_አድርገዉ_የዘይኔን_ቀብር_ዘይረዉ_ከሚሞቱት_ያድርገን፡፡ኣሚን
#መልካም_ምሽት🌹
#ኢንሻአሏህ_ክፍል_3_ይቀጥላል,,,,,,,,,


#ኒሳኡል_መሻሪዕ_የኔ_ያንተ_ያንች ነው። የዑለሞቻችንን መንገድ በጋራ እናስቀጥል ..👇👇

🎖SHARE🎖

┏━ 💗 ━━━━ 💗━┓

@abubkersidik
┗━ 💗 ━━━━ 💓━┛
▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ለበይክ አላሁመ ለበይክ...!🤲 ያ ረብ ወፍቀን!🥺

#Eid_Al_adha_mubarek🤎🤎🤎🤎🤎🤎🤎🤎🤎

JOIN 👉 @abubekersidik
2024/09/28 00:27:06
Back to Top
HTML Embed Code: