Telegram Web Link
አል-ኢዕቲካፍ
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው
1/ የቃላት ፍቺ፡-
ኢዕቲካፍ ማለት ቀጥተኛ ፍቺው፡- ራስን በአንድ ነገር ላይ ማዘውተር ማለት ነው፡፡ ሸሪዓዊ ፍቺው ደግሞ፡- ሶላቱል ጀማዓህ በሚሰገድባቸው የአላህ ቤቶች/ መስጂድ ውስጥ ወደ አላህ በመልካም ሥራ ለመቃረብና ኃጢአትን ለማስሰረዝ ከልብ በመነየት/በመወሰን የተወሰነ ጊዜ (ለደቂቃ፣ ለሰዓታት፣ ለቀናት፣ ለሳምንታት) ቆይታ ማድረግ ማለት ነው፡፡
2/ የድርጊቱ ሸሪዓዊነት፡-

በአላህ ቤቶች ውስጥ ኢዕቲካፍ ማድረግ፡ ለወንዶችም ሆነ ለሴቶች፡ በቅዱስ ቁርኣንና በሐዲሥ የተደገፈ ሸሪዓዊ መሠረት ያለው ተግባር ነው፡፡ የአላህ ቃል በአላህ ቤቶች ውስጥ ኢዕቲካፍን ያደረገ አንድ ሙስሊም ከባለቤቱ ጋር የግብረ-ሥጋ ግኑኝነት መፈጸም እንደሌለበት ሲያስተምር፡ እግረ-መንገዱንም ኢዕቲካፍ የሚባል ነገር መኖሩን ጠቁሞናል፡፡ ቃሉ እንዲህ ይላል፡-

"…وَلَا تُبَاشِرُوهُنَّ وَأَنْتُمْ عَاكِفُونَ فِي الْمَسَاجِدِ…" سورة البقرة 187
"…እናንተም በመስጊዶች ተቀማጮች ስትኾኑ አትገናኙዋቸው…" (ሱረቱል በቀራህ 2፡187)፡፡

عَنْ عَائِشَةَ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهَا، - زَوْجِ النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ -: «أَنَّ النَّبِيَّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ، كَانَ يَعْتَكِفُ العَشْرَ الأَوَاخِرَ مِنْ رَمَضَانَ حَتَّى تَوَفَّاهُ اللَّهُ، ثُمَّ اعْتَكَفَ أَزْوَاجُهُ مِنْ بَعْدِهِ» رواه البخاري 2026 ومسلم 2841
እናታችን ዓኢሻህ (ረዲየላሁ ዐንሃ) እንዲህ ትላለች፡- "የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ይህችን ዱንያ እስኪሰናበቱ ድረስ የረመዷንን የመጨረሻዎቹን አሥርት ቀናት ኢዕቲካፍ ያደርጉ ነበር፡፡ ከሳቸው ዱንያን መሰናበት በኋላም ባለተቤቶቻቸው (የምእመናን እናት ረዲየላሁ ዐንሁንነ) ኢዕቲካፍ አድርገዋል" (ቡኻሪና ሙስሊም)፡፡
3/ ቅድመ-ዝግጅቱ (መሟላት ያለበት መስፈርት)፡-

ኢዕቲካፍ ለማድረግ የወሰነ ሙስሊም የአላህ ባሪያ፡ ኢዕቲካፍ ከማድረጉ በፊት፡ ከዚህ ቀጥሎ ያሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅበታል፡፡

ሀ/ ዐቅል ያለው (አእምሮው ያልተዛባ) መሆን፡- ጤናማ አእምሮ ያለው ሊሆን ግድ ነው፡፡ የአእምሮ ህመምተኛ የኾነ ሰው በሕክምና ቦታ ሊታከም ይገባዋል እንጂ፡ የአላህ ቤት መጥቶ አማኞችን ማስቸገር የለበትም፡፡

ለ/ ጡሀራ መሆን፡- ይህ ማለት፡ ከጀናባ፣ ከሐይድ (ከሐይድ ቀን ውጭ የሚፈሰውን የኢስቲሓዷ (የበሽታ ደም) አያካትትም) እና ከኒፋስ (የወሊድ ደም) የጠሩ መሆን አለባቸው፡፡
4/ የኢዕቲካፍ ማእዘናት፡-

አላህ ዘንድ ተቀባይነት ያለው ኢዕቲካፍ እንዲሆንለት የሚፈልግ አንድ ሙስሊም፡ በኢዕቲካፍ ወቅት ቀጥሎ ያሉትን ማእዘናት ሊፈፅም ግድ ይለዋል፡፡ እነሱም፡-

ሀ/ ኒይያ (ቁርጠኛ ውሳኔ)፡- እራሱን በመስጂድ ውስጥ በመገደብ ኢዕቲካፍ የሚያደርገው፡ ወደ አላህ ለመቃረብ እንጂ፡ ቤት መተኛት ስላስጠላው፡ ወይም የቤት ውስጥ ጭቅጭቅ ስለሰለቸው መሆን የለበትም፡፡ ያ ከሆነ ምክንያቱ ኒይያው ተቀይሯል ማለት ነው፡፡ ኢዕቲካፍን የሚነይት የአላህ ባሪያ ዓላማው፡ ብዙ መልካም ነገራትን በማድረግ፡ ኃጢአትንም በመራቅ ወደ አላህ እቃረብበታለሁ ብሎ መሆን አለበት፡፡ ሥራ በጠቅላላ ተቀባይነቱ በኒይያ ነውና፡፡ ለአላህ ብሎ የኢስላምን ባንዲራ ከፍ ለማድረግ ጠላትን የታገለ ሙስሊምም ሆነ፡ ሥምና ዝናን ለማትረፍ፡ በጀግንነት እንዲወሳ የፈለገ ሙስሊም፡ ሁለቱም በጦር ሜዳ ላይ ቢገደሉ ‹‹ሸሂድ›› የሚል የጋራ ስያሜ ይሰጣቸዋል፡፡ ግን አላህ ዘንድ ተጠቃሚውና ባለ-ምንዳ የሚሆነው ኒያውን አስተካክሎ በኢኽላስ የሰራው ብቻ ነው፡፡ ሁለተኛው ግን ኒያው የተበላሸ በመሆኑ፡ አላህ ይቅር ካላለው በስተቀር የሚጠብቀው ሽልማት ሳይሆን ቅጣትና ቁጣ ነው፡፡

ለ/ ቦታው መስጂድ መሆኑ፡- የኢዕቲካፍ ስፍራ መስጂድ ብቻ ነው፡፡ በተለይ ጁምዓ ጭምር የሚሰገድበት (ጃሚዕ) ቢሆን ይመረጣል፡፡ ወንዶች ሶላቱል ጀመዓህ እና ጁምዓ ስለሚወጅብባቸው፡ የጁምዓ መስጂድ ፍለጋ እንዳይቸገሩ ይረዳቸዋልና፡፡ ያ ከመሆኑ ጋር እሱ ያለበት መስጂድ ጁምዓህ ባይሰገድበትም ‹‹መስጂድ›› ተብሎ እስከተጠራ ድረስ ግን ኢዕቲካፍ ሊያደርግበት ይችላል፡፡ የቁርኣኑም አንቀጽ ከላይ የተናገረው ‹‹በመስጂድ ውስጥ›› በማለት ነውና፡፡
5/ ኢዕቲካፍ አዳቦች/ስርኣቶች፡-

አጅሩ የተሟላ እንዲሆንለትና ይበልጥ ወደ አላህ ቤት የመጣበትን ዓላማ ከግብ ለማሳካት የሚፈልግ ሙስሊም፡ ቀጥሎ ያሉትን አዳቦች ማሟላት ይገባዋል፡-

ሀ/ የዒባዳህ ተግባራትን ማብዛት፡- ሶላት (ሱንናዎችን ጭምር)፣ ቁርኣን ማንበብ፣ ዚክር፣ ኢስቲግፋር፣ ዱዓእ የመሳሰለውን፡፡

ለ/ ከሐሜትና ነገር ማዋሰድ፣ ከጭቅጭቅና ጉንጭ አልፋ ክርክር፣ ጥቅም አልባ ከሆነ ወሬ እራስን ማግለልና በዒባዳህ ተግባር መወጠር፡፡

ሐ/ ኢዕቲካፍ የሚያደርግበትን የመስጂዱን አንድ የተለየ ስፍራ በመምረጥ፡ ኢዕቲካፉን እስኪጨርስ ድረስ፡ ከቻለ በዛ ቦታ ላይ መሆን፡፡

መ/ ኢዕቲካፍ ማለት እራስን ከቤተሰብና ከጓደኞች አግልሎ በአላህ ቤት ማኖር ማለት ስለሆነ፡ አሁንም ከተቻለ ከማንም ጋር ሳይቀላቀል ብቻውን ጉዳዩን እስኪፈጽም ድረስ ገለል ማለት (ለብቻ መሆን)፡፡
6/ የኢዕቲካፍ የጊዜ ገደቡ፡-

ኢዕቲካፍ ማድረግ የፈለገ ሰው በማንኛው ጊዜ (በቀንም ሆነ በለሊት) የፈለገውን ሰዓት ያህል (ለደቂቃም ሆነ ለሰዓት፣ ለቀናትም ሆነ ለሳምንታት) መነየት ይችላል፡፡ የተገደበ ወቅትና መጠን የለውም፡፡ ከሁሉም የተሻለው ግን የረመዷን ወር የመጨረሻው አሥርት ቀናትን መጠቀሙ ነው፡፡ ይህም የረመዷን 20ኛው የፆም ቀን ከመጠናቀቁ (መግሪብ መግባት) ቀደም ብሎ መስጂድ በመግባት፡ ነገ ዒድ ነው እስኪባል ድረስ (የረመዷን 29/30ኛ ቀን ተጠናቅቆ መግሪብ እስኪሰገድ ድረስ) መቆየት ማለት ነው፡፡

7/ የተፈቀዱ ተግባራት፡-

ሀ/ የመስጂዱን ንጽህና ከመጠበቅ ጋር፡ መብላት መጠጣት እንዲሁም መተኛት፡፡

ለ/ ለንጽህና ተግባር (ሽንት ቤት) መውጣት እና የዉዱእ ስፍራ መገኘት፡፡

ሐ/ አስገዳጅ ለሆነ ተግባር ከመስጂዱ ክልል መውጣትና፡ ጉዳዩን በፍጥነት አስተካክሎ መመለስ፡፡

መ/ ፀጉርን ማበጠር፣ የእጅና የእግር ጥፍርን ማስተካከል፣ ገላን መታጠብና ሽቶ መቀባት፡ እንዲሁም ልብስን መቀየር፡፡

ሠ/ ባል ሚስቱን፡ ወይም ሚስት ባሏን ሰላምታ ማቅረብና መነጋገር፡፡ እና ሌሎችም፡፡

8/ ኢዕቲካፍን የሚያበላሹ ነገራት፡-

ሀ/ ከባለቤቱ ጋር የግብረ-ስጋ ግኑኝነት መፈፀም፡፡

ለ/ ከትዳር አጋሩ ጋር የፍቅር ጨዋታ እየተጫወተ የዘር ፈሳሽ ማውጣት፡፡

ሐ/ የወር አበባ ወይም የወሊድ ደም መከሰት፡፡

መ/ ያለ ምንም ዑዝር ከመስጂዱ መውጣት፡፡
@seidaliarg
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from ﷽ህብረ - ሙስሊም 2⃣ (عبد الجلال مانو محمد)
ደስታ የፈለግነውን ማግኘት ሳይሆን ባለን ነገር ረክተን መኖር ነው ፡፡ ባገኘናቸው ቀላል በረከቶች እንኳን ደስተኛ ለመሆን መንገዱ አመስጋኝ መሆን ነው። አልሀምዱሊላህ።
#ሸር_ያድርጉ @hebre_muslim
እኛ ዛሬ የመጨረሻው ቀንችን ቢሆን ኖሮ እንዴት እናጠፋው ነበር?

1 ቁርአንን ማንበብ
2 ዱአ እና ኢስቲግፋር ማድረግ
3 ሳላትን መስገድ
4 ምጽዋት መስጠት
5 ቤተሰብ መሰብሰብ
6 ዕዳዎችን መወሰን/mekfel

ነገር ግን .. እኛ አናውቅም?
@hebre_muslim
Forwarded from 💐🕍 አብዲ ቲዩብ๑ 💐۞๑๑۩ 💐 🕌abdi Tube ๑ 💐 (عبد الجلال مانو محمد)
ይቅር ባይነት ስለ ሌሎች ብቻ አይደለም ፡፡ እንዲሁም ስለራሳችን መንፈሳዊ እድገት ነው ፡፡ ፍቅር እና ይቅርባይነት መለየት አይቻልም ፡፡ ሁሉን ቻይ በሚፈልገው መንገድ ለመኖር ከመረጥን ይቅር ማለት መወገድ የማይችል አማራጭ ነው። ምክንያቱም ሁላችንም ኃጢአተኞች ነን ፣ ሌሎችን ይቅር ማለት አለብን።
@abdu4321
ምንም ዓይነት አካላዊ መልክዎ ምንም ይሁን ምን ፣ በልብዎ ውስጥ ደግነት ሲኖርዎ ፣ በዓለም ላይ በጣም ቆንጆ ሰው ነዎት። https://www.tg-me.com/ustaz_sadat
Forwarded from 💐🕍 አብዲ ቲዩብ๑ 💐۞๑๑۩ 💐 🕌abdi Tube ๑ 💐 (عبد الجلال مانو محمد)
📮 ሰበር ዜና ሰበር ዜና
📮 عاجل عاجل عاجل:-

🔭 تعذر رؤية هلال شوال في تمير ، والخميس أول أيام عيد الفطر بالسعودية.

📮 ሱዑዲ ላይ ጨረቃ ስላልታየች አላህ ካለ ነገ 30ኛው ረመዷን ፆም ይሆናል።

@abdu4321
Forwarded from ﷽ህብረ - ሙስሊም 2⃣ (عبد الجلال مانو محمد)
ከምሽት ጀምሮ ለምትወዱት ቤተሰብ ዘመድ አዝማድ ጓደኛ

ለ1442ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል እንኳን አደረሰህ/አደረሰሽ መልክት በዚሁ ቻናል ማስተላለፍ ትችላላችሁ

ለኔም ይቻላል 😉😉😉

ስም እና አድራሻ ጨምራችሁ ላኩልን

መላኪያ 👉 @abduljilal
እንኳን ለ1442ኛው የዒዱል ፊጥር በዓል አላህ በሰላም አደረሳችሁ!

ዒዱኩም ሙባረክ!

ተቀበለላሁ ሚንና ወሚንኩም!
Forwarded from ﷽ህብረ - ሙስሊም 2⃣ (عبد الجلال مانو محمد)
#እንዳትደናገጡ

ነገ ንጋት 12:00 ላይ ለኢዳችን ድምቀት 9 ግዜ መድፍ ስለሚተኮስ የምትሰሙት የመድፍ ተኩስ ድምፅ የኢድ መልካም ዜና ማብሰርያ መሆኑን ላስታውሳችሁ

ላልሰሙት አሰሙ 🗣🗣🗣🗣


👉 @hebre_muslim
Forwarded from ﷽ህብረ - ሙስሊም 2⃣ (عبد الجلال مانو محمد)
🛩#ኢትዮጵያ_ህዳሴ_ግድቡን ከጥቃት ለመጠበቅ የታጠቀችው ዘመናዊ መሳሪያ!!

ጠላት የፈለገውን ዘመናዊ መሳሪያ ታጥቆ ይፎክራል እንጅ በህዳሴ ግድቡ ላይ እኛ የማንፈቅደው ጥቁር ወፍ መብረር አይችልም። ይህ መሳሪያ በህዳሴው ግድቡ ጎን የተገነባ የህዳሴ ግድቡ ዘበኛ ነው።

የመጀመሪያው s_125 ፒኮራ ሚሳይሎች
ሲሆኑ እስራኤል ሰራሽ የዩክሬን ሲስተም የተገጠመለት ዘመናዊ ራዳር ተሸኪሚ ሚሳኤል ነው።

ሁለተኛው፦S_300 ወይም HQ.9
ሚሳይሎች ጋር ተመሳሳይ የሆነ ሩሲያ ሰራሽ አውዳሚ ሚሳይል ነው።

ሦስተኛው S_6+6 ወይም HQ.6 ሚሳይል ጋር ተመሳሳይ የሆነ ቻይና ሰራሽ ዘመናዊ አነፍናፊ ራዳር ያለው ቻይና ሰራሽ መሳሪያ ነው።

አራተኛው እስፓይደር እስፓይደር ኤም አይ የተባለው ፀረ አውሮፕላን መሳሪያ ሲሆን፣ ሁለት አይነት ሚሳኤሎችን ባንድ ጊዜ ማሶንጨፍ የሚች ነው። አንድኛው ሚሳኤል ከራዳር ሲስተም የተሰሩ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን አነፍንፎ መምታት የሚችል ሲሆን ሁለተኛው ሲስተም ደሞ ፀረ ሚሳይል መቃወሚያ የተገጠመላቸው ጀቶችን መምታት የሚችል ሲሆን ከመሬት ሲወነጨፍ ጭስ አልባ ሚሳኤል ሲሆን ይሄም የጥላት ጦር መሳሪያውን እንዳያከሽፈው መሰወር የሚችል በአንድ ጊዜ 500 ተዋጊ የጠላት አውሮፕላን ማርገፍ የሚችል መሳሪያ ነው።


........ more
𝐉𝐨𝐢𝐧 𝐔𝐬 @hebre_muslim
Abdi 𝚢𝚘𝚞𝚛 𝙱𝚎𝚜𝚝 𝙵𝚛𝚒𝚎𝚗𝚍
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from Deleted Account
🚫.........ሙስሊም ነህ⁉️.........🚫

እንግዲያውስ ከስር ያለውን በጥንቃቄ

open ብለህ ተመልከት

እባክህ ሙስሊም ከሆንክ ብቻ እያው❗️

አላህ ከፈተና ይጠብቀን! አሚን!!!!

ምርጥ ኢስላማዊ ቻይናል።
👇👇👇👇👇👇
---------------------------------
𝐎𝐩𝐞𝐧𝐎𝐩𝐞𝐧
𝐎𝐩𝐞𝐧𝐎𝐩𝐞𝐧
----------------------------------
Forwarded from ﷽ህብረ - ሙስሊም 2⃣ (عبد الجلال مانو محمد)
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🔶 وَهِيَ تَجْرِي بِهِمْ فِي مَوْجٍ كَالْجِبَالِ وَنَادَىٰ نُوحٌ ابْنَهُ وَكَانَ فِي مَعْزِلٍ يَا بُنَيَّ ارْكَب مَّعَنَا وَلَا تَكُن مَّعَ الْكَافِرِينَ

እርሷም እንደ ተራራዎች በሆነ ማዕበል ውስጥ በእነርሱ (ይዛቸው) የምትንሻለል ስትሆን (በአላህ ስም ተቀመጡባት)፡፡ ኑሕም ልጁን ከመርከቢቱ የራቀ ሆኖ ሳለ «ልጄ ሆይ! ከኛ ጋር ተሳፈር ከከሓዲዎቹም አትሁን» ሲል ጠራው፡፡
قَالَ سَآوِي إِلَىٰ جَبَلٍ يَعْصِمُنِي مِنَ الْمَاءِ ۚ قَالَ لَا عَاصِمَ الْيَوْمَ مِنْ أَمْرِ اللَّهِ إِلَّا مَن رَّحِمَ ۚ وَحَالَ بَيْنَهُمَا الْمَوْجُ فَكَانَ مِنَ الْمُغْرَقِينَ

(ልጁም) «ከውሃው ወደሚጠብቀኝ ተራራ እጠጋለሁ» አለ፡፡ (አባቱም)፡- «ዛሬ ከአላህ ትዕዛዝ ምንም ጠባቂ የለም (እርሱ) ያዘነለት ካልሆነ በቀር» አለው፡፡ ማዕበሉም በመካከላቸው ጋረደ፡፡ ከሰጣሚዎቹም ሆነ፡፡
وَقِيلَ يَا أَرْضُ ابْلَعِي مَاءَكِ وَيَا سَمَاءُ أَقْلِعِي وَغِيضَ الْمَاءُ وَقُضِيَ الْأَمْرُ وَاسْتَوَتْ عَلَى الْجُودِيِّ ۖ وَقِيلَ بُعْدًا لِّلْقَوْمِ الظَّالِمِينَ

ተባለም፡- «ምድር ሆይ! ውሃሽን ዋጪ፡፡ ሰማይም ሆይ (ዝናብሽን) ያዢ፡፡ ውሃውም ሰረገ፡፡ ቅጣቱም ተፈጸም፡፡ ጁዲይ በሚባልም ተራራ ላይ (መርከቢቱ) ተደላደለች፡፡ ለከሓዲዎችም ሰዎች ጥፋት ተገባቸው (ጠፉ)» ተባለ፡፡

📚[ሱረቱ ሁድ -41~44]

@hebre_muslim
Forwarded from ﷽ህብረ - ሙስሊም 2⃣ (عبد الجلال مانو محمد) via @BestApps1bot
ከተከበረው የረመዳን ወር በኋላም ቢሆን አላህን ወጥነት ባለው መልኩ ጥሩ ስራ ለመስራት እናስብ ፡፡ ለበጎ አድራጎት መስጠት ቢሆን ፣ የቁርአን አንድ ገጽ እንኳን በማንበብ ወይም 2 ክፍሎችን ለታሃጁድ ማቅረብ። ወጥነት ቁልፍ ሚና አለው!
______________
አንብበን እውቀት ካገኘንበት እና ለምን የምናቀውን አናሳውቅ‼️ ስስታም አንሁን ያወቅነውን እናሳውቅ
ለ 10 ሰው #ሼር_ያድርጉ

@hebre_muslim
2024/09/23 15:27:34
Back to Top
HTML Embed Code: