Telegram Web Link

"በምትናገረው ንግግር !በእንቅስቃሴህ ሁሉ ከአጠጋብህ ተቆጣጣሪ መላእክት እንዳሉ አትዘንጋ!"

🍃👀 @abdu4321👀🍃
Forwarded from ﷽ህብረ - ሙስሊም 2⃣ (عبد الجلال مانو محمد)

እህቴ ፦
ከአላህ በኩል ያለብሽን ግዴታ ሟሟላት አለብሽ፤ ምክንያቱም እኛን አላህ የፈጠረን እሱን ለመገዛት ብቻ ነውና።አስተውይ ሂጃብ መልበስ ከሞት በፊት ከአላህ ዘንድ ታውጇል።
"እና ሂጃብ ደሞ ከላይ ሚለበስ ትንሽ ልብስ ብቻ ሳይሆን የሂወት አንዱ መንገድም ነው።"

🍃👀 @hebre_muslim👀🍃
Forwarded from ﷽ህብረ - ሙስሊም 2⃣ (عبد الجلال مانو محمد)

"አቡ ሁረይራ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፦

"ኢማን ከሰባ ሦስት እስከሰባ ዘጠኝ ወይም ከስድሳ ሦስት እስከ ስድሳ ዘጠኝ የሚደርሱ ቅርንጫፎች አሉት። ከፍተኛው በላጩ «ላ ኢላሃ ኢለላህ»ን ማለት (ከአላህ ሌላ የሚመለክ ኃይል እንደሌለ መመስከር) ሲሆን የመጨረሻውና ዝቅተኛው ከመንገድ ላይ እንቅፋትን ማስወገድ እና «ሐያእ» የኢማን አንዱ ዘርፍ ነው (ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)

👀👀 @hebre_muslim
Forwarded from 💐🕍 አብዲ ቲዩብ๑ 💐۞๑๑۩ 💐 🕌abdi Tube ๑ 💐 (عبد الجلال مانو محمد)

"የአላህ መልዕክተኛ (ሶ.ዐ.ወ) አገልጋይ ሠወባን (አቡ ዐብደላህ አቡ አብዱራህማንም ይባላሉ) (ረ.ዐ) የአላህ መልዕክተኛ (ሶ.ዐ.ወ) ተከታዩን ሲናገሩ አዳምጫለሁ በማለት አሰተላልፈዋል፡፡

"ሱጁድን (ሶላትን) በማብዛት አደራህን (ተጠናክሮ ) ለአላህ አንዲትን
ሱጁድ አትሰግድም አላህ በእርሷ ደረጃን ከፍ ያደረገህ ኃጢአትህንም ያበሰልህ ቢሆን እንጂ፡፡" (ሙሰሊም ዘግበውታል)

👀👀 @abdu43211
በ ፀጉር አስተካካዩ እና በ ፀጉር
ተስተካካዩ መካከል የተደረገ ቃለ
ምልልስ

😳ፈጣሪ የለም😳

ልብ ብለው ያንብቡት
አንድ የእምነት ሰው ጸጉሩን ሊስተካከል ወደ አንድ ጸጉር አስተካካይ ቤት ይሄዳል።
በመሀልም ጫወታ ይጀምራሉ።
ጸጉር አስተካካይ፦ ታውቃለህ ፈጣሪ የለም
ተስተካካይ፦ በመገረም እንዴት
አስተካካይ፦ አይታይህም
ተስተካካይ፦ ምኑ
አስተካካይ፦ እንዴዴዴ ፈጣሪ ቢኖር እኮ ይሄ ሁሉ ጦርነት፣
ረሀብ፣ ችግር፣ ስርአት አልበኝነት
አይኖርም ነበር ስለዚህ ፈጣሪ
አንዴ ፈጥሮን ትቶን ሄዷል
ወይ ሞቷል ማለት ነው አለ።
ተስተካካይ፦ ታውቃለህ ጸጉር
አስተካካይም የሚባል የለም
አስተካካይ፦ በጣም ግራ በመጋባት እና በመገርም እንዴት
ተስተካካይ፦ ጸጉር አስተካካይ
ቢኖርማ ጸጉሩ የጎፈረ ፀጉሩ
የተንጨባረረ ሰው አይኖርም
ነበር አለው ።
አስተካካይ፦ እነዚህ ሰዎች እኮ
ወደ ጸጉር አስተካካይ
አለመምጣታቸው ነው እንጂ
ቢመጡማ ኖሮ አንድም ጸጉሩ
የጎፈረ እና የተንጨባረረ ጸጉር
አታይም ነበር።
ተስተካካይ፦ ትክክል ብለሀል
በአለማችን ያለው ችግርም
ይኸው ነው ሰው ከፈጣሪው
ስለራቀ ነው እንጂ
ፈጣሪ ስለሌለ አይደለም።
꧁﷽꧂
@abdu43211
Shear 🙏

#አቡ ሁረይራ [رضي الله عنه‌‎ ] እንዳወሩት
#ነቢዩ [صلى الله عليه وسلم] እንዲህ ብለዋል፡- #አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡- “የአደም ልጅ እኔን ካደ፤ እንዲህ ለማድረግ መብት አልነበረውም፡፡ ደግሞም ሰደበኝ፤ እንዲህ ለማድረግም መብት አልነበረውም፡፡ እኔን መካዱን የሚያመለክተው ‹መጀመሪያ ላይ እንደፈጠረኝ አድርጎ ዳግም አይሠራኝም› የሚለው ንግግሩ ነው፡፡ ለመሆኑ መጀመሪያ እሱን መፍጠር ነው ወይስ ዳግም መሥራት ለኔ ይበልጥ የሚቀለው?  እኔን መሳደቡን (የሚያመለክተው) ዳግሞ ‹አላህ ልጅ አለው› ማለቱ ነው፡፡ እኔ አንድ ነኝ፤ የሁሉ መጠጊያ ነኝ፤ አልወለድኩም፣ አልተወለድኩም፤ ለእኔ አንድም ብጤ የለኝም፡፡”
ቡኻሪ ዘግበውታል

@abdu43211

#አቡ ሁረይራ [رضي الله عنه‌‎ ] እንዳስተላለፉት #ነቢዩ [صلى الله عليه وسلم] ይህን ተናግረዋል፡- “ኃያሉና የተከበረው #አላህ እንዲህ ይላል፡- “በትንሳኤ ቀን እኔ ጠላት የምሆንባቸው ሦስት ወገኖች አሉ፡፡ በእኔ ስም ቃል ገብቶ ያፈረሰ ሰው፣ አንድን ነፃ የሆነ ሰው ሸጦ ዋጋውን የበላ እና ሠራተኛ ቀጥሮ ከእሱ የሚፈልገውን በሙሉ ከተቀበለ በኋላ ደመወዙን ያልሰጠ ሰው፡፡”
(ቡኻሪ፣ ኢብኑ ማጀህና አህመድ ዘግበውታል)

@abdu43211

اللَّهُ لَا إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ الْحَيُّ الْقَيُّومُ ۚ لَا تَأْخُذُهُ سِنَةٌ وَلَا نَوْمٌ ۚ لَّهُ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَمَا فِي الْأَرْضِ ۗ مَن ذَا الَّذِي يَشْفَعُ عِندَهُ إِلَّا بِإِذْنِهِ ۚ يَعْلَمُ مَا بَيْنَ أَيْدِيهِمْ وَمَا خَلْفَهُمْ ۖ وَلَا يُحِيطُونَ بِشَيْءٍ مِّنْ عِلْمِهِ إِلَّا بِمَا شَاءَ ۚ وَسِعَ كُرْسِيُّهُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ ۖ وَلَا يَئُودُهُ حِفْظُهُمَا ۚ وَهُوَ الْعَلِيُّ الْعَظِيمُ

አላህ ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ ሕያው ራሱን ቻይ ነው፡፡ ማንገላጀትም እንቅልፍም አትይዘውም፡፡ በሰማያት ውስጥና በምድር ውስጥ ያለው ሁሉ የርሱ ብቻ ነው፡፡ ያ እርሱ ዘንድ በፈቃዱ ቢኾን እንጅ የሚያማልድ ማነው? (ከፍጡሮች) በፊታቸው ያለውንና ከኋላቸው ያለውን ሁሉ ያውቃል፡፡ በሻውም ነገር እንጂ ከዕውቀቱ በምንም ነገር አያካብቡም (አያውቁም)፡፡ መንበሩ ሰማያትንና ምድርን ሰፋ፡፡ ጥበቃቸውም አያቅተውም፡፡ እርሱም የሁሉ በላይ ታላቅ ነው፡፡

@abdu43211

6. ሚዛኖቹ የከበዱለት ሰውማ፤
7. እርሱ በምትወደድ ኑሮ ውስጥ ይኾናል፡፡
8. ሚዛኖቹም የቀለሉበት ሰውማ፤
9. መኖሪያው ሃዊያህ ናት
Surah An-Nahl (النّحل), verses: 49

وَلِلَّهِ يَسْجُدُ مَا فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَا فِى ٱلْأَرْضِ مِن دَآبَّةٍ وَٱلْمَلَٰٓئِكَةُ وَهُمْ لَا يَسْتَكْبِرُونَ

ለአላህም በሰማያት ያለው ከተንቀሳቃሽም በምድር ያለው ሁሉ፣ መላእክትም ይሰግዳሉ፡፡ እነርሱም አይኮሩም፡፡
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
﷽ •••••••••• Surah Al-Kahf (الكهف),
#1 ምስጋና ለአላህ ለዚያ መጽሐፉን በውስጡ መጣመምን ያላደረገበት ሲሆን በባሪያው ላይ ላወረደው ይገባው፡፡
#2 ቀጥተኛ ሲሆን ከእርሱ ዘንድ የኾነን ብርቱን ቅጣት ሊያስፈራራበት፣ እነዚያንም በጎ ሥራዎችን የሚሠሩትን ምእመናን ለነሱ መልካም ምንዳ ያላቸው መኾኑን ሊያበስርበት፤ (አወረደው)፡፡
#3 በእርሱ ውስጥ ዘለዓለም የሚቆዩበት ሲኾኑ (ያላቸው መኾኑን)፡፡
#4 እነዚያንም «አላህ ልጅን ይዟል» ያሉትን ሊያስፈራራበት (አወረደው)፡፡

@abdu43211
Forwarded from ﷽ህብረ - ሙስሊም 2⃣ (عبد الجلال مانو محمد)

ነብዩ ሙሳን (ዐ.ሰ) ለመርዳት ባህሩን ለአስራ ሁለት የከፈለው አላህ (ሱ.ወ) ለአንተ ችግሮች በሙሉ የመፍትሄ በር ይከፍትልሀል ሁሌም በአላህ እመን
_____________

@hebre_muslin
Forwarded from ﷽ህብረ - ሙስሊም 2⃣ (عبد الجلال مانو محمد)

ነብዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል “በእኛና በእነርሱ (በከሀዲያን) መካከል ያለው መለያ ሰላት ነው እሱን የተወ በእርግጥ ክዷል፡፡” (ሙስሉም ዘግበውታል)
________

@hebre_muslim👀🍃

«አላህ ሆይ! ከድክመትና ከስንፍና፣ ከፍርሃ
ትና ከስስት፣ ከእርጅናና ከቀብር ቅጣት በአንተ እጠበቃለሁ። አላህ ሆይ! ለነፍሴ
እንተን መፍራትን ስጣት። አጽዳትም። ከማንም ይበልጥ የምታጸዳት አንተ ነህና። እንተ ወዳጇና ረዳቷ ነህ። አላህ ሆይ! ከማይጠቅም እውቀት፡ አንተን ከማትፈራ ቀልብ፡ ከማትጠግብ ነፍስ፡ ተቀባይ ከሌለው ዱዓ በአንተ እጠበቃለሁ።»

@Abdu43211
Forwarded from 💐🕍 አብዲ ቲዩብ๑ 💐۞๑๑۩ 💐 🕌abdi Tube ๑ 💐 (عبد الجلال مانو محمد)
🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂

ልብ ትረጋለች የጌታዋ ስም ሲወሳ ትረካለች።

الَّذِينَ آمَنُوا وَتَطْمَئِنُّ قُلُوبُهُم بِذِكْرِ اللَّهِ ۗ أَلَا بِذِكْرِ اللَّهِ تَطْمَئِنُّ الْقُلُوبُ

(እነሱም) እነዚያ ያመኑ ልቦቻቸውም አላህን በማውሳት የሚረኩ ናቸው፡፡ ንቁ! አላህን በማውሳት ልቦች ይረካሉ፡፡

ልቡን ለአላህ የሰጠና ወደ እርሱም የተጠጋ ፍርሃት ፍፁም የለበትም።


وَتَوَكَّلْ عَلَى اللَّهِ ۚ وَكَفَىٰ بِاللَّهِ وَكِيلًا

በአላህም ላይ ተጠጋ፡፡ መጠጊያም በአላህ በቃ፡፡

فَتَوَكَّلْ عَلَى اللَّهِ ۖ إِنَّكَ عَلَى الْحَقِّ الْمُبِينِ

በአላህም ላይ ተጠጋ፡፡ አንተ ግልጽ በኾነው እውነት ላይ ነህና፡፡

አንተ ሰው ሆይ! መጠጊያህን ምረጥና ጥግህን ያዝ፣ ልብህ በሠላት ትርጋ ወደ ጌታዋ ትቃረብ።

وَاسْجُدْ وَاقْتَرِب ۩

ስገድም፤ (ወደ አላህ) ተቃረብም፡፡

🌹🌹🌹
@abdu4321
=================
Forwarded from 💐🕍 አብዲ ቲዩብ๑ 💐۞๑๑۩ 💐 🕌abdi Tube ๑ 💐 (عبد الجلال مانو محمد)
አንዳንድ ሰዎች ያንን ያስባሉ
በቀልድ ከሆነ ውሸትን መናገር ይፈቀዳል።

ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል
ሰዎችን ለማሾፍ ለዋሸ ወዮለት ፣
ወዮለት ፣ ወዮለት!
አቡ ዳሙድ ፣ ጥራዝ 5 ፣ ሀዲስ ቁጥር 490

ውሸት ሀራም ነው
አንዱ ቢያደርገውም
በቀልድ ወይም በቁም ነገር (ቢሆንም) @abdu4321
Forwarded from ﷽ህብረ - ሙስሊም 2⃣ (عبد الجلال مانو محمد)
ሙስሊም ላልሆኑት ወደ ኢስላምና ጥሪ ስታደር

قُلْ يَٰٓأَهْلَ ٱلْكِتَٰبِ تَعَالَوْا۟ إِلَىٰ كَلِمَةٍ سَوَآءٍۭ بَيْنَنَا وَبَيْنَكُمْ أَلَّا نَعْبُدَ إِلَّا ٱللَّهَ وَلَا نُشْرِكَ بِهِۦ شَيْـًٔا وَلَا يَتَّخِذَ بَعْضُنَا بَعْضًا أَرْبَابًا مِّن دُونِ ٱللَّهِ فَإِن تَوَلَّوْا۟ فَقُولُوا۟ ٱشْهَدُوا۟ بِأَنَّا مُسْلِمُونَ

የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! በእኛና በእናንተ መካከል ትክክል ወደ ኾነች ቃል ኑ፡፡ (እርሷም) አላህን እንጅ ሌላን ላንገዛ፣ በርሱም ምንንም ላናጋራ፣ ከፊላችንም ከፊሉን ከአላህ ሌላ አማልክት አድርጎ ላይይዝ ነው፤ በላቸው፡፡ እምቢ ቢሉም፡- እኛ ሙስሊሞች መኾናችንን መስክሩ በሏቸው፡፡
Surah Aali Imran (آل عمران), verses: 64
@hebre_muslim
2024/09/23 17:14:23
Back to Top
HTML Embed Code: